ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多603
订阅者
-224 小时
-57 天
-1430 天
帖子存档
❖ አፎምያም እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔ ከሌላ ሰው ጋራ ላልገናኝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አድርጌያለሁ ርግቦችና መንጢጦች እንኳ ሌላ ባል አያውቁም በእግዚአብሔር አርአያ ከተፈጠሩ ሰዎች ይህ ሊሆን እንዴት ይገባል፤ ምክሩንም ባልሰማች ጊዜ አርአያውን ለውጦ በላይዋ ጮኸባት እንዲህም አላት እኔ በሌላ ጊዜ እመጣለሁ እርሷም የከበረ የመልአኩ የሚካኤልን ሥዕል ይዛ አሳደደችው።
❖ ከዚህም በኋላ ሰኔ ዐሥራ ሁለት የከበረ የመልአኩ የሚካኤል በዓል በሚከብርበት ዕለት እርሷም የበዓሉን ዝግጅት ስታዘጋጅ ሳለች ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ አፎምያ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እኔ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ ጌታ ወደ አንቺ ልኮኛልና እርሱም ይህን መመጽወትሽን ትተሽ ለአንድ ምእመን ሚስት ትሆኚ ዘንድ ጌታ አዞሻል ባል የሌላት ሴት መልሕቅ የሌለውን መርከብ እንደምትመስል ዕወቂ እንደ አብርሃምና ያዕቆብ እንደ ዳዊትም እንደእነርሱ ያሉ ብዙ ሴቶችን እንዳገቡ እግዚአብሔርንም ደስ እንዳሰኙት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥቅሶችን ያመጣላት ጀመረ።
❖ ቅድስት አፎምያም መልሳ አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ከአንተ ጋራ ወዴት አለ የንጉሥ ጭፍራ የሆነ ሁሉ የንጉሡን ማሕተም ሳይዝ ወደ ሌላ ቦታ አይሔድምና አለችው፤ ሰይጣኑም ይህንን በሰማ ጊዜ መልኩ ተለወጠና አነቃት እርሷም ወደ ከበረው መልአክ ወደ ሚካኤል ጮኸች ወዲያውኑም ደርሶ አዳናት፤ ያንንም ሰይጣን ይዞ ይቀጣው ጀመረ ሰይጣኑም ጮኸ ማረኝ ያለ ጊዜዬ አታጥፋኝ እግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ታግሦናልና እያለ ለመነው ከዚያም ተወውና አበረረው።
❖ የከበረ መልአክ ሚካኤልም እንዲህ አላት ብፅዕት አፎምያ ሆይ ሒደሽ የቤትሽን ሥራ አዘጋጂ አንቺ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለዪአለሽና እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልብም ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻል፤ ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጣት ወደ ሰማያትም ዐረገ፤ የበዓሉንም ዝግጅት እንደሚገባ ከፈጸመች በኋላ ወደ ኤጲስቆጶሱና ወደ ካህናቱ ሁሉ ላከች ወደርሷም በመጡ ጊዜ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ይሰጧቸው ዘንድ ገንዘቧን ሁሉ አስረከበቻቸው፤ ከዚህም በኋላ ተነሥታ ጸለየች የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕል አንስታ ታቅፋ ሳመችው ያን ጊዜም በሰላም አረፈች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን የዚህም የከበረ መልአክ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለአፎምያ ዘሞዐቶ ለመስቴማ። በቃለ ትምይንት ሶበ ተቃወማ። በዛቲ ዕለት በከመ አደማ። ሥዕሎ ለሚካኤል እንዘ ታነብር በፍጽማ። ውስተ ዘለዓለም ዕረፍት ፈለሰት እምፃማ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በማግሥቱም ጎዳናውን ሊጓዝ በተነሣ ጊዜ ሰይጣናዊ ምክንያት አመካኝቶ በግ ጠባቂውን እንዲህ አለው ዕገሊት ወደምትባል አገር በቤቴ የረሳሁት ጉዳይ ስለ አለ እንድልከው ልጅህን ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ እኔም የድካም ዋጋውን ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ አለው፤ የብላቴናውም አባት ስለ ገንዘቡ ደስ ብሎት ልጁ ባሕራንን ሰጠው እንዲህም ብሎ አዘዘው ልጄ ባሕራን ይህ የከበረ ሰው ስለ ጉዳዩ ወደ ቤቱ ይልክህ ዘንድ ና ወደ ቤትህም በሰላም ትመለሳለህ፤ ባሕራንም አባቴ ሆይ እሽ በጎ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።
❖ ያን ጊዜም ባለጸጋው ወደ መጋቢው እንዲህ ብሎ ደብዳቤ ጻፈ ይችን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጉድጓድ ውስጥ ጣለው ማንም አይወቅ በመካከላቸውም የሚተዋወቁበትን ምልክት ጽፎ አሸጋት፤ ለባሕራንም ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው ባሕራንም ተነሥቶ ጉዞውን ጀመረ ሲጓዝም ሰንብቶ የአንዲት ቀን ጐዞ ሲቀረው እነሆ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው አለው ወደ ዕገሌ አገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለጸጋ የተጻፈች መልእክት ናት አለው ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ አለው እርሱም ስለ ፈራ ሠጠው።
❖ በዚያን ጊዜም የከበረው መልአክ ሚካኤል ያቺን የሞት መልእክት ደመሰሳት በእርሷ ፈንታም በንፍሐት ለውጦ እንዲህ ብሎ ጻፈ ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ እገሊትን አጋቡት በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን ወንዶችና ሴቶች ባሮቼን ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ፤ እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም ዕገሌ ሆይ በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት ከዚህ በኋላ አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና ወደ ባለጸጋው ቤት ሒደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጬልሃለሁ አለው፤ ባሕራንም እሺ ጌታዬ ያዘዝኽኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።
❖ ባሕራንም ወደ ባለጸጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በአነበባትም ጊዜ በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ አስተውሎም አርግጠኛ እንደሆነ አወቀ፤ ከዚህም በኋላ ለባሕራን ሠርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለጸጋውን ልጅ አጋቡት፤ አርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ።
❖ ከዚህ በኋላ ባለጸጋው ከሔደበት መመለሻው ጊዜ ሁኖ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምፅ ሰምቶ ይህ የምሰማው ምንድነው ብሎ ጠየቀ እነርሱም ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት እነሆ ለአርባ ቀናት በሠርግ ላይ ነው፤ ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝክ ሰጥተውታል አሉት፤ ይህንንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወደቀ በድንገትም ሞተ።
