የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
前往频道在 Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
显示更多4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
4 374
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ።
JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
👆👆👆
በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ ! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

🌾✞ #ጽኑ_ሰማዕት ✞🌾
https://t.me/EOTC2921
ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ
ነይ ነይ ቅዱስ አትናትዮስ
›› ›› በስዕለት ያገኙሽ
›› ›› ብሉይን ከሀዲስ
›› ›› ጠንቅቀሽ የተማርሽ
›› ›› በፍፁም ትህትና
›› ›› በጸሎት የተጋሽ
›› ›› አርሴማ ልዩ ነሽ
›› ›› አምላክ የመረጠሸ።
#አዝ---✞---
ነይ ነይ ውበትም ሀሰት ነው
›› ›› ደም ግባትም ከንቱ
›› ›› ንብረት ትዳር ሁሉ
›› ›› አላፊ ውዕቱ
›› ›› ንግስት መባልን
›› ›› በፍጹም ሳትሻ
›› ›› አለምን በመናቅ
›› ›› ገባች ወደዋሻ።
#አዝ---✞---
ነይ ነይ አረመኔው ድርጣድስ
›› ›› ቢያሰቃይሽም
›› ›› ውበቴ ክርስቶስ
›› ›› ነው ብለሽ ሰበክሽ
›› ›› አንገትሽን ለሰይፍ
›› ›› አሳልፈሽ ሰጠሸ
›› ›› ክብርሽም ተገልጾ
›› ›› ለአለም አበራሽ።
#አዝ---✞---
ነይ ነይ አርአያ ልትሆኝን
›› ›› ለእኛ ለሁላችን
›› ›› ፈፅመሽ አሳየሽ
›› ›› ታላቅ ተጋድሎሽን
›› ›› ይህን አለም ድል መንሳት
›› ›› አቅቶናል እና
›› ›› አርሴማ አትለይን
›› ›› በእምነት እንድንጸና።
#አዝ---✞---
ነይ ነይ ሀኪምም አልሿ
›› ›› ምን ያደርግልኛል
›› ›› አዋቂም አልሻ
›› ›› ምን ያደርግልኛል
›› ›› በአርሴምዬ ፀበል
›› ›› አይኔ በርቶልኛል።
#አዝ---✞---
4 374
#ተባረኩኝ_ጠራኝ_ጸሎቷ
ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ
ልሳለማት ልሂድ እቤቷ
ፍቅሯ ልዩነው ደግነቷ
እናቴ አርሴማ ሰማእቷ
እግሩ ያነከሰ ክንዱ የዛለበት
ደስታ የራቀው ሰው ህመም የጸናበት
ልቡ የደከመ መንገድ የጠፋበት
አፍሮ አይመለስም ደጅሽ የመጣለት
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ያንሁሉ ቁልቁለት ያንሁሉ ጋራ
እንዴት ልጓዝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ድረሽልኝ ብዬ ላንቺ ስናገር
እንደእንቦሳ ጥጃ እዘለው ጀመር
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ላይድን መችይመጣል ላይለቀው ችግሩ
አንቺስ መችልጠሪው ሲነሳ ከክብሩ
አቤት ቃል-ኪዳንሽ እንዴት ይገለፃል
አምኖ የመጣ ሰው ድኖ ተመልሶል
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
የውስጥ ደዌውን ህመሙን ደብቆ
ገስግሶ የመጣ ካለሽበት ዘልቆ
ድኖ ተመለሰ ዝናሽን አሰማ
ሰማቷ እናቴ እያለሽ አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
አንደበትን ስጪኝ እመሰክራለው
በሶስት ፍሬቆሎ ስታድኚ እያየው
ነግሬሽ ነበረ ችግሬን በሙሉ
አላሳፈርሽኝም ተፈታልኝ ሁሉ
4 374
#አርሴማ_ቅድስት
አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት(፪)
ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ ፊት
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ተዐምርሽ ልዩ ነው.......አርሴማ
ገድልሽ አስደናቅ.........አርሴማ
ስምሽ ብርሃን ነው.......አርሴማ
ማለዳ ፈንጣቅ............አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ሥምሽን እየጠሩ..........አርሴማ
ይጠግባል የተራበው.....አርሴማ
ምስኪኑም ዘመረ...........አርሴማ
በአንቺ አልፎ መከራው......አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ጽኑ ነው ኪዳንሽ..............አርሴማ
