ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
611
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-930 天
帖子存档
መስከረም 29 ✝️

🌹 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹         🌹 #መስከረም ፳፱ (29) ቀን። 🌹 እንኳን #ለታላቋ_ሰማዕት_ለቅድስት_አርሴማ #ለእመቤቷ_አጋታና_ለደናግል_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሐዋርያው ለነባቤ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ለፈለሰበተ ሥጋው  መታሰቢያ  በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከጌታችንና_መድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም በሥጋ #ከተወለደበት_ከልደቱ_ከበዓለ ወልደ ከወራዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                          ✝ ✝ ✝ 🌹 #ታላቋ_ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ እና #እመምኔቷ_ቅድስት_አጋታና_ደናግል፦ ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ። 🌹 እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ። 🌹 ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው። 🌹 ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት። የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። "ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው"። 🌹 ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ። 🌹 አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ። 🌹 ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አርሴማና በቅዱሳን ሰማዕታት ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 29 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ 🌹 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ይትፌሥሐ አድባረ ጽዮን። ወትሐሠያ አዋልደ ይሁዳ። በእንተ ፍትሕከ እግዚኦ"። መዝ 47፥11-12  የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥1-14 ወይም ሉቃ 21፥21-ፍ.ም።                            ✝ ✝ ✝ 🌹 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ። ወአነ ዮም ወለድኩከ። ሰአል እምኔየ እሁበከ አሕዛበ ለርስትከ። መዝ 2፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥21-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅድስት አርሴማ የዕረፍት በዓል፣ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የፍልሠተ ሥጋው መታሰቢያ በዓል ሁላችንም ይሁንልን።           

                           ✝ ✝ ✝ 🌹 #ቅዱስ_አባዲርና_ቅድስት_እኅቱ_ኢራኢ፦ ይህም ቅዱስ ለአንጾኪያ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ለሆነ ለፋሲለደስ የእኅቱ ልጅ ነው እርሱም በአባቱ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ነበር በውስጡም የሚጸልይበት እልፍኝ አለው። ከሌሊቱም እኩሌታ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና እንዲህ አለው "የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ እኅትህ ኢራኢን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ። ስለ ሥጋችሁም እንዲአስብ ሳሙኤል የሚባለውን አንድ ሰው እኔ አዛለሁ" ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥቶት በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። 🌹 እንዲሁ ለእኅቱ ኢራኢ ተገልጦላት እንዲህ አላት "የወንድምሽን ቃሉን ስሚው ትእዛዙንም አትተላለፊ" ከእንቅልፏም ነቅታ እጅግ ተንቀጠቀጠች ወደ ወንድሟም ሒዳ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተገለጠላትና እንደ ተናገራት አስረዳችው። እጅግም ደስ አላቸው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስም ስለ ስሙ ወደ ግብጽ አገር ሒደው ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ በዚህ ምክር ተስማሙ። 