ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
603
订阅者
-324 小时
-87 天
-1730 天
帖子存档
❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤️ ❤️ እንኳን #ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ #ለብርሃነ_ዕርገቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                                       ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የጌታችን_የአምላካችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ+ክርስቶስ_ዕርገት፦ እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሁኖ ዐረገ። ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ። ❤️ በዚህም ዕርገቱ የሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና። አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ። ❤️ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ። ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሽብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ። ❤️ በጌታችንም ዕርገት የቅዱስ ዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል "ሌሊት በራእይ አየሁ እንሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት። የዘላለም አገዛዝ፣ ጌትነት፣ መንግሥት፣ የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የሚያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው"። ለእርሱም ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት8 ስንክሳር።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ። ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ። ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል"። መዝ67፥32-33። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ24፥45-ፍ.ም።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ"። መዝ 46፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 1፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥18-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥14-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የብርሃነ ዕርገቱ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❖ ቅዱሱ ንጉሥ ሁሉ ነገር የተሰጠው አባት ነው፤ ሁሉ ሕይወቱም ለእኛ ት/ቤት ነው፤ ሰው ነውና የኦርዮን ሚስት ቀምቶ ኦርዮን አስገድሎ ነበር፤ ጉዳዩን ነቢዩ ናታን በምሳሌ ሲነግረው ፍጹም ተጸጸተ፤ ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ አለቀሰ፤ መሬትንም በእንባው ክንድ አራሳት፤ ሐረግ እስከ ማብቀልም ደረሰ፤ እግዚአብሔርም ንስሃውን ተቀብሎ ከፍ ከፍ አደረገው፤ በንስሃ ሆነ። ❖ በቤተክርስቲያን ትምህርት ቅዱስ ዳዊትን የሚያህል ነቢይ (ምሥጢር የበዛለት) አልተገኘም፤ 'ከዓለም በፊት እንዲህ ነበረ' ብሎ ከዚያ ከስነ ፍጥረት እስከ ዳግም ምጽዓት የተናገረ እርሱ ነው:: ❖ ስለ መላእክት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ደናግልና መነኮሳት ሁሉ መናገሩ ይደነቃል፤ ስለ ድንግል ማርያምና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስም አምልቶ አስፍቶ ተናግሯል፤ 150 ምዕራፎች ባሉት መጽሐፈ ትንቢቱ ኃላፍያትንና መጻዕያትን ተመልክቷል:: ✍️ስለዚህም አበው "አልቦ ምሥጢር ወአልቦ ትንቢት ዘኢተናገረ አቡነ ዳዊት" ይላሉ:: ❖ ቅዱሱ ነቢይና ንጉሥ በጣም የሚታወቀው በዝማሬው ነው፤ ለራሱ ባለ 10 አውታር ለመዘምራኑ ደግሞ ባለ 8 አውታር በገናን አዘጋጅቶ ፈጣሪውን ያመሰግን ነበር:: ❖ 24 ሰዓት ሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዳይቁዋረጥ 288 መዘምራንን በአሳፍ መሪነት መድቦ ነበር፤ ራሱም በፍጹም ተመስጦ ማር ማር እያለው እግዚአብሔርን ያመሰግነው ነበር። ✍️"ቃልህ ለጉረሮየ ጣፋጭ ነው" እንዲል:: ❖ የዳዊት መዝሙሩ ለአጋንንት ትልቅ ጠላት ነው፤ ቅዱሳን መላእክትም በዳዊት መዝሙር ይዘምራሉ:: ✍️"በዘቦቱ ይሴብሑ ሰማያውያን ወምድራውያን" እንዲል:: 📖መዝ 131፥2 ❖ የፈጣሪውን ፈቃድ ሊጠይቅ ሱባኤ ቢገባ ✍️"አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ 👉አንተ ሳትሆን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው" አለው:: ✍️"ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ 👉እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ሲል ተናግሯል:: ❖ የኪዳኑ ጽላት (ጽዮን) ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ከዙፋኑ ወርዶ ከተራው ሕዝብ ጋርም ተቀላቅሎ በበገናና በመሰንቆ ተጫወተ፤ ስለ ፈጣሪው ክብሩን ተወ፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የሚገዛ ኃያል ንጉሥ ነበርና፤ በጽዮን ፊት እየወደቀ እየተነሳ እየታጠቀ እየፈታ ሲዘምርም ሚስቱ ሜልኮል ናቀችው፤ እግዚአብሔር ግን ከፍ ከፍ አደረገው:: 📖ሳሙ 6፥16 ✍️የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ . . . " የምትል ናት:: 📖ማቴ 1፥1 ✍️ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና፤ እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ" ሲል ተናግሯል:: 📖ራዕ 22፥16 ❖ ነቢየ ጽድቅ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ40 ዓመታት መርቶ አረጀ፤ 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና፤ በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ አሥራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና። 📖ዜና 21፥16 ❖ ሰውነቱ ደከመ፤ በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ70 ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት ዐርፏል፤ በራዕየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ 99ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል፤ ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል:: ❖ በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው፤ በነገረ ማርያም ትምህርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው፤ እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ፤ ክብሩ ታላቅ ነውና:: ✍️በእውነት . . . በእውነት . . . በእውነት . . . ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን

❖ ከዚህ በኋላም ኖኅ በአምላክ ትእዛዝ ደብረ አራራት እስከሚአደርሰው ከእርሱ ጋራ የአባታችን የአዳምን ሥጋ በመርከብ ወሰደው፤ ከዚያም ሴምና መልከ ጸዴቅ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራቸው ይዘውት ሔዱ ከቀራንዮ ቦታ ደርሰው በዚያ ቀበሩት መልከ ጼዴቅም በዕጣንና በቁርባን ሲያገለግል ኖረ። ❖ የእግዚአብሔርም ልጅ መጥቶ ከድንግል ልጁ በተወለደ ጊዜ መድኃኒት በሆነች ሞቱ አድኖ ወደ ቀደመው ርስቱ መለሰው እርሱ ለከበሩ ደጋጎች ነቢያት ለተጋዳዮችም ሰማዕታትና ጻድቃን አባት ነውና ስለ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ዓለም መጥቶ ሰው ሁኗልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባታችን የአዳም የእናታችን የሔዋን የቀደሙ የሁሉም አባቶች በረከት በላያችን ለዘላለሙ ይደር አሜን። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ጻዲቁ ኖኅ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ እርሱም ከአባታችን አዳም ጀምሮ 10ኛ ትውልድ ነው፤ ከታናሽነቱ ጀምሮ ኃጢአት እንደሚበዛና ደጋጎች እንደሚያንሱ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደሚደመሰስ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያይ ሆነ፤ ስለዚህም ፊቱ የተቋጠረ ሆኖ ፈጽሞ ያለቅስ ነበር፡፡ ❖ ጻድቁ ኖኅ ኖኅም የአቡዚር ልጅ የሆነች ሐይከል የምትባል ሴት አግብቶ ወደ እርሷ ሦስት ጊዜ ቢገባ ሦስት ልጆችን ሴም ካም ያፌትን ወለዳቸው፡፡ ❖ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከደብር ቅዱስ ዕንጨት ቆርጦ መርከብን እንዲያሠራ ካዘዘው በኋላ አሠራሯን በዝርዝርና በጥልቀት አስረዳው፤ የቃየል ልጆችም ኖኅን መርከብ ሲሠራ አይተው ዘበቱበት፤ የአዳምንም ሥጋ ወስዶ በውስጡ አኖረ፤ ሴም ወርቁን፣ ካም ከርቤውን፣ ያፌት ዕጣኑን ወስደው ወደ መርከብ አስገቡ፡፡ ❖ ኖኅም ከልጆቹና 500 ዓመት ድንግልናውን ጠብቆ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግል ኖረ፤ ከዚህም በኋላ ሚስት እንዲያገባ እግዚአብሔር አዘዘው፤ ሥጋ የለበሰ ሁሉ እንደሚደመሰስ ከእርሱ ዘር በቀር የሚተርፍ እንደሌለ ነገረው፡፡ ❖ ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ የምድርም ምንጮች ሁሉ ተነድለው ራጃጅም ተራራዎችም እስኪሸፈኑ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዘነመ፤ ውኃውም በላያቸው 15 ክንድ ከፍ አለና ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሞተ፡፡ ❖ ከ150 ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አስቦ ነፋስን በምድር ላይ አመጣና ውኃውን አጎደለ፤ ምንጮች ተደፍነው የሰማይ መስኮት ተዘጋ፤ መርከቢቱም በ7ኛው በ12ው ቀን አራራት ተራራ ላይ አረፈች፡፡ ❖ ከጊዜም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን ከነቤተሰቡ አንድ ላይ ከመርከቡ እንዲወርዱ አዘዘው፤ ኖኅም መሠዊያን ሠርቶ ንጹሕ ከሆኑት ሁሉ ወስዶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መልካም መዓዛን አሸተተ፡፡ ❖ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳያጠፋ ቃልኪዳን ገባለት፤ ምድር ፀንታ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ዘር መከር፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ መዓልትና ሌሊት እንደማይቋረጥ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ❖ እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ግዟት አላቸው፤ ኖኅም ምድርን ያርሳት ይቆፍርራትም ጀመር፤ ወይንም ተክሎ ከእርሶ ፍሬውን አድርሶ ወይን ጠጥቶ በሰከረና ራሱን በሳተ ጊዜ የከነዓን አባት ካም የኖኅን ራቁትነት አይቶ ሳቀ፣ ሄዶም ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው፤ ያፌትና ሴምም ልብስ ወስደው የአባታቸውን ርቃን ሸፈኑ፡፡ ❖ ኖኅም ከስካሩ በነቃ ጊዜ ሁሉም ያደረጉትን ዐወቀ፤ ‹ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም ተገዥ አገልጋይ ይሁን› ብሎ ከረገመው በኋላ ✍️‹‹የሴም ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔርም የያፌትን አገር ያስፋ በሴም ቤትም ይደር›› ብሎ መረቃቸው፡፡ ❖ አባታችን ኖኅ ‹‹እግዚአብሔር በሴም ቤት ይደር›› ማለቱ የጌታችንን ሰው መሆን በትንቢት መናገሩ ነው፤ እርሱም ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ኖረ፤ በአጠቃይ ዕድሜው 950 ዓመት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡ የአባታችን የቅዱስ አባ ኖኅ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል ✍️"እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትም" 📖መዝ 131፥11) ❖ አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም፤ ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ✍️ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ ፈቃዴን የሚፈጽም ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን:: 📖መዝ 88፥20 ❖ እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ ምንስ ይደንቅ ለዚህ አንክሮ ይገባል፤ ጌታ ይቀጥልና ደግሞ 📖መዝ 88፥35 ❖ አቤት አባታችን ዳዊት ክብር የክብር ክብር ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል እንላለን:: 📌 ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት 1. ሃብተ ትንቢት 2. ሃብተ መንግስት 5. ሃብተ ፈውስ 7. ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ:: 📌 በ7ቱ ስሞቹም 2.የዋህ 3.ንጹሕ 4.ብእሴ እግዚአብሔር 6.መዘምር እና 7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል:: ✍️"እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ 👉በኃጢአት ተጸነስኩ" ይላል 📖መዝ 50፥5 ❖ አበው እንደ ነገሩን የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ነው፤ ሚስቱን ሰሊብን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዐይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር:: ❖ አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ግን ያንን ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል፤ በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና እንዲህ ብሏል፤ ቅዱስ ዳዊት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር፤ ሕጸን ሳለ በእረኝነት በጐቹን አያስነካም ነበር፤ አንበሳውን በጡጫ ድቡን በእርግጫ ነብሩን በሩጫ የያዙትን ያስጥላቸው ነበር፤ በጥቂቱ በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእሥራኤል እረኛ ሊሆን ተመርጧል። ❖ በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ 7ቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም፤ በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ፤ ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ፤ በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ፤ በአምላክ ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ፤ ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሱባቸው ጊዜም ጐልያድ የሚሉት የጌት ሰው እሥራኤልን ሲያስጨንቅ ለ40 ቀናት ቆይቶ ነበር:: ❖ ለአምላኩ ስምና ክብር የሚቀና ቅዱስ ዳዊት ግን በድፍረት ገጥሞ በፈጣሪው ኃይል በጠጠር ጥሎታል፤ ከእሥራኤልም ሽሙጥን አርቁዋል፤ ግን ቅዱሱ ብላቴና ጐልያድ ደግሞ 6 ክንድ 3 ሜትር የሚረዝም ሰው ነበር:: ❖ ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ዙፋን አልጠበቀውም፤ ጠላታቸውን ጥሎ ስላዳናቸው ፈንታ ሳዖልን በገና እየደረደረ ስለ ፈወሰው ፈንታም ሊገደል ተፈለገ፤ ፈጣሪው ከእርሱ ጋር ባይሆንም ይገድሉት ነበር፤ እርሱ ግን ለ18 ዓመታት በትእግስት ተሰደደ፤ ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ጠላቱን ሳዖልን አሳቻ ሥፍራ ላይ አግኝቶ በምሕረት ተወው:: ✍️በዚህ የዋሕነቱም በብሉይ ሆኖ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" የምትለውን ሕግ ፈጸማት:: 📖ማቴ 7፥45 📖መዝ 16፥4 ❖ ቅዱስ ዳዊት የስደት ዘመኑ ሲፈጸም ሳዖል ሞተ፤ ምን ጠላቱ ቢሆን 'የሳዖል ገዳይ ነኝ' ያለውን ተበቀለ፤ ስለ ጠላቱም አለቀሰ፤ 30 ዓመት ሲሆነው ነግሦ ለ7 ዓመታት በኬብሮን ለ33 ዓመታት በኢየሩሳሌም (ጽዮን) ሕዝበ እግዚአብሔርን ጠብቁዋል፤ በዘመኑም ጠላቶቹን ሁሉ ድል አድርጉዋል፤ በልጁ አቤሴሎም እጅ መሰደድን በሳሚ ወልደ ጌራ መሰደብንም ታግሷል::

❖ በዚችም ቀን የአባታችን አዳምን የእናታችን ሔዋንን መታሰቢያቸውን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ፤ ይህን አባታችን አዳምን ሳይፈጥረው አስቀድሞ በሰማይና በምድር ያለውን አዘጋጀለት፤ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረ መላእክትንም ስለርሱ ፈጠረ። ❖ ከዚህም በኋላ በኤዶም ተክልን አዘጋጀለት እርሱም የፍሬው ጣዕም በየራሱ ልዩ ነው የሚአሻውን ሁሉ አከናውኖ እነሆ ከምድር መካከል ይኸውም ጎልጎታ ነው አፈር አንሥቶ በሦስት ሰዓት እርሱን ፈጠረው፤ ከአራት በሕርያት ይኸውም ውኃ እሳት ነፋስና መሬት ነው በአርአያውና በምሳሌው ራሱን አስመስሎ ፈጠረው በፊቱም እፍ ብሎ የሕይወት መንፈስን አሳድሮ የሚናገርና የሚያስተውል የሚያውቅ አደረገው የብርሃንንም ልብስ አልብሶ ንጉሥ ነብይ ካህን አስተዳደሪ አድርጎ በፈጠረው ሁሉ ላይ ሾመው። ❖ ከዚህም በኋላ አይቶ ስማቸውን ይሰይም ዘንድ አራዊትን እንስሳትን የሰማይ ወፎችን ሁሉ ወደርሱ አመጣ። አዳምም መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረው ለሁሉም ስም አወጣላቸው። ❖ ከዚህም በኋላ በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣበትና አንቀላፋ ከጐኑም አንድ ዐጥንትን ነሣ ቦታዋንም በሥጋ መላው እግዚአብሔርም ሴት አድርጎ አሳምሮ ሠራት በአዳምም በፊቱ አኖራት፤ አዳምም ነቅቶ ይቺ ከዐጥንቴ ዐጥንት ከሥጋዬ ሥጋ ናት ሚስት ትሁነኝ ብሎ ተናገረ ስሟንም ሔዋን አላት። ❖ አዳምም በጎልጎታ ቁሞ የፈጣሪውን ቃል እየሰማ ሳለ እነሆ ከሚስቱ ከሔዋን ጋራ በፊት በኋላ ሁነው በየነገዳቸው አዳምን ስለ አከበረው መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደመና ተሸክማ ወሰደቻቸው በኤዶም ገነትም አኖራቸው፤ እግዚአብሔርም አዳምንና ሔዋንን በገነት ካለው ተክል ሁሉ ብሉ ግን ከገነት መካከል ዕፀ በለስን አትቡሉ ከእርሱ በበላችው ቀን ሞትን ትሞታላችሁ አላቸው። ❖ አዳምም ገነትን እያረሰና እየቆፈረ ከፍሬዋም እየተመገበ ከመላእክት ጋራ ሲያመሰግን ኖረ፤ የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ግን ከማዕርጉ በወደቀ ጊዜ በአዳም ጌትነትና ክብር ቀንቶ በእባብ አድሮ ወደሔዋን ሔደ፤ ያንን ዕፀ በለስንም ትበላ ዘንድ አታለላት አምላክ የመሆንንም ተስፋ አሳደረባትና አሳታት፤ ያንን ዕፀ በለስንም በአየችው ጊዜ አማራት በልታ ለባልዋም አበላችው ያን ጊዜ የብርሃን ልብሳቸው ከላያቸው ተገፈፈ፤ እነርሱም ራቁታቸውን እንደሆኑ አውቀው በበለስ ቅጠል ኀፍረተ ሥጋቸውን ሸፈኑ፤ እግዚአብሔርም ስሕተታቸውን አውቆ አስቀድሞ እባብን ረገመ በእርሷና በሴቲቱ ዘር መካከል ጠላትነትን አጸና። ❖ በሔዋንም ላይ በፃር በገዐር ውለጂ ወልደሽም መመለሻሽ ወደባልሽ ይሁን እርሱም ይግዛሽ ብሎ ፈረደባት፤ አዳምንም እንዲህ አለው ስለ አንተ ምድር የተረገመች ትሁን ጥረህ ግረህ እንጀራህን ብላ አንተ አፈር ነህና ወደ አፈርነት ትመለሳለህ፤ እግዚአብሔርም የቁርበትን ልብስ አዘጋጅቶ አለበሳቸው ሰባት ዓመት በተድላ ከኖሩ በኋላ በምሽት ጊዜ ከኤዶም ገነት ወጡ። ❖ አዳምም በማለዳ ፀሐይ ሲወጣ ነጭ ዕጣን ቀንዓት ሰሊሖት የሚባል ሽቱ ከሎሚ ውኃ ጋር አጠነ፤ አዳምም በኤዶም ገነት እንደተማረ ምድሪቱን እያረሰና እየቆፈረ ኤልዳ በሚባል ምድር ኖረ፤ አዳምም ሔዋንን በግብር አወቃት ቃየልን ከእኅቱ ጋር ወለደችለት ከእርሱም በኋላ አቤልን ከእኅቱ ጋራ ወለደችው ቃየልና አቤልም አድገው አካለ መጠን አደረሱ፤ ወደ እግዚአብሔርም መሥዋዕት በአቀረቡ ጊዜ ጌታ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ ስለዚህም ቃየል ተቆጣ በአቤልም ቀንቶ ገደለው፤ አዳምም በልጁ በአቤል ሞት እያዘነና እያለቀሰ አራት የዘመን ሱባዔ ኖረ። ❖ ከዚህም በኋላ ሴት ተወለደለት በእርሱም መታሰቢያው ጸና ከእርሱም በኋላ ብዙዎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ እግዚአብሔርም ንስሓውንና ልቅሶውን አይቶ የድኅነት ተስፋ ሰጠው፤ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ወደ ዓለም መጥቼ ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ ሕፃንም ሆኜ በሜዳህ ውስጥ እድሀለሁ በመስቀሌና በሞቴም አድንሃለሁ አለው። ❖ አዳምም ከገነት በወጣ ጊዜ የወሰደውን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ለልጁ ለሴት ሰጠው እንዲህም አለው በኋላ ዘመን የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ ከድንግል ይወለዳል ያን ጊዜ የጥበቡ ሰዎች ይህን ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን እጅ መንሻውን ያመጡለታል እርሱም መዝግቦ በዕቃ ቤት አኖረው፤ ወደኖኅም እስኪደርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ኖረ ከኖኅም የምሥራቅ ሰዎች ወደ ሆኑ የጥበብ ሰዎች እስኪ ደርስ ተላለፈ። ❖ እነርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምጥተው ለእግዚአብሔር ልጅ እጅ መንሻ አድረገው አቀረቡለት እመቤታችንም ከእጃቸው ተቀበላ በኋላ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሰጠችው ቅዱስ ጴጥሮስም ለቀሌምንጦስ ሰጠው፤ አዳምም የሚያርፍበትን ሰዓት በአወቀ ጊዜ ልጁ ሴትን ጠርቶ ከመሞቴ በፊት ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ወደእኔ አቅርባቸው አለው፤ የአባቱን ቃል ሰምቶ ዕንባው በጉንጩ ላይ እየፈሰሰ ወጣ ወደ አዳምም አቀረባቸው። ❖ አዳምም በአያቸው ጊዜ ከእሳቸው ስለ መለየቱ አለቀሰ፤ እነርሱም ሲያለቅስ በአዩት ጊዜ ሁሉም በአንድነት ወደ እግዚአብሔር በግምባራቸው ተደፍተው አለቀሱ ምድር እንዴት ትሸፈንሃለች ከዐይኖቻችንስ እንዴት ትሠወራለህ አሉ። ❖ ከዚህም በኋላ አባታችን አዳም ሁሉን ልጆቹን ባረካቸው መረቃቸው፤ ልጁን ሴትን እንዲህ አለው ይቺ ዓለም ድካምና ችግርን የተመላች ናትና በእግዚአብሔር እየታመንክ ዕውነትን ንጽሕናን ጠብቅ ሰይጣን ወደ ሚያሳይህ ምትሐቱና ወደ ነገሩ አታዘንብል፤ በሞትኩ ጊዜም ሥጋዬን ወስዳችሁ ሰሊክ ሚዓ በሚባል ሽቱ ገንዛችሁ በግምጃ ቤት አኑሩኝ የጥፋት ውኃ ይመጣ ዘንድ አለውና ፍጥረት ሁሉ ይሰጥማል ከስምንት ነፍስ በቀር የሚቀር የለም፤ ልጄ ሆይ ለወገኖችህ ቋሚ ሁነህ እግዚአብሔርን በመፍራት ጠብቃቸው የዕውነት መንገድንም ምራቸው ለስይጣንም እንዳይ ታዘዙና እንዳያጠፋቸው አደራ አስጠብቃቸው፤ ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ከቃየል ልጆች ለያቸው አንድ ይሆኑ ዘንድ ከቶ አትተዋቸው ወደ ሥራቸውና ወደ ጨዋታቸውም አይቅረቡ። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ ልጁ ወደ ሴትና ወደ ሔዋን መለስ ብሎ ያንን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከእርሳቸው ጋራ አኑረው ይጠብቁት ዘንድ አደራ አላቸው፤ እንዲህም አላቸው የጥፋት ውኃ በመጣ ጊዜ ሥጋዬን ከወርቁ ከከርቤውና ከዕጣኑ ጋራ ወደ መርከብ ያስገቡ ከዚያም በኋላ በምድር መካከል ያኑሩት። ❖ ከብዙ ዘመናት በኋላም ያቺን አገር ይወርዋታል እሊህንም ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከብዙ ምርኮ ጋር ይወስዱትና አካላዊ ቃል መጥቶ ሰው እስከሚሆን ድረስ በዚያ ይጠበቃል፤ ነገሥታትም ይዘው መጥተው ይገብሩለታል ወርቁ ስለ መንግሥቱ ዕጣኑ ስለ ክህነቱ ከርቤውም ማሕየዊት ስለሆነች ሞቱ ነው። ❖ ለአባታችን አዳምም ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሲሆን መላልኤልም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ሲሆነው በተፈጠረባት ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት አረፈ ያረፈባትም ሰዓት ከገነት የወጣባት ናት በዚያን ጊዜም የመላእክት ሠራዊት ከልጆቹ ጋራ ተሰበሰቡ፤ መልካም አገናነዝም ገነዙት በብዙ ሽቱዎችም መዓዛውን አጣፈጡ። ❖ ይህም በገነትና በደብር ቅዱስ ያለ ነው ሥጋውንም በፀሐይ መውጫ በኲል በዋሻ ውስጥ አኖሩ የሚያበራ መብራትም አኖሩ ከእርሱም ጋራ ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን አስቀመጡ ዋሻውንም በአዳምና በሔዋን በሴት ቁልፍ ቆልፈው አተሙት፤ የጥፋት ውኃም እስከ መጣ ድረስ ሴትና ልጆቹ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግሉ ኖሩ።

ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፮ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ስድስት በዚች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብጻዊት ማርያም አረፈች። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ግብጻዊት ማርያም ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው፤ ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆናት ጊዜ የመልካም ሥራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ሥጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና ። ❖ በዚህም በረከሰ ሥራ ውስጥ ኖረች በየዕለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር፤ ሰውን የሚወድ የእግዚአብሔርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት። ❖ ከእሳቸውም ጋራ ትሔድ ዘንድ ልቧ ተነሣሣ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች፤ ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ሥራ አልተወችም፤ የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት፤ እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም። ❖ ከዚህም በኋላ ስለ ረከሰ ሥራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር ዐይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አየች፤ በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ሥራዬን የፈጸምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት፤ እንዲህም ስትል ወደ ጌታችንመቃብር ቤተክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበዓሉን ሥራ ፈጸመች። ❖ ከዚህም በኋላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ሥዕል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ጸሎትን ጸለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ ዕረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ፤ ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት። ❖ ከዚያም በኋላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ጽኑዕ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት ዓመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር፤ እርሷ ግን በተጋድሎ ጸናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች፤ ሁለት ሁለት