🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts
前往频道在 Telegram
ይህ በአቡ ጁነይድ ሳላህ አህመድ የቀረቡ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክቶች የሚሰበሰቡበት ቻነል ነው። አላህ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር ያግራልን! You can contact me here @salehom100
显示更多2 212
订阅者
-124 小时
-67 天
-3230 天
帖子存档
🔖 የኑህ መርከብ
🎙 አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
የቢድዓን አደጋዎች የሚያብራራ እና ለቢድአ አራማጆች ማደናገሪያ ሹብሐዎች ምላሽ የሚሰጥ በጃሊያ አዳራሽ የቀረበ ጠቃሚ ትምህርት
ትምህርቱ በነሲሓ ድረ
http://nesiha.com/wp-content/uploads/2018/05/የኑህ-መርከብ.mp3
@abujunaidposts
📌 በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!!
ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በተከበሩት መልእክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። በመቀጠል፤
ያለንበትን የረጀብ ወር በማስመልከት የሚፈፀሙ የቢድዓ ተግባራት ተበራክተዋል። የረጀብን የመጀመሪያ እለት፣ የመጀመሪያ ጁምዓ፣ አስራ አምስተኛውን እለት እንዲሁም ሀያ ሰባተኛውን ቀን ማክበር ቢድዓ መሆኑን፤ በሌሎች ወሮች እንደሚፈፀሙት የሰኞና ሀሙስ ወይም አያመልቢድ ፃሞች ካልሆነ ወሩን አስመልክቶ የተደነገገ ልዩ ፆምም ይሁን ሰላት እንደሌለ ገልጫለሁ። ይህ ማለት ግን ረጀብን ከሌሎች ወራቶች የሚለየው ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም።
የረጀብ ወር፤ በሱረቱል ተዉባህ ቁጥር 36 ከተጠቆሙት የተከበሩ አራት ወራት (አሽሁሩል ሁሩም) አንዱ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፤
[إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِنْدَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْراً فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ فَلا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنْفُسَكُمْ] التوبة/36
« አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር፤ በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ (በጥብቁ ሰሌዳ ለውሀልማህፉዝ) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን (የሰየመው) ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤» አልተውባህ 36
عَنْ أَبِي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ , ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ , وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ) رواه البخاري ومسلم.
ከአቢ በክራህ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «አመት አስራ ሁለት ወራት ነው፤ ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት) የ”ረጀብ” ወር ነው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ዙልሂጃ የታወቀው የሀጅ ወር ነው፤
ዙልቂዕዳ ደግሞ ሁጃጆች ወደ መካ የሚያቀኑበት ወር ሲሆን፤
ሙሀረምም ከሀጅ ስነስርአት በኋላ ሰዎች ወደቀያቸው የሚመለሱበት ወር ነው። አላህ ረጀብንም ከእነዚህ የረከበሩ ወራት አድርጎታል።
እነዚህ ወራት (የተከበሩ) ናቸው ስንል፤
1- እነዚህ ወረሰቶች ጦርነት የተከለከለባቸው ወራት ናቸው።
ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈፀመባቸው እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ ካልሆነ በስተቀር ውጊያ አይፈቀድም።
2- በነዚህ ወራት አላህ ክልክል ያደረጋቸውን ነገሮች መፈፀም በሌላ ወራት ወንጀልን እንደመፈፀም አይደለም። ስለዚህም አላህ እነዚህን ወራቶች ለይቶ ነብሳችንን እንዳንበድል አሳስቦናል፤ «በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ» ።
እራስን መበደል አስከፊ መሀይምነት ነው። በአንድ ሰውና በጌታው መካከል የሚፈፀም እራስን መበደል ለአላህ መፈፀም የሚገባን ሀላፊነት አለመወጣት ነው። በራስ ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ትልቁ በአምልኮ ፍጥረታትን ከአላህ ጋር ማጋራት “ሽርክ" ነው። ሰዎች ላይ የሚፈፀም በደልም ቢሆን የሚጎዳው ሰሪዉን ነውና እራስን መበደል ነው። ለራሱ ያወቀ በማንኛውም ጊዜ ከበደል ይርቃል።
ኢባደላህ!