የተሰጠሽ ከአምላክ........አርሴማ
በአይኔ አይቻለው............አርሴማ
ጠላት ሲንበረከክ............አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ዓለም ይስማው ዛሬ........አርሴማ
ስለ ተጋድሎሽን..............አርሴማ
ይገረም ይደነቅ...............አርሴማ
ይመስክር ዝናሽን.........አርሴማ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ሥምሽን እየጠሩ.........አርሴማ
ይጠግባል የተራበው......አርሴማ
ምስኪኑም ዘመረ...........አርሴማ
በአንቺ አልፎ መከራው.......አርሴማ።
4 374
☞ “…ለሊሁ እግዚአብሔር ዘበአማን ወወልደ እግዚአብሔር ዋሕድ ብርሃን
ዘእምብርሃን ወሕይወት ወኀይል ነሥአ ዘኢዚኣሁ…” (… አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ሕይወት ኀይል የሚኾን ርሱ እግዚአብሔር ባሕርዩ
ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወነአምን ቦቱ ከመ ውእቱ እግዚአብሔር ቃል ዘበአማን ወለድንግልሂ ንጽሕት ወላዲተ አምላክ ንሰምያ እመ እግዚአብሔር” (በእውነት ርሱ እግዚአብሔር ቃል እንደኾነ እናምንበታለን፤ አምላክን የወለደች ንጽሕት ድንግልንም የእግዚአብሔር እናት እንላታለን) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ምንት ውእቱ ተሳትፎ በእሉ ከመዝ ዘእንበለ ከዊኖቱ ከማነ በሥጋ ወደም እምድንግል ቅድስት ወላዲተ እግዚአብሔር ማርያም እንዘ ውእቱ አምላከ ጽድቅ…” (በሥጋ ሰዎችን መምሰሉ ምንድን ነው? የባሕርይ አምላክ ሲኾን እግዚአብሔርን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በነፍስ በሥጋ እንደ እኛ ሰው መኾኑ ነው እንጂ፤ ይኸውም ከአብ የተወለደ አካላዊ ቃል ነው፤ ለዘለዓለምም ከአብ ጋራ ትክክል ነው፤ በባሕርዩ ቀዳማዊ ነው፤ ልዕልና ባለው ጌትነት ርሱ ብቻውን ያበራል) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወከመዝ ንሕነ ነአምን ከመ ድንግል ቅድስት ኮነት ታኦዶኮስ (ቴኦቶኮስ)
ዘውእቱ ወላዲተ እግዚአብሔር ብሂል ወሶበ ወለደቶ ለነ መንክረ ለዋሕድ
ክርስቶስ በተሣትፎቱ ደመ ወሥጋ ከማነ” (እንደኛ ነፍስን ሥጋን በመዋሐዱ አንድ
ክርስቶስ ድንቅ በሚያሰኝ ልደት በወለደችው ጊዜም ንጽሕት ድንግል ታኦዶኮስ (ቴኦቶኮስ) (Θεοτόκος,) እንደኾነች እናምናለን፤ ይኸውም እግዚብሔርን የወለደች ማለት ነው) (ቅዱስ ቄርሎስ)
☞ “ወኮነ ሰማይ ዓለመ ወዓለምሂ ሰማየ ወኮነ እግዚአብሔር ሰብአ በታሕቱ
ወረሰዮ ለሰብእ ውስተ አርያም…” (ሰማይ ዓለም ኾነ፤ ዓለምም ሰማይን ኾነ፤
እግዚአብሔር ሰው ኾኖ በዚኽ ዓለም ተገኘ፤ ሰውንም በላይ በአርያም አደረገው፤ በሰማይ የሚቀርበው ምስጋና በዚኽ ዓለም ተደረገ፤ በአብ ዕሪና ያለ ርሱ
በማርያም ክንድ ተይዞ ታየ፤ እግዚአብሔር አብ በማይመረመር ምስጢር ያለ እናት የወለደውን ማርያም በማይመረመር ምስጢር ያለ ዘርዐ ብእሲ በሥጋ ወለደችው) (ቅዱስ ሳዊሮስ)
☞ “ወካዕበ ይቤ እስመ እግዚአብሔር አስተርአየ ለሰብእ በተወልዶ ወመጽአ ኀበ
ዕጓለ እመሕያው፤ ወዓዲ ይቤ ዝንቱ ውእቱ ቃለ እግዚአብሔር ዘኢይትገመር
ዘሀሎ እምቅድመ ኲሉ መዋዕል ዘአልቦቱ ሥጋ ነሥአ ሎቱ ሥጋ” (ዳግመኛ
እግዚአብሔር በመወለዱ ለሰው ተገለጠ፤ ወደ ሰውም መጣ አለ፤ ዳግመኛም የማይወሰን ከቀን ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እግዚአብሔር ቃል ይኽ ነው፤ ሥጋ ያልነበረው ሥጋን ነሣ) (ቅዱስ ሱኑትዩ)
☞ “በፈቃደ አቡሁ ወረደ ኀበ ማርያም ተአንገደ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ” (በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ
እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ) እንዲል ቅዱስ ዲዮስቆሮስ
በቅዳሴው
🙏[ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የኾንኽ አምላካችን
ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፈጽመን እናመሰግንኻለን]🙏
[ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾✞ #የኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔርነት ✞🌾
❖ የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት ትንቢትን በተናገሩ በቀደምት ነቢያት ፈንታ፤ በዓለሙ ኹሉ እግዚአብሔርነቱን በግልጥ ያስተማሩ ሐዋርያት ተተኩ፤ ከዚያም ምስጢሩን የሚያመሰጥሩ ሊቃውንት በሐዋርያት እግር ተተክተው የአምላካቸው የክርስቶስን እግዚአብሔርነት አምልተው አስፍተው
አስተምረዋል፤ ይኽም ትምህርታቸው ጥልቅና ሰፊ ሲኾን በጥቂቱ ትምህርታቸው እነሆ፡-
☞ “ወአግሐዶ ዮሐንስ ወአጥመቆ በውስተ ዮርዳኖስ፤ ተመከረ በገዳም
ወተዐውቀ ከመ እግዚአብሔር ውእቱ” (ዮሐንስ ገለጠው፤ በዮርዳኖስም
አጠመቀው፤ በገዳም ተፈተነ፤ ርሱም እግዚአብሔር እንደኾነ ታወቀ) (ቅዱስ
ሄሬኔዎስ)
☞ “ተሰቅለ በሕማመ ሥጋ ወሐይወ በኀይለ እግዚአብሔር ዘውእቱ መለኮቱ፤
ወወረደ ውስተ መትሕተ ዕመቀ ምድር ወጼወወ ነፍሳተ ሰብእ” (ለሥጋ
በሚስማማ ሕማም ተሰቀለ፤ በእግዚአብሔርነቱ ኀይል ተነሣ፤ ይኸውም መለኮቱ ነው፤ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ማረከ) (ቅዱስ ሄሬኔዎስ)
☞ “እግዚአብሔር ቃል ስለ እኛ እንደታመመ እግዚአብሔር ለእኛ ቤዛ እንደሞተ ብትሰማ፤ እኛ መለኮትን ከትስብእት ጋራ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አድርገን ለእግዚአብሔርነቱ በሚገባ በዚኽ ባንድ ስም እንደምንጠራው ዕወቅ… የእኛ አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፈቃድ በግብረ መንፈስ ቅዱስም ከዳዊት ዘር ከእመቤታችን ማርያም ተፀነሰ” (ቅዱስ አግናጥዮስ)
☞ “ክርስቲያኖች በምድር ከሚኖሩ ሰዎች ኹሉ በልጠው እውነትን አገኙ፤
በመንፈስ ቅዱስም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ወልድን፤ የኹሉ ነገር
ፈጣሪንና ሠሪን እግዚአብሔርን አወቁ” (አርስቲደስ)
☞ “እናንተ ግሪኮች እግዚአብሔር ከሰው ልጅ እንደተወለደ ስናስገነዝብ ስንፍናና
እየተጫወትን ወይም ተርታ ነገር እየተናገርን አይደለም” (ቴሽያን ሶርያዊ)
☞ “የእግዚአብሔር ቃል ክርስቶስ ከአብ ጋር በህልውና ያለ፤ እኛንም ያስገኘ፤
አኹንም ይኸው ቃል ሰው ኾኖ ተገለጠ፤ ርሱ ብቻ እግዚአብሔርም ሰውም የኾነ
እና የበጎ ነገራት ኹሉ ምንጭ ነው… በተዋሐደው ሥጋ ሲያዩት የተናቀ ቢኾንም እንደ እውነቱ ግን እጅግ ያማረ የተወደደ የተፈቀረ ነው፤ ኢየሱስ መድኀኒታችንና ኀጢአታችንን ይቅር ያለ ፈውሳችን የኾነ መለኮታዊ ቃል ሙሉ በሙሉ በርግጠኛነት በእውነት እግዚአብሔር ነው” (ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ)
☞ “እግዚአብሔር ክርስቶስ የኹሉም ነገር አምላክ በመኾኑ ከሰው ዘር በመላ
ኀጢአትን ጠራርጎ ዐጥቦ አሮጌውን ሰው ዐዲስ አድርጎታል” (ቅዱስ ሂፖሊተስ
(አቡሊዲስ))
☞ “ክርስቶስ ዕሩቅ ብእሲ ቢኾንማ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የኾንኽ አንተን
የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይኽች የዘላለም ሕይወት ናት”
በማለት ያስቀመጠውን ሕግ ለምን እንድናምን አደረገ? (ዮሐ ፲፯፥፫)፤
እግዚአብሔር መኾኑን እንድረዳው ባይፈልግ ኖሮማ ለምን “የላክኸውንም
ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ” ብሎ ለምን አከለበት? ይኽም እንደ
እግዚአብሔርነቱ እንድንቀበለው ነው፤ ይኽ ባይኾን ኖሮማ “የላክኸውን ሰው
ኢየሱስ ክርስቶስን” ይለን ነበር፤ በርግጥ ግን ርሱ ይኽነን አላከለበትም፤ ወይም
ክርስቶስ ራሱን ፍጹም ሰው ብቻ እንደኾነ አድርጎ አላቀረበልንም፤ ኾኖም ግን
ርሱ ራሱ እግዚአብሔር እንደኾነ እንድንረዳው ፈልጎ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር አስተካከለ እንጂ፤ በዚኽ መልኩ እንድረዳው ባይሻ ኖሮማ ራሱን በመነጠል ያቀርብ ነበር” (ኖቬሺያን)
☞ “ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደኾነ የካደ ሰው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ
(መቅደስ) ሊኾን አይችልም” (ቆጵርያኖስ (ሲፕርያን ዘካርቴጅ (ዘቅርጣግና))
☞ “የሕያው አካላዊ ቃል አባት አንድ እግዚአብሔር አለ፤ ርሱም ሕያው ጥበብ፣ ኀይልና ዘላለማዊ አካል ያለው፤ ፍጹም የኾነው ወልድን አካል ዘእምአካል
ባሕርይ ዘእምባሕርይ የወለደ የአንድያ ልጁ የባሕርይ አባት ነው፤ አንድ ጌታ
ከብቸኛው ከአብ የተገኘ ዋሕድ፤ ከእግዚአብሔር የተገኘ እግዚአብሔር፤ አባቱን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው፤ ከሃሊው ቃል፤ የኹሉም ነገር መሠረትና ማጠቃለያ የኾነ ጥበብ ባለቤትና የፍጥረታት ኹሉ አስገኚያቸው፤
የእውነተኛው አብ እውነተኛ ልጅ ወልድ፤ ከማይታይ የተገኘ ኅቡእ፤ ኅልፈት
ውላጤ ከሌለበት የተገኘ ኅልፈት ውላጤ የሌለበት፤ ከማይሞት የተገኘ ሕያው፤
ከዘላለማዊ የተገኘ ዘላለማዊ … እናም ወልድ ፈጽሞ አብን ወደ መኾን
አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም ወልድን ወደ መኾን አይለወጥም፤ ግን ያለምንም ልዩነት እና ያለምንም ለውጥ በእግዚአብሔርነት የተካከሉት ሥላሴ
ለዘለዓለም ይኖራሉ” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት)
☞ “እንግዲኽ የኾነ አንድ ቁጡ፤ የተናደደ እና የተደሰተ ሰው የእናንተ አምላክ
ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው? ብሎ ሊል ይችላል፤ በርግጥም ርሱ እግዚአብሔርና የተሰወሩት ኹሉ ኀይላት አምላካቸው ነው ብለን እንመልስለታለን” (አርኖቢዩስ)
☞ “ዝ ውእቱ ዘአጥፍኦ ለሞት ወሠዐሮ ለዲያብሎስ ዘምስሌሁ እዘዘ ሞት
በትንሣኤሁ ባሕቲቱ እግዚአብሔር ዘኮነ ሰብአ ወአስተርአያ በአርአያ ብእሲ” (ሞትን ያጠፋው ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ የሞት ሥልጣን የነበረው
ዲያብሎስን የሻረው ርሱ ነው፤ ሰው የኾነ በሰው ባሕርይ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
☞ “ዝንቱ ዘበአማን እግዚአብሔር ወወልደ እግዚአብሔር ወውእቱ እግዚእ ቡሩክ ላዕለ ኲሉ…” (ርሱ በእውነት እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ ከኹሉም በላይ የሚኾን የባሕርይ ገዢ ነው…) (ቅዱስ አትናቴዎስ)
☞ “ወውእቱ እግዚአብሔር ዘቦቱ ልደት በሥጋ በሕማማት ዲበ ዕፀ መስቀል
ወመዊት ወትንሣኤ” (በሥጋ መወለድ በመስቀል መከራ መቀበል መሞት፣
መነሣት ገንዘቡ የኾነ ርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው) (ቅዱስ ፊልክስ)
☞ “ተፈሥሒ ኦ ማርያም ምድር ቅድስት ዘበጽሐኪ እግዚአብሔር እንዘ ይጼዐን
ዲበ ደመና ብሩህ ወቦአ ውስቴትኪ፤ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ዘአስተርአየ እምኔኪ
እግዚአብሔር ዘየዐርፍ በቅዱሳኒሁ፤ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ዘሠምረ እግዚአብሔር ዘሀሎ እምቅድመ ዓለም ይትወለድ እምኔኪ ቃል ዘንሰግድ ሎቱ ምስለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ” (እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ኾኖ ወደ አንቺ የመጣ፤ በአንቺም ያደረ ምድር ቅድስት ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በቅዱሳን ዐድሮ የሚኖር እግዚአብሔር ቃል ከአንቺ ተወልዶ የተገለጠ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምንሰግድለት ቃል ከአንቺ ይወለድ ዘንድ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ እግዚአብሔር አንቺን የወደደ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ) (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
4 374
❖ “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ” (በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ)
የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ይደርብን፤ በቃል ኪዳኗ ትጠብቀን፡፡
🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
