Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 335 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 641,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 191 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 335 名订阅者。
根据 15 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -80,过去 24 小时变化为 -1,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.23%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.47% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 409 次浏览,首日通常累积 1 605 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 16 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 335
订阅者
-124 小时
-117 天
-8030 天
帖子存档
#ኅዳር_26
#_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተማርያም፡፡
፠ አቡነ_ሀብተማርያም በሽዋ (የራውዕይ /ቡልጋ/) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክ ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡
፠ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መናኝ ነበረች፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡
፠ ጻድቁ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ ይህንንም በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፤ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡
፠ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ መንነዋል፤ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኰሱ በኋላም ብዙ ትርፋትንና ተጋድሎን ሠሩ፡፡ ለአብነትም፤
*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ፤
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ፤
*በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ፤
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ነው፤
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ፤
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ፥ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ፤
*በልባቸው ውስጥ በፍጹም ቂምን፥ መከፋትን አላሳደሩም፡፡
* ረአዬ ኅቡዓት በመባል ይታወቃሉ፡፡
* በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርኩት ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
* ‹‹#ጽድቅና_ትሩፋት_እንደ_ሀብተ_ማርያም፠››
፠ ጌታችን ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔዱ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤
* ‹‹ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ፤ ስለ ምናኔህ፣ ስለ ተባረከ ምንኵስናህ፣ ስለ ንጹሕ ድንግልናህ፣ ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ፣ ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ፣ ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ፡፡››
* በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን፤ 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ፡፡ በስምህ የሚለምኑ፤ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ ‹አማንየ በርእስየ› ብዬሃለሁ›› አላቸው፡፡
* ቅዱሳን መላእክትም ‹‹ሀብተ ማርያም ወንድማችን›› ሲሉ አቀፏቸው፡፡ ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው፡፡ ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡ በዝማሬም ወሰዷት፡፡
✤ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. #_መብረቅ፣
2ኛ. #_ቸነፈር፣
3ኛ. #_ረሃብ፣
4ኛ. #_ወረርሽኝ፣
