ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多608
订阅者
-124 小时
-37 天
-1130 天
帖子存档
ታሕሳስ ፳፩ /21/
በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ የሆነ ቅዱስ ሐዋርያ በርናባስ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሌዊ ነገድ የሆነ ሀገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክብር ይግባውና ጌታችን ከመከራው በፊት ይሰብኩ ዘንድ ከላካቸው ከሰባ ሁለት አርድእት ጋር መረጠው ስሙንም በርናባስ ብሎ ጠራው።
በባለ ሃምሳ ጊዜ እርሱም ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ። የእርሻ ቦታ ነበረውና ሽጦ ዋጋውን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር በታች አኖረው።
ቅዱስ ጳውሎስም በጌታችን አምኖ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እርሱ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ ሐዋርያት አላመኑትም ነበር። ይህ በርናባስ ጌታችን በመንገድ እንደ ተገለጸለትና እንደአነጋገረው እርሱም በጌታ ኢየሱስ ስም በደማስቆ እንደ አስተማረ ነገራቸው።
ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙ ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ሳውልንና በርናባስን እኔ እነርሱን ለመረጥኩለት ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ከዚህም በኋላ ጹመው ጸልየው እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው።
በቆጵሮስ አገር የሚኖሩ አይሁድም ቀኑበት በመኳንንቱም ዘንድ ወንጅለው እጅግ ብዙ ስቃይን አሰቃዮት በመጨረሻም ከእሳት ጨመሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ ማርቆስም ከርሱ ጋር አለ ግን እግዚአብሔር ጠብቆ አተረፈው። እርሱም ቅዱስ በርናባስን ከእሳት ውስጥ አወጣው ሥጋውንም እሳት ከቶ አልነካውም በአማሩ ልብሶችም ገነዘውና ተሸክሞ ወስዶ ከቆጵሮስ ከተማ ውጭ በዋሻ ውስጥ አኖረው።
የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ታሕሳስ ፳ /20/በዚች ቀን ከሌዊ ነገድ ከአሮን ትውልድ የሆነ ነቢይ ሐጌ አረፈ። እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ ወላጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ወደ ባቢሎን አገር ተማርከው ሔዱ ዳርዮስ የተባለውም ኵርዝ በነገሠ ጊዜ በሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ይህ ነቢይ ትንቢት ተናገረ። የእስራኤልን ልጆች ወደ አገራቸው ይገቡ ዘንድ ኵርዝ ዳርዮስ በአሰናበታቸው ጊዜ እነርሱም ከገቡ በኋላ ቤተ መቅደስን ከመሥራት ቸል በአሉ ጊዜ እነርሱ ግን በአማሩና በተሸለሙ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ነበርና እንዲህ አላቸው።
ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ አለ የኔ ቤት ፈርሷል እናንተ ግን ሁላችሁም ቤታችሁን ታጸናላችሁ አላቸው። ስለዚህ ከምድር በላይ ያለች ሰማይ ዝናም ለዘር ትነሣለች ምድርም ፍሬዋን አትሰጥም አላቸው።ከሕዝቡም ደጋጎቻቸው ሰምተው እጅግ ፈሩ የእግዚአብሔርንም መመስገኛ ቤት እንደሚገባ መሥራት ጀመሩ። ይህም ጻድቅ ነቢይ ሰባ ዓመት ያህል ኖረ የትንቢቱም ወራት ክብር ይግባውና ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። ከዚህ በኋላም በሰላም በፍርቅ አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ለመጋቤ_ሐዲስ_ለሊቀ_መላእክት #ለቅዱስ_ገብርኤል_አናንያን_አዛርያን_ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከነደደ እሳት ለዳናቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከካህናት ወገን ከሆነ #ከሀገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ_የመልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና።
❤ በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ።
❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ገብርኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 12 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የአገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ_አባ_ዮሐንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጅቹ የከበሩ ናቸው እነርሱም ከገንዘባቸው ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር ወላጆቹም በአረፉ ጊዜ የተዉለትን ገንዘብ ወስዶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ ዳግመኛም የእግዳ ቤት ሠራ በውስጡም መጻተኞችንና በሽተኞችን ሰብስቦ የሚያገለግላቸው ሆነ የሚሹትንም ሁሉ ያቀርብላቸዋል።
❤ በዚያም ወራት ወደርሱ አንድ መነኵሴ መጣ የምንኵስናንም ሥራ አመሰገነለት ክብሩንም ገለጠለት ያ መነኵሴም ከሔደ በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጥቶ አባ ዳንኤል ለአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሁኖ በነበረበት ወራት ወደ አስቄጥስ ሒዶ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ በዋሻ ውስጥም ብቻውን ሁኖ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ስለ መልካም ተጋድሎውም ሰይጣናት ቀኑበት ብዙ ዘመንም ታሞ ከኖረ በኋላ በደዌ መቅሠፍት ቀሠፉት።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈወሰውና ኃለኛ ጽኑዕ አደረገው በእግዚአብሔርም ፈቃድ ቡርልስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶሰነት ተሾመ በዘመኑም በአገሮች ውስጥ ብዙ ኑፋቄ ነበር እርሱም እንክርዳዱን ከሥንዴ መካከል ይነቅል ዘንድ ብዙ ድካምን ደከመ ከላይኛው ግብጽ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ብዙ ነገርንም ይቀርባጥር ነበር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምሥጢር ይገልጥልኛል በማለት እርሱ ብዙ ሰዎችን አሳታቸው ይህንንም በአወቀ ጊዜ ይዘው ይገርፋት ዘንድ አዘዘ ስሕተቱንም አመነ ከአገርም አሳደዱት።
