HiTech
前往频道在 Telegram
HiTech | Learn. Fix. Create. 📱💻🎨 Your Ethiopian tech hub! We teach: ✅ Smartphone Repair ✅ Laptop & Chip-Level Repair ✅ Graphics & Motion Design ✅ Coding & Web Development ✅ Tools, Tips & Tech Reviews Join the HiTech family — grow your skills & build
显示更多1 635
订阅者
+224 小时
+127 天
+2630 天
帖子存档
1 636
የላፕቶፕዎን (Laptop) ባትሪ የቆይታ ጊዜ የሚያራዝሙባቸው 9 ጠቃሚ መንገዶች
ዛሬ ይዤላቸው የቀረብኩት አብዛአኞቻቸን ችግር የሆነውን የላፕቶፕ ባትሪ የቆይታ ጊዜ አንዴት ማስተካከል እና ማሳደግ እንደምንችል ነው:: ሁላቸንም አንደምናውቀው በአሁኑ ጊዜ ላፕቶፖች አና ታብሌቶች (Tablets) የዴስክቶፕ (Desktop) ኮምፒውተርን ቦታ በመተካት ሥራችንን በቀልጣፋና በፈጣን ሁኔታ አንደንሰራ እያደረጉን ቢገኙም የባትሪያቸው ቶሎ ማለቅ ግን የሁላችንም ራስ ምታት እየሆነ ይገኛል::
አብዛኛዉን ጊዜ የዚህ አይነት ችግር የሚፈጠረው ባትሪያቸንን አንዴት መቆጠብ እና የጊዜ ቆይታውን መጨመር እምንችልባቸውን መንገዶች ባለማዎቅ አና ለባትሪያቸን በቂ ጥገና ባለማድረግ ነው::አንዳንድ ሰዎች የባትሪ ቶሎ ማለቅ ችግር ሲያጋጥማቸው ወዲያው ለመቀየር ይዎስናሉ ነገር ግን አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማድረግና ጠቃሚ መንገዶችን በመከተል ከ አላስፈላጊ ወጭ መዳን ይቻላል::
የሚከተሉትን 9 መንገዶች በመከተል የባትሪዎን የቆይታ ጊዜ ማሳደግ ይችላሉ
1. ለጊዜው እማንጠቀመባቸውን መገልገያዎችን(devices) በመንቀል አና መሰኪያዎችን(ports) ነፃ በማድረግ ነው::
- በዚህ ቀላል መንገድ የባትሪያችንን ጊዜ ቆይታ ማሳደግ አንችላለን:: ለጊዜው የማንጠቀመባቸውን መገልገያዎችን
ለመሳሌ:- ማውስ (mouse), ኪቦርድ (keyboard) የመሳሰሉትን በመንቀል የጊዜ ቆይታዉን ማሳደግ አንችላለን::
2. አላሰፈላጊ ፕሮግራሞችን (programs) አና ፕሮሰሶችን (processes) በመዝጋት
- አላሰፈላጊ ፕሮግራሞችን አና ፕሮሰሶችን በመዝጋት የባትሪያችንን ጊዜ ቆይታ ማሳደግ እንችላለን::ምክንያቱም አንዳንድ ፕሮሰሶች የፕሮሰሰራችንን ሰዓት በመጋራት አና በፕሮሰሰራችን ላይ ጫና በመፍጠር ፕሮሰሰራችን የላፕቶፓችን ባትሪ በከፍተኛ ሁኔታ አንዲጠቀም ያደርጉታል::
- አነዚህን አላሰፈላጊ ፕሮሰሶች (Processes) በ ታስክ-ማናጀር (Task-manager) Ctrl + alt + del በመጫን ታስክ-ማናጀርን መክፈት ይቻላል::
3. ኮምፒውተራችንን ባትሪ ሴቨር ሞድ (Battry-saver mode) ላይ በማድረግ
- የኮምፒውተራችን ሃይል ቆጣቢ ሞድ (Power saving mode) የላፕቶፓችንን (Laptop) ሀይል የመጠቀም አቅም ያስተካክለዋል::
4. የኮምፒተራችን ሴቲንግ (setting) በማስተካከል
- የተለያዩ መገልገያዎች (devices ) ስንጠቀም ለምሳሌ ማውስ (mouse ) እና ኪቦርድ ስንጠቀም የላፕቶፓችን ሴቲንግ ልናስተካክል ይገባናል::
- የኪቦርዳችን የጀርባ ብርሃን (back light) በጨለማ ውስጥ ስንሆን ብቻ በማብራት በላፕቶፓችን ባትሪ ከአላሰፈላጊ ብክነት መታደግ እንችላለን::
የላፕቶፓችን ስክሪን ድምቀት (screen brightness) በማስተካከል ቀን ላይ ከሆንን በመቀነስ::
5. በአንዴ ብዙ ኣስፈላጊ ስራዎችን የምንሰራበትን ግዜ በመቀነስ (Reducing multi-tasking)
- በአንዴብዙ ስራዎችን መስራት (multi-tasking )ማለት ብዙ ፕሮግራሞችን (application ) በኣንዴ እንዲሰሩ ማድረግ ነው ::
- ስለዚህ እነዚህን የመሳሰሉ አላስፈላጊ ፕሮገራሞችን በመቀነስ ባትሪያችንን መቆጠብ እንችላለን
6. ስታንድባይ (Stand by) ከማድረግ ይልቅ ሀይበርኔት (Hibernate) በማድረግ
- ኮምፒውራችንን ስታንድባይ (stand by) ላይ በማድረግ ባትሪያችን እንደሚቆጥብ የታወቀነው ግን ሙሉ በሙሉ ላፕቶፓችን ባትሪ እንዳይጠቀም ኣያደርገውም ::
- ሀይበርኔት (hibernate ) ግን ላፕቶፑ ባትሪ እንዳይጠቀም ስለሚያደርገው በዚህ መንገድ ባትሪያችንን መቆጠብ እንችላለን::
7. የላፐቶፓችን ራም (RAM) በመጨመር
- ራም (RAM) ማለት ጊዜያዊ ሜሞሪ (temporary storage) ሲሆን በስራ ላይ ያሉ ፕሮግራሞች እሚቀመጡበት ቦታ ነው::
- ላፕቶፓችን በጣም ትንሽ ስራም ካለው አንዳንድ ትልቅ ራም ከሚፈልጉ ፕሮግራሞች የተለያዩ የላፕቶፓችንን የሜሞሪ ክፍሎች በመጠቀም ይጀምራሉ ይህ ሁኔታ ደግሞ ኮምፒተራችንን በማጨናነቅ ብዙ ሃይል እንዲጠቀም የደርገዋል::
ስለዚህ ራም በመጨመር ባትሪያችንን መቆጠብ እንችላለን::
8. የላፕቶፕዎን የባትሪ ማገናኛዎች (contacts) ንፁህ በማድረግ
- የላፕቶፓችንን የባትሪ ማገናኛዎች በሁለት ወይም በሶሰት ወር አንድ ጊዜ ማፅዳት ያሰፈልጋል::
- ላፕቶፓችን የባትሪ ማገናኛዎች ንፁህ ማድረግ ባትሪያችን ቻርጅ (charge) በሚደረግበት ግዜ ቶሎ ቻርጅ ለማድረግ ስለሚያስችለን እና የሃይል ዝውውሩን በማስተካከል የባትሪያችንን ጤንነት ለመጠበቅ ያስችለናል::
9.ባትሪያችንን ከመጠን በላይ ቻርጅ ከማድረግበ መቆጠብ (preventing from over charging )
- ባትሪያችን ከሞላ በኃላ ቻርጀራችንን (chargers) መንቀላችንን መርሳት የለብንም::
- ባትሪያችንን ከመጠን በላይ ቻርጅ ማድረግ ባትሪያችንን እና የተለያዩ የላፕቶፓችንን ክፍሎችል ሊያቃጥል ይችላል:: ስለዚህ ለባትሪያችን ጤንነት ከእንደዚህ ዓይነት ተግባራት ልንቆጠብ ይገባናል፡፡
እባክዎን ይሄ ፅሁፍ ጠቃሚሁኖ ካገኙት “share” በማድረግ ሌሎች ወዳጆችዎ ያዳርሱ::
==========================
የወደዳችሁት ሁሉ ሼር እያደረጋችሁ ለወዳጅዎ #ያጋሩ እኛንም ያበረታቱን !
