ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
602
订阅者
无数据24 小时
-87 天
-1630 天
帖子存档
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፲ (10) ቀን። ✝ እንኳን #ለሠላሳ_ስድስቱ_ቅዱሳት_አንስት ለበዓላቸው መታሰቢያና #ለሃምሳ_ቅዱሳት_ንጹሐት #መነኰሳይያት
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝       ✝ #ኅዳር ፲ (10) ቀን። ✝ እንኳን #ለሠላሳ_ስድስቱ_ቅዱሳት_አንስት ለበዓላቸው መታሰቢያና #ለሃምሳ_ቅዱሳት_ንጹሐት #መነኰሳይያት_ደናግልና_ለእናታቸው ለነበረች #ለቅድስት_ሶፍያ በዑልያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በእስክድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ድሜጥሮስ ዘመን ስለ ጾም ሥርዓት ቅዱሳት ሊቃነ ጳጳሳትና የኤጲስ ቆጶሳት የአንድነት ጉባኤ ከተደረገበት (#የቅዱስ_ድሜጥሮስን ቀመር አቡሻህርን በሁሉም ዘንድ እንዲጠቀሙበት በጉባኤ ወሰኑ)፣ #ከጳውሎስና_ከሦስት_ሰማዕታት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                 ✝ ✝ ✝ ✝ #ቅዱሳት_ንጹሐት_መነኰሳይያት_ደናግል #እናታቸው_ቅድስት_ሶፍያ፦ እሊህም ቅዱሳት ከተለያዩ አገሮችና ቦታዎች ሲሆኑ መለኮታዊ ፍቅር በአንድነት ሰበሰባቸው የምንኲስናንም ልብስ ለበሱ ይኸውም የመላእክት ልብስ ነው። በሮሜ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ የሚኖሩ ሆኑ ቅድስት ሶፍያም በእነርሱ ላይ እመ ምኔት ሆነች። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፱ (9) ቀን። ✝ እንኳን #ሃይማኖት_ላቀኑ_ለአባቶቻችን_ለሦስት_መቶ_ዐሥራ-ስምንቱ (ሠለስቱ ምዕት) ኤጲስቆጶሳት ከሃዲ አ
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ኅዳር ፱ (9) ቀን። ✝ እንኳን #ሃይማኖት_ላቀኑ_ለአባቶቻችን_ለሦስት_መቶ_ዐሥራ-ስምንቱ (ሠለስቱ ምዕት) ኤጲስቆጶሳት ከሃዲ አርዮስን #በ325_ዓ.ም #በኒቅያ_ጉባኤ #በጻድቁ_ንጉሥ_በቈስጠንጢኖስ ዘመን አውግዘው ለለዩበት ቀን ለበዓላቸው መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያ አርባ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ #ከቅዱስ_አባት_አባ_ይስሐቅ እግዚአብሔር አምላክ ዕረፍት ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፰ (8) ቀን። ✝ እንኳን #የቅድስት_ሥላሴ_መንበር_ለሚሸከሙ ሥጋ ለሌላቸው #ለአርባዕቱ_እንስሳ_ለኪሩቤል ለመታሰቢያ ዓመታ
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝       ✝ #ኅዳር ፰ (8) ቀን። ✝ እንኳን #የቅድስት_ሥላሴ_መንበር_ለሚሸከሙ ሥጋ ለሌላቸው #ለአርባዕቱ_እንስሳ_ለኪሩቤል ለመታሰቢያ ዓመታዊ በዓላቸው፣ ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_አፍኒን_ለተሸመበት_በዓል፣ #ለአቡነ አምደ_ሚካኤል ዘወሎ ለልደታቸው በዓል፣ #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ ኪሮስ ለቅዳሴ ቤታቸው  መታሰቢያና  ለበዓላቸው ለአረማዊ መኰንን ልጅ ለነበረ #ለአባ_ቅፍሮንያ_ለዕረፍትበዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ዮሐንስ ከመታሰቢያው፣ #ከንጉሥ_ቈስጠንጢኖስ መስቀል ከተገለጠለትና ከሰማዕት #ከቅዱስ-ኤስድሮስ ማኅበር ከሆኑ #ከመቶ_ሰማንያ ሁለት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ። በብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌና የአፋር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ
+6
ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ። በብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌና የአፋር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሚመራውና ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ። ጉባኤው ባለ 14 ነጥብ የጋራ አቋም መግለጫ ያለው ቃለ ጉባኤ በመጋቤ ሥርዓት ቀሲስ ዘነበ ብርሃኑ የሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ከቀረበ በኋላ በ2015 የበጀት ዓመት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመልካም አስተዳደር፣ በስብከተ ወንጌል ማስፋፋት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር ፣ ራስ አገዝ ልማትን በማፋጠን መልካም የሥራ ውጤት ላስመዘገቡ የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችና የገዳማትና አድባራት ጽ/ቤቶች የሰርተፍኬትና የተለያዩ የማጠናከሪያ ሽልማቶች ከብፁዕነታቸው እጅ ተቀብለዋል። እንዲሁም ጥር 27ቀን 2015 ዓ/ም በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመቆም በሕግ በኩል መብቷን አስጠብቀው ከሕገወጡ ዘረፋ ለታደጉ 4 የበጎ ፈቃደኞች የሕግ ባሙያዎች ያበረከቱት አስተዋጾ ተገልጾ የዕውቅና ሰርተፍኬትና የምስጋና ሽልማት ከብፁዕነታቸው እጅ ተቀብለዋል። በጉባኤው ማጠቃለያ በብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌና የአፋር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንናቡራኬ ጉባኤው ፍጻሜ አግኝቷል።

