ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 047 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 280,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 239 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 047 名订阅者。

根据 27 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 518,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 24.70%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.29% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 963 次浏览,首日通常累积 1 651 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 29。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 28 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

16 047
订阅者
无数据24 小时
+987 天
+51830 天
帖子存档
ጕባኤ ደቂቀ አበው ፱፤ ‹‹#ነገረ_ማርያም_ዘቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ_፡፡›› ጥር 3/2012 ዓ.ም. በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ጥናት አቅራቢ፤ መምህር ግርማ ባቱ (የ
+2
ጕባኤ ደቂቀ አበው ፱፤ ‹‹#ነገረ_ማርያም_ዘቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ_፡፡›› ጥር 3/2012 ዓ.ም. በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ጥናት አቅራቢ፤ መምህር ግርማ ባቱ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር)፡፡

* 200 ቋድ (ኩብ መስሎ የተሠራና አንገት ላይ የሚነገት * 200 ሻሽ * 200 የውጭ ሀገር መሐረብ በድምሩ ለ1ድ ሰው ልብስ 60ብር የፈጀ አሠርተው፤ 100ውን ልብስ በአቶ አፈወርቅ ላንድሮቨር መኪና፤ 100ውን ደግሞ ሀብታሙ ዘውዴ በአውሮፕላን አስጭኖ በ19620ዓ.ም. ከልደት በዓል ከ3 ቀን በፊት ላልይበላ ደረሱ፡፡ የላልይበላ አለቃ፣ የ10ሩ መቅደስ ገበዝ (መሪጌቶች) በተሰባሰቡበት፤ እስከሚያደርስ ድረስ ብዙ ጊዜ አግልግሎት ለሚሰጡ፣ የተማሩና በአጋፋሪው እየተመረጡ ማሚ ጋራ ጋር ወጥተው ለሚያስረግጡ ደባትር ይሰጥ ላልደረሰው ለሚቀጥለው ዓመት እናመጣለን ብለው ተሰጠ፡፡ ‹‹#የተሰደደ_ዘመድ_ያለው_ለበሰ ፥ #የሌለው_ሳይለብስ_ቀረ›› 200 ሙሉ ልብስ ለ10ሩ መቅደስ መደበኛ አግልጋዮችና ማሚ ጋራ ለሚወጡ ሲታደል ከአ.አ. በኮሚቴት ለመጡ ለእነ መዘምር ሐኪም ማሞ. ለእነ አፈወርቅም ተሰጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ከ40 የማያንሱ ደባትር ሳይደርሳቸው ቀረ፤ በተለይም 2ቱ ደባትር (አለቃ ባዬ አለሙና መጋቤ ቢሰጥ ዘአሸተንና የደብረ ሮሐ መጋቢ ሊቆችና ባለቅኔዎች ስለሆኑ) ልብሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ በመሆኑ ከፍቷቸው ኖሮ፤ የልደት ክብረ በዓል ማሚ ጋራ ላይ ባለ ቀይ ጃኖ የለበሱ ከፊት ሲሰለፉ እነርሱ ግን የቀድሞ ሸማን በመልበሳቸው ከኋላ በመሰለፋቸው እንዲህ ብለው በቅኔ ተናገሩ፤ አለቃ ባየ አለሙ፤ ‹‹እንደ ፍየል ቆዳ ተፈየድን (ወደቅን፤ ልብሱ ሳሰጠን ቀረ፡፡ የተበላሸ ይወድቃልና)፡፡›› መጋቤ ቢሰጥ ‹‹የተሰደደ ዘመድ ያለው ለበሰ ፥ የተሰደደ ዘመድ የሌለን (አጥተን) ሳንለብስ ቀረን፤ ብለው ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡ በዓመቱ ግን ለ60 ሰዎች ሙሉ ልብሱ ከ2ቱ ባለቅኔ ምሁራን ጭምር ደረሰ፡፡ ልዩ ማስታወሻ፤ በቅዱስ ላሊበላ በ1962ና 63 ዓ.