ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
603
订阅者
-224 小时
-57 天
-1430 天
帖子存档
❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️            ❤️ #ሰኔ ፲፯ (17) ቀን። ❤️ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን_አንዱ_ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ይስሐቅ ባደረጉት ተአምር ስማቸው #አባ_ገሪማ_ለተባሉት ከዚህ ዓለም #ከሞት_ለተሰወሩበት_ዓመታዊ_መታሰቢያ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አቡነ_ይስሐቅ_አባ_ገሪማ፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ የሮም ንጉሥ ነበር ስሙም መስፍንያኖስ ይባላል። የንግሥት እናቱ ስምም ሰፍንግያ ነው እርሷም መካን ስለሆነች በእናቱ በቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ከማላጅነት በመማፀን ወደ እግዚአብሔር እየለመነች ኖረች። ከዚህ በኋላ ይህን የተባረከ ልጅ ተቀበለች ስሙንም ይስሐቅ ብላ ጠራችው። ጥቂት በከደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት አስተምረው ዲቁና አሾሙት። ❤️ አባቱ በሞተ ጊዜ የሮም ሰዎች በአባቱ ዙፋን ላይ አነገሡት እየፈረደና በቅን እየገዛ ሰባት ዓመት ኖረ። በዋሻ የሚኖረው አባ ጰንጠሌዎንም በሰማ ጊዜ እንዲህ ብሎ ወደርሱ ላከ "ልጄ ይስሐቅ ሆይ ሙታኖቻቸውን ይቀብሩ ዘንድ ሙታኖችን ተዋቸው አንተ ግን ክብር ይግባውና የክርስቶስን የማያልፍ መንግሥት ትሻ ዘንድ ወደ እኔ ና" አባ ገሪማም መልእክቱ ደርሶት በሰማ ጊዜ መንግሥቱን ትቶ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ያንጊዜም ጌታ የላከው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጠለት ብርሃናውያን በሆኑ ክንፎቹም ተሸክሞ የዐሥር ወር የሚሆነውን መንገድ በሦስት ሰዓት አደረሰው በአባ ጰንጠሌዎንም ደጅ አቆመው ይህም በኢትዮጵያ ንጉሥ በእልአሚድ ዘመን ነበር። ❤️ አባ ጰንጠሌዎንም ቅዱስ ይስሐቅን በአየው ጊዜ ደስ ብሎት አቅፎ ሳመው ወደ በዓቱም አስገብቶ የምንኲስና ልብስን አለበሰው። ይስሐቅም በጾም በጸሎትና በስግደት ተጠምዶ ቆዳው ከዐፅሙ እስከሚጣበቅ ሲጋደል ኖረ። ❤️ ከዚህም በኋላ መደራ ወደተባለ ቦታ ሔደ በዚያም ድንቅና ተአምር እየአደረገ በሽተኞችን በመፈወስና አጋንንትን በማስወጣት ብዙ ዘመን ኖረ። በአንዲት ዕለትም በጥዋት ሥንዴ ዘራ በሠርክም መሥዋትን አሳረገ። በማግሥቱም በግራር ዛፍ ላይ በሮችን አውጥቶ የሥንዴውን ነዶ አበራየ ሰባ ሰባት የእንቅብ መስፈሪያም ሆነ። ሁለተኛም የወይን አረግ በአለት ላይ ተከለ ወዲያውም በቀለች አበበችና አፈራች በእርሷም መሥዋዕትን አሳረገ። አንዲት ቀንም ሲጽፍ መሸና ፀሐይ ሊጠልቅ ተቃረበ በቦታውም እንዲቆም አዘዘው ጽሕፈቱንም እስቲጨርስ ቆመ። ምራቁንም ትፍ ባለበት ዘንድ ጠበል ፈልቆ እስከ ዛሬ ለበሽተኞች ፈውስ ሆኖ ይኖራል። ❤️ በአንዲት ዕለትም ሰዎች ወደ አባ ጰንጠሌዎን መጥተው "ቀሲስ ይስሐቅ እኮ ከበላ በኋላ የቁርባን ቅዳሴ ቀደሰ" ብለው ነገሩት አባ ጰንጠሌዎንም ወደርሱ ሒዶ "ልጄ ይስሐቅ ሆይ ምሥጢር ስለ አለኝ ከአጠገባችን ሰዎችን አስገልል" አለው ይስሐቅም "ሰዎችን ተውና ዕንጨቶችና ድንጋዮችም ይገለሉ" አለ። ወዲያውኑም ዕንጨቶችና ድንጋዮች አንድ ምራፍ ያህል ሸሹ። አባ ጰንጠሌዎንም "ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ" አለ ስለዚህም ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ገሪማ ተባለ። ❤️ መልካም ተጋድሎንና የቀና አካሔዱን በፈፀመ ጊዜ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት "ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያው ለሚያደርግ፣ ገድሉንም ለሚጽፍና ለሚያጽፍ፣ ለሚያነበውና ለሚተረጉመው ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ዳግመኛም "የተራበውን ላበላ፣ የተጠማውንም ላጠጣ እኔ የሕይወት እንጀራን እመግበዋለሁ የድኅነት ጽዋንም አጠጣዋለሁ" አለው። በቤተ ክርስቲያንህም በማኅሌት ያመሰገነውንና የፀለየውን እኔ የመላእክትን ምስጋና አሰማዋለሁ የተራቆተውንም ለሚያለብስ የብልህ እጅ ያልሠራው የብርሃን ግምጃን አለብሰዋለሁ ነፍሱም ከሥጋው በምትለይ ጊዜ የጨለማ መላእክት አይቀርቡትም። የብርሃን መላእክትም በዙሪያው አቆማቸዋለሁ። በስምህም ቤተ ክርስቲያን ለሠራ በሰማያት አርባ ሰባት የብርሃን ቦታዎችን እኔ እሰጠዋለ፣ ለቤተ ክርስቲያንህ መባ የሚሰጠውንም እኔ በመንግሥቴ እቀበለዋለሁ፣ ቦታህን የሚያከብረውንም እኔ በመንግሥቴ አከብረዋለሁ፣ ጠላቶች አጋንንትን ረግጦ የሚገዛበትንም እሰጠዋለሁ"። ❤️ አባ ገሪማም "ይህን ታላቅ ሀብት በቸርነትህ ብዛት የሰጠኸኝ አቤቱ ስምህ ይክበር ይመስገን ግን ጌታዬ ሆይ መታሰቢያዬን ላደረገ፣ ገድሎንም ለጻፈ እስከ ስንት ትውልድ ትምርልኛለህ" አለ። መድኃኒታችንም "እስከ ዐሥራ ሁለት ትውልድ እምርዋለሁ" አለው አባ ገሪማም መድኃኒታችንን "ልጆች ባይኖሩትስ ምን ታደርግለታለህ" አለው። መድኃኒታችንም "ዐሥራ ሁለት ዕጽፍ ክብር እሰጠዋለሁ" ብሎ መለሰለት። ❤️ ዳግመኛም "የሞት ጥላ እንደማያገኝህ ታላቅ የምሥራች እነግርሃለሁ" አለው ይህንንም ተናግሮ ሰላምታ ሰጥቶት በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ቅዱስ አባ ገሪማም በልቡ ደስ ተሰኘ ወዲያውኑም ሰኔ 17 ቀን በብርሃን ሠረገላ ተነጥቆ ብሔረ ሕያዋን ገባ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም አባ ገሪማ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 17 ስንክሳር።

