ch
Feedback
HiTech

HiTech

前往频道在 Telegram

HiTech | Learn. Fix. Create. 📱💻🎨 Your Ethiopian tech hub! We teach: ✅ Smartphone Repair ✅ Laptop & Chip-Level Repair ✅ Graphics & Motion Design ✅ Coding & Web Development ✅ Tools, Tips & Tech Reviews Join the HiTech family — grow your skills & build

显示更多
1 635
订阅者
+224 小时
+127
+2630
帖子存档
HiTech
1 636
Series/parallel በአንድ ላይ ልናገኝም እንችላለን። @cellphonetechnology
Series/parallel በአንድ ላይ ልናገኝም እንችላለን። @cellphonetechnology

HiTech
1 636

HiTech
1 636

HiTech
1 636
•ፓራሌል/ parallel circuit:- ~ትይዩ ሰርኪዩት ሲሆን ሁሉም አምፖሎች ቀጥታ ሶርስ ስለሚያገኙ አንዱ ቢበላሽ እንኳን ቀሪዎቹ ይሰራሉ። ~በዚህ ጊዜ ደግሞ: √እያንዳንዱ ቮልቴጅ ከዋናው/ሳፕላይ ቮልቴጅ እኩል ነው። √የእያንዳንዱ ከረንት ድምር ደግሞ ከዋናው ከረንት እኩል ነው። √የሪዝስታንስን ድምር ለማግኘት ደግሞ የእያንዳንዱን ሪዝስታንስ ግልባጭ በመደመር ምናገኘው ዉጤት ግልባጭ/resprocal መዉሰድ ነው። @cellphonetechnology

HiTech
1 636
💡ኤሌክትሪካል ሰርኪዩት አይነቶች:- ~ሁለት አይነት ሰርኪዩቶች አሉ። እነርሱም:- ስሬስ/series እና ፓራሌል/parallel ናቸው። •ስሬስ/sereis circuite: ~ተከታታይ የሆነ እና እያንዳንዱ component በአንድ ነጠላ ገመድ የሚያያዙ ናቸው። ~ምናልባት አንዱ አምፖል ወይም ሎድ ከተበላሸ ሰርኪዉቱ ይቋረጣል። ~ ወጥ የሆነ ወይም እኩል ከረንት አላቸዉ ሁሉም አምፖሎች። ~የእያንዳንዱ ቮልቴጅ ድምር ዉጤት ደግሞ ከሳፕላይ ቮልቴጅ እኩል ነው። ~ጠቅላላ ሪዚስታንስ ደግሞ የያንዳንዱ ሪዚስታንስ ድምር ውጤት ነው። @cellphonetechnology

HiTech
1 636
💡የ ከረንት፣ ቮልቴጅና ሪዚስታንስ ዝምድና:- I=v/R ወይም v=I*R ሲሆን ኦምስ ሎው በመባል ይታወቃል። ~ዝምድናቸውን በደንብ ለመረዳት በጠባብ ቱቦ ውስጥ የሚፈስን ውሃ ብንወስድ:- የዉሃው ግፊት= ቮልቴጅ ሲሆን የሚፈሰው ውሃ = ኤሌክትሪክ ከረንት ውሃው እንዳይፈስ የሚከለክለው=ሪዚስታንስ ልንለው እንችላለን። @cellphonetechnology

HiTech
1 636
3. ሪዚስታንስ/Resistance :- ~በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁሶች ውስጥ የኤሌክትሮኖችን እንቅስቃሴ የሚያግድ/የሚቃወም ነው። ~ምልክቱ R ሲሆን መለኪያዉ ደግሞ Ohm ይባላል። ~ቁሶች/substances ኤሌክትሪክ የመቃወም ባህሪያቸውን መሰረት በማድረግ በ 3 ይከፈላሉ። • ኮንዳክተር/conductor:- ዝቅተኛ ኤሌክትሪክ የመቃወም ባህሪ ያለውና እጅግ ባጣም ጥሩ ኤሌክትሪክ ማስተላልፍ የሚችል ነው። ላምሳሌ:- Silver Concrete Gold Dirty water Copper Platinum Aluminum Lemon juice Steeel Brass Iron Bronze Seawate Graphite Mercury ወ.ዘ.ተ. •ሰሚ ኮንዳክተር/Semiconductor:- ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የመቃወም ባህሪ ያለውና በከፊል የሚያስተላለፍ ነው። ለምሳሌ:- Cadmium Boron Aluminum Gallium Indian Germanium Silicon Phosphorus Arsenic Antimony ወ.ዘ.ተ. •ኢንሱሌተር/insulator:- እጅግ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የመቃወም ባህሪ ያለውና ኤሌክትሪክ የማያስተላለፍ ነው። ለምሳሌ:- Rubber Glass Pure water Oil Air Diamond Dry wood Dry cotton Plastic Asphalt Fiberglass Dry paper Porcelain Ceramics Quartz ወ.ዘ.ተ. ያወቁትን ለሌሎች ማጋራት መልካምነት ነው @cellphonetechnology

