✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
前往频道在 Telegram
የጥበብ አፍቃሪ ኖት እንግዲያውስ ትክክለኛውን ቻናል አግኝተዋል። በቻናላችን 👉 በኔና በሌሎች የተፃፉ 👉ግጥሞች🌸 🌹ወጎች 🌸 🌹ልቦለዶች 🌸 አዝናኝ አስተማሪ ታሪኮችና ሌሎች ፅሁፎችን ያገኛሉ... ━━━━━━━━ ✦ ለማንኛውም አስተያየት @itsmetsita Paid Promotion @Tsiyon_awit ይጠቀሙ። Join us @Tsion_liboled
显示更多7 782
订阅者
+624 小时
-197 天
-4330 天
正在加载数据
吸引订阅者
十月 '2610月 '26
十月 '26
+38
在0个频道中
九月 '260
在0个频道中
Get PRO
八月 '260
在0个频道中
Get PRO
七月 '260
在0个频道中
Get PRO
六月 '260
在0个频道中
Get PRO
五月 '260
在0个频道中
Get PRO
四月 '260
在0个频道中
Get PRO
三月 '260
在1个频道中
Get PRO
二月 '260
在0个频道中
Get PRO
一月 '260
在0个频道中
Get PRO
十二月 '25
+12
在0个频道中
Get PRO
十一月 '25
+115
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+127
在1个频道中
Get PRO
九月 '25
+129
在1个频道中
Get PRO
八月 '25
+153
在1个频道中
Get PRO
七月 '25
+164
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+154
在2个频道中
Get PRO
五月 '25
+158
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+205
在4个频道中
Get PRO
三月 '25
+195
在4个频道中
Get PRO
二月 '25
+157
在2个频道中
Get PRO
一月 '25
+176
在3个频道中
Get PRO
十二月 '24
+264
在2个频道中
Get PRO
十一月 '24
+225
在1个频道中
Get PRO
十月 '24
+201
在2个频道中
Get PRO
九月 '24
+201
在2个频道中
Get PRO
八月 '24
+243
在1个频道中
Get PRO
七月 '24
+416
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+284
在0个频道中
Get PRO
五月 '24
+265
在1个频道中
Get PRO
四月 '24
+227
在3个频道中
Get PRO
三月 '24
+219
在1个频道中
Get PRO
二月 '24
+289
在1个频道中
Get PRO
一月 '24
+309
在2个频道中
Get PRO
十二月 '23
+145
在2个频道中
Get PRO
十一月 '23
+326
在2个频道中
Get PRO
十月 '23
+375
在3个频道中
Get PRO
九月 '23
+242
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+248
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+387
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+395
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+385
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+208
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+354
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+223
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+281
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+392
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+490
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+350
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+380
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+280
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+359
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+197
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+179
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+102
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+146
在0个频道中
Get PRO
二月 '22
+76
在0个频道中
Get PRO
一月 '22
+93
在0个频道中
Get PRO
十二月 '21
+94
在0个频道中
Get PRO
十一月 '21
+68
在0个频道中
Get PRO
十月 '21
+160
在0个频道中
Get PRO
九月 '21
+432
在0个频道中
Get PRO
八月 '21
+626
在0个频道中
Get PRO
七月 '21
+556
在0个频道中
Get PRO
六月 '21
+408
在0个频道中
Get PRO
五月 '21
+401
在0个频道中
Get PRO
四月 '21
+670
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 27 十月 | +1 | |||
| 26 十月 | +8 | |||
| 25 十月 | +5 | |||
| 24 十月 | +1 | |||
| 23 十月 | +2 | |||
| 22 十月 | 0 | |||
| 21 十月 | +4 | |||
| 20 十月 | +2 | |||
| 19 十月 | +5 | |||
| 18 十月 | 0 | |||
| 17 十月 | 0 | |||
| 16 十月 | 0 | |||
| 15 十月 | +3 | |||
| 14 十月 | +3 | |||
| 13 十月 | +1 |
频道帖子
| 2 | Nothing in this world truly excites me anymore. Everything that comes into my life seems to bring its own struggles, burdens, and challenges.
The only thing my heart longs for, day after day, is to dwell in the presence of God. For in His presence, I find a peace that the world cannot offer, a rest that nothing else can give, and a contentment that goes beyond all understanding.
His presence is my peace, His love is my satisfaction, and being with Him is all my heart truly desires.
As the psalmist declares in Psalm 73:25–26:
“Whom have I in heaven but you? And earth has nothing I desire besides you. My flesh and my heart may fail, but God is the strength of my heart and my portion forever.”
At the end of it all, I don't want a life filled with everything this world has to offer; I want a life filled with the presence of God. Let the world chase its treasures, its pleasures, and its temporary glory. As for me, give me Jesus. He is my greatest treasure, my eternal hope, and my soul's resting place. For to live is Christ, and to die is gain (Philippians 1:21). My heart belongs to Him, now and forever. 🙏❤️
Jesus Loves you | 1 437 |
| 3 | አንቺ ልጅ ነግሬሻለሁ ፍቅር ለወጣትነት እንጂ ለኑሮ አይሆንም.. የእኔስ ተበላሽቷል ሳይብስበት እገላገለዋለሁ እንጂ... እዪለች እያጉረመረመች ትሄዳለች...
አባቴ እናቴን ይፈራታል ስልህ ገርሞህ ነበራ? ወንድነት ጎድሎትኮ አልነበረም... ግን እሷ እንደምትፈልገው ሀብታም ባለመሆኑ ስታሳቅቀው አቅም አጣ.. የእሷ እንጂ የእሱ ፍቅር ገና አላለቀም ነበር... እና ሊረዳት ስለሚሞክር.. ስለምታሳዝነው ነው የሚሽቆጠቆጥላት...
እናቴ ለምን እራሷን እንዳጠፋች እኔም አባቴምእናውቃለን... እነዛ ለእናቴ ባለቀስኳቸው ስድስት ወራት ውስጥ የእናቴን ሕይወት ላለመድገም ስምል ስገዘት ነበር...
አንተ ግን በድንገት መሀላዬን ሰበርከው.. እንደ ክርስቶስ ሕጌን በፍቅር ሰበርከው...
እኔ ግን ይሁዳ ነኝ ወደሕጌ ተመለስኩ ፍቅርህን ሸጥኩት..."
ከተንተራስኳቸው ጭኖቿ መነሳት ባልፈልግም እየተነሳሁ
"ተይ እንደሱ አትበይ ያንቺ ጥፋት አይደለም አባትሽ ነው እሱንም ቢሆን ተረድቼዋለሁ እንደሚስቱ እንዳትሆኚ..."
"አይደለም! አይደለም! መስ ልትሰማኝ ይገባል እውነቱን መናገር አለብኝ... አባቴ አይደለም ያንን ያሰበው አባቴ ያመጣልኝ ሀብታም የለም እኔው እራሴ ነኝ ላገባው ነው ብዬ ለአባቴ ያስተዋወኩት... በቃ እነሱ ልክ ናቸው! አባቴን አስገድጄው ነው... እሱ እንዳውም ምን እንዳለኝ ታውቃለህ?
"እናትሽ ያልኖረችውን ሌላኛውን መጥፎ ምዕራፍ ልትኖሪው ወሰንሽ? እናትሽን ማዳን አልቻልኩም አሁን ደግሞ አንቺን" አለኝ እኔ ግን እንቢ አልኩት..."
"ውሸትሽን ነው!" መልሼ ጭኖቿ ላይ ልንተራስ ዘመም ስል.. በእጆቿ ጭንቅላቴን እየገፋች
"መስ እውነቴን ነው... ስለፈራሁ ነው.. እንደእናቴ የምሆን መሠለኝ... እኔም ልጄን በገዛ ፀፀቴ የማሰቃያት መሠለኝ... እራሴን ስገድል ማሰብ ፈራሁ.. በቃ ፍርሃቴ ከፍቅርህ ገዘፈብኝ..."
ተነሳሁ ትቻት ሄድኩ...
"መስ... መስ... ይቅርታ ልልህ አይደለም ግን ያንተን እሩቅ መልስ ስትደርስበት ግን ለመስማት ዝግጁ ነኝ ሙቼ ቢሆንምኳን.. ሰማኸኝ መስ... መስ..." ድምጿ እየራቀእ እየራቀኝ መጣ..
ትቻት ሄድኩ... ተናደድኩ በእራሴ ተናደድኩ.. እንደእናት ሲያደርጋት በነበረችው አሮጊት ተናደድኩ... በሯንና መስኮቷን ሰባብሬላት ወጣሁ... ሌላ ቤት ተከራየሁ...
እህቴ ያስመዘገበችኝ ውድድር በቴሌቪዥን ስለሚተላለፍና በጣም ጥሩ አካሄድ ላይ ስለነበርኩ ትልልቅ ቤቶች ላይ ስራ አገኘሁ...
ጥሩ ቤት ጥሩ ገቢ አለኝ.. ውድድሩም መጨረሻው ላይ ደርሶ አሸናፊው የሚለይበት የመጨረሻው ውድድር ላይ ነኝ
በሯን አንኳኳሁ... ልጇ ነበረች የከፈተችልኝ... አይገርምም ልክ ምናቤ ውጥ እንዳለችው ናት.. የሆነ አባት የሆንኩ ልጄ የሆነች ከሠላሜ የወለድኩ መስሎ ተሰማኝ... ግን እንደማይሆን ግልፅ ነው የረዠም ጊዜ የምናቤ ቅዠት ስለነበር ነው...
"እናትሽ አለች ሚጣዬ..."
"አዎ አለች ማሚ..."
እየጠራቻት ትታኝ ገባች...
"ጠይቀሽኝ ነበራ እሩቁ መልሴ ጋር ስደርስ እንድነግርሽ.."
በጭንቅላቷ አዎንታዋን ገለፀችልኝ ልታለቅስ እየዳዳት...
"ነገ የአሸናፊዎች ውድድር አለብኝ መልሱን መስማት ከፈለግሽ መምጣት ትችያለሽ" ብዬ መጥሪ ወረቀት ሰጠኋት።
እህቴ ምን ብላው እንደሆነ አላውቅም አባቴም ውድድሩን ለመመልከት መቶ ነበር... ግጥሙም ዜማውም እኔው ስለሆነና ሰምተውት ስለማያውቁ ዳኞቹ እንዳይጥሉኝ ፈርቻለሁ ግን ደግሞ ስሜቴን ነው የምዘፍነው...
ተራዬ ደረሰና ማይኩን ጨበጥኩ...
"ልሰማ አልጓጓሁም እንዴት እንደመጣ ስህተት..
ሆነ ምን ያደርጋል ቃልሽ ላይቀይረው እውነቱን!
ተይው ምን ያደርጋል ይቅር..
ጊዜ ያልፈቀደው ፍቅር!
እኔማ ፈራሁት ሁኔታሽን ሁሉ ሲወራ..
የሰው አፍ እንዲህ ነው ጠብቂ እራስሽን አደራ!
ምንም ባላቆይሽ ከኔ..
ክፉሽን አልየው ባይኔ!
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ደጁን አያምንምና
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ልቡን አያምንምና...
የሄደን ሰው ምን ይሉታ..
ከራስ አልፎ ለማን ይወቅሱታል!
እውነቱን አውቄ..
ህመሙን ደብቄ..
ልኑረው ዝምታን ሰንቄ!
ልጠይቅሽ ሁሉን ሲቻል..
ኧረ እንዴት ነው መለየት የሚቻል?
ልኑር ስንት አመታት..
የሰጠሽኝ ብርታት..
ቢሰጠኝ ፍቅርሽን ለመርሳት!
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ደጁን አያምንምና
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ልቡን አያምንምና...
ቀናት አልፎ ቀን ሲተካ..
ልብሽማ ከኔ ርቋል ለካ!
አላወኩም ነበር..
ይህ ሁሉ ሲፈጠር..
የፍቅራችን ፅዋው ሲሰበር!
በወደደው ሰው ሲገፋ..
የሞት ያህል ሀዘኑ ቢከፋ!
ስሜት እየጎዳ..
ቢሰጥም ለስቃይ.
አይሆንም ከይቅርታ በላይ!
ሌላው ሌላው ነገር ይቅር..
አይነገር ይሁን ያልፋልና ብቻ..
ሁኚ ደህና!
በሄድሽበት ክፉ አይንካሽ..
የቀረበሽ ርቆ አይጉዳሽ!
ሌላ ሌላው ነገር ይቅር..
አይነገር ምንም ቢኖር ጥፋት..
አልይ ያንቺን ጉዳት..
ልብሽ ወዶ ሰው አይጣ..
ላንቺ አይስጥሽ የኔን እጣ!
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ደጁን አያምንምና
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ልቡን አያምንምና..."
ለእሷ ብዬ ነበር አዝማሪ የሆንኩት.. እሷም ይሄ ስለሚገባት ዓይኖቼን እያየች አዝማሪ አላገባም ማለት ከብዷት በአባቷ አንደበት ተናገረችኝ...
ያልዘጋነው አንድ ነገር ነበር... እሱም እኔ ፍቅር ሲይዘኝ እንዴት እንደምገልፀው ማሳየት ነበር ደህና ይግጠምሽ ብዬ አሳይቻታለሁ.. ከእንግዲህምን ቀረኝ?
✍ሌዊ
@Lewi_derest | 1 523 |
| 4 | ፍቅራችን ለምለም ነበር.. ንፁህ አየር የሚወለድበት ንፁህ የተፈጥሮ ፍቅር... እዛች ቦታ ፍቅር ካልሰራን ተራራና ሜዳው የሚደርቅ እስኪመስለኝ ድረስ በፍቅራችን ተመካሁ...
ላፕቶፔንና መፅሀፎቼን ጥዬ ጊታርና ማይክ ሳነሳ አባቴ ከቤት አባረረኝ... አሁን መዝፈን ብቻ ሳይሆን መስራትም ግድ ሆነብኝ.. የምሽት ቤት ውስጥ መዝፈን ጀመርኩ.. በቂ ባይሆንም የቤት ኪራይና ሠላምዬ እቤት ስትመጣ ለምታፈላው ሻይ ይሆናል...
