ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多603
订阅者
无数据24 小时
-87 天
-1630 天
帖子存档
የምሕላና የጸሎት መርሐ ግብርን በተመለከተ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ ማሳሰቢያ።
*
ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ከኅዳር 15 አስከ21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሔደው የምህላና የጸሎት መርሐ ግብር ከላይ በተጠቀሱት ሰባት ቀናት ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 1:00 ሰዓት በምሽት መርሐ ግብር ደግሞ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ የሚከናወን ሲሆን ሕዝበ ክርስቲያኑ በየ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በመገኘት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፍ እየገለጸ አጠቃላይ መርሐ ግብሩ ቀደም ሲል በተሰጠው መግለጫ መሰረት የሚፈጸም መሆኑን ያስታውቃል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት
ምንጭ: EOTCPR
ቆሞሱ ከሚፈጠሩ ሰው ሠራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ባለ አቅማቸው የቅርሱን ደኅንነት በመንከባከብ ፣ አጥሩን በዘመናዊ ፕላን በማሳጠር እንዲሁም አገልጋይ መምህራን፣ ካህናት ለችግር እንዳይጋለጡ የራስ አገዝ ልማትን በማስፋፋት ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ መወጣታቸውንና ራሳቸውን ለአገልግሎት የሰጡ ብርቱ አገልጋይ መሆናቸዉን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ( ዶክተር ) መስክረውላቸዋል።
በኹሉም ዘንድ ምስጉን የነበሩት ቆሞስ አባ ጽጌሥላሴ መዝገቡ ህክምናቸውን አጠናቀው ባለመመለሳቸው በሕዝቡና በቅርሱ ላይ የተደቀነው የአደጋ ስጋት ከፍ እያለ በመምጣቱ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስና አቡነ ኤርምያስ) ቆሞስ አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ እንዲመደቡ አድርገዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ወልድያ መንበረ ንግሥት ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበሩት ቆሞስ አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ ኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከማኅበረ ካህናቱና ምዕመናን ጋር ተዋውቀው ሥራ ጀምረዋል ሲል የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ጽ/ቤት ዘግቧል::
አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ (ቆሞስ) የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ።
ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም
ገዳሙን ሲያስተዳድሩ የነበሩት አባ ጽጌሥላሴ መዝገቡ (ቆሞስ) ለህክምና ወደ አሜሪካ ከሄዱ ከሰባት ወራት በላይ ቢሆንም ከህመማቸው አገግመው መመለስ ስላልቻሉ በምትካቸው ቆሞስ አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ ከኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአስተዳዳሪነት ተመድበዋል።
ደብሩ ከሰባት ወራት በላይ ያለ አስተዳዳሪ በመቆየቱ አባ ጽጌሥላሴ ህክምናቸውን በሀገር ቤት እየተከታተሉ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ በብፁዓን አባቶች ቢጠየቁም በሀገረ አሜሪካ የጀመሩት ህክምና በሂደት ላይ ያለ ቀጠሯቸውም ገና በመሆኑ መምጣት እንደማይችሉ በማሳወቃቸው በምትካቸው አስተዳዳሪ መመደቡን ሀገረ ስብከቱ አስታወቋል።
አባ ጽጌሥላሴ መዝገቡ የቅዱስ ላሊበላና አካባቢው ካህናትና ሕዝብ ኑሮ በቱሪዝም ገቢ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት በኮሮና እና በጦርነት ምክንት የቱሪዝሙ እንቅስቃሴ በቆመ ጊዜ በተለያዩ መንገዶች አስተባብረው ሕዝቡን ከርኃብና ከጉዳት የታደጉ በመሆናቸው በሁሉም ዘንድ ተወዳጅና ተቀባይነት ያላቸው እንደነበሩ የደብሩ ካህናትና ምዕመናን መስክረውላቸዋል።
በተለይ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተው የሰላም እጦት በቅዱስ ላሊበላና አካባቢው ፍልፍል፣ ውቅርና የዋሻ ውስጥ አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ፣ በሕዝብ ላይ እየደረሰ የነበረውን የርኃብና የጦርነት ጉዳት በመቀነስ የሠሩት የአባትነት ሥራ ጊዜ የማይሽረው መሆኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል።
ዶክተር መርሻ አለኸኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሥልጠናውን በሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የኢዮብ ሉዶልፍ ማዕከል የኢትዮጵያና የኤርትራ የጥናት ተቋም የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዶክተር መርሻ አያይዘውም “ኢትዮጵያ ብዙ የሥነ ጽሑፍ ሀብት ያላት ሀገር በመሆኗ እነዚህ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች በዚያ ዘመን የነበረውን የፍልስፍና ዕውቀት ለአሁኑ ትውልድ መድረስ አለባቸው፡፡ በዚህ መሠረት ሠልጣኞቹ የኢትዮጵያውያን ጥንታውያን መዛግብት የማጥናት ሞያ ያገኛሉ፡፡ የጥናቱ ስልት እንዴት ነው? በእያንዳንዱ የጥናት መስክ ምን ዓይነት ዕውቀት ሊገኝ ይችላል? ከሚለው በተጨማሪ በልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችም እንዲሳተፉ ያደርጋቸዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዝግጅቶች በሚዲያም ሲቀርቡ ብዙ ሰዎች የኢትዮጵያን ሀብት፣ ማንነት እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል” በማለት የሥልጠናውን ጥቅም ገልጸዋል፡፡
በሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ በኢዮብ ሉዶልፍ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጥናት ማዕከል የቤተመጻሕፍት ፕሮጀክት ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዴኒስ እንዳብራሩት ቤተመጻሕፍት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በግእዝ የተጻፉ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች (Manuscript Study) የሚያጠና መሆኑን ገልጸው፤ በዚህ ሥልጠና የተሳተፉትም ቀድሞ ካላቸው በጠጨማሪ ዕውቀት እንደሚያገኙ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጀርመን ከሚገኘው ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ጥንታውያን መዛግብት (Manuscript Study) እና የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ዙሪያ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሥልጠናና ዐውደ ጥናት አካሄደ፡፡
ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ በሰሜን ሆቴል ከኅዳር 10 -14 ቀን 2016 ዓ.ም በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት የመጡ ምሁራንና ሊቃውንት የተሳተፉበት ጉባኤ ነው፡፡
በጉባኤው የመክፈቻ ሥነ ሥርዐት ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት፡- “ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል ያላት አፍሪካዊት ሀገር ናት፡፡ በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው የአባ ገሪማ ወንጌል በግእዝ ቋንቋ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው በዚያ ዘመን ሀገሪቱ፣ ቤተክርስቲያኗ እና ሕዝቡ በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ነው፡፡ ዛሬ የግእዝ ቋንቋ በማኅበረሰቡ ዘንድ በስፋት ስለማይታወቅ በውስጡ የያዛቸውንም ጥበብ ያለ መታወቅ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ የግእዙ ሥነ ጽሑፍ በአብዛኛው መንፈሳዊውን ጉዳይ የያዘ ነው፡፡ በዘመናችን ያለው ትውልድ ደግሞ ከመንፈሳዊው ዕውቀት ጋር ክፍተቶች ይታያሉ፤ ስለዚህ ዛሬ በዚህ ሥልጠና የምትሳተፉ ምሁራን ሁለቱን ማያያዝ ” ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
#ኅዳር ፲፫ (13) ቀን።
እንኳን #ለቅዱስ_እግዚአብሔር አብና #ለአእላፍ_መላእክት_ለዓመታዊ_መታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ዐሥራ_ሦስት_ወንበዴዎች ስርሱ በእርሱ ሃይማኖት ከዓለም የተለዩ #ከከበረ_ባለጸጋ_ከቅዱስ_አስከናፍር ዕረፍትና ከአገረ እንጽና ኤጲስቆጶስ ከከበረ ከአባት #ከአባ_ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ስልሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዘካርያስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ በዚች ቀን የአእላፍ መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን፦ እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ ለዓለሙ ሁሉ የሚማልዱ ናቸው። ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ "በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም አእላፋት መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው" አለ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በምዕራብ ሐረርጌ ርእሰ ከተማ በጭሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።
ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በድምቀት ተከበረ።
ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሀዋሳ ደ/ም/ቅዱስ ገብርኤል እና በሀዋሳ ደ/ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ/ያን በድምቀት ተከበረ።
ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ
ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ
ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በወልዲያ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ
ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
ይህም ቀን፦ሕዳር 12
🔔 በዓለ ሲመቱ ነው።
በ99ኙ ነገደ ቅዱሳን መላእክት ላይ ለተሾመበት መታሰቢያ ነው።
🔔 እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ወጥተው ወደ ምድረ ርስት እንዲገቡ ለመምራቱና ለመራዳቱ መታሰቢያ ነው።
🔔 ለነዌ ልጅ ለነቢዩ ለቅዱስ ኢያሱ ለተገለጠበት መታሰቢያ ነው።
🔔 ዱራታዎስና ሚስቱን ቴዎብስታን ለረዳበት መታሰቢያ ነው።
📣📣📣እንኩዋን አደረሰን 📣📣📣
✨✨✨✨✨✨✨✨አንተኑ ሚካኤል ለእስራኤል መና ዘአውረድከ:: ✨✨✨✨✨✨✨✨✨
💥 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 "" ነገሠ : ቅዱስ ሚካኤል ነገሠ::
የጠላትን ምክር ፈጥኖ አፈረሠ:: ""💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
💫እስራኤልን በበርሃ . . .
