ch
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

前往频道在 Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

显示更多
2 275
订阅者
+124 小时
+117
+3230
帖子存档
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! እንኳን ለደብረ ምጥማቅ ፅድቃኔ ማርያም አመታዊ የመገለጥ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። ✣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟ በአንደበታችን ይደርብን በዓሉን የሰላም የፍቅር የበረከት በዓል ያድርግልን ከመጣብን መከራ ችግር እመቤታችን በኪዳኗ ትጠብቀን አለው ትበለን ከአምላክ ታስታርቀን። አሜን! ፃድቃኔ ማርያም ደጓ እናቴ ግንቦት 21 እመቤታችን ማርያም ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው። ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር። እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር። ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል ፤እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤ አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው። ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤ አሁን ግን ኃጢያታችን ሲበዛ በረድኤት ወይም ለበቁ ካልሆነ ካልሆነ በገሃድስ ተገልጻ አትታይም። ለእናቱ ለቅዱስተ ቅዱሳን ለንፅህተ ንፁሀን ለአዛኝቷ ድንግል እመቤቴ ለቅድሳን እናታቸው ለነቢያት ትንቢታቸው ለሰማእታት እክሊላቸው ለሆነች ለእናቱሲል ይማረን በቃቹህ ይበለን ከመጣብን ከዚህ ክፉ በሽታ ይሰውረን በቃችሁ ይበለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

#በእምነት_መቁጠሪያን_ስንጠቀም_እንዲህ_ይሆናል!! https://youtu.be/aN9ufr6erEw?si=-wvihP3lKaxxrsgA

#መጽሐፈ_ቆጵሪያኖስንና_መፍትሔ_ሥራይን_እንደ_ጸሎት_መጽሐፍ!! በርሜል ጊዮርጊስ ሲሄድ የገጠመኝ አስደንጋጭ ታርክ!! ገዳም ከመሄዳችን በፍት ይኼንን አድርጉ!! https://youtu.be/m-cMXt1ra9M

የዕለቱ ወንጌል (የማቴ.16፡24-28) «በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ። እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋ
የዕለቱ ወንጌል (የማቴ.16፡24-28) «በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ። እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል። እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።» #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

#እሸቱ_መለሰ_ምን_እያለን_ነው_ወላጆች_አድምጡ!! በእጮኝነት ጊዜ ድቀት ቢያገኘንና ሴቷ ብታረግዝ ምን እናድርግ?? አስራት የማታወጡ ሰዎች ይኼንን አዳምጡ!! https://youtu.be/a_Imleok9f4

ግንቦት ፳ /20/ በዚችም ቀን ከአባቶች መምህራን ዐሥራ ስድስተኛ የሆነ በደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት ሆኖ የተሾመ የከበረ አባት አባ ዘትረ ወንጌል አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ መላእክት
ግንቦት ፳ /20/
በዚችም ቀን ከአባቶች መምህራን ዐሥራ ስድስተኛ የሆነ በደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት ሆኖ የተሾመ የከበረ አባት አባ ዘትረ ወንጌል አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ መላእክት ንጽሕናን የለበሰ ትሕትናን ቅንነትን የሚወድ ነበረ። የምንኵስናንም ልብስ ከለበሰ በኋላ መልካም ገድልን ተጋደለ በክርስቶስ መንጋ ላይም ጠባቂ ሆኖ ተሾመ ከዚያም በኋላ በበጎ እርጅና አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

#ዘወትር_ጸልዮና_ሰግዶ_የሚተኛ_ሰው_የሚያገኛቸው_በረከቶች!! ብዙ ወጣቶች በኃጢአታቸው መብዛት ምክንያት እንዲህ ያስባሉ!! #hailegebrielreacts19 https://youtu.be/XYmLaYIGE5c

🙏 እንኳን ለገናናው መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ወርሀዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ። ቅዱስ ገብርኤል አለሁ ይበላችሁ። ረድኤት በረከቱ ቃልኪዳኑ በሁላችን ላይ ይደር። መልካም ቀን ይሁንላችሁ። 🙏🙏
🙏 እንኳን ለገናናው መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ወርሀዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ። ቅዱስ ገብርኤል አለሁ ይበላችሁ። ረድኤት በረከቱ ቃልኪዳኑ በሁላችን ላይ ይደር። መልካም ቀን ይሁንላችሁ። 🙏🙏🙏