የሆነኛው ቀን ላይ የምላቸው ብዙ ናቸው.. ከእነዚል ብዙ የሆነኛው ቀኖቼ መሀል የሆነኛው ቀን ላይ ሠላሜ ደወለችልኝ
"መስ... ቶሎ ና ድረስልኝ አባቴ ለሀብታም ሊድረኝ ነው..." ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ነገረችኝ... ሄድኩኝ ስሮጥ ስበር ሄድኩኝ...
አባቷ ምን የሚያክል ዱላ ይዘው... "ልጄን ትነካና ውርድ ከራሴ! ጭራሽ ላዝማሪ ልጁን ዳረ ልታስብለኝ ነው?.. ዞርበል ብዬሀለሁ... በየበረንዳው አፍ ሲከፍቱ ማደር ሞያ መስሎሀል..."አባቷ ውሻ አርገው አባረሩኝ...
ተሰማኝ በጣም ተሰማኝ... ሠላምዬ እያየኋት መኪና ውስጥ ገብታ በረረች...
አከራዬ በጣም ጥሩ ሴት ናቸው የቤት ኪራይ ከከፈልኩ አመት ሊሆነኝ ነው.. እሳቸው ግን እንኳን የቤት ኪራይ... ከቦታችን ውዬ ስመጣ ምግብ ሁሉ ቤቴ አስቀምጣ ትጠብቀኝ ነበር...
በመንገድ ልጆች ሲያዩኝ ፈርተው ይሮጣሉ ፀጉሬና ፂሜ አድገው ጥቁር ጥርስ እንጂ ፀጉር አይመስሉም ነበር...
አንዳንዴ በሕፃናቱ ፈንታ ትላልቆቹ ምናለ ፈርተውኝ ቢሸሹ ብዬ እመኛለሁ... እኔን ሲያዩ ከከንፈር መጠጣቸው ቀጥሎ ሠላምዬን ያሙብኛል...
"ሠላም በል ብላው እንጂ አቶ መላኩ እንዲህም የሚናገር አይደለም..."
ሌላኛዋ ተቀብላ.. "ኧረ ስንቴ ከባለመኪናው ጋር ስትንዘላዘል አይቻታለሁ.. ሁሌ አይደል እንዴ መታጠፊያው ድረስ የሚሸኛት..."
እኔ ከልቧ ስታለቅስ አይቻታለሁኮ ይሄ ከእነሱ ሀሜት አይበልጥም? የእኔ ሠላም እንዲህ ታረጋለች?... ሲያወሩ በሰማሁበት ስፍራ ተዘርፍጬ እነፋረቃለሁ...
ብያችኋለሁ የሆነኛው ቀኖቼ ብዙ ናቸው.. የሆነኛው ቀኔ ላይ እንዲሁ ሠላምዬን ሲያሙብኝ ሰምቼ ናፍቃኝ በጣም ናፍቃኝ... በየመንገዱ ስነፋረቅ...
እህቴ እንደዚህ ትልቅ ሁና አላቃትም... ከየት እንደመጣች እኔጄ በጥፊ ሦስቴ አራቴ አላቅም ብቻ ፊቴ ላይ አጨበጨበችብኝ...
"መሣይ ደከመኝ... እኔምኮ የሚጠብቀኝ ሕይወት አለኝ... እስከመቼ ነው ላንተ እያዘንኩ ባንተ እየተሰቃየሁ የምኖረው?"
"እነዚህን ሰዎች አየሻቸው? ልክ እኔን ሲያዩ ነው ሀሜት ትዝ የሚላቸው.. አንቺም እንደ እነሱ ነሽ! ዛሬ ባጋጣሚ በመንገድ ብታገኚኝ አታስመስይ.."
"ጥሩ ከዚህ ብኋላ የቤት ኪራይ ማን እንደሚከፍልልህ እናያለን.. ምን እንደምትበላም ጭምር... ያንተ ነገር በቅቶኝ ነበር.. ጥሩ በል ደህና ሁን"
ያቺ አሮጊት ለካ ደግነት አልነበረም... ለካ ጨለማዬ ጭላንጭልም ብትሆን ብርሃን ነበራት.. ዛሬ ግን እሷም ቀልጣ አለቀች
የእህቴ ጥፊዎች ልከኛ ሳይሆኑ አይቀርም እራሴን ታዘብኩት... አውቃለህ ህመሜን ማዳን አልችልም ግን ቢያንስ ከህመሜ ጋር መኖርን መልመድ አለብኝ...
እህቴን በመንገድ ጠብቄ እንድታግዘኝ ጠየኳት እራሴን በትንሹም ቢሆን መቀየር እንደምፈልግ ነገርኳት...
በነጋታው የተወሰኑ ልብሶችን አመጣችልኝ "የፍቅረኛዬ ነው እሱም እንዳንተ ግርማ ሞገስ ያለው ስለሆነ ልብሶቹ አምረውብሀል" አለችኝ...
ከፍቅረኛዋ ጋር ፀጉር ቤት ገባን... ሁሉ ነገሬ የዳነ መሰለ ዓይኖቼ ግን የቀረ የማይሽር ህመም እንዳለ መደበቅ አቃታቸው...
"ከነገ ወዲያ አንድ የሚመረቅ ሆቴል አለ.. እና እነሱ የመድረክ ዘፋኝ ስለሚፈልጉ አውርቼልህ ከባንዱ ጋር መቶ ይለማመድ ተብሏል... ከዛ በተጨማሪ እኔ በወንድሜ ስለምኮራ የድምፅ ውድድር ላይ አስመዝግቤሀለሁ.." አለችኝ እህቴ ደስ እያላት...
በምርቃቱ ላይ የታደሙት ሰዎች ሁሉ ድምፄንና የዘፈን ምርጫዬን ወደዱት... እኔ ግን አልወደድኩትም.. ግድ ሁኖብኝ እኝጂ ለሠላሜ ለፍቅሬ የሚሆን ዘፈን መዝፈን ነበር ፍላጎቴ...
"ዕረጋ ከማለቱ በቀር ድምፅህ እንደድሮው ውብ ነው..." ይሄን ድምፅ ማመን አልቻልኩም... ዓይኖቼ ብቻቸውን ወደኋላ የዞሩ እስኪመስለኝ አንገቴ ፍጥነቱ... አዎ እሷ ናት ሠላሜ ናት!
"መስ ባለቤቴና ልጄ እየጠበቁኝ ነው ግን ስላንተ ስሰማ በጣም ተፀፅቼ ነበር.. እንደዚህ ሁነህ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል ግን ልነግርህ የምፈልገው ነገር አለ... ሰፈር ውስጥ የሚወራው ነገር..."
"ሹሹ.. ዝም በይ ተያቸው ያውሩ... አንቺም አታስረጂኝ አትንገሪኝ ሂጂ በቃ ኑሮሽን ኑሪ..."
ልጅ መውለዷን መስማቴ ሙሉ በሙሉ ስሜቴን ቀይሮት ነበር... ከእሷ የመውለድ ህልም ነበረኝ...
ቦታችን ላይ ቁጭ ብዬ ስተክዝ ሠላሜ ያለችኝ ነገር ትዝ አለኝ... "ስሜታችንን ነው የምንዘፍነው!" አዎ ስሜቴን መዝፈን አለብኝ...
እስክሪብቶና ወረቀት ከቦርሳዬ አወጣሁ ፃፍኩ ከተወሰኑ ስንኞች ብኋላ ግጥም አልመጣልህ ሲለኝ ላሉት ስኝኞች ዜማ መስራት ጀመርኩ....
"ልሰማ አልጓጓሁም እንዴት እንደመጣ ስህተት..
ሆነ ምን ያደርጋል ቃልሽ ላይቀይረው እውነቱን!
ተይው ምን ያደርጋል ይቅር..
ጊዜ ያልፈቀደው ፍቅር!
እኔማ ፈራሁት ሁኔታሽን ሁሉ ሲወራ..
የሰው አፍ እንዲህ ነው ጠብቂ እራስሽን አደራ!
ምንም ባላቆይሽ ከኔ..
ክፉሽን አልየው ባይኔ!
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ደጁን አያምንምና
ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2)
የሸኘ ልቡን አያምንምና..."
"መስ ስለእኔ በዚህ ልክ እንድትብሰለሰል አልፈልግም እኔ ንፁህ አይደለሁም ከመንደሩ አፍ ልትጠብቀኝ አትሞክር አይገባኝምኮ!" በድጋሚ የልብ ምቴን በደቂቃ አእላፍት ጊዜ የሚጨምር ድምፅ ሰማሁ...
ባሁኑ ግን አንገቴም ዓይኖቼም የሆነ ነገር ከብዷቸው ነበር መዞር አልቻሉም መታ ልክ ድሮ እንደምንቀመጠው ተቀመጠች... ሁሌ ሳደርግ እንደነበረው ጭኖቿን ተንተራስኩ... ልክ እንዳስለመደችኝ... እናቴ ያስለመደቻት ይመስል የእናቴ እጆች እስኪመስሉኝ እጆቿን በቲሸርቴ አሳልፋ ጀርባዬን በስሱ እየደባበሰች...
"ታስታውሳለህ የእነዚህ ጥያቄ መልሶች እሩቅ ናቸው የተባባልናቸውን?"
እያለቀስኩ ስለነበር ቃል ማውጣት አቅቶኝ በአዎንታ ጭንቅላቴን ነቀነኩ...
"የአንተን አላውቅም የእኔ ያ እሩቅ ነው ያልኩህ መልስ ላይ ግን ዛሬ ደርሰናል...
እናቴ ታማ ወይም አደጋ ደርሶባት አይደለም የሞተችው... እራሷን አጥፍታ ነው..." ቀና ብዬ አየኋት... እያለቀሰች ነበር እሷም አየችኝ.. እያለቀስኩ ነበር... እንባዬን እየጠረገችልኝ ቀጠለች...
"እናቴ የሚፀፅታትና ደጋግማ የምትለኝ ምን እንደነበር ታቃለህ?... "አባቴ ክብር ቢኖረው ኑሮ ልጄን ለቀጥቃጭ አልድርም!" ባለ ነበር እሱ ግን እኔ በፍቅር ስታወር እሱ ምን እንዳወረው አላቅለትም አንስቶ ላባትሽ ዳረኝ...
አልክድም በስአቱ በአባትሽ ፍቅር እብድ ብዬ ኘበር... ግን የጋሽ ንጋቱ ልጅ ላግባሽ ብሎ ያን ሁሉ ሀብት ጥሎሽ ሲያመጣ እንቢ ስል አባቴ እሺ ማለት ነበረበት... እሱን አግብቼ ቢሆን አሁን ከአብሮ አደጎቼ ባላነስኩ ነበር...
እንደእነሱ ተኳኩዬ ዘንጬ ለመዝናናት በመኪናዬ በተንፈላሰስኩ ነበር... አሁን ግን የት እንዳለሁ እዬ.. አባትሽ እንጨትኛ ቆርቆሮ ቀጥቅጦ የገዛውን የብረት ስሀን እያጠብኩ ነው.... | 973 |
| 5 | ደህና ይግጠምሽ!
የሄደን ሰው ምን ይሉታል
ከራስ አልፍ ለማን ይወቅሱታል?
ተፈጥሮ ግን ቅጥአንባሯ የወጣ ናትሳ... አሁን ሜዳና ተራራ እንዴት በአንድ ገፅታ ይሆናሉ? ተቃራኒ ናቸው! እንደሚገባኝ ከሆነ ደግሞ ተቃራኒ ነገሮች ሁሉ በተቃራኒ እንጂ በአንድ ገፅታ አይሆንም.....
እዚህ ግን ሜዳና ተራራ በአንድ ሆኑ እያልኳችሁ ነው... እንዴት እንደሆነ አትጠይቁኝ ግን ሜዳው ተራራ ነው ተራራው ሜዳ ነው..አንዱን ብቻ ማለት ይከብዳል...
ተፈጥሮአዊ ቦታ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ወደዚህ ይመጣሉ ግን በጣም ትልቅ ስለሆነ ሰው ያለም እስከማይመስል ፀጥ ያለ ነበር...
ሁሌም የምቀመጥባት ቦታ አለችኝ... ፊትለፊቴ ገዘፍ ያለ ዲንጋይ አለ... በቃ ደስ ሲለኝ ከዲንጋዩ ጋር.. ከፈለኩ ወደአንደኛው ዛፍ ዙሬ ከእሱጋር... አብዛኛውን ጊዜ ግን ከእራሴ ጋር ነው የማወራው።
ከሆነ ጊዜ ብኋላ ግን እቺ ቦታዬ ሌላ ሰው ሳትለምድ አትቀርም ሂጄ በመጣሁ ቁጥር ሁሌ የሚሸተኝ የሆነ ጠረን አለ...
እሺ ውሻ አይደለሁም ጠረን አሸታለሁ ምናምን ብዬ አልሰክሳችሁ ግን የምቀመጥበት ቦታ ላይ ምን የመሰለ ዳሌ ተሸክሞ እንደነበር የሚያሳብቅ ወረቀት አገኛለሁ...
ቦታዬ ላይ ሌላም ሰው መቀመጥ ስለጀመረ ቀንቼ ይሁን ወይም ለተፈጥሮ ተቆርቁሬ አላውቅም ብቻ እኝደመበሳጨት እያረገኝ...
"ተፈጥሮን ፈልገው ከመጡ ዝም ብለው አይዘረፈጡም? ወረቀት ላይ ምናምን ይቀመጣሉ እንዴ? ቀሽሞች" ምናምን እያልኩ እያጉረመረምኩ ወረቀቱን በእግሬ አብንኜ እቀመጣለሁ....
ዲኔጋዩ ይሁን ዛፎቹ ባላውቅም ለሚመጣው ሰውማ ስለእኔ ያሳብቁለታል... እንጂማ እንደዚህ እኔን ለማናደድ እንደዚህ ቆርጠው አይነሱም ነበር...