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፯ (7) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ደቡብ ወሎ ከወግዲ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ከባሕር ጠለል 6652
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ኅዳር ፯ (7) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ደቡብ ወሎ ከወግዲ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ከባሕር ጠለል 6652 ጫማ ከፍታ ላይ የሚገኘውን #ታላቁ_ገዳም_ደብረ ቆዘት_ለመሰረቱትና ያፈለቁት፤ #ጠበል_መቊጠሪያ_ለሚሰራው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ገብረ_እንድርያስ፣ #ለቅድስት_ወለተ_ክርስቶስና_ለቅድስት_እኅተ_ክርስቶስ ለበዓላቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ✝ #የአቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ደብረ ቆዘት፦ የሚባለው ገዳማቸው ደቡብ ወሎ ከወግዲ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ከባሕር ጠለል 6652 ጫማ ከፍታ ላይ ይገኛል። ገዳሙ በአባይ ተፋሰስ ዙሪያ ከጣቀት ወንዝ በስተሰሜን፣ ከደብረ ዘመዶ ማርያም (ዘሞድ) መንደር በስተደቡብ ምሥራቅ እና ከደብረ ሰኮሩ ሥላሴ በስተምዕራብ አቅጣጫ ላይ ይገኛል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

▪ቁስቋምም እመቤታችን ከስደት ስትመለስ ከልጇ ከጌታችን ከፃድቁ ከዮሴፍ ከቅድስት ሰሎሜ ጋራ ያረፈችበት ተራራ ነው ። ▪ስለዚህ በዓሉ ቁስቋም ተብሎ ይከበራል። እመቤታችን ከልጇ ጋራ 42 ወር ተሰዳ በግብፅ ከኖረች በሇላ አሳዳጃው ሄሮድስ ሰለሞተ ወደሀገራ እንድትመለስ መልአኩ ለዮሴፍ ነግሮት ሲመለሱ በዚህ ተራራ ላይ አርፈዋል። ▪በዚም ተራራ ላይ ቅዱሳን መላእክት ክንፋቸውን ዘርግተው በእመቤታችን እና በጌታችን ላይ ረበዋል ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ~ዮም ፀለሉ መላእክት ላእለ ማርያም ወላእለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም~ ብሎ እንደተናገራው በዚህ ተራራ መላእክት ረበው ዘምረውበታል አመስግነውበታል ▪እመቤታችን ተአምራት ባደረገችበት ዕለትና ተራራ ተሰይሞ በአለ ክብሯ ይከበራል። ▪ስለዚህ ቁስቋም ማለት ማርያም ማለት አይደለም እመቤታችን ያረፈችበት ተራራ ነው እንጂ ▪ልደታ በአታ ኪዳነ ምህረት ፍልሰታ ማለትም ማርያም ማለት ሳይሆን ልዩ ልዩ ታሪኳ የተከናወነበት ቀን ነው ▪ልደታ ብለን የምናከብረው የተወለደችበትን ቀን ነው ▪በአታ ብለን የምናከብረው ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን ነው ▪ኪዳነ ምህረት ብለን የምናከብረው የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበትን ቀን ነው ፍልሰታ ብለን የምናከብረው ተነስታ ሥጋዋ ወደሰማይ በእርገት የፈለሰበትን ቀን ነው 💫💫💫የእመቤታችን ፍቅሯ ይደርብን 💫💫💫 √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺💥እንኳን አደረሰን!💥🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 ለክብርሽ ተደርሶ፥ ለፍቅር የተቆመ፤ ሥሙር ማኅሌትሽ፥ በቸር ተፈጸመ፤ #ድን
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺💥እንኳን አደረሰን!💥🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 ለክብርሽ ተደርሶ፥ ለፍቅር የተቆመ፤ ሥሙር ማኅሌትሽ፥ በቸር ተፈጸመ፤ #ድንግል #እመቤቴ፦ የኛ መከራ ግን፥ አለቅጥ ረዘመ! 💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 ቁስቋም ማርያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤ ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው 'ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤ ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል። በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን፤ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል። እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን። ይህም ቀን ቁስቋም ተብሎ ተሰይሟል። ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት እንደሆነ ደብረ ታቦር ማለትም የታቦር ተራራ ማለት እንደሆነ ደብረ ሲና ማለት የሲና ተራራ ማለት እንደሆነ። ደብረ ሊባኖስ ማለትም የሊባኖስ ተራራ ማለት እንደሆነ። ደብረ ቁስቋም ማለት የቁስቋም ተራራ ማለት ነው ጌታችን ታምራት በሰራባቸው ተራራዎች በአሉ በተራራዎች ተሰይሞ ይከበራል።