💫በደመና የመራህ::
💫መና ያወረድህ::
💫ክንፍህን የጋረድህ::
💫ውሃን ያፈለቅህ::
💫የብርሃን ምሰሶን ያቆምህ . . . ርሕሩሑ መልአክ ሚካኤል አንተ ነህ!
✨✨✨ ዛሬም ረድኤትህ ፈጥኖ ይደረግልን!✨✨✨
💥እንኳን አደረሳችሁ።💥
⚡️💫መልካም በዓል።💫⚡️
✨✨✨✨✨ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ✨✨✨✨✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✝ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፲፪ (12) ቀን።
✝ እንኳን #ለሰው_ወገን_ለሚያዝንና_ለሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረት ሁሉ ለሚማልድ #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል_እስራኤልን_ከግብፅ_ባርነት ሲወጡ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጋር በሆነ ሕዝብ በመንዳቸው ሁሉ እየመራ የኤርትራ ባሕር ለከፈለበት፣ #ለነዌ_ልጅ_ለነቢዩ_ለቅዱስ_ኢያሱ ለተገለጠለት፣ #ዱራታዎስና_ሚስቱን_ቴዎብስታ_ለረዳበት_ዓመታዊ_በዓልና #ለኢትዮያዊው_ንጉሥ #ለጻድቁ_ለዐፄ_በእደ_ማርያም_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ ራሱ በደብረ ማህው ከታየችበት፣ ከእስክድርያ ስልሳ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ፊላታዎስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጾመ ነቢያት ጸሎትና ምሕላ እንዲካሔድ መግለጫ ሰጡ።
ቅዱስነታቸው የሰጡትን ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“ሰላምየ አኀድግ ለክሙ ወሰላመ አቡየ እሁበክሙ፡- ሰላሜን እተውላችኋለሁ፥ የአባቴ ሰላምም እሰጣችኋለሁ” (ዮሐ.14፡27)
ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነት ማስፈንን አስመልክቶ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤
ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና ደኅንነት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቀዳሚ ተልእኮዎች ናቸው፡፡ በሃገራችን ሰላምን ለማስፈን ቅድስት እናት ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞ ጀምሮ ብዙ ጥረት ስታደርግ ኑራለች፡፡ አሁንም ሊኖራት የሚገባውን ተግባራዊ ሚና መወጣት ይኖርባታል፡፡
በተለይም ሰላም በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊ፣ በግለሰብ፣ በተቋም፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ክበብ ውስጥ ያለውን የተሣሠረ ሁለንተናዊ ትርጉም ከግምት ውስጥ ያስገባ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
ለሰላም መደፍረስና መታጣት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን በማንሳትና ያስከተሉትን የሰው ልጅ እልቂት፣ ሞትና ስደት፣ የአብያተ ክርስቲያናትና የመንፈሳዊ ቅርሶች ውድመት፣ የካህናትና የሊቃውንት ስደትና መከራ፣ የቋሚና የተንቀሳቃሽ ንብረቶች ውድመት፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት መናጋት፣ በዜጎች መካከል ጥላቻ መስፋት፣ መተማመን መጥፋት፣ የኑሮ ዋስትና ማጣት፣ በስጋት መኖር፣ የማያባራ መከፋፈል፣ የሰብአዊ ክብር ማጣት፣ የመብት ጥሰት፣ የኑሮ ውድነትና የሕዝቦች መፈናቀል በአደባባይ እየታዩ ያሉ ሰብኣዊ ሰቆቃዎች ናቸው፡፡
“ብፁዓን ገባርያነ ሰላም እስመ እሙንቱ ውሉደ እግዚአብሔር ይሰመዩ፡- የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና” (ማቴ.5፡9) በማለት ጌታችን ያስተማረው ትምህርት የቤተ ክርስቲያን መመርያ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን የሰላምና የአስታራቂነት ድርሻ፣ የሃገር አንድነትና የሕዝብን ሰላም ለመጠበቅ በታሪኳ ያደረገችው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም፡፡
የቤተ ክርስቲያን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነትና የሊቃውንቷን ሰላምን የማስፈን ክሂሎት፣ ችግርን የመፍታት ጥበብ አሁንም ተጠናክሮ መተግበር ይኖርበታል፡፡
