ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 553 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 399,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 163

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 553 名订阅者。

根据 20 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 12,过去 24 小时变化为 7,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 26.73%。内容发布后 24 小时内通常能获得 14.92% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 157 次浏览,首日通常累积 2 320 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 21 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 553
订阅者
+724 小时
+77
+1230
帖子存档
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ......///...... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቧንቧ ጥገና ሰራተኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስታወቂያ ማውጣታችን
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ......///...... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቧንቧ ጥገና ሰራተኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊትለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የማሰልጠኛ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም

EXTERNAL VACANCY ANNOUNCEMENT - ETHIOPIAN ELECTRIC POWER (EEP) ......///...... Ethiopian Electric Power (EEP) is looking for
EXTERNAL VACANCY ANNOUNCEMENT - ETHIOPIAN ELECTRIC POWER (EEP) ......///...... Ethiopian Electric Power (EEP) is looking for qualified and competent applicants for the following vacant positions on a contract basis:- Additional Application Instruction 1   Registration announcement Ten (10) consecutive days starting from the date of this vacancy. 2 Candidate must have to fill the online application form properly using alternative links listed below. 3 Application in unrelated fields & unrelated experience is not acceptable. 4 EEP we notifies you that we have the right to cancel the announcement as necessary. 5. We inform you that we will not accept applicants who come in person with information. Link: https://forms.gle/YG8tQfFos66zHkju9 💡 "Clean Energy for a Better Life!" Facebook | Telegram | Twitter | YouTube | TikTok | Website | LinkedIn February 13, 2026

ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው …….///….…. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪ
+3
ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው …….///….…. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን የ2018 የግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል። በግምገማው ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው የተቋሙን የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጨረታዎች ወጥተው በሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም

በሪጅኑ ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ….///…. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራና መልሶ ግንባታ ሥራ ሙሉ በሙሉ
+9
በሪጅኑ ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ….///…. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራና መልሶ ግንባታ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የሪጅኑ ዳይሬክተር ገለጹ፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ሐሰን መሐመድ እንደገለጹት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በሪጅኑ በሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በሪጅኑ-ሲከናወን-የቆየው-የኮንዳክተር-ቅ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙን ለተቀላቀሉ ሠራተኞች የሙያ ደህንነትና ጤና ጥበቃ ስልጠና ተሰጠ ……///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለተቀላቀሉ ሠራተኞች በሙያ ደህንነት እና ጤንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥ
+4
ተቋሙን ለተቀላቀሉ ሠራተኞች የሙያ ደህንነትና ጤና ጥበቃ ስልጠና ተሰጠ ……///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለተቀላቀሉ ሠራተኞች በሙያ ደህንነት እና ጤንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየተሠጠ ይገኛል። በተቋሙ የሙያ ደህንነት እና ጤንነት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኮርሳ ታቶ እንደገለፁት ሥልጠናው ተቋሙን የተቀላቀሉ ሠራተኞች ወደ መደበኛ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት በተቋሙ ውስጥ ያለውን የሥራ ከባቢ በውል እንዲገነዘቡ ያለመ ነው፡፡ ሠራተኞቹ በሥራ ላይ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ የሙያ ደህንነት ስጋቶችን በመለየት መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ የታሰበ መሆኑንም ነው የገለፁት። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙን-ለተቀላቀሉ-ሠራተኞች-የሙያ-ደህን&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም

የሸኽዲ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠግኖ ኤሌክትሪክ መስጠት ጀምሯል ........///........ ‎በሸኽዲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ምክንያት ኃይል ተ
+6
የሸኽዲ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠግኖ ኤሌክትሪክ መስጠት ጀምሯል ........///........ ‎በሸኽዲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ምክንያት ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢዎች ዳግም ኃይል እንዲያገኙ መደረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን መምሪያ አስታወቀ። ‎የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተሻገር እንዳስታወቁት በእሳት አደጋው በአንድ የ33 ኪሎ ቮልት ገቢ እና ሦስት የ33 ኪሎ ቮልት የወጪ መስመሮች ላይ የሚገኙ ፓናሎች እና ብሬከሮች ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። በተከሰተው አደጋ ለመተማ ዮሐንስ ከተማና አካባቢው ኃይል ተቋርጦ መቆየቱን ያቀርብ  ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የሸኽዲ-የኃይል-ማከፋፈያ-ጣቢያ-ተጠግኖ-ኤ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