@cellphonetechnology
1 636
#Repost
✍About Google
ጉግል ስለእርስዎ ብዙ ያውቃል፤እርስዎስ ስለ ጉግል ምን ያውቃሉ?
▁▁▂▃▄▅▆▅▄▃▂▁▁
✠ጉግል 20ኛ ዓመት የልደቱን በዓሉን ሊያከብር ሽር ጉድ እያለ ነው። ይህን ተንነተርሰን ስለ ጉግል ምናልባት የማያውቋቸው ነጥቦች ይዘን ብቅ ብለናል።
✠ከጉግል በፊት ሕይወት ምን ትመስል ነበር? አንድ መረጃ በፍጥነት ሲፈልጉ ምን ያደርጉ እንደነበር ያስታውሱታል?
ምንም ይፈልጉ ምን፤ የአንድን ቃል ትርጓሜ እና አፃፃፍም ይሁን የቦታ ጥቆማ፤ ብቻ የሆነ ነገር ሲፈልጉ ወደ ጉግል መሮጥ የተለመደ ሆኗል።
✠ 'ዕድሜ ይስጠውና' ጉግል ፊት ነስቶን አያውቅም፤ 'ጎግለው' እንዲል የሃገሬ ሰው።
✠በየሰከንዱ ይላል ፎርብስ የተሰኘው መፅሄት መረጃ. . .በየሰከንዱ 40 ሺህ ሰዎች 'ይጎግላሉ'፤ በቀን 3.5 ቢሊዮን እንደማለት ነው።
ጉግል ሁሉ ነገር ሆኗል፤ ማስታወቂያ በሉት፣ የቢዝነስ ዕቅድ እንዲሁም ግላዊ መረጃ መሰብሰቢያ ነው።
✠እንግዲህ እውነታውን ልናፈራርጠውም አይደል፤ እናማ ስለጉግል አንድ ሚስጢር እንንገርዎት። መረጃ ፍለጋ ወደ ጉግል በሮጡ ቁጥር ጉግል ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ይሰበስባል።
⌘ «ግን ምን ያህል መረጃ?» አሉን?፤ መልካም! እነሆ የጠየቁንን ጨምሮ ስለጉግል ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች።
❏① ስያሜው
ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።
በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።
እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።
❏② የጀርባ ማሻ
የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።
ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ።
ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።
❏③ የተንጋደደ
ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።
እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።
ውጤቱ አዩት?
❏④ ፍየሎች🐐🐐
ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው።
አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ።
ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።
❏⑤ እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'
ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።
❏⑥ ዱድል
ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።
ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።
አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።
❏⑦ ለሌሎች ያመለጠ ዕድል
በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።
ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።
አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።
❏⑦ መሪ ቃላት
'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።
'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።
❏⑧ ምግብማ ግድ ነው
ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።
❏⑨ የጉግል ባልንጀራ
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።
ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።
አጀብ ነው!
✅Source:- BBC አማርኛ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🗣➹share &Join Us
👇🏾👇🏾👇🏾
@cellphonetechnology
1 636
ኮምፒውተር Keyboard ላይ ከላፍ ያሉትን(F1-F12) ጥቅምማቸውን ያውቁ ኖሯል?
➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡
➢ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::
❖ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል ....
☛ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡
❒የ F1 ጥቅሞች
► ከ”Windows ቁልፍ (button) ጋር በጋራ ስንነካው help menuን ያመጣልናል፡፡
► Excel እና Word በምንጠቀምበት ወቅት ከ Control ጋር በጋራ ስንነካው Hides or displays ribbon menu ያደርግልናል፡፡
❒የ F2 ጥቅሞች
◕ Alt + Ctrl + F2 - opens Document Library in Microsoft Office
◕ Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer
❒የ F3 ጥቅሞች
► Opens search feature in Windows Explorer
► Shift + F3 - lets you change from lowercase to uppercase to all caps in Word
► Opens find feature in Firefox and Chrome
❒የ F4 ጥቅሞች
◕ Alt + F4 closes window
◕ Places the cursor in the address bar in Explorer
❒የ F5 ጥቅሞች
► Starts slideshow in Power Point
► Refreshes Internet browser pages
► Opens Find and Replace in Microsoft Office
❒የ F6 ጥቅሞች
◕ Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word
◕ Ctrl + F6 lets you easily switch between Word documents
❒የ F7 ጥቅሞች
► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word
► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word
❒የ F8 ጥቅሞች
◕ In Excel, enables extend mode for arrow keys
◕ Enables safe mode in Windows
❒የ F9 ጥቅሞች
► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word
► Updates fields in Word
❒የ F10 ጥቅሞች
◕ Opens menu bar
◕ Ctrl + F10 maximizes window in Word
◕ Shift + F10 does the same thing as a right click
❒የ F11 ጥቅሞች
► Exits and enter full screen mode in browsers
► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel
❒የ F12 ጥቅሞች
◕ Opens Save As in Word
◕ Shift + F12 saves Word document
◕ Ctrl + F12 opens Word document
@cellphonetechnology
1 636
📲የሞባይል ኢንተርኔትን በላፕቶፕ ላይ ለመጠቀም
(በኬብልና ያለኬብል ለማገናኘት)
ክቡራን የፔጃችን ታዳሚዎች… እንዴት አርገን ሞባይላችንን ከኮምፒውተር ጋር በማገናኘትና የሞባይላችንን የኢንተርኔት ዳታ ለኮምፒውተራችን መጠቀም እንደምንችል እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡
❶. የሚከተሉትን steps ማዛነፍ አይፈቀድም
➢step ①
የሞባይሎን ኢንተርኔት ዳታ ያብሩ
➢step ②
ሞባይሎን ከኮምፒተሮ ጋር በUSB cable ያገናኙ
➢step ③
የሞባይሎን setting ይክፈቱ
➢step ④
more በሚለው ይግቡና ከሚመጣሎ አማራጭ tethering and portable hotspotን ይክፈቱና USB tethering የሚለውን on ያድርጉ
➢step ⑤
ወደ ኮምፒውተሮ በመመለስ የፈለጉትን browser (chrome, Firefox or opera) በመጠቀም በኮምፒተሮ ኢንተርኔት ማግኘት ይችላሉ
-------
❷. other method
Internet sharing የሚል ሴቲንግ ያላቸው ሞባይሎች ያለ ኬብል መጠቀም ይችላሉ፡፡
•► መጀመሪያ ዳታ ማብራት
•►ከዚያ ኢንተርኔት ሼሪንግ የሚለውን ኦን ማድረግ፤ ከዚያ ሄደው ላፕሮፕ ላይ ልክ እንደ ዋይ ፋይ የሞባይሎን ዳታ ያገኙታል፡፡
•► ኢንተርኔት ሼሪንግ የሚለው ሴቲንግ ውስጥ የተቀመጠውን የፓስዋርድ ቁጥር ላፕቶፑ ላይ ማስገባት
•► ከዚያ መጠቀም መጀመር
⚠️ነገር ግን በሞባይል ከምታገኙት ኢንተርኔት ይህ ዋጋው ከፍ ይላል፡፡ የሞባይሎን ካርድ ቶሎ ነው የሚበላው፡፡
⌘ሌላው ማወቅ ያለብዎ ሞባይሎን ነቅለው መልሰው ከኮምፒውተሮ ጋር ሲያገናኙ ከላይ የተጠቀሱትን steps እንደአዲስ መከተል ግድ ይላል በርግጥ ይህንን አጠቃቀም ምታውቁ እንደምትኖሩ አንጠራጠርም፡፡
✅ ሼር መደረግ አለበት ሌሎች መንገዶችን በቀጣይ ዝግጅታችን ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🗣➹share &Join Us
👇🏾👇🏾👇🏾
☄@cellphonetechnology
1 636
✴️ የዛሬዋ ፕሮግራማችን እጥር ምጥን ያለች ናት አዲስ Bot እናስተዋውቃችኋለን የተከታታይ ፊልም አፍቃሪዎች በቀላሉ በቴሌግራም ከ206 ፊልሞችን በላይ የያዝ ቦት ሲሁን የምፈልጉተን ከፍታችሁ መኮምኮም ነው ከናንተ የሚጠበቀው Wi-Fi ወይም አሪፍ ዳታ ነው አጠቃቀሙ ካልገባችሁ inbox እንደተለመደው ጠይቁን ግን እጅግ በጣም ብዙ ጥያቄዎች ሰላሉ ሁላችሁንም በየተራ ነው የምንመልሰው።
🍭የዛሬው Bot ስም
👉 @TvSeriesRoBot 👈
ሲሆን በምፈልጉት ፊልም ስር የምፈልጉትን Season ከፈለጋችሁት Episode ጋር ይዞላችኋል።
🍭ከፈለጋችሁ ደግሞ👉@TvSeriesHub እዚህ channel ላይ ብዙ ፊልሞች አሉላችሁ።
👏👏 እኔ ተመችቶኛል 👏👏
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔘 @cellphonetechnology
1 636
🇪🇹 ውድ የሆናችሁ የዚህ ቻናል ተከታታዮች ትናንት ቃል በገባንላችሁ መሰረት የፌስቡክ አካውንቶትን ሌላ ሰው
ሲጠቀም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ሞባይሎት ላይ እንዲደርሶት ማድረግ የሚችሉበትን ቀለል ያለ ዘዴ እነሆ ብለናል።
✍
1.የፌስ ቡክ አካውንቶት ውስጥ በተለመደው ሁኔታ ከገቡ በኋላ ሴቲንግ የሚለውን አማራጭ ይጫናሉ ሴቲንግ የሚለው ቦታ እንደ ምትጠቀሙት ብሮዘራችሁ ሰለሚለያይ ፈልጉት
2. በመቀጠልም ከሚመጡት አማራጮች ሴኪዩሪቲ
ሴቲንግ የሚለውን አማራጭ እንመርጣለን ከዚህ በኋላ ሎግ ኢን አለርት የሚለውን አማራጭ እንጫናለን።
3. ከዚህ በኋላም ከተቀመጡት ሶስት አማራጮች ውስጥ ቴክስት ሜሴጅ የሚለው አማራጭን በመጫን የሞባይል ቁጥሮን ያስገባሉ፡፡
4. በመቀጠልም ሴቭ የሚለውን ቁልፍ ሲጫኑ ወደ ሞባይሎ የማረጋገጫ ኮድ ይልክሎታል ይህ ኮድ ሞባይሉ የእርሶ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚላክ ሲሆን ያንን ኮድ ኮምፒተሩ ላይ በተቀመጠው ክፍት ቦታ በማስገባት ሴቭ ማለት በመጨረሻም ቁጥሮ የገባበትን ምርጫ በመጫን ሴቭ ቼንጅስ የሚለውን ስትጫኑ አክቲቭ ይሆናል፡፡ ከዛም በኋላ የትኛውም ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ላይ ፌስ ቡኮት ላይ ሲገቡ መግባቶን በአጭር
ጽሁፍ መልእክት ሞባይሎ ላይ ይደርሶታል ማለት ነው፡፡
✍አስተውሉ⚠️ ይሄን አክቲቬት አድርገው በስልኮ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከተላኮለት ያኔ የፌስቡክ አካውንቶን ሌላ ሰው እየተጠቀመ ነው ማለት ነው ያኔ ቶሎ ብለው የአካውንቶን ሚስጥር ቁጥሮን መቀየር አሎበት።
➖➖➖➖➖➖➖
@cellphonetechnology
1 636
🇪🇹ለComputer ተጠቃሚዎች የፈለጉትን windows እና office activate ያደርግሎታል።
®Windows-10-8-7
®Office-2018-2013-activator
🕹Ratiborus KMS Tools
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@cellphonetechnology
1 636
🔐 ሰላም የዚህ ቻናል ተከታታዮች ዛሬ ብዙ ሰዎች የሚቸገሩበትን ቀለል ያለ ዘዴ እንዴት አድርገን ክፍያ የሚጠይቁ App በነፃ ማውረድ እንደምንችል Method one ላሳያችሁ 100% ይሰራል ሌሎቹን ዘዴዎ በሌላ ጊዜ አቀርብላችኋለው።
✍
How to download paid apps from playstore
Requirements
1. GetApk Market
2. Your Device
3. A functional playstore
Procedure
1. Download getapk market.
2. Install it on your device.
3. Open PlayStore and navigate to the Paid Apps Section
4. Select an app.
5. Scroll down to the Share section and select share with GetApk
6. Continue to open with GetApk
7. Upon availability confirmation, select the get apk prompt. Next select the server with the latest version of the app.
8. Select your preferred option of either continuing the process through the embedded browser or open it through your custom browser.
9. Download the app.
Download link for the getapk app http://www.apkmarket.org/app/getapk-market/
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔐Join us; @cellphonetechnology
1 636
♐️የ KEYPAD ስልኮች Boot key
ብዙ ጊዜ የkeypad ስልኮችን የሶፍትዌር ስራዎች ስንሰራ ቡትኪያቸዉን ማወቅ ይኖርብናል። driver install ሆኖም bootkeyውን ካላወቅን ስልኩ ከኮምፒዉተር ጋር ኮኔክት አይሆንም ማለት ነው።
✴️ MTK ለሆኑ ለምሳሌ tECNO,ITEL,PLUZZ...እና የመሳሰሉት
💮 ብዙዎቹ mTK ስልኮች ያለ ቡት ኪይ ይገናኛሉ ነገር ግን አንዳንዶቹ ከታች በተዘረዘሩት ካልሆነ አይሰራልንም።
👉🏿Contact button
👉🏿Menu button
👉🏿Calling button
ተጭነን ኬብሉን እንሰካዋለን።
✴️ COOLSAND/RDA
ለምሳሌ ፦ KG-TEL, ROCKTEL, I-PLUS etc
👉🏿0 button
👉🏿 0 button + menu button
✴️ SPREADTRUM (SPD)
Itel, Samsung feature phone, Alcatel, Viettel Halotel, Zen, Walton
and China Nokia phone
👉🏿menu button
👉🏿 calling + menu button
😈yd Ram:
✴️ ለSPD Android ሰልኮች ደግሞ V+/V- በመጠቀም ከኮምፒውተር ጋር connect ማድረግ እንችላለን ማለት ነዉ
1 636
💥ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ
🌟This Application Stopped Working‼️
🌟Crashing‼️
🌟Won’t open‼️
🌟Won’t respond‼️
🌟Isn’t working properly‼️
🔆እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ⬇️
1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍
⚠️ስልካችሁን?? #Restart አድርጉት።
⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።
⚠️_Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።
2⃣.*Update Google Play Services *
⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።
3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ *Setting* ውስጥ ገብታችሁ #Forced\Stop አድርጉት።
⚠️System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።
4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።
⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.
5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ?? ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።
⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️ እነሱ ስልኮች📲 ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው።😁
⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
የወደዳችሁት ሁሉ ሼር እያደረጋችሁ ለወዳጅዎ #ያጋሩ እኛንም ያበረታቱን !
1 636
#Graphics_cards
✠✠✠✠✠✠✠✠✠✠✠
✔Graphics/Display/Video Card ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/
አሁን አሁን የምንሸምታቸውን ላፕቶፖች Graphics card አለው ወይስ የለውም ብሎ ማጣራት የተለመደ ሆኗል። በነገራችን ላይ መጠኑ እና ጠቀሜታው ይለያይ እንጂ ኮምፒውተር የተባለ ነገር ሁሉ በኛ አጠራር ግራፊክስ ካርድ አለው።
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የሒሳብ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።
⇒በተለይም አዳዲስ ጌሞች እና ለ Rendering የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች ለመጠቀም( Photo Shop , Revit...) በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተለይ ለ Architecture ተማሪዎች ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። በአሁን ጊዜ በስፋት የሚታወቁት #Nividia እና #AMD ናቸው።
⇒ሁለት አይነት ካርዶች ሲኖሩ የመጀመርያዎቹ ከ mother board ጋር ተጣብቆ / integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ intel በስፋት ይታወቅበታል። ሁለተኛው ደግሞ ለብቻ የሚሸጡ dedicated ናቸው።
እኛ ሀገር በስፋት ከ ላፕቶፖች ጋር integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ መጨመርም ሆነ መቀየር የማንችላቸው ናቸው።
➲ከ Nividia እና ከ AMD የትኛው ይሻላል?፨፨
AMD( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል። በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ Radeon Brand የሚወጣ ነው። Nividia ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም ግራፊክስ ካርዶችን ማምረት ነው። በ Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።
➲ኮምፒዩተራችን Graphics card እንዳለው እና እንደሌለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?፨
⇒ የ window 10 ተጠቃሚ ከሆናቹ Task Manager ላይ ገብታቹ performance ላይ side bar ላይ ያለውን GPU በመጫን ማየት የምትችሉ ሲሆን
✔ የ window 7 ተጠቃሚዎች ደግሞ Run ( window key + R ) ላይ dxdiag ብላቹ ከጻፋቹ በኋላ በሚመጣላቹ window ላይ display በመጫን ማግኘት ትችላላቹ!
✔ብዙ ጊዜ ካልተላጠ ደግሞ keyboard አከባቢ ተለጥፎ ይገኛል።
!!ማሳሰቢያ!!
❖ Driver ያልተጫነበት ኮምፒዩተር በጣም ቀርፋፋ እና graphics ካርዱን ማግኘት አይችልም!
❖አንዳንድ ላፕቶፖች ደግሞ ለመሰረታዊ አግልግሎት የሚሆኑ intel graphics እና ከዛ ለበለጡ አገልግሎቶች የሚሆኑ AMD አልያም Nividia geforce graphics ካርዶችን አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል።
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#Share with your friend
@cellphonetechnology
🌐Read More👇
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Graphics_processing_unit
1 636
✨✨✨✨ መፍትሄ 1 ✨✨✨✨
💥 PART ONE💥
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
✍ የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
🔸Network ሰጪ ድርጅቶች በመላው አለም ላይ ይገኛሉ። በሀገራችንም ethio telecom ይገኛል። በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከ አንድ በላይ network አቅራቢ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በመንግስት ስር ሳይሆን በግል ተቋማት ስር ስለሆኑ ነው።ለዚህም ጎሮቤታችን Kenya ጥሩ ማሳያ ናት። ከአንድ በላይ የመኖሩ ጥቅም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያገኛል ድርጅቶቹም የተሻለ ነገር ለማቅረብ ፉክክር ዉስጥ ይገባሉ። አንድ አንድ network ሰጪ ድርጅቶች ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና አላቸው።
🔘ለምሳሌ T-mobile, verizon, orange, vodafone.....
እነዚህ ድርጅቶች ከሚፎካክሩቸው መንገዶች አንዱ ደንበኞችን ለመሳብ ሲሉ የስልክ ቀፎዎችን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ። ይህን የሚያደርጉት ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዛቸዉ ቁጥር ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ የስልክ ቀፎዎች ከተገዙበት የnetwork ሰጪ ተቋማት ውጪ ያሉ sim cardoችን አይቀበሉም ይህም ምክንያቱ በ security code ስለሚቆለፉ ነው። እንደዚህ አይነት ስልኮች ሀገር ስለቀየሩ ሳይሆን እንቢ የሚሉት ከተገዙበት የ network ሰጪ ድርጅት ዉጪ ባሉ network ሰጪ ድርጅቶች sim card ስለማይሰሩ ነው።
🔹የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ።
Sim not valid, wrong sim,unknown sim, phone restricted, contact service provider.....
🔘ከ network ሰጪ ድርጅቶች የተገዛ ስልክ ለመክፈት ሁለት መንገድ አለ።
✅1. Computer , flasher box, እና flasher file በመጠቀም መክፈት ይቻላል።
▪️ይህ ዘዴ አሁን ላይ ethio telecome የሚዘጋቸውን ስልኮችንም ይመለከታል ነገር ግን በዚህ Method ለመክፈት Computer, flasher box እና flasher file ያስፈልገናል።
🔺ስለ Computer ማብራራት አያስፈገኝም ነገር ግን በዚህ Method ትንሽ አሸጋሪ የሚሆነው Universal flasher box ማግኘት ነው ይሄ box የተለያዩ ጥቅሞች ሲኖሩት ከዚህም ውስጥ በስልኩ ሞዴል የራሱን flasher file ከ Google ላይ በማወረድ ከስልኮቻችን ጋር በማገናኘት የትኛውንም ስልክ ማስተካከል እንችላለን ከ hardware ውጪ ምንም አይነት ችግሮችን እንድናስተካክል ያስችለናል።
🔺ይህ universal flasher Box orginale ስልኮችን IMEI create በማድረግ አሁን ላይ ላለው ethio telecome ለሚዘጋቸው ስልኮች ፍቱን መድሃኒት ሲሆን የ flasher box ዋጋ በ Ethiopia 4326birr አከባቢ ሲሆን የተወሰኑ ሞባይል ቤቶች በ addis abeba እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
▫️ለምሳሌ ለመጠቆም ያህል መርካቶ ይርጋ ሃይሌ building ላይ በኛ በኩልም ይህን flasher box ማግኘት ይችላሉ።
✅ 2. ለ ድርጅቱ መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም ማስከፈት ሲሆን:-
▪️ለምሳሌ iphone በ icloud የተዘጉ ስልኮችን መጥቀስ ይቻላል እንደዚህ አይነት ስልኮች የ e-commerce እንዲሁም credit card ይጠይቃሉ። ይሄ አገልግሎት ደግሞ እኛ ሀገር ስለሌለ ያለው አማራጭ ውጭ ሀገር በምናቀው ሰው ማስከፈት ነው። ይህ ማለት ድህረ ገፁ ላይ ግብተን የስልኩን ሞዴል ስናስገባ ክፍያ ይጠይቀናል ክፍያውም የሚከናወነው በ ማስተር ካርድ ስለሆነ ክፍያውን ውጪ ሃገር ማስተር ካርድ ባለው ሰው ከባላንሱ ላይ እንዲፈፅምልን በማድረግ ክፍያው ከተፈጸመላቸው ድርጅቱ ኮዱን በሚያስገባው Email አድሬስ ስለሚልክልን ወድያውኑ መክፈት ይቻላል።
⚠️ በ icloud የተዘጉ ስልኮች በማስተር ካርድ በ አሁን ጊዜ የሚያስከፈለው 104$ ዶላር ነው ለዚህም ነው በአዲስ አበባ በተለያዩ የ ሞባይል ቤቶች በተለይ መርካቶ ላይ ከ200$ ዶላር በላይ የሚጠይቁት ጥቅማቸውን በማሰብ ማለት ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ውጪ ሃገር ላይ የ ማስተር ካርድ ቪዛ ኮዱን አስገብቶ ክፍያውን ሊፈፅምላችሁ እና በ Email የሚላክለትን Code ሊልክላችሁ የሚችል ወዳጅ ከሌላችሁ ምንም አይነት አማራጭ የላችሁም ከ200$ ዶላር በላይ ከፍለን ከማስከፈት ውጪ ስልኩን መጠቀም አንችልም።
🔐 በ i Cloud ያልተዘጉ ስልኮችን እና እንዲሁም የተወሰኑ icloud locked የሆኑ iphone ስልኮችን DNS method በመጠቀም መክፈት የምንችልበትን ዘዴ ሰፋ ባለ Program ከዚህ በፊት አቅርበንላችኋል ወደኋላ በመመለስ Check ማድረግ ትችላላችሁ።
✨✨✨✨ መፍትሄ 2✨✨✨✨
💥 PART two 💥
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
♻️ ይሄ መንገድ ስላካችንን በመጀመሪያ ሩት ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለ ሩት ከዚህ በፊት Post ላይ ማብራሪያ ስለሰጠን ከዛ ላይ ገብተው ያንብቡ። ሩት የሆነ ቀፎ ካለን እንደሚከተለው በማድረግ imei መቀየር እንችላለን ።
🔸ይህን ዘዴ ለመጠቀም ሁለት ፕሮግራሞች እንጠቀማለን የመጀመሪያው:-
▫️1.Mobileuncle MTK IMEI Write Tool የሚለውን ሶፍትዌር ኮምፒውተራችን ላይ ዳውንሎድ እናደርጋለን ከዛ በዚፕ ያለውን ፕሮግራም ስንከፍት የሚያመጣልን ዊንዶው ላይ Y ብልን ፅፈን enter እንጫናለን ከዛ የሞባይላችንን imei እንፅፍና
create IMEI .BAK ብለን አዲስ የተፈጠረውን imei.bak ፋይል ወደ ሜሞሪ ካርድ እንልከዋለን።
ሜሞሪ ካርዱን ቀፎ ውስጥ ካስገባን በኋላ...
▫️2.ይህን አፕሊኬሽን ቀፏችን ላይ እንጭናለን mobileuncle_MTK_toolv2.9.9.apk
▫️3.ከዛ የጫነውን አፕሊኬሽን ስንከፍት ሩት ኣክሰስ ጥያቄ ሲጠይቅ grant ብለን ፍቃድ እንሰጠዋለን።
ከዛ IMEI backup and restore የሚለውን ከፍተን ,restore IMEI.bak. ስንል ቅድም ሜሞሪ ላይ ያስቀመጥነውን ፋይል ወደ ቀፏችን ይፅፍልናል።
ሲጨርስ ቀፏችንን Restart አድርገን መደወያው ላይ *#06# አስገብተን በትክክል መፃፉን እናረጋግጣለን።
⚠️ ነገር ግን ሚሞሪ የማይወስዱ ስልኮች እና የተወሰኑ ሞባይሎች ለምሳሌ iphone...etc በmobile Uncle tools ImEI backup restore የሚለው not supported ካላችሁ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርንው በ method one የሚከፈቱ ስለሆኑ የግድ Flasher box መግዛት ይጠበቅባችኋል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📢: @cellphonetechnology
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬
1 636
✳️ Laptop ስንገዛ #corei3፣ #corei5 #corei7፣#corei9 ሲባል ምን ማለት ናቸው?
እነዚህ ነገሮች ስለ ላፕቶፑ ምን ይነግሩናል?
ኮምፒውተር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች መካከል #CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ #አእምሮ ማለት ነው።
ይህ #CPU ወይም #processor የተለያዩ ክንዋኔዎችን(Tasks) ተራ በተራ ማከናወን የሚያስችል የኮምፒውተሩ ዋና ክፍል ነው።
በሌላ አነጋገር #CPU ወይም #processor ላፕቶፓችን በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን በከፍተኛ ፍጥነት እንዲሰራ የሚያስችለው የላፕቶፑ ዋና ክፍል ነው።
ታስታውሱ እንደሆነ የመጀመሪያዎቹ ኮምፒውተሮች በአንድ ግዜ አንድ ሰራ ብቻ ነበር መስራት የሚችሉት።ለምሳሌ #Word ከፍታችሁ እየሰራችሁ ከሆነ ጎን ለጎን excel ወይም ሌላ ሶፍትዌር ከፍታችሁ መስራት አትችሉም ነበር።
እዚህ ጋር #Core የሚለው ቃል ይመጣል ።#Core ማት #አንድ ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።#CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ ትልቅ አእምሮ ብትሉት፤ #Core ማለት ትልቁ አእምሮ ውስጥ ያለ #አንድ_ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።
እንደምታውቁት የዘንድሮ ዘመናዊ #ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎች በከፍተኛ ፍጥነት ማከናወን ይችላሉ ።ለምሳሌ #Word ላይ እየሰራን ጎንለጎን #Excel ላይም ልንሰራ እንችላለን፤እንዲሁም ዩቲዩብ ከፍተን ልናይ እንችላለን።....ባጭሩ ብዙ ስራዎችን በአንድ ግዜ ማከናወን ይችላሉ ።
ታድያ #አንድ_core ሜለት #አንድ_አእምሮ ነው ካልን እና #አንድ_አእምሮ ደሞ በአንድ ግዜ አንድ ስራ ብቻ ከሆነ የሚያከናውነው፤የዘመኑ ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንዴት ቻሉ?
አሁን #corei3፣ #corei5 #corei7፣#corei9 የተባሉት ነገሮች ይመጣሉ።
▫️ Corei3 ማለት 3 #processors ወይም 3 አእምሮች ማለት ነው።
▫️ Corei5 ማለት 5 #processors ወይም 5 አእምሮች ማለት ነው።
▫️Corei7 ማለት 7 #processors ወይም 7 አእምሮች ማለት ነው።
▫️ Corei9 ማለት 9 #processors ወይም 9 አእምሮች ማለት ነው።
የ #core ቁጥር እያደገ ሲመጣ ላፕቶፑ በአንድ ግዜ የሚያከናውናቸው ሰራዎች ከፍ እያሉ ይሄዳል ማለት።ፍጥነቱን ሳይቀንስ።እንደውም በከፍተኛ ፍጥነት።
በሌላ አነጋገር የ4ኛ ክፍል ተማሪ አእምሮ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪ አእምሮ አንድ ነው? አይደለም።
#core ማለት ይህ ነው።
@cellphonetechnology
1 636
#Repost
◼️Android ምንድን ነው?🙄🤔
◽️Android Open #Source የሆነ #Operating #System ሲሆን በብዛት ለስማርት ስልኮች ያገለግላል!
◽️ጉግል በ 2003 #አንድሮድን ያገኘ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች በጣም ታዋቂው #Operating #System ሲስተም ሊሆን ችሏል!
▪️Android ስራው ምንድን ነው?
◽️አንድሮድ #Operating #System ሲስተም ስለሆነ ዓላማው ተጠቃሚውን እና መሣሪያውን ማገናኘት ወይም ማግባባት ነው!
▫️ለምሳሌ : አንድ ተጠቃሚ #Text መላክ በሚፈልግበት ጊዜ አንድሮይድ ለተጠቃሚው የመፃፊያ #Keyboard ይሰጣል! ፅፎ ሲጨርስ ደግሞ ተጠቃሚው መላኪያውን በሚነካበት ጊዜ #Android መልእክቱ እንዲልክ ስልኩን ይመራዋል!
◽️Google በየአመቱ ለ Android System #Update ይለቃል! ምንም እንኳን Google ለ #Android እድገት ትልቅ ሚና ቢጫወትም ጉግል የ #Android #Operating ሲስተምን ለሞባይል አምራቾች በነፃ ይሰጣል!
◽️Electric ፣ Samsung ፣ LG ፣ Huawei ፣ Lenevo እና Sony አንድሮይድን በሚያመርቷቸው ስልኮች ላይ ከሚጭኑ አምራቾች ጥቂቶቹ ናቸው! በአሁን ሰአት Android Operating System በአንድ ቢሊዮን ሞባይሎች ላይ ተጭኖ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል!
◽️ብዙ ሰዎች የሚያነሱት አንድ የተለመደ ጥያቄ Android ለምን በተለያዩ ስልኮች ላይ የተለያየ መልክ ይይዛል? የሚል ነው! መልሱም ብዙ የ #Android ስሪቶች አሉ ምክንያቱም #AndroidOpenSource #ሶፍትዌር ስለሆነ የሞባይል አምራቾች በሶፍትዌሩ ላይ የሚፈልጓቸውን ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ!
🔵 አንድሮይድ ስማርት ስልካችንን እንዴት ማሻሻል /update/ ማድረግ ይቻላል?
በስማርት ስልኮች ኦፕሬቲንግ ሲስተም ገበያ ውስጥ አንድሮይድ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባለቤት የሆነው ጎግል፥ በየጊዜው በአንድሮይድ ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ያደርጋል።
በዚሁ ጊዜም የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን ማሻሻል /update/ ማድረግ ይጠበቅብናል።
➚አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን በየጊዜው ለምን ማሻሻል ያስፈልጋል…?
↬የስልካችን የመስራት አቅም እንዲጨምር
↬የስልካችን እድሜምን ለማርዘም
↬አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለመጠቀም
↬የሰልካችንን ደህንነት ለመጠበውቅ
↬ስልካችንን ከተለያዩ የቫይረስ ጥቃት ለመከላከል
↬የስልካችን ባትሪ የቆይታ እንድሜን ለማርዘም
➠አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለማሻሻል /update/ ለማድረግ መከተል ያለብን ቅደም ተከተል..
1. የአንድሮይድ ስልካችን መተግበሪያ ውስጥ በመግባት ሴቲንግስ /Settings/ መክፈት
2. ከሚመጡልን ዝርዝር ውስጥ “About phone” ወይም ሌላ ተመሳሳይ አማራጭ መክፈት
3. ከዛም “System Updates” ወይም “Software Update” የሚል አማራጭ የሚመጣልን ሲሆን፥ እዛ ውስጥ በመግባት ማሻሻል እንችላለን።
4. “System Updates” በምንከፍትበት ጊዜ በርከት ያሉ አማራጮች የሚመጡ ከሆነ “Check for updates now”፣ “Software update check” ወይም ሌሎች ተመሳሳይ አማራጮች ውስጥ በመግባት የስማርት ስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማሻሻል /update/ ማድረግ እንችላላን።
ማስጠንቀቂያ፦
❗️በዳታ ብዙ ብር ሊቆርጥብቆት ስለሚችል ይጠንቀቁ በWiFi Update ቢያደርጉት ይመረጣል።
❗️በቅድሚያ ስልክዎትን በበቂ ሁኔታ ቻርጅ ያድርጉ Update እያደረገ ባለበት ሁኔታ ቻርጅ ቢዘጋ ስልኮ አደጋ ውጥ ሊገባ ይችላል።
share በማድረግ ሌሎችንም ያሳውቁ!!
1 636
✳️ የዘመናዊ ኮምፒዉተር አፈጣጠርና እድገት አጭር ታሪክ
◽️ 1950ዎቹ - በ "ቫኪዩም ቲዩብ" ብቻ ይሰሩ የነበሩት ኮምፒዉተሮች መጠናቸዉ የአንድ ቤት መጠን እስኪያክል ድረስ እጅግ ግዙፍ የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ እጅግ ቀርፍፍ ነበሩ። በወቅቱ እነዚህን ኮምፒዉተሮች በብቸኝነት ይጠቀምባቸዉ የነበረዉ የአሜሪካ ሚሊቴሪ ተቋም ሲሆን ዋጋቸዉም ውድ ነበር።
◽️1960ዎቹ - በትራንዚስተሮች መፈጠር የተነሳ ቀርፍፍዉን የ"ቫኪዩም ቲዩብን" አሰራርን በመቀየር የኮምፒዉተሮች የአካል መጠን መቀነስ ሲቻል ብቃታቸዉንም ማሻሻል ተቻለ። በዚህ ወቅት ነበር ሜይንፍሬም (mainframe) የተባሉ ፈጣንና ወድ ኮምፒዉተሮች ተፈጥረዉ ከማሊቴሪና የመንግስት ተቋም አልፎ ለግል ድርጅቶች ጥቅም መዋል የጀመሩት።
◽️1970ዎቹ - በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮችን ያካተተ ኢንቴግሬትድ ሰርኪዩት "Intergrated Circute Board" አንድ ክፍልን ሊሞላ የሚችል መጠን ያለዉን የሜይንፍሬም ኮምፒዉተር አሳንሶ በጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒዉተር "Desktop" እንዲፈጠር አስቻለ።
◽️1980ዎቹ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮች እጅግ በጣም ትኝሽ መጠን ባለዉ የኮምፒዉተር ቺፕ ዉስጥ ህያዉ መሆን የኮምፒዉተር በጣም አንሶ በአንዲት ቦርሳ ዉስጥ የሚገባና ከድርጅት አልፎ ለግል ጥቅም መዋል የሚችልበት "Personal Computer (PC)" ዘመን ተወለደ። ኮምፒዉተሮች ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጥ አልፈዉ ጭን ላይ የሚቀመጡበትን መጠን ይዘዉ "laptop" በሚል ስያሜ ብቅ አለ።
◽️ 1990ዎቹ - የኢንተርኔት መወለድ ኮምፒዉተሮች እርስ በእርሳቸዉ እና በሌላ ቦታ ከሚገኝ ከፍተኛ አቅምና የመረጃ ብዛት ያለዉ የኮምፒዉተር ስብስብ "data center" ጋር ተገናኝተዉ ከዚህ ቀደም በራሳቸዉ አቅም ብቻ ከሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የላቀ ጥቅምን በፍጥነት መስጠት እንዲችሉ አደረገ።
◽️ 2000 - ለእጃችን መዳፍ እንኳን የማይሞሉ፣ ነገር ግን ብቃታቸዉ ከአንድ መጠኑ ከፍ ካለና ምርጥ ከሚባል ኮምፒዉተር ያልተናነሰ ተግባር ማከናወን የሚችሉ እንደ ረቀቀ ስልክ (Smartphone) ያሉ ተንቀሳቃሽ ቁሶች ላይ ዋሉ። ከስልኮችም አልፈዉ ታብሌቶቻችን፣ ሰዓቶቻችን፣ የቤት ቁሶቻችን፣ መኪናዎቻችን እና ልብሶቻችን ሳይቀሩ የኮምፒዉቲንግ ብቃት እየተካተተላቸዉ ይገኛል።
◽️ ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዘመን አብሮን ባለ ኮምፒዉተር ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ እንደ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ (Cloud computing) እና የመሴሰሉት የተራቀቁ በኢንተርኔት ተገናኝተዉ መሰራት የሚችሉ እና ከእኛ ርቀዉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተበታትነዉ በሚገኙ እጆግ ፈጣን ኮምፒዉተሮች አማካኝነት በርካታ ተግባር ማከናወን ተቻለ።
◽️ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ ማለት የኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች ሶፍትዌርኝ፣ ሃርድዌርን፣ መረጃን አና የተለያዩ ዲጂታል አሠራሮችን በራሳቸዉ ኮምፒዉተር ላይ ከመጫን ይልቅ ካሉበት ሰርቨሮች በኢንተርኔት አማካኝነት በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ልክ መቦራትና ዉሃ ቤታችን ድረስ እንደሚመጣዉ ከአገለግሎት ሰጪዎች ላይ በሚፈልጉት መጠን መጠቀም የሚያስችል አሠራር ነዉ።
◽️ የኮምፒዉተር እድገትና ፍጥነት አሁንም ሩጫዉን ቀጥሏል። ከላይ የተጠቀሰዉን አስደናቂ የኮምፒዉተር የለዉጥ እድገት ህያዉ ያደረገልን የMoore's Law ወደ ፍጻሜ እየመጣ ያለ ይመስላል። ምክንያቱም የትራንዚስተሮች እጅግ አናሳ በሆነ መጠንና በጣም በተጠቀጠቀ ሁኔታ በአነስተኛ ቦታ ላይ እንዲያርፉ የሚደረግበት የቺፕ አሠራር የመጨረሻ ገደቡና ጥጉ ላይ እየደረሰ ስለመጣ ነዉ። አንድን ትራንዚስተር ምንም ያህል እናሳንሰዉ ብንል ከአቶሚክ መጠን በታች ልናደርገዉ አንችልም።
◽️ ይህ ሂደት ወደ ፍጻሜዉ እየተቃረበ የመምጣቱን ባለሞያዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና አምራቾችም ይስማሙበታል። የትንቢቱ ባለቤት ጎርደን ሙር እራሱ በ2015 ዓ.ም. በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ከ50 ዓመታት በፊት የተነበየዉ Moore's Law ማክተማያዉ እየተቃረበ እንደመጣ ጠቁሟል።
◽️ ኮምፒዉተር እስከዛሬ በዚህ አይነት የረቀቀ የእድገት ሂደት ዉስጥ ካለፈ፣ "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?" የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮ ይመጣል።
🔺"ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?"