የሰላምን ወሳኝ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባትና ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የሰላምና የዕርቅ ሰነድ በማዘጋጀት የመሪነት ተሳትፎ እንድትፈጽም ገለልተኛና ሰውን ማእከል በማድረግ ታገለግላለች፡፡
ካህናትና መላው አገልጋዮች የሰላም ልዑካን እንዲሆኑ፤ ሰላምን ግንባር ቀደም ሐዋርያዊ ተልእኮዋ አድርጋ ትንቀሳቀሳለች፡፡
በሃገራዊ የሰላምና የዕርቅ ጥረቶች አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚያስችል ይፋዊ ውክልና እንዲኖራት፣ በሥነ ምግባርና በግብረ ገብነት ትምህርት የራስዋን ኃላፊነት እንድትወጣ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሃገራዊም ሆነ በራስዋ መዋቅር በሰላም ዙርያ አስተዋጽኦዋን ለማሳደግና የሚጠበቅባትን ለመወጣት ትችል ዘንድ የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሚገባ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ለቤተ ክርስቲያን መመርያዋ ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን አጥብቀህ ተከተል ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ያዘዘው መመሪያ ነው፡፡ (፪ኛ ጢሞ. ፪፡ ፳፪)
ሰላምን ሳታዳላ በሩቅም በቅርብም ላሉት ትሰብካለች፡፡
• “ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ” እንዲል (ኤፌ.፪፡፲፯)፡፡
ለቤተ ክርስቲያን ሰላም መሣርያዋ፣ ሕይወቷ፣ ጸሎቷ፣ ቀኖናዋና ዶግማዋ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ “ሰላም ከሌላችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የለም” በማለት የሰው ልጅ ሰላማዊ እንዲሆን ታስተምራለች፡፡
ጥላቻን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡ “ጥልን በመስቀሉ ገደለ” የሚለውን መልእክት እንደ ሰንደቅ የምትጠቀምበት መለያዋ ነው፡፡ ስለዚህ በሰዎች መካከል የተከሰተውን ጥላቻ በተሰጣት መንፈሳዊ ጥበብ ማስወገድ ተልእኮዋ ነው፡፡
በሰላም ግንባታ ኢትዮጵያውያንን ያለ ልዩነት በማሳተፍ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ሚናዋን በጥበብና በማስተዋል በቋሚነት ትሠራለች፡፡
ሰላምን ያሳጡን ጦርነቶችና ግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙና በአጭሩ እንዲቋጩ ጥሪዋን ታስተላልፋለች፤ እምቢ ባዮችንም በማውገዝ ዘላቂ መፍትሔ የሚገኝባቸውን ሂደቶችን ትቅይሳለች፡፡
የሰላም ሰነዶችን በማዘጋጀት አስቸኳይ የሆነ ሃገራዊ የሰላም ንቅናቄ በፍጥነት እንዲጀመርና በዚህም ውስጥ ውጤት ሊያመጣ የሚችል ሥልት ተቀይሶ ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረግ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡
ቤተ ክርስቲያን የራስዋ የሰላም ከፍተኛ ልዑክ ኖሯት በመዋቅሯ ሁሉ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ የሰላም ሥምሪት ለማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ ታደርጋለች፡፡
በሃገራዊ የሰላም ጥረቶች፣ የውይይትና የምክክር መድረኮች ባለድርሻ እንድንሆን ከሚመለከተው ጋር ተቀራርቦ መሥራት የሚቻልበትን አሠራር ትዘረጋለች፡፡
በማኅበራዊ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪ ተቀባይነት እንዲኖረው በትጋት ትሠራለች፡፡
በሰብአዊ ድጋፍና በእርዳታ ማስተባበር ለወገኖቻችን መድረስ እንዲቻል ልጆቿን አስተባብራ ትንቀሳቀሳለች፡፡
በመግቢያችን እንደተጠቀሰው “ፈኑ እዴከ አንሥእ ኃይለከ” ብለው የለመኑ ነቢያትን የሰማ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታችንን እንደሚሰማን ከልባችን በማመን በእርሱ ያለንን ትምክህታችን ይህ በመሆኑ ከጽኑ ተስፋና ፍቅር ጋር እንድንፈጽመው አደራ እንላለን፡፡