❤️ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ "ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ። ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ። ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ" አላቸው ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋራ ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት18 ስንክሳር።                                                     ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን"። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ 77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ 24፥1-13።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ117፥24-25 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥20-41፣ 1ጴጥ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 2፥1-21 ወይም 2፥22_37። የሚነበው ወንጌል ዮሐ 20፥1-19 ወይም 14፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️ ❤️ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካች #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለመንፈስ_ቅዱስ (ለጰራቅሊጦስ) በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና ደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ "#ወበ፶ ዕለት ፈነወ ሎሙ #መንፈሰ_ቅዱሰ ከመ ዘእሳት #ወተናገሩ_በነገረ_ኵሉ_በሐዉርት"። ትርጉም፦ #በሃምሳውም_ቀን_በእሳት_አምሳል_መንፈስ_ቅዱስን ሰደደላቸው #በአገሩ_ሁሉ_ቋንቋ_ተናገሩ። #ሊቁ_ቅዳሴ_ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ቅዳሴው_ላይ።                                                    ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #ጰራቅሊጦስ፦ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኃጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጉምን ይሰጣል መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት። ❤️ የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ፤ ከትንሣኤ በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠርጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። ❤️ "እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ" አላቸው። ሁለተኛም "ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል" አላቸው። ❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው "እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናስበውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ"። ይህንንም ሲነግራቸው እንሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደ ርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ። የተከፋፈለ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ። በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ። ❤️ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ "በዓለ ኃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ። ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ መላው የተከፋፈለ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀምጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየአገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና። ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ። "እንሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ፣ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን። በሁለት ወንዝ መካከል በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣ በፍርግያም በጽንፍልያም፣ በግብጽም፣ በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እንሆ እንሰማቸዋለን። ሁሉም ደግጠው የሚናገሩትን አጡ። እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው "ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል" አሉ። ❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው "የይሁዳ ሰዎቼ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደለም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና። ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለውነው፦ "እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴ አሳድራለሁ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁ ሕልምን ያልማሉ። ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ። ደግሞ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሓይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል"። ❤️ ዳዊትም እንዲህ አለ "ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ድኅነትህንም ስጠኝ። በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው"። ሁለተኛም "መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ" አለ። ደግሞ "ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ" አለ። ደግሞም "በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"። ❤️ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ"። ❤️ ጌታችንም እንዲህ አለ "ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ። ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። እኔ ሰላም እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣች። እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም። እኔ እሔዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ"። ❤️ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ "እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይምሰክራል። እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና። ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሰዋል። ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንዲህም አታዩኝም ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና" አላቸው። "የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ። ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና"። ❤️ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁ የሚለን"። ጌታ ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐውቀባቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ። እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል"።

"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️               ❤️ #ሰኔ ፲፮ (16) ቀን። ❤️ እንኳን #የእግዚአብሔር_መልአክ_ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦለት #ሕፃኑንና_እናቱንም_ይዞ_ወደ #እስራኤል_አገር_እንዲመለስ_ላአዘዘበት_ዕለትና #መልካም_ሽምግልና_ላለለው ስም አጠራሩ ለከበረ በገዳም ለሚኖርና በገድል ለተጠመደ #ለስልሳ_ዓመት ብቻው ሰው ሳያይ ለኖረ አባት ለላይኛው ግብጽ ሰው #ለአባ_አቡናፍር_ለዕረፍቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #የአባ_አቡናፍርን_ገድል ከተናገረ #ከአባ_በፍኑትዮስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አባ_አቡናፍር፦ የዚህም አባት ገድል የተናገረ አባ በፍኑትዮስ ነበር እርሱ ቊጥሩ ከገዳማውያን ነውና። አባ በፍኑትዮስም ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ዛፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ። ❤️ በአንዲት ዕለትም አባ በፍኑትዮስ ወደርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍርን አየው ፈርቶም ደነገጠ የሰይጣን ምትሐት የሚያይ መስሎታልና ይህም አባት አቡናፍር ልብስ አልነበረውም ጸጒሩና ጽሕሙ ሥጋውን ሁሉ ይሸፍናሉ አባ በፍኑትዮስም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ አጽናናው በፊቱም አቡነ ዘበሰማያት ጸለየ ከዚህም በኋላ "አባ በፍኑትዮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" አለው ይህንንም በማለት ከእርሱ ፍርሃቱን አራቀለት። ❤️ ከዚህ በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ። ከዚህም በኋላ ወደዚህ በረሀ ከዓለም አወጣጡ እንዴት እንደሆነ በዚያ በረሀ አኗኗሩ እንዴት እንደሆነ ይነግረው ዘንድ አባ በፍኑትዮስ አባ አቡናፍርን ለመነው። አባ አቡናፍርም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ ደጋጎች ዕውነተኞች መነኰሳት በሚኖሩበት በአንድ ገዳም እኖር ነበር የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኑአቸውም ሰማሁ "እኔም ከእናንተ የሚሻሉ አሉን?" አልኳቸው እነርሱም "አወን እነርሱ በበረሀ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን በበረሀ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው" አሉኝ። ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልቤ እንደ እሳት ነደደ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የፈቀደውን ይመራኝ ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ተነሥቼ ጸለይኩ። ትንሽ እንጀራም ይዤ ተጓዝኩ አንድ ጻድቅ ሰውም አግኝቼ የገዳምውያንን ገድላቸውንና ኑሮአቸውን እያስተማረኝ በእርሱ ዘንድ ኖርኩ። ❤️ ከዚህም በኋላ ወደዚህ ደረስኩ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝን ይቺን ሰሌን አገኘኋት በየዓመቱም ዐሥራ ሁለት ዘለላ ታፈራለች ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚች ምንጭ እጠጣለሁ በዚች በረሀ እስከ ዛሬ ስልሳ ዓመት ኖርኩ ከቶ ያላንተ የሰው ፊት አላየሁም" አለኝ። ይህንንም ሲነጋገሩ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ወረደ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ሰጣቸው። ከዚያም በኋላ ከሰሌን ፍሬ ጥቂት ምግብ ተመገብን። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ እንደ እሳትም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክኮ ሰገደ ለአባ በፍኑትዮስም ሰላምታ ሰጠው ያን ጊዜም ነፍሱን በጌታ እጅ ሰጠ። ቅዱስ በፍኑትዮስም በጸጉር ልብስ ገንዞ በዚያች ቦታ ቀበረው። ❤️ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ አሰበ በዚያን ጊዜ ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች የውኃውም ምንጭ ደረቀ። ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ወደ ዓለም ተመልሶ የገዳማውያንን ዜና ይልቁንም የቅዱስ አባ አቡናፍርን ዜና ይሰብክ ዘንድ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ የከበሩ ገዳማውያን በአባ አቡናፍርና በአባ በፍኑትዮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 16 ስንክሳር።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ "#ሰላም_ለአቡናፍር_ጊዜ ተዳደቆ_መዊት። እንተ ተለወጠ ገጹ አምሳለ ውዑይ እሳት። ድኅረ ቀበሮ በፍኑትዮስ በውሳጤ በዓት። ኢትትዋስ ለካልአን ዘተውህበቶ ሲሲት። ነቅዐ ማይ የብስት ወወድቀት በቀልት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_16።

የሰንበት ትምህርት ቤት መማሪያ መጻሕፍት ሊመረቅ ነው!!! ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ6 የትምህርት ዓይነት የተዘጋጁ 23 የሰንበት ትምህርት ቤት መማሪያ መጻሕፍት
የሰንበት ትምህርት ቤት መማሪያ መጻሕፍት ሊመረቅ ነው!!! ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ6 የትምህርት ዓይነት የተዘጋጁ 23 የሰንበት ትምህርት ቤት መማሪያ መጻሕፍት ሊመረቅ ነው። በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ  ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በመሉ ትግበራ ላይ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ6 የትምህርት ዓይነት የተዘጋጁ 23 መጻሕፍትን የያዙ በ4 ጥራዝ የተዘጋጁ መጻሕፍትን ሕትመት ተጠናቆ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ የየመምሪያውና የድርጅት ኃላፊዎች፣ ከየሀገረ ስብከቱ የሚወከሉ የሰንበት ት/ቤት አንድነት አመራሮች እና የአዲስ አበባ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤት አመራር አባላት በታላቅ ድምቀት ሰኔ 16 2016ዓ.ም በበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰንበት ት/ቤቶች ቀን ያስመርቃል። 13ኛው ዓለም አቀፍ ሰንበ ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ከሰኔ 15 እስከ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል። 👉 የመማሪያ መጻሕፍቱ #የ4ቱም ጥቅል ዋጋ #ብር_2000 ሲሆን ሰንበት ት/ቤቶች መግዛት የምትችሉትን የመጻሕፍት ብዛት ቀድማችሁ በደብዳቤ ለአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ትምህርት ክፍል እንድታሳውቁ እናሳስባለን።

❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️               ❤️ #ሰኔ_፲፭ (15) ቀን። ❤️ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሰማይ_ጭፍራ ለተባለ #ለቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ ክርስቲያን_መርዩጥ በተባለ አገር #ለከበረችበት_ለቅዳሴ_ቤቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅዳሴ_ቤት፦ ከዚህ አስቀድሞ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ተሠውሮ ይኖር ነበር ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበሸ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጒድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ። ❤️ ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋራ አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ ለንሡም የቊስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ ከዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች። ❤️ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አላት። ከእንቅልፍም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ስሟም መርዩጥ ተባለች። ❤️ እግዚአብሔር ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቊጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ሰኔ 15 ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ15 ስንክሳር።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ "#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ እንተ ተሐንፀት በመርዩጥ። በትእዛዝ ንጉሥ ሥሉጥ። #ሚናስ ዘአንቃሕከ በድነ ሐራውያ እምጸጥ። አስተዋጺኦሙ ዕደው ዘበበ፪ቱ ቂራጥ። መባአ ለከ ዘነሥኡ በሤጥ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_15።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ውእተ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ። ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል። ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ"። መዝ 88፥19። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 7፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 25፥1-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥44-51። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ የቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚናስ የቅዳሴ ቤት በዓልና የበዓለ ዕርገቱ ሰሞን  ለሁላችንም ይሁንልን።