❤ ነቢይ ዕንባቆም ይታየኛል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥልኛ የሚል ሌላ ሰው ነበር ብዙዎችም ተከተሉት እርሱንም አሳደደው ትምህርቱንም አጠፋ መጻሕፍቱንም ቀደደ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ይህ አባ ዮሐንስ መሥዋዕት ለማሳረግ በሚቀድስ ጊዜ ፊቱ እሳት ይሆናል ሥጋውም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንደወጣ ይሆናል ዕንባውም እንደ ዝናብ ይዘንባል የመላእክትን ሠራዊት በመሠዊያው ዙሪያ በመሠዊያው ዙሪያ በግልጥ ያያቸዋልና። ኅብስቱ በሚፈተት ጊዜ ሦስቱን የመፈተቻ ምስጋናዎች አንብቦ ጽዋውን ሲባርከው እንደ ፍም የጋለ ሁኖ ጽዋውን ያገኘዋል።
❤ በኋላ በዘመኑ በቀን ከበሉ በኋላ በአንድ ቀን ሁቸተኛ የሚቆርቡ ክፉዎች ሰዎች ተነሡ አስተምራቸው ገሠጻቸው ባልተመለሱም ዳግመኛ አወገዛቸው ባልተመለሱም ጊዜ ስለርሳቸው ጌታን ለመነው እሳትም ከሰማይ ወርዶ አለቃቸውን አቃጠለው የቀሩትም ይህን አይተው እጅግ ፈሩ ተጸጽተውም ወደ ቀናች ሃይማኖት ተመለሱ።
❤ ከዚህም በኋላ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም እግዚአብሔር ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ ቅዱሳን አባ እንጦስና አባ መቃርስን ወደርሱ ላካቸው እነርሱም ዕረፍቱ እንደ ደረሰ አስረዱት ሕዝቡንም ሰብስቦ ሕግና ሥርዓትን እንዲጠብቁ እርስ በርሳቸውም ይፋቀሩ ዘንድ በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ በመኝታው ላይ ጋደም ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 19 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ማኅሌት_ምስባክ፦ "ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵሎሙ መላእክቲሁ። ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ። ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ። መዝ 102፥20-21። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥29-34።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስምከ"። መዝ 137፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ተሰ 1፥6-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥30-35። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥11-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው።መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

ታሕሳስ ፲፰ /18/በዚችም ቀን የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የቲቶ ሥጋ አቅራጥስ ከሚባል አገር ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ የፈለሰበት መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው ታላቁ ጻድቅ ቈስጠንጢኖስ በእግዚአብሔር ፈቃድ በነገሠ ጊዜ ስለ አብያተ ክርስቲያናት ሥራ አስቦ በሚገዛቸው አገሮቹ ሁሉ ሠርቶ በመልካም ጌጥ አስጌጣቸው በዕንቊዎችና በከበሩ ደንጊያዎችም ይልቁንም በቊስጥንጥንያ ከተማ እርሷ መናገሻ ከተማው ናትና። የሐዋርያትንም ሥጋቸውን ከሁሉ ቦታ ከከበሩ ሰማዕታትም ብዙውን ሰበሰበ ስለ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ሥጋ አቅራጥስ በሚባል አገር እንዳለ በሰማ ጊዜ የካህናትን አለቆች ከብዙ ገንዘብ ጋር ላካቸው እነርሱም የቅዱስ ቲቶን ሥጋ በታላቅ ክብር ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት ንጉሡም ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠራለት ሥጋውንም ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ አኖሩ። እግዚአብሔርም ታላላቅ አስደናቂዎች ተአምራትን ከሥጋው ገለጠ ከዕብነ በረድ የተሠራ ሥጋው ያለበትን ሣጥን በተሸከሙ ጊዜ ከአንድ ሰው ላይ ወድቆ እግሩን ቀጥቅጦ ሰበረው እርሱም ከቅዱስ ቲቶ ሥዕል ፊት ካለው የመብራት ቅባት የተሰበረ እግሩን ቀብቶ ሲያመው እየጮኸ አሠረው። ወደ ቤቱም መሔድ ባልተቻለው ጊዜ የቅዱስ ቲቶ ሥጋ ሣጥን በአለበት በዚያ አደረ። በማግሥቱም አይቶ በውስጡ መድኃኒት ሊያደርግ እግሩን በፈታው ጊዜ ከቶ ምንም ምን ሕማም እንዳላገኘው እንደ ሁለተኛው ደኅና ሁኖ አገኘው ግን የደም ፍለጋ ምልክት አለ ይህን ድንቅ ሥራ ያዩ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት እርሱም የዳነው ፈጽሞ እያመሰገነ ወደ ቤቱ ገባ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
ታሕሳስ ፲፯ /17/በዚች ቀን የቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ የሥጋው ፍልሰት ሆነ። እርሱም ከፋርስ አገር ነው በመጀመሪያ በመቶ ጭፍራ ላይ መኰንን ሁኖ ተሹሞ ነበር ከዚህም በኋላ ሹመቱን ትቶ የምንኵስና ልብስን ለበሰ። በአንድ ገዳም ውስጥ ገብቶ በብዙ መጋደል ጀመረ በዚያም ቅስና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ከዓምድ ላይ ወጥቶ በላዩ ሦስት ዓመት ቆመ በስሙም መልአክ ጠርቶት ከአንድ ገዳም አደረሰው። ከዚህም በኋላ የማይናገር ሆነ ከሰው ጋር ከቶ እንዳይናገር ከአፉ ውስጥ ደንጊያ ጐረሰ ዳግመኛም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ዳርቻ ይሔድ ዘንድ መልአክ አዘዘው። ለእርሷም አቅራቢያ ወደ ሆነች ወደ አንዲት ቦታ ሔደ ከምሰሶ ላይም ወጥቶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጠው አስደናቂዎች ተአምራትን በማድረግ ወደርሱ የሚመጡትን ብዙዎች በሽተኞችን ፈወሳቸው። እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ በዚህ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን አረፈ የሚያገለግለውም ረድ ለጳጳሳት አለቆችና ለካህናት አለቆች ስለ ዕረፍቱ ነገራቸው እነርሱም መስቀሎችን፣ ጽንሐዎችን፣ መብራቶችን ከመያዝ ጋር በዚያን ጊዜ ተነሥተው ወደ መኖሪያው ሔዱ በላዩም ጸልየው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰዱት። በአረፈ በሦስተኛው ቀን ታኅሣሥ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አደረሱት ወደ ቤተ መቅደስም አስገብተው የከበረ ሥጋው በአለበት እንደ ሚገባ ጸሎትን ፈጸሙ። ከእርሱም ተባረኩ የተሰበሰቡትም ሁሉ ተባረኩ ከዚህም በኋላ ከእርሱ አስቀድሞ የቅዱሳን ሥጋቸው ወዳለበት ሣጥን ውስጥ ጨመሩት። የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ17 ቀን።