5ኛ. #_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
፠ በተሰጣቸው ቃል ኪዳንም ከላይ ያሉትን 5ት መቅሰፍቶች የሚያርቁ በመሆናቸው፤ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን በደብረ ሊባኖስ ገዳም እነዚህ 5ቱ መቅሰፍቶች እንዳይቀርቡ የሀብተማርያም ካህናት ከኅዳር 1-7(10) ማዕጠንት ያጥናሉ፤ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም ለደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም 1ድ በሬ ስጦታን ያበረክታሉ፡፡
፠ በዛሬው ዕለት በኅዳር 26 ባረፈ ጊዜ፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው፤ በዝማሬ ፥ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ፥ ከብርም የጠራ ፥ ከሁሉ የሚበልጥ ፥ የተመረጠ ፥ ሀብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)
#_በዛሬዋ ዕለት #በናግራን ያሉ ክርስቲያኖች በ6ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት የኾኑበት ዕለትም ነው፡፡
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
፠ ጻድቁ በአጠቃላይ 44 ዓመታትን ማለትም፤
* 20 ዓመት በይትባረክ ዘመነ መንግሥት
* 15 ዓመት በይኵኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት
* 9 ዓመት በአግብዓ ጽዮን ዘመነ መንግሥት የኖሩ ሲኾን፤ ለ44 ዓመታት በገዳም ቆይታቸው ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም፥ ለሰውነታቸውም(ለጎናቸውም) ምኝታን አላስለመዱትም፡፡
‹‹እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ፤
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ፡፡›› እንዲል፡፡
ጻድቁ በሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩም የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር፡፡
** የማረፊያው እለት በደረሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱና ሰዎች ተሰባሰቡ፤ በደብረ ነጐድጓድ ያደገውን ተክለ ኢየሱስን መምህር አድርጎ ሾመላቸው እነርሱንም ባርኳቸው፤ ኅዳር 26 በ1286ዓ.ም. በእለተ እሑድ ጧት ፀሐይ ስትወጣ ዐረፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም እንደሚገባ አድርገው በፍየል ሌጦ አድርገው ገንዘው በክብር ቀበሩት፡፡
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
#ኅዳር_26_ #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ፤
#_ከደብረ_ዳሞ_ቀጥሎ_በሃገራችን_ሁለተኛውን_መካነ_አእምሮ(#University)#የመሠረተ፤
#_በሃገራችን_ወርቃማ_ዘመን_ተብሎ_የሚታወቀውን_ዘመን_ፋና_ወግቶ_የጀመረ_
#_መጻሕፍትን በእጁ በመጻፍ ለትውልድ የታሪክ አሻራን ያሳረፈ
#_የሐይቅ_እስጢፋኖስ_ገዳምን_ዳግመኛ_ያቀናና_ያስፋፋ፥
#በደብረ ዳሞ አስኬማ ዘመላእክትን የተማረ
#እንደ እስጢፋኖስ ጸጋን ጽድቅንና ሞገስን የተመላ፥ በሥራው ፍጹም የኾነ፥
#የመጀመሪያውን_የዐቃቤ_ሰዐት_ማዕርግ_ያገኘ፡፡
#_ለቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ፥ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ ፥ #አቡነ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫና_ #ለሌሎችም_በርከካታ_ቅዱሳን_ወላዴ_አእላፍ_ቅዱሳን_የኾነ፡፡
* በበጌምድር ዳኅና(አሁን ስማዳ) ገብርኤል በተባለ ቦታ ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ነሐሴ 26 ሰኞ ተጸንሰው፤ ግንቦት 26/1205 ዓ.ም. ረቡዕ በቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ዘመነ መንግሥት ተወለዱ፡፡ ወንድሞቻቸው ገብረ ጽዮንና ስቡሕ አምላክ ይባላሉ፡፡
*እስከ 30 ዓመታቸው ድረስ በእናት አባታቸው ቤት እያገለገሉና ትምህርት እየቀሰሙ ቆዩ፤ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾላቸው ወደ 5ኛው የደብረ ዳሞ አበምኔት ዳግማዊ አቡነ ዮሐኒ ዘንድ እንዲሄዱ በራዕይ ነገራቸው፤ በመንገድም ሲሄዱም የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን አግኝተው ይምጻአ ምሕረት የሚባል ዲያቆንን አስከትለው ወደ ደብረ ዳሞ እንዲሄዱ መልአኩ ባዘዛቸው መሠረት ወደ ገዳሙ አቀኑ፡፡
