ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 622 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 362,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 204 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 622 名订阅者。

根据 08 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 67,过去 24 小时变化为 14,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.25%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.62% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 288 次浏览,首日通常累积 721 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 09 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 622
订阅者
+1424 小时
+867 天
+6730 天
帖子存档
ከአሰላ ያገኘነው መረጃ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ምሽት 3:45 አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሚገኘው መንበረ ጵጵስናቸው ተወስደው መታሠራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ሕገ ወጡ ቡድን ሾሜዋለሁ ያለው ግለሰብ በነገው ዕለት እንደሚመጣ የተነገረ ሲሆን በሌሎች ቤተእምነት ተከታዮችን በማስተባበር የአዲሱን ተሿሚ ፎቶ በባነር ለመስቀል ሲሞክሩ ተስተውሏል። በሐረር የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪና በይቅርታ ወደ ሥራው የተመለሰው ግለሰብ ለምዕራብ አርሲ ተሾሟል መባሉ ምእመናኑ አስቆጥቷል። EOTC TV +++++++++++++++++++++++++++++++++++

ልዩ መረጃ! ብፁዕ አቡነ ያሬድ ታሠሩ! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ) ብፁዕ አቡነ ያሬድ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ምሽት 3:45 አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሚገኘው መንበረ ጵጵስናቸው ተወስደው መታሠራቸው ተገለጸ። ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት ማምሻውን ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ ስብከታቸው መድረሳቸውን ተ.ሚ.ማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። በተጨማሪም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ ቤትም መከበቡንና እስካሁን ያለውን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉም ነው ምንጮቻችን የገለጹት። ሕገ ወጡ ቡድን ሾሜዋለሁ ያለው ግለሰብ በነገው ዕለት እንደሚመጣ የተነገረ ቢሆንም ምእመናኑ ሕጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስን ብቻ እንደሚቀበሉም ገልጸዋል። #Ethiopia #Tewahedo_Media_Center #TMC_Addia_Ababa

የእነ አቶ አካለወልድ ሞገስ ሕገወጥ ቡድን የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳምን ለመውረር ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ !!! ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ (ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ) ሕገወጥ ቡድኑ በፔንሲዮን መሽጉ የሰነበተ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በተለያዩ አህጉረ ስብከት የጸጥታ ኃይሎችን ተገን በማድረግ የአህጉረ ስብከት መንበረ ጵጵስናዎችን እየሰበረ ወረራ ሲፈጽም የቆየ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በወለጋ የሚገኙ አራት አህጉረ ስብከት መንበረ ጵጵስናዎችን በወረራ ተቆጣጥሯቸዋል። በተመሳሳይም በነገው ዕለት አቶ አካለ ወልድ ሞገስ ቀድሞ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት የበላይ ጠባቂ ሆነው ሲመሩት የነበረውን የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳምን ለመውረር ዝግጅት ማድረጋቸውን የተ.ሚ.ማ ምንጮች ጠቁመዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ሥርዓት እንዲያስከብር ጥሪ ቢያቀርብም እስከ አሁን ድረስ ከመንግስት የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም። ©ተ.ሚ.ማ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሩስያን ፌዴሬሽን የፓርላማ አባል እና በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሩስያን ፌዴሬሽን የፓርላማ አባል እና በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ በተፈጠረው ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር መፍትሔ ለማግኘትና ሐሳብ ለመለዋወጥ እንዲሁም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አብሮነታቸውንና ድጋፋቸውን ለመግለጽ መሆኑን ገልጸዋል። ©የፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ "የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ! ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።" ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል። በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ

ልዩ መረጃ! በሻሸመኔ ከተማ የሚገኘው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በመንግሥት የጸጥታ አካላት መታሸጉ ተገለጸ። በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በድጋሚ መታሰራቸውን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ሌሎች የሀገረ ስብከት ሰራተኞችም እየተሳደዱ እንደሆነ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሕገ ወጡን ቡድን ተቀበሉ የሚል እንደሆነ ተ.ሚ.ማ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መንግሥት ራሱን ጨምሮ ሌሎች የአደጋ ስጋት ምንጮችን ገምግሞ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን። በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር በአንክሮ ሲከታተል ቆይቷል። ፓርቲያችን በሀገራችን የሚገኙ የዕምነት ተቋማት የማኅበረሰቡን እሴት በመገንባት የሚውስዱት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ያምናል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነች። ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላይ እየተዳደረችበት ባለው ሕገ መንግሥት አንቀፅ 11 ላይ በግልጽ እንደሰፈረው መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው። መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ብሎ ከደነገገው በተቃራኒ የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለው እርምጃ አሳስቦናል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተስተዋሉ ያሉ ጣልቃ ገብነቶች መዘዛቸው ከባድ መሆኑን ተረድቶ በአስቸኳይ ሕግ እና ሥርዓትን አክብሮ እንዲያስከብር እንጠይቃለን። የተለያዩ የፖለቲካ ዓላማ ያነገቡ ግለሰቦችም ሆኑ ሌሎች ቡድኖች በተፈጠረው ችግር ውስጥ የሚያደርጉት ተሳትፎ ችግሩን አባብሰው ደም አፋሳሽ ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ አዝማሚያዎች እየተስተዋሉ በመሆኑ፤ መንግሥት ራሱን ጨምሮ ሌሎች የአደጋ ስጋት ምንጮችን ገምግሞ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን። የሃይማኖት ተቋማት ላይ በማናቸውም ወገን የሚደረግ ጣልቃ ገብነት መዘዙ ብዙ ስለሆነ፤ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን። ፓርቲያችን በተደጋጋሚ እንደሚገልጸው ፖለቲካ በዘር፣ በሃይማኖት፣ እና ሌሎች ልዩነቶች ላይ ሳይሆን ሕዝቡን በእኩልነት በሚያስተሳስረው ዜግነት ላይ ሊሆን እንደሚገባ አሁንም በጽኑ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ድርጊት እንዳስጨነቃቸውና በቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ ሕግ ብቻ መፈታት እንዳለበት እንደሚያምኑ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ገለጹ:: ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደሩ ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት ግንኙነት እንዳላቸውና ለዚህም ጥንካሬ መንፈሳዊ ትስስሩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ባህል እምብርት ናት በማለት የሀገሪቱን ታሪክ ሳይቀር የሰነደች መሆኗንም ጠቅሰዋል። ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ሰዓት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይቀር እውቅና ያገኙበት እንቅስቃሴ ቢኖርም በኢትዮጵያ ታሪክ ግን በቤተ ክርስቲያኗ ለዘመናት የተሠራው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ቤተ ክርስቲያኗን "የአረንጓዴ አሸራ እምብርት" ያደርጋታል ብለዋል። አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን አክለውም በአሁኑ ሰዓትያለችበት ሁኔታ እንዳሳዘናቸውና እንደኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይነታቸውም እንዳስጨንቃቸው ገልጸዋል። ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስቸጋሪ ጊዜ ላይ በሆነችበት ሰዓት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ፓትርያርኳ በኩል ሀዘናቸውን በመግለጽ አጋርነታቸውን ማሳየታቸውን አስታውሰዋል። በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ በርካታ የፈተና ጊዜያት አልፈዋል ያሉት አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ከባድ ጊዜ እንደምታልፈው እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል። አምባሳደሩ በቆይታቸውም ጥያቄ ያነሳው አካልም "አጥቂ" እርምጃ ከመውሰድና ከመገንጠል ይልቅ ቅሬታውን በቀጥታ ለአባቶችና ምእመናን ማሳወቅና በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መሄድ ይገባው ነበር ብለዋል። በቀጣይም በራሷ በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መሰረት በውይይት እንዲፈታ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይቺን ቤተ ክርስቲያን ማፍረስ ማለት ሀገር ማፍረስ በመሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲሉ አጽንዖት የሰጡት አምባሳደሩ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትም እንደቀደመው ጊዜ በመተባበር እንደሚቀጥሉም አሳውቀዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናንንም አንድነታቸውን እንዲያስጠብቁና ይህ ባይሆን በቀጣይ ትውልድ ሁሉ የሚያስጠይቅ ይሆናል "በዚሁ ሂደትም ከጎናችሁ እንደምንቆም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" በማለት መልእክት አስተላልፈዋል። ሙሉ ቃለ መጠይቁን ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን እና የዩቱዩብ ቻናል ይጠብቁን፡፡