❤ እንኳን #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ሉቃስ_ዘዓምድ ለሥጋው ፍልሰት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ሰማዕታት #ከአርድዮስ_ከአውስዮስ_ከሲርዮስ_ከማርቆስ #ከያርዋልኤልና በገድል ከሚደክም ከመነኰስ #ከአባ_ናትናኤል ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ሉቃስ_ዘዓምድ፦ እርሱም ከፋርስ አገር ነው በመጀመሪያ በመቶ ጭፍራ ላይ መኰንን ሁኖ ተሹሞ ነበር ከዚህም በኋላ ሹመቱን ትቶ የምንኵስና ልብስን ለበሰ። በምሥራቅ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ ገዳም እየተጋደለ ብዙ ወራት ኖረ የምንኵስናንም ሥራ ተጋድሎንና ትሩፋትንም በፈጸመ ጊዜ በዚያ ገዳም ውስጥ ቅስና ተሾመ። በተሾመም ጊዜ በዚያ በኖረበት መጠን የብረት ልብስ ለበሰ ከዚያቺም ወዲህ ስድስት ቀን የሚጾም ሆነ በክርስቲያን ሰንበት ቀንም ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ይቀበላል ከዚህም በኋላ ከጐመን ጋር አንድ የዳቦ ለከት ይመገባል።
❤ ከዚህም በኋላ ከዓምድ ላይ ወጥቶ በላዩ ሦስት ዓመት ቆመ በስሙም ሲጠራውና ከዚያም ዓምድ ላይ እንዲወርድ ሲያዝዘው የመልአክን ቃል ሰማ የብርሃን መስቀል ተከተለው ከገዳማት ወደ አንዱ ገዳም እስከ አደረሰውም ድረስ መራው በዚያም የሚኖር ሆነ ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ በትምህርቱ ይረጋጉ ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ የማይናገር ሆነ ከሰው ጋር ከቶ እንዳይናገር ከአፉ ውስጥ ደንጊያ ጐረሰ ዳግመኛም ወደ የቊስጥንጥንያ አገር ዳርቻ ይሔድ ዘንድ መልአክ አዘዘው ለእርሷም አቅራቢያ ወደ ሆነች ወደ አንዲት ቦታ ሔደ ከምሰሶ ላይም ወጥቶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጠው አስደናቂዎች ተአምራትን በማድረግ ወደርሱ የሚመጡትን ከብዙዎች በሽተኞችን ፈወሳቸው።
❤ እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ በዚህ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን ዐረፈ የሚያገለግለውም ረድ ለጳጳሳት አለቆችና ለካህናት አለቆች ስለ ዕረፍቱ ነገራቸው እነርሱም መስቀሎችን፣ ጽንሐዎችን፣ መብራቶችን፣ ከመያዝ ጋር በዚያን ጊዜ ተነሠሰተው ወደመኖሪያው ሔዱ በላዩም ጸልየው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰዱት በዐረፈ በሦስተኛው ቀን ታኅሣሥ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አደረሱት ወደ ቤተ መቅደስም አስገብተው የከበረ ሥጋው በአለበት እንደሚገባ ጸሎትን ፈጸሙ። ከእርሱም ተባረኩ የተሰበሰቡትም ሁሉ ተባረኩ ከዚህም በኋላ ከርሱ አስቀድሞ የቅዱሳን ሥጋቸው ወዳለበት ሣጥን ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም እጅግ ጠቃመመ የሆኑ አስደናቂዎች ተአምራትን አብዝቶ ገለጠ አምነው በሚመጡ በብዙዎች በሽተኞች ላይ ታላቅ ፈውስ ሁኗልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ በቅዱስ ሉቃስ ዘአምድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኘረ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ለፍልሰተ_ሥጋከ_ዕበያ። በስብሐት ወበሃሌ ሉያ። #ሉቃስ_ዘዓምድ ቢጸ #ሉቃስ_ሐዋርያ። ለነፍስየ ስረይ ኃጢአታ ወኅድግ ጌጋያ። እስመ ፈውሰ ሕማም ወደዌ የአምር ኬንያ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_17።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት። ወተኀሠዩ ሎቱ በረዓድ። አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር"። መዝ 2፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥18_31፣ ያዕ 1፥17_22 እና የሐዋ ሥራ 15፥10_13። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 11፥1-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ለሁላችንም ይሁንልን።

የተለያየ እንዲሆን አድርጋለች፡፡
❤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌምም በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ ሰውን የሚበሉ ፍጡሮች ወደሚኖሩበት አካባቢ ስትደርስ 60 የሚሆኑ አገልጋዮቿን ለመብላት ይዘው ሳር ቅጠል እንዲበሉ በማድረግ ዓይናቸውን በጉጠት በማውጣት ለወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጉባቸው ሰይጣንንም ያመልኩ ነበርና ከ4 ወራት በኋላም በዓል አድርገው ለመብላት ከእሳት ውስጥ ጨመሩአቸው፡፡ እነርሱ ግን ምንም አልሆኑም፡፡ ያን ጊዜም "እናንተ ሰዎች ምንድን ናችሁ?" ብለው ጠየቋቸው፡፡ ቅድስት እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስም ክርስቲያን መሆናቸውንና እነርሱ የሥላሴ ሕንጻ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብትመክራቸው "ምን እንበላለን?" አሏት፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምሕረት ስትነሳ የእህል ዘርን ለአገልጋዮቿ አስይዛ ስለነበር ከዚያ ስንዴ ወስዳ ዘራችው፡፡ስንዴውም በአንድ ቀን ተዘርቶ በቅሎ፣ ታጭዶ፣ ደርቆ፣ ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡ ቅድስት እናታችንም ቀምሳ ስታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርታላቸዋለች፡፡ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጅዋ ጽፋ አስቀመጠችላቸው፡፡
❤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጣላት በልጅዋ ምክንያት ስለ ደረሰባት ሀዘኖች አውርታላታለች፡፡ የፈለገችውንም እንድታደርግበት በእጅዋ ያለውን መስቀል ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሰጥታታለች፡፡ በዚህም መስቀል ባሕር ከፍላ ደቀ መዛሙርቶቿን አሻግራለች፡፡
❤ እናታችን የአባታችን የአባ ኤዎስጣቴዎስን ገድል በማንበብና በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እርዳታ ባሕሩን በአጽፏ ተሻግራ ወደ አገረ ናግራን ሄዳለች፡፡ እንዲሁም በበትረ መስቀል እንደ ዘርዐ ቡሩክ ከባሕር ውስጥ የሰጠሙ የደቀ መዛሙርቶቿን መጻሕፍት ምንም ሳይሆኑ ማውጣት ችላለች፡፡ በሁሉም አገር እየዞረች ቅዱሳት መካናትን ትሳለም ነበር፡፡ ደብረ ደሞ ሄዳ "ሴቶች መውጣት አይችሉም" ቢሏት በሀዘን ስታለቅስ ቅዱስ ሚካኤል በሥውር ወስዶ አድርሷታል፣ አቡነ አረጋዊም ተገልጸውላት ባርከዋታል በዚያም ሥጋ ወደሙን ተቀብላለች፡፡
❤ እናታችን ወደ ኢየሩሳሌምም ሄዳ ቅዱሳት መካናትን እየተሳለመች ለ7 ዓመታት ቆይታለች ቅዱስ ሚካኤልም በዓምደ ብርሃን እየመራት ተመልሳ ወደ አገራችን መጥታ በድጋሚ ከሱስንዮስ ጋር ተሟግታለች፡፡ ሙታንንም እያስነሳች እንዲመሰክሩላት ብታደርግም እርሱ ግን ከጥፋቱና ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም ነበር፡፡ የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ መልእክቷንም በንስር አሞራ አድርጋ እየላከች ትመክረው ነበር ፡፡