*በደብረ ዳሞ ቆይታቸውም እህልን በመፍጨትና ለገዳሙ ንግድን (ሩቅ መንገድንና አስጨናቂ ኹኔታዎችን በማለፍ ) ይነግዱ ነበር፡፡ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጻፍ (በመገልበጥም) ትጉህ ጸሓፊ ናቸው፤ ይህ ይታወቅ ዘንድ በቅርብ የደብረ ዳሞ ዕቃ ቤት እስከተቃጠለበት ድረስ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእጃቸው የጻፉት ወንጌል ይገኝ ነበር፡፡
*37ዓመት ሲኾናቸው ከአባ ዮሐኒ ሥርዐተ አስኬማ ዘመላእክትን ከተቀበሉ በኋላ መልአኩ ወደ ሐይቅ እንዲሄዱ በገለጻላቸው መሠረት በ1237 ዓ.ም. ወደ ሐይቅ በመምጣት በሐይቁ ዳር በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤ.ክ. ለ6ወራት አገለገሉ፤ በዚሁ ደብር የሚገኘው ‹‹#ሔር_አምላክ_›› የተባለ ካህንም የጻድቁን ታሪካቸውን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ ወደ ደሴቱ አስገባቸው፤ የአካባቢው ሕዝብም አገልግሎታቸውንና መንፈሳዊ ተጋድሏቸውን አይተው ንጉሡ ይትባረክ ዘንድ በመሄድ የገዳሙ አበምኔት እንዲያደርገው ጠየቁት እርሱም ሾመው፡፡ ጻድቁም ይህን ገዳም በዮዲት ጉዲት ከጠፋ ከ300 ዓመታት በኋላ ዳግም አቅንቶታል፡፡
*እርሳቸውም ደሴቲቷም ስለወደዷት ከገዳሟ ላለመውጣት፤ የባሕሩን ወደብም ላለመርገጥ ብፅዓት ገብተው 20 ዓመታት ያህል እንደኖሩ፤ አፄ ይኵኖ አምላክ እንደነገሠ ጻድቁ ወደ ንጉሡ እንዲመጡ ላከበቸው፤ እርሳቸው ግን ከሐየቁ እንደማይወጡ ብፅዓት እንዳለባቸው፤ ንጉሡ ወደ እርሳቸው እንዲመጣ ላኩበት፤ ንጉሡም በበቅሎ እስከ ጉልበቱ ድረስ ወደ ባሕሩ ገብቶ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ኂሩተ አምላክና ኀረየነ ክርስቶስ ከሚባሉ ደቀመዛሙርቶቹ ጋር በታንኳ (በጀልባ) መጥተው ተጨዋወቱ፤ ንጉሡም ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ሲላቸው፤
* ገዳሟ የወንዶች ገዳም እንድትኾን ነው አሉት፤ ንጉሡም በቦታው ያሉትን ሴቶች ይህ ቦታ የወንዶች ገዳም ብቻ እንዲኾን ስለወሰንኩ የፈቀዳችሁ ከእኔ ጋር በከተማዬ መኖር አሊያ በፈቀዳችሁትና በመረጣችሁት ቦታ መኖር ትችላላችሁ የምትፈልጉትንም ኹሉ እሰጣችኋለሁ በማለት ሥርዐት አበጁለት፡፡ ደሴቲቱን ለቀው እየሄዱ ካሉት ሴቶች መካከልም አንዲቷ ምጧ ደርሶ ነበረና በደሴቱ ጫፍ ወለደች ቦታውም ‹‹#ምጥ_ገበታ_›› ተባለ፡፡ ዛሬ ክብረ በዓል የሚከበረው በዚሁ ምጥ ገበታ በተባለው ቦታ ነው፡፡ (ከምጥ ገበታ በስተምዕራብ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ፤ በስተሰሜን ምዕራብ መካነ አእምሮ (University)፤ በስተሰሜን የሴቶች ገዳም ይገኛል)
* በንግግራቸው ሳሉም እባብና አለቅት በንጉሡን በቅሎ እግር ላይ ተጠመጠሙ፤ ጻድቁም መርዛማነት ያላቸው እንስሳት በዚህ ገዳም ሰውን እንዳይጎዱ አወገዟቸው፤ የደወልም ድምፅ ተሰማ ንጉሡም አሁን ስንት ሰዐት ነው የደወል ድምፁስ ምንድን ነው ብሎ ጻድቁን ጠየቀ፤ ጻድቁም ፱ኝ ሰዐት በመኾኑ ደወሉ ከገዳሙ የተደወለ መኾኑን ነገሩት ንጉሡም ለጻድቁ #የዐቃቤ_ሰዐት_ ማዕርግን ሰጣቸው (በአሁኔ ሰዐት ዐቃቤ ሰዐት የጠቅላይ ሚንስትሩ ዋና አማካሪ ከሚለው ጋር የተካከለ ነው)፡፡ (ምንም እንኳን እርሳቸው በሹመቱ ለመጠቀም ባይፈልጉም)፤ ከተከታያቸው ከአባ ዘኢየሱስ አንስቶ እስከ 16ኛው መጀመሪያ አጋማሽ ድረስ በሐይቅ መምህራን እጅ ቆይቷል፤ ኋላ የንጉሦች መናገሻ ከሸዋ ወደ ጎንደር ሲዛወር በቦታ ርቀት ምክንያት ይህ ሹመት በገጽ የሚሰጥ ሹመት ሁኗል፡፡)
✤ንጉሡ ይኵኖ አምላክ ለገዳሟ የሚከተለውን ሥርዐት ሠርተው መደ መናገሻቸው፤ ጻድቁም ወደ ደሴታቸው ተመለሱ ፤
መኳንንት፣ መሳፍንትና ነገሥታት የሰጡትን የገዳሙን ርስት ጉልት ማንም እንዳይነካ፤
ሴቶች ወደ ገዳሙ እንዳይገቡ (የአባቶች መነኰሳትና የባሕታውያን ብቻ መኖሪያ እንዲኾንና እኅቶች እንዳይቀላቀሉ በማሰብ)
መነኰስ ያልኾነ ማንም በሐይቅ ገዳም ቤትን እንዳይሠራ፡፡
፠ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በሃገራችን አንጋፋና ቀደምት በኾነው ደብረ ዳሞ መካነ አእምሮ (University) የተማሩ እንደመኾናቸው፤ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሲመለሱም በሃገራችን በትምህርት መካነ አእምሮነቱ ዋናና ግንባር ቀደምቱን፤ በርካታ ሊቃውንትን ቅዱሳንን ያፈለቀውን የሐይቅ እስጢፋኖስ መካነ አእምሮ መሠረቱ፤ በዚህም የኢትዮጵያን ወርቃማ ዘመን መሥራች ነው፤ ልጆቻቸውም ይህን ወርቃማ ዘመን አስቀጥለውታል፡፡ በቆብ የወለዷቸው ቅዱሳን ሊቃውንት ብዙ ቢኾኑም ለአብነት ያህል ዐበይቶቹ፤
✤ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል (ምድረ ዐማራን፣ ሸዋንና ደቡብን፤ ምድረ ትግራይን ያስተማሩ፤ የአቡነ ተክለሃይማኖት የመጀመሪያ መምህር የኾኑ)