◽️ የወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች በጨረር፣ በኳንተም የፊዚክስ ህግ እና በሰዉነታችን ዉስጥ በሚገኙ በዲኤንኤ አማካኝነት የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በማንኛዉም ቁስ ላይ ተለጥፈዉ የሚገኙ፣ ወይም ደግሞ የራሳችን ኮምፒዉተር ሳያስፈልገን በሌላ ቦታ ተቀምጠዉ በኢንተርኔት አማካኝነት ያላቸዉን አቅም ሙሉ በሙሉ ከፈለግነዉ ቦታ ሆነን መጠቀም የምንችልባቸዉ አይነቶችም ሊሆኑ ይችላሉ።
◽️ የፋይበር ኦፕቲክስ "Finer-optic" ወይንም በጨረር አማካኝነት መረጃን ከአንድ ኮምፒዉተር ወደ ሌላዉ በፈጣን ሁኔታ በማስተላለፉ አሰራር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በፋይበር ኦፕቲክስ የሚተላለፉ መረጃዎች በኤሌትሪክ ሽቦ ዉስጥ ከሚተላለፉት ፍጥነታቸዉ በእጅጉ የተሻለ ሲሆን፣ በተጨማሪም እንደ ኤሌክትሮማግኔቲክ ያሉ የተለያዩ ጣልቃ ገብ ግብዓቶች አሠራሩን አያደናቅፉትም።
◽️ ይህ ከተቻለ የኮምፒዉተሮችን የዉስጥ የመረጃ አቀማመር አቅም እጅጉን እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን ተመራማሪዎች በዚህ ዙርያ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ስራዎች ቢያከናዉኑም መጠኑ ያነሰና በብዛት ተመርቶ በኮምፒዉተሮች ዉስጥ ሊገጠም የሚችልን በጨረር የሚሠሩ ቺፕ ህያዉ ለማድረግ ሙሉ ስኬትን እስከአሁን አላገኙም።
◽️ በጨረር አማካኝነት የሚሰሩ ኮምፒዉተሮችን ለመፍጠር በሚደረገዉ ምርምር የኢትዮጵያዉ ዶክተር ሰለሞን አስፍ እጅ አለበት። ዶክተር ሰለሞን የበርካታ ፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን በዋናነት የሚታወቅበት የፈጠራ ስራዉ በተለመደዉ አሠራር በኤሌትሪክ ከሚሰሩ ትራንዚስተሮች ይልቅ ኮምፒዉተሮች በብርሃን ጨረር (optical pulse) አማካኝነት መረጃን ለማስላት የሚችሉበትን ሙከራ ያደረገበት የምርምር ስራዉ ነዉ።
◽️ ይህ ግኝት ለወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች አሁን ካሉት ማሽኖች እስከ አንድ ሺህ እጥፍ ፍጥነት እንደሚሰጣቸዉ ሲጠበቅ፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታንም በእጅጉ ይቆጥባል ተብሏል። የዶክተር ሰለሞን ዋና ግኝት ፎቶዲቴክተር (photodetector) የሚባሉትና የብርሃን ጨረር መልዕክትን (optical signals) አጉልተዉ የሚያስተላልፉ ቁሶች ("amplifiers") እንዴት አድርገዉ መልዕክትን ለማይክሮፕሮሰሰሮች በሚገባ መንገድ በማስተላለፍ ጨረር መልዕክቶችን ወደ (electrical signals) በመቀየር ለኮምፒዉተር አሰራር ጥቅም እንዲዉሉ ማድረግ ነዉ።
1 636
📱ሞባይላችንን ተጠቅምን ቢሮ፣ሱቅ ወይንም እቤት ውስጥ ያለን ኮምፒወተራችንን መንካት ሳያስፈልግ፣
ካለንበት ስፍራ እንዴት መቆጣጠር እንችላለን???
━━━•••••━━ ••••• ━ •••• ━
✏️ድርጅት ኖሯችሁ ባጋጣሚ እሩቅ ቦታ ቢሆኑና ሂሳብ ለመዝጋት(Zreport) በሞባይሎ ትዛዝ ማውጣት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
✏️ኮምፒውተሮት አዲስ አበባ ሆኖ እርሶ ሆነ ለመዝናናት ውጭ ሃገር ከሆነ ያሉት፣ ያሉበት ሆነው ማን በኮምፒውተሮት ምን እየተጠቀመ እንደሆነ በደንብ መከታተል ተመኝተው ባለሞያው
✏️ለስራምባሉበት ሆነው ኮምፒውተሮ ላይ የሆነ ነገር ቢበላሽ የኮምፒውተር ባለሞያው መምጣይ ሳያስፈልገው ካለበት ሆኖ ችግሩን እንዲፈታስ?
✏️ምን እሱ ብቻ ባሉበት ሆነው ሙዚቃ መቀየር ፣ሰራተኛ በስንት ሰአት እንደገባ፣ጌም ማን እየተጫወተ እነደሆነ፣በቀን ምን ያህል እነደተሰራ፣ልጆቾት ምን አይነት ፊልም እያዩ እንደሆነ በተጨማሪም እቤትዎ ትንሽ ካሜራ ካሎት የትም ሆነው ማን እንደገባደረገ ነው የሚለውን መከታተልስ?
መልሳችሁ አዎ ከሆነ ምኞቶን የምታሳካ አሪፍ ዘዴ ይዘንላችኅል።
━━━━━━━━━━━━━━━
✏️በሞባይል ቀፏችን ተጠቅመን ኮምፒወተራችንን ባለንበት ቦታ በቀላሉ መቆጣጠር እንችላለን።
በመጀመሪያ ለዚህ ስራ የሚጠቅመን በሞባይላችን እና ኮምፒውተር ላይ የምንጭነው ቲም ቪወር (Team Viewer) የተባለ ሶፍትዌር ዳውንሎድ ማድረግ አለብን። ለ ኮምፒዩተራቹ ከዚህ በይነ መረብ ታገኙታላቹ።
✏️ሶፍትዌሮቹን ዳውንሎድ ካደረግን በኅላ በፕሮግራሙ ያጫጫን step መሰረት በኮምፒተራችን እና ስልካችን ላይ እንጭናለን።
ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ በራሱ መለያ ወይንም መገናኛ ኮድ እና መግቢያ ፓስዎርድ ይሰጠናል።
✏️ፓስዎርድ በራሱ ጊዜ ኮምፒውተራችንን ስንከፍት ስለሚቀያየር ለሁልጊዜ የሚሆን የራሳችንን ፓስዎርድ team viewerፓስወርድ setting ውስጥ በመግባት Setup Unattended Access የሚለውን ምርጫ ነክተን የራሳችንን እንሰጠዋለን።
✏️በመቀጠል ስልካችን ላይ የጫነውን ፕሮግራም ከፍተን ቅድም ኮምፒውተራችን ላይ የሰጠንን ID እናስገባና connect እንልዋልን።
በዚ ጊዜ ፓስዎርድ ስለሚጠይቅ ኮምፒውተሩ ላይ የፈጠርነውን ፓስዎርድ በማስገባት በቀላሉ መቆጣጠር እና መጠቀም እንጅምራለን ማለት ነው።
📌📌ይህ ዘዴ በምንኛው ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት በኮምፒውተሩም በሞባይላችንም ላይ ሊኖረን ይገባል።
የፈጠርነውን ፓስዎርድ እና ID ለስራ ካልሆነ ለሌላ ሰው ማሳየት የለብንም ምክንያቱም ሌሎች ሰዎ በፈለጉት ጊዜ ገብተው ችግር ሊፈጥሩብን ይችላሉ።
━━━━━━━━━━━━━━━
@cellphonetechnology
━━━━━━━━━━━━━━━
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