HiTech
1 636
2. ቮልቴጅ/Voltage:- ~በኤሌክትሪክ ቻርጆች የግፊት ሀይል የሚፈጠር ልዩነት ነው። ምልክቱ v ሲሆን መለኪዉ ደግሞ ቮልት ሜትር(V) ይባላል። ~~~ ሁለት አይነት የቮልቴጅ አይነቶች አሉ። እነርሱም:- ዲሲ ቮልቴጅ/DC voltage እና ኤሲ ቮልቴጅ/AC Voltage ናቸው። 💡ዲሲ ቮልቴጅ:- ~የማይለዋወጥ/ቋሚ የሆነ ዋጋ አለው። ~የምናገኘዉም ከ ባትሪ፣ ከ ፀሃይ ብርሃን ሊሆን ይችላል። ~በእጃችን ብንነካው ሊነዝረን ይችላል እንጅ የከፋ ጉዳት አያደርስብንም። ~ ሞባይል ስልኮች፣ልፕቶፖች ወ.ዘ.ተ. የሚጠቀሙት ይህንን ቮልቴጅ ነው። ~ቤታችን ዉስጥ ያሉት ሶኬቶች ግን የሚሰጡን ኤሲ ቮልቴጅ ነው ነገር ግን ቻርጀሮቻችን ኮንቨርተር ስላላቸው ወደ ዲሲ ቮልቴጅ ይለውጡልናል። 💡ኤሲ ቮልቴጅ:- ~ይህ ደግሞ ተለዋዋጭ የሆነና ዋጋው በሰዓት ላይ የተመሰረተ ነው። ~ኤሲ ቮልቴጅ ሲንግል ፌዝና ስሪ ፌዝ ተብሎ በሁለት ይከፈላል። ሲንግል ፌዝ ሁለት ገመድ ሲኖረው አንዱ እሳት/hot line ሲሆን ሁለትኛው ደግሞ ኒዉትራል የምንለው ሲሆን ኤሌክትሪክ የለዉም። በቮልት ሜትር ስንለካውም የምናገኘዉ ዋጋ 220/240V ሊሆን ይችላል። ስሪ ፌዝ ደግሞ ባለ 4 ገመድ ሲሆን ሶስቱ ገመዶች እሳት ሲኖራቸው አንዱ ግን ኒውትራል የምንለው ነው። ~ኤሲ ቮልቴጅን ከ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎች እና ከ ኤሲ ጀነሬተሮች እናገኛለን። የሚለካዉም 380V ወይም 400V ሊሆን ይችላል። ~ለህይወታችን በጣም አደገኛ ስልሆነ ልንጠነቅምቀቅ ይገባል። ያወቁትን ለሌሎች ማጋራት መልካምነት ነው @cellphonetechnology

HiTech
1 636
1.ኤሌክትሪክ ከረንት/electric current: ~የኤሌክትሪክ ቻርጆች ወይም የኤሌክትሮኖች በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁሶች የሚያደርጉት ፍሰት ኮረንቲ ይባላል። ለምሳሌ:- መዳብ፣ ሲሊቭር፣ ወርቅ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ ባህሪ ሲኖራቸው እንደ አሉሚንየም፣ የጨውነት ባህሪ ያለው ዉሃ፣ የሰወች ሰዉነት፣ ዛፎች/ እርጥብ እንጨት ወ.ዘ.ተ. ኤሌክትሪክ ማስተላለፍ ይችላሉ። ኤሌክትሪክ ማስተላለፍ የማይችሉ ደግሞ ፕላስቲኮች፣ ደረቅ እንጨት፣ ንፁህ ውሃ እና ሌሎች የብረት ባህሪ የሌላቸዉ ንጥረ ነገሮች እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ። ~~ኮረንቲ/electric current- ምልክቱ I ሲሆን መለኪያዉ ደግሞ ኣሜትር(A) ይባላል። t.me/cellphonetechnology

