ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
608
订阅者
-124 小时
-37 天
-1130 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ #ለኖላዊ  መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ በ፪ "#ኖላዊ_ዘመጽአ_ውስተ_ዓለም ወልዱ ወቃሉ #ለእግዚአብሔር፤ ዘወረደ እምላዕሉ በአቅሙ #ክርስቶስ፤ እስመ ውእቱ #እግዚአ_ለሰንበት፤ ይቤሎ #አብ_ለወልዱ_ወልድየ_ንበር_በየማንየ። ትርጉም፦ ወደ ዓለም የመጣው #እረኛ_የእግዚአብሔር_አብ ቃሉና ልጁ ነው ከላይ የወረደውም #ክርስቶስ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው። (ፍጹመ አካል ፍጹመ ክብር ነው) #የሰንበት_ጌታ እሱ ነውና #አብ_ልጁን_ልጄ_በቀኜ_ተቀመጥ_አለው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                                        ❤ " #ኖላዊ_ኄር " ❤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 21 ይህችን ዕለት "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች። ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች (ከታኅሣሥ 21-27)። በነዚህ ቀናች እሑድ የዋለበት ቀን ማኅሌት ተቆሞ ኖላዊ ተብሎ ይከበራል። መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10፥1) ነው። "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር-ርሕሩሕ-አዛኝ" እንደ ማለት ነው። ❤ ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል። ከአባታችን አዳም ስህተት በኋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው። እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ። ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር። ❤ ኤዶም ገነት የለመለመች። ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና። አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር። ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ። ❤ እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ። ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው። ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ። ከሴ፣ ኄኖስ፣ ከኄኖስ፣ ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ። ❤ ከኖኅም በሴም ከአብርሃም፣ ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ። ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ። እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም። ❤ ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው። "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ። (መዝ. 79:1) ❤ ጩኸቱም ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ። ይህንን የሰማ ጌታም በጊዜው ከድንግል ማርያም ተወለደ። በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ። መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው። ❤ ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5፥36, ዮሐ. 10፥8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ። እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ 10፥7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ። ❤ እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ 10፥11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል። በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት መንጋው (በጐቹ) ከኋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው። ❤ መድኃኒታችን ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን፤ በመራቆቱ የጸጋ ልብስን፤ በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ። ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ ጌታ (ዘፍ 1፥1, ዮሐ. 1፥2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን። ❤ በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን፤ ሐዋርያትን (ዮሐ 21፥15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ 20፥28) ካህናትን (ማቴ 18፥18) ሾመልን። እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ። እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻም የክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም፤ ኃላፊነቱም አለባቸው። (ማቴ 28፥19) ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ፔጅ።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዚህ_ሳምንት_ምስባክ፦ "ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ። ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ። ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ"። መዝ 79፥1። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 13፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥22-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የኖላዊ በዓል፣ ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

ሁላችንም የሰንበት ት/ቤት አባላት የመገኘት ግዴታ አለብን ለራሳችንም አገልግሎት ምንድን ነው ገብቶንስ ነው ወይ እያገለገልን ያለነው መዘመር ብቻ ነው አገልግሎት ??? ስለ ሁሉም መንፈሳዊ አገልገሎቶ
ሁላችንም የሰንበት ት/ቤት አባላት የመገኘት ግዴታ አለብን ለራሳችንም አገልግሎት ምንድን ነው ገብቶንስ ነው ወይ እያገለገልን ያለነው መዘመር ብቻ ነው አገልግሎት ??? ስለ ሁሉም መንፈሳዊ አገልገሎቶች በአባቶች ግሩም ነገር ስለሚነገረን በሰዓቱ እንገኝ እና እራሳችንን እናሻሻልበት ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን🙏

ታሕሳስ ፳፮ /26/ በዚች ቀን ከሮሜ አገር የከበረች አንስጣስያ በሰማዕትነት አረፈች። የዚችም ቅድስት አባቷ ጣዖትን የሚያመልክ ነው እናቷ ግን ክርስቲያን ናት ይቺንም ቅድስት በወለደቻት ጊዜ አባቷ
ታሕሳስ ፳፮ /26/