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፮ (6) ቀን። ✝ እንኳን #ክብር_ይግባውና_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም #ከአረጋዊ_
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ኅዳር ፮ (6) ቀን። ✝ እንኳን #ክብር_ይግባውና_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም #ከአረጋዊ_ዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ #ደብረ_ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸውም ድካም #ላአረፉበት_ዓመታዊ_መታሰቢያ በዓል፣ #ለሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ፊልክስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ፍሞስ_ከቅዱሳን_ለንዲዎስ_ከይላጥስ፣ #ከማርትሮስ_ከኢላስዎስ_ከቆርናልዮስ_ከሱኪሮስ #ከናውኔኖስ_ከሊባዲቆ_ከሲላስዮስና #ከሰማዕት_ኤስድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ከሁለት_መቶ_ሰባ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

በአጠቃላይ 14 አድባራትና ገዳማትና ለሜቄዶንያ የአረጋውያን መጦሪያ ሀብትና ንብረታቸው ተሸጦ ገንዘቡ እንዲሰጥላቸው ተናዘዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በኑዛዜያቸው በመንፈስ ቅዱስ አባትነት ላሳደጓቸውና ለረዷቸው በሥጋ ለማይወለዷቸውም ጭምር ለ 22 ሰዎች የበረከት ስጦታ እንዲሰጥላቸው ወስነዋል፡፡ በቅርቡ በሕይወተ ሥጋ የተለዩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባለንበት ዘመን የሰው ልጅ በዘር በተመነዘረበት ጊዜ ሰው ሁነው እኛን ሰው ያደረጉ ነበሩ ሲሉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ40ኛ መታሰቢያ በዓላቸው ላይ ተናግረዋል፡፡

የብፁዕ አቡነ ሰላማ ኑዛዜ ይፋ ተደረገ፡፡ በኑዛዜያቸው በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያምን ጨምሮ ለጎጃም ፈረስ ቤት ደጋ ዳሞት ቅዱስ ሚካኤል፣ እና ለሌሎች 14 አ
+2
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ኑዛዜ ይፋ ተደረገ፡፡ በኑዛዜያቸው በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያምን ጨምሮ ለጎጃም ፈረስ ቤት ደጋ ዳሞት ቅዱስ ሚካኤል፣ እና ለሌሎች 14 አድባራት ያላቸው ንብረት ተሸጦ ለበረከት እንዲሰጥላቸው ተናዘዋል፡፡ ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም በ1928 ዓ.ም በትግራይ ክልል በመቀሌ በዓታ ለማርያም የተወለዱት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ቆይተው ሐምሌ 9 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው የጳጳሳት ምርጫ የአክሱምና ማዕከላዊ ዞን ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው በልዩ ልዩ አህጉረ ስብከት ሐዋርያዊ ተግባራቸውን ሲፈጽሙ የቆዩት የጸሎት እና የቅድስና አባት የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ይህን ዓለም በዕረፍተ ሥጋ ተለይተው ወደ ሰማያዊው አባታቸው ተጉዘዋል። የብፁዕ አቡነ ሰላማ የ40ኛ ቀን መታሰቢያ በዓል በተከበረት ዕለት የብፁዕነታቸው ኑዛዜ ይፋ ተደርጓል፡፡ በኑዛዜያቸው አንድ መኖሪያ ቤት ለአዲስ አበባ ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ በሙሉ እንዲሰጥ ሲወስኑ፤ በስማቸው የሚገኘው ንብረት ተሸጦ ብፁዕነታቸው በኑዛዜ መሠረት በመላው ኢትዮጵያ ከሚገኙ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት መካከል • ለቅድስት ሥላሴ ካቴድራል • ለአክሱም ጽዮን ማርያም • ለአዲስ አበባ በዓታ ለማርያም • ለግቢ ቅዱስ ገብርኤል • ለመቀሌ በዓታ ለማርያም • ለስሬ ጊዮርጊስ • ለመቄዶንያ አረጋውያን መርጃ • ለእንጦ ማርያም • ለአሰላ መድኃኔዓለም • ለቡራዩ ጼዴንያ ማርያም • ለጎጃም ፈረስ ቤት ደጋ ዳሞት ቅዱስ ሚካኤል፣ • ለመተሀራ መድኃኔዓለም • ለሀረር ኪዳነ ምሕረት • ለማርያም ደመረይቲ (ደብሪ)