✤ አቡነ ተክለሃይማኖት (ሐዲስ ሐዋርያ ተብሎ የተሰየመ፤ በሐይቅ ከመመንኰሳቸው በፊት 7 ዓመታት፣ ከመነኰሱ በኋላ 3 ዓመታት ተቀምጠዋል)
✤ አባ ሕዝቅያስ (ከምድረ ወግዳ ይዞ እስከ ጎጃም ያስተማሩ)
✤ አባ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት (በጸበላቸው የእንጨት ቅርፊትን እንደ ደንጊያ መቁጠሪያ የሚያደርጉ፣ በድንጋይ ሠረገላ የሚጓጓዙ)
✤ እጨጌ አባ አሮን ዘደብረ ዳሪት (ከምድረ ዋድላ አንስቶ እስከ ዳውንት፤ ከበጌምድር እስከ ደምቢያ የሰበከ)
✤ አባ ገብረ ናዝራዊ ዘበለሳ (ምድረ ትግሬን ያስተማረ)
✤ አባ ኂሩተ አምላክ ዘዳጋ (እንደ መምህሩ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእስጢፋኖስ ስም በጣና ላይ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን የመሠረተ፤ ምድረ ሳርክን ይዞ እስከ ጋዝጌ፤ መላዋን የአላፋና ጣቁሳ እና የአገው ምድርን ያስተማረ)
✤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ዘደብረ ባሕርይ) (የኢትዮጵያ መብራት)፤ አብዛኛዋን የኢትዮጵያ ምድር ያስተማረና ቤተ ክርስቲያንን ከ40 በላይ በሚደርሱ ድርሳናቱ ያስጌጠ፡፡
✤ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፡፡
✤✤ እንዲሁም ንጉሡ ይኵኖ አምላክ (ከንግሥናው በፊት በልጅነቱ ያደገውና የተማረው ከጻድቁ ዘንድ ነው፡፡)
ቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕሉ ሲያሸበሽብ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፤ ጣርማ በር ወረዳ፤ ጋሹ አምባ ቀበሌ፤ አርማንያ ቅዱስ መርቆሬዎስ፡፡
t.me/finotehiwott
መልክዓ_ሊቀ_ሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ1.pdf1.28 MB
#ጋሹ_አምባ_አርማንያ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_፤ (ስዕሉ በበዓለ መርቆሬዎስ ቀን የሚያሸበሽበው)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ሲና፥ ጣርማበር ወረዳ፥ አርማንያ ቀበሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ሲና → አርማንያ(ጋሹ አምባ)፡፡
.#ደሴ_ደብረ_መዊዕ_ኪዳነ_ምሕረትና_መርቆሬዎስ_፤ ደሴ፤
#ናዝሬት_ደብረ_ሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_፤
ናዝሬት(አዳማ)፤
፡፡
#አማን_ጎሪቃ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምዕራብ ሃገረ ስብከት፥
#ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ በድርብነት
#ጎፋ_መብራት_ኃይል የመርቆሬዎስ ቤ/ን አለ
#በተጨማሪም ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤልም በድርብነት አለ ይነግሣል
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
ኅዳር 25 በዓለ_ ዕረፍቱ ለሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ (#ፒሉፓዴር)፤
#Share ያድርጉ
*አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
*የወላጆቹ (አባቱን ኖህ እናቱን ታቦት) አገር አስሊጥ የምትባል ስትኾን እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ፒሉፓዴር ነው፡፡
* ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሯቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሯቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብረውት ነበሩ፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሯቸውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡
**በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡
ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡
✤ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እንዲሁም ጎርጎርዮስን ረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ በስዕሉ ላይ ያለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ይዞ ከተሳለው ጦር ጫፍ ላይም ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
✤ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡ መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስሏቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኰሳትን አፍርቷል፡፡