❤ በአንድ ወቅትም በአገራችን እህል መታጣት ሆነና ቅድስት እናታችን ዝክር የምታደርግበት እህል አጣች፡፡ደናግል ልጆቿንም ጠርታ ትንሽ ዱቄት እንዲያመጡላት ነግራቸው በእርሱ ጸሎት አድርጋበት "ወደ ቦታው መልሱት" አለቻቸው፡፡ በማግስቱም እንሥራው ጋኑ ሁሉ በዱቄት ተሞልቶ አግኝተውታል፡፡ የካቲት ኪዳነ ምሕረትንም በዓል በደስታ አክብረዋል፡፡
❤ መልአኩም ከቅድስት አገር ኢየሩሳሌም መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካመጣት በኋላ ዛሬ ገዳሟ ካለበት ቦታ ስትደርስ ከቦታዋ ላይ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ በቀስተ ደመና ተከቦ አይታ "ይህች ቦታ ምንታምር" ብላ ጠራቻት፡፡ በቦታውም ላይ በመድኃኔዓለም ትእዛዝ የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ቤተ ክርስቲያን በአንዲት ቀን ታህሣሥ 14 ቀን በዕለተ ዓርብ ጧት በሰንሰል (በስሚዛ) እንጨት ጀምራ ማታ እንደተፈጸመ በ3ኛው ቀን እሁድ ታህሣሥ 16 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር በድርገት (በቊርባን) ጊዜ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት መላእክት ጋር ወርዶ መቅደሱን ሲባርክ መቅደሱ በ4ቱ ማዕዘን ለጌታ ሰገደ። ለጌታ እንደ ሰገደ ዛሬም ድረስ ይታያ፡፡
❤ ጌታችንም "ይህ መቅደስሽ ሳይፈርስ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ይቆይልሻል፡፡ በዚህ ቦታ ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ ኃጢአቱ ይሰረይለታል፡፡ በምድርም ስምሽን የጠራ፣ መታሰቢያሽን ያደረገ፣ የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ የተረጐመ ሁሉ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን ለነዚህ ሁሉ ዋጋቸውን እሰጣቸዋለሁ፡፡ ከሩቅም ከቅርብም ከቀኝም ከግራም መጥቶ መቅደስሽን ለተሳለመ ሁሉ እስከ 12ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ፡፡ላልምረው ቦታችን አላስረግጠውም፡፡ በረከቴም በእሱ ላይ በልጆቹም በንብረቱ ላይ ለዘለዓለሙ ይኖራል፡፡ ስለጾምሽ፣ ስለጸሎትሽ፣ ስለተጋድሎሽ፣ ስለ ስግደትሽ ሰባት አክሊል ሰጠሁሽ" አላት፡፡
❤ ፃድቋ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ብዙ ገድል በሠራችበት ብዙ መነኰሳይያትን በአቋቋመችበት ገዳሟ በእመ ምዑዝ ኪዳነ ምሕረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም የካቲት29 ቀን ዐረፈች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክት ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር መጥቶ ነፍሷን ተቀብሎ ወደ ገነት ወስዶ አኖራት፡፡ ባረፈች ጊዜ በሥጋዋ ላይ ታላቅ የብርሃን ዓምድ ተተክሎ የታየ ሲሆን እንደ ፀሓይም ከጠዋት እስከ ማታ ያበራ ነበር፡፡ በመካነ መቃብሩዋም ላይ እስከ አርባ ቀን ድረስ ብርሃን ተተክሉ ታይቷል፡፡ ምንጭ፦ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ። ከእናታችን ከቅድስ ፍቅርተ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን። በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚገኘውን #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ድማህ ለመሰረቱት #በነጭ_እምነታቸው_በተለይ_ለነቀርሳ_በሽታ_ፈዋሽነት_ለሚታወቁት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_መርቆሬዎስ ለዕረፍት በዓል፣ ለእናታችን #ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ-ምዑዝ) በአንድ ቀን በስሚዛ (በሰንሰለት) ቤተ ክርስቲያን ሰርታ #ታኅሣሥ_14 ቀን ጨርሳ በሦስተኛ ቀን #ታኅሣሥ_16 ቀን_ቅዳሴ_ቤቱ_ሲከበር በድርገት (በቊርባን) ጊዜ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት መላእክት ጋር ወርዶ መቅደሱን ለባረከበት መቅደሱ በአራቱም ማዕዘን ለጌታ ለሰገደበት ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_መርቆሬዎስ፦ ትውልድ አገራቸው ትግራይ አካባቢ ወንበርታ (ሐይ ቀምሳ) ሲሆን ከእናታቸው ከቅድስት ሰሎሜ ከአባታቸው ከቅዱስ ቶማስ 1284 ዓ.ም ነሐሴ 29 ቀን ተወለዱ። ስማቸው በገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ በስፋት ተጠቅሷል። በደብረ ዳሞ ተሹመው ብዙ ዘመን አገልግለዋል። ጻድቁ ካቶሊካውያንን በመርታትና በማስተማር መፈናፈኛ ያሳጧቸው ስለነበር ብዙ መከራ ያደርሱባቸው ነበር። ጻድቁ ብዙ ሲጋደሉ ቆይተው በ130 ዓመታቸው ከእግዚአብሔር ብዙ ቃል ኪዳን ተቀብለው ዐርፈዋል።
❤ አቡነ መርቆሬዎስ ካዐረፋ በኋላ ካቶሊካውያን እንደገና ማመሳቸውን ቀጥለውበት ነበር ነገር ግን በእነ አቡነ መርቆሬዎስ እግር የተተኩ ሌሎቹ ቅዱሳን አባቶቻችን እየተከራከሩና እያስተማሩ ሃይማኖታችንን ጠብቀው አቆይተውልናል። አቡነ መርቆሬዎስ አስክሬን ቢያርፍባቸው 11ሙታን ከሞት ተነስተው መስክረዋል። ምንጭ፦ ከደብረ ድኅማ ገዳሙ አባቶች በቃል የተገኘ ማስታወሻና መዝገበ ቅዱሳን።
✝ ✝ ✝
❤ #ጻድቅ_ወሰማዕት_ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ ምዑዝ)፦ በጎንደር ክፍለ አገር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አጠገብ ኮክታ ማርያም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ውስጥ ተወለደች፡፡ዛሬም ይህ አካባቢ እመ ምዑዝ መንደር ይባላል፡፡የአባቷ ስም ቅዱስ ላባ የእናትዋ ስም ቅድስት ወንጌላዊት ይባላል፡፡ እነዚህም ወላጆቿ እጅግ ደጋግ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ለተራበ፣ ለተጠማ የሚያዝኑና የሚራሩ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ በጎ ምግባር ያላቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን በረከት ሁሉ በሥራ ላይ የሚያውሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልጅ ስላልወለዱ ወደፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸር አምላክ ስለሆነ እንደ ቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል ጸሎታቸውን ሰምቶ የተመረጠች ደግ ሴት ልጅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በሚያዚያ 4 ቀን ተፀንሳ ታኀሣሥ29 ቀን ከእነሱ ተወለደች፡፡ ስመ ጥምቀቷ ማርያም ጸዳላ የዓለም ስሟ ሙዑዚት ሲሆን ሙዑዚት ማለት ጣፋጭ ማለት ነው፡፡ (ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ደግሞ የቆብ ስሟ ነው።)
❤ በተወለደችም ጊዜ በእግርዋ ቆማ "በማኀየዊ ቸርነትህ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል" ብላ አመሰገነች ከእግዚአብሔር የተላከ መነኵሴም ወደ እርሷ በመሄድ የዳዊትን መዝሙር፣ መጻሕፍትንና የቤተክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ አስተምሯአታል፡፡