❖ ባሕራንም በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ሆነ የተገለጸለትና ከመገደል ያዳነው የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል እንደሆነ ሊገድለው የሚሻውን የባለጸጋውን ጥሪቱን ሁሉ ያወረሰውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ የዚህንም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ጀመረ ቤተ ክርስቲያንም ሠራለት የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕሉን አሥሎ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ አደረገው ከእርሱም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ባሕራንም ቅስና ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ሁኖ ኖረ በዚህ በከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል አማላጅነት ከእናቱና ከአባቱ ከልጆቹም ጋራ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።
❖ መድኃኒታችን በተነሣበትም ቀን ይህ ክቡር መልአክ ሚካኤል ከውስጠኛው መጋረጃ ውስጥ ገብቶ በክብር ባለቤት ፊት እንዲህ እያለ ይለምናል እውነት ስለሆነ ቃል ኪዳንህ በምድር መታሰቢያዬን የሚያደርጉትን ትምርልኝ ዘንድ ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አገልጋይህና መልእክተኛህ ከቸርነትህ እለምናለሁ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና፤ የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል የመንፈሳውያን ሰማያውያን መላእክት አለቃቸው ሚካኤል ሆይ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ መሸከም እንደምትችል ከሲኦል ሦስት ጊዜ በክንፎችህ ተሸክመህ እንድታወጣ እነሆ እኔ አዝዤሃለሁ።
❖ ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት የበዓሉን መታሰቢያ ከሚያደርጉት በክንፎቹ ተሸከሞ የእሳቱን ባሕር አሳለፋቸው እነርሱንም ከብቻው ጌታ በቀር የሚቆጥራቸው የለም፤ ስለዚህም የዚህን ታላቅ የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ለማድረግ መታገል ይገባናል እርሱ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን ዘንድ በዘመናችን ሁሉም ይጠብቀን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይ ዘንድ መከራችንንም ያርቅ ዘንድ የምድራችንንም ፍሬ ይባርክ ዘንድ ፈቃዱንም ለመሥራት ይረዳን ዘንድ ከእኛ ወገን የሞቱትን ዕረፍተ ነፍስ ይሰጥ ዘንድ ወደ መንገድ የሔዱ አባቶቻችንና ወንድሞቻችንን ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በጤና ይመልሳቸው ዘንድ በመካከላችንም ፍቅር ያደርግልን ዘንድ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ ይለምናልና፤ የክርስቶስ ወገኖች የሆኑ መኳንንቶቻችንንም ጠብቆ በወንበሮቻቸው ላይ ያጸናቸው ዘንድ የእሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖቱ ይመልሳቸው ዘንድ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መልአክ አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለሚካኤል መሐሪ ውእቱ። ወተአዛዚ ለሰብእ በዲበ ሠናይቱ። ለቀርነ ዝንቱ መልአክ በድምዐ ንፍሐቱ። በከመ ኮነ ቀዳሚ ውስተ ሰማያት ዕርገቱ። ለእግዚአብሔር ይከውን ዳግመ ምጽአቱ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ቅድስት አፎምያ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ዳግመኛም በዚች ቀን እግዚአብሔርን የሚፈራ አስተራኒቆስ የሚስቱ የቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ፤ ይህም ሰው በየወሩ ሦስት በዓላቶችን እያከበረ ኖረ እሊህም ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በየወሩ በሃያ ዘጠኝ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል መታሰቢያ በየወሩ በሃያ አንድ፣ የከበረ የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያም በየወሩ በዐሥራ ሁለት ናቸው።
❖ የሚሞትበትም ጊዜው ሲቀርብ እርሱ ሲሠራው የነበረውን ምጽዋት ይልቁንም እሊህን ሦስቱን በዓላት እንዳታስታጉል ሚስቱን ቅድስት አፎምያን አዘዛት፤ አርሷም የከበረ የመልአኩ የሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባሏን ለመነችው እርሱም አሠርቶ ሰጣትና በቤቷ ውስጥ በክብር አኖረችው።
❖ ባሏም ከአረፈ በኋላ ባሏ ያዘዛትን መሥራት ጀመረች ሰይጣን ግን ቀናባት በመበለት ሴት መነኲሲት ተመስሎ ከእርሷ ጋራ ተነጋገረ እንዲህም አላት እኔ አዝንልሻለሁ እራራልሻለሁም ገንዘብሽ ሳያልቅ የልጅነትሽም ወራት ሳያልፍ አግብተሽ ልጅ ትወልጂ ዘንድ እመክርሻለሁ ባልሽም መንግሥተ ሰማያትን ወርሷል ምጽዋትም አይሻም።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፲፪
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
የመላእክት አለቃ ሊቀ መልአኩ ቅዱሰሰ ሚካኤል
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ የሚያከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው፤ እስክንድርያ በምትባል ከተማ አክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበረና፤ በየዓመቱ ሰኔ በባተ በዐሥራ ሁለት ቀን በዚያ ምኲራብ ሕዝቡ ተሰብስቦ ታላቅ በዓል ያደርጉ ነበር።
❖ በዚያም ምኩራብ ውስጥ ዙሐል የሚሉት ታላቅ የነሐስ ጣዖት ነበረና በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ብዙ ፍሪዳዎችን ያርዱለት ነበር፤ አባ እለእስክንድሮስም እስከተሾመበት ዘመን ድረስ ለዚያ ጣዖት እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ፤ ይኸውም ሦስት መቶ ዓመተ ምሕረት ተፈጽሞ በአራተኛው ምዕት ውስጥ ነበር፤ አባ እለእስክንድሮስ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት ስለ ተስፋፋች ያን ጣዖት ሊሠብረው ወድዶ ሳለ ጐስቋሎች ሰዎች ከለከሉት እንዲህም አሉት እኛ በዚህ ቦታ ይህን በዓል ማክበርን ለምደናል እነሆ ከአንተ በፊት ዐሥራ ስምንት ሊቃነ ጳጳሳት አልፈዋል ይህን ልማዳችንንም አልለወጡብንም ።
❖ አባ እለእስክንድሮስ ግን ገሠጻቸው አስተማራቸውም ስሕተታቸውንም በመግለጥ እንዲህ ብሎ አስተማራቸው ይህ ጣዖት የማይጎዳና የማይጠቅም ነው እርሱንም የሚያመልክ ሰይጣናትን ያመልካቸዋል ምክሬንስ ብትሰሙ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ ይህን በዓል እሠራላችኋለሁ ይኸውም ጣዖቱን እንድንሰብረው ምኵራቡንም እንድንባርከውና በከበረ መልአክ በመላእክት አለቃ በሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አድርገን እንድንሰይመው ነው እኛም ይህን ታላቅ በዓል እንሠራለን፤ የሚታረዱትም ላሞችና በጎች ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ለችግረኞችም በከበረው መልአክ ስም ምግብ ይሁኑ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ያለው ስለሆነ ስለእኛ ይማልዳልና ይህንንም ብሎ በዚህ በጎ ምክር አስወደዳቸው እነርሱም ታዘዙለት።