በዚች ቀን ከሮሜ አገር የከበረች አንስጣስያ በሰማዕትነት አረፈች። የዚችም ቅድስት አባቷ ጣዖትን የሚያመልክ ነው እናቷ ግን ክርስቲያን ናት ይቺንም ቅድስት በወለደቻት ጊዜ አባቷ ሳያውቅ የክርስትና ጥምቀትን በሥውር አጠመቀቻት።በቀናች ሃይማኖት እስከ አጸናቻት ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረቻት። አድጋ አካለ መጠን በአደረሰችም ጊዜ አባቷ እንደርሱ ላለ ከሀዲ ሰው አጋባት እርሷ ግን እጅግ ጠላችው ልትገናኘውም አልፈለገችም በሴቶች ላይ በሚሆነው ግዳጅና አንዳንድ ጊዜም በደዌ የምታመካኝ ሆነች እንዲጠላትና ከእርሷ እንዲለይ ያደፈና የቆሸሸ የተጐሳቈለ ልብስ ትለብስ ነበር። ባሏም ወደ ሥራው ወጥቶ በተሰማራ ጊዜ እርሷም ስለ ቀናች ሃይማኖት የታሠሩ እስረኞችን ትጐበኝ ዘንድ ትሰማራለች ታገለግላቸውና የሚሹትን ትሰጣቸዋለች። ባሏም ይህን የምትሠራውን በአወቀ ጊዜ ወደ ውጭ እንዳትወጣ በቤት ውስጥ ዘጋባት እርሷም ከእጁ ያወጣት ዘንድ አዘውትራ በመረረ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር የምትለምን ሆነች ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ያንን ሰው አጠፋው። እርሷም በሞቱ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ለድኆችና ለምስኪኖች ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመታመን ለታሠሩ እሥረኞች ገንዘቧን ሁሉ ሰጠች። የሮሜ ንጉስም ዜናዋን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣት ስለ ሃይማኖቷም ጠየቃት ክርስቲያን እንደሆነች ተናገረች ሊደልላት ቢሞክርም አልተሳካለትም። ከዚህም በኋላ በብዙ አሰቃያት በመጨረሻም የእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሯት ዘንድ አዘዘ በጨመሯትም ጊዜ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

Repost from N/a
እዚህን የመሰሉ ጌታችን የተወለደበት ምሣሌ የሆነውን ግርግም ገዝተው በዓሉን ያክብሩ በተለያየ size ለማዘዝ በ 0907176727 0945455578 ይደውሉ ባሉበትም እናደርሳለን
እዚህን የመሰሉ ጌታችን የተወለደበት ምሣሌ የሆነውን ግርግም ገዝተው በዓሉን ያክብሩ በተለያየ size ለማዘዝ በ 0907176727 0945455578 ይደውሉ ባሉበትም እናደርሳለን

ታሕሳስ ፳፭ /25/
በዚችም ዕለት በሚዶናውያንና በሞዓባውያን ዘመነ መንግሥት የከበሩ አምስቱ መቃባውያን በሰማዕትነት ሞቱ። ክፋትን የሚወዳት ስሙ ጺሩጻይዳን የሚባል አንድ ንጉሥ ነበረ። የሚያመልካቸውም ኃምሳ በወንዶች ሃያ በሴቶች አምሳል የተሠሩ ጣዖቶች አሉት በጥዋትና በማታ መሥዋዕትን ያቀርብላቸዋል ሰዎችንም እንዲሠዉ ያስገድዳቸው ነበር። ከብንያም ወገንም የሆነ ስሙ መቃቢስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ለርሱም መልከ መልካሞች የጸኑ ሦስት ልጆች አሉት ከእርሳቸውም ግሥላውን እንደ ዶሮ አንቆ የሚገድል አለ ። በአንዲት ዓመታትም አንበሳ የሚገድል አለ። በአንድ ጊዜ ሰይፍ መዘዛም በሰልፍ ውስጥ መቶ ሰው የሚገድል አለ እነርሱም ውበትንና ግርማን የተሸለሙ ናቸው። ከሁሉ የሚሻል እነርሱ የሥጋ ሞትን ያልፈሩ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ናቸውና ንጉሡም እናንት ዓመፀኞች ለአማልክቶቼ እንዴት አትሰግዱም አላቸው። እነሱም በአንድ ቃል እኛ ለረከሱ አማልክቶችህ አንሰግድም እኛንም አንተንም ለፈጠረ ሕዝቡንም በዕውነትና በቅንነት ትጠብቅ ዘንድ ላነገሠህ አንተ ግን ቸለል ብለህ ለዘነጋኸው እግዚአብሔር እንሰግዳለን እንጂ ብለው መለሱለት። ከዚህም በኋላ የተራቡ አራዊትን በላያቸው እንዲሰዱ አዘዘ እነዚያም ለቅዱሳን ሰግደው ተመልሰው ከከሀድያን ሰባ አምስት ሰዎችን ገደሉ በጭንቅም ወደማደሪያቸው መለሱአቸው። እሊህንም ቅዱሳን ወደ ወህኒ ቤት ጨመሩአቸው ሌሎች ሁለት ወንድ ሞቻቸውም መጥተው ከእነርሱ ጋር ቀላቀሉ። ንጉሡም አምስቱን ወንድማማቾች አይቶ እጅግ ተቆጥቶ ከሚነድ እሳት ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ አስረከቡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

❤️ አባ ጳውሊም ይህን ባየ ጊዜ ስለ ኃጢአታቸው በጣም አዝኖ "ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?" ቢላቸው እነርሱም "አባቶቻችን ያዘዙን ትእዛዝና ባሕላችን ነው" አሉት፡፡ አባ ጳውሊም ወደዚያ ቤት ሲገቡ አይቶ እጅግ በማዘን ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡ ጸሎቱንም እንደፈጸመ አንድ ጥቁር ሰው ከዝሙት ቤቱ ዕራቁቱን ሆኖ የእሳት ሰይፍ ተሸክሞ መጣ፡፡ አባ ጳውሊም ካማተበበት በኋላ "አንተ ማነህ? ማንንስ ትሻለህ?" አሉት፡፡ ጥቁሩም ሰው "እኔ ሰይጣን ነኝ፣ አንተ ወደ ጌታህ በለመንህ ጊዜ ላከኝ" አለው፡፡ አባ ጳውሊም "የምታስትበትን ነገር ሁሉ ትነግረኝ ዘንድ እጠይቅሃለሁ" አለው፡፡ ሰይጣንም "የምትሻውን ጠይቀኝ" አለው፡፡ አባም "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ በሰው ላይ ታድር ዘንድ ምክንያት እንዴት ታገኛለህ?" አለው፡፡ ሰይጣንም "ሰው በእግዚአብሔር ሕግ ጸንቶ ሳለ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም በጠራ ጊዜና በንጽሕና ሆኖ የክርስቶስ ሥጋና ደምን በሚቀበል ሰው ላይ ለማደር ሥልጣን የለኝም" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ የሚያስትበትን ሁሉ በዝርዝር ነገረው፡፡ ሊቀ ጳጳሳትን፣ ጳጳሳትን፣ መነኮሳትን፣ መእመናንን፣ ባለትዳሮችን፣ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችና ሕፃናትን…ሁሉንም ነገር እያንዳንዱን በምን በምን እንደሚያስት ሁሉንም ነገር በዝርዝር ነገረው፡፡ ወዲያውም የሰይጣን መልኩ ተለውጦ እንደ እሳት ነበልባል ሲሆን አባ ጳውሊ ተመልክቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ቅጽበት የታዘዘ መልአክ መጥቶ አባ ጳውሊን አበረታው፡፡ ❤️ በዚያችም ሌሊት መቅሰፍት ወርዶ በዝሙት ቤት ያሉትን አጠፋቸው፡፡ ከ5 ወንዶችና ከ5 ሴቶች በቀር የተረፈ የለም፡፡ አባ ጳውሊም "ይህን ለምን ታደርጋላችሁ?" ቢላቸው "በየወሩ አንዲት ቀን ወደ ውሽባ ቤት እየገባን በሩን ዘግተን መብራት አጥፍተን ከእጃችን የገባችዋን ሴት ይዘን አንተኛለን" አሉት፡፡ "ከእናንተ ውስጥ እኅቱን ወይም ልጁን እንዴት ያውቃል?" አላቸው፡፡ "እንደ እንስሳ በመሆን እንጃ ማወቅ የለም" አሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን የክርስቶስን ወንጌል ሰበከላቸውና አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ ሥጋ ወደሙንም አቀበላቸው፡፡ በሃይማኖት ካጸናቸው በኋላ ወደ በዓቱ ተመልሶ ገድሉን ፈጽሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳውለመ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አባ_ፊሎንጎስ፡- ይኽም ቅዱስ አስቀድሞ ሚስት አግብቶ አንዲት ልጅ ወለደ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስቱ ሞተች፡፡ እርሱም ከዚህ በኋላ የምንኩስና ልብስ ለብሶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ኖረ፡፡ ስለ መልካም ተጋድሎውትና ስለ ትሩፋቱ በአገልግሎትም ስለመጠመዱ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው፡፡ በተሾመም ጊዜ የክርስቶስን መንጋዮች ምእመናንን በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው፡፡ ከአርዮሳውያን ከመቅዶንዮስና ከሰባልዮስ ነጣቂ ተኩላዎች በሚገባ ጠበቃቸው፡፡ በሊቀ ጵጵስናውም የሹመት ወቅት አኗኗሩን እንደ መላእክት አደረገ፡፡ መልካም የሆነ ገድሉንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ24 ስንክሳር።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አድኅነኒ እምደም እግዚአብሔር አምላክ መድኃኒትየ። ይትፌሣሕ ልሳንየ በጽድቀ ዚአከ እግዚኦ። ትከሥት ከናፍርየ ወአፉየ ያየድዓ ስብሓቲከ። መዝ50፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ11፥25-ፍ.ም።                             ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ። በእንተ ጸላኢ። ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ"። መዝ 8፥2። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 4፥11-17፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 19፥11-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