❤ ቅድስት እናታችን አምላኳን አስከ መጨረሻው በድንግልና ማገልገል ብትፈልግም ዕድሜዋ ከፍ ሲል ቤተሰቦቿ ዘርዐ ክርስቶስ ከሚባል አገረ ገዥ ጋር በቤተክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል አጋቧት ፡፡ እርሷ ግን በጫጉላ ቤት ሳሉ በእኩለ ሌሊት ባሏን "ወንድሜ ሆይ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ድንግልናችንን እንጠብቅ" አለችው፡፡ እርሱም "እሺ" ብሏት ይህንን ተመካክረው በጸሎት ሲተጉ አደሩ፡፡ ለእግዚአብሔር እየተገዙ በጾም በጸሎት በንጽሕናና በድንግልና ኖሩ በሌሊትም ወደ፡ባሕር ውስጥ እየገቡ ጸሎት ያደርጉ ጀመር፡፡ በመጨረሻም እርሷ በጳጳሱ በአባ ማርቆስ እጅ ስትመለኵስ ባሏም ድንግልናውን እንደጠበቀ በሰማዕትነት አንገቱን ተሰይፎ አርፏል፡፡ እርሷ በነበረችበት ዘመን ንጉሥ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ" የሚለውን የረከሰ የሮማውያንን ሃይማኖት ሕዝቡ ሁሉ እንዲያምን በማወጁ ምክንያት በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የሃይማኖት ግጭት ስለተነሣና ከ8ሺህ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከእነ አቡነ ስምዖንና ከሌሎችም ቅዱሳንና ቅዱሳት ጋር ተሰልፋ ሰማዕትነትን ተቀብላ ለሃይማኖትዋ ምስክር ሆናለች፡፡ ባለቤቷ ዘርዐ ክርስቶስም በሰማዕትነት ዐርፎ ሰባት አክሊላት ወርደውለታል፡፡
❤ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሱስንዮስ በአደባባይ ሲያስገርፋቸው ሥጋቸው እየተቆራረጠ መሬት ላይ የወደቀውን የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ሰብስባ "ይህን ለንጉሡ እጅ መንሻ ስጡልኝ" ብላ ላከችለት፡፡ "ይህ የሃይማኖ ፍሬ ነው፡፡ እኛስ አስከአሁን በሃይማኖታችን አለን፣ አንተ ብትገለን መከራም ብታደርስብን ሃይማኖታችንን አልካድንም፡፡ ነገር ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ከሞት አስነሣን ይህን የሥጋዬን ቁራጭና የእህቶቼን የደናግላንን ሥጋ ብላው ፣ ደማችንን ጠጣ ሃይማኖትህ የከፋ፣ ሰነፍ፣ የረከስህ ነህ" ብላ ልካለታለች፡፡ መልእክተኞቹም ለንጉሡ ወስደው ሰጥተውታል፡፡
ሱስንዮስ አዋጁን እንዳወጀ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖንም ካህናትንና ክርስቲያን ልጆቻቸውን አነሳስተው እያስተማሩና እያጠነከሩ እያለ በጦር ተወግተው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
❤ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖን በሰማዕትነት ከማረፋቸው በፊት ግን እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስን፣ ቅድስት አካለ ክርስቶስን፣ ቅድስት እመ፡ወተትን ... ወዘተ አነሳስተው ንጉሡን መክረውታል፣ ገሥጸውታል፣ ንጉሡ ግን ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይልቁንም ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የሃይማኖቷን ጽናት ስላየ ሥጋዋ እየተቆረሰ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በብረት በትር አጥብቆ ያስገርፋት ጀመር፡፡
በመጨረሻም ምድር እየሰወረቻት ለመግረፍ የማይመቻቸው ቢሆን ከሌሉቹ ሰማዕታት ጋር አንገቷን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡ በዚህም ጊዜ ፍጹም ጨለማ ሆኖ ምድርም ተነዋወጠች፡፡ ስምንት ሺህ ዐሥር ቅዱሳንም በሰማዕትነት ዐረፉ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን አንገቷን በሰይፍ ቢቆርጧትም ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ 14ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት አስነሥቶ ወደ ቦታዋ መለሳት፡፡
❤ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤልም ከሞት ካስነሣት በኋላ መናኝ ሆና በየገዳሙና በየአድባራቱ እየሄደች ዓለምን ስትዞር ያቀናቻቸው ብዙ ገዳማት አሉ፡፡ ለምሳሌ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ በሆኑት በአባ ጉባ ተመሥርታ በግራኝ ወረራ ጠፍታ የነበረችውን ራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳምን አቅንታ የወንድና ሴቶች መነኰሳት በጋራ አብረው ይኖሩ የነበረ ቢሆንም የበጎ ሥራ ጠላት የሆነው ሰይጣን በማኀበረ መነኰሳቱ መካከል ሊፈጥር ያለውን ክፉ ፈተና ለእናታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገልጾላት በገዳሟ ውስጥ የወንዶችና የሴቶች መነኰሳት መኖሪያ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን #ለእስራኤል_መሳፍንት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ጌዴዎን ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና #ለቅዱስ_ሙሴ_እኅት_ማርያም ለመታሰቢያ ቀን በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሀገረ አክሚምና ከጋውር #ከቅዱሳን_ሰማዕታት #ከአባ_ሐርወግ_ከሐናንያ_ከኵዚ_ከሰንሰራዲን_ከአውንያስና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የእስራኤል_መሳፍንት_የሆነው_ቅዱስ_ጌዴዎን፦ ይህም ከነገደ ምናሴ የሆነ የአባቱ ስም ዮአስ ይባላል ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጠለትና ለእስራኤል ሾመው። የጠዖታትንም መሠዊያ እነሰዲያፈርስ ዛፎችንም እንዲቆርጥ አዘዘው መሠዊያም ለእግዚአብሔር ሠርቶ በዚያ በሰበረው ዕንጨት እንዲሠዋ አዘዘው ሁሉንም እንዳዘዘው አደረገ። እግዚአብሔር የላከው መልአክም ተመለከተው "እስራኤልን ከምድያም እጅ ታድናቸዋለህና ከሠራዊትህ ጋር ሒድ እነሆ ላክሁህ" አለው።
❤ ጌዴዎንም "አድናቸዋለሁ እንዳልክ እስራኤልን በእጄ ታድናቸው እንደሆነ እነሆ እኔ በአደባባይ የተባዘተ ፀምርን እዘረጋለሁ ጠል በምድር ላይ ሳይወርድ በፀምሩ ላይ ብቻ ቢወርድ አድናቸዋለሁ እንዳል እስራኤልን በእጄ እንድታድ ናቸው ያን ጊዜ አውቃለሁ" አለ እንዳለውም ሆነ። ጌዴዎንም በማግሥቱ ማልዶ ሒዶ ያንን ጨመቀው ከዚያ ፀምር አንድ መንቀል ሙሉ ውኃ ወጣ።
❤ ጌዴዎን እግዚአብሔርን "በቊጣህ አትቆጣኝ ዳግመኛ አንድ ጊዜ ልናገር በፀምር ላይ ብቻ ሳይወርድ ጠል በምድር ሁሉ ላይ ይውረድ" አለው። እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዳለው አደረገ። ፀምሩ ብቻ ደረቅ ሁኖ ጠል በምድር ሁሉ ላይ ወረደ። ጌዴዎንንም የእግዚአብሔር መንፈስ ረድኤት አጸናው ነጋሪትንም መታ አብያዜርም በኋላው ሁኖ ደነፋ ወደ ነገደ ምናሴር፣ ወደ ነገደ ዛብሎን፣ ወደ ነገደ ንፍታሌምም መልክተኞችን ላከ ወጥተውም ተቀበሏቸው። ጌዴዎንም ከርሱ ጋር ያሉ ወገኖቹም ሁሉ ሔዱ አሮኤድ በሚባል አገርም ሰፈሩ የመሰድያምና የአማሌቅ ሠራዊትም በእንበሬም ቆላ መሠዊያ ቀኝ ሰፈሩ።