Building a Greener, Brighter Ethiopia! 🌱⚡️ We are working diligently to ensure renewable energy development that exists in perfect harmony with nature. Watch the full video on our TikTok page: 👇 https://www.tiktok.com/@ethio_power/video/7605151725237832976 #Ethiopia #GreenLegacy #Prosperity #RenewableEnergy #Sustainability 💡"Clean Energy for a Better Life!" Facebook | Telegram | Twitter | YouTube | TikTok | Website | LinkedIn

በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት የፈጸሙ አካላት በእስራት ተቀጡ …..///…… በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት የፈጸሙ ወንጀለኞች በእስራት መቀጣታቸውን የተቋሙ የሕግ አገ
+1
በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት የፈጸሙ አካላት በእስራት ተቀጡ …..///…… በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት የፈጸሙ ወንጀለኞች በእስራት መቀጣታቸውን የተቋሙ የሕግ አገልግሎት መምሪያ አስታወቀ፡፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር ወ/ሮ መስከረም በቀለ እንዳስታወቁት ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከ107 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የመቱ - ማሻ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት 100 ሜትር ርዝመት ያለው የኮንዳክተር ገመድ ላይ የስርቆት ወንጀል ተፈፅሟል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በኃይል-መሰረተ-ልማቶች-ላይ-ስርቆት-የፈጸ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ሠራተኞች ወደ ሥራ ሲሰማሩ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅባቸዋል …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ወደ ሥራ ሲሰማሩ ሙያዊ ሥነ- ምግባርን ባከበረ መል
+9
ሠራተኞች ወደ ሥራ ሲሰማሩ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅባቸዋል …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ወደ ሥራ ሲሰማሩ ሙያዊ ሥነ- ምግባርን ባከበረ መልኩ ሥራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው በተቋሙ የሰው ሀብት ሥራ አስፈፃሚ አቶ አታላይ አበበ አሳሰቡ፡፡ የኢትዮ ፓወር አካዳሚ ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ባዘጋጀው የሥራ ላይ ትውውቅ ስልጠና ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ሥራ አስፈፃሚ አቶ አታላይ እንደተናገሩት ስልጠናው ስለ ተቋሙ አጠቃላይ ገጽታ እና ሠራተኞች ወደ ፊት ስለሚያከናውኗቸው ሥራዎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ሠራተኞች-ወደ-ሥራ-ሲሰማሩ-ኃላፊነታቸውን&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+9

በክልሉ  የኃይል መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ .......///........ በሲዳማ ክልል የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን  ከስርቆት ለመከላከል በየደረጃው ከሚገኙ የመስተዳድር አካላት እና ከተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች ጋር በይርጋለም ከተማ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ አንድ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ንጉሴ ስለ ተቋሙ አጠቃላይ ታሪካዊ ዳራ እና ሪጅኑ እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት ገለፃ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2022 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሀገራዊና ክፍለ አህጉራዊ የኃይል ፍላጎትን ሊሸከም የሚችልና ተመራጭ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢ ተቋም ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ፍላጎትን ለሟሟላት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የተደረገባቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች የተገነቡ ቢሆንም ማህበረሰቡ መሰረተ ልማቶችን በእኔነት ስሜት ባለመጠበቁ ለጉዳት እየተጋለጡ እንደሚገኙ ነው የገለፁት፡፡ በዚህም በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ከማድረጉም ባለፈ ለማህበረሰቡ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በሚከናወነው ሥራ ላይ ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡ በሪጅኑ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞሲሳ ገልቻ በበኩላቸው በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ በየትኛው ቀበሌና አካባቢ ስርቆት በስፋት እንደተፈጸመ፣ በየቀበሌዎቹ በምን ያህል ምሰሶዎች ላይ እንደተፈፀመ፣ ምን ያህል የምሰሶ አካላት እንደተወሰዱ እና ምን ያህል ምሰሶዎች እንደወደቁ እንዲሁም በብር ሲሰላ ምን ያህል ኪሳራ እንደደረሰ የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት አቅርበዋል፡፡ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችን ለመከላከል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ማህበረሰቡ በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም የሥራ ኃላፊዎቹ አሳስበዋል፡፡ በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ አንድ ሪጅን የሥራ ኃላፊዎች፣ በሲዳማ ክልል በየደረጃው የሚገኙ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ እና የከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣  የፀጥታ አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሴቶች ማኀበት ተወካዮች ተሳትፈዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም

‎ቀጣናዊ የኃይል ትስስሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ‎....///.... ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀጣናዊ የኃይል ትስስሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ
‎ቀጣናዊ የኃይል ትስስሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ‎....///.... ‎የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ  ኃይል ቀጣናዊ የኃይል ትስስሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። ‎ ‎በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ከሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ጋር በኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማት ለመተሳሰር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። ‎ ‎ከደቡብ ሱዳን ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችለውን ሥምምነት ከሦስት ዓመታት በፊት የተፈረመ ሲሆን በሁለቱም ወገን ሂደቱን የሚከታተል የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።            ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ቀጣናዊ-የኃይል-ትስስሩን-ለማጠናከር-የ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም

በበጀት ዓመቱ ውሳኔ ካገኙ የፍትሀብሔርና የሥራ ክርክሮች ከ806 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል ‎………///…… ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ስድስት ወራት በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች
በበጀት ዓመቱ ውሳኔ ካገኙ የፍትሀብሔርና የሥራ ክርክሮች ከ806 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል ‎………///…… ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ስድስት ወራት በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች ክርክር ካካሄደባቸው የፍትሀብሔርና የሥራ ክርክር መዝገቦች ከ806 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገለፀ፡፡ ‎ ‎በተቋሙ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ መስከረም በቀለ እንደገለፁት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በተቋሙ ውስጥ ግልጽ እና ወጥ የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ በማድረግ እንዲሁም ክስ የመርታት አቅምን በማሳደግ የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡  ‎  ‎በዚህም በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ደረጃ ላይ የሚገኙ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የገንዘብ መጠን ያላቸው 244 የፍትሀብሔር መዝገቦች ላይ ክትትል ሲደረግ መቆየቱንና 73 መዝገቦች ላይ ውሳኔ መሰጠቱን አንስተዋል፡፡ https://www.eep.com.et/?amh-news=በበጀት-ዓመቱ-ውሳኔ-ካገኙ-የፍትሀብሔርና&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል አቅርቦት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ ነው .......///....... በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች እና በዙሪያቸው ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሰራ መሆ
+5
የኃይል አቅርቦት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ ነው .......///....... በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች እና በዙሪያቸው ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን አስታወቀ፡፡ የሪጂኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ እንደተናገሩት በሪጅኑ ውስጥ አምስት ባለ 132 እና ሦስት የባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም የተለያየ የኪሎ ቮልት መጠን ያላቸው 973 ነጥብ 68 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ በሪጅኑ በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች እና አካባቢያቸው ያለው  የኃይል ፍላጎት ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-አቅርቦት-ጥያቄዎችን-ለመመለስ-እ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ የኒውክሌር ኮሚሽንን ለማጠናከር የሚያስችል ድጋፍ እያደረገ ነው .......///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ የገባውን የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽንን ለማጠናከር የሚያስችል የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን በተቋሙ የኮርፖሬት ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ገለፀ፡፡ የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደገለፁት ኮሚሽኑ የሚያከናዉነው ሥራ እንደ ሀገር ብሎም ተቋም ያለውን የኢነርጂ ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ኮሚሽኑ ለሚያከናውነው ሥራ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበት በመንግስት አቅጣጫ መሰጠቱን ያነሱት አቶ ደመረ ይህን ተከትሎም ተቋሙ ለኮሚሽኑ ሥራ መነሻ የሚሆን የዓይነትና የገንዘብ ድጋፎችን ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ተቋሙ ምንም እንኳን ከፍተኛ ፕሮጀክቶችን እየመራና እያስተዳደረ የሚገኝ ቢሆንም በቀጣይ የሚገኘውን ጥቅም ለማስጠበቅ የፋይናንስ አቅሙን ባገናዘበ መልኩ የግማሽ ቢሊየን ብር እና ከ67 ነጥብ 21 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገዙ ሁለት ዘመናዊ ተሸከርካሪዎችን ድጋፍ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ በፊት ለኮሚሽኑ የተሰጠ ሲሆን ተሸከርካሪዎችን ደግሞ በትላንትናው ዕለት ማስረከብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡ እንደ አቶ ደመረ ገለፃ ተቋሙ የፋይናንስ ችግሩን ተቋቁሞ ለኮሚሽኑ ያደረገው ድጋፍ ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች በማሳለጥ የተቋቋመበትን ዓላማ ከማሳካት ባለፈ እንደ ሀገር ያለውን የኢነርጅ ፍላጎት ለማሟላት ያግዛል፡፡ በቀጣይ ተቋሙ የፋይናንስ አቅሙን መሰረት ባደረገ መልኩ ለኮሚሽኑ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው አረጋግጠዋል። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጷጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምርቃ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር “ኢትዮጵያ የህዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ በቅርቡ ሥራ ትጀምራለች” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ዕቅዱን ለማሳካትም ከሩሲያ ጋር ከተደረገው የኒውክሌር ኃይል የድርጊት መርሃ ግብር ስምምነት በተጨማሪ ከኒውክሌር ኃይል የማመንጫ ሥራ የዓለም አቀፍ የህግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን በተከተለ መልኩ እንዲፈፀም ለማድረግ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