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአገልግሎት ላይ ሳሉ በጥይት የተመቱትን አስተዳዳሪ በሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ ! ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አ
+3
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በአገልግሎት ላይ ሳሉ በጥይት የተመቱትን አስተዳዳሪ በሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ ! ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም በአገልግሎት ላይ ሳሉ በጥይት የተመቱትን መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ በሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል። መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ የቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ በደብሩ ለሁለት ቀን በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት የዓውደ ምህረት አገልግሎት ላይ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ ነው ብፁዕነታቸው ለጥየቃ በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የተገኙት። ብፁዕነታቸው ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እንደሚነጋገር ገልጸው ለአገልጋዮች ነገ ዋስትና እንዲኖራቸው መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በተፈጸመው ድርጊት የተደፈረችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት ብለዋል ብፁዕነታቸው አቡነ ሄኖክ ፤ ብፁዕነታቸው በሆስፒታሉ የሚገኙ ሌሎች ሕሙማንንም የጎበኙ ሲሆን ቡራኬ በመስጠት ሕሙማኑ ፈጥነው ያገግሙ ዘንድ ጸሎት አድርሰዋል።

የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛ መደበኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። +++++++++++++++++++++++++++++ (#EOTCTV ኢኦተቤ ቴቪ ኅዳር 3 ቀን 20
+6
የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛ መደበኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። +++++++++++++++++++++++++++++ (#EOTCTV ኢኦተቤ ቴቪ ኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ምምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዞን አቀፍ ጉባኤው ለሦስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በጉባኤው ላይ የወረዳ ሊቃነ ካህናት ፣ የወረዳ ሰባክያነ ወንጌል ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርትና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች ፣ የማኅበራት ተወካዮች ታድመዋል። በሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና ጭሮ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ ልብሰተክህኖ በለበሱ በደብረ ጽዮን ቅ/ልደታ ለማርያም ካህናት ጸሎተ ወንጌል ተደርሷል። በመቀጠልም በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በመጋቤ ሥርዓት ቴዎድሮስ ዓለሙ የጉባኤው መርሐ ግብር ከተነበበ በኋላ የሀገረ ስብከቱ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጁ የ2015 ዓ/ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።ከዚያም በመቀጠል የየወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የወረዳ ሊቃነ ካህናት ሪፖርታቸውን አቅርበዋል። ጉባኤው የየወረዳዎችን ሪፖርት አደምጦ በመወያየት ; ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የሥራ መመሪያ ተቀብሎ የአቋም መግለጫ በማውጣት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። EOTC TV ++++++++++++++++++++++++++++++++++++