ቀን ሦስት ሦስት ቀን ጹማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሣር ተመገበች። ❖ በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ ሰባት ዓመት ሲፈጸምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ጾምን ሊፈጽም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ፤ በሱ ደብር ላሉ መነኰሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየዓመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ጾም እስከ ምትፈጸም በጾምና በጸሎት ተጸምደው በገድል ይቆያሉ ። ❖ ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚጽናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው፤ በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሐት መሰለችው በጸለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት፤ ወደርሷም ሔደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኋላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ❖ ከዚህም በኋላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው፤ በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይጸልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ። ❖ ከዚህም በኋላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው፤ እርሷም በሚመጣው ዓመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት፤ ዓመትም በሆነ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን በጽዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሔድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ጸለዩ ከዚህም በኋላ ሥጋውንና ደሙን አቀበላት። ❖ በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጅዋ ጥቂት ወሰደች፤ ደግሞም በሁለተኛው ዓመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው፤ ሁለተኛ ዓመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብጻዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ጽሑፍ አገኘ፤ ከጽሑፉ ቃልም የተነሣ አደነቀ። ❖ ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ጸሎት አድርጎ ቀበራት፤ ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኰሳቱ የዚችን የከበረች ግብጻዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልዑል እግዚአብሔርንም አመስገኑት፤ መላው ዕድሜዋም ሰማንያ አምስት ሁኗታል። እግዚአብሔርም በእርሷ ጸሎት ለዘላለሙ ይማረን አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለማርያም ህየንተ ረከባ ምንዳቤ። አንበሳ ዘኮነ በድነ ሥጋሃ ዐቃቤ። ቀበራ ዘሲማስ በአጽፋ እሰመ አልባቲ ግልባቢ። ረኪቦ መልዕልተ ርእሳ መጽሐፈ ነባቤ። ለማትያም ግብጸዊት ቅብራ ዘይቤ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጐኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመንኩ አለ። ❖ ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት፤ በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶቹም ጸሎት በታጋዮች ጻድቃንም በድል አድራጊዎች ሰማዕታትም ጸሎት ይልቁንም በእመቤታችን ማርያም በአማልጅነቷ ይምረን ዘንድ ወደርሱ እንለምን ለዘላለሙ አሜን። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱሳን አዳምና ሔዋን (የዕረፍታቸው መታሠቢያ) ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ከዚህም በኋላ አንጾኪያ ከተማ አደረሱትና ወደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አቀረቡት እርሱም በእሳት በአፈሉት በወይን በሙጫ ድፍድፍ በማቃጠል አሠቃየው ከዚያም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አዳነው። ❖ ዳግመኛም በአንገቱ ከባድ ደንጊያ በሰንሰለት አሥረው ወደ ባሕርም አንከባለው ግማሽ ሥጋውን እንዲአሠጥሙ ግማሹን ግን እንዳያሠጥሙ አዘዘ እነርሱም በባሕሩ ዳር ታላቅ ምሰሶ ተከሉ በዚያም እንዳዘዛቸው አድርገው አሥረው ተውት በዚህ ሥቃይም ከቀኑ እስከ ሰባት ሰዓት ዋለ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ፈትቶ አወጣው እንደ ቀድሞውም ጤነኛ አደረገው ንጉሡም አይቶ አደነቀ ሰያፊውንም ፈጥኖ አንገቱን እንዲቆርጥ አዘዘው ያን ጊዜም አንገቱን ቆርጦ በባሕር ዳር ከምድር ላይ ጣለው ሥጋውንም አንሥቶ ከቁርበት በተሠራ ጋን ውስጥ ጨመረው ሥጋውም ከራሱ ጋራ ተገናኘና እንዳልተቆረጠ ሆነ ጋኑም በሃያ ቀን እስክንድርያ እስከሚደርስ ድረስ ሰው ሳይሸከመው ብቻውን የሚጓዝ ሆነ፤ የቦሀ ሀገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ መጡ ተሸክመውም በቦሀ አገር ከአለው ቤቱ ውስጥ አስገብተው ከወንድሙ ጴጥሮስ ጋራ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለብሶይ ዘምድረ ቦሀ ሀገሩ። እለ አውጽኡ በመጥባሕት አሥራወ እዴሁ ወእግሩ። ላዕሌሁ ዳግመ እንዘ ይትዔየሩ። መንፈቀ ሥጋሁ ውስተ ባሕር ወገሩ። ወመንፈቆሰ ኢይረድ ዲበ ዐምድ አሠሩ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ዕለት ደግሞ ቅዱስ ቢፋሞን ምስክር ሆነ፤ ይህ ቅዱስ ለዮሐንስ ዘሐራቅሊ የእናቱ ወንድም ልጅ ነበር ዮሐንስም ታሥሮ ሳለ ያገለግለው ነበር፤ ዮሐንስም ገድሉን በፈጸመ ጊዜ ሥጋውን ገነዘ በበድኑ ላይም እንዲህ ብሎ አለቀሰ ከእግዚአብሔር የተለየሁ ሁኜ ብቻዬን እንዴት ትተወኛለህ ከቅዱስ ዮሐንስ ሥጋም እንዲህ የሚል ቃል ወጣ ወዳጄ ቢፋሞን ከእኔ ጋራ መኖርን ከፈለግህ ፈጥነህ ወደ መኰንኑ ሒደህ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ታመን ነገም ወደ እኔ ትመጣለህ። ❖ ይህንንም ሰምቶ የዮሐንስን ሥጋውን ቀበረ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሔደ፤ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየታመነ የረከሱ ጣዖታቱን ሰደበ፤ መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጠ የምስክርነትንም አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። በዚችም ዕለት ደግሞ የመርቆሬዎስና የመቃርስ የይስሐቅና የዕብሎን የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፤ የአብላርዮስም የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው። እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን። በዚች ዕለት ደግሞ ቅዱስ መቃርስ ምስጋና ይግባውና በጌታችን ስም በባሕር ውስጥ በመስጠም አረፈ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለከ መቃርስ ኅሩይ። በእንተ ክርስቶስ ዘሞትከ በስጥመተ ማይ። እምእረድ አንሰ ቈላተ ብካይ። ነዓ ነዓ ዓቃቤ ሥራይ። እስመ እፈቅድ ለጥዕይ ብእሲ ድውይ። በዚችም ዕለት ሃይማኖቷ የጸና ምግባርዋም የቀና ክርስቶስ ያደረባት የመነኰሳዪት የቅድስት ማርታ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው በስደት ሳለችም አረፈችና በተራራ ውስጥ ተቀበረች በረከቷ ከእኛ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ አምስት በዚች ቀን ታማኝና ተጋዳይ ይሆነ ምሥራቃዊው አባት ያዕቆብ አረፈ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይህም ቅዱስ ከምእመን ዋልንጦስ ዘመን በኋላ የታላቁ ቈስጠንጢኖስ ልጅ በሆነ በታናሹ ቈስጠንጢኖስ ዘመንና በከሀዲው ሉልያኖስ ዘመን በምሥራቅ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም በገድል ተጠምዶ ኖረ፤ ዋልንጦስ ከተገደለ በኋላም በእርሱ ፈንታ ወንድሙ ነገሠ እርሱም አርዮሳዊ ነበር የጣዖት ቤቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሃይማኖታቸው የቀናውን የምእመናንን አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲዘጉ አርዮሳውያንን አዘዛቸው ወደ ከፋችና ወደ ተበላሸች ሃይማኖታቸው ምእመናን በግዳጅ እስቲገቡ ድረስ እንዲሁ አደረጉ። ❖ ይህም የንጉሡ ትእዛዝ በሚገዛው አገር ሁሉ ደረሰ፤ ይህ አባ ያዕቆብም ይህን በሰማ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ ያንጊዜም ተነሥቶ ወደ ቊስጥንጥንያ ሔደ በምዕራብ በኩል የተነሡበትን ጠላቶቹን ሒዶ ለመውጋት ሲወጣ ንጉሡን አገኘው። ❖ ይህ አባት ያዕቆብም በፊቱ ቆሞ ንጉሥ ሆይ በጠላቶችህ ላይ እግዚአብሔር ይረዳህ ዘንድ ምእመናን እንዲጸልዩልህ አብያተ ክርስቲያናቸውን ክፈትላቸው ብዬ እለምንሃለሁ ይህን ካላደረግህ ግን እግዚአብሔር ይጥልሃል ከጠላቶችህም ሸሽተህ በእሳት ቃጠሎ ትሞታለህ አለው። ❖ ንጉሡም ይዞ ለሚጠብቀው ወታደር በሰላምና በደኅንነት እስከምመለስ ጠብቀው ብሎ ሰጠው፤ ቅዱስ ያዕቆብም አንተ በደኅና ከተመለስክ በእኔ አንደበት እግዚአብሔር አልተናገረም ማለት ነዋ አለው፤ ያንጊዜም ቅዱሱን ይዘው ደብድበው አሠሩት ንጉሡም ከሠራዊቱ ጋራ ወደ ጦርነቱ ሔደ በረከሰች ጸሎታቸው አርዮሳውያን ምንም ቢራዱት ክብር ይግባውና ጌታችን በጠላቶቹ አንጻር ጣለው እነርሱም ጠላቶቹ እየተከተሉት ሸሽቶ ከአንዲት አአድ ውስጥ ገባ በዚያም በረከሰች ሃይማኖት ከሚያምኑ ወገኖቹ ጋራ በእሳት አቃጠሉት። ❖ የቀሩትም ሠራዊት ሁሉ ሽሽተው ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሱ ይህንንም መልካም ዜና ሃይማኖታቸው ለቀና ምእመናን ተናገሩ የዚህ ጻድቅ አባት ያዕቆብም ትንቢቱ ተፈጸመ ከእሥር ቤትም በክብር አስወጡትሠ ምእመናንም ከሀዲያንም በላዩ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ተረዱ ከአርዮሳውያንም ብዙዎቹ የአባቶቻችን ሐዋርያት ወደሆነች ቅን ሃይማኖት ተመለሱ በዚህ አባት እግር በታች ሰግደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ ታመኑ፤ ከዚህም በኋላ ይህ አባት ወደ ቦታው ተመለሰ አርፎ የሕይወትና የሰማዕትነት አክሊልን እስከ ተቀበለ ድረስ እንደ ቀድሞው በገድል ተጠምዶ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለያዕቆብ በብሔረ ምሥራቅ ዘአስተርአየ። ከዊኖ በንጽሕ ሶበ ኀበ እግዚእ ጸለየ። ላዕለ አርዮሳዊ ንጉሥ ከመ ተነበየ። እምገጸ ጾላእቱ ዘመንገለ ዐፀድ ጐየ። ምስለ እሊአሁ ኅቡረ በእሳት ውዕየ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ አባ ብሶይ (ኃያል ሰማዕት) ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ዕለት የተመረጠ ኃያል ተጋዳይ አባ ብሶይ አረፈ፤ የዚህ ቅዱስ አባቶቹ ክብር ይግባውና ጌታ ክርስቶስን የሚያመልኩና ትእዛዙን የሚጠብቁ ክርስቲያን ነበሩ የአባቱም ስም ታግኅስጦስ ነው እርሱም ከአንጾኪያ የቃው ገዥ ነበር የእናቱም ስም ክሪስ ይባላል። ❖ እነርሱም ልጅ ሳይኖራቸው ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖሩ ስለዚህም እጅግ እያዘኑ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ይለምኑ ነበር፤ ከሌሊቶችም በአንዲቱ ለታግኀስጦስ ብርሃን የለበሰ ሰው ተገልጦለት እንዲህ አለው የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቷል ሚስትህም ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች ስሙንም ብሶይ ትለዋለች እርሱም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ዕቃ ይሆናል እርሱም ደግሞ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ ምስክር ይሆናልና ብዙ ሥቃይና መከራም ተቀብሎ የሰማዕትነት አክሊልን ይቀዳጃል። ❖ ከእንቅልፉ ነቅቶ ራእይ እንዳየ ለሚስቱ ነገራት ከጥቂት ቀኖች በኋላም ፀንሳ ይህን ቅዱስ ሚያዝያ አንድ ቀን ወለደችው ዕውቀትን ጥበብንና ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት፤ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ አክሚም ዮሴፍ ወደሚባል አንድ አረጋዊ መምህር ላኩት በዚያም እየተማረ ከወንድሙ ጴጥሮስ ጋራ በጸሎትና በጾም ተጠምዶ ድንቆች ተአምራትን እያደረገ ኖረ። ❖ ከዚህ በኋላም ሃያ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ የስዒድ መኰንን ወዳለበት ወደ ቃው ከተማ መጣ እርሱም ክርስቲያኖችን እያሳደደ ከእርሳቸው ይገድል ነበር፤ ያን ጊዜም ክፉዎች ሰዎች ወደ መኰንኑ መጥተው ለቃልህ የማይታዘዙና ለአማልክት መስገድንም እምቢ የሚሉ ሁለት ዲያቆናት አሉ ብለው እኒህ የከበሩ አባ ብሶይንና አባ ጴጥሮስን ከሰሱአቸው። ❖ በዚያን ጊዜም እንዲአቀርቧቸው አዘዘና አቅርበው በፊቱ አቆሙአቸው ስለ ሥራቸውም መረመራቸው ክርስቲያን እንደ ሆኑም ከቃላቸው ሰምቶ እንዲአሥሩአቸው አዘዘ፤ ከሦስት ወር በኋላም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦላቸው እኔ የምሥራች የምናገር ገብርኤል ረዳችሁና እነግራችሁ ዘንድ ወደ እናንተ እግዚአብሔር ላከኝ ስም አጠራራችሁና መታሰቢያችሁ ለዘላለሙ ይኖር ዘንድ አለውና አላቸው፤ አንተም ወዳጄ ብሶይ ታላቅ ተጋድሎ አንተን ይጠብቅሃል ወደ እስክንድርያ ከተማ ሊሰዱህ አላቸው ከዚያም ወደ አንጾኪያ ወስደውህ በዚያ የምስክርነትህ ገድል ይፈጸማል። ❖ ከዚህ በኋላም መኰንኑ ከወህኒ ቤት አውጥቶ ለጣዖት እንዲሰግድ አስገደደው እምቢ ባለውም ጊዜ ከባላ ላይ አውጥተው በግንድ ውስጥ እጅግ እንዲጨምቁት ወታደሮችን አዘዘ። በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወረደ ግንዱን ሰብሮ ቅዱስ ብሶይን በመዳሠሥ አዳነው። ❖ ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ጨመሩት በዚያም ብዙ በሽተኞችን ፈወሳቸው፤ ዳግመኛም እንዲህ አዘዘ ከወህኒ ቤት አውጥተው በመርከብ ሆድ ውስጥ አስገብተው አንገቱን በብረት ሰንሰለት እጆቹንና እግሮቹንም እንዲሁ በብረት ማሠሪያ እንዲአሥሩት እንጀራና ውኃ እንዳይሰጡት አዘዘ እንዲዚህም ሆኖ ዐሥር ቀን ኖረ። ❖ ከዚህም በኋላ አውጥቶ በፊቱ አቁሞ ለአማልክቶቼ ስገድ አለው እምቢ ባለውም ጊዜ ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ከባላ ግንድ ላይ አውጥተው አጥብቀው እንዲጨምቁት ሁለተኛ አዘዘ፤ እንዲሁም በእርሱ ላይ አድርገው በውህኒ ቤት አሠሩት፤የእግዚአብሔር መልአክ ገብርኤልም ደግሞ ተገለጠለትና አይዞህ መልካም ገድልህን እስከምትፈጽም እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አትፍራ አለው። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወደ ቁልቁልያኖስ መኰንን ሰደዱት እርሱም ስለ ሥራው ሁሉ መረመረውና ሕዋሳቱ ተቆራርጦ እስቲወድቅ ድረስ ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ፤ ሁለተኛም ዘይትን አፍልተው በጆሮው በአፉና በደረቱ ላይ እንዲአፈስሱ ጐኖቹንም በእሳት መብራት እንዲአቃጥሉ አዘዘ ደግሞም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በዐይኖቹ ውስጥ አደረጓቸው፤ ሁለተኛም የእጆቹንና የእግሮቹን ሥሮች ሕዋሳቱንም ሁሉ እንዲነቅሉ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሕዋሳቱን ሁሉ ፈወሰው።

ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ ✝️💚💛❤️✝️💚💛❤️✝️💚💛❤️✝️💚💛❤️✝️ ✍️"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ቀን የአርቃድዮስ የእኅቱ የዲሙናስያ የግብጻውያኑ የአሞኒና የሚናስ የንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም የገድላቸው ፍጻሜ ሆነ፤ እሊህን ቅዱሳን በእሳት ምድጃ ውስጥ ከአባ ብሶይ ጋራ በጨመሩዋቸው ጊዜ የመላእክት አለቃ ገብርኤል መጥቶ ከነበልባሉ መካከል አወጣቸው ። ❖ ወደ ንጉሡም ደርሰው ረገሙት እንዲህም አሉት የምስክርነት ሞት ፍጻሜያችንን የማትጽፍ ከዕለት ወደ ዕለት ለምን ትከፋለህ። ንጉሡም ሰምቶ ተቆጣ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡና ሥጋቸውን በእሳት እንዲያቃጥሉ አዘዘ እንደዚህም የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባው እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለአርቃድዮስ ወዲሙናስያ እኅቱ። አሞኒ ወሚናስ ለእግዚአብሔር ሰማዕቱ። አመ ወደዮሙ ንጉሥ ውስተ ግበ እሳት ለ፬ቱ። ያድኅኖሙ መጽአ እምሰማይ አድኀኔ ደቂቅ ፫ቱ። መልአከ ፍሥሐ ገብርኤል ዘፍጡን ሩጸቱ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ዕለት በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ተጋዳይ የሆነች ቅድስት ሶፍያ አንገቷን በመቆረጥ በሰማዕትነት አረፈች፤ የዚች ቅድስት ወላጆቿ ክርስቲያን ነበሩ በወለዱዋት ጊዜም በመልካም አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የአባቶቻችን ሐዋርያትንም ሕግና ሥርዓት ሁሉ እያስተማሩ አሳደጓት። ❖ ከዚህ በኋላም በአደገች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ መስፍን ልጅ ሊአጋቧት ፈለጉ ቅድስቲቱም ይህን በመንፈስ ቅዱስ ዐውቃ ከተቀመጠችበት ተነሥታ ፊቷን ወደ ምሥራቅ መልሳ መቶ ስግደትን ሰገደች ቆማም ረጅም ጸሎትን ጸለየች በጸሎቷም ውስጥ እንዲህ አለች የክብር ባለቤት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህን ለእኔ ለባርያህ ለሶፍያ ምራኝ ወደ ጥፋት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ የሚጠፋውንም ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው ወላጆቼ በሚመክሩብኝም በረከሰ በሥጋ ፍትወት ውስጥ የኃጢአት ባሪያ እንድሆን አቤቱ አትተወኝ የከበደ የዓለማዊ ፍላጎት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትክሻዬን ዘንበል አድርገው እንጂ። ❖ ጸሎቷንም ከፈጸመች በኋላ በዐልጋዋ ላይ ተቀመጠች ጥቂትም ቆይታ እንዲህ የሚል ሃሳብ መጣባት ተነሥቼ በሥውር ልውጣ ወደ ሩቅም ሒጄ ከበረሀ ውስጥ ገብቼ ለልዑል አምላክ ላገልግል። ❖ ከዚህም በኋላ ወላጆቿ የሰጧትን የምታገለግላትን ብላቴናዋን ጠራች ወይን አምጥታ እንድታጠጣትም አዘዘቻት በአመጣችላትም ጊዜ እርሷ ጥቂት ቀምሳ ያመጣችው ወይን እስቲያልቅ ትጠጣ ዘንድ ብላቴናዋን አዘዘቻት፤ ከስካርም የተነሣ ልቧ በተሰለበ ጊዜ ልብስሽን አምጪ የእኔንም