🌹 የቅዱስ አባዲር እናትም ይህን ነገር በአወቀች ጊዜ ልብሷን ቀዳ አለቀሰች ከባሮቿም ጋር ወደ ቅዱስ አባዲር መጥታ በሰማዕትነት እንዳይሞት ታምለው ጀመር እርሱም ስለ ሰማዕትነት ነገር ዲዮቅልጥያኖስን እንዳይናገረው ማለላት በዚያንም ጊዜ ከልቅሶዋ ታግሣ ጸጥ አለች። ወደ ሌላ ቦታ ሒዶ በሰማዕትነት እንደሚሞት ግን አላሰበችም። ቅዱስ አባዲርም በየሌሊቱ ሁሉ እንዲህ የሚያደርግ ሆነ ልብሱንም ለውጦ ከቤቱ ይወጣል በወህኒ ቤት ላሉ እሥረኞችም ውኃ በመቅዳት ያጥባቸዋል እስከሚነጋም እንዲህ ያደርጋል በር የሚጠብቀውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው "ይህን ለማንም አትናገር ይህንንም ሥራ ብትገልጥ እኔ ራስህን በሰይፍ እቆርጣለሁ"። 🌹 ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባዲር ተነሣ እኅቱን ኢራኢንም ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሒዶ እስክንድርያ ደረሰ። ከወታደሮችም ያወቁት አሉ "አንተ የሠራዊት አለቃ ጌታችን አባዲር አይደለህም እንዴ" አሉት። እርሱም ፈገግ ብሎ "ብዙዎች እንዲሁ ይሉኛል እኔ ግን እመስለው ይሆናል እንጂ እርሱን አይደለሁም" አላቸው ከዚያም ወደ ሌላ ቦታ ሔደ። በዚያም እንደቀድሞው እርሱ አባዲር እንደ ሆነ ተናገሩት እርሱም አይደለሁም ይላቸው ነበር። 🌹 ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ከተማ ወጥቶ ወደ ታላቋ የምስር ከተማ ሔደ በዚያም ከአባ አበከረዙን ጋር ተገናኝተው ከእርሱ ቡራኬ ተቀበሉ። ከዚያም ወደ እስሙናይን ደርሰው ከዲያቆን ሳሙኤል ጋር ተገናኙ በማግሥቱም ወደ እንጽና ከተማ ሔዱ በመኰንን አርያኖስም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመኑ። መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃያቸው ጀመረ ቅዱስ አባዲርም በሥቃይ ውስጥ ያጸናቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ያን ጊዜ ጌታችን የእርሱን ነፍስና የእኅቱን ነፍስ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወስዶ ሰማዕታት የሚኖሩበትን የብርሃን ቤቶችን አሳያቸውና ከዚህም በኋላ ወደ ሥጋቸው መለሳቸው። 🌹 መኰንኑም ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሳቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ራሳቸውንም ከሚቆርጧቸው በፊት መኰንኑ አርያኖስ ቅዱስ አባዲርን እንዲህ አለው "አንተ ማን እንደሆንክ ስምህም ማን እንደሆነ አንተም ከወዴት እንደሆንክ ትነግረኝ ዘንድ በፈጣሪህ አምልሃለሁ" አለው። ቅዱስ አባዲርም "በነገርኩህ ጊዜ ራሳችንን እንዲቆርጡ ያዘዝከውን ትእዛዝ እንዳትለውጥ አንተም ማልልኝ" አለው መኰንኑም ማለለት ያን ጊዜም "የሠራዊት አለቃ እኔ አባዲር ነኝ" አለው መኰንኑ አርያኖስም እንዲህ ብሎ ጮኸ "ወዮልኝ ጌታዬ ሆይ በአንተ ፈንታ እኔ ልሞት ይገባኛል ይህን ሁሉ ጽኑ ሥቃይ እስከ አሠቃየሁህ ድረስ አንተ ጌታዬ እንደሆንክ እንዴት አላስረዳኸኝም ቅዱስ አባዲርም አንተም እንደኔ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ አለህና አትዘን አሁንም ምስክርነታችንን በፍጥነት ፈጽም" ብሎ መለሰለት። 🌹 በዚያንም ጊዜ ራሳቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አርያኖስ አዘዘና እርሱንና እኅቱ ኢራኢን ቆረጧቸው። ያማሩ ልብሶችንም ዘርግተው ገነዙአቸው ዲያቆን ሳሙኤልም የመከራው ወራት እስከሚያልፍ ወደ ቤቱ ወስዶ አኖራቸው ከዚያም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ታነፀችላቸውና ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በአባዲርና በእኅቱ ኢራኢ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 28 ስንክሳር።                                                                            ✝ ✝ ✝ 🌹 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለእንስሳ። ወለእጒለ ቋዓት እለ ይጼውዕዎ። ኢይፈቅድ ኃይለ ፈረሰ"። መዝ 146፥9-10 የሚነበበው ወንጌል 12፥22-32።                              ✝ ✝ ✝ 🌹 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ 55፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-22፣ 2ኛ ያዕ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 12፥12-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥3-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።