❤ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን "እጃችን አዳነችን ብለው እንዳመኩብኝ የምድያምን ሰዎች በእጃቸው መጣል እንደማልችል ካንተ ጋር ያሉ ሕዝብ ብዙ ናቸው" እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው "ከእናንተ የሚፈራ የመመደነግጥ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይመለስ" ብለህ ለሕዝቡ ንገራቸው። ሕዝቡም ከገለዓድ ተመለሱ ከሕዝቡም ሁለት እልፍ ከሁለት ሽህ ተመልሰው እልፍ ሰዎች ቀሩ።
❤ እግዚአብሔር ጌዴዎንን "ገና ብዙ ሕዝብ አሉ ወደ ውኃ አውርደህ በዚያ ፈትናቸው እኔ ይሒዱ የምልህ ሰዎች እነርሳቸው ካንተ ጋር ይሒዱ" አለው ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረዳቸው። እግዚአብሔር ጌዴዎንን "ውሻ በምላሱ ጠለፍ ጠለፍ አድርጎ እንዲጠጣ ከውኃው ጠለፍ ጠለፍ አድርጎ የሚጠጣውን ሁሉ ለብቻው አቁመው ውኃን ይጠጣ ዘንድ በጉልበቱ የተንበረከከውንም ሁሉ ለብቻው አቁመው" አለው። በምላሳቸው ጠለፍ ጠለፍ አድርገው የጠጡ ሰዎች ቊጥራቸው ሦስት መቶ ሆነ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃን ይጠጡ ዘንድ በጉልበታቸው ተንበረከኩ።
❤ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን "እንደዚህ በእጃቸው ውኃን በጠጡት በእነዚህ ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ የምድያምን ሰዎች ወደ ቤታቸው ይመለሱ" አለው። በዚያችም ሌሊት እሊህ ሦስት መቶ ሰዎች መለከትን ነፉ "ይህ የእግዚአብሔር ኃይልና የጌዴዎን ጦር ነው" ብለው ጮኹ። የምድያምም ሰዎች የመለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔር በልባቸው ፍርሀትን አሳድሮባቸው ደንግጠው ሸሹ እግዚአብሔርም ያንዱን ሰይፍ ወዳንዱ ወደ ጓደኛው መለሰ በሠራዊቶቻቸው ሁሉ እርስበርስ መተላለቅ ሆነ መኳንንቶቻቸውን ኄሬብንና ዜብን ነገሥቶቻቸው ዛብሄልንና ስልማናንም ገደሏቸው ከምድያምም ሠራዊት ፈረሰኞችና ጦረኞችን አንድ መቶ ሁለት ሽህ ገደሉ።
❤ ከዚህም በኋላ የምድያም ሰዎች በእስራኤል ፊት ተዋረዱ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም በጌዴዎንም ዘመን ምድር አርባ ዘመን ዐረፈች። ከዚህም በኋላ በዚች ቀን ታኅሣሥ 16 በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
❤ "#ሰላም_ለከ_ጌዴዎን_ኃያል። መስፍነ እስራኤል። ዘተከሥተ ለከ እምኀበ ልዑል። ትእምርተ ልደቱ እማርያም ድንግል። ውስተ ስፍሐ ይብስት ፀምር እንዘ ይወርድ ጠል"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_16።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥9። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 10፥26-29፣ 1ኛ ጴጥ 3፥5-7 እና የሐዋ ሥራ 13፥20-24። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥1-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ መርቆሬዎስ የዕረፍት በዓልና የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
ታሕሳስ ፲፭ /15/በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ለንጉሡ አማልክት አልሠዋም ስላለ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጨመረውና በዚያ 15 ዓመት ኖረ። አንዲት ሴትም በድብቅ ምግቡን ታመጣለት ነበር። ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ሊአገባት ሽቶ ነበርና በእርሷ ምክንያት ደናግሎችን ገደላቸው። ሥጋቸውም በተራራ ወድቆ ቀረ። ንጉሡም ስለ ገደላቸው ደናግል ይልቁንም ስለ ቅድስት አርሴማ አብዝቶ የሚያዝን ሆነ። ከዚህም በኋላ ወገኖቹ እንዲህም አሉት አውሬ ታድን ዘንድ ወደ ዱር እንውጣ የልብህም ኀዘን ይወገድልሃል። እርሱም ወደ ዱር ወጣ ። ወዲያውኑ ሰይጣን አደረበትና እንደ እሪያ አደረገው። የንጉሡ እኅት ግን ጎርጎርዮስን ከጒድጓድ ካላወጡ እንደማይድኑ በራዕይ አየችና ነገረቻቸው። ጎርጎርዮስም ከዚያ አውጥተው ወደ ቤተ መንግሥት አደረሱት። በዚያንም ጊዜ ንጉሱ ያስገደላቸውን የደናግሉን ስጋ ሰብስቦ በክብር አኖረው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸለየ ከንጉሡም ላይ በእሪያ አምሳል የነበረውን ሰይጣንን አስወጣው። ዳግመኛ እንዳይታበይ ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀረ ከዚህ በኋላም የቤተ መንግሥት ሰዎችን ሁሉንም አዳናቸው ከላያቸውም አጋንንትን አስወጥቶ ሰደዳቸው። ከዚህም በኋላ ያጠምቋቸው ዘንድ ወደ አርማንያ ሊቀ ጳጳስ መልክተኞችን ልኮ አጠመቃቸው ዳግመኛም ሊቀ ጳጳሳቱ የአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሾመው። በዚያም መልካም ጎዞውን ፈጸሞ በሰላም አረፈ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ከፋሌ_ባሕር አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው #የኢያሪኮን_ባሕር_ለተሻገሩት መታሰቢያ በዓል፣ እጅና እግር የሌላቸውና የእኔ ቢጤ ለነበሩት ጽድቃቸውን ማንም ሳያውቅባቸው ለኖሩት ለታላቁ ጻድቅ #ለአባ_ቆራይ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_የኢያሪኮን_ባሕር #በዓጽፍቸው_ስለመሻገራቸው፦ ወደ አርማንያ ሔደ ወደኢያሪኮ ባሕርም ሲደርስ በመርከባቸው ያሳፍሩት ዘንድ መርከበኞችን ለመናቸው በከለከሉትም ጊዜ ዓጽፉን በባሕሩ ላይ ዘረጋ በቅድስት ሥላሴ ስም በላዩ ባረከ ራሱንም በመስቀል ምልክት አማተበ እንደ መርከብም ሁኖለት በላዩ ተጫነ ሁለት መላእክትም ቀዛፊዎች ጌታችንም እንደ ሊቀ ሐመር ሆኑለት። ከባሕሩም ግርማ የተነሣ እንዳይፈሩ ልጆቹን አጽናናቸው። ግን እንዲህ አላቸው "ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ ለኔ ግን ከእናንተ አንዱ እንደ ሚጠፋ ይመስለኛል" ይህን ሲናገረሰ ልቡ የቂም የበቀል ማከማቻ ስለሆነ ወዲያውኑ አንዱ ከእነርሱ መካከል ሠጠመ። በእግዚአብሔርም ፍቃድ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ አርማንያ ከተማ ደርሶ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ተገናኘ ሰገደለትም ከእርሱም ቡራኬን ተቀበለ ሊቀ ጳጳሱም በአየ ጊዜ ታላቅ ደስታ ደስ አለው በፍቅርም ተቀበለው። አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ሁሉም በትምህርቱ አንድ እስከሆኑ ድረስ የአርማንያን ሰዎች ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው የሠሩትን ሥርዓት እያስተማራቸው ኖረ። ከአባታችን ከአቡነ ኤዎስጣቴዎስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ የመስከረም18 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የእኔ_ቢጤው_አባ_ቆራይ፡- እጅና እግር የሌላቸውና የእኔ ቢጤ የነበሩት ጽድቃቸውን ማንም ሳያውቅባቸው የኖሩት አባ ቆራይ ጻድቅ መሆናቸው ካረፉ በኋላ ነው የታወቀው፡፡ ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ ቅዱሱ በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት በትግራይ ተንቤን አውራጃ አዲ ራእሶት-የራሶች (የታላላቅ ሰዎች አገር) በሚባለው ቦታ የእግርና የእጅ ጣቶች የሌሏቸው አባ ቆራይ ወንበር በምትመስል ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ተገለጡ፡፡