#Share ያድርጉ
የበዓለ ዕረፍቱ ክብረ በዓል የሚከበርባቸው
#ደብረ_ጽባሕ_ጸዶየ_መርቆሬዎስ_፤ (በዐፄ ይኵኖ አምላክ ዘመን የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ አኵሱም ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጸዶየ፡፡
#ርዕሰ_አድባራት_ወገዳማት_ደረስጌ_ደብረ_ጽዮን_ማርያም_፡፡
አድራሻ፤ ሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ስሜን፥ ጃናሞራ ወረዳ፥ መካነ ሰላም ከተማ (ራስ ደጀን ተራራ አናት አጠገብ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → ጃናሞራ፡፡
#ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ጎንደር ሀገረ ስብከት፤
#ጎንደር ደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት፤
አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤
ኅዳር 24 እንኳን ለ የ24ቱ_ካህናተ_ሰማይ(ሱራፌል)_በዓል እና በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ ከካህናተ ሰማይ ጋር #የሥላሴን መንበር ላጠኑበት ዕለት በሰላም አደረሳቹህ ፡፡
፨ካህናተ ሰማይ የዐውዶ ሡራሄ፤
ሎቱ ለባህቲቱ ይደሉ ስባሔ፨ /ሰዐታት/
#Share ያድርጉ
ካህናት ሰማይ
ከሠራዊተ #ሩፋኤል (ሊቃናት) ሃያአራት ሊቃናት መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙርያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል፡፡ ሕዝ 1 ፥11-12
※ስማቸውን #ካህናተ_ሰማይ አላቸው የእሳትና የወርቅ ጽና አስያዛቸው ፤ የብርሃን አክሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሃን ዘውድ ደፋላቸው የብርሃን ዘንግ ማኀተሙ መስቀል የሆነ አስያዛቸው ፤ የብርሃን ላንቃ ኀብሩ መብረቅ የመሰለ አለበሳቸው ፡፡ ‹‹በዙፋኑ ዙርያ ሀያአራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዋች ተቀምጠው ነበር›› ዮሐ ራዕ 4፥-5
ካሕናተ ሰማይ ( ሱራፌል ) የሐዲስ ኪዳን ካህናት ምሳሌዎች ናቸው ፡፡ እነዚያ በሰማይ ሲያገለግሉ የሐዲስ ኪዳን ካሕናት ደግሞ በምድር ያገለግላሉ ፡፡
ሰማውያኑ አክሊል ተቀዳጅተው ፣ መብረቅ ለብሰው ሲያገለግሉ ምድራውያኑ ደግሞ ለአክብሮተ ወንጌል ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰው ማዕጠንተ ወርቃቸውን ይዘው ጸሎታችንን ለማሳረግ ሲወጡ ሲወርዱ ይኖራል ፡፡
እነዚህ መላእክት ለምሕረት ወደዚህ አለም እንደሚመጡ ከልዑለ ቃል ኢሳይያስ እንረዳለን ይህም እግዚአብሔር ኢሳይያስን ይቅር ብሎ ሃብተ ትንቢትን ሲሰጠው የላከለት ከሱራፌል አንዱን ነው ፡፡ ኢሳ 6 ፥ 5
※እነዚህም በአንድ ላይ በአጠኑ ጊዜ ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ #መብረቅ ፤ ድምጹ ነጎድጓድ ፣ መዓዛው መልካም የሆነ ነው ፡፡ ‹‹ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምርው ብዙ ዕጣን ተሰጠው ፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ወጣ››ዮሐ ራዕ 8 ፥3-5
※የሚያጥኑት ምንድን ነው ቢሉ የጻድቃን ጸሎት ፤ የሰማዕታት ገድል ፣ የደጋግ ሰዎች ምግባር ነው ፡፡ በእናንተ እየጣጠነ ወደ እኔ ያርግ ( ይድርስ ) ብሏቸዋልና ፡፡ ያለ እነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም፡፡
የሥላሴን መንበር ካጠኑ ቅዱሳን ውስጥም ፤
ለምሳሌም ፤ በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር አጥነዋል ፨ አቡነ ዮሴፍ ዘጂፋት፣ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንዲሁ አጥነዋል ፡፡
#Share ያድርጉ
፨ካህናተ ሰማይ የዐውዶ ሡራሄ፤
ሎቱ ለባህቲቱ ይደሉ ስባሔ፨ /ሰዐታት/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
ዜና ዕረፍት #ዐራት_ዐይና_አባ_ይባቤ_ዐረፉ!
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የአቡሻኽር፣ የፍትሐ ነገሥት እና የቅኔ መምህር፤ የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰማ።
በየኔታ ይባቤ በላይ ዕረፍተ ሥጋ የተሰማንን ኅዘን እየገለጽን ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው፣ ለገዳሙ መነኮሳትና መነኮሳይያት መጽናናትን እንመኛለን።
ምንጭ :- የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