HiTech
1 636
የራም ማስታወሻን ለመዘርጋት የሚያገለግሉ መስመሮች በሁለት ዋና ክፍሎች እንከፍላቸዋለን፡፡ 1. ተቀያያሪ ራም (Dynamic RAM) 2. የማይቀያየር ራም (Static RAM) 1. ተቀያያሪ ራም (Dynamic RAM) በካፓሲተር ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው በየጊዜው የማስታወስ ሀይሉን ካፓሲተሩን በመሙላት የሚያገለግል ነው ፍጥነቱ ዝግ ያለ ሲሆን የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ግን አነስተኛ ነው ብዙ መጠን መረጃን የማቀፍ ችሎታ አለው የያዘውን መረጃ በተደጋጋሚ በኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያስታውስ ይደረጋል፡፡ አልበለዚያ መረጃው ይጠፋል በብዙ ኮምፒተሮች ውስጥ እንደ ዋና ማስታወሻ ክፍል ይጠቀሙበታል፡፡ 2. የማይቀያየር ራም (Static RAM) መረጃውን የኤሌክትሪክ ሀይል እስካለ ድረስ ያለምንም ችግር በፍጥነት መረጃን የመመዝገብ ችሎታ አለው በትራሲስተር ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ኤሌክትሪክ በተደጋጋሚ በመስጠት ይዘቱን እንዲያስታውስ ማድረግ አያስፈልግም፡፡ የሚጠቀመው የሀይል መጠን ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ሙቀት ያመነጫሉ በአብዛኛውን ጊዜ ፍጥነት በሚያስፈልጋቸው ኮምፒተሮች ላይ እንጠቀምበታለን መረጃን ለመመዝገብ የሚያስፈልገው የማስታወሻ የመያዝ መጠኑ አነስተኛ ነው፡፡ ROM (Read Only Memory)፡- ይህ የሚሞሪ ዓይነት ከስሙ መረዳት እንደምንችለው መረጃዎችን ለማንበብ ብቻ ይገለግላል፡፡ እዚህ ሚሞሪ ላይ ያሉትን መረጃዎች መጻፍ ወይም መቀየር አይቻልም፡፡ መረጃዎችን ግን ለዘለቄታው ያስቀምጣሉ፡፡ ROM የምንለው የማስታወሻ አካል ወይም ሜሞሪ ተለዋዋጭ ያልሆነ መመሪያዎችን ለሁል ጊዜ የሚይዝ ነው፡፡ ኤሌክትሪክ ኃይል ቢቋረጥም ሆነ ባይቋረጥ የያዘውን መረጃ የማያተን ነው፡፡ ROM ኮምፒተሩ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን በላዩ ላይ የተሰሩትን የተለያዩ ትዕዛዞችን እንዲያነብ እንጂ እንዲፃፍበት የማይፈቅድ እና ኮምፒተሩ በተደጋጋሚ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን የሚጠቀምበት መመሪያዎችን የሚይዝ የሜሞሪ ዓይነት ነው፡፡ ተጠቃሚው በውስጡ ያሉትን መረጃዎች ለማንበብ ይችላል እንጂ የመለወጥ ወይም በላዩ ሌላ ተጨማሪ መረጃ መፃፍ አይችልም፡፡ ስለዚህም በሮም ላይ ያሉ መረጃዎች በዋናነት እንዲያገለግሉ ተደርገው ኮምፒተሩ በፋብሪካው በተሰራበት ወቅት የተፃፈ መመሪያዎችን የያዘ ማስታወሻ ወይም ሜሞሪ ሲሆን በኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት የያዘውን መረጃ አያጠፋም፡፡ ROM የምንለው ማስታወሻ ዋና ዋና ትዕዛዞችን የያዘ መመሪያ የምናስቀምጥበት ስፍራ ነው፡፡ እነዚህንም መሠረታዊ መነሻ ሀሳብንና ውጤቱን ማቀናጃ (Basic input output system (BIOS) መመሪያዎችን ኮምፒተሩ ስራ በሚጀምርበት ጊዜ መጀመሪያ ሊያገኘው የሚፈልገው መነሻ ሀሳብ ነው፡፡ እነዚህ መሰረታዊ መመሪያዎች በዋናነት በኤሌክትሪክ መረጃ መዝገብ ተመስግበው ይቀመጣሉ፡፡ ለምሳሌ አንድን በስርዓት የተዘጋጀ መጽሀፍ ብንገዛ እናነበዋለን እንጂ ያለደራሲው ፍቃድ የማሻሻል እና የመፃፍ መብት የለንም፡፡ @cellphonetechnology

HiTech
1 636
All mobile phone flash file available for only 1500 birr Samsung Tecno Infinix Nokia Huawei Itel Iphone and others More than 1.2 TB file 0922888396