❖ ከዚህም በኋላ ያንን ምኵራብ አድሰው በዚህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አደረጉት በዚችም ዕለት አከበሩዋት። እርሷም የታወቀች ናት። እስላሞችም እስከ ነገሡበት ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ አፈረሱዋት። ይህም በዓል ተሠራ እስከ ዛሬም ጸንቶ ይኖራል።
❖ ዳግመኛ በዚች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፤ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል ይማልዳልም።
❖ የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙዎች ናቸው፤ ከእነርሱም አንዱ ይህ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው ነበረ አርሱም የከበረ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ይልቁንም በሰኔና በኅዳር ወር አብልጦ ያከብር ነበር፤ በጐረቤቱም ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ፤ ይህን እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሰው የከበረ መልአክ የሚካአልን በዓል በሚያደርግበት ጊዜ ይጠላውና ያቃልለው ነበር ለድኆች ስለ መራራቱም ይዘባበትበት ነበረ።
❖ የሕይወቱ ዘመንም ተፈጽሞ የሚሞትበትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካምም የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ የክቡር መልአክ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ታደርግ ዘንድ ምጽዋት ሰጭም ትሆን ዘንድ ሚስቱን አዘዛት።
❖ ከዚህም በኋላ አረፈና ገንዘው ቀበሩት ሚስቱም ፀንሳ ነበረች የመውለጃዋ ጊዜም ደርሶ ምጥ ያዛት በታላቅ ጭንቀት ውስጥ ሳለችም እንዲህ ብላ ጸለየች የእግዚአብሔር መልአኩ ሆይ ራራልኝ በእርሱ ዘንድ ባለሟልነት አለህና በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ እኔ ለምንልኝ፤ ይህንንም በአለች ጊዜ በቤቷ ውስጥ ብርሃን በራ ከችግርም ዳነች መልኩ ውብ የሆነ ወንድ ልጅንም ወለደች የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን እንዲህ ብሎ ባረከው ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት ጥሪቱንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዝዟል ባለጸጋውም በቤቱ በዐልጋው ላይ ሳለ ጌታ ጆሮውን ከፍቶለት ይህን ነገር ከመልአኩ ሰማ።
❖ ይህንንም በሰማ ጊዜ ታላቅ ኀዘን ደረሰበት ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመረ ነገር ግን ክብር ይግባውና ጌታ ይጠብቀው ነበር፤ ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ምክንያት አዘጋጅቶ የሚያገለግለኝ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ ልጅሽን ስጪኝ እኔም እየመገብኩና እያለበስኩ አሳድገዋለሁ ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ አላት።
❖ ይህንንም ነገር ከባለጸጋው በሰማች ጊዜ ስለችግሯ እጅግ ደስ አላት ልጅዋንም ሰጠችው እርሱም ሃያውን ወቄት ወርቅ ሰጣት ልጅዋንም ወሰደው የምሻው ተፈጸመልኝ ብሎ ደስ አለው።
❖ ከዚህም በኋላ በልጁ ቁመት ልክ ሣጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበት እስከ ባሕርም ተሸክመው ወስደው በባሕር ጣሉት ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሠጥም ከዚያች አገር የሃያ ቀን መንገድ ያህል ርቃ ወደምትገኝ ወደ አንዲት አገር ወደብ እስከሚደርስ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ።
❖ በባሕሩም አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበረና ሣጥኑን በውኃ ላይ ተንሳፎ አየው እርሱም ከባሕሩ አውጥቶ ወደ ቤቱ ወሰደው ይህንም ሣጥን እንዴት እንደሚከፍተው ያስብ ጀመረ ይህንም ሲያስብ ወደ ባሕሩ ይሔድ ዘንድ ጌታችን በልቡናው ኃሳብ አሳደረበት ወዲያውኑም ተነሥቶ ወደ ባሕሩ ሔደና አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ።
❖ ዓሣ አጥማጁንም መረብህን በኔ ስም ጣል ለሚያዘውም ዓሣ ዋጋውን እሰጥሃለሁ አለው አጥማጁም እንዳለው አደረገ ያን ጊዜም ታላቅ ዓሣ ተያዘ ዋጋውንም ሰጥቶ ዓሣውን ተቀበለ ዓሣውንም ይዞ ወደቤቱ ሔደ ለራትም ይጠብሰው ዘንድ አረደው በሆዱም ውስጥ መክፈቻ አገኘ። በልቡም ይህ መክፈቻ ይህን ሣጥን ይከፍተው ይሆን አለ በሣጥኑ ቀዳዳም በአስገባው ጊዜ ፈጥኖ ተከፈተ በውስጡም ይህን ታናሽ ብላቴና አገኘ፤ ልጅ የለውም ነበርና ታላቅ ደስታ ደስ አለው ጌታችንንም አመሰገነው። ሕፃኑንም በመልካም አስተዳደግ አሳደገው ሕፃኑም አድጎ ጐልማሳ ሆነ፤ ከብዙ ዘመናትም በኋላ ያ ባለ ጸጋ ተነሥቶ ወደዚያ አገር ሔደ በመሸም ጊዜ ወደ በግ ጠባቂው ደጅ ደረሰ በግ ጠባቂውን እስከ ነገ የምናድርበት ማደሪያ በአንተ ዘንድ እናገኛለን ኪራዩንም እሰጥሃለሁ አለው በግ አርቢውም እንዳልክ ይሁንና እደር አለው ባለጸጋውም በዚያ አደረ።
❖ እራት በሚቀርብም ጊዜ ሕፃኑን ባሕራን ብሎ ጠራው ባለጸጋውም ሰምቶ ልጅህ ነውን ብሎ ጠየቀው በግ ጠባቂውም አዎን ታናሽ ሕፃን ሆኖ ሳለ ከባሕር አግኝቼዋለሁና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጄ ነው አለው ባለጸጋውም በምን ዘመን አገኘኸው አለው እርሱም ከሃያ ዓመት በፊት ብሎ መለሰለት፤ ያን ጊዜም እርሱ ወደ ባሕር የጣለው መሆኑን አውቆ እጅግ አዘነ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
❤️ #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን።
❤️ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ነገረ ማርያምን ወደ ግእዝ ቋንቋና አራቱ ወንጌልን ወደ ተለያየ ቋንቋ ለተረጎሙት #ለአቡነ_መዝሙረ_ድንግል ለዕረፍታቸው በዐልና #በግብጽ_ቤተ_ክርስቲያ_ጨምር_ቅድስና ለተሰጣቸው #ለአብረ_ገብረ_ኢየሱስ_ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️#አቡነ_መዝሙረ_ድንግል፦ የተባሉት ጻድቅ አገራቸው ጎጃም ነው፤ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው። ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል።
❤️ ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር። በጣም ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው። ከአቡነ መዝሙረ ድንግል እግዚአብሔር አምላክዐ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ፦ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በአገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌል ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብጽ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብጽ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ። ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ። አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብጻውያን ይቀኑባቸው ነበር።