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ ኅዳር ፭ (5) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዮሐኒ_እንደ_መላእክት_ክንፍ_አብቅለው (ተሰቷቸ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝             ✝ ኅዳር ፭ (5) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዮሐኒ_እንደ_መላእክት_ክንፍ_አብቅለው (ተሰቷቸው) ወደ ብሔረ ሕያዋን በመግባት #ከሞት_ለተሰወሩበት ለመታሰቢያ በዓላቸውና #አባ_ዮሐኒን_ላሳደጉ_ላስተምረው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አሞኒ_ለዕረፍት_በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ✝ #አቡነ_አሞኒና_ልጃቸው_አቡነ_ዮሐኒ ደቀ መዝሙራቸው #አባ_አበይዶ፡- የአባ ዮሐኒ አባታቸውን መጽሐፍ ዘስዩመ ተንቤን እሁሁ ይላቸዋል፡፡ እናታቸው ደግሞ ዓመተ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ ደገኛ ምግብራቸው ያማሩ ሀገር ወዳድ ናቸው፡፡ አቡነ አሞኒ የካቲት 5 ቀን አክሱም ውስጥ ሲወለዱ ሰይጣናት የወላጆቻቸውን ቤት ከበው በማየታቸው እንደተወለዱ በእጃቸው ቢያመለክቱ በአንድ ጊዜ 60 ሰይጣናት ተሸንፈው እንደጢስ በነው ጠፍተዋል፡፡ አሞኒ ማለት አሸናፊ ማለት ነው፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨ ስደተኞች  ክፍል አንድ ፩✨✨ ተዋንያን      ሳሙኤል ገዛኸኝ      አቤል ለታ     ረድኤት ብርሃኑ ምንጭ ከ ቪኒሲያ መፅሐፍ

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥር በሚገኙ የ7ቱም ክፍላተ ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አን
+3
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥር በሚገኙ የ7ቱም ክፍላተ ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በኩል በሦስት ዙር ሲካሄድ የቆየው  ጠቅላላ ጉባዔ ተጠናቀቀ። የየካ ፥ የላፍቶ እና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍላተ ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባዔ  ጥቅምት 17 አና 25/2016 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን የአራዳ እና ጉለሌ ፣ የልደታ አዲስ ከተማ ቂርቆስ ፣ የቦሌ እና ለሚ ኩራ ፣ የአቃቂ ቃሊቲ  ክፍላተ ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባዔ ደግሞ ህዳር 2/2016 ዓ.ም  ተካሂዷል። በየክፍለ ከተሞቹ በተደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የየሰንበት ት/ቤቱ   ሰብሳቢ ፥ የጠቅላላ ጉባዔው አባላት ፥ እንዲሁም የየክፍላተ ከተማው የሥራ አመራሮች የተገኙ  ሲሆን በጉባዔው ላይ ያለፉት 3 ዓመታት የሥራ ሪፓርት ቀርቦ እና ውይይት የተደረገበት ሲሆን የ3ዓመት የሥራ ጊዜያቸውን ባጠናቀቁ የየክፍላተ ከተማው የሰ/ት/ቤቶች  አንድነት ሥራ አመራር ምትክ ለቀጣይ 3 ዓመታት የየክፍላተ ከተማው አንድነቱን የሚመሩ ሥራ አመራሮች እና ለአዲስ አበባው አንድነት የሚወከሉ የሥራ አመራሮች ምርጫ በማካሄድ በሦስት ዙር የተደረገው የጠቅላላ ጉባዔ ፍጻሜ አግኝቷል። በቀጣይ ሕዳር 15 እና ሕዳር 16/2016 ዓ.ም ደግሞ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያደርግ ይሆናል። የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፬ (4) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ የዚህን ዓለም ሥራ ለተዉ #ለአባ_ዮሐኒ ደቀ መዝሙር ለሆኑት ለታላቁ አባ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ኅዳር ፬ (4) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ የዚህን ዓለም ሥራ ለተዉ #ለአባ_ዮሐኒ ደቀ መዝሙር ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአባ_አበይዶ_ለዕረፍት_በዓል በሰላም አደረሰን።                          ✝ ✝ ✝ ✝ "#ብፁዕ_ውእቱ_አባ_አበይዶ ረድአ ዘኮኖ #ለአባ_ዮሐኒ ብፁዕ ብእሲ በትዕግሥቱ ዘፈጸመ ገድሎ"። ትርጉም፦ #ለአባ_ዮሐኒ_አገልጋይ የኾነው #አባ_አበይዶ ንኡድ ክቡር ነው፤ ተጋድሎውን በትዕግሥቱ የፈጸመ የኾነ ርሱም ንኡድ ክቡር ነው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                             ✝ ✝ ✝ ✝ "#ሰላም_ለአባ_አብይዶ ለጸላኢ ዘኬዶ"። ትርጉም፦ ጠላትን የረገጠው ለኾነ #ለአባ_አበይዶ_ሰላምታ_ይገባል።                            √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስልጠና እና አቅም ማጎልበቻ ክፍል ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ስልጠና እና አቅም ማጎልበቻ ክፍል ጋር በመተባበር የም
+8