HiTech
1 636
ካፓሲተርምንድንነው ? WhatisCapacitor ? ==================== 👉ካፓሲተር የኤሌክትሪክ ሀይልን(Electrical Energy) በኤሌክትሪካል ቻርጅ (Electrical change) መልክ ማከማቸት የሚችል የኤሌክትሪካል ኮፖነንት ነው። 👉ካፓሲተሮች በአይነት በጣም ብዙ ሲሆኑ ከበጣም ትናንሽ እስከ ትላልቅ ለፓወር ፋክተር ማስተካከያነት እስከሚያገለግሉት የሚገኝ ሲሆን ሁሉም ግን ተመሳሳይ አገልግሎት ነው ያላቸ፤ እሱም ኤሌክትሪክ ቻርጅ ማከማቸት(Store Electrical changes) ነው። 👉ካፓሲተር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ትይዩ ኮንዳክቲቭ (ብረት) ሳህኖች እርስ በርስ የማይገናኙ ወይም የማይነካኩ ነገር ግን በኤሌክትሪክ የሚለያዩት በአየር ወይም በሌላ መከላከያ ቁሳቁስ ለምሳሌ በሰም በተሰራ ወረቀት፣ ሚካ፣ ሴራሚክ፣ ፕላስቲክ ወይም ሌላ የፈሳሽ ጄል እንደ ኤሌክትሮላይቲክ ካፓሲተር የሚያገለግሉ ናቸው። 👉በካፓሲተር ሰሌዳዎች(Capacitor plates) መካከል ያለው የኢንሱሌሽን ንብርብር በተለምዶ ዳይኤሌክትሪክ (Dielectric) ይባላል። 👉ካፓሲተሮች የተለያየ አይነት ያላቸው ቢሆኑም ሁሉም የተለዩ ቢያንስ ሁለት የኤሌክትሪክ ሊዶች (ሳህኖች) ይይዛ 👉ሊዶቹ የብረት ፣ የአሉሚኒየም ፎይል ወይም ዲስኮች ወዘተ ቀጭን ፊልሞች(thin films) ሊሆኑ ይችላሉ 👉ዳይኤሌክትሪክ (Dielectric) መስታወት ፣ ሴራሚክ ፣ የፕላስቲክ ፊልም ፣ አየር ፣ ወረቀት ፣ ማይካካ ፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል። 👉 ከተቃዋሚ በተቃራኒ ፣ አንድ ካፓሲተር ኃይልን አያጠፋም። 👉ይልቁንም አንድ ካፓሲተር ኃይል በውስጡ ሳህኖች መካከል በኤሌክትሮ ስታቲክ መስክ መልክ ሃይልን ያከማቻል። 👉ካፓሲተር በኤሌክትሪክ አስተላላፊ እቃዎች ላይ ሊፈጠር የሚችል የሃይል ልዩነት ሲኖር (ለምሳሌ ፣ አንድ ካፓሲተር ከባትሪ ጋር ሲያያዝ) ፣ የኤሌክትሪክ መስክ በዳይኤሌክትሪክ ላይ ይገነባል ፣ ይህም ፖሰቲቭ የኤሌክትሪክ ቻርጅ (+Q) በአንድ ሳህን ላይ እንዲሰበሰብ እና ኔጌቲቭ የኤሌክትሪክ ቻርጅ (-Q) በሌላ ሳህን ላይ እንዲሰበሰብ ያደርጋል። 👉አንድ ባትሪ ከካፓሲተር ጋር ለተወሰነ ጊዜ ከተያያዘ ፣ ምንም የኤሌክትሪክ ፍሰት በካፓሲተሩ ውስጥ ሊፈስ አይችልም። ነገር ግን ፣ የተፋጠነ ወይም ተለዋጭ ቮልቴጅ በካፓሲተር ሊድ ላይ ከተተገበረ የመፈናቀያ ኤሌክትሪክ ፍሰት ሊፈስ ይችላል። #የካፓሲተር_አገልግሎት/ #Applications_of_Capacitor ➖የኤሌክትሪክ ኢነርጂ ለማከማቸት፣ ➖አላስፈላጊ ድግግሞሽን/frequency ለማስወገድ ➖የቮልቴጅ ለውጥን ለማዘግየት ➖እንደ ሴንሰር መሳሪያ(Sensing device) ሆኖ ያገለግላል። ➖ለተሽከርካሪዎች ድምፅ ለማውጣት ያገለግላል ➖AC እና DC ቮልቴጅን ለመለየት ያገለግላል። 👉 #ሌላ_እንድናቀርብላችሁ_የምትፈልጉትን_ሀሳብ_መስጫ_ላይ_ፃፉልን @cellphonetechnology