❤️ ስልሳ ስድስተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ገብረ ክርስቶስ ባረፉ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ተሰብስበው ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለከበረች ሹመት የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ተቀመጡ። በዚህም ጊዜ በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ለሚኖሩት ለጻድቁ አቡነ ገብረ ኢየሱስ የታዘዘ መልአክ ተገልጦላቸው "ለኤጲስ ቆጶሳቱ ለዚህች ለከበረች ሹመት የሚገባው ስሙ ገአርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና እርሱን ሹሙት አትዘኑ" በላቸው ብሎ ነገራቸው። አቡነ ገብረ ኢየሱስም "ከመካከላችሁ ስሙ ገአርጊ የሚባል ጻድቅ አለና እርሱን ሹሙት" ብለው መልአኩ የነገራቸውን መልእክት ነግረዋቸው አባ ገአርጊን ስልሳ ሰባተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመዋቸዋል።
❤️ አባ ገአርጊም ስማቸው አባ ቄርሎስ ተብሎ ከተሾሙ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል። የጻድቁ አባታችን ገዳላቸው በጣና ይገኛል። ሰኔ11 ቀን ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥተዋቸው ታቦት ቀርጸውላቸው በዓላቸውን በሚገባ ያከብሩላቸዋል። ከአቡነ ገብረ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
❤️ #ሰኔ ፲ 10
❤️ እንኳን #ለክርስቲያን_ወገኖች_በዓለሙ_ሁሉ #ታላቅ_ደስታ_ለሆነበት_መላእክትም_በሰማያት_ደስ #ለተሰኙባት_ቀን_በዓል (#በንጉሥ_ቈስጠንጢኖስ ዘንድ #የጣዖት_ቤቶች_እንዲዘጉ_አብያተ_ክርስቲያናትም_እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ወጥቷልና፣ ለቅዱሳን ደናግል #ደባሞንና_ብስጣሞን_ለእናታቸው_ለቅድስት_ሶፍያ_ሰማዕታት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከእነ ቅድስት ሶፍያ ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበሉ #ከቅድስት_ዮና #ከቅዱሳን_ዋርስኖፋና_አውሎጊስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሰማዕት_ከቅዱስ_አቅሊሞስ፣ #ከአባ_ነአንና #ከይስካ_ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
✝️#በዚች_ዕለት_ለክርስቲያን_ወገኖች_በዓለሙ_ሁሉ_ታላቅ_ደስታ_ሆነ_መላእክትም_በሰማያት_ደስ_ተሰኙባት። በዚች ቀን እውነተኛ ምዕመን ከሆነ ከንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ የጣዖት ቤቶች እንዲዘጉ አብያተ ክርስቲያናትም እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ወጥቷልና።
❤️ ደስታን የተመላች ያች መልእክት ወደ እስክንድርያ ከተማ እንደ ዛሬዋ ቀን በደረሰች ጊዜ ፈጽሞ ደስ ተሰኙ ወደ ግብጽ አውራጃዎችም ሁሉ ላኳት ምዕመናን ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን ክብር ከፍ ከፍ ማለት ደስ አላቸው የጣዖታት ቤቶችንም ዘጓቸው አብያተ ክርስቲያናትንም ከፈቱአቸው እንደ ዛሬም በዚች ዕለት ሰኔ 10 ቀን በዓል አደረጉ ይኸውም ቈስጠንጢኖስ በነገሠ በዐሥራ አንድ ዓመቱ ነበር እለእስክድሮስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመባት በመጀመሪያ ዓመት ነበር። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ቸርነቱ ይደረግልን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ ቅዱሳን ደናግል ደባሞንና ብስጣሞን እናታቸው ቅድስት ሶፍያ፦ እንዲህም ሆነ ስሙ ዋርስኖፍ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በወደዱ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ናባ አውራጃ እሊህ ደናግል ወዳሉበት ወደ ግሕሙን ደርሶ በዚያ አደረ። በዚያቺም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት "ከዚህ ለምን ትተኛለህ ተነሥተህ ተጋደል ለአንተና ሰማዕት መሆን ለሚሹ ሁሉ አክሊል ተዘጋጅተቀልና አሁንም ተነሥተህ ወደ መኰንኑ ሒድ በፊቱም ቁመህ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመን" አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ራእይን እንዳየ ለቅዱሳን ደናግል ነገራቸው።
❤️ ሲነጋም ተነሥተው ከእርሱ ጋራ ወደ መኰንኑ ሔዱ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ታመኑ። መኰንኑም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸውና ወደ ወህኒ ቤት ጨመራቸው ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ከዚያ አውጥቶ ከቅዱስ ዋርስኖፍ ጋራ ወደ ስንሑር ላካቸው እናታቸውም ትከተላቸው ነበር። መኰንኑም "ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ" አላቸው ባልታዘዙለትም ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ አጸናቸው ቊስላቸውንም ፈወሰ።
❤️ ከዚህም በኋላ መኰኑኑ ከእርሱ ጋራ ወደ አገረ ፃ ይዞአቸው ሔደ። የጣዖታቱ ካህናትም ጣዖታቱን እንደምትረግም ስለ ቅድስት ደባሞን ነገሩት እንዲሁም ባልጀራዋ ዮና የምትባል ሴት እንዳለች ነገሩት እርሱም ኅብራቸው በየራሱ የሆኑ መልካም ልብሶችን እየሠሩ ለምግባቸው ይሸጡ ነበር የተረፋቸውንም ይመጸውቱ ነበር። መኰንኑም የዮናን ዜና ሰምቶ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጥ ባለሰይፉን ላከው የሰያፊውም ስም አውሎጊስ ነው። ወደርሷም በቀረበ ጊዜ ፊትዋ እንደ መላእክት ፊት ብርሃንን ተመልቶ አየና ፈራ እርሷንም ወደ መኰንኑ እንዲወስዳት እንጂ እንዳይገድላት የእግዚአብሔር ጸጋ አስገነዘበችው ቤተ ሰቦቿም ተሰናባብተዋት ጸንፋ ከሚባል አገር ወጣች ወደ አገረ ፃ ደርሳም መኰንኑን ተገናኘችው ከቅዱስ ወስኖፍና ከባልንጀሮቹ ጋራ እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ። ሰያፊው አውሎጊስም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነና ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ እንዲሁም እሊያን ቅዱሳት ደናግልንም ራሳቸውን ቈረጧቸው ገድላቸውንም ፈጽመው የድል አክሊልን ተቀበሉ።
