Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 381 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 584,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 199 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 381 名订阅者。
根据 03 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 21,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 21.13%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.50% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 250 次浏览,首日通常累积 1 462 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 16。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 04 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 381
订阅者
-724 小时
+117 天
+2130 天
帖子存档
የዐቢይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት
#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ
ጾም ማለት፤
፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።
፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።
፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤
፠ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤
፠ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤
፠ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤
፠ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤
፠ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ ምሳሌ ከጭፈራ ወይም ዳንኪራ ቤቶች)፤
….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም።
ዐቢይ ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው።
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤
፩ኛ. #ዘወረደ_ይባላል፤
‹‹ #ሃሌ_ሃሌ_ሉያ_ዘወረደ_እምላዕሉ_አይሁድ_ሰቀሉ፤
#ወሚመ_ኢያእመሩ፤
#እግዚአ_ኵሉ_ዘየሐዩ_በቃሉ፡፡››
‹‹ #ዘወረደ_እምላዕሉ_እመልዕልተ_ኵሉ››፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/
፪ኛ. #ጾመ_ሕርቃል_ይባላል፡፡
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው፤ እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
፫ኛ. #ሙሴኒ
የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ.4፥1-4/፡፡
Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem

40 sew becha kere
Gone legone ande lay share wanawn channel
በሰንበት ት/ቤቱን #ዋና የቴሌግራም ቻናል #ከመንሰጠው_አገልግሎት በተጨማሪ #ለተለያዩ_ጉዳዩች ይረዳን ዘነድ፤ የስንበት ት/ቤቱን #ዋና የቴሌግራም ቻናል ያልተቀላቀልን በመቀላቀል ለሌችም ሼር በማድረግ ዛሬን በቻ #ከ_100 _ሰዎች_በላይ እናጋራ፣እናቀላቅል፡፡ ነገም እንቀጥላለን ፡፡
ሊንኩ ይኸው .. https://t.me/medihanaelem ኮፒ በማድርግ ሁላችም በየደቂቃው እናጋራ
የተወሰኑ ውሳኔዎች ይፈጸሙ፡፡
#ፍትህ ለፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት
#ዛሬን_ብቻ_100 ሰዎች #share #share
https://t.me/medihanaelem
ፍትሕ ለፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት
የተወሰኑ ውሳኔዎች ይፈጸሙ
ፍትህ ለቤተክርስቲያንናችን፡፡
ፍትህ ለቤተክርስቲያንናችን
ፍትሕ ለፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት
የተወሰኑ ውሳኔዎች ይፈጸሙ
፡፡
#Share የማያደርግ ሰው እንዳይኖር
በትላንትው ዕለት (26/06/2013) ዓርብ ጕባኤ ልናካሂድ ስንል በአስተዳዳሪው ትዕዛዝ አዳራሻችን ተቆልፎ ማግኘታችን ይታውቃል ፡፡ይህንንም አስከትሎ ዛሬ በ 27 / 06 / 2013 ዓ.ም ጠዋት በዓውደ ምሕርት ላይ ምእመናን የማንቃት ስራ ተሰርቷል ፡፡ ቢዚህም ብዙ ምእመናን ጉዳዩን የሚያውቁት መሆኑን እና ከእኛ ጋር መሆናቸውን አረጋግጠናል ያማያወቁትም እጅግ መሪር ሃዘንን በማዘን ፣ ዕንባቸውንም በማፍሰስ እዛው በጸሎት እንዳሰቡን ፣ ደብራችንን እንዳሰቧት እና ከእኛ ጋር እንደሆኑም ጭምር በድጋሚ አውቀናል ፡፡የማንቃት ስራው እንዳይሰራ ግብ ግብ የፈጠሩ ብዙዎች ሲሆኑ በሰላም እንዲያልቅ ለረዱን ደግሞ ምስጋናችን የላቅ ነው፡፡
#Share የማያደርግ ሰው እንዳይኖር
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሁን ፡፡
telegram : https://t.me/medihanaelem
በሰንበት ት/ቤቱን #ዋና የቴሌግራም ቻናል #ከመንሰጠው_አገልግሎት በተጨማሪ #ለተለያዩ_ጉዳዩች ይረዳን ዘነድ፤ የስንበት ት/ቤቱን #ዋና የቴሌግራም ቻናል ያልተቀላቀልን በመቀላቀል ለሌችም ሼር በማድረግ ዛሬን በቻ #ከ_1500 _ሰዎች_በላይ እናጋራ፣እናቀላቅል፡፡ ነገም እንቀጥላለን ፡፡
ሊንኩ ይኸው .. https://t.me/medihanaelem ኮፒ በማድርግ ሁላችም በየደቂቃው እናጋራ
የተወሰኑ ውሳኔዎች ይፈጸሙ፡፡
#ፍትህ ለፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት
#ዛሬን_ብቻ_1500 ሰዎች #share #share
https://t.me/medihanaelem
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 