በሚቀመጡበት ወረቀት ስናደድ ጭራሽ የሶፍት ምአት ቆልለው ይሄዳሉ? ሴት ይሁን ወንድ አላቅም ግን ስድስትና ሰባት ወር ሙሉ ጉንፋን ይይዛል እንዴ?
አመቱን ሙሉ በሉት ሶፍቱን ስለቅም ሳቃጥል....
እሰይ... እሰይ.. ዛሬስ ወረቀቱን ከነዳሌው ደረስኩበት...
እንዴት እንዴት በስድብ ከፍ ዝቅ እንደማደርጋት በጋለ አእምሮዬ ምስል እየታየኝ ገሰገስኩ... የሆነ ሰልካካ... ምን ልበላችሁ? ለጡት ጉች ጉች... ለከንፈር ኢንጆሪ.. ለጥርስ በረዶ... አቦ ለድምፅ ምን ቁልምጫአለው? ከቁጣ ግስገሳዬ አደናቅፎ ያቆመኝ እንቁርጉሮዋን ሰማሁ...
"የልቤን ስብራት ባንተ እንዳልጠግነው..
የኔ ማቶንበት ምክንያቱ ብዙ ነው!
የምቶድህ ልቤ የሰው መሆንህን አምና ተቀብላ...
ይመስልሀል እንዴ ሰላሟን አግኝታ የምትልህ ችላ!..."
"ምን ልታረጊኝ?ልክ ቦታዬን እንደቀማሽኝ ሚስቴንም ልትቀሚኝ?" አልኳት ፈገግ ብዬ
"Noo.. ለዘፈኑ ያክል ነው..."
"ድምፅሽ ያምራል"
"ዘፈኑስ?"
"እኔ የሀገራችንን ዘፈኖች አልወዳቸውም"
"Ok...ፍቅር ይዞህ አያቅም ማለት ነዋ!"
"ቢይዘኝም ፍቅሬን በዛቻማ አልገልፅም..."
"እና በምንድነው የምትገልፀው?"
"አንዳንድ ጥያቄዎች መልሶቻቸው እሩቅ ናቸው... ለማንኛውም ዛሬ ጎበዝ ሁነሻል ቦታዬን በሶፍት አላዝረከረክሻትም"
"አታስብ ከዚህ ብኋላ አላቆሽሽብህም"
"በስተመጨረሻ ጉንፋኑ ለቀቃት.. ቢጨንቀኝኮ ትኩስ ነገር ባስቀምጥላት ብዬ ሳስብ ነው የተሻለሽ"
"አይደል..!" በትካዜ ተዋጠች...
"ኦ sorry ምክንያቱን ሳላውቅ ቀባጠርኩብሽ.. ምን ነበር የሶፍቶቹ ሚስጥር?"
"ከሶፍቶቹም በፊት እመጣ ነበር..."
"አው አውቅ ነበር..."
"ያን ታውቅ ነበር?"
"አዎ ጠረንሽ ሁሌም ይሰማኝ ነበር.."
"ገባኝ ወረቀቱ.." ብላ ከዳሌዋስር ጎትታ አወጣችውና ጨመዳዳ ወረወረችው...
"ሶፍቶቹ እንግዶችሽ የሆንበትን ምክንያት ንገሪኛ?"
"የቤቱ አባውራ አባቴ ሳይሆን እናቴ ነበረች... የምገባበትን የምወጣበትን ስአት የምትፈቅድልኝ እሷ ነበረች... አባቴ እናቴን ይፈራት ነበር"
"ለምን?" አልኳት ተገርሜ
"አንዳንድ ጥያቄዎች መልሶቻቸው ሩቅ ናቸው ያልከው እራስህ አይደለህ!... ባጭሩ አስር ስአት ሲል ከዚህ መሄድ ነበረብኝ ለዛ ነበር ሁሌ የማታገኘኝ.."
አባቷ እናቷን ደበደባት... ከዛ ተለያዩ... እያለቀሰች ነበር.... አይ ሄዬ ጭንቅላቴ እስኪ ዝም በል እሷ ልትነግርህ አይደል እንዴ...
"እና ምን ተፈጠረ.. ዛሬ እንዴት ዘገየሽ?"
"እናቴ ስለሞተች!"
"sorry በጣም አዝናለሁ በቃ ወሬ እንቀይር..."
"አትዘን ስድስት ወር ሙሉ አዘንኩላት አይበቃትም? አሁን ወደእራሴ አለም እየተመለስኩ ነው... በነገራችን ላይ ሠላም እባላለሁ" አለችኝ
"መሣይ..." እጆቿን ጨበጥኳቸው... የድምጿን ያክል ውበት አላቸው...
ከዚህ ትውውቃችን ብኋላ ሁሌም እንገናኛለን.. እናወራለን እናወራለን ሠላምዬ ዘፈን ትወዳለች... በእሷ ምክንያት ዘፈን ከመስማት አልፌ ዘፋኝ የመሆን ህልም ሁላ እየጀማመረኝ ነው ነው የምላችሁ...
"መስ..."
"ወዬ ሠላሜ..."
"አንድ ጨዋታ እንጫወት?"
"ምን አይነት ጨዋታ?"
"እየውልህ አንዳችን መዝፈን እንጀምራለን ልክ የዘፈኑ የመጀመሪያው ስንኞች ሲያልቁ ሌላኛው ሰው ከዛ ዘፈን ጋር የሚስማማ ሌላ ዘፈን ይቀጥላል.. እያልን እያልን መቀጠል ያቃተው ሰው ቸኮሌት ይጋብዛል"
"ዝብለሽ ቸኮሌት ግዛልኝ አትይም ጦጣ..."
"እኔ እንድንጫወት ነዋ የምፈልገው..."እንጫወታለን አንድም ቀን ቸኮሌት ጋብዛኝ አታውቅም ምክንያቱም አሸንፌያት ስለማላውቅ....
መቼም መሸነፌ አይቀርም ብዬ ቸኮሌት ገዝቼ ቦታችን ላይ ተገናኘን...
"መስ.. ዛሬ አዲስ ሕግ ልጨምር ነው.. ግን ከዛሬ ውጪ ስለማይሰራ ተጠቀምበት..."አለችኝ እንደሆነ ነገር እያደረጋት
"አንቺ በቃ ሁሌ መረበሽ ብቻ ነዋ የምታውቂው እሺ አዲሱ ህግሽ ደግሞ ምንድነው?"
"ዛሬ ዘፈን ብቻ አይደለም የምንዘፍነው... ስሜታችንንም ጭምር ይሆናል!"
"ማለት? እንዴት?"
"በቃ አሁን በዚህ ስአት እየተሰማህ ያለውን ስሜት ሊገልፅልህ የሚችል ዘፈን መዝፈን..."
"አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ?"
"እሺ ባክህ..."
"ከዚች ቦታ ውጪ ቀሪው ዓለም ላይ የሌለሽ ቢሆንስ? የሆነ አለ አይደል እዚህ ቦታ በተደጋጋሚ ለረዥም ጊዜ በመምጣቴ የሆነ መንፈስ ነገር እኝደሰው ሆኖ እያወራኝ ቢሆንስ ብዬ አስባለሁ... በቃ የሆነ መልዐክ ወይ ሌላ ነገር ብቻ የሆነች ጣኦት ነገር ነው የምትመስይኝ..."
"እንግዲህ ቤቴን ታቀዋለህ.. ትምህርት ቤቴ ትመጣለህ.. አየህ ሰው ነኝ በል አሁን አታረሳሳኝ ወደጨዋታችን.. በል ጀምር መቼስ ተሸናፊ እንደሚጀምር የማንሽረው ህጋችን ነው" አለችኝ...
አሰብኩ.. አሁን የሚሰማኝ ምንድነው.. ይሄንን ስሜቴንስ ምን ዘፈን ይገልፀዋል?... አሃ ቅድም ስሰማው የነበረው ዘፈን....
"እሺ ልጀምር ነው..." ለመስማት ምንድነው የዚህን ያክል ተስተካክሎ መቀመጥ... በቂጧ ነው እንዴ የምትሰማው?
"መራርጬ ቃላቴን
ልገልፅላት ስሜቴን
በቃ ዛሬስ እነግራታለሁ ብዬ ወስንና
እፈራለሁ ብቅ ስትል ዓይኗን ሳየው ገና..."
እሷ ቀጠለች፦
"አሄሄ ቆላውን ደጋውን.. ካንተ ጋር ደክሜ..
ደክሜ.. ደክሜ
አሄሄ ለፍቅራችን ነበር.. ያለኝን እንዳቅሜ..
ያለኝን.. እንዳቅሜ..."
እንዴት ከንፈሮቻችን እንደተጣበቁ አላውቅም.. ይመስለኛል እሷም አታውቅም...
እሷን ለማስደሰት ከእሷ እኩል በዘፈን ፍቅር ወደኩ...
ምናቤ ሁሉ የተሞላው የሆነ ቀን ለእሷ ስዘፍንላት.. መድረክ ላይ ሳቀብጥ ሳቆላምጣት ነው.... | 923 |
| 6 | movie recommendation
Silo
ያበደ tv series ነው
ሕግ ያስፈለገው እኛን ለመጠበቅና ፍትህ ለማስፈን እንደሆነ አብዛኞቻችን እናስባለን...
ይሄንን ፊልም ካየሁ ብኋላ ግን ምናልባት ሕግጋቶች እኛን ሳይሆን የተዋሸናቸውን ውሸቶች ቢሆንስ የሚጠብቁት? ብዬ ማሰብ ጀምሪያለሁ...
ብዙ ነገር ታዩበታላችሁ...
ፊልሙን በትርጉምም በእንግሊዝኛም ታገኙታላችሁ ከፈለጋችሁ በውስጥ አዋሩኝ እልክላችኋለሁ... @Mr_Lewi
ያያችሁት ካላችሁ ከፊልሙ ብኋላ እንዴት ናችሁ?
@lewi_derest | 1 134 |
| 7 | ጉዳዩ፦ የ"ደራሲው...♾" channelን ይመለከታል
ለካ 2k ገብተናል👏!
ያው እንደምታውቁት ማሰብ የማያቆም በሽተኛ አእምሮ አለኝ... እናም "2k ገባን" ስለው
"ለምን challenge አንሰጣቸውም?" አለኝ
እናም የዚህ የበሽተኛው አእምሮዬ ሀሳብ ምን መሠላችሁ
እናንተ የፈለጋችሁትን ዘፈን መርጣችሁ መወያያ group ላይ ትልኩልኛላችሁ... ከዛ እኔና በሽተኛው ደግሞ ብዙ react የተደረገበትን ዘፈን መርጠን ልብ ወለድ እንፅፍላችኋለን!
እኔ በበኩሌ የበሽተኛውን ሀሳብ ወጅጄዋለሁ... እናንተስ?
✍ሌዊ
@Lewi_derest | 2 217 |
| 8 | አንድ ሚስጥር ግን ለሴቶች ብቻ ሹክ ልበላችሁ.... ወንዶቻችሁ አልጋላይ ሚስጥሮቻቸው ምንም ናቸው! ማግጦብሽ ቢሆን እንኳን ከጭኖችሽ ሳይወጣ ጠይቂው ዘክዝኮ ይነግርሻል!
እውነት ለመናገር የእኔውስ ያሳዝናል... ወንድሜን አይቼ ነው የተጎዳሁት ይለኛል...
የቱ ጋር እንደምመስለው አላውቅም እንጂ በአመለካከት ከወንድሙ ጋር የሚመስል ነገር አለኝ....
የወንድሙን boundary ሌሎች ሰዎች አልነበሩም የሚጥሱበት እሱ እራሱ ነበር የእራሱን boundary የሚጥሰው...
ሰዎች ስለእራሳቸው ያወሩለት ሁሉ የእውነት ያ የእነሱ boundary እየመሰለው ሊጠብቅላቸው ይታገላል...
በጣም የሚወዳት ፍቅረኛው... ከትዳር በፊት ምንም ማድረግ አልፈልግም ስትለው ጠበቀላት...
እሷስ ምን አደረገች? ሲጣሉ ጠብቃ ባደባባይ ወንድነቱን እንደምትጠራጠር ተናገረች...
ሰው ሲጣላ ስለ ልቡ.. አስተሳሰቡ ምናምን ይሳደባል... አጅሪት ግን ቀጥታ ብልቱን ተሳደበች...
"ንፁህ ሀሳብ ንፁህ ልብ አለው... ቆለጥ ግን ያለው አይመስለኝም!" አለች በሴቶች ፊት እየሰማት...
ባለጌዎች እንዲህ ናቸው... ጭራሽ የቤታቸው የውጭ አጥር ላይ እንደጥቅስ ፃፉበት... ወንድሙ... መጀመሪያም ብልህ አልነበረም እራሱን ሰቅሎ ሞተ....
ከዚህ ብኋላ ነው የእኔው ጉድ "ለሰዎች boundary ብዬ የምሸሽገው አንዲች ቃል የለችም!" የሚል አመል ያመጣው።
..................................................
ከወንድሜ ብኋላ የማግባትና የመውለድ ተስፋዬ ጠፍቶ ነበር... የዚህችን ቀጫጫ ጥፊ ግን አልቻልኩትም....
እውነት ለመናገር ጥፊዋ ሳይሆን ልጄ ነው ማግባት እንዳለብኝ ያሳመነኝ...
ልጅህን ወለድኩ ስትለኝ... የሆነ ነገር ተሰማኝ ስበር ሄጄ አየሁት....
አፍንጫው ትንሽዬ ናት...እጆቹ ስስነታቸው ሲያስፈሩ... እግሮቹማ ጫማ አይንካችሁ የሚያስብሎ... ትንሿ ጣቴን እንደጡጦ በግጉ ሲግጣት የተሰማኝ ስሜት ልቤን ፍስስ አደረጋት!
✍ሌዊ
@Lewi_derest | 2 739 |
| 9 | ደራሲው...∞:
boundary እና protocol የሚያበዙ ሰዎች፦ እራሳቸው ላይ ቲያትር የሚሰሩ ጅሎች ናቸው!
የዘገየች ጥፊ
አሁን በዚህ ቅጥነቷ እንዴት አምኜ ነው አልጋ ላይ ይዣት የምወድቀው?
ደግሞ እኮ የሴት ወጉ ጡቶችን አንጉታለች.... በስስት ሳያቸው ስጋት ያዘኝ እጄ ላይ ቢሟሙስ?
"ምን እያሰብክ ነው? እንደዚህ ትተኸኝ የጠፋኸው"
"ስላንቺ..."
"ስለእኔ ምን?"
"ጡቶችሽ እጄ ላይ ሲሟሙ...ወይ በወንድነት ትግሌ መሀል ወገብሽ ቅንጥስ ሲልብኝ ምናምን...."
"በቅጥነቴ ብዙ ቀልዶችን ሰምቼ አውቃለሁ.. ብዙ ግልፅ የሆኑ ሰዎችንም አይቼ አውቃለሁ በዚህ ልክ ግን አጋጥሞኝ አያውቅም" አለችኝ።
"እኔም ብዙ ጭኖችን አውቃለሁ እንዳንቺ ግን ያላቅሟ ወሲብን ፊር የምታደርቅ ትእቢተኛ ነፍስ አጋጥማኝ አታውቅም!"
"ትንሽ ብልግናህ አልበዛም?"
"ግልፅ ነህ አላልሽኝም?"
"የሕይወት ፍልስፍናዬ ድንበር ነው!"
"የኑሮሽስ?"
"ማለት?"
"ሳይሽ አኗኗርሽ ላይ ብዙም ሕግና ስርአት አታበዚም ምናልባት ፍልስፍናሽ በቲዮሪ ብቻ ሁኖ ከሆነ ብዬ ነው"
"ልክ ነህ ይሄ ጥፊ ገና ጡቶችሽ ስትል ነበር ፊትህ ላይ ማረፍ የነበረበት"
ኡፍ... እንደቃሪያ ደስ እያለ የሚያቃጥል ጥፊ.. በቃ የጥዋት ፀሐይ ምን ያደርግልኛል?
ባሎች ሆይ በቀትር 7 ስአት ከሚስቶቻችሁ ጋር እየተጨቃጨቃችሁ ተቃጠልን አትበሉ...
እስኪ ቀኑ ሳይከር ገና በለጋነቱ ጭቅጭቋን ሙቁ! ምናለ በሉኝ በብርዳችሁ ላይ የመጣች ሙቀት ትሆናለች ለዛም ደስ የምትል መቃጠል ውስጣችሁ ትፈጥራለች...
እንዲህ የሚያስበው የአእምሮ ክፍሌ ግን ከየት አምጥቶ እንደሚቀባጥር አላውቅም... የጭቅጭቅ ጥዋት.. ቀትር.. ምናምን ብሎ ነገር አለ? ያውም ለሚስቶች?!
አቦ እነዚህንማ ሪንግ ውስጥ ነበር መልቀቅ... ሀሳቦቼ ሲደባደቡ ምናምን...
የእኔ አእምሮ ግን የግራና የቀኝ ብቻ ነው? የላይ የታች... የፊት የኋላ... የግራ የቀኝ... የላይ የፊት.. የግራ የታች... የቀኝ የኋላ... ምናምን ብዙ ነው የሚያስበው.. ደግሞኮ አንዱ ከአንዱ ቢስማማ እሺ...
አስራ ስድስት የሐሳብ ሰይጣን አናቴ ላይ ሲጨፍር እንጂ አሁን አንድ ጥፊ ይሄን ሁሉ ያስለፈልፋል?
..................................................
አንዳንዴ አስባለሁ ሕይወት Stop button ቢኖራት ብዬ አስባለሁ...
ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ ድንበሩን እየተላለፈ ነው የሚኖረው!
የሰውን ድንበር ስትጠብቅ... ትወደዳለህ የመጨረሻ ጭዋ ትባላለህ
የእራስህን ድንበር ስታስጠብቅ ግን እንደትዕቢተኛ.. ጉረኛ.. ምናምን ትታሰባለህ...
ዛሬ የሰነዘርኳት ጥፊ ግን በአግባብነቷ ላይ ጥያቄ ፈጥሮብኛል...
"መስመሬን እንዳታልፉ ባልሽ ቁጥር የሰዎችን ነፃነት ክየገደብሽ እንዳይሆን ተጠንቀቂ ካልሆነ ግን እራስ ወዳድነት ብቻ ይሆንብሻል" ብሎኝ ነበር አስተማሪዬ...
የመናገር ነፃነት ነበረው.. መስመሩን ያለፈው የቱ ጋር ነበር? እ.. አዎ እኔን ለወሲብ እኝዳሰበኝ ሲነግረኝ...
ልክ ነኛ በርግጥ ጥፊዬ ዘግይታለች.... ግን ሰው በዛ ልክ እንዴት ግልፅ ሊሆን ይችላል? እየቀለደ ቢሆንስ? መጠየቅማ አለብእ....
ደወልኩለት... ቀጠርኩት.. አገኘሁት..
"ምነው የቀረ ጥፊ አለሽ?" አለኝ
"አዎ..." ቆንጆ ጥፊ.. ደገምኩት
"መቀመጥ እችላለሁ?" አልኩት
"ጥፊሽ ሰላምታ መሆኑ ነው?" ኮስተር ብሎ... አ..አህ አሁን አስፈራኝ ያው ወንድ አይደለ
"ያኔ አወራን ነገሩን በሰላም ፈታነው ምንም እንኳን ጥፊ ቢኖረውም ያ በጣም ጥሩ መንገድ ነበር... ነገር ግን አንቺ ተመልሰሽ መጣሽ ለምን? የቀረሽን ጥፊ ልትማቺ!
ነገሩ አብቅቷል ብዬ ስላሰብኩ ደስተኛ ነበርኩ... ምንም ሀሳብ ውስጤ አልነበረም.. አንቺም ከዛ ብኋላ ልታወሪኝ አልሞከርሽም...
ቆይ ቆይ ጥፊ መማታት ሲያምርሽ ሲያምርሽ እኔ ጋር ነው እንዴ የምትመጪው?"
"እስካሁን ቁመህ እያወራህ ነው? ካፌ ነው ያለነው እኮ! ካፌ ቁጭ ብለን እንጂ ቁመን እናውራ ሲባል ሰምቼ አላውቅም..."
"አንቺ ተመልሰሽ ስትመጪ እኔ አንድ ነገር አሰብኩ... በሕይወቴም ሆነ በዙሪያዬ ያሉ... ለእነሱ ስሜት የሌለኝን ነገሮችና የማልፈልጋቸውን ነገሮች ማፅዳት እንዳለብኝ።
ለዛ ነው ከዚህ ብኋላ እንድታወሪኝ የማልፈልገው...
በዚህ ልግ ላስረዳሽ የሞከርኩት... አውሬነቴ ልክ እንዳንቺ ፍልስፍና ሚዛን እንዲስት ስለማልፈልግ ብቻ ነው" ብሎ ጥሎኝ ሄደ...
"እኔም ሚዛኑን ለመጠበቅ ነው የመጣሁት... ጥፊው ቀልድ ነበርኮ..."
"እኔም ድንበሬን እየጠበኩ ነበርኮ!"
እንዴት ነው በዚህ ፍጥነት ትክክለኛውን መልስ አስቦ የሚመልሰ?
ስለሱ መስማት... ማጣራት ጀመርኩ... ንግግሩ ከሚሰብራቸው ይልቅ ግልፅነቱ የሚማርካቸው ሴቶች ይበዛሉ.. እሱም አሜን ብሎ ተቀብሎታል ተራ በተራ ወደ አልጋው ያመላልሳቸዋል....
..................................................
አይደለም ለፊቴ ለስሜ ተጠንቅቀው በቁልሞጫ የሚጠሩኝ ስንት ቆነጃጂቶች እያሉ ጥፊ ከምትወድ ሴት ጋር ምን እንዳጣበቀኝ አይገባኝም...
እሷ ሆን ብላ ይሁን ወይም እኔ ሆን ብዬ ወይ ደሞ አጋጣሚዎች በቃ በዛም በዚህም አገኛታለሁ... እናወራለን ብዙ እናወራለን... የምንለያው ግን ሸኝቻት ቸው ተባብለን አይደለም...
መቼ እንዳሰመረችው እንኳን ለማታቀው መስመሯ.... በጥፊ እየቀጠቀጠችኝ "መስመርህን ባታልፍ ጥሩ ነው!" ብላኝ ነው እየተመናቀረች የምትሄደው...
እኔ ግን ታሳዝነኛለች... boundary እና protocol የሚያበዙ ሰዎች፦ እራሳቸው ላይ ቲያትር የሚሰሩ ጅሎች ናቸው! እነዚህ ነገሮች ሕግና ስርአት እንጂ ክብር አይደሉምኮ!
"ቀይ መስመር ስላበዛሽ ብቻ ትከበሪያለሽ ማለት አይደለም... ሰዎች የሚያከብሩት የሚጠቀምባቸውን ነው!"
"አንተ በዛ መንገድ ነው ክብርህን የምትጠብቀው?"
"አዎ!"
.................................................
በፊት በፊት ንግግሩ ይሰብረኝ ነበር የእኔ ጥፊ አይጎዳውም እንጂ... አሁን አሁን ግን ግልፅነቱ ከሚማርካቸው ሴቶች መሆኔ ነው...
"ለምንድነው ግን ቅጥነቴን ከsex ጋር ያገናኘኸው?" ስለው
"እናቴ.. እህቴ ወይም ዘመዴ ያልሆነች ሴት ፊት ስቆም ቀድሜ የማስበው እርቃኗን ነው!
አእምሮዬ ሳያስባት... ልቤ ሳይመኛት ገና ምናቤ ቀድሞ ከቀሚሷ ባሻገር ሲርመጠመጥ አየዋለሁ..." ብሎ የሚመልስ
"እኛ ሀበሾች ከተቀረው ዓለም የምንለይበት የእራሳችን ወግና ልማዶች አሉን.. ጥቂቶቹን የሚጠቅስልኝ ይኖራል?" ብሎ ሲጠይቅ
"ሀበሾች፦ መብራት አጥፍተውና በብርድ ልብስ ተደብቀው ነው ወሲብ የሚፈፅሙት... ከማን እንደሚደበቁ ግን አይገባኝም!" ብሎ ለአስተማሪ የሚመልስ ያውም ክፍል ውስጥ! እንዲህ ባለው መገረሜ ብርቅ ነው?
ነገረ መልሱ ሁሉ ከወሲብ ጋር የተቆራኘበት ይሄ ማነው? ስል... እኔው ቁራኛው ሁኜ ቀረሁ እንጂ
አንዳንዴ መሸነፌን ላለማመን... የሚናገረውን ያደርገዋል ወይስ ወሬ ብቻ ነው የሚለውን ለማረጋገጥ ነው አልጋው ላይ የወደኩለት እላለሁ....
መሸነፌን ግን በግድ ያሳመነኝ አልጋው ላይ ወድቄ ስነሳ ብቻዬን አልተነሳሁም....
ከአልጋው ይዤ የተነሳሁትን ከመንገሬ በፊት.. አልጋው ላይ እያለሁ የተናዘዘውን ልንገራችሁማ... | 1 984 |
| 10 | እናቴ.. እህቴ ወይም ዘመዴ ያልሆነች ሴት ፊት ስቆም ቀድሜ የማስበው እርቃኗን ነው!
አእምሮዬ ሳያስባት... ልቤ ሳይመኛት ገና ምናቤ ቀድሞ ከቀሚሷ ባሻገር ሲርመጠመጥ አየዋለሁ....More
ነገ ማታ ይለቀቃል
✍ሌዊ | 1 789 |
| 11 | እሷም በቁምጣ ከሜዳ ወደሽኝት ቤት ስትመጣ አየኋት.... ጠብቀኝ ምልክት በእጇ አሳየችኝ...
"ፎርፈክ ነው?"
"ኧረ አይደለም ለሽንት..."
"እስፖርት ወተን እኮ.. (ቀኝ እግሯን በቄንጥ ከፍ አድርጋ አንገቷን ወደቀኝ አዙራ ቂጧን እያየች) እንዴት ነው በቁምጣ አላማረብኝም?" አለችኝ
ሽንት ቤታችን ከፊትና ከኋላ አንድ ላይ የተሰራ ነው... በፊተኛው በኩል የሴቶች ሽንት ቤት ነው እሷ ግን ፈጠን ብላ ወደጀርባው ወደ ወንዶች ሽንት ቤት ሮጣ ሄደችና አንዱ ላይ ገባል...
እኔም ተከትያት ገባሁ... ኧረ እቺ ውብ መልዐክ ብቻ ሳትሆን እብድ ሰይጣንም ናት...
እሁድ ማታ ሳስበው ያደርኩት ከንፈሯን በግላጭ አገኘሁት... ከአመታት ብኋላ ጣቶቼ ከእናቴ ጡት ብኋ የአበባዬን ጡቶች አወቁ...
በቃ እንነጋገራለን በሆነኛው ክፍለ ጊዜ እንወጣለን የሆኑ የሆኑ አካሎቻችን ተላፍተው እንመለሳለን....
በሽንት ቤት ሽታ የተቀመመ ፍቅራችን አድጎ ጎርምሶ... ትልቅ ሁነን ቀለበት ገዛሁላት...
አባቷ ቄስ..አጎቷ ቄስ.. ክርስትና አባቷ ቄስ... ቄሶች በቤታቸው ተሰብስበው ቁርጥ ሲቆርጡ የአበባዬን ጣቶች ተመለከቱ....
ከነቆባቸው "ከማን ነው?" ቢሏት....
"አንዴት አንዴ እዚህ አንዴ እዛ ከሚረግጥ ጴንጤ ነው ትበላቸው?" አለችኝ እህቷ...
"እና ከማን ነው አለቻቸው?" አልኳት...
"ይሄው የመጥሪያ ካርዱ እዚህላይ አለልህ።" በላኝ መጥሪያ ሰታኝ ሄደች...
"ታላቅሽ እያለች ቀድመሽ ልታገቢ ነው?" አልኳት እየቀለደች መስሎኝ..
"የእሷ እኮ ነው! ያመዋል እንዴ" አለች
ኧረ ትናት እኮ ቤቴ ነበረች... አታረገውም እያጉረመረምኩ ወደቤቴ ገባሁና መጥሪያውን አነበብኩት...
አብርሃም? ለምን እሱን? እሺ በእኔ ደስተኛ አትሁን ግን ቢያንስ የማልጠላውን ሰው አታገባም ነበር?
ነው በቀል ነው? ለምን ትበቀለኛለች?
እህቷ ከሠርጉም ብኋላ ብዙ ልታፅናናኝ ሞከረች ግን ከበደኝ... ምንም አላለችኝም ነበርኮ....
ለሰርጓ ዋዜማ መጥሪያ በእህቷ ልትልክልኝ ነገር ለምን ቀድማ ቤቴ መጣች?
መቼስ ዛሬ ጠይቀዋት ነገ አይጋቡም አይደል? ለምን ታዲያ ያን ሁሉ ጊዜ ዋሸችኝ?
ለጥያቄዬ መልስ ሳጣ... ለማጣቴ ፍልስፍና ጀመርኩ...
መልዐኬ ስለነበረች ስሜቴን ገርቼ የእውነት አፈቀርኳት.. ፍቅር ግን ሕመምና ቁስል አሸከመኝ...
እስኪ ደግሞ ፍቅርን ገርቼ ስሜቴን ልከተል የሚል ፍልስፍና አመጣሁ...
እነሆ ፍልስፍናዬ ይህቺን ቆንጆ ጣለልኝ...
ቆንጆ ናት እኔ ግን ለመጅመሪያ ጊዜ አበባዬን ሰብሉን ካፈቀርኳት ብኋላ ሴት አፍቅሬ አላውቅም....
ስሜቴን ስከተል... ደስታም ሰላምም ያገኘሁ መሠለኝ... ከስሜቴ ብኋላ በማፍቀር ውስጥ ያሉ.. እነ መቅናት... እነ መከዳትና መጎዳት ተሰምተውኝ ስለማያውቁ ልክነት ተሰማኝ...
ሴትን እስከ አልጋ እንጂ እስከ አጋር ማሰብ ማቆሜ ምቾት ነበረው
ከዚህችኛዋ ልች ጋር በጣም ተቀራርበናል ወሲብ ሲቀረን ሌላውን ሁሉ አድርገናል።
ከንፈሬ ከንፈሮቿን ጎርሰው ያውቃሉ.. ጣቶቼ ከጡቶቿ ጋረሰ ደንሰዋል.. ልቤ ከልቧ ጋር በሰመመን አውርተዋል..... ነገር ግን አላፈቅራትም....
ማፍቀር ፈልጌ አቅቶኝ አይደለም በቃ ማፍቀር ስላልፈለኩ አላፈቀርኳትም...
ቤቴ መምጣት አትፈራም... አብዛኛውን ጊዜ ሁላ መጀመሪያ የምትስመኝ እሷ ነች...
ግን መቶ ቀን ቤቴ ብትመጣ አንዱንም ቀን ወሲብ አናደርግም!
ከአንገቷ ከከንፈሯ መፍሰስ የጀመርኩት ወንዝ በእንብርቷ አልፌ ልወርድ ስል ትደነግጣለች...
እንደ ሎጥ ሚስት ቀጥ ያርጋትና! አሁን በዚህ ስአት ይሄ ጥያቄ ይጠየቃል?
"እኔና አንተ ግን ምን እና ምን ነን?" ትለኛለች...
ጠላቴ ነሽ ልላት ይዳዳኛል እንዴት 11ኛው ስአት ላይ ታስቆመኛለች!...
ተረጋግቼ እንኳን መመለስ የማልችለውን ጥያቄ ነው እኮ ደግሞ የምትጠይቀኝ....
ፍቅረኛሞች እንዳልላት... ፍቅረኛ የመሆን ሸክምን የምትሸሽ ፈሪ ናት... ግን ምክንያት ያላት ይመስላታል....
ወንድምና እህት እንዳልላት... ገና እጆቼን ከጡቶቿ መሀል አላወጣሁም....
እነሆ እቺም ፍልስፍና አስታቀፈችኝ...
ይህ ፍልስፍናዬ ግን የሁሉንም ቤት ያንኳኳ ይመስለኛል...
"በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን trauma በማከም ለምን መኖሬን እጨርሳለሁ?" የምትል ጣፋጭ ፍልስፍናን አስታቀፈችኝ....
እና ታዲያስ ፍልስፍናዬ ዋሸች ወይ?
አብዛኞቻችን የቤተሰቦቻችንን... የወንድምና የእህቶቻችንን ጭምር trauma ስንሸከም አልኖርንም?
እነሱን የማከም አቅም ሳይኖረን... የእነሱን ስነ-ልቦና በመንከባከብ እኛ አልታመምንም?
የእናንተን አላውቅም እኔ ግን በመኖር ፈንታ የሰዎቼን trauma ለማከም ፍቃደኛ አይደለሁም....
የስነ-ልቦና ቀውሶቻቸው በባለ ሞያ እንጂ በእኛ መርመጥመጥ አይድኑማ!
ታዲያ ለምን ብዬ በመኖሬ ፈንታ በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ኮሽታ እጠብቃለሁ?
መኖር ከፈለጉ እነሱ ጤነኛ ሁነው ይምጡ እንጂ እኔ የእነሱን trauma በማከም መኖሬን አላባክንም! የምል ትዕቢተኛ ሁኜ ቀረሁ...
ይህ ትዕቢቴ ግን ለሦስተኛው ፍልስፍናዬ ያበቃኝ ይሆን ወይስ ይገድበኝ ይሆን?
እዩልኝ ብቻ ይሄ ጭንቅላቴ ምን እንደሚዘባርቅ... ጥያቄ ቢያጣ እንኳን.. ጥያቄ እራሱ ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ደፋር ጭንቅላት ተሸክሜ ተሰቃየሁ እኮ...
✍ሌዊ
@lewi_derest | 2 528 |
| 12 | ደራሲው...∞:
The Body Keeps the Score
በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን trauma በማከም ለምን መኖሬን እጨርሳለሁ?" የምትል ጣፋጭ ፍልስፍናን አስታቀፈችኝ....
ማፍቀር አልወድም!.. አፈቀርን የሚሉ ሰዎችን ሳይ ምን ያክል የሞኝነት ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ እያየሁ አዝንላቸዋለሁ...
ብዙ ሰዎች ደስታ ያለው ፍቅር ውስጥ ይመስላቸዋል... አይደለም ደስታ ያለው ስሜት ውስጥ ነው...
ታዲያ ለምን ብዬ ፍቅርን አሳድዳለሁ?
መቼስ የመጀመሪያ ፍቅር የሕይወት ሀሁ ነውና እኔም ከመጀመሪያ ፍቅሬ የቆጠርኩትን ሀሁ ልንገራችሁ...
ፍቅር፦ ቁስልና ህመም ብቻ ነው ያለው... ስሜት ግን ደስታና ሰላም አለው! ብዬ ብጀምርላችሁስ?
ቆይ ቆይ እንዴ ለመፍረድማ አትቸኩሉ..
እሷ ጭዋ ነበረች... ቅንድቦቿን ልትሸፍናቸው ጥቂት እስኪቀራት ድረስ ግንባሯን ነጠላ አልብሳ ሳያት... በዛ ላይ የመዘምራን ልብሱን ስትለብስበትማ?!
ሻራባራባላ... ሃሌሉያ!
ልቤ የሚመታላት እንስት ሳትሆን እግዜር የላካት መልዐክ ነበር የምትመስለው...
ጠዋት በለሊቱ ማርያም ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ ታይቼ... ከረፋፈደ ከ4 ስአት ብኋላ ደግሞ የክብር ደመና ቸርች ውስጥ በመንፈስ ስመነፈስ በልሳን ስለስስ እሁዴን ብሩህ አደርጋታለሁ....
በሁለቱም በኩል ያሉ ሀይማኖተኞች በቁጣ ገስፀውኛል... ከአንዱ ተሰብሰብ ይላሉ ዝም ብለው...
እኔ ወድጄ ነው እንዴ? ነፍሴ በጌታ ቤት.... ልቤ እንስት ልብ ተከትላ ከማርያም ቤት
እኔ የት ነኝ? ማነኝ? ከየት ነኝ?... ደግሞ ወደ አንድ ተሰብሰብ ይሉኛል እንዴ? እኔ እንኳን ወደ አንድ ልሰበሰብ እራሴን እንኳን አንድ ማድረግ ከብዶኛል ደደቦች!
ታውቃለች እሷን ብዬ እንደማስቀድስ.... ሆን ብላ ይመስለኛል እንደዛ ውብ ሁና የምትመጣው
መዘምራንን የሚያሰልፋቸው ሰው እራሱ ሆን ብሎ እኔ እንዳያት ብሎ ሁሌ ከፊት የሚያሰልፋት እየመሠለኝ በውስጤ "ፀጋውን ያብዛልህ!" እለዋለሁ
መእመኑ ሁሉ በመዝሙሩ መንፈስ ተነክተው ሲያመሠግኑ እኔ በእሷ ውበት ተነክቼ ጠቢቡ ሰለሞንን መሆን ይዳዳኛል...
መቼስ አእላፍት ሚስቶችን አስማምቶ ሚስት በማድረጉ መሆን አለበት ጠቢብ ያስባለሁ...
አይ አይ እኔ እንኳን የሰሎሞንን ጥበብ የፈለኩት ለአእላፍት ሚስቶች አይደለም...
መልዐክት የሆነች እንስትን.. ለደረደ ተባዕት ልብ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል በጥበቡ ልጠበብበት ነበር....
ይህንን ጥበብ የሰጠኝ ማን እንደሆነ ማወቅ ተስኖኝ.... ለሁለቱም ስለቴን ላስገባ ብዬ ወሰንኩ...
የመልዐክት ፍቅር እውር ብቻ ሳይሆን መሀይምም ያደርጋል መሠለኝ....
እኔ የእናንተ አፍቃሪ የክብር ደመና ቸርር ጧፍና ዣንጥላ...
ማሪያም ቤተክርስቲያን ደግሞ ዘይትና 8ደርዘን ግማሽ ሌትር ውሃ ስለት ነው ብዬ ማስገባት....
ይህ መደናበሬም ይገባታል....
በዛ በመልዐክት ሞገሷ ወደ ቄሱ ጆሮ ጠጋ ብላ ሹክ ስትለው... በደስታ "እሰይ እሰይ... እኳን እመቤቴ እረዳችህ... ችግር የለም... ሁሉንም ታቀው ትለምደዋለህ!" ብሎ በመስቀሉ ግንባሬን ሦስት ጊዜ መታ መታ አድርገው ያሳልሙኛል...
"አንቺ ጦጣ" እላታለሁ...በከንፈሮቻችን ልፊያ መሀል...
"እየሳምከኝ ስናወራ አፍራለሁ አላልኩህም?" አለችኝ እጄን ወደወገቧ እየሳበች እንድይዘው እያደረገችኝ
ይገባኛል እሷ ከወገቧ ጉዳይም የላት... ይህ የሴት ቋንቋ ነው... ውበቶቼ.. ድምቀቶቼ.. ጡቶቼ ከጣትህ ጋር ሊደንሱ ይሻሉ ማለቷ ነው...
ደመነፍሴ ይህን እንዴት እንደሚረዳ አላውቅም! አእምሮዬ በማወራት ነገር ተይዞ ደመነፍሴ ግን ወደፍላጎቷ ሲጓዝ እይዘዋለሁ... ከንፈሯ ላይ የማስታውሰው ሁነት ጡቶቿ ላይ እንዴት እንደደረሰ ሳላውቅ ጣቶቼ ቁና ቁና እየተነፈሱ ከጡቷቿ ጋር ሲላፉ አገኛቸዋለሁ...
"ለምን ታፍሪያለሽ?"
"ሁሌ በተቀደሰ ልብስ ስለምታየኝ ነዋ! ስታወራኝ ስሜቴ ይረግብና እንደተዋረድኩ እንደቀለልኩ ይሰማኛል...
አለ አይደል አስመሳይ መልዐክ ምናምን አይነት ሴት የሆንኩ መስሎ ይሰማሀል ወይም ይሰማኛል ብዬ ስለምፈራ ነው.."
"ውበትሽን እንጂ ቅድስናሽን ፈልጌ አልነበረምኮ የማይሽ! ለምን እንደሱ ትሳቀቂያለሽ የኔ አበባ!"
"አትሟዘዝብኝ እሺ ሞዛዛ!" እየሳቀች በሳቆቿ መሀል "ምን ልትለኝ ነበር እሺ?" የሚሉ የርህራሄ ቃላቶችን ወለደች።
"ቄሱን ግን ምን ብለሽ ሹክ ብትያቸው ነው እንደዛ ባንዴ ከድንጋጤ ወደደስታ ፊት ተለውጠው በፍቅር ያወሩኝ።
"ልቤን ሰረቅሽው አላልክም?"
"እናስ አበባዬ..."
"ታዲያ ልብህ ምን እንደሚያስብ አውቃለኋ!"
"እስኪ ንገሪኝ የኔ ጣኦት... ልቤ ምን ቢልሽ ነው የአባን ፊት የመቀየር ጥበብ የተቆናፀፍሽው?" አንገቷን እየሳምኳት...
"ግንባሬን... ከንፈሬን አንገቴን... ምናምኔን ሳመኝና እነግርሃለሁ.."
ልስማት ስል....
"እየሳምከኝ ስታወራኝ አፍራለሁ አላልኩህም.. አፈርኩ በቃ..." ብላ ገፍተር አድርጋኝ የአልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለችና...
"ፕሮቴስታንት ነበር ምን እንደሚሳል ስለማያቅ ነው.. ብያቸው ነዋ"
"አንቺ? ቱ! የመልዐክት ውሸታም አንቺን አየሁ! እንደዚህ ይዋሻል? እስኪ በሞቴ...." በሳቅ ንፍር ትላለች....
የሆነኛው እሁዴ ላይ እኛ ሰፈር ዝክር ነበርና የአበባዬ እናት ስራ ልታግዝ ስለመጣች አበባዬ ከቤተክርስቲያን ስትወጣ እናቷ ነይ ስላለቻት እኛ ሰፈር ነበር የምትሄደው...
"ዳጊዬ..." አለችኝ
ወዬ ልበላት? አይ እንደማፈቅራት ብታውቅብኝስ? ኧረ አርፌ አቤት ልበል! ምናምን እያልኩ ከእራሴ ጋር ስሟገት....
"አንተ ዳጊ? አይሰማም እንዴ" አለች
"ወዬ አቤት... ሠ.. ሠብሊ እንዴት ነሽ..."
በአውቄብሀለሁ አይነት ፈገግታ እየቀረበችኝ "እነ እታለም ሰፈር አህ አይደል?" አለችኝ
"አዎ ጎረቤት ነን..." አልኳትና እያወራን ወደ እኛ ሰፈር ሄድን... ባጃጆች እኮ ነበሩ ግን ሁለታችንም እረስተናቸው ስናወራ ስናወራ.... እንደምታውቅ ነገረችኝ....
"ትምህርት ቤት ሁላ እኮ የሚወራው ስላንተ ነው..."
"ምን ተብሎ?"
"ዳግም ሠብለን ወዶ አበደ... ጠዋት ቤተክርስቲያን ከሰአት ከጴንጤዎች ቤት ይውላል ተብሎ ነዋ!"
"እና አመንሻቸው?"
"አዋ! የመዝሙሩ ግጥም እስኪጠፋብኝ ድረስ እንደምታፈጥብኝ የማላውቅ መሠለህ?! ሂሂሂ"
"ከትምህርት ቤት ይልቅ ቤተክርስቲያን ሳይሽ መልዐክ ትመስይኛለሽ..."
"ታቃለህ እንዲህ ያለ ፍቅር ፊልምና መፅሐፍ ላይ ብቻ ነው ያለው ብዬ በውስጤ አስብ ነበር... አንተ ግን አሳየኸኝ... ለዛ ነው ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ለአንተም ውብ ለመሆን መስታወት ፊት በነጠላ የምኳኳለው!"
ይህን ማመን አልቻልኩም ነበር... ወደፊትና ወደኋላ ዞር ዞር ብላ አየችና ከንፈሬን ሳመችኝ...
ደነገጥኩ...
"ጭዋነት ላይመስልህ ይችላል... መልዐክህ ብቻ ሳልሆን እንስትህም ነኝ!
ደግሞ አንድ ለአንድ ቅድስና ነው!" አትለኝ
አበስ ገበርኩ... ማመን አቃተኝ ትቻት ወደቤቴ እሮጥኩ... ገባሁ... በሬን ዘጋሁ ...
"ማንኛህ ነህ የሰማኸኝ? የትኛው ቤተክርስቲያን ላይ ነው የሰማኸኝ ስለቴን ላስገባ" ብል? ከዚህ ነው የሚለኝ አጣሁ...
አሰብኩ ምን ነበር የተሳልኩት?
እሁድ እስክትደርስ ጓጓሁ... ፈጣሪ ሀሳቡን ሳይቀይር.. ሰምተኸኛል ብዬ ስለቴን ላስገባ ቸኮልኩ...
በነጋታው... ትምህርት ቤት በአምስተኛው ክፍለ ጊዜ ለሽንት ስወጣ.... | 2 006 |
| 13 | The Body Keeps the Score
ከንፈሬ ከንፈሮቿን ጎርሰው ያውቃሉ.. ጣቶቼ ከጡቶቿ ጋረሰ ደንሰዋል.. ልቤ ከልቧ ጋር በሰመመን አውርተዋል.....
ነገር ግን አላፈቅራትም!...More | 2 101 |
| 14 | በሠላምም ባይሆን እንኳን ከ2018 ተላቀቃችሁ
ለሠላምም ባይሆን እንኳን ወደ 2019 ተሻገራችሁ!
ደግሞ ትናንት ያላልኳችሁ ፆም ስለነበረ ነው🤭 Anyway እወዳችኋለሁ🥰
✍Lewi
@lewi_derest | 2 719 |
| 15 | ደስ አለችኝ እሷን ቀና እያልኩ እያየሁ ህልሜን አንድ በአንድ አስታውሼ ለመፃፍ ሞከርኩ....
ተብሰለሰልኩ ሌላ አድካሚ ስራ ሕልም መፍታት.. ግን ከስሬ አላውቅም ሕልሜን ከፈታሁት ብኋላ ትክክለኛ መፍትሄ አገኝበታለሁ
ሕልሙ ሲፈታ እንዴት ያለ ኮተት እንደሆነ ላሳያችሁማ....
conscious መሪ ቢሆንም የመሪነቱ ስልጣን ያለው ግን Ego ጋር ነው.... ሻዷችን የኢጎአችንን አንባ ገነንነት ይፈራል...,ኮንሸስም በኢጎ ተደብቆ የኢጎን ፍላጎት ለማስፈፀም ከፊት ይሆናል....
ጭንብሎቻችን እንኳን ሳይቀሩ የኢጎአችን ወታደሮች ናቸው ኢጎን ነው የሚጠብቁትና የሚንከባከቡት... ይሄ ኢጎ ማለት ያ ወጣት ንጉሥ ማለት ነው! እነዛ ስዕል የሚመስል ፊት ያላቸው ወታደሮቹ ደግሞ በኢጎ የተገነቡት ጭንብሎች ኛቸው!
ግን አንድ ነገር አለ ከዚህ ኢጎ ጋር fit የሚያደርግ... ይህንን fitter ማየት የሚችለው ግን ከኢጎው ያፈነገጠ conscious ብቻ ነው።
ኢጎ ሰው የመሆን እራስ ነው! self ነው..... ሰው የስነ-ልቦና ቀውሰ ውስጥ የሚገባው ኢጎው ሲታመም ነው! በሳይኮሎጂ እነ ሻዶ... ኢድ... conscious and unconscious... persona.... የሚባሎ ምናባዊ አእምሮዎች አሉ... ቀውሱ የሚፈታውም በእነዚህ ዙሪያ ነው.... ሚስጥሩ ያለው እንግዲህ እዚህ ጋር ነው...
traumaም... manipulateም... abuseም... bullyም... የተለያዩ ከልቶች መጀመሪያ የሚያጠቁት ኢጎን ነው... ከዛ ብኋላ ነው እነጭንብል.. ሻዶ... unconscious ትርምስ የሚጀምሩት... ምክያየቱም ሻዶ የኢጎን አባበገነንነት ስለሚፈራው ይደበቃል... unconscious ደግሞ አንባገነንነቱን ስለሚጠላው ይቃወመዋል...
ጥበበኛው ሽማግሌ ማለት unconscious ነው የወጣቱን(የኢጎን) አንባገነንነት ሸሽተው የመጡት ሕዝቦችም ሻዶዎች ናቸው።
ይሄ ልጅ በኢጎው እና በደመነፍሱ መሃል ትልቅ ጦርነት ውስጥ ነው... ጦርነቱን ያስነሳው ደግሞ የሻዶዎች መብዛት ነው... ይሄ ማለት ልጁ አብዝቶ የሕግና የስርአት ሰው ለመሆን ይጥራል ማለት ነው።
ለዛ ነው ልማዶቹን በአንዴ ገፍቶ አዲስ ሕግና ስርአት ለመጠበቅ ሲሞክር ደመነፍሱ ሲዘናጋ ጠብቆ በቀድሞ ልማዶቹ አሁን ማድረግ የማይፈልገውንና የሚጠላውን ነገር በማድረግ ኢጎን ያጠቃዋል...
በዚህ ጥቃት ኢጎ በብስጭት consciousን ይቆጣዋል... እንዴት ይሄንን ሲያደርግ አንተ ንቁ አልሆንክም ብሎ በንዴት... በፀፀት.. ምናምን ይቀጣዋል....
ከህልሜ በተጨማሪ የምኮራባት ሦስተኛ ዓይን አለችኝ... እሷም ተቅበጥብጣ ወደአንድ ደጀ ገነት አማተረች... እነሆ በደጀ ገነቱ የሚመላለስ ድምፅ ሰማሁ...
"አዳም ሆይ ወዴት ነህ?" የሚል
"አለሁ!"
"የት አለህ?"
"ከደጀ ገነቱ ውጪ..."
"ደግ አደረክ አንዳንዴ ስፍራ መቀየር መልካም ነው"
"ከደጀ ገነት በላይ?"
"ታዲያ ምን ሽተህ ከደጀ ገነት ወጣህ? እራስህን መለወጥ.. ካለህበት የተሻለ ነገር ማግኘት ፈለክ... ለዚህ ፍላጎትህ ደግሞ የሚበጀውን ነው ያደረከው...
የኔ ልጅ እራስህን መለወጥ ላይ ብቻ ችክ አትበል ይጎዳሀል! አንዳንዴ እራስህን ከመቀየርህ በፊት መቀየር ያሉብህ በዙሪያህ ያሉ ሲስተሞች ሊኖሩ ይችላሉ!" አለኝ...
ተግባራዊ ቴራፒያችንን ጀምረናል....
"እስኪ ለዛሬ በጣም ቀላል የቤት ስራ ልስጥህ" አልኩት
"እሺ ስጠኝ"
"20 ሌትር ወይም ከዛ በላይ የሆነ ጀሪካን ፈልግና ይሄ ቤትህ ያስቀመጥከውን የውሃ ባልዲ አውጥተህ ጣል.... ከዛ የሚያሳስት ጆግ የሚባል ነገር አይኖርም!" አልኩት።
ዘለለ ደስ አለው... "እውነትህን እኮ ነው!" እያለ ጀሪካን ፍላጋ ደዋወለ...
ይሄም የሦስተኛዋ ዓይኔ ተንኮል ነው...
አብዛኛው ሰው ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ከችግሩ ጋር ተላምዶ ለመኖር ነው የሚፍጨረጨረው... ለዛ ነው በዙሪያው ላሉት ሲስተሞች ግድ የማይሰጠው....
አንዳንዴ ችግሮቻችንን ለመፍታት ቁልፉ ያለው እኛ ጋር ሳይሆን ሲስተሙ ላይ ሊሆን ይችላል...
ልክ ባልዲውን በጀሪካን የመቀየር ያክል ቀላል የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ከእራሳችን ጋር እየታገልን የስነ-ልቦና ባለሞያ ጋር እስከመምጣት የሚያደርስ ኮተት ያመጡብናል።
"አንተ ሰው መዳን ትፈልጋለህ?"
"ዶክተር ያምሀል እንዴ? ታዲያ ለምን መጣሁ?"
😂.... አባባሉ አሳቀኝ... ዶክተር ብሎ ያምሀል አላለም!...
"እራስህን ስርዓት ከማስያዝህ በፊት መጀመሪያ እይዛቸዋለሁ የምትላቸው ስርዓቶች ጤነኛ መሆናቸውን አረጋግጥ... ምናልባት እነሱ ታመው ሊሆን ይችላል እኮ አልያዝ ያሉህ... በእነሱ መታመም አንተ እንዴት ስርአት የለኝም ብለህ እራስህን ትወቅሳለህ?"
.........................................
መታከም አለብህ መባሌን ወደድኩት!.. እውነት ለመናገር መጀመሪያ ተናድጄባቸው ነበር በተለይ በአባቴ ላይ...
አሁን ግን እንኳንም ታከምኩ... ይህ ሰው በሽታዬን ብቻ አልነበረም የፈወሰልኝ... ወደ ደጀ ገነት ጎራ የምልበትን ጥበብም ጭምር ነበር የሰጠኝ!
✍ሌዊ
@lewi_derest | 3 162 |
| 16 | ይሄም የሦስተኛዋ ዓይኔ ተንኮል ነው...!
ደጀ ገነት!
እንግዳ የሆኑ ስሜቶቼ እንግዳ የሆኑ ድርጊቶችን ይወልዱብኛል...
የሆነ አቃጣሪ መንፈስማ አለ! መቼስ እኔ ከእኔ ወጥቼ እኔን እያየሁ ነው አትሉኝማ?
ስሜቶቼ የወለዷቸው እንግዳ ድርጊቶቼን ስታዘብ...እኔን ሳይሆን የሆነ ደደብ ሰውዬን እያየሁ ነው የሚመስለኝ!
አሁን ለምሳሌ በቀደም ለት... Xዬ ሚኒ ለብሳ ከፍቅረኛዋ ጋር ስትሄድ... ወሳጅ መንገድ መላሽ መንገድ አገናኘን... እሷ እንደሆነች እኮ አውቂያለሁ...
ገና ከላይ ስትመጣ ነው እሷ እንደሆነች ያወኩት... ግን እኔ ምን አደረኩ?
"ማማዬ ቀሚስሽ ታምራለች!" ብዬ መላከፍ...
"አንተ እብድ ነህ እንዴ Xህ ነበረች እኮ? ይሄ በሽተኛ ነው እንዴ" ምናምን ብሎ መሄድ....
እሷ ትስቃለች...
"ሂሂሂሂ አይ ሰሎሞን በቃ የምታረገውን አታቅማ? ኪኪኪኪ" የሳቋ ቀለሞች ብዛታቸው
ያኔ እንድወዳት ያደረገኝም ሳቋ ነበር... አላውቅም ግን ስትስቅ የሆነ የማይባት ቁንጅና አለ... ግን ምን ያደርጋል ይሄ ወዝጋባ እኔ ሳልጠግባት... ከእኔ አራቃት....
ፍቅር ማጣፈጫ ከሚባሉት ባንዱ ቀናችን... ከእሷ ጋር ውለን ለማደር ቀጠሮ ይዘን ነበር የተገናኘነው...
ቀኑን ሙሉ ኤኮ ደስ ብሎን ውለን ነበር... ፍቅራችን ጨምሮ ምናምን.. ከዛ ለማታ ብለን ገዛዝተን ልንገባ አስበን ሌሎቹን ከገዛዛን ብኋላ ወደዳቦ ቤት ሄድን....
ልጅ እያለሁ በጣም የምወደው ግን በችግር ምክንያት ሁሌ እንዳማረኝ የሚቀረውን ዶናት አየሁት... ብዙ ክሬምም አለ... አማረኝ! ዶናት የመብላት ጉጉት ያዘኝና ለእሷም ለእኔም ገዛን...
አላስችልህ ብሎኝ ከዳቦ ቤቱ እየወጣን... እኔ ዶናቴን ለመብላት እየተዘጋጀሁ...
"አባ? አባ? ስጠኝ?... እርቦኝ ነው?" የሚል ህፃን በአንድ እጁ በቀኝ በኩል ሱሪዬን ይዞ በሌላኛው እጁ ይለምነኛል...
እንዲህ ቁልቁል ሳየው ተበሳጨሁ... አለ አይደል በቃ የምወዳቸውን ነገሮች ሁሉ አገኘሁ ስል የሚነጥቀኝ መስሎ ነው የተሰማኝ...
የልመና ልምዱን የሚያስረሳ ደህና ኩርኩም አቅምሼ አባረርኩትና ዶናቴን ገምጬ ሳጣጥም...
ከማን አንሼ የሆነች ጥፊ ከፍቅረኛዬ ተሰነዘረብኝ...
"ሁለተኛ አጠገቤ እንዳትደርስ... አውሬ!" ብላኝ ጥላኝ ሄደች.....
እኔ እሺ ምን ላድርገው ሠውነቴ አእምሮዬን ትቶ ስሜቶቼን ሁኗል የሚታዘዘው...
ፍቅረኛዋ ቀንቶ ይሁን ምን አላውቅም ብቻ Xን እኝደተላከፍኩ ሂዶ ለአባቴ ነገረው።
ከዚህ ብኋላ ነው ታመሀል ብለው ካላሳከምንህ... የሚሉኝ...
............................................
መፈላሰፍ አለብኝ መሠለኝ... ካልሆነ ጭንቅላቴ መፈንዳቱ ነው!
የዛሬ የሰማሁት ቀውስ ደግሞ ጫን ያለ ነው!
የሳይኮሎጂስት ያለህ!? ብለው አንጠልጥለው እኔ ጋር አምጥተውት ምን ይሉኛል ብዬ ነው እንጂ... "ይሄንንማ ፀበል ውሰዱት.."ልላቸው ነበር!
መንፈስ እንጂ ቀውስ ያለበት አይመስልምኮ...
"እስኪ እየተቸገርክበት ያለኸውን ነገር ንገረኝ?" አልኩት
"ከማድረጌ በፊት ደስተኛ ነኝ ወይ ደብሮኛል ወይም ደግሞ ሞቅ ብሎኛል... ብቻ ከnormal ሙዴ ከፍም ዝቅም ያለ ስሜት ሲሰማኝ የሆነ ድርጊት አደርጋለሁ... ድርጊቱን ሳደርግ ከውስጤ ወቶ ሰውነቴ የሚያደርገውን የሚያይ አለ....
ከዛ ከድርጊቱ ብኋላ ድንገት ንቅት እላለሁ... ከዛ ድርጊቱ ልክ እንዳልነበር አስባለሁ... ሠውነቴና አእምሮዬ ሁሌም ከድርጊቱ ብኋላ አይስማሙም...
እነሱን ለማስታረቅ በስአቱ የተፈጠረውን ሳስታውስ... እኔ ከሰውነቴ ወጥቼ ሰውነቴ ያንን ነገር ሲያደርግ ከእግር እስከ ጥፍሩ አየዋለሁ... ትዝ የሚለኝ ሁሌም እንደዚህ ነው... እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ ከሰዎች ጋር እያጋጩኝ ነው" አለኝ
እሺ ይሄንን አሁን ምን ትሉታላችሁ? ፍንጭ ፈለኩ ታሪኩን ሁሉ አወራን ያንን አሰልቺ የአክስቶቹን ልጆች ታሪክ እንኳን ታግሼ ሰማሁት ግን ምንም ፍንጭ አላገኘሁም።
ስለዚህ ያለኝ አማራጭ አብሬው እየዋልኩ እሆናለሁ የማለውን ነገር ማየት ነው... ተስማምተን ቀን ቆርጠን... ተገናኘን...
ቡና ጠጥተን..ወክ አርገን ምሳ ለመብላት ወደእሱ ቤት ሄድን.. ምሳ በልተን ፊልም አይተን ምናምን ልንወጣ ስንል ለምሳ የተጠቀምንባቸውን እቃዎች ማጣጠብ ጀመረ።
አንድ ነገር አስተዋልኩ... ባልዲው ውስጥ ጆግ አለ... ከዛ ማስታጠብያውም ላይ ጆግ አለ... እና እቃዎቹን የሚያጥበው ማስታጠቢያ ላይ ባለው ጆግ ነው... ውሃ ሲያልቅበት ባልዲ ውስጥ ያለውን ጆግ እየረሳው የማስታጠቢያውን ጆግ ሊቀዳበት ጫፍ አድርሶት ሲያየው ነውበባልዲውጆግ የሚቀዳው...
ደጋግሞ ሲሳሳት ሳየው... ትኩረቴን ሰጥቼ መመልከት ጀመርኩ... ከስህተቶቹ አንዱ ላይ በማስታጠቢያው ጆግ ከባልዲው ቀዳ... ከቀዳ ብኋላ ባልዲ ውስጥ መግባት ያልነበረበት ጆግ መሆኑ ትዝ አለው... ከዛ ጆጉ ውስጥ ያለውን ውሃ መልሶ ባልዲው ውስጥ ገልብጦ ከእንደገና በባልዲው ጆግ ቀድቶ ወደ ማስታጠቢያው ጆግ ገለበጠ...
"እንዴ አንዴ ቀዳኸው እኮ ለምን መልሰህ ወደባልዲ ትገለብጣለህ?" አልኩት
"ምን ባክህ ሁሌ ነው የምሳሳተው እንደዚህ እያረኩ ካልሆነ አለምደውም ብዬ ነው..." እያለኝ እያወራን አጣጥቦ ጨረሰና.... በደመነፍስ የማስታጠቢያውን ጆግ ባልዲው ውስጥ ከቶት ከደነውና "በቃ እንውጣ ጨርሻለሁ" አይለኝም😂
"ባልዲ ውስጥ የከተትከው ጆግ እኮ..." አልኩት
ከፍቶ ሲያየው ተበሳጨ... "ይሄው በቃ እንደዚህ ነው የሚያደርገኝ..." አለኝ...
አሁን ቁጭ ብለን አወራን... "እስኪ አስታውስ ከአንተ ወጥቶ አንተን የሚያሳይህ ነገር ያሳየህን ሁሉ ንገረኝ.." አልኩት.... አይገርምም ልክ እኔ እንዳየሁት ነው የነገረኝ...
ለብቻዬ ተብሰለሰልኩ አሰብኩ... ያላገላበጥኳቸው መፅሐፎች የሉም... ብዙ ቆፈርኩ ግን አቃተኝ እዛው በላይብረሪዬ ውስጥ ጠረጴዛው ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ....
እነሆ የእኔም መንፈስ ተነሳበት... የሆነን ነገር ለመፍታት ወይም እዛ ላይ ለመድረስ አጥብቄ ስጥርና በተራመድኳቸው እርምጃዎቼ ውስጤ እርካታ ካልተሰማው አስደሳች መፍትሔ የማገኘው በሕልሜ ነው...
አለምኩ ህልሙም እንዲህ ነበር....
ጥበበኛ በሆነ ሽማግሌ ንጉሥ እና በወጣትንጉሥ መሀል ጦርነትተነሳ....
የወጣቱ አገዛዝ አንባገነንነት አለው... ወታደሮቹ እንኳን ሁሌም በጣም በቅልጥፍና ነው የሚያገለግሉት.... የወታደሮቹም ፊት ስዕል እንጂ ትክክለኛ ፊት አይመስልም።
የጥበበኛው ሽማግሌ አገዛዝ ደግሞ ሕግless ነው... ምክንያቱም እሱ ጋር ያሉት ሕዝቦች ሁሉም የአንባ ገነኑን ወጣት ሕግ ሸሽተው የመጡ ናቸው...
ወጣቱ በትዕቢት ወታደሮቹ እንዲያጠቁ ትዕዛዝ ሲሰጥ... ጥበበኛው ሽማግሌ በትዕግስት ጥቃቱን ይመክታል...
ለሕዝቡም እንዲህ ይላቸዋል "አትፍሩ ይህ ወጣት ንጉስ በጣም እያጠቃን ያለው መጠቃትን አጥብቆ ስለሚፈራ ነው... ስለዚህ ትንሽ ካጠቃነው ሙሉ በሙሉ ይበተናል ስለዚህ ከማጥቃት የሚደክምበትንና ለዘብ የሚልበትን ክፍተት እስክናገኝ በፀጥታ እንመክት አትፍሩ" ይላቸዋል።
ልክ እንዳለውም... ከማጥቃት ለዘብ ሲሉ ሳያስቡት ጥበበኛው ሽማግሌ አጠቃቸው በጣም በጥቂቱ ነው ያጠቃቸው ግን በአንዴ ፈራረሱ... የወጣቱ አገዛዝ በቀላሉ የተናደው ጥበበኛው ሽማግሌ በሚፈራው በኩል ስለመጣበት ነው... በቀስታ ዓይኖቼን ገለጥኩ ወደመስኮቱ ስመለከት ፍም የመሰለች ግን ዓይን የማትረብሽ የጠዋት ፅሐይ አየሁ.... | 2 635 |
| 17 | እንግዳ የሆኑ ስሜቶቼ እንግዳ የሆኑ ድርጊቶችን ይወልዱብኛል...
የሆነ አቃጣሪ መንፈስማ አለ! መቼስ እኔ ከእኔ ወጥቼ እኔን እያየሁ ነው አትሉኝማ?...more | 1 822 |
| 18 | ብር ለማሙላላት ብዬ ግቢ ውስጥ ተጥሎ የኖረ የውሻ ቤቱን እንኳን ሳይቀር እንዲገዛኝ አድርጋዋለች...
በእሷ ቤት እኔን ድሀ ለማድረግ ነበር... ያልገባት ነገር ግን እኔ ድርጆቶቼን አስተዳድር የነበርኩ ሰው ነኝ... በእኔ የሀብት ደረጃ ያሉ ሰዎችን ብዙ ጊዜ እንደማገኝ ዘንግታዋለች...
ዴት ሳደርጋት የነበረችውም ሴት ከእነዛ ብዙዎቹ አንዷ ናት... ለእሷ እልህ እኔም ሀብታም ሴት ግብቼ.. ቀቀድሞ ሚስቴ ጋር የተካፈልጉትን ሀብት አንድ ቅርንጫፍ ከፈትንበት...
ይህንንም ቅርንጫፍ ስናስመርቅ ያው ባሏ ባለሀብት ነውና ጠርተነው ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር መጣ....
ባመቱ የልጄን ክርስትና ትልቅ ሆቴል ውስጥ ደግሰን አሁንም ከተጠሩት ሰዎች ውስጥ እነሱ ነበሩበት....
በጉጉት ስናፍቃት የነበረችው ስአት ደረሰች ንግግር ለማድረግ ማይኩን ተቀበልኩ... ብዙ አላወራሁም ያልኩት ይህቺን ብቻ ነው!
"ቅርንጫፍ የማያወጣ ድርጅትና የማትወልድ ሴት ስሰጥህ የጎዳኸኝ መስሎህ ነበራ?... ነው ወይስ ሁለቱም መሀን ሆኑብህ?"
ሚስቴ ተኮሳትራ እያየችኝ "እንደሱ አይባልም ዞርበል ወደዛ" ብላ ማይኩን ቀማችኝ
ሰውዬው እያየሁት ፊቱ ቀልቶ በቁጣ ሚስቱን እንደበግ እየጎተተ... ይዟት ወጣ...
እነሆ ከእዛች ቀን ብኋላ ሰውዬው ለእኔን ለመብለጥ ቅርንጫፍ ሲያበዛ... ልጅ ሲያስቆፈቁፋት... ወጪ በስቶበት እዳ በእዳ ሁኗል።
እኔን የገረመኝ የእሷ ነገር ነው መውለዷ ላይቀር እኔ ላይ ተመናቅራ... እኔኮ አንድ ልጅ ነበር የጠየኳት... እኳ ግን እዛ ሂዳ ስድስት ልጆችን ቆፈቅፈቻታ!
ልጄንም ሚስቴንም እወዳቸዋለሁ ግን የጓጓሁለትን የሕይወት ትርጉም አላገኘሁም... የታዘብኩት አንድ ነገር ግን... ለካ ሰው ወዶ አይደለም እር በእርስ የሚጣላው... የውስጡን ጥያቄ ጭጭ ለማስባል ነው...
አይገርምም ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር እልህ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ትዝ ብሎኝ የማያውቀው ትርጉም ማጣት... ልክ በዝረራ እንዳሸነፍኳት ሳውቅ እሷም ተስፋ ቆርጣ ስትፀፀት ሳይ... መልሼ ትርጉመቢስ ሆንኩ...
ልጄን እያየሁ... አስባለሁ... አሁን ምን ብዬ በዚህ ሕፃን ትርጉም እሰራለሁ? ካለ እኔ መኖር አይችልም ብዬ? እኔ ልክ በእሱ እድሜ እያለሁ ካለ አባቴ ነውኮ ያደኩት..
አንዳንዴ ማወቅ መጥፎ ነው... መሀይምነታችን የሰጠንን ሠላም ይነጥቀናል!
እንደዛ መኖርን ባላውቅ ኑሮ ለልጄ ለመኖር እጓጓ ነበር!
የሆነኛው ቀን ላይ ተኝቼ በህልሜ ምን በሙት ቤተሰቦቼ መሀል እንደቀላቀለኝ አላውቅም እነሱን መስዬ ከእነሱ መሀል ተቀምጬ... የሆነ የጎሰቆለ ሽማግሌ ... በቁጣ ይናገረናል...
"በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት?
የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን?
ከእናን መሀል ነገን የሚያውቅ ወይም ትናንትን የሚመልስ ሀያል አለ?...." እያለ ያንባርቃል
እሱ እንደዛ እየጮኸ እኔ እያንቀላፋሁ የአባቴን ትከሻ ተኝተርሼ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገኝ ሽማግሌው በቁጣ በከዘራቸው... "ተነስ... አንተ ንቃ ብዬሀለሁ.... ሲለኝና በእውኑ አለም ልጄ... "አባቢ ተነስ እረፈደኮ ንቃ" ሲለኝ አንድ ሆነ....
ከዛች ቀን ብኋላ ልጄ የሕይወት ትርጉሜ አልሆነም ግን ለልጄ ሕይወትን ላወርሰው ፈለኩ...
ልጄ ሆይ ከሕይወት ጋር አትታገል ልለው ይዳዳኛል!
እውነታው እሱ ነዋ... ስለትናቱም ስለነገውም የእኛ ድርሻ የለበትም...የእኛ ድርሻ መኖር ብቻ ነው... ማሳለፍ ፈልገን ያለፍነው ትናንት የለንም... መድረስ ፈልገንም የደረስንበት ነገ የለንም ሁሉም ከእኛ ፍቃድ ውጪ በእራሱ ፍቃድ የሚመጣና የሚሄድ ከሆነ ለምን እኛ ለመያዝና ለመልቀቅ ከሕይወት ጋር ግብግብ እንገጥማለን?
አውቃለሁ ይህ የጅል ምክር ነው! ግን ደግሞ የሚያድነውም የጅል መንገድ ነው! ጥቂት ስለትናንት ጥቂት ስለነገ... ብዙ ስለዛሬና ስለእራስ ማሰብ ትልቅ ፈውስ ነው...
✍ሌዊ
@lewi_derest | 2 777 |
| 19 | ደራሲው...∞:
በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት?
የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን?
አጋጣሚ.... ከምዕራፍ ፬ የቀጠለ
ሁሉም ስሜታቸውን የሚከተሉ በጎች ስለሆኑ እንጂ ላለመሞት እኮ ምክንያት ነበራቸው!
ሁሉም መሞታቸው ውስጥ እኔ ቦታ አልነበረኝም... ማናቸውም ከመሞታቸው በፊት ሕመማቸው እንጂ እኔ ትዝ አላልኳቸውም ነበር...
እናቴ ስትሞት በጥፊ ስለመመታቷ እንጂ ስልጇ አደራ ያለችው ነገር አልነበረም... አያቴም ስለልጅነቷ ፍቅር እንጂ ሰለልጅ ልጇ ግድም አልሰጣትም... "አለሁልህ!" ሲለኝ የነበረው አባቴ እንኳን... በቤተክርስቲያን መቃብሩ ላይ ዘፈን እንዲፃፍለት ድፍረት እስኪኖረው ስሜቱ አውሮት እኔን ዘነጋኝ።
እንዲህ ከነመፈጠሬም ሊረሱኝ ነገር እሱስ ቢሆን ምን በእስተርጅናው ወጣት ሴት ጋር ጢል ያደርገዋል? እሷስ ብትሆን ጥፊ ለማይችል ልቧ ምን ሽማግሌ ላይ ይለጥፋታል? የእነሱ ጦስ በእነሱ መለጣጠፍ ለተወለድኩት እኔ ተረፈ!
አውቃለሁ እናቴ ስሜቷ ተጎድቶ ነበር... አባቴም ለዘመናት ያረገዘው እውነት ሀሰት ሁኖ ተወልዶበት ፀፀት አንጀቱን ቢበላው ነው... ግን እኔስ? ሰለእነሱ እንደዛ መሆን ምን አገባኝ?
እኔን ከመውለዳቸው በፊት ጣጣቸውን አይጨርሱም ነበር? እኔን ለምን የቁስላቸው አጋር ያደርጉኛል? ምናልባት በልጄ ከካሰኝ ብለው የሚወልዱኝ የእኔ ሕይወት ቀልድ ነበር እንዴ?
የእነሱ በጭፍን መኖር እኔን ጨካኝ አድርጎኛል... በዘር ፍሬዬ ውስጥ የተከማቹ ነፍሶችን ሕያውነት እስከከለክላቸው ድረስ ጨካኝ አድርጎኛል...
ልጅነቴን እያየሁ ሌላ ልጅነት የተሞላበት ሕያውነት ለምን እንዲመጣ አደርጋለሁ?
ሕይወት እንደሆነች ደደብ ነገር ናት ትኝሽ ትልቅ አትልም... ታዲያ ለምን ብዬ? ና ተቸገር ተሰቃይ ከዛ ሙት ብዬ ልጅ የምወልደው?
ይህ የእብደት አስተሳሰቤ ነበር ከሌላ እብድ ሴት ጋር ያጋባኝ... እሷም የእኔ ቢጤ ናት! ለምን እወልዳለሁ ባይ አመፀኛ!
ላለመውለድ ሠርገን ተጋባን! ሕይወት ደደብ ናት አላልኳችሁም? እኮ...
በ18 አመቴ የአባቴን ድርጅቶች ሳስተዳድር... ገና መኖር ስላልጀመርኩ ነው ብዬ ነበር... በ20 አመቴ የኔ ቢጤ እብድ ሳገባም ገና መኖር እየጀመርኩ ስለሆነ ነው ብዬ ነበር....
አሁንም ግን የመኖር ምክንያትና ትርጉም አጣሁ... አሁን አሁን እነዛ ስሜታቸውን የሚከተሉ በጎች ናቸው ያልኳቸው ቤተሰቦቼ እንኳን ያስቀኑኝ ጀምረዋል...
እነሱ ቢያንስ ለመሞት ምክንያት ነበራቸው! ስሜታቸውን ለመከተል ስሜታቸውን የፈጠረ ትናንት ነበራቸው!
እኔ ግን ትናንትን የሚመስል ዛሬን እየኖርኩ... ለመኖርም ለመሞትም ትርጉም ያጣሁ ሰው ሁኜ ቀረሁ...
ለብቻዬ ስሆን... እኔም እንደቤተሰቤ ልሙት እንዴ እላለሁ... ይሄ አወኩ ባይ አእምሮዬ ድንገት ብድግ ይልና ሙተህስ? ይለኛል... እሺ በቃ ልኑር ስል መልሶ ምን አገኘሁ ብለህ? ይለኛል!
በመኖርና ባለመኖር መሀል ሌላ ጨካኝነት ተወለደ...
ለእኔ የመኖር ትርጉም ከሰጠኝ ስለልጁ ስሜት ምናገባኝ!...
ሴተኛ አዳሪዎች የሚዳሩበት አልጋ ላይ እንኳን ሳይቀረው ትንሽዬ ስህተት እየፈለገ ነፍስ በነፃ የሚያድለው እግዜር ሰብአዊነት ካልተሰማው እኔ ምን ቤት ነኝ.. ልጄን ያለፍቃዱ ወደዚህች ዓለም... ምናምን ብዬ የምመፃደቀው?! የሚል ሀሳብ ውልብ አለብኝ...
ይታያችሁ በጥዋቱ አራት ስአት ሚስቴን ደውዬ ካልመጣሽ አልኳት... ስራ አስፈቅዳ ስትደናበር ቤት ደረሰች...
የምናወራው ነገር አለ ስላልኳት ሳሎን ሶፋው ላይ ተኮፍሼ ተቀምጬ ምናምን ጠብቃ ነበር... መኝታ ቤት ነኝ ስላት እየተገረመች...
"ገና በጥዋቱ ሴት ሰይጣን ለከፈችህ? ሆሆ..." እያለች እንደመሳቅ እያደረጋት የሸሚዟን ቁልፍ እየፈታች መጣች...
"ሴት መሆኗ ነው የሚገርምሽ? ጎረምሳዬን ብቻ ሳይሆን አእምሮዬንም ጭምር ነው አቁማብኝ የሄደችው"
"የዛን ያክል ቆንጆ ናት? ከእኔ ትበልጣለች?" ብላ እንደማኩረፍ አደረጋት...
ከመቼው ሸሚዟን ፈታ እንደተጣበቅን አላውቅም አኩርፋ ፊቷን ስታዞር ነው አጠገቧ እኝደነበርኩ የታወቀኝ...
"ሃሃሃሃሠ በሰይጣን እየቀናሽ ባልሆነ ብቻ!"
"ኧረ ባክህ አልቀረብህም!"
"አጠይቂኝም! እሷ ከእኔ በምን ተሽላ ነው አእምሮህን ጭምር...." ገና ተናግሬ ሳልጨርስ
"እ...? አንተ እስኪ ንገረኝ እ በምን ተሻለች?"
"ያኔ እባቡ ሄዋንን ምን አላት? እንደ እግዜር ትሆኛለሽ! የእኔዋ ሰይጣን ደግሞ ምን አለችኝ መሠለሽ..."
እሺ ባክህ ምን አለችህ"
"አትናደጂያ!"
"መስሎህ ነው አልተናደድኩም ቀጥል"
"አንተ ከእግዜር ትበልጣለህ ወይ? እሱ ነፍስ ለመስጠት ያልሰሰተውን አንተ ማናባህ ስለሆንክ ነው ሥጋውን የምትከለክለው? አትለኝ መሠለሽ"
"ሂሂሂ ለማን ነው ሥጋ የከለከልከው?"
"አንቺ ደግሞ ለልጃችን ነዋ!"
"እቺን ሰይጣንማ እገላታለሁ! ባሌን ምን አርግ ነው የምትለው!"
"ፈርታሽ ሲኦል ተደበቀች ሂደሽ ትገያታለሽ ወይስ ልጅ ትወልጂልኛለሽ?"
"ወረኛ... ናበል አሁን! እንደሚያጠባ ሴት ከስራ ተሯሩጬ የመጣሁትስ ነገር ሆ!"
"እየቀለድኩ ግን አይደለም ልጅ መውለድ እፈልጋለሁ!"
አሁን ከአልጋው ተነሳች... በፍጥነት የፈታችውን የሸሚዝ ቁልፍ በዝግታ እየዘጋች...
"ከምወልድ ሲኦል ወርጄ ያቺን ሰይጣን ብገድላት ይቀለኛል"
"አልቀለድኩም!" አልኳት
"እኔም አልቀለድኩም...ማግባት እራሱ እንደማልፈልግ ታውቃለህ! ላለመውለድ ሀሳባችን ስለገጠመ እንጂ!"
"አንቺ ከፈለግሽ ወደ ሲኦል ውረጂ እኔ ግን መውለድ እፈልጋለሁ!"
"ከሌላም ሴት ቢሆን?"
"የቅድሟ ሰይጣን ማርገዝ ከቻለች ከእሷም ቢሆን እወልዳለሁ!"
"ክፉ ነህ! ጨካኝ... እንዴት ምንም የማያውቅን ሕፃን እዚህች ከንቱ ዓለም ውስጥ ልማግድ ትላለህ?"
"እኔኮ ሥጋ እንጂ ነፍ አይደለም የምሰጠው... ጨካኝ ከተባለም አስቀድሞ ነፍስ የሰጠው እግዜሩ ጨካኝ ይባል እንጂ እኔ ምን ቤት ነኝ..."
"አንተ ልጅ ከወለድክ እበቀልሀለሁ... ከሌላ ሴት ጋር ስለሆንክ ሳይሆን ስለወለድክ ብቻ እበቀልሀለሁ"
እየተመናቀረች ቦርሳዋን ይዛ ወጣች... እንደተኮራረፍን ሳምንታትና ወራት መጡ... ይገባታል ሌላ ሴት ዴት እያደረኩ እንደሆነ
ሳልቀድመው ልቅደመው ይመስል ካርድ ሰጠችኝ የጥሪ ካርድ... አነበብኩት...
"አባትሽ መሠልኩሽ እንዴ እኔ ቤት ተቀምጠሽ የሠርግ መጥሪያሽን የምትሰጪኝ? ቀሽም!" የእውነት አናዳኝ ነበር... እኔ ሌላ ሴት የማገኘው በቅንሀት እሺ ትለኛለች ብዬ እንጂ ልተዋት ፈልጌ አልነበረም።
ሴቶች ቀድመው ይበስላሉ ይባላል ግን ቀድመው ያሰቡ እየመሠላቸው ቀድመው ያራሉ እንዴ! የማትረባ
"ይሄ ነው የገረመህ..." ብላ ሌላ ወረቀት ሰጠችኝ... የፍቺ ወረቀትና ንብረቴን ለመካፈል የከሰሰችበትን ወረቀት ሰጠችኝ... ሁለቱም ላይ ፈረምኩላት..
"ይሄው ከአሁኗ ስአት ብኋላ ባልሽ አይደለሁም የንብረቴ ግማሽ ሀብት ባለቤት ሁነሻል... ይሄ ቤት ግን በአባቴ ስም ስለሆነ አሁኑኑ ከዚህ ቤት ውጪልኝ ላይሽ አልፈልግም"
"ልብዞቼን ለአዲሷ ሚስትህ አልብሳት..."ብላ ስልክ እየደወለች ተመናቅራ ወጣች...
የንብረቶቼ ግማሽ ባለድርሻ ስለሆነችና የንብረቶቼ ግማሽ በብር ሲቀየር የተገመተላት ገንዘብ በንብረት እንጂ በብር ደረጃ እጄ ላይ ስለሌለ ድርጅቶቼን ለመሸጥ ተገደድኩ...
የዛን ያክል እንዳስቀየምኳት የገባኝ... የሸጥኳቸውን እያንዳንዳቸውን ንብረት የገዛኝ የእሷ ባል መሆኑን ሳውቅ ነው... | 2 371 |
| 20 | በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት?
የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን?....more | 2 195 |