❤ አንድ የአካባቢው ሰው በመንገድ ሲያልፍ አባ ቆራይ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ጸሎት ሲያደርጉ አያቸውና በሁኔታው ተገርሞ ወደ እርሳቸው ጠጋ ብሎ ስማቸውንና የመጡበትን አገር ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም "ስሜ አባ ቆራይ ይባላል፣ አገር ግን የለኝም" አሉት፡፡ እርሱም "እባክዎን ወደ መንደር እንሂድና የጸሎትና ቤት ሠርተንልዎት በዚያ ይቀመጡ" አላቸው፡፡ አባ ቆራይ ግን "ማረፊያዬ ይህቺ ናት፣ ከዚህች ሥፍራ አልነሣም" አሉት፡፡ አባ ቆራይም በዚያው እንደተቀመጡ ዝናቸው በሁሉ ዘንድ ተሰማና ሰዎች መጥተው በተቀመጡበት ድንጋይ ዙሪያ ጎጆ ቀለሱላቸው፡፡
❤ ከዚህም በኋላ መንደርተኞቹ በየተራ በምግብ ሊረዷቸው ዕጣ ተጣጥለው ወደየቤታቸወ ሄዱ፡፡ በመጀመሪያ ተራ የደረሰው ሰው ከአንድ ሰዓት በኋላ ምግብ ይዞ ቢመለስ የአባ ቆራይ ጎጆ በብርሃን ተሞልታ አገኘ፡፡ ወደ ጎጆዋም ሲጠጋ ነበልባሉ እየፈጀው አላስቀርበው አለ፡፡ እርሱም በድንጋጤ ወደ መንደሩ ተመልሶ ለአካባቢው ሰው ነግሮ ሁሉም ተሰብስበው መጡ፡፡ መንደርተኛውም ካህናትን ይዘው ብዙ የምሕላ ጸሎትና እግዚኦታ ካደረሱ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ጎጆዋ እንዲገቡ ፈቀደላቸውና ገቡ፡፡ ነገር ግን አባ ቆራይን በሕይወት አላገኟቸውም፡፡ አስክሬናቸውን ብርሃን ከቦት አገኙት፡፡ ከአስክሬናቸው አጠገብ "የአባ ቆራይን አስክሬን ከዚህች ጎጆ ውስጥ እንድትቀብሩት፤ ወደ ሌላ ቦታ ወይም ቤተ ክርስቲያን ወስደን እንቀብራለን ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ ነገሩን በድፍረት ብትፈጽሙት በሀገሩ ላይ እግዚአብሔርን ቁጣ ታመጣላችሁ" የሚል ትእዛዝ በብራና ተጽፎ ተገኘ፡፡ በዚሁ ትእዛዝ መሠረት የአሀሩ ሕዝብ ተሰብስቦ አባ ቆራይን ታኅሣሥ 15 ቀን እዚያው ቀበሯቸው፡፡
❤ ከጥቂት ዘመናት በኋላ ባልና ሚስት የሆኑ ሰዎች መቆመም ሆነ መራመድ የማይችል ድውይ ልጃቸውን ይዘው ወደ ጸበል ሲሄዱ መሸባቸውና በአካባቢው ማደሪያ ሲፈልጉ የአባ ቆራይ ጎጆ ክፍት ሆኖ ታያቸውና ልጃቸውን ይዘው ሄደው ገቡ፡፡ ድውይ ልጃቸውን በአባ ቆራይ መቃብር ላይ ቢያስተኙት የኤልሳዕን አጥንት እንደነካውና ፈጥኖ እንደተነሣው ሙት ይህ ድውይ ልጅም በአባ ቆራይ መቃብር ላይ እንዳረፈ ወዲያው አፈፍ ብሎ በመነሣት እንደ እንቦሳ ጥጃ መዝለል ጀመረ፡፡ ወላጆቹም እልልታቸውን አቀለጡት፡፡ ወላጆቹም በነጋ ጊዜ ወደ መንደርተኛው ሄደው የተደረገላቸውን ተአምር ተናገሩ፡፡ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ የአባ ቆራይ በዓል በአካባቢውና አጎራባች ቦታዎች ሁሉ ዘንድ መከበር ጀመረ፡፡ የዕረፍታቸውም በዓል ታኅሣሥ 15 ቀን ሆነ፡፡
❤ አባ ቆራይ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለይተው እንደ ቅዱስ አልዓዛር (ሉቃ 16፡19-35) ለዚህ ዓለም ውዳቂ መስለው ለታላቅ ክብር የበቁ ጻድቅ አባት ናቸው፡፡ ዛሬም ልብሳቸውንና አካላቸውን ብቻ እያየን የምንንቃቸው ሰዎች እንደ አባ ቆራይ ያሉ ቅዱሳን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከልዑል እግዚአብሔር በቀር ማንም ማንንም የሚያውቅ የለም። ከባታችን አባ ቆራይ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
✝ #ከታኅሣሥ 14-20 ያለው ጊዜ " #ዕለተ_ብርሃን" ይባላል ። ፦ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱስ ያሬድን አስተምሕሮ መሠረት አድርጋ ታኅሣሥ 14 ቀን "ዕለተ ብርሃን" ትለዋለች። ሳምንቱን (ከታኅሣሥ 14-20 ነው)። በእነዚህ ዕለታት እሑድ በዋለበትን ቀን ማኅሌት ተቁሞ ብርሃን ተብሎ ይከበራል። ደግሞ "ሰሙነ ብርሃን" ስትል ታስባለች::
✝ "ብርሃን" በቁሙ የ #እግዚአብሔር ስሙ፤ አንድም የባሕርይ ገንዘቡ ነው። " #እግዚአብሔር ብርሃን ነውና:: ጨለማም በእርሱ ዘንድ የለችምና።" (ዮሐ 1፥4)
✝ በዚህ ዕለት "ብርሃን" በሚል መነሻ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ታስተምሠራለች:-
1. #እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑን። (ዮሐ 1፥5)
2.አምላካችን በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን (በዕለተ እሑድ) ዲያብሎስ ቅዱሳን መላእክትን ሲረብሽ "ለይኩን ብርሃን" ብሎ ብርሃንን መፍጠሩን። (ዘፍ. 1፥2 አክሲማሮስ)
3.ነቢያት አበው በጨለማው ዓለም ሆነው መከራ ሲበዛባቸው "ፈኑ ብርሃነከ - ብርሃንህን ላክልን" እያሉ መጮሃቸውን። (መዝ 42፥3)
4.ጩኸታቸውን የሰማ ከሦስቱ አካላት አንዱ #ወልድ (እውነተኛው ብርሃን) ወደዚህ ዓለም መምጣቱን። (ሉቃ 1፥26)
5."እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ሲል የባሕርይ ብርሃንነቱን እንደ ነገረን። (ዮሐ 8፥12)
6.ብርሃነ መለኮቱን በገሃድ መግለጡን። (ማቴ 17፥1)
7.ብርሃን የሆነችውን ሕግ፤ ወንጌልን እንደ ሠራልን:: (1ዮሐ 2፥9)
8.ድንግል #እመቤታችን ብርሃን፤ የብርሃንም እናቱ መሆኗን። (ሉቃ 1፥26፣ ራዕ 12፥1)
9.ቅዱሳኑ ብርሀን መባላቸውን። (ማቴ. 5፥14)
10.እኛ በሰው ፊት ሁሉ እንድናበራ መታዘዛችን። (ማቴ 5፥16) ሁሉ ይታሰባል።
✝ እርሱ ፈጣሪያችን #ክርስቶስ ጨለማውን በምሕረቱ አርቆልናልና ዳግመኛ ወደ ጨለማ እንዳንሄድ እየለመንን እናመስግነው።
✝ " #ክርስቶስ ብርሃን ዘአሰሰልከ ጽልመተ።
ላዕለ ኪሩቤል ነቢረከ ዘትሬኢ ቀላያተ።
ስቡሕኒ ወልዑል አንተ"። (መልክአ ኢየሱስ) ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካች_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ #ለስብከት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፪ "#ወልዶ_መድኅነ_ንሰብክ ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ፣ አዝ፤ #አክሊለ_ሰማዕት_ሠያሜ_ካህናት ወተስፋ መነኰሳት #ወልዶ_መድኅነ_ንሰብክ ወልዶ መድኅነ ንሰብከ"። ትርጉም፦ ቅድመ ዓለም በክብር በጌትነት የነበረ ዛሬም ያለ ወደ ፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር #መድኃኒት_ልጁን_እንሰብካለን እርሱም #የሰማዕታት_ዘውድ_ነው_የካህናት_ሿሚ_ነው፣ የመነኰሳት ተስፋ ነው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው።
✝ ✝ ✝