#ጉደኞች!_ዘጠና_መስገድ_አቅቶን_ሰይጣንና_አጋንንት_ምን_ስልጣን_አለው_እንላለን!! በትዳር ውስጥ ያለ ዝሙትና ንጽሕና! በተመስጦ ለመጸለይ ይኼንን እናድርግ!! https://youtu.be/W6RAlAYlK64

ግንቦት ፲፰ /18/ በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው። በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረ
ግንቦት ፲፰ /18/
በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው። በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ። ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኋላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል። የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኋላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ይልቅ አባቱንና እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ። ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ። አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው። አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥ ሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ። በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር #Subscribe #Like #Share 👇👇 www.youtube.com/@haileG2239

የዕለቱ ወንጌል (ማቴ.16፡23-28) => እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን። ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ
የዕለቱ ወንጌል (ማቴ.16፡23-28) => እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን። ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ። እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል። እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ። #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

100% ሕይወታችንን የሚቀይር መምህር ተስፋዬ ያስተማረን ድንቅ ትምህርት!! መምህር ተስፋዬ አበራ #hailegebrielreact በማለዳ ንቁ! #ethiopia https://youtu.be/87hs3OumGuM

🙏 ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ። በያላችሁበት የእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ለሰኔ 12 የኃያሉ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዝክር መር
🙏 ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ። በያላችሁበት የእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ለሰኔ 12 የኃያሉ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዝክር መርሀ ግብር ለማዘጋጀት አስበናል እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ። ታዲያ በዚህ የበረከት ሥራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ቤተሰቦቼ በውስጥ መስመር እኔን በቀጥታ ማናገር ትችላላችሁ። እንዲሁ ደግሞ በዚህ የስልክ መስመር በመደወል ማናገርና በምን ማገዝ እንዳለባችሁ መወያየት ትችላላችሁ። ታዲያ ሁላችሁም ቤተሰቦቼ የክርስትና ስማችሁን መጻፋችሁን እንዳትረሱ በጸሎት እንዲያስቧችሁ ለማድረግ። እኔን ለማናገርና መረጃ ለመቀበል https://t.me/haile_gebriel_tube_bot የዝክሩን አስተባባሪዎች ለማግኘት በዚህ ስልክ ይደውሉ! 0903162292 / 0945957646 ሁላችሁም በዚህ የበረከት ሥራ ተሳተፉ ማንም ሰው እንዳያመልጠው። ለብዙ ሰዎች ሸር አድርጉ። የኃያሉ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። በርቱ!

#ፍታችን_በማዲያትና_ቁስል_ከተመታና_ጸጉራችን_ከተበላሸ_ከሸተተ_ይኼንን_አስተውሉ!! በውበታችን የቀና የቡዳና የአይነጥላ መንፈስ ፈተናና ሴራ!! #ethiopia https://youtu.be/iDa5K8L8vmk

#እውቀታችን_ዕድላችን_በመተትና_አጋንንት_እንዲህም_ልወሰድ_ይችላል! በክርስትና ስማችን መተትና ሟርት እንዴት ልሰራ ይችላል? #hailegebrielreacts19 https://youtu.be/TdrDc9ezPq4?si=O2im17OA4N0miSja

#ብዙዎቻችን_በክርስትና_ሕይወታችን_የምናማርረው_ይኼንን_ስላላወቅን_ነው!! ያልሄድኩት ገዳም የለም ግን አንዱም ችግሬ አልተፈታም! #hailegebrielreact https://youtu.be/hstEw5ueLqE

ግንቦት ፲፮ /16/ በዚችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳ
ግንቦት ፲፮ /16/ በዚችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ የሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው። በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን። ከዚህ በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ። ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

#ሦስቱ_መምህራን_የነገሩን_ከባድና_ልናውቃቸው_የሚገቡ_የመናፍስት_ውጊያ_ምስጢሮች!! ጸልያለሁ ሰግዳለሁ ጾማለሁ ግን አንዳች ለውጥ በህይወተ የለም!! #ስግደት https://youtu.be/RGL7Qj43UWo