HiTech
1 636
#የኤሌክትሪክ_ጥገና / #Electric_Maintenance ===================== 👉በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃወች ወይም የቤታችን መሰመር ብልሽት ሲያስተናግድ የምናስተካክልበት መንገድ ጥገና ይባላል። 👉ብልሽት ሊይስከትሉ የሚችሉ ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው። 1. #ክፍት_የኤሌክትሪክ_መስመር ( #open_circuit) 👉የክፍት የኤሌክትሪክ መስመር(open circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም ➖የጭነት መብዛት ➖የፊዉዝ መቃጠል ➖የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መበጠስ ➖በደንብ አለመገናኘት ወይም አለመርገጥ ➖መዛግ ➖መላላት 2. #የተገናኘ_የኤሌክትሪክ_መስመር (#short_circuit) 👉የተገናኘ የኤሌክትሪክ መስመር(short circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም፦ ➖የመቃጠል ➖የሙቀት መብዛት ➖የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ ➖እርጥበት 3. #የኤሌክትሪክ_መስመር_ከአካሉ_ጋር_መገናኘት ( #grounding) 👉የኤሌክትሪክ መስመር ከአካሉ ጋር እዲገናኙ የሚያደርጉ መንስኤዎች ➖የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ ➖እርጥበት ➖የመቃጠል ➖የመላላት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ብልሽቶች ይሁኑ እንጂ እያንዳንዱ ብልሽት አንዱ ሌላዉን እንደሚያመጣ ይታወቃል።ለምሳል የኤሌክትሪክ ሥርጭት በአቐራጭ መገናኘት ከአካሉ ጋር መገናኘትን መበጠስን ያመጣል። ብልሽቶች በመብራት ፣ በሞተር፣ በትራንስፎርመር ላይ ተመሣሣይ ቢሆም ምልክታቸዉና የጥገና ሥራቸዉ ይለያያል።ለምሳል መብራትን የወሰድ እንደሆነ አምፖሉ ከተቃጠለ ያለዉ አማራጭ መጣል ነዉ።ሞተርን ወይም ትራንስፎርመር ሽቦ(winding) ከተቃጠለ ተጠግኖ በሥራ ላይ ይዉላል። #ብልሽትን_የመለየት ዘዴ 👉ብልሽቶች በተለያዩ መንገዶች ይታወቃል። 👉መረጃን የማወቅ የመለየት ዘዴ አጠቃቀም አንደሰዉ ልምድ ቢለያይም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ። ➖በማየት ➖በመስማት  ➖በመመርመሪያ መሣሪያ በመጠቀም #በማየት 👉የኤልክትሪክ ዕቃዎች ብልሽት ( ለምሳል ምጣድ,ምድጃ ) የተበጠሰ ወይም የተቃጠለ ከሆነ በመፍታተ ውስጡን በመመልከት ብልሽቱ ማወቅ ይቻላል። #በመስማት 👉በመስማት ዕቃዎቹ ብልሽቱ ሲያጋጥማቸዉ ሙሉ በሙሉ ሥራቸዉን በማቐማቸዉ ብቻ ሳይሆን እየሰሩ በሚፈጥሩት ድምፅ ሊደርስ የሚችለውን ብልሽት አስቀድሞ ማስተካከል ይቻላል። #በመመርመሪያ_መሣሪያ_በመጠቀም 👉ማንኛዉም የኤሌክትሪክ ዕቃ ብልሽት ሲገጥመዉ በቀላሉ የመመርመሪያ መሣሪያዎችን በመጠቀም የብልሽቱ ዓይነት ለይቶ ለማወቅና ለጥገና አመቺ መሆኑንና አለመሆኑን መለየት ይቻላል። የመፈተሻ መሣሪያዎች:- ➖መልቲ ሜትር ➖ሜገር ➖መብራት ➖ቴሰተር #መልቲ_ሜትር 👉ይህ የመመርመሪያ የመፈተሻ መሳሪያ ቮልቴጅን ፣ከረንትንና የሬዚስታንስ መጠን የሚለካልን መሣሪያ ነዉ። 👉በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃዎች ሁሉ በዉስጡ ሬዚስታንስ (ከረንት ተቃዋሚ) አለዉ። 👉ከፍተኛ ጉልበት ያለዉ የኤሌክትሪክ ዕቃ ሬዚስታንሱ ሲለካ አነስተኛ ነዉ። 👉አነስተኛ ጉልበት ያለዉ የኤሌክትሪክ ዕቃ ሬዚስታንሱ ሲለካ መጠኑ ከፍተኛ ነዉ። 👉የተበጠሰ ገመድ ወይም ያልተገናኘ መስመር ሬዚስታንሱ በጣም ከፍተኛ ነዉ። 👉ያልተበጠሰ ገመድ ወይም በአቐራጭ የተገናኘ መስመር ሬዚስታንሱ ወደ ዜሮ ይጠጋል። #በኤሌክትሪክ_የሚሰሩ_መሳሪያዎች_ጥገና 👉በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን ለመጠገን በመጀመሪያ እቃዎችን ጠንቅቆ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ። 👉በዚህ መሰረት አንድ ኤሌክትሪሺያን ማወቅ የሚገባዉ:- ➖እቃዉ እንዴት እንደሚሰራ መረዳት ➖በኤሌክትሪክ እቃ ላይ የተፃፉትን መረጃዎች ማወቅ ➖ለእቃዉ መጠገኛ የሚዉሉትን መለኪያ መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ ➖የሚጠገኑ እቃዎች ሲፈቱ በጥንቃቄ መረጃዎችን መሰብሰብ  ➖የጥገና ቅደም ተከተል መሰረት በማድረግ መታየት የሚገባቸዉ የመሳሪያዉ አካል በኃይልና በኤሌክትሪ መፈተሻ መሳሪያ መመርመር ➖ከኤሌክትሪክ መሳሪያው ወይም ከሚጠገኑ እቃዎች ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ሰራተኞ ወይም ግለሰቦች ስለ እቃዉ ሁኔታ ማነጋገርና መረጃ መሰብሰብ። ያወቀቱን ማካፈል መልካምነት ነው ። #ለሌሎችም ያጋሩ❗️ Telegram 👉 @cellphonetechnology

