ch
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

前往频道在 Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

显示更多
2 277
订阅者
+224 小时
+97
+3830
帖子存档
"እባቡና የቤተሰቦቼ ነገር (ከኮሜንት የተገኘ)" => አዎ ወንድሜ ይህ ታሪክ በአንተ ቤተሰብ ብቻ አይደለም ያለው በእኔም ጭምር እንጂ እባብ ይጠሉታል፤ ነገር ግን ደግሞ የምመለክ እባብ አለ በኦሮምኛ tiksa(ጠባቂ) ነው የምሉት የምያደርጉት እኔም አስታውሳለሁ ከታላቅ ወንድሜ ጋራ ለእናቴ ልጅ ሆኜ ምንም ስለዝህ ስለመናፍስቱ አሰራር በማላውቀው ግዜ ነበርና ለእናታችን እሷ ስታመልክበት የነበረው ጎጆ(galma) ይባላል በኦሮምኛ ልፈርስ ስል እየጠገንለት እያለን በቤቱ ስር ትልቅ እባብ አየን ነገር ግን ድንጋይ ውስጥ ተጠቅልሎ ስለነበረ እኛም ልጆችም ስለነበርን ፈርተን አጎታችንን ጠርተን በስለት ማለት በማረሻ ወግተን እንግደለው ስንለው አይሆንም አይነካም ይህን ከደረጋችሁ ሌላ መጥተው ይነድፋችዋል ወይም በሀብት፣ በጤናችን፣ ብቻ የሆነ እንከን እንደምገጥመን ስነግረን ፈርተነው ተውነው። => ታሪኩ ብዙ ነው ረጅም ነው ነገር ግን የምያሳዝነው እስከዛሬ ድረስ የጣኦት አምልኮ የበአድ አምልኮ በእኛ ቤት ውስጥ ይመለካል ይህን ለማስቆም ያለደረኩት ጥረት የለም ነገር ግን ቀሪ ወንድሞቼም ሆነ ሌላ የአካባቢያችን ማህበረሰብ ንሰሐ አባት እንኳን ይህን ነገር አየተቋወሙ እንድያግዙ ለአስር አመት ያህል ስጮህ እዝህ ደርሻለሁ ምክንያቱም አሁንም በቤታችን በግ እየታረደ ይገበራል ሌላም ግብር ይቀርብለታል ጨሌም ይመለካል ይልቅ በቤተሰብ ውስጥ ሰላም ፍቅር መግባባት አብሮ መሆን ወዘተ ግን በእኛ ቤተሰብ አይታሰብም። ምክንያቱም ይህ የበአድ አምልኮ አለና ነገር ግን ከአባቶቻችን በገኘውት ምክር አንድ ሰው በነፃ ፍቃዱ ሰይጣን ይሸለኛል ብሎ በሰውም በንስሐ አባቱም ተመክሮ አልተውም ከለ ግን ከዛ ሰው ህይወት ርቆ ከእግዚአብሔር ጋር በንስሐ ህይወት እየኖረ ከቤተሰብ የመጣበትን የዛር መንፈስ በትግል ማሸነፍና ከህይወቱ ማራቅ ይችላል። => እንደምችልም ተነገረኝ ያንንም እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ከእኔ ብወጣና ከህይወቴ ብርቅ እናቴ ላይ ያለው፣ የዛር ቡዳና፣ የዘር አይነጥላ፣ አዳልሞቲ ወሰንጋላ፣ ሌሎችም መናፍስቶች እኔን እሷ ላይ ሆኖ አይፈትነኝም ማለት አይደለም ነገር ግን አባቶቻችን በምያስተምሩንና በምመክሩን መንገድ ከጠላታችን ሰይጣን ጋር እየተዋጋን ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ያስፈልጋል ብዙ ነው የእያንዳንዳችን ቤት ውስጥ ያለው መከራ እግዚአብሔር ክብሩን በቤተሰቦቻችን ውስጥ ይግለፅ። => የሰይጣን ፈተና ቀላል አይደለም በርቱ ወንድማችን ከእኔ የህይወት ታሪክና በቤተሰቦቼ ውስጥ እየተደረገ የነበረውና እየሆነው ያለው ነገር ተመሳሳይ ሆኖብኝ ነው ሁላችንም እንደዝህ አይነት ትምህርቶችና በማይሰለቹ አጭር ቁምነገር አስተማሪ የሆኑትን አሳጥረው ስለምታቀርብልን እናመሰግናለን በርታ። የተዋህዶ ልጆች በርቱ ሰይጣን እንኳን እኛን የፈጠረውን እየሱስ ክርስቶስን እንኳን ፈትነዋል ግን እግዚአብሔር አሸናፊ ስለሆነ በሀይሉና በስልጣኑ ድል አድርጎታል እኛ እግዚአብሔርን ይዘን እናሸንፋለን። እንበርታ! #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