https://telegram.me/EOTC2921
4 374
#ሰማዕቷ_ቅድስት_አርሴማ
https://telegram.me/EOTC2921
✔✞ መስከረም 29 ቀን ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ያረፈችበት እለት ነው፤ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የቅድስት አርሴማ እናት አትኖስያ ትባላለች። ልጂ በማጣት ለረዥም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር። በኃላም እግዚአብሔር ልመናዋን ሰማት። ይህቺን ክብርት ቅድስት ልጅም ሰጣት። ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፣ 15 አመት ሲሆናት ሊያጋቧት አሰቡ፣ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም በድንግልና ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚያም በኃላ እንዲህ ሆነ፤ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጢያኖስ ሊያገባት ወደደ። ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማኒያ ሄደች። በዚያም በበረሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች። በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበረሃ እንደሚኖሩ ሰማ፤ ወታደሮቹንም ልኮ አስመጣቸው። የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ፤ የፊቷ ውበት እፁብ ድንቅ ግርማዋ የሚያስደንቅ ልብ የሚያርድ ነበረና ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም። በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት። ሌሎቹን ግን ለጣኦት እንዲሰግዱ ገፋፋቸው። ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃየኝ እያለች አምርራ ታለቅስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ወደደ፤ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦቱንም ትረግም ነበር። እርሷ ፀንታ ደናግሉን ታፀና ነበር፤ ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር። ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጣው ባወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ።
https://telegram.me/EOTC2921
✔✞ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በሗላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆርጧት ከእርሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል። በአገራችን በስሟ ሰሜን ወሎ ውስጥ ሲሪንቃ ቅድስት አርሴማ የሚያስገርም ገዳም አላት። በዚህ ገዳም 7 ቀን ብቻ ሱባኤ የሚገባ የልቡን መሻት
ትፈፅምለታለች። በመዲናችን አድስ አበባም የቅድስት አርሴማ
ቤተክርስቲያኖች አሉ። እንዲሁም አስኮ ቃሎ ተራራ ላይ የሚያስገርም ቤተ ክርስቲያን አላት። ይህንን የቃሎ ተራራ ሲወጡ ዝቋላ ትዝ ይላል። መስከረም 29 በደማቅ ተቦተ ህጉ ወጥቶ ተከብሮ ይውላል። ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ነው።
#የቅድስት_አርሴማ_ተጋድሎ_በቀደምት_የኢትዮጵያ_ሊቃውንት፦
https://telegram.me/EOTC2921
❖ ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕላቷን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ ገድሏን አጽፈዋል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች፤ ሊቁ እንደጠቀሰው እጅግ መልከ መልካም ነበረች ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር፤ በጊዜው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ
አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖ እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም
እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖ ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡ ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ
በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖ የመልኳን ደም ግባትም በማየት ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው ብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖ ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በክድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት
መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖ ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው።
❖ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ፤ ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን ተገልጾ ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም ፳፱ በ፪፻፺
ዓ.ም አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለችና፤ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ ፮ ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡
❖ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡
በረከቷን ለመሳተፍ በባሕር ማዶ የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ፣ በአውሮፓ በስዊድን በማልታና ስኮትላንድ ግላስኮ ይገኛሉ፨
❖ ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡- “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ” (በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡ (ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ
ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖ እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨
4 374
በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩት እንዳታልፋ
በቻናሉ ቀን በቀን አዳዲስ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይለቀቃል በማግስቱም
የቻናሉ አባላት ድምፅ ከሰጡ በኋላ
መልሱ ይለቀቃል። በጣም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ ቻናል ቻናሉን ለመቀላቀል
ከስር ያለውን JOIN የሚለውን ይጠቀሙ።
JOIN JOIN JOIN
JOIN JOIN JOIN
ከመከፈቱ የብዙዎች ቀልብ የሳበው
ማህሌት ቲዩብ እሆ አስተማሪ በሆኑ
ቪዲዮዎች መቶልናል። በቻናሉም
◽️መንፈሳዊ ጥያቄዎች
◽️መዝሙሮች
◽️ገድላት
◽️ታሪኮች
🔖ሁሉንም በአንድ ላይ በ ማህሌት ቲዩብ ያገኛሉ ይቀላቀሉን።
ቻናላችንንsubscribeበማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም
እንጠይቃለን ።
ማህሌት-ቲዩብን ለመከታተል
ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
4 374
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ።
JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
👆👆👆
በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ ! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
4 374
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ።
JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
👆👆👆
በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ ! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
4 374
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ።
JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
👆👆👆
በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ ! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
4 374
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ።
JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
👆👆👆
በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ ! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
4 374
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ።
JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng
👆👆👆
በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ ! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
https://youtu.be/SY-D-qGgT0U
👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው።
👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇
4 374
#ተይው_አታንሽው_ኀይሉን_ያሳይ!
https://t.me/EOTC2921
💠የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ በስደቷ ወራት ያደረገችው ተዓምር ይህ ነው፦ ደም ማፍሰስ የለመደ ርጉም ሄሮድስ ሚስቱን ማርያናንም ከገደላት በኋላ ይበቀሉኛል በማለት ከእርሷ የወለዳቸውን የገዛ ልጆቹንም ገደላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በሥጋው ጽኑ መከራ መጣበትና እግዚአብሔር የደዌውን ዘመን አስረዘመበት፡፡ ቢበላ ቢበላ አይጠግብም ይልቁንም ረሀብና ጥም ይበዛበታል፣ አንጀቱም ተቋጠረ፣ ሰውነቱም ተልቶ ሰው ሁሉ አልቀርበው አለ፡፡ ማቆ ሲያበቃ በመጨረሻም ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡
💠የእግዚአብሔርም መልአክ ዮሴፍን ሄሮድስ ስለሞተ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል እንዲመለስ ነገረው፡፡ ተመልሰውም በፍልስጤም አልፈው ድልማጥያ ወደምትባል አንዲት ገር ደርሰው በበረሃ ውስጥ ተቀመጡ፡፡ እመቤታችንም ከነልጇ ረኃቡ ቢጠናባት ትዕማን ወደምትባል አንዲት ከበርቴ ባለሀብት ቤት ሄዳ ቁራሽ እንጀራንና ለልጇም ጥቂት ወተትን ለመነቻት፡፡ ያቺ ክፉ ሴት ግን ልብን በሀዘን የሚሰብር ክፉ ንግግርን ተነጋረቻት፡፡ ጻድቅ ዮሴፍም ‹‹እንግዳን ካለ ይሰጡታል ከሌለ በሰላም ይሸኙታል እንጂ ለምን ክፉ ንግግርን ትናገሪያታለሽ?›› እያለ ሲነጋገሩ አሽከሯ ኮቲባ የእመቤቷን ቁጣ ሰምታ መጥታ ጌታችንን ከመሬት ላይ ጥላ እንደ ድንጋይ አንከባለለችው፡፡
💠እመቤታችንም እጅግ ደንግጣ እያለቀሰች ልጇን ፈጥና ልታነሣው ስትል ዮሴፍ ‹‹ተይው አታንሽው ኀይሉን ያሳይ›› አላት፡፡ ያንጊዜም ትዕማንን ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ገረዷ ኮቲባም በለምጽ ተመታች፡፡ በቤታቸውም ውስጥ በሕይወት የቀረ የለምና የሩቅ ቤተሰቦቿም ጦጣ ሆነው ከተራራ ወደ ተራራ ሸሹ፡፡ እመቤታች፣ ዮሴፍና ሰሎሜም በትዕማን ቤት 6 ወር ከተቀመጡ በኋላ መልአኩ ተገልጦ ከዚያ እንዲወጡ አዘዛቸውና ወጡ፡፡ አርዲስ ወደምትባል ሀገርም ደርሰው የሀገሪቱ ሰዎች በሰላም ተቀብለው አስተናገዷቸው፡፡ እመቤታችንም ከሀገረ ገዥው ሆድ ውስጥ በጸሎቷ እባብ ስላወጣችለትና ከሕመሙ ስላደነችው በጣም አከበሯቸው፡፡ ዕውሮችን፣ አንካሶችን፣ ለምፃሞችንና አጋንንት ያደሩባቸውን ሁሉ እያመጡላት የልጇን እጆች ይዛ ከሩቅ እያማተበች ፈወሰቻቸው፡፡ ሄሮድስም እንደሚያፈላልጋቸው መልአኩ ሲነግራቸው ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር እየተዘዋወሩ ታችኛው ግብፅ ንሂሳ ድረስ ደረሱ፡፡ እመቤታችንም በዚያ ያሉ ሕመምተኞችን ፈወሰችላቸው፡፡