❤ #ስብከት፦ ይህች ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት "ስብከት" ትባላለች:: ስብከት ማለት በቁሙ "የምስራች አዲስ ዜና መንገርን" የሚመለከት ሲሆን ዋናው ምሥጢር ግን ከነገረ ድኅነት (ከመዳን ትምሕርት) ጋር የተገናኘ ነው።
❤ በዚህ ዕለት (ሳምንት) ሁሉም ነቢያት ከነ ትንቢታቸው ይታሰባሉ። ዘመነ ስብከትም ከታኅሣሥ 7 እስከ 13 ያለውን ይይዛል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ በአንዱ እሑድ በሚውለበት ቀን ማኅሌት ተቁሞ ስብከት ተብሎ ይከበራል።
❤ ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሀብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ። በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፤ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት። በኋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው።
❤ ከዚህ በኋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር። ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር፤ ሱባኤ ይቆጠር፤ ምሳሌም ይመሰል ገባ።
❤ ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ። ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል። ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት/ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል።
❤ ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም፤ በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል። እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል። መድኅን ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል::
❤ ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር)፤ መጻዕያትን (ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው። ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በጸጋ ይሰጠዋል። እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ።
❤ ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም። በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ። (የሐዋ ሥራ 11፥27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ፣ ይገስጻሉ።
ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር፤ ወተናጸሩ ገጸ በገጽ፤ መንፈስን ንጹሕ በማድረግ ነቢያት እግዚአብሔር አይተውታልና ፊት ለፊት ተያይተዋልና"። እንዳለ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም።
❤ የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ፤ አንዳንዶቹም በእሳት፣ አንዳንዶቹም በሰይፍ፣ አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል። ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል።
❤ ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ፤ እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል። ዮሐ. 4፥36
❤ ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል፣ ሽተዋልም። "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል። (ማቴ. 13፥16፣ 1ኛ ጴጥ 1፥10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው፤ ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ።
ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት 15ቱ አበው ነቢያት፣ 4ቱ ዐበይት ነቢያት፣ 12ቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ።
❤ "15ቱ አበው ነቢያት" ማለት፦
1 ቅዱስ አዳም አባታችን
2 ቅዱስ ሴት
3 ቅዱስ ሔኖስ
4 ቅዱስ ቃይናን
5 ቅዱስ መላልኤል
6 ቅዱሴ ያሬድ
7 ቅዱስ ኄኖክ
8 ቅዱስ ማቱሳላ
9 ቅዱስ ላሜሕ
10 ቅዱስ ኖኅ
11 ቅዱስ አብርሃም
12 ቅዱስ ይስሐቅ
13 ቅዱስ ያዕቆብ
14 ቅዱስ ሙሴና
15 ሳሙኤል ናቸው።
✝ "4ቱ ዐበይት ነቢያት"
1 ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
2 ቅዱስ ኤርምያስ
3 ቅዱስ ሕዝቅኤልና
4 ቅዱስ ዳንኤል ናቸው።
❤ "12ቱ ደቂቀ ነቢያት"
1 ቅዱስ ሆሴዕ
2 ቅዱስ አሞጽ
3 ቅዱስ ሚክያስ
4 ቅዱሴ ዮናስ
5 ቅዱስ ናሆም
6 ቅዱስ አብድዩ
7 ቅዱስ ሶፎንያስ
8 ቅዱስ ሐጌ
9 ቅዱስ ኢዩኤል
10 ቅዱስ ዕንባቆም
11 ቅዱስ ዘካርያስ
12 ቅዱስ ሚልክያስ ናቸው።
❤ "ካልአን ነቢያት" ደግሞ፦
1 ቅዱስ ኢያሱ
2 ቅዱስ ሶምሶን
3 ቅዱስ ዮፍታሔ
4 ቅዱስ ጌዴዎን
5 ቅዱስ ዳዊት
6 ቅዱስ ሰሎሞን
7 ቅዱስ ኤልያስ
8 ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው።
❤ ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ፦
1 የይሁዳ (ኢየሩሳሌም)
2 የሰማርያ (እሥራኤል)
3 የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ።
❤ በዘመን አከፋፈል ደግሞ፦
1 ከቅዱስ አዳም እስከ ቅዱስ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት)።
2 ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ እስከ ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)።
3 ከቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት)።
4 ከቅዱስ ዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ። ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ፔጅ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ፈኑ እዴከ እምአርያም። አድኅነኒ ወባልሐኒ እማይ ብዙኅ። ወእምእዴሆሙ ለደቂቀ ነኪር"። መዝ 143፥7። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 1፥1-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 3፥1-10 እና የሐዋ ሥራ 3፥17-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥44-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የስብከት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።