ም. የተሠራውና 50 ዓመታት ያስቈጠረው ጃኖ ሙሉ ልብስ ብዛቱ 260 ነው፡፡ #ማሚ_ጋራ፤ #ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም፡፡ ማሚ ጋራ ከ10ሩ ቤተ መቅደሶች በቤ ማርያም በስተምዕራብ በቅኔ ማኅሌቱ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን፡፡ መላእክትና ኖሎት ተብሎ ይጠራል፡፡ ከላይ ከተራራው ላይ ጃኖ ለብሰው የሚያስረግጡበት፤ (ማሚ ጋራው) መላእክት ሲባል፤ ከታች መሬት ላይ እየሰገዱ የሚያስረግጡበት ደግሞ፤ ኖሎት ይባላል፡፡ ቤዛ ኵሉ ዓለም እየተባለ ከላይና ከታች በቅብብሎሽ ነው የሚባለው፡፡ ማሚ ጋራ ላይ ለልደት ወጥቶ የሚያስረግጥ፤ የከበሮ አመታቱና የማስረገጡ ሂደቱ ለየት ያለ ስለሆነ የላሊበላን ቀለም ከልጅነቱ ጀምሮ ያልተማረ ከሆነ ስለሚከብደው ከሌላ አካባቢ የመጣ ሊቅም ቢሆን በሥርዐተ ማኅሌቱ አገልግሎት ላይ ይሳተፋል እንጂ ከማሚ ጋራው ላይ አይወጣም፡፡ ይኸውም በጌታችን በመድኀኔ ዓለም መወለድ ሰውና (እረኞችና) መላእክት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰለማ በምድር ስምረቱ ለሰብእ›› እያሉ የማመስገናቸው ምሳሌ ነው፡፡ (ወደ ቅዱሳ ላለበላ የሄዳችሁ እንደምታውቁት ቅዱስ ላሊበላ ውሃ መውረጃው ሳይቀር በምሳሌነት የተሠራ፤ ዕፁብ ዕፁንብ የሚያስበል ነው፡፡) ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተመረጠ በኋላ በግንባር ቀደምትንት ለማሚ ጋራ ተሰላፊ የሚዋደዱት ጓደኛማቾች መዘምር ሐኪም ማሞና … አፈወርቅ ተመርጠዋል፡፡ መዘምር ሐኪም ማሞ ሃገራቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግሉ ከርመው፤ በሰለምና በጤና ‹‹እንበለ ደዌ ወሕማም›› (ያለ በሽታና ያለ ሕማማ) በ106 ዓመታቸው ሰኔ 16/20111 ዓ.ም. አርፈዋል፤ ሥርዐተ ግብዐተ መሬቱም ከ72 ዓመታት በላይ ባገለገሉበትና በኖሩበታ በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም በቤተ ልሔም ቅጽር ግቢ ውስጥ ከአበው መቃብር አጠገብ አርፈዋል፡፡ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ነፍሳቸውን ከደጋጎቹ ከነቅዱስ ላሊበላ ካሉበት ጋር ይደምርልን፤፡፡ /ታሪኩን የነገሩን ከ1942 ዓ.ም. እስከ 2011 ዓ.ም. ለ70 ዓመታት ድረስ እንደ ወንድም ጭምር የቅርብ ጓደኛቸው የሆኑት ሊቀ ካህናት አፈወርቅ መኮንን፣ እና የኔታ ሙሴ ዘደብረ ሰላም ናቸው፡፡/ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#መዘምር_ሐኪም_ማሞ_ገዛኸኝ፤ #የታላቁ_ደብር_ታላቁ_መዘምር፡፡ (ያረፉት ሰኔ 16 ነው፤ ነገር ግን በሰኔ 15ቱ የባሕር ዳር የባለሥልጣናት ሞት ምክንያት ወቅቱ በሀገራችን ኔትወርክ ስላልነበር ሳንዘግብ በመቅረታችን ይቅርታ እየጠየቅን፤ የ6ወር መታሰቢያ ላይ በወርኀ ታኅሣሥ ዘገብነው፡፡) ፠ #ከ72 #ዓመታት_በላይ_ታላቁን_ደብር_ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔ_ዓለምን_በመዘምርነት_በነጻ_ያገለገሉ፤ ፠ #የ101 #ዓመታት_የዕድሜ_ባለጸጋ፡፡ ፠ ከልጅነት እስከ ዕርግና በነጻ ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉ፤ በልጅነትና በወጣትነት ዘመናቸው በቅዱስ ላሊበላ በቤተ ጎልጎታ በዲቁና ፤ ከ1930ዎቹ እስከ 2011 ዓ.ም. በቀጨኔ ደብረ ሰላም በመዘመርነት በነጻ ያገለግሉ፡፡ ፠ ያገለገሉት አምላካችን መድኀኔ ዓለምም በዕድሜ (101 ዓመታትን)፤ በልጆች (13 ልጅ፤ 26 የልጅ ልጅ) ወልደው፤ በጤና (እስከ በዓለ ዕረፍታቸው አቅራቢያ ድረስ ማኅሌት በመቆም እያገለገሉ) በሰላምና በጤና ያረፉ፤ ፠ ደወል ተደውሎ ፥ ‹‹ስቡሕ..