የከበረ አግናጥዮስም ተቆጥቶ "ንጉሥ ሆይ ከንቱ የሆነ ጣዖትን ከማምለክ ሰዎችን ስለሳብኳቸውና ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ስለአስገባኋቸው በእኔ ላይ ትቆጣለህን ለረከሱ ጣዖቶችህስ እንድሠዋ ታዘኛለህን እኔ ግን ቃልህን ተቀብዬ ለሰይጣናት አልሠዋም ለእውነተኛ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሠዋለሁ እንጂ" አለው። ❤️ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ተቆጣ ከሥጋው ምንም ምን ሳያስቀሩ ይበሉት ዘንድ ሁለት የተራቡ አንበሶችን በላዩ እንዲሰዱ አዘዘ። የከበረ አግናጥዮስም አንበሶች ወደርሱ ሲቀርቡ በአያቸው ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሕዝብን እንዲህ አላቸው "ከዚህ የተሰበሰባችሁ እናንተ የሮሜ ሰዎች ቃሌን ስሙ እወቁም እኔ ይህን ሥቃይ የታገሥኩት በትዕቢትና በትምክህት አይደለም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ  ፍቅር እንጂ። አሁንም እኒህ አንበሶች እንደ ሥንዴ ይፈጩኝ ዘንድ ነፍሴ ወደደች የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ልትሔድ ነፍሴ ሽታለችና"። ❤️ ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ አደነቀ ድንጋጠረም አድሮበት እንዲህ አለ "የክርስቲያኖች ትዕግሥታቸው ምን ይብዛ ስለ አምልኮት ከአረማውያን በእንዲህ ያለ ሥቃይ ላይ የሚታገሥ ማን ነው" አለ። እነዚያ አንበሶችም ወደ ቅዱሱ ቀረብ ብለው ደንግጠው ቆሙ። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ እጁን ዘርግቶ አንገቱን ያዘው በዚያንም ጊዜ ደስ ብሎት ነፍሱን በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ ልመናውንም ፈጸመለት። ❤️ ለእነዚያ አንበሶችም ሥጋውን ይዳስሡት ዘንድ አልተቻላቸውም የክብር ባለቤት ክርስቶስ ዳግመኛ እስከ ሚመጣ የተጠበቀ ሆነ እንጂ ከዚህም በኋላ በክብር በምስጋና ከከተማ ውጭ ቀበሩት እንደዚህም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመልካም ተጋድሎ ምስክርነቱን ፈጸመ ለምእመናንም ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ገድሉን ጻፉ የበዓሉንም መታሰቢያ አደረጉለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ በቅዱስ አግናጥዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የአሚናዳብ_ልጅ_ቅድስት_አስቴር፡- የአይሁድ ወገን የሚሆን ስሙ መርዶክዮስ የሚባል የኢያኤሩ ልጅ ከብንያም ወገን የተወለደ የቄስዩ ልጅ አንድ ሰው በሱሳ አገር ነበረ፡፡ ከኢሩሳሌምም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ የተማረከ ነው፡፡ ያሳደጋት ልጅ ነበረችው፡፡ እርሷም የአባቱ ወንድም የአሚናዳብ ልጅ አስቴር ናት፡፡ ከዘመዶቿ ተለይታ በወጣች ጊዜ ልጅ ትሆነው ዘንድ አሳደጋት፡፡ እርሷም እጅግ መልከ መልካም ነበረች፡፡ በአንዲትም ዕለት ንጉሥ አርጢክስስ ብዙ ተድላ ደስታ አድርጎ መኳንንቶቹን ሁሉ ጠራ፡፡ የመኳንንቶቹንም አለቃ አማሌቃዊውን ሐማንንም ጠራው፡፡ እርሱ ከሁሉም መኳንንት የከበረ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሥ 7ቱን ባለሟሎቹን ጠርቶ ንግሥቲቱን አስጢንን አምጥተው የእቴጌነት ዘውድ ያቀዳጇት ዘንድ እርሷ መልከ መልካም ናትና ለአሕዛብም አለቆች ሁሉ መልኳንና ውበቷን ያሳዩ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ንግሥቲቱ አስጢን ግን የንጉሡን ትእዛዝ ባለመቀበል እምቢ አለች፡፡ ከባለሟሎቿም ጋር ትመጣ ዘንድ ባለወደደች ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተናዶ ከንግሥትነቷ ሻራት፡፡ ከዚህም በኋላ 127 ከሚሆኑ ከሚገዘቸው አገሮች አንድ ሺህ ቆነጃጅቶችን ይመርጡለት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ ከሺህ መቶ፣ ከመቶ ዓሥር፣ ከዓሥር ሦስት መረጡ፡፡ ከሁሉም በመልክ፣ በውበት፣ በደም ግባትም አንደኛ ሆና አስቴር ተመረጠች፡፡ ንጉሡም አስቴርን አነገሣት፡፡        ❤️ ንጉሡም አስቴርን እጅግ አድርጎ ወደዳት፣ በሴቶቹም ሁሉ ላይ የበላይ አድርጎ ሾማት፡፡ ከዚህም አስቀድሞ መርዶክዮስ አገሩንና አደባባዩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ ባለሟሎች ጋር በአደባባይ ኖረ፡፡ እነርሱም ስማቸው ታራ እና ገቦታ ይባላል፡፡ እርሱም እነዚህ ሁለቱ በንጉሡ ላይ ያሰቡትን ተንኮላቸውን ሰማ፡፡ ንጉሥ አርጤክስስን ይገድሉት ዘንድ ወንጀልን እንዳዘጋጁ ባወቀ ጊዜ መርዶክዮስ ሄዶ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገራቸውን መርምሮ ቀጣቸውና ይህን ነገር ታሪክና ወግ በሚጻፍበት ላይ ጻፈው፡፡ ሐማ ግን አማሌቃዊ ነበረና መርዶክዮስንና እስራኤላውያንን ይጠላቸው እጅግ ነበርና የአይሁድን ወገን ሁሉ ለማጥፋት ተነሣ፡፡ መርዶክዮስም ይህንን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፡፡ መርዶክዮስም የሀዘኑን መርዶ ለአስቴር እንዲደርሳት አደረገ፡፡ አስቴርም "እስከ ሦስት ቀን ጹሙ ጸልዩ እኔም ደንገጡሮቼም እንጾማለን" ብላ ላከችለት፡፡ ሱባኤዋንም እንደጨረሰች የማቅ ልብሷን አውልቃ ጥላ ወደ ንጉሡ አዳራሽ በገባች ጊዜ "እስከ መንግሥቴም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁና የሆንሽውን ንገሪኝ" አላት፡፡ በዓልንም አደረገና ሐማንና መኳንንቱን ሁሉ ጠራ፡፡ በበዓሉም ላይ ድጋሚ "ላደርግልሽ ፈቅጂውን ንገሪኝ" አላት፡፡ ❤️ ንጉሡም ለመርዶክዮስ ውለታ ያደረገለትን ሲያስብ ምንም እንዳላደረገለት ዐወቀ፡፡ ወዲያውም ሐማ መርዶክዮስን በመስቀል ላይ ሰቅሎ ሊገድለው እንደሆነ ተነገረ፡፡ ንጉሡም ሐማን "ንጉሥ የወደደውን ሰው ምን ያደርግለት ዘንድ ይገባል?" አለው፡፡ ሐማም "ይህስ ለእኔ ነው" ብሎ "በክብር ይሾም ዘንድ ሹመቱም አዋጅ ይነገርለት ዘንድ ይገባዋል" አለ፡፡ ንጉሡም ለሐማ ይህን ጊዜ "መልካም ተናግረሃል፣ ለመርዶክዮስ እንዲሁ ይደረግለታል" አለው፡፡ ሐማም የንጉሡን ትእዛዝ ተቀብሎ መርዶክዮስን በፈረስ አስቀምጦ በከተማው በማዞር በክብር መሾሙን በአዋጅ አስነገረለት፡፡ ❤️ ከዚህም በኋላ ንጉሡና አስቴር ለማዕድ አብረው በተቀመጡ ጊዜ ንጉሡ "ጉዳይሽን የማትነግሪኝ ለምንድነው?" አላት፡፡ እሷም ይህን ጊዜ "ንጉሥ ሆይ ዝም ባልኩ በወደድኩ ነበር ነግር ግን ወገኖቼና እኔ ለሞት ተላልፈን ተሰጥተናል" በማለት ሐማ እስራኤላውያንን በአዋጅ ሊያጠፋ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም "ማነው ይህን በማድረግ የደፈረኝ?" አላት፡፡ እሷም ሐማ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም ሐማ መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው መስቀል ላይ ራሱ ሐማን እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ሐማም ተሰቅሎ ሞተ፡፡ የእስራኤል ወገኖችም ሁሉ በጻድቂቱ አስቴር መዳናቸው በእርሷ ተደርጓልና ሁሉም አመሰገኗት፡፡ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡  የእስራኤል ወገኖች ሁሉ ድኅነታቸው በእርሷ ተደርጓልና ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አቡነ_ጳውሊ_ዘሀገረ_ሰሎንቅያ፡- ሰሎንቅያ በምትባል በምስር አገር ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ያነጋገሩትና ብዙ ምሥጢርን እንዲናገር ያደረጉት ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የሰሎንቅያ አገር ሰዎች የሄሮድስ ወገን የሆኑ ክፉዎች ናቸው፡፡ ከዱሮ ጀምረው ሴቶችና ወንዶች ሆነው በጋራ በአንድነት ወደ አንድ ክፍል ገብተው እንስሳዊ ግብራቸውን ይፈጽማሉ፡፡ ብዙ ሆነው ገብተው በሩን ዘግተው መብራት አጥፍተው በእጃቸው የገባውን ይዘው ያድራሉ፡፡ እኅቱም ትሁን ልጁ ወደዚያ ቤት የገባ ሰው ሌላውን አይለየውም፡፡ ይህም ሰይጣናዊ ተግባራቸው ባሕላቸው ሆኖ በወር አንድ ጊዜ ያደርጉታል፡፡

❤️ ከዚህም በኋላ አስታውሱት ከወህኒቤትም አውጥተው በንጉሡ ፊት አቆሙት ንጉሡም "አግናጥዮስ ሆይ አማልክቶቼን ብታያቸው ውበታቸው ባማረህ ነበር" አለው። ቅዱሱም "ንጉሥ ሆይ አንተ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ብታምን ሙታኖችን የምታሥነሣቸው በሽተኞችንም የምትፈውሳቸው ባደረገህ ነበር"። ንጉሡም "ለፀሐይ ከመስገድ የተሻለ የለም" አለ የከበረ አግናጥዮስም "መንግሥቱ የማያልቀውን ፈጣሪ ትተህ ለተፈጠረ ፀሐይ ትሰግዳለህን?" ብሎ መለሰ ንጉሡም "ለራስህ መልካም አልክ ግን በመተላለፍ የአንጾኪያና የሶርያን ሰዎች ስበሕ ወደ ክርስቶስ አምልኮት አስገባሃቸው እንጂ" አለው።

