ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 381 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 584,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 199

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 381 名订阅者。

根据 03 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 21,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 21.13%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.50% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 250 次浏览,首日通常累积 1 462 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 16

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

凭借高频更新(最新数据采集于 04 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 381
订阅者
-724 小时
+117
+2130
帖子存档
በድጋሚ ፤ አዎ የብጹዕነታችው ውሳኔ እየተከበረ አይደለም :: ሊንኩን 👇👇👇👇በመጫን ወደ facebook ገጹ ሔደው አስተያየት ይስጡ ::አሁኑኑ! https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/posts/2884002708584475

ለሰ/ት/ቤቱ አባላት እንዲሁም ለአጥቢያችን ምእመናን በሙሉ #_የብጹዕ_አባታችን_አቡነ_መልከጼዴቅ ውሳኔ አሁንም ሊተገበር አልቻለም:: የአካባቢው ምእመናን እና ሰ/ት/ቤቱ በጋራ ሆነን ወደ ሐገረ ስብከቱ #_ለአፈጻጸም_እንሂድ_የሚል_ጥያቄ_እየበረታ_ነው፡፡ ብጹዕነታቸው የካቲት 29/2013 ዓ.ም የደብሩን አስተዳደር እና የደብሩን ሰንበት ት/ት ቤት እንዲሁም የአጥቢያውን ምእመናን በሐገረ ስብከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ካወያዩ በኋላ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዚሁ እለት ወደ ደብራችን በመምጣት የመስክ ምልከታ አድርገው እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ብጹዕነታቸው ከመስክ ምልከታ በኋላ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 3008/13/13 የደብሩ ሰንበት ት/ት ቤት ወደ ቀደመ ቦታው መዋዕለ ህጻናት ግቢ ውስጥ እንዲገባ ውሳኔያቸውን ልከዋል፡፡ ከውሳኔውም በኋላ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም በሐገረ ስብከቱ ቢሮ የደብሩን ሰንበት ት/ት ቤትና የደብሩን አስተዳደር ሰራተኞችን በመጥራት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ውሳኔው እንዲፈጸምና የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዴት መፈጸም እንዳለበት በቃለ ጉባኤ ተነጋግረን እንድንመጣ መመርያ ተሰጥቶን በብጹዕነታቸው ጸሎት ስብሰባውን አጠናቀን ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ የደብሩ ማኅበረ ካህናት የመረጧቸው 4 ካህናት አባቶች ጋር ሆነን የጋራ ስብሰባ ካደረግን በኋላ በ24/07/2013 ዓ.ም ስብሰባችንን ጨርሰን የጋራ ቃለ ጉባኤ ይዘን ተፈራርመን የጨረስን ቢሆንም አሁንም የደብራችን አስተዳደር ከካህናቱ ጋር የተፈራረምነውን ቃለ ጉባኤ ለብጹዕነታቸው አስማሚ በሆነ መንገድ ሊያደርስ አልቻለም፡፡ ሰ/ት/ቤቱም ቃለ ጉባኤውን ያቀረብን ቢሆንም እስካሁን ድረስ ከስራ አስኪያጁ ቢሮ ወጥቶ ብጹዕነታቸው ጋር መድረስ ግን አልቻለም፡፡ ከብጹዕነታቸው ስር ያሉ #_ሹማምንቶች_ውሳኔው ወደ አፈጻጸም እንዲሄድ የሚያደርጉት ምንም አይነት ጥረት አይታይም፡፡ ለበርካታ ጊዜያት ይህንን የሰ/ት/ቤቱን ጉዳይ እያስተባበሩ የሚገኙ ወንድሞች እና እህቶች ወደ ሀገረ ስብከቱ በተደጋጋሚ ቢያቀኑም ተጨባጭ መልስ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም :: በዚህ ምክንያት የደብሩ ሰ/ት/ቤት በቀን 9/08/2013 ዓ.ም በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጉዳያችንን #_በህብረት_ሄደን_ማስፈጸም_መቻል_ አለብን የሚል ውሳኔ ወስኗል፡፡ የአካባቢው ምእመናን እና ወጣቶችም በዚህ ሳምንት ውስጥ በህብረት ሆነን ለልጆቻችን የተወሰነውን ውሳኔ ማስፈጸም መቻል አለብን የሚል ጥያቄ በብርቱ #_እያነሱ_ነው፡፡ ሰ/ት/ቤቱ ለሰላም ሲባል፣ ለአንድነት ሲባል ብዙ ብንጥርም ፣ አንጋፋ የሆኑ የአካባቢውን ሽማግሌዎች ብንልክም የደብሩ አስተዳደር ሽማግሌዎቹን መቀበልም አልቻለም፣ ከዚህ ይልቅ 14 የሰንበት ት/ት ቤታችን አባላት ‹‹ ሰላም በማደፍረስ ከሰናል›› ብለው የደብራችን አስተዳዳሪ በተናገሩት መሰረት #ክስ_ከፍተዋል፡፡ ምድራዊ እስር ቤትን የሚፈራ ሰንበት ተማሪ ባይኖርም አሁንም ግን የምንጠይቀው ጥያቄ #_የብጹእነታቸው_መመርያ_ይተግበር የሚል ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን ጥያቄ ከመላው የቀጨኔ ምእመናን ጋር ሆነን ለብጹዕነታቸው እናቀርባለን:: #Share በማድረግ ለመላው የአጥቢያችን ምዕመናን እንድናደርስ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃልን፡፡ #share #_ሰላመ_እግዚአብሔር_አይለየን

#መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ቡራኬያቸው ይድረሰንና የካቲት 29/2013 ዓ.ም ብጹእ አቡነ መልከጸዴቅ የአ.አ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደብሩን ሁኔታ በአካል ተገኝተው የመስክ ምልከታ
#መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ቡራኬያቸው ይድረሰንና የካቲት 29/2013 ዓ.ም ብጹእ አቡነ መልከጸዴቅ የአ.አ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደብሩን ሁኔታ በአካል ተገኝተው የመስክ ምልከታ ካደረጉ በኀላ የወሰኑት ውሳኔ::

#ታህሳስ 12/2013 ዓ.ም አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የአ.አ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መምህር አካለወልድ ተሠማ መስከረም 28/2013 ዓ.ም የተወሰነው ውሳኔ የደብሩ አስተዳደር አለመፈጸሙ
#ታህሳስ 12/2013 ዓ.ም አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የአ.አ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መምህር አካለወልድ ተሠማ መስከረም 28/2013 ዓ.ም የተወሰነው ውሳኔ የደብሩ አስተዳደር አለመፈጸሙን ተረድተው የወሰኑት ውሳኔ::

#መስከረም 28/2013 ዓ.ም በወቅቱ የነበሩት የአ.አ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ ለውሳኔ እንዲረዳቸው ከቅዱስ ፓትርያሪኩ በተሰጠ መመርያ 5 አባላት ያሉትን
#መስከረም 28/2013 ዓ.ም በወቅቱ የነበሩት የአ.አ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ ለውሳኔ እንዲረዳቸው ከቅዱስ ፓትርያሪኩ በተሰጠ መመርያ 5 አባላት ያሉትን አጣሪ ኮሚቴዎች ልከው ከኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት መነሻነት የወሰኑት ውሳኔ:

ሰንበት ት/ት ቤታችን ላለፉት 2 ዓመታት በቋሚ የማስተማርያ ቦታ ጥያቄ ምክንያት በርካታ ፈተናዎችን በመድኃኔዓለም ቸርነት እያለፈ እዚህ ደርሷል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም የተለያዩ ውሳኔዎች ተወስነዉለታል እነዚህም፡- #መስከረም 28/2013 ዓ.ም በወቅቱ የነበሩት የአ.አ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ ለውሳኔ እንዲረዳቸው ከቅዱስ ፓትርያሪኩ በተሰጠ መመርያ 5 አባላት ያሉትን አጣሪ ኮሚቴዎች ልከው ከኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት መነሻነት የወሰኑት ውሳኔ:: #ታህሳስ 12/2013 ዓ.ም አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የአ.አ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መምህር አካለወልድ ተሠማ መስከረም 28/2013 ዓ.ም የተወሰነው ውሳኔ የደብሩ አስተዳደር አለመፈጸሙን ተረድተው የወሰኑት ውሳኔ:: #መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ቡራኬያቸው ይድረሰንና የካቲት 29/2013 ዓ.ም ብጹእ አቡነ መልከጸዴቅ የአ.አ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደብሩን ሁኔታ በአካል ተገኝተው የመስክ ምልከታ ካደረጉ በኀላ የወሰኑት ውሳኔ::