አላህ እነዚህን ወራቶች አክብሯቸዋልና እኛም ከፍተኛ ክብር መስጠት ይገባናል።
እነዚህ ወራቶች ሲገቡ፤ አላህ ክብርን እንደለገሳቸው ልናስታውስና ከወንጀል ለመራቅ ያለንን ቁርጠኝነት ልናድስ ይገባል። ይህ ልባዊ ኢባዳ ነው።
ወንጀልን በማንኛውም መፈፀም የተከለከለ ቢሆንም በነዚህ ወራት ግን ክልክልነቱ የበረታ ነው።
ስለዚህም ከምንም አይነት ወንጀሎች መጠንቀቅ እና ወደ አላህ መመለስ ያስፈልገናል። ከትናንሽም ይሁን ከትላልቅ ወንጀሎች በአላህ እንጠበቅ።
ሸይጣንን እናሸንፍ!
አላህ ከጥፋት ይጠብቀን..
አሚን!!
አኹኩም ፊላህ አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
http://t.me/abujunaidposts
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
#መጅሊስ በአዋጅ መፅደቁ በእጅጉ ያስደስታል። በቀጣይ ተቋሙን በሚመጥን አደረጃጀት በአስቸኳይ ይታደስ ዘንድ የሁሉንም ጥረት ይጠይቃል።
አላህ ያግራው!
http://t.me/abujunaidposts
የሸዋልን ፆም ለጀመሩ እህቶች አምስት አስፈላጊ ጥቆማዎች
الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه، أما بعـد:
ከሸዋል ፆም ጋር በተያያዘ ብዙ እህቶች ከሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በመነሳት አምስት ጥቆማዎች ይኖሩኛል፤
1) ቀዳ ያለባት ሴት ከቀዳና ከሸዋል ሱና የትኛውን ታስቀድም?
☞ በሀይድ ወይም በወሊድ ደም ምክኒያት ረመዳንን አሟልታ ያልፆመች ሴት፤ ከሸዋል ስድስት ቀናት መፆምን አስመለክቶ በሀዲስ የተጠቀሰውን የአንድ አመት ፆም ምንዳ ለማግኘት አጅሩን እንደሚያገኝ ቃል የተገባለት ረመዳንን ካሟላ በኋላ የፆመው ሰው ስለሆነ፤ ቅድሚያ ረመዳንን መፆም ግድ ስለሚል በተቻላት መጠን ከሸዋል ሱና በፊት የረመዳንን ቀዷ ለማጠናቀቅ መሞከር ይኖርባታል።
📚 የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ይህንን በማስመልከት እንዲህ ብሏል፤ ¹ «ከረመዳን የተወሰኑ ቀናት ያሉበት ሰው በቅድሚያ እነሱን ሊፆምና ከዛ በኃላ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ሊፆም ይገባል፤ ምክኒያቱም ረመዳንን አስከትሎ ከሸዋል ስድስት ቀን ሊፆም የሚችለው ረመዳንን አሟልቶ ከፆመ ነው።» ፈታወለጅናህ 10/392
ይህንን መተግበር ሴቶች ያለባችውን ቀዷ በጊዜ መክፈል ይችሉ ዘንድ ያበረታቸዋል።
2) የረመዳንን ወር በሙሉ ካልፆመችስ?
📚 ሸይኽ ኡሰይሚን እንደገለፁት²
በወሊድ ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክኒያት ረመዳንን ሙሉዉን መፆም ያልቻለች ሴት ሸዋልን ቀዳ በማውጣት ከጨረሰችና ስድስቱን የሱና ቀናት መፆም የምትችልበት ጊዜ ሸዋል ውስጥ ካላገኘች የዘገየችው ከአቅም በላይ በሆነ ምክኒያት (ደሩራ) ስለሆነ ቀጣዩ የዙልቂእዳ ወር ከገባ በኃላም ቢሆን በሸዋል ሱና ነይታ ፆሟን ብታሟላው ኢን ሻ አላህ አጅሩን ታገኛለች። ይህንን መልእክት ያዘለውን የሸይኽ ኡሰይሚን ፈትዋ በመጅሙኡል ፈታዋ 20/19 ያገኙታል
3) ቀዳና የሸዋል ሱናን በአንድ ኒያ መፆም
📚 ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ (ኑሩን አለደርብ)² የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ላይ ተጠይቀው ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፤ «የስድስቱን ቀናት ፆም ከፈለገች በቅድሚያ ቀዳ አውጥታ በመቀጠል ሱናውን ፆም ትፁም። በሸዋል ወር ቀዳ አውጥታ ስድስቱን ቀናትም ከፆመች ትልቅ ኸይር ነው። የስድስቱን የሸዋል ቀናት ፆም ከቀዳ ጋር በአንድ ኒያ ብትፆም ግን የስድስቱን ቀናት አጅር ታገኛለች ብዬ አላስብም። የሸዋል ፆም የሚፆመው በተገደበ ጊዜ ሲሆን እራሱን የቻለ ኒያ ይፈልጋል።»
ስለዚህም ሁለቱን በአንድ ላይ መፆም ሳይሆን ቅድሚያ ረመዳንን አሟልቶ ሱናውን ፆም መጀመር ተገቢ ነው።
4) የሸዋል ወር ሳያልቅ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቀናት ቢያልፉስ?