ሁለም የሚደመጡ የአባቶቻችን ተግሳጽና ምክር ክፍል 1 ቁጡ ሰው ምን ይመስላል? || የማይጠቅም ፍርሃት @haileG2239 #ethiopia #ebs 🔥💥 https://youtu.be/pb0Lg5bqRFU?si=-L2JBYKiYLVL1Ugb

እንድትሞት ከፎቅ ወረወርኳት ግን ተረፈች የኩፉኝ በሽታና መናፍስታዊ ሴራው ቅዳሴና መረሳት የሌለባቸው ነገሮች | መምህር ግርማ | ተስፋዬ አበራ 😱🚩🔥 https://youtu.be/kxSyv5ndKg0

🙏 እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ቅዱስ ገብርኤል መሻታችሁን፣ አሳባችሁን ይሙላላችሁ። 🙏🙏🙏
🙏 እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ቅዱስ ገብርኤል መሻታችሁን፣ አሳባችሁን ይሙላላችሁ። 🙏🙏🙏

ይገርማል!! እባቡና የቤተሰቦቼ ነገር መምህር ግርማን ከማወቀ በፍት እባብን እንደ ጠባቂ መልአክ || ዕውር የሚያደርጉ የዛር መንፈሶች #ebs 😱😭🚩🔥 https://youtu.be/KgeFtW9NfkE

"ብፁዕ ቅዱስ ፍሬምናጦስ (አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን)" => በ፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተወለዱት ቅዱሱ አባታችን በሀገራችን ክርስትናን ያስፋፉ ታላቅ አባት ናቸው> በማይመረመር የእግዚአብሔር ሀሳብ
"ብፁዕ ቅዱስ ፍሬምናጦስ (አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን)" => በ፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተወለዱት ቅዱሱ አባታችን በሀገራችን ክርስትናን ያስፋፉ ታላቅ አባት ናቸው> በማይመረመር የእግዚአብሔር ሀሳብ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው፦ ክርስትናን ካስፋፉ ዋነኛ አባቶች አንዱ ሆኑ፥ ሀገራችንን ከሌሎች ክርስቲያን ሀገሮች ጋር አስተካከሉ፥ በህዝባችን የተወደዱ አባት ሆኑ። አባታችን ብፁዕ አቡነ ሰላማ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተዘዋወሩ ክርስትናን ሰበኩ፤ ብዙዎችን ከጨለማ ወደ ብርሃን አመጡ። ለዚህም ነው ብርሃን ገላጭ፣ ሰላማ የተባሉት። ሰላማ ማለት "ሰውና እግዚአብሔርን የሚያስታርቅ" ማለት ነው። የቤተክርስቲያናችን ፓትርያርክ ሆነው በብዙ አገልግለዋል። ጻድቁ አባታችን ብዙ ሰዎች ከጣኦት አምልኮ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ እንዲመጡ ተግተዋል። የቅዱሱ አባታችን ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ምልጃና በረከት አይለየን። #ሸር_ሸር! #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

በጥፍር ቀለም በጓደኛዋ የተመተተባት ዕድሏና እውቀቷ የተወሰደባት | ክርስቶስ ዘወትር ወደ እኛ እንዲመጣ ይሄን እናድርግ | መምህር ኢዮብ ይመኑ ተስፋዬ አበራ https://youtu.be/6PyLthTf3gM?si=ZSAIrXrVO0OWUWnt