HiTech
1 636
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox @Tekle21

HiTech
1 636
photo content

HiTech
1 636
ከቻርጅ ጋር የተያያዙ ችግሮች ጥገና 1. ቻርጅ የሚደረግ ስልክ 1.1 የባትሪዉን የቮልቴጅ መጠን በመልቲ ሜትር መለካት • ማንኛዉም ባትሪ የቮልት መጠኑ ከ3 ቮልት በታች ከሆነ ቻርጅ አያደርግም ። የባትሪያችን ትክክለኛው ቮልቴጅ መጠን ከ30 ቮልተት እስከ 3.7ቮልት መሆን አለበት ። ከ3.0 ቮልት በታች ሲሆን የባትሪው መቀስቀስ ይፈልጋል ። የመቀስቀስ ሂደት የቮልቴጁን መጠን ከ3.0 ቮልት በላይ እንዲሆን ማድረግ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ እንችላለን ። አንዳንድ ሰዎች ባትሪ መቀስቀስ የባትሪዉን አቅም የሚጨምር ይመስላቸዋል ።ይህ ግን ስህተት ነዉ ። ባትሪ መቀስቀስ ማለት ባትሪዉ የያዘዉን የቮልቴጅ መጠን ከ3.0 ቮልት በታች ከሆነ ቢያንስ 3.0 ቮልት ወይም ከዚያ በላይ እንዲሆን ማድረግ ማለት ነዉ ። 1.2 ቻርጅ ኮኔክተሩን ማየት • እግሮቹ ተሰብረዉ ወይም ታጥፈዉ ከሆነ ተገቢዉን ሚስተካከያ ማድረግ ወይም መቀየር ተገቢ ነዉ ። የቻርጅ እንቴርፌስንም ቆሽሾ ከሆነ ወይም ከቦታው ተነስቶ ከሆነ ማየት ይኖርብናል ። ከቆሸሸ ማጽዳት አለብን ። 1.3 የቻርጅ ከረንት ማለፊያ መንገድን በመልቲ ሜትር ማረጋገጥ ይኖርብናል • ቻርጅ አይሲ ሁለት ተግባራትን በአንድ ጊዜ ይሰራል ፣ አንደኛዉ ባትሪን ቻርጅ ማድረግ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ለሲፒዩ ቻርጅ መሰካቱን ሪፖርትን ማድረግ ነዉ ። ሲፒዉ ደግሞ ለስክሪን ትእዛዝ በማስተላለፍ ቻርጅ መደረጉን የሚያሳየን ምልክት ማየት እንድንችል ያደርጋል ። ፊዩዚ ከመጠን ያለፈ ቮልቴጅን ይቆጣጠራል ። ዳዮድ ደግሞ ከመጠን ያለፈ ቮልቴጅን ይቆጣጠራል ። የሁለቱም ዋነኛ አላማ ቻርጅ አይሲ እንዳይጎዳ ማድረግ ነዉ ። አንዳንድ ስልኮች ላይ ዳዮድ በካፓሲተር ሊተካ ይችላል ። ዳዮድም ሆነ ካፓሲተሩን ከፍተኛ የሆነ (ከመጠን ያለፈ) ቮልቴጅን ወደ ግራዉንድ ይልካሉ ። • ቻርጅ ኢንተርፌስን መለየት ፣ ይህም ቻርጅ የሚሰካበት የሚሰካበት ቦታ ላይ እናገኘዋለን ። • የትኛዉ ፖዘቲቭ እና የትኛዉ ኔጋቲቭ እንደሆነ ለመለየት መጀመሪያ የመልቲ ሜትራችንን አንድ እግር ከስልካችን ግራዉንድ ወይም የብሎን ማሰሪያ ቀዳዳ ጋር የሚገኘዉ ወርቃማ ከኢንተርፌሶቹ ጋረ እናገናኛለን ። ኮንቲኒቲ የሚሰጠዉ ኔጋቲቭ ሲሆን ቀሪዉ ፖዘቲቭ ነዉ ማለት ነዉ ። • አንዱን የመልቲ ሜትር እግር ፖዘቲቭ ላይ ይዘን ቀሪዉን እግር በምንጠረጥርበት የስልካችን ማንኛዉም ኢንዴክተር እና ካፓሲተር ያለበት ቦታ ላይ በመሞከር ኮንቲኒቲ ስናገኝ የቻርጅ ማድረጊያ ግሩፕ እንደሆነ እንረዳለን ። የምንጠረጥረዉ አብዛኛዉን ጊዜ የቻርጅ ማድረጊያ ክፍሎች ከቻርጅ ኢንተርፌስ አጠገብ ስለሆነ በዙሪያው ያሉተትን አካላት ለማለት ነዉ ። • የቻርጅ አይሲን ለመለየት R22 የሚል ፅሁፍ ያለበት ሬዚስተር እናገኛለን ። R22 የሚያገለግለዉ ከቻርጅ አይሲ የሚወጣዉን ከረንት ለመመጠን ነዉ ።ቻርጅ አይሲያችን በትክክል መስራት አለመስራቱን ለማረጋገጥ ስልኩ ላይ ቻርጅ እንሰካለን ። ባትሪዉን እንነቅለዋለን በፍጥነት ባትሪ ኮኔክተሩ ላይ ያለዉን የቮልት መጠን እናያለን ። ከ3.6 ቮልት እስከ 4.0 ቮልት የሚያነብ ከሆነ ቻርጅ አይሲያችን በትክክል ይሰራል ማለት ነዉ ። #ሼር እያረጋቹ አይደለም እስኪ ሼር እናርግ ይህንን ፖስት። #Shar #Like #Comment ያስፈልገናል