❤️ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️          ❤️ #ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን። ❤️ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት ለልደት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰሎንቅያ በምትባል በምስ አገር ለሆኑ ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ላነጋገሩ ለታላቁ አባት #ለአባ_ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ ለአሚናዳብ ልጅ ለጻድቂቱ #ለቅድስት_አስቴር ለዕረፍቷ መታሰቢያና ከዘጠኙ ቅዱሳንን ከፊሎች እነ አቡነ አረጋዊን ላመነኰሱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎድሮስ_ኃይለ_መነኰስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳስ ከከበረ ከአባት #ከአባ_ፊሎንጎስ ዕረፍት፣ የእግዚአብሔር መልአክ ከነገራቸው #በከዲህ_ከአሉ_ጻድቃን በአንዲት ቀን ዕረፍታቸው ከሆነና ከአዝቂርም ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #የአባታችን_የአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ልደት፦ ... ከዚህም ቀጥሎ ከዘጠኝ ወር በኋላ በታኅሣሥ በሃያ አራት ቀን ፍስሐ ጽዮን ተወለደ። በዚያችም ቀን በጸጋ ዘአብ ቤት ታላቅ ደስታ ተደረገ መካን የነበረች ሚስቱ እግዚእ ኃረያ ወንድ ልጅ ወልዳለችና። መልኩ እጅግ ድንቅ ነው እንደ ብርሌ እንደ መስታወት የሚያንጸባርቅ ነው። ቅላቱም እንደ ጽጌ ረዳ ነው ለነዳያንም ግብዣ አድርገው ዋሉ። ለአገራቸውም ሰዎች እንደየማዕርጋቸው ምሳ አደረጉላቸው። ❤️ በዓሉንም ካከበሩ በኋላ ለእግዚእ ኃረያና ለጸጋ ዘአብ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን በጐ ሥራውን ሁሉ እያደነቁ ወደ የቤታቸው ተመልሰው ገቡ። ይህም እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችውም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው ቀን በዕለተ ሰንበት ማለት ነው። ከቀኑ በሦስት ሰዓት ይህ ብላቴና እጆቹን አንሥቶ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እግዚአብሔርን በማመስገን እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ "ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በህልውና አንድ የሚሆን አብ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በባህሪይ በሕልውና አንድ የሚሆን ወልድ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከወልድ ጋር በባህርይ በሕልውና አንድ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ አመሰገነ። ❤️ በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደበት ስለሚወርድ ሕፃኑም መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ አይቶ እሱ እንዳስተማረው ለፈጣሪው እየተገዛ ይህን ሦስት የምስጋና ቃል አቀረበ። እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ልዩ ምስጋና ሰምታ በልቡናዋ እያደነቀች "ልጄ ፍሥሐ ጽዮን ምን ትላለህ ይህ ቃል የአባትህ ሥራ ነው። ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት ነውና"። ባሏ ጸጋ ዘአብ ተመልሶ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ልጁ የተናገረውን ነገር ሁሉ ነገረች። ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀና "ልጄ እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ። በቤተ እግዚአብሔርም እንዲህ እያልክ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለሁ" አለ። ❤️ ይህንም ብላቴና መላእክት ክንፋቸውን እየጋረዱ ዘወትር ይመግቡታል። እርሱም ክንፋቸውን ሲጋርዱት ባያቸው ጊዜ ከእነሱ ጋራ ይጫወት ነበር። ሁል ጊዜ ይስቅ ነበር እንጂ ሕፃናት እንደ ሚያለቅሱ አያለቅስም ነበር ቅኖች ሰዎች ዘወትር ደስ ይላችዋልና። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ም16።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #አቡነ_ቴዎድሮስ_ኃያል_መነኰስ፦ አገራቸው ሮም ሲሆን በ27 ዓመታቸው በአባ ጳውሊ እጅ መነኰሱ። የታላቁ አባት ጳኲሚስ ረዳት የነበሩ ሲሆን መጽሐፍ ሊቀ ጳጳሳትም ይላቸዋል። የመነኰሳት ቁጥር ከጀመሠሪው ከአባ እንጦስ እስከ ቴዎድሮስን ያለው ትውልድ ይባላል። በድንቅ ተአምረሠታቸው ዓለምን ያደነቃቸው ተሰዓቱ ቅዱሳን የተነሱት በዚህ ጻድቅ መናኝ ጊዜ ስለነበር ከፊሎቹንም ያመነኰሷቸው እሳቸው ናቸው። ይለብሱት የነበረው የብረት ልብስ ነበር። ❤️ እንጦስ በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል እጀሰ መነኰሱ፤ እንጦንስም መቃርስን አመነኰሱ፤ መቃርስም ጳኲሚስን አመነኰሱ፤ ጳኲሚስም እኚህን ታላቅ መነኰስ ቴዎድሮስን አመነኰሱ። እርሳቸውም እነ አቡነ አረጋወመንና ሌሎቹንመሰ ቅዱሳን አመነኰሰዋል። ❤️ በዐፄ ገላውዲዮስና በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን ወደ አገራችን የገባውን ቅዱስ ገድላቸውን ፊልክሲዮስ፣ ገብረ ክርስቶስ፣ አረጋዊና መንፈሳዊና ማር ይስሐቅ ናቸው የተረጐሙት።ጻድቁ የተወለዱባትን ሮምን በከሃዲነቷ በእጅጉ ይጠሏት ነበር። ሮም የእነ ልዮንን የኑፋቄ ትምህርተሰ ተከትላ ሁለት ባሕሪይ በማለቷ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ሆነው አውግዘዋል። በስማቸው የተሠሩ ቤተ ክርስቲያኖች በጎንደር በትግራይ ሁለት አሉ። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤️ #ቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ፦ ይህም ቅዱስ የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙሩ ነው። በስብከተ ወንጌልም በማገልገል ከእርሱ ጋር ብዙ አገሮችን ዙሮ አስተምሮአል ከዚህም በኋላ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው በውስጥዋመሰ ሕይወተሰ የሆነ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ብዙዎችንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በትምህርቱም ልቡናቸውን አበራላቸው። ❤️ ከዚህም በኋላ ጣዖትን ለሚያመልኩ ስሕተቻተውን በገለጠላቸው ጊዜ ተቆጡ። ወደ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጠራብዮስ ሔደው ከሰሱት እንዲህም አሉት "አግናጥዮስ የአማልክቶችህን አምልከሸ ይሽራል እኮን ሰዎችንም እያስተማረ ክርስቶስን ወደ ማመን ያስገባቸዋል"። በዚያንም ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስመጣውና "አግናጥዮስ ሆይ ለምን ይህን አደረግህ የአማልክቶቼን አምልኮስ ለምን ሻርክ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ አስገብተሃቸዋልና" አለው። አግናጥዮስም "ንጉሥ ሆይ ቢቻለኝስ ያክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ባስገባሁህ ነበር" አለው ንጉሡም "ይህን ነገር ትተህ ለአማልክቶቼ ሠዋ አለዚያ በታላቅ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። "በእኔ ላይ የምትሻውን አድርግ እኔ ግን ለረከሱ አማልክቶችህ አልሠዋም ሥቃይህንም እሳትም ቢሆን አንበሳንም ቢሆን አልፈራም ከሕያው ንጉሥ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው። ይህንንም ሲሰማ ንጉሡ ተቆጣ ያሠቃዩትም ዘንድ አዘዘ በተለያዩ በብዙ ሥቃዮችም አሠቀሠዩት በእጆቹም ውስጥ እሳት አድርገው ከእጆቹ ጋር በጉጠት ይዘው አቃጠሉት። ❤️ ከዚህም በኋላ በዲንና በቅባት እያነደዱ ጎኖቹን አቃጠሉ በሾተሎችም ሥጋውን ሠነጠቁ። ከማሠቃየትም በደከሙ ጊዜ የሚያደርጉበትን እስከመክሩ ድረስ ከወህኒ ቤት ጨመሩት ብዙ ቀኖችም በዚያ ኖረ።