የማከፋፈያ ጣቢያው ለኢንዱስትሪዎች መመስረት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የጎላ ሚና አለው …….///……. የኮምቦልቻ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እና በአካባቢው ለሌሎ
+6
የማከፋፈያ ጣቢያው ለኢንዱስትሪዎች መመስረት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የጎላ ሚና አለው …….///……. የኮምቦልቻ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እና በአካባቢው ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች መመስረት እንዲሁም ለሥራ ዕድል ፈጠራ መሰረት የጣለ መሆኑን የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙስጠፋ ጀማል እንደተናገሩት ማከፋፈያ ጣቢያው ለፋብሪካው የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በመገንባቱ ፋብሪካው እና ማከፋፈያ ጣቢያዉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ ፋብሪካዉ በተለያየ ጊዜያት የማስፋፊያ ሥራ ባከናወነበት ወቅት የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ኃይል ከጣቢያው ሲያገኝ መቆየቱን በመጠቆም አሁን ላይም 6 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ኃይል እየተጠቀመ እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የማከፋፈያ-ጣቢያው-ለኢንዱስትሪዎች-መመ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም

የማከፋፈያ ጣቢያው ለኢንዱስትሪዎች መመስረት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የጎላ ሚና አለው …….///……. የኮምቦልቻ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እና በአካባቢው ለሌሎ
+6
የማከፋፈያ ጣቢያው ለኢንዱስትሪዎች መመስረት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የጎላ ሚና አለው …….///……. የኮምቦልቻ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እና በአካባቢው ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች መመስረት እንዲሁም ለሥራ ዕድል ፈጠራ መሰረት የጣለ መሆኑን የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙስጠፋ ጀማል እንደተናገሩት ማከፋፈያ ጣቢያው ለፋብሪካው የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ በመገንባቱ ፋብሪካው እና ማከፋፈያ ጣቢያዉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ ፋብሪካዉ በተለያየ ጊዜያት የማስፋፊያ ሥራ ባከናወነበት ወቅት የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ኃይል ከጣቢያው ሲያገኝ መቆየቱን በመጠቆም አሁን ላይም 6 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ኃይል እየተጠቀመ እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የማከፋፈያ-ጣቢያው-ለኢንዱስትሪዎች-መመ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግደብን ስትገነባ ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታም ሆነ ብድር አልወሰደችም ……..///……. ኢትዮጵያ የታላቁ ኢትዮጵ ህዳሴ ግደብን ስትገነባ ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታም ሆነ ብድር አለመውሰዷን የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር አረጋገጡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጡ እንደተናገሩት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ ግንባታ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታም ሆነ ብድር አልወሰደችም፡፡ በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ለግድቡ ማን እንደከፈለ ታውቃላችሁ? ዩናይትድ ስቴትስ” ሲሉ በዋይት ሐውስ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስልጣን የመጡበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታዲያ ”በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም” ብለዋል፡፡  ”በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨክነው በጋራ ቆመው ስለሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት ነው” ሲሉም አክለዋል:: ”ህዳሴን ካለ አንድ ብር እርዳታ፣ ካለ አንድ ብር ብድር ያሳካ መንግስት ፕሮጀክት አይሰራም ሊባል አይችልም ግፍ ነው” ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶችም እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+1