HiTech
1 636
ለሞባይል ጥገና የሚስፈንልጉን መሳሪያዎች • 1. መፍቻ 👉 ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል፡፡ • 2. መልቲ ሜትር 👉 ሬዚስታንስ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመንካት እና የሰርኪዩት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል፡፡ • 3. ቲነር 👉 ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡ • 4. ፔስት👉 አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ስአት ቦርዳችንና የሚነቀለዉ አይሲ በሙቀት እንዳይጎዳ ይጠቅማል፡፡ • 5. ብሎወር👉 ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ ይጠቅማል፡፡ • 6.ካዉያ👉 ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ ይጠቅማል፡፡ • 7. ሊድ👉 ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ እንደ ቀላጭ የምንጠቀምበት ነዉ፡፡ • 8. ጃምፐር ዋየር👉 ሁለት የተለያዩ የሰርኪዩት ክፍሎችን/የተላቀቁ ክፍሎችን/ ለማያያዝ የሚጠቅም ቀጭን ሽቦ ነዉ፡፡ • 9. ትዊዘር (ፒከር)👉 አይሲ ወይም ሌሎች የሞባይል ክፍሎች በብሎወር ስናሞቅ እንደ መቆናጠጫ የምንይዝበት ነዉ፡፡ • 10. ዲሲ ፓወር ስፕላይ👉 ከባትሪ የምናገኘውን 3.7 ቮልት የሚሆን ቮልቴጅ የሚሰጥ ክፍል ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስልኮች ኦፕን ይሁን ሾርት ወይም ስልኮች የሶፍትዌር ችግር እንዳላቸዉና እንደሌላቸዉና ሊያሳየን የሚችል በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ስፒከርን ወይም ሪንገርን ለመፈተሽ ይጠቅመናል፡፡ • 11. ኮምፒዩተር👉 ለሶፍትዌር ጥገና፣ ለሀርድዌር ላይብረሪ እና ሙዚቃ ለመጫን ይጠቅመናል፡፡ • 12. ፍላሽ ቦክስ👉 በሶፍትዌር ጥገና ስአት በሞባይልና በኮምፒውተር መሃል የሚገኝና ሁለቱን አካሎች የሚያግባባቸዉ መሳሪያ ነዉ፡፡ • 13. ቦርድ ፕሌት👉 የስልካችንን ቦርድ በምንበይድበት ጊዜ ወይም አይሲ በምንነቅልበት ጊዜ ቦርዱ እንዳይነቃነቅ የሚአደርግ መያዣ መሳሪያ ነዉ፡፡ • 14. ሶፍትዌር ኬብል👉 በሶፍትዌር ጥገና ሰአት ስልካችንን ከፍላሸር ቦክስ ጋር የሚያግባባ ነዉ፡፡ • 15. ቫይብሬተር👉 ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ወይም ስታክ ያደረገ ስልክ እንዲሰራ ቫይብሬተር ዉስጥ ተዘፍዝፎ፣ የተወሰነ ደቂቃ ይቆያል፡፡