❤ ቅዱስ ዳዊትም እጁን ወደ ድጉ ሰዶ አንዲት ደንጊያ አውጥቶ ወነጨፋት ያንንም ኢሎፍላዊ ግንባሩን ገመሰው ያቺም ደንጊያ  ከግንባሩ ገብታ ናላውን በጠበጠችው በምድር ላይም በግንባሩ ተደፋ። ዳዊትም ሩጦ የገዛ ሰይፉን አንሥቶ ራሱን ቆረጠው ከእስራኤልም ልጀጆች ስድብን አራቀ። ቅዱስ ዳዊትም መላው ዕድሜው ሰባ ነው መንግሥትን ሳይዝ ሠላሳ ዓመት ኖረ ከያዘ በኋላ አርባ ዓመት ኖረ። የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት በሽህ አንድ መቶ ሃያ ዓመት ውስጥ ትንቢት የተናገረበት ዘመን ነው በሰላምም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በልበ አምላክ በቅዱስ ዳዊት በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበሩ_ቅዱሳን_አባቶቻችን_አባ ሳሙኤል_አባ_ስምዖንና_አባ_ገብርኤል፡- አባ ሳሙኤል የተባለው ይኽም ቅዱስ ባሕታዊ ሆኖ ቀርጣሚን በምትባል አገር የሚኖር ነው፡፡ በዚያም አቅራፎስ የሚባል ሰማዕት ዐፅም ስለነበር ከእርሱ በረከትን እየተቀበለ እየተሳለመ ይኖር ነበር፡፡ ሰሊባ የሚባል አንድ መኮንን ነበር፡፡ እርሱም ስምዖን የሚባል ልጅ አለው፡፡ ልጁም ለሞት በሚያበቃ ጽኑ ሕማም ታመመ፡፡ መኮንኑ በልጁ ላይ ይጸልይ ዘንድ ወደ አባ ሳሜኤል ላከ፡፡ ነገር ግን አባ ሳሙኤል ሲደርስ ልጁ ሞቶ አገኘው፡፡ አባ ሳሙኤልም በጸሎቱ ከሞት አስነሣው፡፡ ልጁ ስምዖንም ከሞት ከተነሣ በኋላ የአባ ሳሙኤል ደቀመዝሙሩ ሆነ፡፡ ሁለቱም በጋራ በተጋድሎ አብረው ኖሩ፡፡ ❤ ቅዱስ ስምዖን ውኃ ሊቀዳ ሲሄድ ሰይጣን እንስራውን ሰበረበት፡፡ አባቱም ሌላ መቅጃ ቢሰጠው እርሱንም ሰበረበት፡፡ የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና ወደ ሌላ ቦታ ሄደው ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ አዘዛቸው፡፡ ንጉሥ አንስጣስዮስም ቤተ ክርስቲያኑን ሠራላቸው፡፡ እነርሱም ለመነኮሳትና ለነዳያን መኖሪያ 500 መኖሪያ ቤቶችን ሠሩ፡፡ አባ ሳሙኤልም ባረፈ ጊዜ መነኮሳት ልጆቹን ለአባ ስምዖን አስረክቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ መነኮሳቱም 12 ሺህ እስኪሆኑ ድረስ በዙ፡፡ አባ ስምዖንም በሚገባ ይመራቸው ነበር፡፡ በዘመኑም "ትንሣኤ ሙታን የለም" የሚል ሰይጣን በልቡ ያደረ አንድ መናፍቅ ተነሣ፡፡ አባ ስምዖንም ቢመክረውና ቢያስተምረው የማይለስ ሆነ፡፡ አባ ስምዖንም በሞተ ሰው ላይ ጸልዮ ያንን ሙት አስነሥቶ እንዲመሰክርለት ቢያደርገው አላምን አለው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ስምዖን ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያንን መናፍቅ አቃጠለውና ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ አባ ስምዖንም አገልግሎቱን ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ❤ ከአባ ስምዖንም በኋላ አባ ገብርኤል ተሹሞ መለኮሳቱን የሚጠብቅ እረኛ ሆነ፡፡ እርሱም ምግባሩ ያማረ ሃይማኖቱ የሰመረ በትሩፋት በተጋደሎ ያጌጠ ነው፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ፡፡ ከዕለታም በአንደኛው ቀን መነኮሳቱ ለእንጀራ ማቡኪያ የሚሆን እጅግ ትልቅ የሆነ የድንጋይ ገንዳ ወደ ገዳሙ ሊያስገቡ ቢሉ ከክብደቱ የተነሣ እምቢ አላቸው፡፡ አባ ገብርኤልም በዚህ ጊዜ በገዳሙ ያሉት ሁሉ ወጥተው እንዲራዱ በቃላቸው ባዘዙ ጊዜ 10 ሺህ ሰዎች ከሙታን ተነሡ፡፡ አባ ገብርኤልም ይህን አይቶ "እናንተን ያልኩ አይደለም በሕይወት ያሉትን ነው እንጂ" አሏቸውና ወዲያው ወደ መቃብራቸው ተመለሱ፡፡ ❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አንድ ሰው ብዙ የሆነ ወርቁን ከአንዱ መነኩሴ ዘንድ በአደራ አስቀምጦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፡፡ ሰውየውም በተመለሰ ጊዜ መነኩሴው ለማንም ሳይናገር በሞት ዐርፎ አገኘው፡፡ የመነኩሴውም ረድእ አባቱ ያስቀመጠበትን ቦታ እንዳልነገረው አስረዳ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ገብርኤል ወደሟቹ መነኩሴ መቃብር ሄዶ መቃብሩን ስለዚያ ወርቅ ጠየቀው፡፡ ሟቹም መነኮሴ ወርቁን ያኖረበትን ቦታ ለአባ ገብርኤል ነገረውና ወስዶ ለባለቤቱ ሰጠው፡፡ ባለወርቁም እጅግ እያደነቀ ወርቁን ተቀብሎ በሰላም ሄደ፡፡                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ጢሞቴዎስ፡- ደጋግ የሆኑ ወላጆቹ የቤተ ክርስቲያንን ትምህት እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ በደገም ጊዜ ዓለምን ንቆ መንሶ ገዳም በመግባት በተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ መጻተኞችንና ጦም አዳሪዎችን ይመግባቸው ዘንድ ከገዳሙ አቅራቢያ መኖሪያን አበጀ፡፡ ነዳያንንም እየመገበ በመንፈሳዊ ተጋድሎው እየጸና 5 ዓመት ያህል ከኖረ በኋላ የበጎ ነገር ጠላት የሆነ ሰይጣን በቅናት ተነሣበትና የእጅ ሥራውን ትገዛ ዘንድ አንዲት ጋለሞታን ወደ እርሱ አመጣበት፡፡ ❤ እርሷም ወደ አባ ጢሞቴዎስ ከመመላለሷ የተነሣ የኃጢአት ፍቅር አድሮባቸው በመብል ጊዜ አብረው የሚመገቡ ሆኑ፡፡ ከዚህም በኋላ ከእርሷ ጋር በኃጢአት ወደቀና በኃጢአት ሥራ ውስጥ 7 ወር ያህል ኖረ፡፡ እግዚአብሔር ሁለቱንም አልጣላቸውምና በዕለተ ምፅዓት በፊቱ የሚቆሙ መሆናቸውን አሳሰባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጢሞቴዎስ ተነሥቶ ጥቅጥቅ ወዳለ ጫካ ገብቶ በዚያ እየታደለ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡ እግዚአብሔርም ጣፋጭ የሆነች የውኃ ምንጭንና ቴምርን አዘጋጀለት፡፡ እርሷን እየተመገበ በተጋድሎ ሲኖር ሰይጣን ዳግመኛ በቅናት ተነሣበትና አስጨናቂ የሆድ ሕማም አመጣበት፡፡ አባ ጢሞቴዎስ ከሕማሙ ጽናት የተነሣ በግንባሩ ምድር ላይ የወደቀ ሆኖ ቀረ፡፡ በዚህም ጊዜ ነፍሱን ‹‹ነፍሴ ሆይ ይህ የሠራሽው የኃጢአትሽ ፍሬ ነውና በዚህ ደዌሽ ታገሺ›› ይላት ነበር፡፡ በዚህም አስጨናቂ ሕማም ውስጥ ሆኖ 4 ዓመት ኖረ፡፡ ❤ ከ4 ዓመትም በኋላ መሐሪና ይቅር ባይ የሆነ እግዚአብሔር ለአባ ጢሞቴዎስ መልአኩን ላከለት፡፡ መልአኩም የአባ ጢሞቴዎስን ሆድ በእጁ አሸው፡፡ ጎኑንም በጣቱ ሰነጠቀና ጨንጓራውንና አንጀቱን አፀዳለት፡፡ በኋላም ወደቦታው መልሶ እንደቀድሞው አያይዞ አዳነውና "እነሆ እንግዲህ ጤነኛ ሆንክ፣ ዳግመኛ አትበድል ከዚህ የከፋ እንዳይደርስብህ" አለው፡፡ አባ ጢሞቴዎስም በበረሃ እየተጋደለ 40 ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያ በፊት በገዳም 17 ዓመት በዋሻ 10 ዓመት ኖሯል፡፡ በእነዚህም ዘመናቱ ከልብስ ተራቁቶ ኖረ፡፡ የራሱም ፀጉር ከፊትና ከኋላ ሸፍኖት ነበር፡፡ ስለ አገልግሎቱ፣ ስለ ተጋድሎውና ስለ አምልኮቱ የዱር አራዊት እስኪደግዱለትና የእግሩን ትቢያ እስኪልሱለት ድረስ እግዚአብሔር ትልቅ ጸጋን ሰጠው፡፡ አገልግሎቱንም ፈጽሞ ታኅሣሥ23  በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 23 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለዳዊት_ትሕትናሁ_ሶበ_ርእየ። ወየውሀቶ ፍጹም ዘአልቦ እከየ። #እግዚአብሔር ይቤ እንዘ ይነብብ ሰደየ። እምነ ሕዝብየ አልዓልኩ ኅሩይየ። ወረከብክዎ #ለዳዊት_ገብርየ"። ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ_23።