❤️ ቅድስት ደባሞንን ግን ጽኑዕ ሥቃይ ያሠቃዩአት ዘንድ በመንኰራኵር ላይ ሰቀሉአት። በዚህ ሥቃይም ውስጥ ለብዙ ቀኖች ኖረች የእግዚአብሔር መልአክም ያጸናት ያስችላትና ቊስሎቿን ይፈውሳት ነበር መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገባት በዚያም ጥቂት ቀን ኖረች ወደ ፍርድ ሸንጎም አስቀርቦ "ለአማልክት ሠዊ"" አላት ባልሰማችውም ጊዜ ራሷን እንዲቆርጡ አዘዘ። ራስዋንም ሊቆርጡ ከከተማ ወደ ውጭ በአወጧት ጊዜ ሴቶች ሁሉ እያለቀሱ ከብበዋት ነበር ራስዋንም በሰይፍ ቆረጥዋት እንዲሁም እናቷንና እኅቷን በሰይፍ ቆረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የድል አክሊል ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳት ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይድረስን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 10 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ለሶፍያ_ወለአዋልዲሃ_ዲባሞን #ወብስጣሞን_ዘሳተፋ። ይሰነዓዋ ለስምዕ ምስለ ዋርስኖፋ። እማ ወዮና ዘሀገረ ጸንፋ። እምነ ወዲቅ ኪያየ ይሐቅፋ። ከመ ዕጐሊሃ ተሐቅፍ ዶርሆ በክንፋ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_10።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ተፈሣሕነ ወተሐሰይነ በኲሉ መዋዕሊነ። ወተፈሣሕነ ህየንተ መዋዕል ዘአሕመምከነ። ወህየንተ ዓመተ አንተ ርኢናሃ ለእኪት"። መዝ 89፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥25-35፣ 1ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 15፥30-36። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 11፥20-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ የዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የበዓለ ዕርገት ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።
መዝሙር ዘሰንበት
መዝሙር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
በሰንበት ዐርገ ሐመረ ገሠፀ ባሕረ፤ ወገሠፆሙ ለነፋሳት፤ ወይቤሎሙ ኢትናፍቁ፤ ወኢይምጻእ ኑፋቄ ውስተ ልብክሙ፤ በከመ ፈነወኒ አቡየ አነኒ እፌንወክሙ፤ ውስተ ቤተ አቡየ ብዙኅ ማኅደር ቦቱ፤ ካዕበ እመጽእ ወእነሥአክሙ ከመ ተሀልዉ ምስሌየ፤ በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት።
ዓራራይ
ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ወሰበረ ኆኃተ ብርት እግዚአ ለሰንበት፤ አመ ሣልስት ዕለት ሞዖ ለሞት፤ ወዓርገ ውስተ ሰማያት።
ዕዝል
ተንሢኦ ዐርገ ሰማያተ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ በይባቤ ዐርገ ወበቃለ ቀርን፤ ኄር ለኄራን።
ሰላም
ወልድ እኁየ ውእቱ ፍቁርየ ውእቱ ተንሥአ እሙታን ገብረ ሰላመ ለኲሉ ዓለም ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ሎቱ ስብሐት ለዘቀደሳ ለሰንበት።
🔆 መልካም ዕለተ ሰንበት 🔆
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
❤️ #ሰኔ ፱ (9) ቀን።
❤️ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘው #ደብረ_ምዕዋን ለመሰረቱ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ብፁዕ_አምላክ_ደቀ_መዝሙር ለሆኑት #ለአቡነ_በኵረ_ድንግል_ዘደብረ_ምዕዋን_ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አቡነ_በኵረ_ድንግል፦ የአቡነ ብፁዐ አምላክ ረድእ የነበሩ ሲሆን እርሳቸውም ካረፉ በኋላ ተመርጠው በደብረ ምዕዋን ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆነው ተሾመው ብዙ አገልግለዋል" ጻድቁ በምድረ ኤርትራ በምንኩስና እና በብሕትውና ጸንተው ለትልቅ ሰማያዊ ክብር የበቁ ታላቅ ጻድቅ ናቸው። በዓለ ዕረፍታቸው ሰኔ 9 ነው።
❤️ የአቡነ በኵረ ድንግል፦ አባታቸው ማርቆስ እናታቸው እግዚእ ክብራ የሚባሉ ሲሆን ጻድቁ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ ብዙ ተኣምራት ይሠሩ ነበር" ሲወለዱም የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከነልጇ (ምስለ ፍቁር ወልዳ) በልባቸው ላይ ተሥላ ተገኝታለች" በማሕፃን ሳሉ ተመርጠዋልና በአኵሱም ሲወለዱ እንደሌሎቹ ቅዱሳን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ብለው ስመ ሥላሴን ጠርተው አመሰገኑ። በዚያ የነበሩና ይህንን የተመለከቱ ሰዎችም ባዩትና በሰሙት ነገር እጅግ ተደነቁ።
❤️ በ40ኛው ቀናቸውም በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት እንዲቀበሉ ወላጆቻቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዷቸው በወቅቱ የነበሩት ጳጳሱ አቡነ ሰላማ ሕፃኑ ትልቅ መነኵሴና የአቡነ ብፁዐ አምላክ ደቀ መዝሙር እንደሚሆን ተገልጾላቸው ትንቢት ተናገሩ። ዳግመኛም ጳጳሱ ቅብዓ ሜሮን ሊቀቡት ሲሉ ሥዕለ ማርያም ከነልጇ በሕፃኑ ደረት ላይ ተሥላ አይተዋት ደነገጡ ወዲያውም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጸ ሳይፈሩ ሥርዓተ ጥምቀቱን እንዲፈጽሙ አዘዛቸው ዳግመኛም ..… "ስሙን በኵረ ድንግል በለው ትርጉሙም በልቡ ላይ ያየኸው ሥዕል ነው" ብሎ ነገራቸው" ሕፃኑም ከተጠመቀ በኋላ እመቤታችን ከነልጇ ጋር ተገልጻ በትእምርተ መስቀል ባረከችው ያ ትእምርተ መስቀልም ዳግመኛ በሰውነታቸው ላይ ተሳለ።
❤️ ከዚህም በኋላ አቡነ በኵረ ድንግል አድገው ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ በእረኝነት እያገለገሉ በመልካም አስተዳደግ አደጉ" ዕድሜአቸው ለትምህርት እንደደረሰ ወላጆቻቸው ለንቡረ እድ ዮፍታሔ ሰጧቸውና አስተማሯቸው። ከቋንቋዎች ግእዝ፣ ዐረብ ዕብራይስጥ፣ ጽርዕ እና ሮማይስጥ ተማሩ፤ ብሉይንና ሐዲስን እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን ሁሉ አጠናቀው ተማሩ። ቅኔ ድጓ ጾመ ድጓ እና የቅዱስ ያሬድን ዜማዎችም በሚገባ አጠኑ። ትምህርታቸውንም ከጨረሱ በኋላ መምህራቸው ወደ ሊቀ ጳጳስ ወሰዱአቸው በልባቸው ያለች የእመቤታችን ሥዕልም ለጳጳሱ ተገልጣ "ይህ የምወደው ልጄ ስለሆነ በልቡ ተሳልሁ ስለዚህ ዲቁና ቅስና ስጠው፣ ኤጲስ ቆጵስነትም ሹመው" አለቻቸው። ጳጳሱም ባዩትና በሰሙት ነገር ተደንቀው ተነሥተው እንደተባሉት በሦስቱ መዕረግ ሾሟቸው። ከሹመታቸውም በኋላ በአከባቢው ያሉ ሰዎች አቡነ በኩረ ድንግልን ብርሃን ለብሰው ስላዩዋቸው በጣም ተደነቁ።
❤️ ከዚህም በኋላ አቡነ በኵረ ድንግል ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ወላጆቻቸው በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ሚስት ሲያጩላቸው አቡነ በረ ድንግል ግን "እኔስ ፍላጎቴ በድንግልና መኖር እንጂ ማግባት አይደለም" ብለው ሌሊት ተነሥተው ከቤታቸው ጠፍተው ወደ እግዚአብሔር ቤት ሔደው "አቤቱ ጌታ ሆይ! ከዘለዓለም እሳት ከዲያብሎስ እሥራት ሰውረኝ መጥፎውን ሐሳብ ከእኔ አርቀህ ፍቃድህን እፈጽም ዘንድ እርዳኝ የእመቤታችን ሥዕል ከነልጇ በልቤ አለና ወደ ጋብቻ ዓለም ለመግባት ኅሊናዬ አልፈቀደልኝም ስለዚህ ፍቃድህ ቢሆንልኝ እንደ መላእክት ንጹሕ ሁኜ እንድኖር እለምንሃለሁ፣ አንተ ድኃና ምስኪን የማትንቅ አምላክ መሆንህን ዐውቃለሁና…" እያሉ ጸለዩ። እየጸለዩ ሳለ ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤል አስከትላ ተገለጠችላቸውና "ልጄ ሆይ! ጸሎትህ ተሰምቷልና ወደ ደብረ ዳሞ ወደ አባትህ ሒድ፣ እንዲሁም ደግሞ ወደ ደብረ ናዝሬት ወደ ብፁዐ አምላክ ዘንድ ሒድ የብዙዎች አባትም ትሆናለህ" በማላት ከባረከቻቸው በኋላ ተሰወረች።