በተጨማሪ ይህንን መንፈሳዊ ሥርዓትና መደበኛ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሁሉም በቅንነት እንዲረዳው በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ዓለማውያን ምሁራን ሃገሮቻቸውን ለመጠበቅ፣ የሕዝባቸውን አንድነት ለማስቀጠል፣ የተረጋጋና እርስ በርሱ የሚተማመን ማኅበረሰብን ለማጽናት በሕግ የሚያስቀጡ “የጥላቻ ንግግርን” የሚያስቀር አዋጅ ያወጣሉ፡፡ ሃገራችንም የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የሚከለክል አዋጅ አላት፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጥላቻንና ሐሰተኛ ትርክቶችን ታወግዛለች፡፡
የአሁኑ ጸሎተ ምኅላ የሚደረገው አለመግባባት በምክክር፣ በውይይት፣ በመደማመጥ እንዲፈታ፤ መከራን በመረዳዳት እንድንሻገር፣ እንደየ ኃላፊነታችን የሚጠበቅብንን ለመወጣትና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ እንድንችል፣ ችግራችን ሁሉ ተፈትቶ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሃሊው አምላክ እንዲያግዘን በአንድነት ለመጮኽ ነው፡፡
ስለዚህ ይህ ዓላማው መንፈሳዊ ብቻ የሆነ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ አዋጅ መሆኑን ተረድታችሁ የሚድያ፣ የትምህርትና የፍትሕ፣ መሰል ተቋማት በሚያስፈልገው ሁሉ እንድትተባበሩን በዚሁ አጋጣሚ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም አባታዊ ማሳሰቢያን እናቀርባለን፡፡
በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን በታሪክም ሆነ በትውልድ የሚያኮራ ውጤታማ ሥራን እንድትሠራና ከቃል ወደ ተግባር እንድትሸጋገር ለማድረግ ይህ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ ይቀድስ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
✨✨እንኳን አደረሳችሁ ✨✨
✝✝ኅዳር_ሚካኤል ✝✝
✨ኑ የእግዚአብሔርን መልአክ እናክብር
✨ኑ የልጅነት አባታችንን እናመስግን
✨ኑ በልጅነት አንደበታችን ስሙ በልባችን የታተመውን ገናናው መልአክን እናመስግን ::
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፲፩ (11) ቀን።
✝ እንኳን #አምላክ_ለወለደች_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_እናት ለሆነች ለተመሰገነነች #ለቅድስት_ሐና_ለዕረፍት_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሁለተኛው #ከቅዱስ_አርኬላዖስ_ሰማዕት፣ #ከአበምኔት_ኤልሳዕ፣ #ከመነኰስ_ጳኵሚስና #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ቅድስት_ሐና፦ ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት። ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥምቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥ ወለደቻት።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ።
ኅዳር 9/2016 ዓ.ም
ዛሬ"መቄዶንያ" የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን የመጎብኘት ትልቅ እድል አግኝተናል። የማዕከሉ መሥራቾች ብሎም ሠራተኞች ለተቸገሩ ወገኖቻችን እንክብካቤ እና ድጋፍ ለማድረግ ያሳዩት ቁርጠኝነት ያስመሰግናቸዋል።
የመቄዶን ማዕከል ነዋሪዎች በጣም ተጋላጭ ከሆኑት የሕብረተሰባችን አባላት መካከል ጥቂቶቹ እና ብዙ ጊዜ የተረሱ እንዲሁም የተገለሉ ናቸው። ከማዕከሉ ኃላፊዎች ጋር ባደረግነው ቆይታ ጽናታቸው እና የማይናወጥ እምነታቸው አስደንቆኛል የሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች ቢኖሩም፤ የሰላም እና የደስታ ስሜት ይፈጥራል።
ወደ መቄዶንያ ማዕከል ያደረግነው ጉብኝት ሁላችንም የተቸገሩትን ለማገልገል የተጠራን መሆናችንን ለማስታወስ ነው። የተጠራነው ለተሰቃዩት ርኅራኄ እና ፍቅር እንድናሳይ ነው። በዓለም ላይ ለውጥ እንድናመጣ ተጠርተናል።
መቄዶንያ ማዕከልን እንድትጎበኙ እና እዚያ እየተደረገ ያለውን አስደናቂ ሥራ እንድትመለከቱ አበረታታችኋለሁ።
እግዚአብሔር አምላክ ሕሙማንን ይፈውስ ! ።
ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !