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta): ❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን #ለልበ_አምላክ_ለእሴይ_ልጅ ለእስራኤል ንጉሥ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ዳዊት_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ተጋዳይ አባት ለገዳማዊ #ለአባ_ጢሞቴዎስ_ዕረፍት በዓል፣ ለቅዱሳን #ለአባ_ሳሙኤል_ለአባ ስምዖን_ለአባ ገብርኤል ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከይስሐቅ_ከአባ_አሞን፣ #ከአባ_አቦሊ_ከመቃርስ_ከአይተለአትካ_ከፊልጦስ_ከመርቆሬዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                                        ✝ ✝ ✝ ❤ #ልበ_አምላክ_ነቢዩ_ንጉሥ_ቅዱስ_ዳዊት፦ ይህም ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት መልካም ጒዞን የተጓዘ ከእራኤልም ነገሥታት ሁሉ እውነተኛ ፍርድን ያደረገ ነው እርሱም አገሩ ቤተልሔም የሆነች ከይሁዳ ነገድ ነው ሳኦልም የእግዚአብሔር ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ ለእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ መረጠው ነቢይ ሳሙኤልንም ቅብዐ መንግሥትን የእሴይን ልጅ ይቀባ ዘንድ ላከው። ሳሙኤልም ታላቁን ኤልያብን ተመለከተ መልኩ ያማረ አካሉም የጸና ነበርና እግዚአብሔር ግን አልመረጠውም። "የኤልያብ ፊቱን አትይ የመልኩንም ማማር አትመልከት እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ የሚያይ አይደለምና" አለው እንጂ "ሰው መልክ ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን" ያያል። ❤ ከእሴይ ከሰባቱ ልጆች በኋላ ነቢይ ሳሙኤል ዳዊትን በእስራኤል ልጆች ላይ ይነግሥ ዘንድ ቀባው እግዚአብሔርም በሥራው ሁሉ ከእርሱ ጋር ሆነ። ከልቡናው ንጽሕና ከየዋህነቱም ብዛት የተነሣ ጠላቱን ሳኦልን ብዙ ጊዜ ሲያገኘው በላዩ ምንም ምን ክፉ ነገር አላደረገበትም። በአንዲትም ዕለት ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትን ከሰዎቹ ጋር ይፈልገው ዘንድ ዋሊያዎች ወደሚታደኑበት ሔዶ በጐዳና አጠገብ ያሉ ዘላኖችም ወደሚሠማሩበት ደረሰ በዚያም ዋሻ ነበር ሳኦልም ይናፈስ ዘንድ ወደዚያች ዋሻ ውስጥ ተቀምጠው ነበር። ዳዊትም ተነሥቶ ቀስ ብሎ ከልብሱ ጫፍ ቆረጠ። በሁለተኛም ጊዜ በድንክ አልጋ ላይ ተኝቶ ወዳለበት ከአቢሳ ጋር ገብቶ ከራስጌው ጦሩንና ውኃ ያለበትን ረዋቱን ይዞ ተመልሶ ሔደ ክፉ ነገርንም አላደረገበትም ሰዎቹም ጠላትህ ሳኦልን ግደለው በአሉት ጊዜ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን ልዘረጋ አይገባኝም ብሎ መለሰላቸው። ❤ ስለ ሳኦልም መገደል አንድ ሰው በነገረው ጊዜ ዳዊትም "ያንን ሰው ማን ገደለው" አለው ሰውዬውም "እኔ ገደልሁት" አለው ዳዊትም እጅግ አዘነ ልብሱንም ቀደደ ያንንም ሳኦልን እኔ ገደልሁት ያለውን ሰው ገደለው። እግዚአብሔር በዚህ በጻድቅ ዳዊት ልብ ብዙ ትሩፋትን፣ ትሕትናን፣ የዋህነትን፣ ቅንነትን፣ ትዕግሥትን ፍቅርን አከማቸ ክብር ያለው ንጉሥ ሲሆን ራሱን ውሻ ትል እንስሳም አድርጎ ይጠራል ስለዚህም ከምድር ነገሥታት ሁሉ ከፍ ከፍ አደረገው እንዲህም ብሎ አመሰገነው "የእሴይን ልጅ ዳዊትን እንደ ልቤ ሆኖ አገኘሁት ፈቃዴን ሁሉ የሚያደርግ ታማኝ ሰው ነው"። ❤ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች ኢየሩሳሌምንም ስለ ዳዊት ደግነት ብዙ ጊዜ ጠበቃቸው እርሱ ካለፈ በኋላም በነቢያቶቹ አንደበት አከበረው ነገሥታትንም ከእርሱ ዘር አደረገ። እርሱም በሁሉ ዓለም የታወቀ የመዝሙሩን መጽሐፍ ደረሰ ይኸውም በሰይጣናት ላይ ጋሻና ጦር የሆነ መልካም ቃልንም የተመላ በሰማይና በምድርም ያሉ በእርሱ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ነው። ❤ ቅዱስ ዳዊትም ፊቱ እንደ ሮማን ቀይ ነው ቁመቱም መካከለኛ የሆነ አካሉም የጸና ብርቱ ነበር ታናሽ ብላቴናም ሁኖ ሳለ እርሱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አንበሳ ወይም ተኵላ መጥቶ ከመንጋው ውስጥ በግ ነጥቆ በሚወስድ ጊዜ ተከትሎ ገድሎ ከአፉ ያስጥለው ነበር ሊጣላውም ቢነሣበት ጒረሮውን ይዞ ይሠነጥቅዋል። ከፍልስጥዔማውያንም ጋራ ሰልፍ በሆነ ጊዜ ብርቱ ሰው ስሙ ጎልያድ የሚባል ከጌት ሰዎች የተወለደ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ ከኢሎፍላውያን ሰፈር ወጣ። በራሱ ላይ የነሐስ በርቦርቴ ደፍቷል የነሐስ ጽሩርም ለብሷል በርሱ ላይ ያለ የብረቱና የነሐሱ ሁሉ ሚዛኑ አምስት ሽህ ወቄት ነበር። በእግሮቹ ባቶችም ላይ የነሐስ ሰናፊል ታጥቆ ነበር በጫንቃውም መካከል የነሐስ እባቦች ነበሩ። የጦሩም ዛቢያ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሁኖ በላዩ ሽቦ ነበረበት የጦሩም ብረት መጠን ስድስት መቶ ወቄት ነበር ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሔድ ነበር። ❤ ቁሞም ወደ እስራኤል ሰፈር ይጮህ ነበር "ከእኛ ጋር ትዋጉ ለምን ወጣችሁ እኔ የኤሎፍላውያን ወገን ነኝ ከእናንተ የሳኦል ባሮች አይደላችሁምን ከእናንተ አንድ ሰው መርጣችሁ ወእኔ ይውረድ ከእኔ ጋር መዋጋት ችሎ ቢገድለኝ ባሮች እንሆናችኋለን እኔ ከርሱ ጋራ ችዬ ብገድለው እናንተ ባሮች ሁናችሁ ትገዙልናላችሁ" አላቸው። ያም ኢሎፍላዊ ለወገኖቹ "ዛሬ በዚች ቀን አንድ ሰው ስጡኝና ሁለታችን ለብቻችን እንደዋጋ ብሎ የእስራኤልን አርበኞች እነሆ ተገዳደርኳቸው" አላቸው። እስራኤል ሁሉና ሳኦልም ይህን የኢሎፍላዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ እጅግም ፈሩ የእራኤልንም ወገኖች እንዲህ እየተገዳደራቸውና እየተመካባቸው አርባ ቀኖች ያህል ኖረ ከእስራኤልም ወገን ወደርሱ ይወጣ ዘንድ የደፈረ የለም። ❤ በዚያም ወራት ቅዱስ ዳዊት ወንድሞቹን ሊጐበኝ ወጣ ያንንም የኢሎፍሊ ወገን የሆነ ሰው የእግዚአብሔር ወገኖችን ሲገዳደራቸው በአየው ጊዜ አምላካዊ ቅናትን ቀና ሳኦልንም እንዲህ አለው "እኔ ሔጄ ይህን ያልተገረዘ ቈላፍ ገድዬ ዛሬ ከእስራኤል ሽሙጥን አርቃለሁ። ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔርን አርበኞች ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ቁም ነገር ነው ከድብ አፍና ከአንበሳ አፍ ያዳነኝ እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ ካልተገረዘ ኢሎፍላዊ እጅ ያድነኛል"። ሳኦል "ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ዳዊትም ወንጭፋን በእጁ ያዘ ከወንዝ መካከልም ሦስት ደንጊያዎችን መረጠና ወደዚያ ኢሎፍላዊ ሔደ። ጎልያድም ዳዊትን በአየው ጊዜ ናቀው እንዲህም አለው "ደንጊያና በትር ይዘህ ወደኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ውሻ ነኝን" ዳዊትም "ከውሻ የምትሻል አይደለህም ከውሻ ትብሳለህ እንጂ" ቈላፍ  ጎልያድም ዳዊትን በጣዖቶቹ ስም ረገመው። ❤ ያም ኢሎፍላዊ ዳዊትን "ወደ እኔ ና ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለዱር አራዊት እሰጣሁ" አለው ዳዊትም ያንኑ ኢሎፍላዊ  "አንተ ጦር ሰይፍና ጋሻ ይዘህ ወደኔ ትመጣለህ እኔ ግን አሸናፊ በሚሆን በእግዚአብሔር ስም ወዳንተ እመጣለሁ። ዛሬ የእስራኤልን አርበኞች የተገዳደርክ አንተን ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ይጥልሃል እገድልህምአለሁ ራስህንም እቆርጣለሁ የኢሎፍላውያን ሠራዊት ሬሳና ያንተን ሬሳ ዛሬ ለዱር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጣለሁ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ ሠራዊትም ሁሉ እግዚአብሔር በጦርና በሰይፍ የሚያድን እንዳይደለ ያውቃሉ ድል የእግዚአብሔር ገንዘብ ነውና"።   

ታሕሳስ ፳፪ /22/ በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ዳናህ በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከ
ታሕሳስ ፳፪ /22/
በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ዳናህ በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከበረችበት ነው የዚያች ሀገር ኤጲስቆጶስ አርኬላዎስም ምስክር የሆነበት ነው። ይህም መልአክ ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር የታመነ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት። ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድም ካህኑን ዘካርያስን ያበሠረው እርሱ ነው ይህ መልአክ እጅግ የከበረ የተመረጠ ገናና የሆነ ነውና ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ዘንድ ልባችንን አንጽተን ወደዚህ የከበረ መልአክ እየለመንን መታሰቢያውን ልናደርግ ይገባናል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