«ቀኖና የመደንገግ የዖዛን ቅንነት!» => የአሚናዳብ ልጅ ዖዛንን በእስራኤል በተመረጡ 32ሺ ሰዎች መሃል ለቀናት በቤታቸው የሰነበተችውን ታቦተ ጽዮንን ከሚያመጡ ሰዎች መሃል ነበር። => ታቦተ ጽዮን የከበረችበትን ሰረገላ ከወንድሙ ጋር ይነዳ ነበር። ነገር ግን የሰረገላውን ድንገት መንገጫገጭ ያሳሰበው ዖዛን ለቀናት በአባቱ ቤት የሰነበተችውን ታቦተ ጽዮን "ከሰረገላ እንዳትወድቅ" በሚል እጁን ዘርግቶ ደግፎ ሊያጸናት ሞከረ። ከእዘህ በኃላ ያለው ውጤት ሲጠቃለል"“የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው፤ በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ። — 2ኛ ሳሙ 6፥7" ሲል ይዘገዋል። => አሁን ላይ በቅንነትም ይሁን ሆን ተብሎ(በተዋሕዶ ስም የተሃድሶ እና ቅባት ተወካዮች ስላሉ) በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የአገልጋይነትን ስያሜ የወሰዱ ሰዎች በድፍረት ስርዓተ ቤተክርስቲያን ላይ ጨክነው አዲስ በር ሲከፍቱ እናያለን። => "ስትሰብክ ለምን ነጠላ ለብሰህ፣ መስቀልህን እያሳየህ፣ በስመ አብ በወልድ...ብለህ አትጀምርም" የሚል ጥያቄ የተነሳበት አንድ ቲክቶከር "ዘመኑን አይመጥንም እንደዛ ብዬ አልጀምርም" የሚል ጥቅል መልስ አይነት ሲሰጥ ሰማው። ቤተክርስቲያን የማትናገራቸው፣ ከመቅደሱ ያልዋለ፣ ከኦርቶዶክሳዊነት የስብከት ምንጭ ያልፈለቀ ወንጌል በቤተክርስቲያን ስም እዚህ እና እዛ ቆመው እየተፋጩ ወተት ለሚፈልገው ምዕመን አጥንት ሊያስግጡ ይሞክራሉ። => ዛሬ ደግሞ እንደ ላቲን እና ካቶሊክ ስእለ ማርያምን እንደ ኦሪቱ ጽላት አክብረው የሚዞሩ ወጣቶች አዲስ የቅዱሳት ስእላት የመገልገል ቅኖና ድንጋጌ ሰርተዋል። እንደ ወረርሽን የመስፋት እድሉ ሰፊ እንደሆነ እንጠብቃለን። እንግዲህ በጎም ሆነ መጥፎ ትላንት የቅድስት ቤተክርስቲያን ስርዓት እና ልምድ ያልሆኑ ልምምዶችን ላይ መድፈር ማቆም አለብን። => እንደ ታቦተ ጽዮን አዘነበሉ ብለን ለእግዚአብሔር ብለን ነው በሚል ቅንነት ልንነካው የማይቻለን ስርዓቶች አሉን። አዳዲስ ልምምዶች ስርዓት እንዲሆኑ፣ ነባሮች እንዲለወጡ(እንዲሻሻል) የመደንገግ እና ልምምድ ውስጥ እንዲገቡ የውሳኔ ልዕልና ያለው አንድ ጉባኤ አለን። ግብሩም ቅዱስ ስሙም ሲኖዶስ ይባላል። #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

ብዙዎችን የሚቀይር ድንቅ ትምህርት || በጎረቤቶቻችን መካከል ያለው አጋንንታዊ ሴራ || የዲያብሎስ እሳት የበላው ትውልድ | መምህር ግርማ | ተስፋዬ አበራ 🚩 https://youtu.be/TljYlEnmc5M

=> እንኳን ለቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። => "ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።" (ሐዋ.
=> እንኳን ለቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። => "ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።" (ሐዋ. ፯፥፷ /7፥60/) => እንደ ነደ እሳት ያለ ሰይፍ የሚቆርጥ ቃለ እግዚአብሔርን የሰበክ፤ ስለመለኮትም ያስተማርክ፣ የተዘጋ መጽሐፍ ገልጠህ የምትተረጉም። ቀዳሜ ሰማዕት ንዑድ ክቡር ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በጸሎትህ አስበን። የቅዱሱ ሰማዕት አባታችን በረከትና ምልጃ አይለየን። በበረከቱ የፀናን እንሆን ዘንድ ይርዳን። አሜን! #ሸር_ይደረግ! #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

ጠቋርን ከሌሎች መናፍስቶች ልዩ የሚያደርጉ ነገሮች | ሴቷ አጋንንት ሻንቂት ወንዱ ደግሞ ጠቋር ይባላል | የአዛዝኤል ልጆችና ምልክታቸው | መምህር ግርማ 😱💥🔥 https://youtu.be/3s7pIifzZ3g

"የእመቤታችን ዕረፍትና ዕርገት በአባ ጽጌ ድንግል" => አባ ጽጌ ድንግል እንዲኽ እያለ ያወድሳታል:-"እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ” => (ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ) => “ትእምርተ ፍልሰትኪ እምድረ ጽጌ ድንግል በክልኤ በደመና ሰማይ አርአየ ዘሐዋርያት ጉባኤ ወእለ ሞቱ አንቅሐ እምከርሠ መቃብር ቀርነ ጽዋዔ ለነሰ እንዘ ይብሉ ሶበ ሰማዕነ ውዋዔ መሰለነ ዘበጽሐ ትንሣኤ” => (በኹለት ወገን ድንግል የኾንሽ ማርያም ሆይ አበባ ካለበት ምድር ወደ ሰማይ የማረግሽ ተአምር በሰማይ ደመና የሐዋርያት ጉባኤን አሳየ፤ የሞቱትንም ከመቃብር ውስጥ በተአምር ነጋሪት ድምፅ አስነሣ፤ ለእኛስ የምስጋና ከፍተኛ ድምፅን በሰማን ጊዜ የሙታን መነሣት የደረሰ መሰለን እስኪሉ ድረስ)። => “አመ ነሥኡኪ እምኤዶም አዕላፈ ማሕሌት ጾታ እንዘ ይጼልሉኪ ድንግል በአክናፈ መባርቅት ከመ ወልታ ሰራዊተ ሰማይ ይቤሉ ለክብረ ፍልሰትኪ ግርማ ትርሲታ መኑ ይእቲ ዛቲ ዘገዳመ ጽጌ ዕጥነታ ወከመ ሠርጸ ጢስ ዘስኂን ይምዕዝ ዕጥነታ” => (ድንግል ወገኖች አመስጋኞች መላእክት በየነገድ በየነገድ ኾነው በመባርቅት ክንፎች እንደ ጋሻ ጋርደው ከኤዶም ገነት በተቀበሉሽ ጊዜ የሚያስደንቅ ክብር ለተገለጸባት ለዕርገትሽ የሰማይ ሰራዊት አበባ ካለበት በረሓ የምትወጣ መዐዛዋም ከነጭ ዕጣን ይልቅ የሚሸትት አወጣጧም እንደ ጢስ አወጣጥ የኾነችይኽቺ ማናት? ይኽቺ ማን ናት ይላሉ (መሓ ፫፥፲፮))። [የአምላክ እናት ሆይ እወድሻለሁ] #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

ጉድ! በዝምድና ውስጥ ወሲብ የሚያስፈጽሙ መናፍስቶች አገልጋዮች ከሸለቆ መውጣት አለባቸው መምህር ግርማ | ተስፋዬ አበራ | ዲያቆን ዘላለም ታዩ 💥🔥😭 https://youtu.be/q9SIW5Up1Ws

TikTok ያመጣብን አጋንንታዊ ልምምድ የጠቋር መንፈስ አገልጋይ ሲሆን መንፈሳዊ ዛሮችና ፈተናቸው || መምህር ግርማ ተስፋዬ አበራ #ebs #ንቁ 🔥💥 https://youtu.be/wXT1SffCtkQ

ጠባቂ መልአክ ለምን ዝም ይላል? ሕጻናት ሲደፈሩ፤ ሰዎች ሲገደሉ? መነሻውና መድረሻው የጠፋው ትውልድ መምህር ግርማ || መምህር ተስፋዬ አበራ 💥🚩🔥😱 https://youtu.be/yUOKmH3cEgA

ሰይጣን ሁለም ለመቅደም ይታገላል! አሁን የሰይጣን የመቅደም ጊዜ ነው! ትዳርና እጮኝነት | ሰውነት የረከሰበት ዘመን እግዚኦ! | መምህር ግርማ 🚩😭🔥 https://youtu.be/zP4Ldpic6Ec

ስለ በርሜል ጸበል ቀሲስ ሄኖክ የተናገሩት || ዓይን አፋርነትና የአጋንንት ሴራ || ጠላታችን ሰይጣን ዲያብሎስ ነው | ቀሲስ ሄኖክ | ግርማ ወንድሙ 😭😱🚩💥 https://youtu.be/GhxXVGN-4Sg