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስልጠና እና አቅም ማጎልበቻ ክፍል ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ስልጠና እና አቅም ማጎልበቻ ክፍል  ጋር በመተባበር የምክክር እና የመስክ ጉብኝት ተካሔደ። ሕዳር 2/2016 ዓ.ም በዕለቱ  በመርሐ ግብሩ ላይ  በሁለቱ የሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢዎች ማለትም በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል አንቀጸ ብጹዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢ በሆኑት መምህር ጳውሎስ ደምሴ እና በመካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ራዕየ ቴዎፍሎስ ሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢ በሆኑት በዲያቆን ዮናስ ኢሳይያስ ስለ ግንባታው ሂደት ለታዳሚዎቹ ልምድ ያካፈሉ ሲሆን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስልጠናና አቅም ማጎልበቻ ክፍል ሰብሳቢ በሆኑት መምህር ኤርሚያስ ዘመነ የስልጠና ክፍል አስፈላጊነት እና ከመንፈሳዊ ትምህርት በተጨማሪም  በየዘርፋ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎች ለሰንበት ት/ቤቶች እድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ  በመሆኑ በስፋት በተግባር በመግባት   ያሉብንን ክፍተቶች ለመሙላት ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለው መልእክት አስተላልፈዋል። በዕለቱ ከ20 በላይ የሚሆኑ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች  የተውጣጡ  ሊቃነመናብርት ጋር በጉዳዩ ውይይትና ልምድ ልውውጦች ተደርገዋል። በውጤቱም የህንፃ ግንባታ ላይ የሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች ጥሩ ልምድ እንደቀሰሙና ውጤታማ ውይይቶች የተካሄዱበት እንደነበር ተገልጿል። የሀገር አቀፍ  እና የክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የስልጠና ክፍል ኃላፊዎች በተጋባዥ እንግድነት በቦታው የተገኙ ሲሆን የሀገር አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ ቀሲስ ጥላሁን ደሲሳ በቦታው ተገኝተው መልእክት አስተላልፈው መርሐግብሩ ተጠናቋል።

በተያያዘ ዜና በአራዳ እና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ሊያስገነባ ላቀደው #B+G+4 ሕንጻ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ በሆኑት ብጹዕ አቡነ ሔኖክ የመሠረት ድንጋይ በዕለቱ በተዘጋጀለት ቦታው ተቀምጧል። የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ኅዳር ፫ (3) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን አኲሱም አካባቢ የሚነኘውን #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_በንኰልን ለመሰረቱት
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝                 ✝ #ኅዳር ፫ (3) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን አኲሱም አካባቢ የሚነኘውን #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_በንኰልን ለመሰረቱት ሰባቱን ከከዋክብት የተባሉት እነ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባን_አስተምረው ላመነኰሱትና ውኃ ይቀዳላቸው የነበረውን አህያቸውን አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ #አንበሳውን_7ዓመት_ለገዳማቸው_ውኃ_ላስቀዱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ፣ ለጻድቁ የኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለቅዱስ_ነአኵቶ_ለአብ እንደነ #ሄኖክና_ኤልያስ_በሞት_ፈንታ_ለተሰወረው_ዕለት ለመታሰቢያ በዓሉና #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ለነበሩት ሰማዕቱ #አቡነ_ዓምደ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላምና በጤና አደረሰን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከኢየሩሳሌም አፈር አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኰሳቱ "ገዳሙ በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው# አህዮቹን_ክንፍ_አውጥተው_እንዲበሩ_ላደረጉት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ፍሬ_ካህንና_ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።    √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