ሰባተኛው ሳምንት ꔰኒቆዲሞስꔰ ይባላል፤ በዚህ ሳምንትም ይህ ይታሰብበታል፡፡ ‹‹ኒቆዲሞስ››፤ * አይሁዳዊ ሲሆን ከፈሪሳውያን ወገን የነበረ ነው * በኢየሩሳሌም በሀብት ቢሉ በዕውቀት እንዲሁም በሥልጣን የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ * ማታ ማታ ጌታችን ዘንድ እየተገኘ ይማር ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ አስቀምጦልናል፦ ꔰ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ ‹‹መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህ ተዓምራቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ꔰ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ፨ ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ꔰ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።›› /ዮሐ. ፫፥ ዘ፩-፲፭//ፍ.ሕ.ሰ.ት.ቤት/ ለምን በሌሊት ይመጣ ነበር? ꔰ አይሁድ ‹‹ማንም ከእኛ ወገን የሆነ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሆነ ሀብት ንብረቱ ይወሰድ፣ በቤተመቅደስ አይግባ፣ መሥዋዕት አይሥዋ›› ብለው ነበርና አይሁድን ፈርቶ፥ ሀብት ንብረቱን ወዶ እንዳይታወቅበት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ꔰ በሌላ በኩል ደግሞ የቀን ልብ ባካና ነው፤ ዓይን ብዙ ያያል፥ ሐሳብ ይበታተናል፡፡ በተሰበሰበ ልብ ለመማር፤ በተጨማሪ ‹‹ሊቅ ነኝ›› እያለ ‹‹እስከ ዛሬ ትምህርት አልጨረሰም›› እንዳይሉት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ꔰ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን ለመማር የመጣውን እራሱ እየሄደ ያስተምር ነበርና ኒቆዲሞስ ምንም በሌሊት ቢመጣም ማወቅን ፈልጎ ነውና ስለዳግም መወለድ /ስለጥምቀት/ በእግዚአብሔር ልጅ ስለማመንና ስለ ጽድቅ ስራ በዝርዝር አስተምሮታል፡፡ ꔰ ኒቆዲሞስ በመጨረሻው ቀን በዕለተ ዐርብ በስቅለቱ ጊዜ፤ ከመስቀል ላይ ሥጋውን ለማውረድና ገንዞ ለመቅበር ቀድሞ ተገኝቷል፡፡ /ዮሐ. ፲፱፥፴፰/ /ፍ.ሕ.ሰ.ት.ቤት/ ከኒቆዲሞስ ሕይወት የምንማረው፡- ፩. ትሕትና፦ ኒቆዲሞስ በትምህርት፣ በሹመት፣ በባለጸግነት የአይሁድ አለቃ ሲሆን አለቅነቱ ግን ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ እርሱ ተገኝቶ ለመማር አልከለከለውም፡፡ /በጽሑፉ መጨረሻ ያለውን ቅኔ ተመልከቱ/ ፪. አለማመካኘት፦ ከመጀመሪያ ሰዎች ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ ሰዎች በምክንያተኝነት በአመፅ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ ኒቆዲሞስም ወደ ጌታ በመቅረቡ የጸሐፍት ፈሪሳውያን አድማና ግርግር ታላቅ እንቅፋትና ምክንያት መሆን እንደሚችል ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት እንደማያዋጣ አውቆ የሚያወጣውን አደረገ፡፡ ፫. ጥበብ፦ በክርስትና ጉዞ ውስጥ ጥበብ የመጀመሪያ ቦታ ትይዛለች፡፡ ኒቆዲሞስም ጕዞውን በጥበብ አደረገ፡፡ በሌሊት ያደረገበት ምክንያት፡- ራሱ መምህር ሆኖ ሌላ ትምህርት አስፈለገው ብለው ሌሎች እንዳይሰናከሉበት፣ የመዓልት ልቦና ስለሚሰበሰብ በቂ ዕውቀት ለማግኘት፣ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት በመዓልትም በሌሊትም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብን ለማጠየቅ፣ ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ያሉ ነፍሳት በሲዖል ይገኛሉ ሲል፣ በመዓልትም በሌሊትም ብትፈልጉ ትገኛለች ሲል ነው፡፡ በእውነት ግሩም ጥበብ! ፬. የተነገረውን አምኖ በመቀበሉ፡- ጸሐፍት ፈሪሳውያን ብዙ ምክንያቶች እየደረደሩ የጌታን አምላክነት አምኖ መቀበል ሲያቅታቸው እርሱ ግን ጌትነቱን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ፭. ለእውነት መመስከር፡- እነርሱ ሲክዱ ጌታ ላይም ትርፍ ቃል ሲናገሩ፤ በድፍረት መክሰሳቸውን እየነገራቸው የጌታችን አምላክነቱን በግልጽ ይመሰክር ነበር፡፡ ፮. ጽንዓት፡- ብዙዎች በመከራ ጊዜ ላይለዩት ቃል ቢገቡም መጨረሻ ላይ ያኔ በመከራ ሰዓት ከመስቀሉ ሥር ሊገኙ የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስም በዚች ሰዓት ያንን መከራ ታግሶ በጽነዓት ከዮሴፍ ጋር የጌታን ሥጋ ከመስቀል አውርደው በአዲስ መቃብር ቀብረውታል፡፡ ꔰ ወስብሐት ለእግዚአብሔርꔰ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem Finotehiwotsundayschool.com

ሚያዝያ 6 ጌታችን በትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጸለት:: #share በእጆቹና በእግሮቹና ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጎኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የ
ሚያዝያ 6 ጌታችን በትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጸለት:: #share በእጆቹና በእግሮቹና ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጎኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ ሆይ መነሣትህን አመንኩ አለ ፡፡ ጌታችንም የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት፡፡ ቶማስ እጁን ወደ ጎኑ ባስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሣት ተቃጠለ በአመነ ጊዜ ደግሞ እጁ ከመቃጠል ዳነች ፡፡ ‹‹ ትርጓሜ ወንጌል ›› ሚያዝያ 6 ይህች ዕለት የአዳም እና የሔዋና መታሰቢያ ናት! ሚያዝያ 6 ልደቱ ለኖኀ ወቅዱስ ዳዊት /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem Finotehiwotsundayschool.com