ታሕሳስ ፳፩ /21/ በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ የሆነ ቅዱስ ሐዋርያ በርናባስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሌዊ ነገድ የሆነ ሀገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክ
ታሕሳስ ፳፩ /21/ በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ የሆነ ቅዱስ ሐዋርያ በርናባስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሌዊ ነገድ የሆነ ሀገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክብር ይግባውና ጌታችን ከመከራው በፊት ይሰብኩ ዘንድ ከላካቸው ከሰባ ሁለት አርድእት ጋር መረጠው ስሙንም በርናባስ ብሎ ጠራው። በባለ ሃምሳ ጊዜ እርሱም ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ። የእርሻ ቦታ ነበረውና ሽጦ ዋጋውን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር በታች አኖረው። ቅዱስ ጳውሎስም በጌታችን አምኖ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እርሱ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ ሐዋርያት አላመኑትም ነበር። ይህ በርናባስ ጌታችን በመንገድ እንደ ተገለጸለትና እንደአነጋገረው እርሱም በጌታ ኢየሱስ ስም በደማስቆ እንደ አስተማረ ነገራቸው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙ ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ሳውልንና በርናባስን እኔ እነርሱን ለመረጥኩለት ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ከዚህም በኋላ ጹመው ጸልየው እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው። በቆጵሮስ አገር የሚኖሩ አይሁድም ቀኑበት በመኳንንቱም ዘንድ ወንጅለው እጅግ ብዙ  ስቃይን አሰቃዮት በመጨረሻም ከእሳት ጨመሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ ማርቆስም ከርሱ ጋር አለ ግን እግዚአብሔር ጠብቆ አተረፈው። እርሱም ቅዱስ በርናባስን ከእሳት ውስጥ አወጣው ሥጋውንም እሳት ከቶ አልነካውም በአማሩ ልብሶችም ገነዘውና ተሸክሞ ወስዶ ከቆጵሮስ ከተማ ውጭ በዋሻ ውስጥ አኖረው። የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

ታሕሳስ ፳ /20/ በዚች ቀን ከሌዊ ነገድ ከአሮን ትውልድ የሆነ ነቢይ ሐጌ አረፈ። እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ
ታሕሳስ ፳ /20/
በዚች ቀን ከሌዊ ነገድ ከአሮን ትውልድ የሆነ ነቢይ ሐጌ አረፈ። እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ ወላጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ወደ ባቢሎን አገር ተማርከው ሔዱ ዳርዮስ የተባለውም ኵርዝ በነገሠ ጊዜ በሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ይህ ነቢይ ትንቢት ተናገረ። የእስራኤልን ልጆች ወደ አገራቸው ይገቡ ዘንድ ኵርዝ ዳርዮስ በአሰናበታቸው ጊዜ እነርሱም ከገቡ በኋላ ቤተ መቅደስን ከመሥራት ቸል በአሉ ጊዜ እነርሱ ግን በአማሩና በተሸለሙ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ነበርና እንዲህ አላቸው።
ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ አለ የኔ ቤት ፈርሷል እናንተ ግን ሁላችሁም ቤታችሁን ታጸናላችሁ አላቸው። ስለዚህ ከምድር በላይ ያለች ሰማይ ዝናም ለዘር ትነሣለች ምድርም ፍሬዋን አትሰጥም አላቸው።
ከሕዝቡም ደጋጎቻቸው ሰምተው እጅግ ፈሩ የእግዚአብሔርንም መመስገኛ ቤት እንደሚገባ መሥራት ጀመሩ። ይህም ጻድቅ ነቢይ ሰባ ዓመት ያህል ኖረ የትንቢቱም ወራት ክብር ይግባውና ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። ከዚህ በኋላም በሰላም በፍርቅ አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን #ለመጋቤ_ሐዲስ_ለሊቀ_መላእክት #ለቅዱስ_ገብርኤል_አናንያን_አዛርያን_ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከነደደ እሳት ለዳናቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከካህናት ወገን ከሆነ #ከሀገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                       ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ_የመልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና። ❤ በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ። ❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ገብርኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 12 ስንክሳር።                                                                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የአገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ_አባ_ዮሐንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጅቹ የከበሩ ናቸው እነርሱም ከገንዘባቸው ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር ወላጆቹም በአረፉ ጊዜ የተዉለትን ገንዘብ ወስዶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ ዳግመኛም የእግዳ ቤት ሠራ በውስጡም መጻተኞችንና በሽተኞችን ሰብስቦ የሚያገለግላቸው ሆነ የሚሹትንም ሁሉ ያቀርብላቸዋል። ❤ በዚያም ወራት ወደርሱ አንድ መነኵሴ መጣ የምንኵስናንም ሥራ አመሰገነለት ክብሩንም ገለጠለት ያ መነኵሴም ከሔደ በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጥቶ አባ ዳንኤል ለአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሁኖ በነበረበት ወራት ወደ አስቄጥስ ሒዶ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ በዋሻ ውስጥም ብቻውን ሁኖ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ስለ መልካም ተጋድሎውም ሰይጣናት ቀኑበት ብዙ ዘመንም ታሞ ከኖረ በኋላ በደዌ መቅሠፍት ቀሠፉት። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈወሰውና ኃለኛ ጽኑዕ አደረገው በእግዚአብሔርም ፈቃድ ቡርልስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶሰነት ተሾመ በዘመኑም በአገሮች ውስጥ ብዙ ኑፋቄ ነበር እርሱም እንክርዳዱን ከሥንዴ መካከል ይነቅል ዘንድ ብዙ ድካምን ደከመ ከላይኛው ግብጽ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ብዙ ነገርንም ይቀርባጥር ነበር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምሥጢር ይገልጥልኛል በማለት እርሱ ብዙ ሰዎችን አሳታቸው ይህንንም በአወቀ ጊዜ ይዘው ይገርፋት ዘንድ አዘዘ ስሕተቱንም አመነ ከአገርም አሳደዱት። ❤ ነቢይ ዕንባቆም ይታየኛል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥልኛ የሚል ሌላ ሰው ነበር ብዙዎችም ተከተሉት እርሱንም አሳደደው ትምህርቱንም አጠፋ መጻሕፍቱንም ቀደደ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ይህ አባ ዮሐንስ መሥዋዕት ለማሳረግ በሚቀድስ ጊዜ ፊቱ እሳት ይሆናል ሥጋውም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንደወጣ ይሆናል ዕንባውም እንደ ዝናብ ይዘንባል የመላእክትን ሠራዊት በመሠዊያው ዙሪያ በመሠዊያው ዙሪያ በግልጥ ያያቸዋልና። ኅብስቱ በሚፈተት ጊዜ ሦስቱን የመፈተቻ ምስጋናዎች አንብቦ ጽዋውን ሲባርከው እንደ ፍም የጋለ ሁኖ ጽዋውን ያገኘዋል። ❤ በኋላ በዘመኑ በቀን ከበሉ በኋላ በአንድ ቀን ሁቸተኛ የሚቆርቡ ክፉዎች ሰዎች ተነሡ አስተምራቸው ገሠጻቸው ባልተመለሱም ዳግመኛ አወገዛቸው ባልተመለሱም ጊዜ ስለርሳቸው ጌታን ለመነው እሳትም ከሰማይ ወርዶ አለቃቸውን አቃጠለው የቀሩትም ይህን አይተው እጅግ ፈሩ ተጸጽተውም ወደ ቀናች ሃይማኖት ተመለሱ። ❤ ከዚህም በኋላ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም እግዚአብሔር ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ ቅዱሳን አባ እንጦስና አባ መቃርስን ወደርሱ ላካቸው እነርሱም ዕረፍቱ እንደ ደረሰ አስረዱት ሕዝቡንም ሰብስቦ ሕግና ሥርዓትን እንዲጠብቁ እርስ በርሳቸውም ይፋቀሩ ዘንድ በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ በመኝታው ላይ ጋደም ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 19 ስንክሳር።