❤️ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤️             ❤️ #ሰኔ ፲፬ (14) ቀን። ❤️ እንኳን #ለቅዱሳን_አባ_አክራና_ለዮሐንስ፣ #ለአብጥልማና_ለፊልጶስ_ሰማዕትነት_ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #ቅዱሳን_አባ አክራ_ዮሐንስ_አብጥለሰማና ፊልጶስ፦ ይህም ቅዱስ አክራ ከግብጽ ደቡብ ይምንሑር ከሚባል አገር ሰዎች ወገን ነው ስሙ ፊልጶስ የሚባል ወንድም ነበረው እነርሱም ባለጸጎች ነበሩ ስማቸው ዮሐንስና አብጥልማ ከሚባል ሁለት ቀሳውስት ጋራ ሰማዕታት ይሆኑ ዘንድ ተስማሙ አራቱም ቀርጥስ ወደሚባል አገር ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመኑ። መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው። ❤️ ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አደረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ሰኔ 14 ቀን ቆረጡአቸው። ❤️ ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጠ። ❤️ እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዱሳን የፊልጶስን፣ የአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገንዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቊጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን ሰማዕታት በአባ አክራና ዮሐንስ፣ አብጥልማና ፊልጶስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ14 ስንክሳር።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ "#ሰላም_ለአብጥልማ_ወፊልጶስ_አብያጽ። ዮሐንስ ወአክራ ዘደቡብ ግብጽ። አመ ቆሙ ለስምዕ በዐውደ መኰንን ስሑጽ። እግዚአብሔር ባልሖሙ እምዘ ይሰርር ሐፅ። ወአድኃኖሙ ካዕበ እምእሳት ብቊፅ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የሰኔ_14።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥7-15፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 27፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ መልካም በዓልና የበዓለ ዕርገቱ ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን።

ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፲፫ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ አረፈ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ አባ ዮሐንስ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይህም ቅዱስ በቅዱስ አባ ኢላርዮንና በታላቁ አባ ኤስድሮስ ገዳም በታናሽነቱ መነኰሰ ከአባ ኤጲፋንዮስ ጋራም በገድል በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ የደግነቱ የተጋድሎውና የትሩፋቱ ዜናም በቦታው ሁሉ ተሰማ። ❖ ከዚህም በኋላ ኤጲፋንዮስ በቆጵሮስ ሀገር ኤጲስቆጶስነት ከተሾመ በኋላ እርሱን መርጠው በኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስነት ሾሙት፤ ይህ አባት በሹመት በነበረ ጊዜ ሰይጣን በገንዘብ ፍቅርና በዚህ ዓለም ክብር አሳተው ብዙ ገንዘብ ሰብስቦ ለማዕዱ የሚመገብበት የወርቅና የብር ሣህን አሠርቶ ነበርና ለድኆችና ለምስኪኖችም መራራትን ተወ ምንም የእንጀራ ቁራሽ አይሰጣቸውም ነበር። ❖ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሰማ ጊዜ የቀድሞውን ተጋድሎውንና የዓለም መናኒነቱን ፍቅሩንም አስታውሶ እጅግ አዘነ ከቀድሞ ጀምሮ በመንፈስ ወንድሙና ወዳጁ ነበርና፤ ስለዚህም ብፁዕ ኤጲፋንዮስ ከቆጵሮስ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አባ ዮሐንስ መጣ አባ ዮሐንስን በጥበብ ከስሕተት ያድነው ዘንድም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ባለበት ቤተ መቅደስ ለመስገድ እንደመጣ አመካኘ፤ በተገናኙም ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን ወደ ቤቱ አስገብቶ ማዕድ አዘጋጀለት በማዕድም ላይ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ሣህኖችን አኖረ አባ ኤጲፋንዮስም በልቡ አዘነ ለድኆችና ለምስኪኖች ርኃራኄ እንደሌለውም አየ። ❖ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ ወጥቶ በኢየሩሳሌም ካሉ ገዳማት በአንዱ አደረ፤ ምክንያትም አዘጋጀ ይህም እንዲህ ነው ወደ አባ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከ ወንድሜ ሆይ ከቆጵሮስ አገር ሽማግሌዎችና የሕዝቡ መምህራን ወደ እኔ መጥተዋልና በእነርሱ ፊት ታከብረኝ ዘንድ ከወርቅና ክብር የተሠሩ የማዕድ ዕቃዎችን ይመገቡባቸው ዘንድ እንድትልክልኝ እሻለሁ እርሱም ላከለት፤ ያን ጊዜም አባ ኤጲፋንዮስ ዕቃዎቹን ወስዶ ሸጣቸው ዋጋቸውንም ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወታቸው። ❖ ከዚህም በኋላ በተገናኙ ጊዜ አባ ዮሐንስ አባ ኤጲፋንዮስን የላኩልህን የማዕድ ዕቃዎቼን መልስ አለው እርሱም እሺ አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ ነገረው አባ ኤጲፋንዮስም እሺ አለው፤ በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና የጌታችን መቃብር ካለበት ቤተ መቅደስ ሲወጣ አገኘው ያን ጊዜም ያዘውና ገንዘቤን እስከምትሰጠኝ አልለቅህም አለው አባ ኤጲፋንዮስም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያን ጊዜም የአባ ዮሐንስ ዐይኖቹ ታወሩ። ❖ ያን ጊዜም ይቅር ብሎት ዐይኖቹን ይገልጥለት ዘንድ እያለቀሰ ወደ አባ ኤጲፋንዮስ ማለደ እርሱም መጸጸቱን አይቶ አንዲቱን ዐይኑን ገለጠለት እንዲህም አለው ነፍስህን ታስብ ዘንድ አንዲቷ ዐይንህ ዕውርት እንደሆነች ትቶልሃል፤ ገሠጸውም እነሆ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀድሞ ድካምህን ብርታትህንና ተጋድሎህን አስቦ ራራልህ ከስሕተትም አዳነህ አለው፤ የማዕድ ዕቃዎችንም እኔ እንደሸጥኳቸውና ስለ አንተ ለድኆችና ለምስኪኖች እንደ መጸወትኳቸው ዕወቅ አንተ በገንዘብ ፍቅር መጠመድህንና የቀድሞውን መልካም ሥራህን መተውህን ብሰማ ነው እንጂ ከቆጵሮስ ወደ ኢየሩሳሌም አልመጣም ነበር። ❖ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ቅዱስ ዮሐንስ ከእንቅልፍ እንደነቃ ሆነ በርኅራኄም መንገድ ሔደ ያለውንም ጥሪቱን ሁሉ ሰጠ ምንም ምን አላስቀረም፤ ልብሶቹንም ለተራቆቱ ሰጠ በሞተ ጊዜ አንድ አላድ ከዚያም በታች ከእርሱ ዘንድ እስከ አልተገኘ ድረስ ሰጠ፤ ጌታችንም የመፈወስ ሀብትን ሰጠው ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ ከተቀደሰ ዘይት እየቀባ ፊታቸውንም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት እያማተበ ደዌ ያለባቸውን ሁሉ አዳናቸው። መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ ክብር ይግባውና ጌታችንን አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ዕብል ለዮሐንስ ፍጹም። ኤጲስቆጶስ ዘኢየሩሳሌም። ገዲፎ ዕበየ ወክብረ ዝንቱ ዓለም። መጽወተ ለነዳያን እንበለ መስፈርት ወዓቅም። እስከ በዕረፍቱ ኢተረክበ ፩ ድርህም። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ መላእክት አለቃ ገብርኤል ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዚችም ዕለት ለከበረ መልአክ አዲስ የምሥራች ነጋሪ ለሆነ የመላእክት አለቃ ገብርኤል በዓልን ያደርጉለት ዘንድ መምህራን በግብጽ አገር ለክርስቲያን ወገኖች ሥርዓት ሠሩላቸው፤ ይህ የከበረ መልአክ የእስራአል ልጆች ከሰይጣን እጅ ስለመዳናቸውና ከምርኮም ስለ መመለሳቸው ነቢዩ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር በሚጸልይና በሚማልድ ጊዜ አስቀድሞ የተገለጠለትና ስለ ድኅነታቸውና ስለ ቤተ መቅደስም መታነፅ የነገረው ነውና። ❖ ዳግመኛም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ መምጣትና መገደል ስለ ቤተ መቅደስም መፍረስ ከዚያም በኋላ ስለ ሐሳዊ መሲሕ መምጣት ነገረው፤ ለመድኀን መምጣትም በሱባዔ የወሰናቸው ዘመናት በተፈጸሙ ጊዜ ይህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ወደ ቅድስት ድንግል ወደ እመቤታችን ማርያም መጣ ዓለምን ስለ ማዳን የእግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ስለመሆኑ ነገራት። ❖ ስለዚህም የበዓላቶቹን መታሰቢያ እንድናደርግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን፤ እኛም ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ያድነን ዘንድ ለመንግሥቱም የተዘጋጀን ያደርገን ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ስለ እኛ እንዲማልድ እንለምነው፤ ልዕልና ችሎታም ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የዚህም የከበረ መልአክ ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ለገብርኤል በእደዊሁ ዘተአሥሩ። መላእክተ ሰማይ ጌጋየ በትውልደ ሰብእ ዘገብሩ። ለዝንቱ መልአክ በእንተ ዕበዩ ወክብሩ። በብሔረ ግብጽ መምህራነ ሥርዓት አንበሩ። በዛቲ ዕለት ይትገበር ተዝካሩ። ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ የሄኖስ ልጅ ቃይናል ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የሄኖስ ልጅ ቃይናን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፤ ቃይናንም 170 ዓመት ኖሮ መላልዔልን ወደለደው፤ መላልዔልንም ከወለደው በኋላ 740 ዓመት ኖረ፡፡ ❖ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ የቃይናንም መላ ዘመኑ 910 ዓመት ሲሆነው በዚህች ዕለት ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን ❖ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የሄኖስ ልጅ ቃይናን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፤ ቃይናንም 170 ዓመት ኖሮ መላልዔልን ወደለደው፡፡ ❖ መላልዔልንም ከወለደው በኋላ 740 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ የቃይናንም መላ ዘመኑ 910 ዓመት ሲሆነው በዚህች ዕለት ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን በዚችም ቀን የሰማዕቱ አቡላግና የሁለት መቶ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው ስለ ዕውነትም የተሰደደ የአባታችን የማትያንም መታሰቢያው ነው። እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanz
√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 በዛሬው ዕለት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ዓ
+9
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 በዛሬው ዕለት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል። ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!!

ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ፵ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ ሰዎቹም ‹‹ባሕራን የተባለ ጎበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታሉ፤ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ፵ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል›› አሉት። ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጎልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቈጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡ #፫. አፎምያን ያዳነበት ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጕል ከአደራ ጋር አዘዛት እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት በከበረ ቦታም አኖረችው ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፤ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም ፥ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኵሴ መስሎ አጋንንትን መነኰሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት እርሷም ‹‹ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ›› አለቻቸው ሰይጣናቱም ‹‹እኛማ በነግህ ጸልየናል?›› አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን ‹‹...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ›› አላት ቅድስት አፎምያም ‹‹አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው አትጹሚ፥ አትጸልይ ያልከኝ ጌታ ምጽዋትን መጽውቱ ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም፤ ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?›› ብላ ሞገተችው የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?›› በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው ለጊዜው ‹‹በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም›› ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡ #፬. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው። + የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከትና ምልጃ በሁላችን ላይ ይደርብን ሀገራችንን ይጠብቅልን አሜን።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል #ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓል የሚከበርበት ምክንያት # ፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ #፪. ባሕራንን ያዳነበት ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጎረቤት ነበረው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሌ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡     ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጎ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት  ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር። ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጎዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጎልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያድርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው። ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ‹‹ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ›› ሲል ጠየቀው ልጁም ‹‹እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ›› አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ‹‹ይህችን መልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው፤ ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ›› የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ በአገልጋዩ (በሹሙ)ና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆን ስንቅ ሰጠው ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው ባሕራንም ‹‹ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ እየሄድኩ ነው›› አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል›› አለው መልአኩም ‹‹እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ›› አለው ባሕራንም አሳየው ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ ‹‹ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ›› ይልና ‹‹ይህን መልእክት ይዞ ለመጣው ሰው ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን ፥ በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ›› የሚል ጽሑፍ ጻፈበት "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ አለው ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ ጉዞውን ቀጠለናዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።