HiTech
1 636
እንኳን ወደ #Safaricom ኢትዮጵያ አገልግሎት በሰላም መጡ ‼️ Safaricom ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጀምረውን አገልግሎት ለማስተዋወቅ እና የህዝብ ተደራሽነቱን ለማስፋት ያዘጋጀው #3ሺ ብር የሚያሸ
እንኳን ወደ #Safaricom ኢትዮጵያ አገልግሎት በሰላም መጡ ‼️ Safaricom ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጀምረውን አገልግሎት ለማስተዋወቅ እና የህዝብ ተደራሽነቱን ለማስፋት ያዘጋጀው #3ሺ ብር የሚያሸልም በጣም ቀላል ውድድር አዘጋጅቷል ። በሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ይህን ሊንክ ተጭነው ቡታችን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/EthioSafaricombot?start=r0844355282 ✅ የተሸላሚዎችን ዝርዝር ለማየት ቻናላችን ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/+JvNp94lLBGs0NjI0 ይህ የእርስዎ መጋበዣ መልዕክት ነው #SHARE ወይም #FORWARD በማድረግ ውድድሩን ይቀላቀሉ ።መልካም እድል 🎁 🌐 Safaricom Ethiopia™

HiTech
1 636
Bot join አድርጋቺሁ ሞክሩት ይከፍላል . . .

HiTech
1 636
የተለያዩ አይሲዎችን ለመለየት የሚጠቅም ዘዴ 1. ሲፒዩ :- ወርቃማ እግር አለዉ ። 2. ቻርጅ አይሲ:- R22 የሚል አነስተኛ ሬዚስተር አጠገቡ ይገኛል ። 3. ዩአይ አይሲ :- 20 እግር አለዉ እግሮቹም ወጣ ወጣ ያሉ ናቸዉ ። 4. ቪሲኦ :- አብዛኛዉን ጊዚ በቆርቆሮ የታሸገ ነዉ አልያም በወርቃማ መስመር ብቻዉን የታጠረ ነዉ ። ቪሲኦ የሚገኘዉ Rx ክፍል ዉስጥ ነዉ ። 5. ክሪስታል ኦሲሌተር :- ጠፍጣፋ ሬክታንግል መልክ ያለዉ ነዉ ። 6. ኔትወርክ አይሲ :- ከክሪስታል ኦሲሌተር አጠገብ ይገኛል ። ኔትወርክ አይሲ Rx ክፍል ዉስጥ ይገኛል ። 7. ፓወር አምፕሊፋየር :- አብዛኛዉን ጊዜ የመጀመሪያዉ (ከላይ የሚገኝ) አይሲ ነዉ ። 8. ኤፍ ኤም አይሲ(ሬዲዩ አይሲ):- አጠገቡ ባለቀለም ኢንዴክተር ይኖራል : ቀለሙም ደማቅ ወይም ደብዛዛ ሰማያዊ ነዉ ። 9. ብሉቱዝ አይሲ :- ሬክታንግል ቅርፅ ያለዉ ነጭ : አነስተኛና ጠፈር ያለ አካል ካጠገቡ ይገኛል ። 10. ፓወር አይሲ:- አጠገቡ ትንሽ እና ቀጭን አካል (አርቲስ) ሁሌም ይኖራል ። 11. ባካፕ ባትሪ :- የሰአት አይሲ የሚመስል ነዉ ። 12. ላይት አይሲ :- አጠገቡ ጥልቅ ሽቦ (ቡስተር ኮይል) ይኖራል ። 13. ሲም አይሲ :- ትንሽ : አንጸባራቂ : ብራማ ከለር ያለዉና ከሲም ማስቀመጫ አጠገብ ወይም ማስቀመጫ በስተጀርባ ይገኛል ። 14. ኪይ ፓድ አይሲ :- ከኪይ ፓድ እና ከኮኔክተር አጠገብ ወይም ከሲፒዩ አጠገብ ይገኛል ። 15. ካፓሲተር :- ቀለል ያለ ቡኒ ቀለም ያላቸዉ ናቸዉ ። 16. ኢንደክተር :- ጥቋቁር እና አብዛኛዉን ጌዜ ከካፓሲተሮች በመጠናቸዉ ተለቅ ብለዉ ይገኛሉ። 17. ሬዚስተር :- ጥቋቁር እና ትናንሽ ክፍሎች ናቸዉ። @cellphonetechnology