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ማኅሌት_ምስባክ፦ "ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵሎሙ መላእክቲሁ። ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ። ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ። መዝ 102፥20-21። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥29-34።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስምከ"። መዝ 137፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ተሰ 1፥6-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥30-35። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥11-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው።መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን #ለመጋቤ_ሐዲስ_ለሊቀ_መላእክት #ለቅዱስ_ገብርኤል_አናንያን_አዛርያን_ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከነደደ እሳት ለዳናቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከካህናት ወገን ከሆነ #ከሀገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                       ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ_የመልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና። ❤ በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ። ❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ገብርኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 12 ስንክሳር።                                                                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የአገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ_አባ_ዮሐንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጅቹ የከበሩ ናቸው እነርሱም ከገንዘባቸው ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር ወላጆቹም በአረፉ ጊዜ የተዉለትን ገንዘብ ወስዶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ ዳግመኛም የእግዳ ቤት ሠራ በውስጡም መጻተኞችንና በሽተኞችን ሰብስቦ የሚያገለግላቸው ሆነ የሚሹትንም ሁሉ ያቀርብላቸዋል። ❤ በዚያም ወራት ወደርሱ አንድ መነኵሴ መጣ የምንኵስናንም ሥራ አመሰገነለት ክብሩንም ገለጠለት ያ መነኵሴም ከሔደ በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጥቶ አባ ዳንኤል ለአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሁኖ በነበረበት ወራት ወደ አስቄጥስ ሒዶ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ በዋሻ ውስጥም ብቻውን ሁኖ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ስለ መልካም ተጋድሎውም ሰይጣናት ቀኑበት ብዙ ዘመንም ታሞ ከኖረ በኋላ በደዌ መቅሠፍት ቀሠፉት። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈወሰውና ኃለኛ ጽኑዕ አደረገው በእግዚአብሔርም ፈቃድ ቡርልስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶሰነት ተሾመ በዘመኑም በአገሮች ውስጥ ብዙ ኑፋቄ ነበር እርሱም እንክርዳዱን ከሥንዴ መካከል ይነቅል ዘንድ ብዙ ድካምን ደከመ ከላይኛው ግብጽ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ብዙ ነገርንም ይቀርባጥር ነበር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምሥጢር ይገልጥልኛል በማለት እርሱ ብዙ ሰዎችን አሳታቸው ይህንንም በአወቀ ጊዜ ይዘው ይገርፋት ዘንድ አዘዘ ስሕተቱንም አመነ ከአገርም አሳደዱት። ❤ ነቢይ ዕንባቆም ይታየኛል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥልኛ የሚል ሌላ ሰው ነበር ብዙዎችም ተከተሉት እርሱንም አሳደደው ትምህርቱንም አጠፋ መጻሕፍቱንም ቀደደ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ይህ አባ ዮሐንስ መሥዋዕት ለማሳረግ በሚቀድስ ጊዜ ፊቱ እሳት ይሆናል ሥጋውም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንደወጣ ይሆናል ዕንባውም እንደ ዝናብ ይዘንባል የመላእክትን ሠራዊት በመሠዊያው ዙሪያ በመሠዊያው ዙሪያ በግልጥ ያያቸዋልና። ኅብስቱ በሚፈተት ጊዜ ሦስቱን የመፈተቻ ምስጋናዎች አንብቦ ጽዋውን ሲባርከው እንደ ፍም የጋለ ሁኖ ጽዋውን ያገኘዋል። ❤ በኋላ በዘመኑ በቀን ከበሉ በኋላ በአንድ ቀን ሁቸተኛ የሚቆርቡ ክፉዎች ሰዎች ተነሡ አስተምራቸው ገሠጻቸው ባልተመለሱም ዳግመኛ አወገዛቸው ባልተመለሱም ጊዜ ስለርሳቸው ጌታን ለመነው እሳትም ከሰማይ ወርዶ አለቃቸውን አቃጠለው የቀሩትም ይህን አይተው እጅግ ፈሩ ተጸጽተውም ወደ ቀናች ሃይማኖት ተመለሱ። ❤ ከዚህም በኋላ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም እግዚአብሔር ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ ቅዱሳን አባ እንጦስና አባ መቃርስን ወደርሱ ላካቸው እነርሱም ዕረፍቱ እንደ ደረሰ አስረዱት ሕዝቡንም ሰብስቦ ሕግና ሥርዓትን እንዲጠብቁ እርስ በርሳቸውም ይፋቀሩ ዘንድ በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ በመኝታው ላይ ጋደም ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 19 ስንክሳር።                                                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ማኅሌት_ምስባክ፦ "ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵሎሙ መላእክቲሁ። ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ። ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ። መዝ 102፥20-21። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥29-34።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስምከ"። መዝ 137፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ተሰ 1፥6-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥30-35። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥11-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው።መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።