❤️ ከዚህም በኋላ ጻድቁ መጋቢት 9 ቀን በቦታቸው ሆነው በተመስጦ እየጸለዩ ሳሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በደመና ተሸክሞ ወስዶ ደብረ ዳሞ የቅዱሳን ማረፍያ ቦታ አደረሳቸው። እመቤታችን እንደነገረቻቸው በገዳሙ አስቀድማ እንደነገረቻቸው ለረጅም ዓመታት በትሕትና ካገለገሉ በኋላ ወደ አባታቸው ወደ አቡነ ብፁዐ አምላክ ከረጅም ጉዞ በኋላ መጡ። አቡነ ብፁዐ አምላክም አስቀድመው መምጣታቸውን ያውቁ ነበርና አሁን ሲያገኗቸው እግዚአብሔርን አመስግነው በታላቅ ደስታና ትሕትና ተቀበሏቸው።
❤️ በገዳማቸውም በትሕትና እያገለገለ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን አቡነ ብፁዐ አምላክ "ዛሬ በእጅህ ቍርባን እንድንቀበል አንተ ቀድስ" አሏቸው። አቡነ በኩረ ድንግልም ቅዳሴ ገብተው አሐዱ አብ ቅዱስ… ብለው ሲጀምሩ ከመሬት ወደላይ 5 ሜትር ያህል ከፍ ብለው ታዩ፤ ይኽንንም አይተው አቡነ ብፁዐ አምላክ በጣም ተደንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አቡነ በኵረ ድንግልም በእንዲህ ያለ ሕይወት አባታቸውን አቡነ ብፁዐ አምላክን ካገለገሉ በኋላ አቡነ ብፁዐ አምላክ ታኅሣሥ 9 ቀን የገዳማት መነኰሳትን ሰብስበው "ዛሬ ለሁላችሁ መሪ የሚሆን ትሑትና ደግ መምህር እሰጣችኋለሁ ከእኔ በታች እርሳቸውን ስሟቸው ታዘዙአቸውም" ብለው ነገሯቸው።
❤️ ዳግመኛም አባታችን አቡነ ብፁዐ አምላክ የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ የገዳሙን መነኰሳት ሰብስበው ከእርሳቸው በኋላ አባት እንዲሆኗቸው አቡነ በኵረ ድንግልን እጃቸውን ጭነው ባርከው ሾሟቸው። ከዚህም በኋላ አቡነ በኵረ ድንግል በጾም በጸሎት በስግደት ለገዳሙና በገዳሙ ለሚኖሩ መነኰሳት ሁሉ በትሕትና እያገለገሉ በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ። የገዳሙ መነኰሳትም በጣም ወደዷቸው። ተጋድሏቸውንና አገልግሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ በኵረ ድንግል እንዲህ የሚል ቃልኪዳን ገባላቸው።
❤️ "በስምህ ዝክር የሚዘክር ስምህን የሚጠራ በዕረፍትህ ቀን የታመሙትንና የታሰሩትን የጎበኘ በስምህ የተራበ ያበላ ያጠጣ የታረዘ ያለበሰ የልጁን ስም በስምህ የጠራ ይህን ሁሉ ያደረገውን እምረዋለሁ ክፉም አይነካውም፤ በደብረ ምዕዋን በአባትህ በብፁዐ አምላክ ቦታ በአንተም ቦታ የተቀበረ በቦታው ቅዱስ ቍርባን የተቀበለ ክፉ አያገኘውም፣ እምረዋለሁ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምም አስገበዋለሁ ብሔረ ሕያዋንና ብሔረ ብፁዓንንም አወርሰዋለሁ…" የሚሉ ታላላቅ የምሕረት ኪዳናትን ከእግዚአብሔር ከተቀበሉ በኋላ ሰኔ 9 ቀን ትንሽ የራስ ምታት ሕመም ጀመራቸው። የገዳሙ መነኰሳትና ሌሎቹም ታላላቅ ቅዱሳን አባቶች እንደእነ አቡነ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን ያሉት እንደየ ደረጃቸው ከያሉበት ተሰበሰቡ። በዚህም ጊዜ ሥሉስ ቅዱስ ተገልጸውላቸው ድጋሚ ቃልኪዳን ገብተውላቸው አረጋጓቸውና ቅድስት ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች።
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
❤️ #ሰኔ ፱ (9) ቀን።
❤️ እንኳን #ልበ_አምላክ የተባለውን ታላቁን ንጉሥ መዝሙረኛው #ቅዱስ_ዳዊት_ቀብቶ_ላነገሠው ለታላቁ #ነቢይ_ለቅዱስ_ሳሙኤል_ለዕረፍቱ_መታሰቢያ በዐልና #ለቅዱስ_ሉክያኖስ ከሌሎች #አራት_ሰማዕታት ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #ከቅዱሳን_ከዮሐንስና #ከጳጳስ_አርልክሳ_ከዕረፍታቸው_መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #ነቢዩ_ቅዱስ_ሳሙኤል፦ የዚህ ቅዱስ አባቱ ሕልቃና ይባላል የእናቱም ስሟ ሐና ነው እርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው ሐናም መካን ነበረች ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት በቤቷም ሦስት ዓመት አሳደገችው።
❤️ ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ። የካህኑ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበር የሚታይ ራእይም አልነበረም።
❤️ ከዚህም በኋላ በአንዲት ሌሊት እንዲህ ሆነ ኤሊ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ዐይኖቹንም መፍዘዝ ጀምረው ነበር ማየትም አይችልም ነበር። የእግዚአብሔርንም መብራት አብርቶ ለማሳደር ገና አላዘጋጁም ነበር ሳሙኤል ግን በቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ማደሪያ ታቦት አጠገብ ተኝቶ ነበር። እግዚአብሔርም "ሳሙኤል ሳሙኤል ሳሙኤል" ብሎ ጠራው እነሆ እኔ አለሁ አለ። ወደ ኤሊም ፈጥኖ ሔደ "ስለጠራኸኝ እነሆ እኔ መጣሁ" አለው። ኤሊም "አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ" አለው ሒዶም ተኛ። እግዚአብሔርም ዳግመኛ "ሳሙኤል ሳሙኤል ሳሙኤል" ብሎ ጠራው ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ኤሊ ሔደ ስለ ጠራኸኝ እነሆ መጣሁ" አለው ኤሊም "አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ" አለው።
❤️ ሳሙኤልም ከዚህ አስቀድሞ እግዚአብሔርን በራእይ ገና አላወቀውም ነበር ቃለ እግዚአብሔርም አልተገለጠለትም ነበር። ዳግመኛም እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሦስት ጊዜ ጠራው ተነሥቶም ወደ ኤሊ ሔደ "ስለጠራኸኝ እነሆ መጣሁ" አለው ኤሊም ያንን ልጅ እግዚአብሔር እንደጠራው አሰበ። "ልጄ ተመልሰህ ተኛ የሚጠራህ ካለ እኔ ባሪያህ እሰማለሁና ጌታዬ ተናገር በለው" አለው ሳሙኤልም ሒዶ በመኝታው ተኛ። እግዚአብሔር መጥቶ እንደ መጀመሪያው በፊቱ ቁሞ ጠራው። ሳሙኤልም "እኔ ባሪያህ እሰማለሁና ጌታዬ በል ተናገር" አለው እግዚአብሔርም ሳሙኤል "የሰማው ሁሉ ሁለቱን ጆሮዎቹን ይይዝ ዘንድ እንሆ እኔ በእስራኤል ላይ የተናገርሁት ቃሌን አደርጋለሁ። በዚያችም ቀን በኤሊና በወገኑ ላይ የተናገርኹትን ሁሉ አጸናለሁ እጀምራለሁ እፈጽማለሁም። ልጆቹ እግዚአብሔርን ቃል አቃልለዋልና እርሱም አልገሠጻቸውምና በልጆቹ ኃጢአት እኔ ወገኑን በዘላለም እንደ ምበቀለው ነገርሁት። ስለዚህ ነገር በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም በመሆን የኤሊ የወገኑ ኃጢአት እስከ ዘላለሙ ድረስ እንዳይሠረይ ራሴ እንዲህ ብሎ ማልሁ"። በኤሊ ወገኖችና ልጆች ላይ እግዚአብሔር የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ።