☞ ብዙ ሴቶች የሸዋል ፆም የሚባለው ወሩ እንደገባ ያሉት ስድስት ቀናት ብቻ ይመስሏቸዋል። ይህ ስህተት ነው። በሀዲሱ የተጠቀሰው ምንዳ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናት የፆመን ሰው ሁሉ ይመለከታል። ይህ ደግሞ መጀመሪያም መጨረሻም በመካከልም ሊሆን ይችላል።
5) የሸዋልን ፆም አከታትሎ መፆም
☞ ሸዋል እንደገባ ብዙ ሰዎች አከታትለው በመፆም ይጨርሳሉ። ይህም ስንፍናን ለማስወገድና በረመዳን ያካበቱትን የመፆም ብቃት ላለማጣት ከማሰብ ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ሰኞና ሀሙስ እንዲሁም አያመልቢድ በመፆም ሱና ፆም የመፆምን ልምድ ማዳበርም መልካም ነው። አንዳንድ ሴቶች አከታትለው መፆማቸው ግዴታ ስለሚመስላቸው ከመፆም ይሳነፋሉ። ይህ ሊታረም የሚገባው ግንዛቤ ነው።
አላህ ፆማችንን ይቀበለን ዘንድ እማፀነዋለሁ!
አቡጁነይድ ሸዋል 4/10/1436
————// ————
¹ (...والذي ينبغي لمن كان علي شيء من أيام رمضان أن يصومها أولا ثم يصوم ستة أيام من شوال ؛ لأنه لا يتحقق له اتباع صيام رمضان لست من شوال إلا إذا كان قد أكمل صيامه . وبالله التوفيق وصلى الله على نبينا محمد وآله وصحبه وسلم ) فتاوى الجنة الدائمة 10/392
² سئل الشيخ ابن عثيمين رحمه الله تعالى عما إذا كان على المرأة دين من رمضان فهل يجوز أن تقدم الست على الدين أم الدين على الست ؟
فأجاب بقوله : "إذا كان على المرأة قضاء من رمضان فإنها لا تصوم الستة أيام من شوال إلا بعد القضاء ، ذلك لأن النبي صلى الله عليه وسلم يقول : ( من صام رمضان ثم أتبعه ستا من شوال ) ومن عليها قضاء من رمضان لم تكن صامت رمضان فلا يحصل لها ثواب الأيام الست إلا بعد أن تنتهي من القضاء ، فلو فرض أن القضاء استوعب جميع شوال ، مثل أن تكون امرأة نفساء ولم تصم يوما من رمضان ، ثم شرعت في قضاء الصوم في شوال ولم تنته إلا بعد دخول شهر ذي القعدة فإنها تصوم الأيام الستة ، ويكون لها أجر من صامها في شوال ، لأن تأخيرها هنا للضرورة وهو ( أي صيامها للست في شوال) متعذر، فصار لها الأجر" انتهى مجموع الفتاوى 20/19
³ سئل الشيخ ابن باز رحمه الله
هل يجوز للمرأة الجمع بين صيام ستة أيام من شوال وقضاء ما عليها من رمضان في هذه الأيام الستة بنية القضاء والأجر معاً، أم لا بد من القضاء أولاً ثم صيام ستة أيام من شوال؟
نعم، تبدأ بالقضاء، ثم تصوم الست إذا أرادت، الست نافلة، فإذا قضت في شوال ما عليها ثم صامت الست من شوال فهذا خير عظيم، وأما أن تصوم الست بنية القضاء والست فلا يظهر لنا أنه يحصل لها بذلك أجر الست، الست تحتاج إلى نية خاصة في أيام مخصوصة.
http://www.binbaz.org.sa/node/13470
والله تعالى المسؤول أن يوفقنا لما يحب ويرضى
t.me/abujunaidposts
🔊 አህሉልበይት እነማን ናቸው?