💠ከዚህም በኋላ አሁንም መልአኩ ነግሯቸው ደመናም መጥታ ነጥቃ ወሰደቻቸውና የ38ቱን ወራት መንገድ በአንድ ጊዜ አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም ትንሽ ከቆዩ በኋላ ወደ ቤጎር ቆላ ደረሱ፡፡ በዚያም ግብፃውያን እንደ ሕጋቸው ለአማልክቶቻቸው ላሞችን አርደው ሠውላቸው፡፡ በጎሽ፣ በአውራሪስ፣ በነጭ ዝንጀሮ የሚመሰሉ አጋንንትም መጡ፡፡ እመቤታችንም ከሩቅ ሆና ተመልክታቸው እነዚያን አጋንንት በጸሎቷ እንደጢስ በተነቻቸው፡፡ ግብፃውያንም ፈርተው እየጮኹ ሸሹ፡፡ በዚያም ወራት ‹‹ረዳት አማልክቶቻችንን ጠፉብን›› ብለው እያዘኑ ሳለ ዮሴፍን ሲጸልይ አግኝተውት አስረው በምድር ላይ አስተኝተው 40 ግርፋት ገረፉት፡፡ እርሱም በዚህ ጊዜ ‹‹እመቤቴ ሆይ ስለ አንቺና ስለ ልጅሽ ይህ መከራ አግኝቶኛልና እርጂኝ›› ብሎ በኀይል ጮኸ፡፡ እመቤታችንም ድምጹን ስትሰማ የሄሮድስ ጭፍሮች የመጡ መስሏት እጅግ ደነገጠች፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ተገልጦ ካረጋጋት በኋላ ዮሴፍን በኀይል ይደበድቡ የነበሩትን በእሳት ሰይፉ ጨረሳቸው፡፡ ዮሴፍንም በእጆቹ ዳሰሰውና ፈወሰው፡፡
💠እመቤታችንም ዮሴፍን ባየችው ጊዜ ‹‹ይህ ሁሉ መከራ ያገኘህ በእኔና በልጄ ምክንያት ነው›› ብላው አንገት ለአንገት ተቀቅፈው ተላቀሱ፡፡ መልአኩም ‹‹ይሄ ሀዘናችሁ በደስታችሁ ጊዜ ይረሳል…›› እያለ አረጋጋቸውና ዐረገ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ይወጓቸው ዘንድ ወጡና ክፉ ውሾችን ለቀቁባቸው፡፡ ነገር ግን ውሾቹ በሰው አንደበት እመቤታችንን እያነጋገሯት ሰግደው የእግሯን ትቢያ ልሰው በመመለስ ባለቤቶቻቸውን መልሰው መናከስ ጀመሩ፣ ብዙዎቹንም ገደሏቸው፡፡ አገራዊ ዮሴፍም ‹‹እመቤቴ ሆይ በዚህ ሀገር ከምንኖርስ በዱር በበረሀ ብንኖር ይሻለናል›› ብሏት ወደለሌላ ትርጓሜዋ የሰላም ሀገር ወደሆነች ዲርዲስ ሀገር ደረሱ፡፡ ሰዎቹም ‹‹ይህችስ የነገሥታት ወገን ትመስላለች በላያችን ላይ ትነግሥብናለች›› ብለው በክፉ ሲነሱባቸው ደመና ነጥቃ ወስዳ ወደ ጋዛ ምድር አደረሰቻቸውና በዚያ አተር የሚያበራዩ ሰዎችን አግኝታ እመቤታችን ‹‹ለልጄ አተር ስጡኝ›› አለቻቸው፡፡ እነርሱም ክፉዎች ነበሩና ‹‹ይህ አተር ሳይሆን ድንጋይ ነው›› አሏት፡፡ ሕፃኑ ልጇም ‹‹እናቴ ሆይ እንደቃላቸው ይሁንላቸው ተያቸው›› አላት፡፡ ያንጊዜም አተሩ ድንጋይ ሆነ፣ ይህም እስከዛሬም ድረስ አለ፡፡ [በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን]
🙏✞አምላክን የወለደች የክብርት እመቤታችንን ረድኤት በረከቷ ይደርብን! የዓሥራት ሀገሯን ቅድስት ኢትዮጵያን ትጠብቅልን!✞🙏
4 374
😳✝ ታ ላ ቅ የ ም ሥ ራ ች ከ ታቦተ ፅዮን
ለአዲስ ዓመት ለ 2013 በሀገራች ኢትዮጲያ ውስጥ በምትገኘው የኢ/ት ጥንታዊ ገዳሞች ታሪክ የታቦተ ፅዮን ቤተክርስቲያን ታሪኮች ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን አማኞች በትግረኛ , በአማርኛ በ Youtube ቻናል ትምህርቶችን ለማስተማር ዝግጅቶችንን አጠናቀን መተናል ። በዚህ መንፈሳዊ የዩትዩብ ቻናል የተለያዩ ስብከቶችና ትምህርቶች በታላላቅ መምህራን በትግረኛ , በአማርኛ
🌻🎯ወንጌሎችን
🌻🎯 መዝሙሮች
🌻🎯 ስነ ፅሑፎች
🌻🎯 ምክረ አበው እና
ለመናፍቃን መልስ የምንሰጥበት የታቦተ ፅዮን ትክክለኛው የ Youtube ቻናል ነው ። ከታች ያለውን Link ተጭነው የ Youtube ቻናላችንን Subscribe ያርጉ !
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCJQ33VxRatkDMgl3CKcCDOQ?subconfirmation=yes
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ብስም መንበረ ታቦተ ፅዮን ዝተሰየመ መንፈሳዊ ናይ ዩትዩብ ቻናልና ብሊቃውንቲ ትግራይን ብዘማርያንን ዝ/ዩ ስብከታትን መዝሙራትን ምድላዋቱ ዛዚሙ ስርሑ ጀሚሩ ኣሎ ።
"ተመለሱ ፣ ኣበሳኹም መዓንቀፊ ኸይኰነኩምሲ፣ ካብ ኵሉ ግህሰትኩም ተመለሱ። ... ሓድሽ ልብን ሓድሽ መንፈስን ድማ ግበሩ" (ሕዝ 18፡30-31)