❤️ ከዚህም በኋላ የቂስ ልጅ ሳኦልን ቀብቶ ለእስራኤል ልጆች ያነግሠው ዘንድ እግዚአብሔር ሳሙኤልን አዘዘው እንዲአነግሥላቸው ለምነዋልና። ሳኦልም የልዑል ትዕዛዝ በተላለፈ ጊዜ ዳግመኛ ለእስራኤል ንጉሥ ሊሆን የዕሴይ ልጅ ቅዱስ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ ይህን ነቢይ ሳሙኤልን ዳግመኛ አዘዘው።
❤️ ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው። ከዚህም በኋላ ሰኔ 9 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #ቅዱስ_ሉክያኖስና_አራቱ_ሰማዕታት፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ የጣዖት ካህን ነበር የሰማዕታትንም መከራቸውን በእሳት ሲአቃጥሏቸውና ሕዋሳታቸውን ሲቆራርጧቸው ሲሰቅሏቸው ከእሳት ምድጃ ውስጥም ሲጥሏቸው ምንም ምን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በአየ ጊዜ ከዚህ ሥራ የተነሣ አደነቀ ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ ያገለግላቸው የነበሩ ጣዖታት ከእሳት ቢጥሏቸው ፈጥነው ይቃጠላሉ እንጂ ይህን ሥራ ሊሠሩ እንደማይችሉ ተረድቷልና። ዳግመኛም እንዲህ አለ "ይህን ድንቅ ሥራ የሚሠራ አምላክስ በእውነት እርሱ አምላክ ነው"።
❤️ ከዚህ በኋላም በንጉሥ ፊት "እኔ ክርስቲያን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ አምናለሁ" ብሎ በግልጥ ጮኾ ተናገረ። ንጉሡም ወደርሱ አቅርቦ ጣዖት ማምለክን እንዳይተው መከረው ወደ አምልኮ ጣዖት ይመለስ እንደሆነ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባለት። እርሱም ግን አልሰማውም ሥቃዩንም አልፈራም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃየው ጀመረ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት መንጋጋውንም በደንጊያ አሰንዲሰብሩት ታላቅ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ።
❤️ ከዚህም በኋላም አራት ክርስቲያን እሥረኞች ቀረቡና ከእርሱ ጋራ አቆሟቸው ንጉሡም "ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃያችኋለሁ" አላቸው። እነርሱም ለስሕተቱ አልታዘዙለትም በላያቸውም ተቆጥቶ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመራቸው ያንጊዜ ዝናብ ዘነበ እሳቱንም አጠፋው።
❤️ ቅዱስ ሉክዮስን ግን "እንደ አምላክህ እሰቅልሃለሁ" ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ እንዲሰቅሉት አዘዘ በረጃጅም ችንካሮችም ሥጋውን ሁሉ ቸነከሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። እንዚያን አራቱን ሰዎችም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሉክያኖስና በከበሩ አራት ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ቴድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 9 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ለሉክያኖስ_ዘአድምዐ_ተወድሶ። ምስለ ፬ቱ ዕደው ሥቃያተ ስምዕ በተዓግሦ። ሶበ ለአማልክት ኢሦዐ መሥዋዕተ ልዑል አስተኀይሶ። እለ ቀነውዎ እስከ ይመጡ ነፍሶ። እስመ በአዕባን ቀጥቀጡ መንከሶ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_9።
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፰
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ስምንት በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው፤ ይህም እንዲህ ነው ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው።
❖ ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ።
❖"ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው፤ በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት እርሷም እስከ ዛሬ አለች ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።
እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ዕብል ለቅዳሴ ቤትኪ ሕንዕት። ኀበ አንቅዐ ወልድኪ ማየ በረከት። ማርያም ድንግል በስምኪ በቊዔት። እስመ ይትወሀብ ለዘጸለየ በኲሉ ዕለት። ሠናይ ሀብት ወፍጹም ፍት።
በዚችም ዕለት የአንድ ሽህ ሁለት ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው። ደግሞ የአትካሮንና የአውሎጊስ የበዓላቸው መታሰቢያ ሆነ። በጸሎታቸውም ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን እግዚአብሔር ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
በዚችም ዕለት የርማኖስ እናት ትምዳ አረፈች በረከቷ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ሰላም ትምዳ ወውሉዳ። ርማኖስ ወእሙ ዘተካፈሉ ክበዳ። ጽሑፋነ መልክዕ ወስም ለኢየሩሳሌም በዐውዳ። በደመ ስምዖሙ ይትሐበዩኒ እምዕዳ። በእንተ ኃጢአት ወጽድቅ አመ ይከውን ፍዳ።
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
❤️ #ሰኔ ፯ (7) ቀን።
❤️ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለድንግል_ማርያም_ቤተ ክርስቲያን_ለተከፈተበትና ለከበረችበት፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም ለሆነ #ለአባ_አበስኪሮን_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ መኰንን አርማንዮስ ካሠቃያቸው #ከአስራ_ስድስት_ሺህ_ሰማዕታት ከዕረፍታቸው መታሰቢያና ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
#በዚች_ዕለት_አምላክን_የወለደች_የእመቤታችን_የድንግል_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን_የተከፈተበትና_የከበረችበት ነው። እርሷም ዌላ በሚባል አደባባይ ያለች ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ተዘግታ የኖረች ነበረች። ይኸውም በአንድ ሽህ ሃያ ዓመተ ሰማዕታት ነው። ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ሰው ለሆነ ሕይወትና መድኃኒት አድርጎ እርሷን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አባ_አበስኪሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዝ በደረሰችው ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት።
❤️ መኰነንኑም ወደ አገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልደፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስና ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮስ ጋር ተስማሙ። በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ።
❤️ የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ። ይህንም ሁሉ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር።