🎤 አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
🗞 የአቡጁነይድ መልዕክቶች
https://t.me/abujunaidposts/17
የባጢል ሰዎች አጃቢ የፔጅና ግሩፖቻቸው አሟሟቂ እንዳንሆን!
√ እራስን ማጥራት ግዴታ ነው!
በሳንባ በሽተኞች መካከል፤ በተበከለ አየር ውስጥ ካለመከላከያ የሚኖር ሰው ስለጤንነቴ እጨነቃለው ቢለን አትቀልድ እንለዋለን።
ለፀረ ኢስላም አቡጃህሎች ጆሮውን ያዋሰ ሁሉ ሊነቃ ይገባዋል። ግሩፓቻቸውን ያሞቁ ፔጆቻቸውን በላይክ ያደመቁ ሁሉ ሊያስቡበት ይገባል። ለአላህና ለመልእክተኛው ያላቸውን ክብር፤ ለኢስላም ያላቸውን ቁርጠኛ እምነት ካስተዋሉ ከከሀዲያን ጋር ለመቀመጥ ትእግስቱ አይኖራቸውም። አራስን ማፅዳትም ተቀዳሚ ተግባራቸው ይሆናል።
( وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آَيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّى يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ ) النساء/140 .
«በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ፤ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ፣ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከነርሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፤ እናንተ ያን ጊዜ ቢጤያቸው ናችሁና፤ አላህ መናፍቃንን እና ከሐዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና» ኒሳእ 140
ኢስላምን ከምንጩ መማር፤ ልብን ንፁህ በማድረግ፤ እራስን በእውቀት በማበልፀግና በአላህ በመታገዝ ማንኛውንም አይነት መደናገርና የቀልብ በሽታ መከላከል ይቻላል።
የአላህን ውዴታና ፍቅር ከፈለግን ኢስላማዊ እውቀትን ከትክክለኛ ምንጮች እናጣጥም።
ባወቅን ቁጥር ብርሀን እንደሆነና ጨለማን እንደሚገላልጥ እንረዳለን።
አዎ! ኢስላምን ከምንጩ እንረዳው፤ ያን ግዜ ለሚነሱ ሹቡሀቶች ሁሉ የኢስላም ሊቃውንት ምን ያክል የማያዳግሙ ምላሾችን እንደሰጡ በዝርዝር ማወቅ እንችላለን። እነዚህ ግሳንግስ ማወናበጃዎች ሁሉ በቁርአናዊ አስተምህሮ እንደሸረሪት ድር ሲበጣጠሱ እናስተውላለን።
ኢስላምን ስንኖረው ጉዞአችን መሰናክሎች የተደረደሩበት ነው። ስሜታችንን ተከትለን ለዱንያ እጅ ሰጥተን ከመስመር እንድንወጣ፤ አለያም ውዥንብሮችን በመስማት መደናገር ውስጥ እንድንገባ ሌት ተቀን የሚለፉ የሸይጣን ወታደሮች ብዙ ናቸው። ከኛ የሚጠበቀው፤ ጥሩ የጉዞ ጓደኞችን መቅረብና ጉዞአችንን የሚያሰናክሉ ሽፍቶችን መራቅ ነው።
አላማ ያለው ሰው ለስኬት የሚያበቁትን እርምጃዎች መሳት የለበትም፤ መርከብ በየብስ አይጓዝምና!!
Abujunaid
https://t.me/abujunaidposts/15
📄 ነብዩን የሚወድ ባልደረቦቻቸውን አይጠላም!
✍ አቡጁነይድ
በሶሐቦች ታማኝነት ዙርያ ለ አልሐረሪ ዕይታዎች የተሰጠ ማስተካከያ (1434 ዓ.ሒ)
https://t.me/abujunaidposts/13
🗞 የአቡጁነይድ መልዕክቶች
ይህ ከአቡ ጁነይድ ሳላህ አህመድ የቀረቡ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክቶች የሚሰበሰቡበት ቻነል ነው።
አላህ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር ያግራልን!
https://t.me/abujunaidposts
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