ልብስ ወሰጂ አለቻትና ሰጠቻት የወይኑ ስካር አእምሮዋን ነሥቷታልና ተኚ አለቻት በላይዋም እንቅልፍ በከበዳት ጊዜ ማንም ሳያያት ቅድስት ሶፍያ በሥውር ወጣች ከወላጆቿ ማደሪያ የራቀ ነበርና። ❖ ርቃ በሔደችም ጊዜ በተራራና በዋሻዎች ውስጥ ሊሠወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሚሸሹ ሰዎችን አገኘች እናንተ ከወዴት ናችሁ ብላ ጠየቀቻቸው የየአንዳንዳቸውን አገራቸውን ነገሩዋት ደግማ ወዴት ትሔዳላችሁ አለቻቸው እነርሱም ስለሃይማኖት ከዲዮቅልጥያኖስ የሆነውን ሁሉ ነገሩዋት፤ ይቺ መንገድ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ታደርሰኛለችን አለቻቸው አዎን ታደርስሻለች አሏት፤ ❖ ከዚያም ጥቂት ተጉዛ ቁማ ረጅም ጸሎትን ጸለየች ወደ ዲዮቅልጥያኖስም ደርሳ ክብር ይግባውና ክርስቶስን የምታመልክ ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች፤ ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ስም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተመላ ወደርሱም እንዲአቀርቧት አዘዘ በቀረበችም ጊዜ ለአጵሎን ስገጂ አላት የሰው እጅ ለሠራው ለረከሱ የአጋንንትም ማደሪያ ለሆነው እንዴት እሰግዳለሁ አለችው። ❖ ይህንንም ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከብረት በተሠራ ጅራፍም እንዲገርፏት አዘዘ ሁለተኛም በአንገቷ ከባድ ደንጊያ አሥረው ሥጋዋ ተቆራርጦ እስቲወድቅ ድረስ በከተማው ጥጋጥግ እንዲጎትቷት አዘዘ ይህንንም አድርገው ወደ ወህኒ ቤት አስገቧት። ❖ በማግሥቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ በመጣችም ጊዜ በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጵሎን ሠዊ አላት እርሷም ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ሕይወት ነው አለችው እርሱም ከገደልኩሽ በኋላ ድነሽ ትነሺአለሽን አላት አንተ ሰነፍ የእኔን ተወውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ አለችው። ❖ ይህንንም በሰማ ጊዜ ዐጥንቶቿ ሁሉም እስቲሰበሩ በብረት በትሮች እንዲደበድቧት አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉባትሠ ዳግመኛም በብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቿ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ ቀኑ በመሸ ጊዜ ወደወህኒ ቤት እንዲአስገቧት አዘዘ በዚያችም ሌሊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሠሥ አዳናት። ❖ በማግሥቱም ያመጡአት ዘንድ አዘዘ እርሷም ምንም ሕማም እንዳላገኛት ሁና በእግርዋ መጣች ከመታጠቢያ ቤት ታጥባና ተቀብታ የወጣች ትመስል ነበር ንጉሡም ደኅንነቷን አይቶ አደነቀ የዚችን ክርስቲያን ሴት የሥራይዋን ጽናት እዩ ትላንት በእሳት አሠቃይተናት ነበር ዛሬ ድናለች አለ፤ እርሷም ሥራይንስ አላውቅም ነገር ግን ፈጣሪዬ ሥራይን የሚሽር ነው አለችው። ❖ ከዚህም በኋላ እሽ ያሰኛት ዘንድ ሊሸነግላት ጀመረ እምቢ በአለችውም ጊዜ ራስዋን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፤ ሊቆርጧትም ይዘዋት ሲሔዱ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጸላት ብዙ ቃል ኪዳኖችንም ሰጣት በማይታበል ቃሉም መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ በስምሽም የሚመጸውተውን የገድልሽንም መጽሐፍ የሚጽፈውን ሁሉ እቀበለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ አለ፤ ከዚህ በኋላም አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ በጌታችንም ዘንድ የድል አክሊልን ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። አርኬ ✍️አቄርብ ለከ አሞኒ ሰላመ። ወለሶፍያ ምስሌከ ዘተሳተፈት ሕማመ። በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥመሩ ፍጹመ። ከዊነክሙ ትሐፅኑ ኪያየ ደክታመ። ለሊከ አበ ወይእቲ እመ። በዚችም ዕለት የአባ አሞንና የሚናስ መታሰቢያቸው ሆነ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 ሰኔ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት 2. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) 3. ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት 4.ቅድስት ማርያ ሰማዕት 5. ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት) 6. ቅዱስ አሞን ሰማዕት 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊ) 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ ✍️" እንግዲሕ አትፍሯቸው የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ በጀሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን..." 📖ማቴ 10፥26

ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፬ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ አራት በዚች ቀን በልኪም ከሚባል አገር ሳኑሲ በሰማዕትነት ሞተ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይህ ቅዱስ በልጅነቱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እርሱ ሁልጊዜ እስከ ማታ ይጾም ነበር ዘመዶቹም የሚሠራውን አያውቁም ነበር፤ የታመሙ በሽተኞችንም ይጐበኛቸው ነበር፤ በአንዲት ሌሊትም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ሳኑሲ ሆይ የክብር አክሊልን ትቀበል ዘንድ ተነሥተህ ወደ መኰንኑ ሒድ ክብር ይግባውና በፈጣሪህ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመን አለው፤ በነቃም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ እንደተገለጸለትና እንዳዘዘው ለእናቱ ነገራት እርሷም አዘነች አለቀሰችም ነገር ግን ትከለክለው ዘንድ አልተቻላትም። ❖ ከዚህ በኋላ ስብራ በሚባል አገር ስሟ ማርያ የሚባል ድኆችንና መጻተኞችን የምትቀበልና የምትመግባቸው የተቀደሰች ሴት እንዳለች ስለርሷ ሰምቶ ወደርሷ ሔደ፤ በሰማዕትነትም ይሞቱ ዘንድ ከርሷ ጋራ ተስማማ። ❖ አርሳኖስ ወደ ሚባልም መኰንን በአንድነት ሔዱ በምስር ወደብ በመርከብ ውስጥ ሁኖ አገኙትና እኛ ክርስቲያኖች ነን ብለው በፊቱ በግልጥ ጮኹ በየራሱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ቅድስት ማርያም በሥቃዩ ውስጥ ሳለች ነፍሷን አሳልፋ ሰጠች የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለች። ❖ ቅዱስ ሳሉሲ ግን ክብር ይግባውና በላዩ በአደረው በጌታችን በኢየሱስ ኃይል የሚታገሥና የሚጸና ሆነ፤ መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸው ጊዜ ወደ እንዴናው መኰንን ከብዙዎች እሥረኞች ሰማዕታት ጋራ ላከው እርሱም ያሠቃየው ጀመረ ተረከዙንም ሠንጥቀው ገመድ አግብተው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ፤ እንዳዘዛቸውም አደረገ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰበትም ። ❖ ሁለተኛም ሥራየኛ አመጣለትና መርዝ በተመላ ጽዋ ሥራዩን አድርጎ ጠጣ ብሎ አዘዘው፤ ቅዱሱም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ ጠጣው ምንም ምን ጉዳት ሳይደርስበት ቀረ፤ ከማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘና የከበረች ራሱን ቆረጡት የድል አክሊልንም ተቀበለ መሠርዩም አምኖ በሰማዕትነት ሞተ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለሳኑሲ ምቱረ አብራክ ወእድ። ወኅርወ ሰኰና አምሳለ ጒንድ። ለማርያ ሰላም መፍቀሪተ ነግድ። ዘኰነንዋ ምስሌሁ ወሣቀይዋ በዓውድ። ወምስለ መሠርይ ኅቡረ ዘአምነ በወልድ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ዕለት ሐራቅሊ ከሚባል አገር ቅዱስ አባት ዮሐንስ አረፈ፤ፐየዚህም ቅዱስ አባት ስሙ ዘካርያስ ነው እርሱም የጳንጦስና የአብልያ ሀገሮች ገዢ ነበር የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም ይህን የተባረከ ልጅ በተሰጡ ጊዜ ስሙን ዮሐንስ ብለው ጠሩት እርሱ ከአባቱና ከእናቱ ጀምሮ ከመጥምቀ አምላክ ዮሐንስ ጋራ በስም አንድ ሁኗልና በተግሣጽና በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ሂሣቦችንና ጥበቦችን ሁሉ አስተማሩት እናቱም በዘመኗ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳይወጣ ታማፅነው ነበር፤ አባቱም እንዲሁ ይመክረውና ያስተምረው ነበር። ❖ ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ የሃያ ዓመት ልጅ ሲሆን መስፍን ሆነ የጳንጦስና የሐራቅሊ ሌሎችም አገሮች ሁሉ ተገዙለት፤ እንዲሁም እያለ የመልአክ አምሳል ሰይጣን ታየው እንዲህም አለው አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሒደህ የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ አግባ ብሎ ጌታ አዝዞሃል አለው ቅዱሱም በውኑ ይህ መልአክ ነውን ግን ከአፉ የእግዚአብሔር ስም ከሰማሁ አንጾኪያ እሔዳለሁ አለ። ❖ ከዚህ በኋላም ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ተገናኘው ንጉሡም በአየው ጊዜ አከበረው እጅግም ወደደው። በማግሥቱም በምሳ ላይ ከእርሱ ጋራ እያለ ከሃድ ድዮቅልጥያኖስ አጵሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ ያንንም ጣዖት ባመጡት ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ አቃለለው ስለዚህም ሥራ ንጉሡን ረገመው ሰደበውም። ❖ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገውን በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በእሥር ቤት አሠረው። በእሥር ቤትም ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ታየዉ ከእርሱ ጋራም መላእክት አሉ፤ ይዞም ሳመው ብዙዎች ቃል ኪዳኖችንም ሰጠው፤ በማግሥቱም ንጉሡ ልኮ ከእሥር ቤት አወጣዉ ወደ ርሱም አቀረበውና ለአጵሎንና ለአርዳሚስ ስገድ አለው ቅዱሱም የሰው እጅ ለሠራው እንዴት እሰግዳለሁ አለው ንጉሡ ግን ከእርሱ ጋር መታረቅ ሽቶ ብዙ የሽንገላ ነገርን ተናገረው። ❖ ከዚህም በኋላ ግብርን ያስገብር ዘንድ ከሹመት ጋራ ወደ ግብጽ አገር ላከው ወደ ግብጽ ገዢ ወደ ስርያቆስም ስለ ርሱ እንዲህ ሲል ጽፎ ላከ እነሆ ለዮሐንስ ዘሐራቅሊ ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤቶች አፍርሶ አዲስ እንዲአሠራ ከግብጽና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁ። ❖ ቅዱሱም ይህን ምክንያት ይዞ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሶ ተዋቸው፤ በዚያም ወራት ወኰንኑ ስርያቆስ የሰማዕታትን ራስ መቆረጥን ሊያዝዝ በፍርድ አደባባይ ተቀመጠ በዚያን ጊዜ ከስዒድ ዲዮስቆሮስ ፣ ቢፋሞን ፣አሕራጋኖስ ፣ኪሮስ፣ ዮልዮስ፣ እለእስክንድሮስ፣ ዮሴፍ ፣ይስሐቅና ፣ እስጢፋኖስ የሚሉአቸው ሰዎች መጥተው እሊህ ሁሉም እኛ ክርስቲያኞች ነን እያሉ በግልጥ ጮኹ ያን ጊዜ መኰንኑ ይዞ ያለርኅራኄ ያሠቃያቸው ጀመረ። ❖ ቅዱስ ዮሐንስም ይህን በአየ ጊዜ የሹመቱን ሥራ ትቶ እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በግልጥ ጮኸ መኰንኑም ተቆጥቶ በእግር ብረት እንዲአሥሩትና ወደ እንድና አገር ወደ መኰንኑ አርያኖስ እንዲወስዱት አዘዘ እርሱም ስለሆነው ሁሉ መረመረው ከቃሉ መልስም የተነሣ ተቆጣ በባላ እንጨት ላይ ሰቅለው በመንኰራኲር አጣብቀው እንዲጨምቁት ከዚያም ከባላው አውርደው ሥጋው እስኪቀልጥ ሆዱ ላይና ራሱ ላይ በቀጭኔ እንዲደበድቡት አዘዘ ምድሪቱም በደሙ ተመላች ከዚያም ወደ እሥር ቤት አስገቡት። ❖ ከጥቂት ቀኖች በኋላም በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ ያሹት ዘንድ ዳግመኛም አመድ ጐዝጉዘው በላዩ የእሳት ፍም ከጐኑ በታች አድርገው በላዩ እንዲአስተኙት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት፤ ሁለተኛም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በፊቱ ላይ በጀሮዎቹም ላይ እንዲያኖሩዋቸው አዘዘ እንዲህም አድርገው ከወህኒ ቤት ጨመሩት። ❖ በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ሰላምታ ሰጥቶ አጸናው፤ በማግሥቱም ከወህኒ ቤት አውጥተው በጋሉ ብረት ዘንጎች ደበደቡት፤ ከዚህም በኋላ ግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጭራ ላይ በገመድ አሠሩ፤ ከዚህ በኋላም ባለ ሰይፍ ወጥቶ እግሮቹንና እጆቹን ራሱንም ቆረጠ እንዲህም የምስክርነቱን ተጋድሎ ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መስተጋድል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለዮሐንስ ምክሐ ሐራቅሊ ወአድያሙ። ፈዋሴ ዱያን በዐፅሙ። ወበእለ ምስሌሁ ሰላም ዘተጋደሉ ቀዲሙ። ወሰላም ለእንተ ድኅሬሁ ዘተክዕወ ደሙ። እኅወ እሙ ቢፋሞን ስሙ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ፨ የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጅ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፤ ፨ አቡቀለምሲስ የተባልክ ክቡር ዮሐንስ ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፤ ፨ የሐዲስ ሥርዓት
ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ፨ የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጅ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፤  ፨ አቡቀለምሲስ የተባልክ ክቡር ዮሐንስ  ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፤  ፨ የሐዲስ ሥርዓት ሐዋርያ ዮሐንስ ሆይ!  በቤተ ምንዳድ ለደረሰብህ መከራ  ሰላምታ ይገባሀል፤  ፨ በትዕግስትህ የሮምንና ቁጣ ችለህ  የሞተውንም ያስነሳህ ዮሐንስ ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፤ ፨ መከራን የምትታገስ ዮሐንስ ሆይ! እንዳንተ ያለ በምድር ላይ ማነው፤ ፨ ክብርን የተሞላህ ዮሐንስ ሆይ! ሰላምታ ለአንተ ይሁን እያልኩ በምስጋናና በእምቢልታ  የቤተክርስቲያን የጉባኤዋ መሪ እነሆ  አደንቅሀለሁ፤ ፨ በምስጋና እና በማህሌት የመላእክት ወዳጅ የሆንክ እውነተኛ  ዮሐንስ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤  ፨ ዮሐንስ ሆይ! ለሚልህ የመልክህ ደምግባት ምን ያምር፤ የስምህስ አጠራር ምን ይጣፍጥ፤ ፨ አራተኛውን ወንጌል የጻፍክ ዮሐንስ  ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፤ ኮል የተባለ  የምስጋናህ መዓዛ በሰው ሁሉ አፍንጫ  በጎ በጎ ሸተተ፤ ፨ ንስር የተሰኘህ ዮሐንስ ሆይ! ልዑል ከሆነ ከሰማይ ተዋሕዶ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛም አደረ እያልክ በረህ ና                             መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ

√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanz
√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanz
√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፫ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሦስት በዚች ቀን በትኅርምትና በተጋድሎ የጸናች ቅድስት ማርታ አረፈች። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ.ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ ክርስቶስና ወለተ ማርያም ይባላሉ:: ❖ ታህሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው፤ በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ❖ ሕጻን እያሉ ቃለ እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው፤ እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም፤ ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን ነብሩን ተኩላውን ሰብስበው "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: ❖ አራዊቱ ከበጉ ከፍየሉ ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ፤ ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ፤ ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: ❖ 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ ማርያም ሔደው መንኩሰዋል፤ ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት 1. በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል 2. ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል 3. ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) 4. "7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: ❖ ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ.ም (በአፄ ዮሐንስ ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል፤ እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: በረከታቸው ረድኤታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅድስት ማርታ ተሐራሚት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይቺም ቅድስት ከምስር ተወላጆች ውስጥ ነበረች ወላጆቿም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ከታናሽነቷም ጀምራ የረከሰ ዝሙትን የምትወድ ነበረች የከተማ ጐልማሶችና ታላላቆችም በሥውር ወደርሷ እየመጡ ያመነዝሩ ነበር፤ ከዚህ በኋላም ሥራዋ ተገለጠ የርኲሰት ሥራንም በግልጥ አብዝታ የምትሠራ ሆነች። ❖ ክብር ምስጋና ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ ልደቱ በዓል በሆነ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ልትገባም በፈለገች ጊዜ የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ከለከላት እንዲህም አላት አንቺ በምግባር የረከስሽ ስለሆነ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መግባት አይገባሽም ይተዋትም ዘንድ አባበለችው እርሱ ግን ከለከላት በመካከላቸውም ታላቅ ጸብ ሆነ። ❖ ኤጲስቆጶሱም ጩኸት ሰምቶ ተነሥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ደረሰ ማርታንም በአያት ጊዜ የእግዚአብሔር ቤቱ የከበረና የነጻ እንደ ሆነ አታውቂምን አንቺም የረከስሽ ስለሆንሽ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገቢ ዘንድ አይገባሽም አላት። ❖ በዚያን ጊዜም አለቀሰች ንስሓ እገባለሁ እንጂ ወደዚህ ሥራ እንግዲህ አልመለስም ብትቀበለኝም እመነኲሳለሁ አለችው፤ ኤጲስቆጶሱም ገንዘብሽንና ጥሪትሽን ሁሉ ወደዚህ አምጥተሽ በፊትሽ ካላቃጠልነው አላምንሽም አላት፤ ያን ጊዜም ሒዳ ጥሪቷንና ዋጋው ብዙ የሆነ ጌጥዋን አምጥታ በኤጲስቆጶሱ ፊት ጣለችው እርሱም በፊቷ አቃጠለው። ❖ ከዚህም በኋላ የራስዋን ጠጉር ተላጨች ኤጲስቆጶሱም ማቅ አልብሶ ወደ ደናግል ገዳም ላካት በዚያም ታላቅ ተጋድሎን በፍጹም ልቧ ጀመረች ነፍሷንም እንዲህ እያለች ትገሥጻት ነበር በጭቃና በደንጊያ ወደ ታነፀው ቤት ለመግባት ካልተውሽ በብርሃን ወደ ተሠሩ ቤቶችማ ለመግባት እንዴት ትሆኛለሽ ሁለተኛም በጸሎቷ አቤቱ ቤተ ክርስቲያንህን ከሚጠብቀው የደረሰብኝን ኀፍረት ልሸከመው ያልቻልኩ እኔን በቅዱሳን መላእክቶችህ ፊት አታሳፍረኝ አለች፤ ይችም ቅድስት ሰይጣንን ድል እስከ አደረገችው ድረስ ሃያ አምስት ዓመት ስትጋደል ኖረች በዚህ ሁሉ ከገዳም ግቢ ወደ በር አልወጣችም ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለማርታ ጥዕምተ ዝክር ወዜና። ዘተዐጽፈት ሠቀ አልባስ ወርቅ መኒና። አመ ገሠጻ ኢትባእ ውስተ ቤተ መቅደስ እንበለ ንጽሕና። እስከነ ሞዓቶ ለእኩይ ሕሊና። ዓቃቤ ኆኀት ምክንያተ ኮና። በዚችም ዕለት ሰማዕት ኮርዮን አረፈ በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ቅዱስ ኤላርዮስ ሰማዕት ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ቀን ደግሞ ኤላርዮስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ሰማዕት ሆኖ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ከሀዲውን ንጉሥ ዮላኪዮስን ጣዖታትን ስለማምለኩ ይገሥጸውና ይመክረው ነበር ንጉሥ ዮላኪዮስም አይሁድ የሰቀሉትን ባለማምለኬ አንተ ከሀዲ ትለኛለህ እነሆ አሁን እኔ አንተን ከሥቃይ ጽናት የተነሣ ያን የተሰቀለውን አምልኮቱን አስተውኻለሁ አለው። ❖ ከዚህ በኋላም ከመኳንንቶቹ ለአንዱ መኰንን ሰጥቶ ባለመራራት ያለማቋረጥ ሁልጊዜ እንዲአሠቃየው አዘዘው መኰንኑም ወስዶ በየራሱ በሆነ ሥቃይ አንዲት ቀን እንኳ ከቶ ሳያቋርጥ ሁልጊዜ እያሠቃየው አንድ ዓመት ሙሉ ኖረ፤ በዓመቱም ፍጻሜ በእሳት ውስጥ ጣሉት እርሱም ከእሳት መካከል ቆሞ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ ስለዚህችም ምልክት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ብዙዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❖ ከዚህም በኋላ ከአታክልት መካከል እንደ ሚወጣ ሆኖ ከእሳት አወጡት፤ መኰንኑም ከማሠቃየት በደከመ ጊዜ በእርሱ ላይም የሚያደርገውን በእጣ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዝዞ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምሥጋና ይሁን እኛንም በዚህ ተጋዳይ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤️              ❤️ #ሰኔ ፪ (2) ቀን። ❤️ እንኳን #የመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ ሥጋ ከቀናተኛው ከነቢዩ #ከቅዱስ_ኤልያስ ደቀ መዝሙር ከሆነው #ከነቢዩ_ከቅዱስ_ኤልሳዕ_ሥጋ ጋር በአንድነት ለተገኘ መታሰቢያ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦#ከቅዱሳን_ቆርሎስና #ከአክሌጥስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                 ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የመጥምቁ_የቅዱስ_ዮሐንስና_የነቢዩ #ቅዱስ_ኤልያስ_ሥጋ_በአንድነት_መገኘት፦ ከሀዲው ንጉሥ ዑልያኖስ የጥጦስ ልጅ አስባስያኖስ ከአፈረሰው በኋላ በዘመኑ በኢየሩሳሌም የአይሁድ ምኵራባቸውን ሊሠራ በወደደ ጊዜ እርሱ በቅዱስ ወንጌል ደንጊያ በደንጊያ ላይ ተቀምጦ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም የተባለውን የእግዚአብሔር ቃል ሊሽር ፈልጎ መሥራት በጀመረ ጊዜ ሦስት ጊዜ ፈረሰበት። አይሁድም እንዲህ አሉት "የደጋግ ክርስቲያኖች ዐፅሞቻቸው በዚህ ቦታ ስለሚኖሩ ከዚህ ካላወጣሃቸውና ካላቃጠልካቸው በዚህ ቦታ ምኵራብ አይሠራም"። ❤️ በዚያንም ጊዜ የቅዱሳንን ዐፅሞቻቸውን አውጥተው በእሳት እንዲአቃጥሉት አዘዘ በአፈለሱም ጊዜ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልሳዕን ሥጋቸውን ምእምናንም መጥተው ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጡ ንጉሡም ሰምቶ እንዳያጠፋቸው በዚያች አገር እንዲያስቀሩ ከአማሏቸው በኋላ የቅዱሳንን ሥጋ ወሰዱ። ❤️ የዑልያኖስም ዜናው እንዲህ ሆነ የጳጳሳት አለቆች ባስልዮስና ጎርጎርዮስ በአሠራቸው ጊዜ እነርሱ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ዘንድ እያለቀሱ ጸለዩ። የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችንን የከበረ ስሙን ሰድቧልና ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅዱስ መርቆሬዎስ በከአካለ ነፍስ ላከው ዑልያኖስንም በጦር ወጋው ከደሙም ዘግኖ "ኢየሱስ የሰጠኸኝን ነፍስ ተቀበል" እያለ ወደ አየር ረጨ ወዲያውኑም በክፋ አሟሟት ሞተ። ❤️ የከበሩ የቅዱሳን የዮሐንስና የኤልሳዕ ሥጋ ግን እሊህ ሰዎች በእስክንድርያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ አትናቴዎስ አደረሱ። እርሱም በእርሳቸው ታላቅ ደስታ ደስ አለው ቤተ ክርስቲያንም እስኪሠራላቸው ድረስ በርሱ ዘንድ አኖራቸው። በአንዲት ዕለትም አባ አትናቴዎስ በአባቶቹ ቦታዎች ላይ ስለ ጸሐፊው ቴዎፍሎስም አብሮት ሳለ "እግዚአብሔር መልካም ዘመን ቢሰጠኝ ሥጋቸውን በውስጧ አኖር ዘንድ ለቅዱሳን መጥምቁ ዮሐንስና ለነቢዩ ኤልሳዕ በስማቸው በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያ እሠራለሁ" አለ ቴዎፍሎስም ሰማው። ❤️ አባ ቴዎፍሎስም በተሾመ ጊዜ አባ አትናቴዎስ የተናገረውን ያንን ቃል አስቦ ቤተ ክርስቲያን ሠራ። ከርሱ ጋራም ብዙዎች ካህናትና የክርስቲያን ወገኖችን ይዞ የቅዱሳን የመጥምቁ ዮሐንስና የነቢዩ ኤልሳን ሥጋቸውን ወዳለበት ሔደ በታላቅ ክብርም ተሸክመው አምጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡ። ሥጋቸውንም ይዘው በሚጓዙበት ጊዜ በጐዳናቸው አቅራቢያ ቤት ካለበት ቦታ ደረሱ በውስጡም በምጥ ተይዛ አራት ቀናት እየጮኸች ለሞት የተቃረበች ሴት ነበረች። እርሷም አረማዊት ነበረች በቅዱሳኑም ሥጋ ዘንድ ካህናቱ የሚያመሰግኑትን ሰምታ በቤቷ መስኮት ተመለከተች "ይህ ምንድን ነው?" ብላ ጠየቀች። "የቅዱሳን የመጥምቁ ዮሐንስና ነቢዩ ኤልሳዕ ሥጋቸው ነው" እርሷም "ከዚህ ሥቃይ ከዳንኩ ክርስቲያን እሆናለሁ" አለች ገና ቃሏ ከአፋዋ ሳይፈጸም ያን ጊዜ መልካም ሕፃን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብላ ጠራችው። ከዚህም በኋላ ከቤተ ሰቦቿ ሁሉ ጋራ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀች። ❤️ የቅዱሳኑንም ሥጋቸውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከእርሳቸውም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጠ። በቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑም ጊዜ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ ጋራ ብዙዎች ሰዎች ቅዱሳን መጥምቁ ዮሐንስንና ነቢዩ ኤልሳዕን ሲዞሩ አዩአቸው በቀድሞ መልካቸው ያውቋቸዋልና የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ መልክ ሁለመናው ጸጒር ሲሆን ጽሕሙ በደረቱ ላይ የወረደ ነበር ቅዱስ ኤልሳዕም ቁመቱ ረጅም ራሱ በራ ነበር። ❤️ ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሱ አባ መቃርስ በሰማዕትነት በዐረፈ ጊዜ ሥጋውን ከቅዱሳን ዮሐንስና ኤልሳዕ ሥጋ ጋራ አደረጉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና በነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 2 ስንክሳር። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፩ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" 📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፩ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከ የሰኔ ወር ቀኑ ዐሥራ አምስት ሰዓት ነው፤ ከዚህም በኋላ ይጎድላል፤ ሰኔ አንድ ቀን በዚች ቀን ከእርሱ ተአምራት የተገለጡ የሶርያ ሰው የሆነ የቅዱስ ለውንትዮስ የቤተ ክርስቲያኑ ቅዳሴ ነው።