❤️ ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ያም መሠርይ "የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ" ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ። ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን "የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለበት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አንተን ይቀጣሃል" አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ። በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ሰኔ 7 ቀን ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
❤️ ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን እንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ክፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞተ።
❤️ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን በፈረስ ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም "ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ" አላቸው። እነርሱም "ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ" አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ።
❤️ ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅዱሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት። የአገር ሰዎችም በጥዋት ነቅተው ወደ ውጭ በወጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በአባ በአበስኪሮን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 7 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ "#ሰላም_ዕብል_ለርኅወተ_ቤትኪ_ዮም። ከመ ኤልያስ አርኀወ ኆኅተ ዝናም። በስሱ አውራኅ ወበሠላስ ዓም። ማርያም ሥመሪ አርኅዎቶ ለሕሊናየ ሕቱም። ከመ ላዕሌሁ ይትከዐው ምስለ ጽድቅ ሰላም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 7።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ። ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር"። መዝ 86፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥6-10 እና የሐዋ ሥራ 12፥10-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥14-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን ማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም በዓል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዐልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️
❤️ ሰኔ ፯ (7) ቀን።
❤️ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ከሾሟቸውና_በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው #ከ47ቱ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ማቴዎስ_ዘእንደርታ_ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዐልና ለታላቁ አባት #ለጻድቁ_ለሐዋርያም ለደራሲም ለመላእክት በዐል የሚቀደሰው ከ14_ቅዳሴ አንዱ የሆነ በስሙ የተሰየመው ቅዳሴ ለደረሰ ለተከራካሪ መምህርም #ለያዕቆብ_ዘሥሩግ_ለዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አቡነ_ማቴዎስ፦ እኚህ ጻድቅ ትውልድ አገራቸው እንደርታ ሲሆን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሾሟቸውና በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው ከ 47ቱ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ጻድቁ መላ ሰውነታቸው እንደ እሳት ያቃጥል ነበር። ወንጌልን በመስበክና በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ብዙ ያገለገሉ ታላቅ አባት ናቸው። መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤️ #አቡነ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ፦ አገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት አገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ መካከል በምትገኝ ሥሩግ በምትባል አገር ስለሆነ ያዕቆብ ዘሥሩግ ተባለ። በ 3 ዓመቱ እናቱ ቤተ መቅደስ ስትወስደው መልአክ እጁን ይዞ በሊቀ ጳጳሱ እጅ እንዲቆርብ አድርጎታል። በዚህም ጊዜ ምሥጢራት ሁሉ ተገልጠውለታል። ገና በ 7 ዓመቱ ስለ ሦስት ነገሮች በእጅጉ ያለቅስ ነበር። "ነፍሴ ከሥጋዬ ተለይታ ስትወጣ ከጌታችን ጋር ስትገናኝና መጨረሻውን ፍርድ ስሰማ እነዚህን ሦስት ነገሮች በእጅጉ እፈራለሁ" እያለ ያለቅስ ነበር።
❤️ በ 12 ዓመቱ ብሉይንና ሐዲስን አጠናቆ ተመምሮ ጨርሷል። ጸጋውን ዐውቀው 5 ቱ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው እጅ ነስተውት አዲስ ድርሰት ድረስልን ቢሉት እርሱም በፍጹም ትሕትና "በእናንተ ፊት እንኳን አዲስ ድርሰት ልደርስ ቀርቶ የተደረሰውንም መናገር አልችልም"። አላቸው። እርሱ በነበረበት ዘመን በሮማው መናፍቅ ልዮን አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለችበት ጊዜ ነበርና እነ ዲዮስቆሮስ "የውሾች ጉባኤ" ከተባለው ከኬልቄዶን ጉባኤ ተለይተው ሃይማኖትን ሲያጸኑ ልዮንንም ማውገዛቸውን ያዕቆብ ሲሰማ በዲዮስቆሮስ ጽናት በእጅጉ ተደስቶ ደብዳቤ ጽፎ አመስግኖታል። እነ ልዮንን ግን አውግዞ እረግሟቸዋል። ልዮንም ተከታይ ባገኘ ብሎ "እኔን ምሰል" በማለት ለያዕቆብ ደብዳቤ ጻፈለት። ያዕቆብም "ሳጥናኤል ከመላእክት ጋር ምን አንድ አደረገው? አንተ ርኩስ ነህ፤ የዲዮስቆሮስን ጥርስ አስወልቀህ፣ ጢሞን አስነጭተህ፣ ሃይማኖትህን የቀየርህ ከሁለት ዓለም ስደተኛ ጋር አልተባበርም፣ ይልቅስ ንስሓ ግባ፣ ንስሓ ባትገባ ግን አንተ ዲያብሎስ ነህ ተከታዮችህም አጋንንት ናቸው። በማለት መልሱን ጽፎለታል። እምቢ ብሎ በክህደቱ ቢጸናበትም አውግዞ እረግሞ ንጽሕናውን ቅድስናው እንደ መላእክት ነው የተባለለት ያዕቆብ ዘሥሩግ ጻድቅም ሐዋርያም ደራሲም ተከራካሪ መምህርም ነው። ሦስት ድርሰቶች ያሉት ሲሆን በስሙ የተጠራው ቅዳሴም አለው። ዕረፍቱ ሰኔ 7 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ያዕቆብ ዘሥሩግ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱም ይማረን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
