Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 041 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 280,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 239 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 041 名订阅者。
根据 28 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 512,过去 24 小时变化为 -6,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.18%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.37% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 039 次浏览,首日通常累积 1 663 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 30。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 29 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 041
订阅者
-624 小时
+917 天
+51230 天
帖子存档
13-ዘካርያስ ርዕየ.amr1.38 KB
12-ሙሴኒ ርዕያ.amr0.58 KB
11-ጽላት ዘሙሴ.amr1.00 KB
10-ታቦተ ሕጉ.amr0.49 KB
09-አንሶሱ.amr0.96 KB
08-ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን.amr0.85 KB
07-አብርሂ ጽዮን.amr0.61 KB
06-ሃሌሉያ ብሔረ ሮሜ.amr0.87 KB
5_6_2፤_ማርያም_ጽዮን_ታቦተ_ኃይለ_መለኮት_ወምኒልክ.MP33.62 MB
05-ማርያም ጽዮን.amr0.49 KB
04-ሃሌ ሃሌሉያ.amr0.68 KB
03-ታቦተ ሕጉ.amr0.92 KB
02-እንተ ክርስቶስ.amr0.83 KB
01-ወይቤላ ኢትሬዕይኑ.amr1.01 KB
#የኅዳር_ጽዮን_ምልጣንና_እስመ_ወረቦች::
#እንኳን_ለኅዳር_21_ታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_አደረሰን_አደረሳችሁ፡፡
ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/
#ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_፤
፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6)
፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23)
፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/
፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/
፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....)
፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡
፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡
፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡
፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡
#ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_፤
፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤
✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስTጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት) በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/
፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች
✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤
✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/
………
**** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤
«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤
ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡
ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/
በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡
#የኅዳር_ጽዮን_ወረቦችን_በዚህ_በቴሌግራም_አድራሻችን_ያገኛሉ_፤ https://t.me/medihanaelem
#ለኅዳር_ጽዮን_ጕዞ_ወደ_መጠቆሚያ_ማርያም_፡፡
(የሰ/ትቤታችን አባላት፣ 30 የሚጠጉ የሰ/ትቤት ተዋካዮች፣ የአጥቢያችን ምዕመናንና ሕዝበ ክርስቲያንን በአንድነት የሚያሳትፍ ጕዞ)
፠የጕዞ ቀናት፤ ቅዳሜና እኁድ (ከኅዳር 20-21) 2012 ዓ.ም.
፠ለመመዝገብ፤ የሰ/ትቤታችን ልማት ክፍል፣ ትምህርት ክፍል ወይም መዝሙርና ኪነ ጥበባት ክፍል እንዲሁም
በ0910 61 72 58 ወይም 0902 50 39 54 ብለው ይደውሉ፡፡
፠የጕዞ ዋጋ፤ 250 ብር (ምግብን ጨምሮ)
፠የመመዝገቢያ ቀናት፤ እስከ ኅዳር 19/2012 ዓ.ም.
/የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/
፨፨፨ #በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ፤
✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም (ከክርስቶስ ልደት 980 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን ታቦቷ የመጣው)
✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም (በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተመሠረተች)
✣ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም (ደቡብ ሸዋ)
✣ሳዶቅ አምባ ማርያም (በ1670 ዓ.ም. በአባ ሳዶቅ የተመሠረተች ፥ ሰሜን ተራሮች)
✣እንፍራንዝ ደብረ ጽዮን ማርያም (ጥንታዊዋ ደብር)
✣ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም (በወርቅና በዕንቊ ተደርጋ በራስ ውቤ የታነጸች፤ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠባት፤ ስሜን፣ ራስ ደጀን አጠገብ)
✣ ደብረ ጽዮን ማርያም (ነቀምት)
✣ ደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም (ባሕርዳር)
✣ አርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ማርያም
✣ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ማርያም (እንግሊዝ ፥ ለንደን)
በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡
በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem
፨፨፨ #በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ፤
