ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 381 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 584,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 199

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 381 名订阅者。

根据 03 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 21,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 21.13%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.50% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 250 次浏览,首日通常累积 1 462 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 16

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

凭借高频更新(最新数据采集于 04 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 381
订阅者
-724 小时
+117
+2130
帖子存档
አንኳን ለመስቀለ ኢየሱስ መጋቢት 10 በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ #መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤ ...መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤ ...መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤ ...መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤ በአዲስ አበባ በብቸኝነት(እስከ ቅርብ ጌዜ ድረስ) ከቀድሞ ጀምሮ የመስቀለ ኢየሱስ በዓል በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ክብረ በዓሉ ይከብራል፡፡ በዚሁ ደብር በቀደሙት ዘመናት አገልጋዮች የመድኀኔ ዓለምና የመስቀል አገልጋዮች ተብለው በሁለት ምድብ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ነበሩ፤ ** የመስቀል አገልጋይ ካህናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደመወዛቸው ከቤተ መንግሥት ይይከፈላቸውም ጭምር ነበር፤ ….) በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንተ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡ የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ #ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡ መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ ዕፀ መስቀልም በዓፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ ማርያም፣ ጋራ መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡ * "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ * ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/ ***** እንደተለመደው ሥርዐተ ማኅሌቱንም አቅርበንላችኋል፡፡ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በዋይዜማ፣ በሰርክ ጕባኤ፣ በሰዐታቱ በኪዳኑ፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉና በቅዳሴው እንገናኝ፡፡ (ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታሪክ የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት) Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

#_ለአጥቢያ_ምዕመናን_እና_ወጣቶች_በሙሉ ሰንበት ት/ት ቤታችን ላለፉት 2 ዓመታት በጠየቅነው ቋሚ የማስተማርያ ቦታ ጥያቄ ምክንያት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ገጥሞት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የደብራችንን ሰላም ለማስጠበቅ ፣ ታላቅነቱን ለማስቀጠል በማሰብ ውስጥ ባሉት አባላት ብቻ ሸክሙን ተሸክሞ እዚህ ደርሷል፡፡ ይሁንና ለበርካታ ጊዜያት ጉዳዩን ወደ ምዕመን አለማውጣታችን ያስከፋቸው የደብሩ አስተዳደር አካላት የሰ/ት/ቤቱን አዳራሽ እንዳንማርበት በመቆለፋቸው ሁሉንም የሰ/ት/ቤት አባላት እና የአካባቢ ምእመናንን በእጅጉ አስቆጣ፡፡ ሰላማዊውን ደብር ወዳልተፈለገ ብጥብጥ ውስጥ ከተቱት ፣ በሰ/ት/ቤቱ ላለፉት 55 ዓመታት ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ አዲስ እንግዳ ነገር ተከሰተ፡፡ የሁሉም ሰው ውስጡ ደማ ፣ እናቶች መድኃኔዓለም ፍትህ እንዲሰጥ ደብሩ ወደቀደመ ሰላሙ እንዲመለስ በእንባ ጠየቁ ፣ ሐገረ ስብከት ድረስ በእግር በመሄድ ስለ እውነት ጮሁ…. ነገር ግን በሚደንቅ ሁኔታ ይህ ሁሉ እንዳይከሰት ሰ/ት/ቤቱ አስተዳደር አካላትን ለመነ….በስራ አመራር ጉባኤ ፣ በመማክርት ጉባኤ ፣ በየክፍሉ ባሉ አባላት ተለመኑ…ፖሊስ ባለበት ለበርካታ ጊዜያት በርካታ ውይይቶች ተካሄዱ…ግን ሰሚ የለም…አሁን ጥያቄው የሰንበት ተማሪው መሆኑ አልፎ የአጥቢያ ምዕመናን ፣ ወጣቶች ፣ የሌሎች ሰንበት ት/ት ቤቶች ጥያቄ ሆነ …. በማኅበራዊ ድህረ ገጾች የተለያዩ ጽሑፎች መለቀቅ ጀምረዋል፡፡ ቢሆንም ግን አሁንም ሰ/ት/ቤቱ ጥያቄው ከግለሰቦች ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ ጥያቄው ተቋማዊ ነው፡፡ መልሱም ተቋማዊ ነው፡፡ እገሌ እንዲህ አደረገ ብለን ስም ጠቅሰን አንነቅፍም ፡፡ ጉዳያችንም አይደለም ፡፡ በበርካታ ሰዎች የተመሰከረለት ሰላማዊ ሰንበት ት/ት ቤት ነው፡፡ ልጆቼን የማስተምርበት አዳራሽ ሲፈርስብኝ ሌላ ተለዋጭ ቦታ ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ ብቻ ነው ጉዳያችን ፡፡ ይህ ጥያቄ ደግሞ ትክክለኛ መልስ እስኪያገኝ ድረስ ይቀጥላል፡፡ በቅርቡ ብጹእነታቸው ለዚህ ጉዳይ እልባት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን ክፉ ተናግረው ክፉ ከሚያናግሩ ሰዎች መጠበቅ መቻል አለብን …. ሰዎች ያሉትን ይበሉ እኛ ግን መድኃኔዓለምን ይዘን ወንጌልን ከአጥቢያችን አልፈን ለሀገራችን ፣ ከሀገራችን አልፈን ለአለማችን እናዳርሳለን ወንጌሉም የሚለው ይኸው ነውና #_‹‹_ሑሩ_ወመሐሩ…›› ዲ/ን ታምራት ሙሉነህ የሰ/ት/ቤቱ ሊቀ መንበር

#ቅድስት፤ #ሁለተኛው_የዐቢይ_ጾም_ሳምንት ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ #share ፠ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡ ፠ ‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡ ፠ ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡ ፠በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_ክብር፤ 1. በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8 2. በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡ 3. ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡ ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና›› ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ መጋቢት ፭ በዓለ ዕረፍት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #share አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)  ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ *ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ *ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡ ፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል) ፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ (ሥርዐተ ማኅሌቱን የኢንተርኔት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች አድርሱልን፤ በተለይም ወደ ምድረ ከብድ፥ ዝቋላ፥ ገዛዛ አቦና ሌሎች የአባታችን ክብረ በዓል በሚከበርባቸው አድባራትና ገዳማት ያላችሁ አድርሱልን፡፡) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem #share

አፍንጫ ሲነካ አይን እነደሚያለቅስ ሁሉ ፤በሶሻል ሚዲያ ገጻቹ፤ ከጎናችን መሆናችሁን ላሳያችሁን ለአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ምስጋናችን እጅግ የላቀ ነው(፡፡ፍቁረ እግዚእ ፣ ደብረ ሲና ፣ ገነተ ጽጌ )
+2
አፍንጫ ሲነካ አይን እነደሚያለቅስ ሁሉ ፤በሶሻል ሚዲያ ገጻቹ፤ ከጎናችን መሆናችሁን ላሳያችሁን ለአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ምስጋናችን እጅግ የላቀ ነው(፡፡ፍቁረ እግዚእ ፣ ደብረ ሲና ፣ ገነተ ጽጌ ) ፡፡ በአካል በመገኝትም(ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ ፣ ደብረ ሲና ፣ ገነተ ጽጌ ፣ደብረ ታቦር ) አብራችሁን ላደረጋችሁት አስተዋጾ እግዚአብሔር ይከፈላችሁ እያል ይህንን ችግር ቋጭተን እንደኛ አይነት ችግር ላለባችው አብያተ ክርስቲያኖች እርዳታችንን እንድናደርስ መልካም ሞኞታችን ነው ፡፡