›› ተብሎ ማኅሌት ሲጀመር ከሌሎች በነጻ እንደርሳቸው በርካታ ዘመናትን እያገለገሉ ከሚገኙ ጓደኞቻቸው ጋር በሰዐቱ ተገኝተው ማኅሌቱን የሚያደምቁ ናቸው፡፡ (ከሌሎች አድባራት በተለየ ሁኔታ ቀጨኔ ላይ ገና ማኅሌቱ እንደተጀመረ በቀኝ ክንፍ ቆመው ደማቅ እንዲሆን የሚያደርጉ አበው ናቸው) ፤ እርሳቸው በማረፋቸውም በዘንድሮ የ2012 ዓመት የጽጌ ማኅሌት በቀኝ ክፍል ቀዝቅዞ ነበር ያለፈው፡፡ ፠ በሐኪምነት ሙያቸው ሕመም የሚያጋጥማቸውን ካህናት የካህናት ደመወዝ አነስተኛ በመሆኑ እቤታቸው ድረስ በመሄድ በነጻ ሕክምና የሚያደርጉ አባት፤ ፠ #በቅዱስ_ላሊበላ_ማማ_በልደት_ክብረ_በዓል_ላይ_የሚለበሰውን_ለ260_ደባትር_መዘምራን_ቀይ_ጃኖና_ተጓዳኝ_አልባሳት_ከሌሎች_ኮሚቴዎች_ጋር_በመሆን_ከ50_ዓመታት_በፊት_በ1962_ዓ.ም. አሠርተው ያበረከቱ፤ ፠ ከበሮ ሲመቱና በቅዱስ ላሊበላ ማሜ ጋራ ላይ ሲያስረግጡ ልብን የሚመስጡ አባት፤ ፠ ተወልድው ላደጉበት ለቅዱስ ላላበላና በላስታ ለሚገኙ የተለያዩ አድባራትን በልዩ ልዩ ነገሮች ሲያገለግሉ የነበሩ፤ #ልደት_ዕደገትና_ትምህርት፤ በ1910 ዓ.ም. በወሎ ፥ ላስታ ላሊበላ ደንጎባት ላይ ማዶ ቅፋፍ ላይ፤ ከአባታቸው ከአቶ ገዛኸኝ ገፊና ከእናታቸው ከእማሆይ እታገኘሁ ለየኸኝ ተወልደው፤ በቅዱስ ላልይበላ ከተማ በ7 ወይራ ሰፈር አደጉ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን የዲቁና ትምህርት በአካባቢው ከነበረው ቅዱስ ላልይበላ ካነፃቸው አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ከሆነው በቤተ ጎልጎታ በሚገባ ከቀሰሙ በኋላ ዲቁናን ተቀብለው በዚያው በተማሩበት ደብር በቤተ ጎግሎታ በዲቁና ሲያገለግሉ አድገዋል፡፡ ለትምህርት ካላቸው ፍቅርና ትጋት የተነሣም በጎንደርና በጎጃም እየተዘዋወሩ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንደ ንህብ ቀስመዋል፡፡ ከዚያም ወደ ትውልድ ሀገራቸው ወደ ላሊበላ በመመለስ ዘመናዊ ትምህርት ተምረዋል፡፡ #ሥራ፤ *ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በቀድሞው ‹‹ክቡር ዘበኛ›› በመቀጠር በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ አገልግለዋል፡፡ *በመቀጠልም ወደ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር በመዛወር የሕክምና ትምህርት በመማር በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ *በተማሩት የሐኪምነት ዘርፍም በራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታልና በትምህርት ሚንስቴር ሥር ባሉ የተለያዩ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሕክምና አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ በአገራችን በነበረው የሱማሌ ወረራ ወቅትም ከሠራዊቱ ጋር አብረው በመዝመት በሙያቸው በሐኪምነት ለሃገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ አስተዋጽዖን አድርገዋል፡፡ *በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም አጥቢያ ችሎት በሚባል አካባቢ ትዳር መሥርተው፥ ቤት ሠርተው፥ 13ት ልጆችን (6ት ወንዶችንና 7ት ልጆችን) ወልደው፥ 26ት የልጅ ልጆችን ስመው፤ በክርስትና ሕይወታቸው ታማኝና ቅን ሆነው ያስተማረቻቸውን እናት ቤተ ክርስቲያን ባለመርትና ባለመዘንጋት ከ1930ዎቹ እስከ 2011 ዓ.ም. ድረስ ‹‹ዘነሣዕክሙ በጸጋ ፥ ሀቡ በጸጋ›› የሚለውን የጌታ ቃል ቀድሞም በልጅነታቸው በቤተ ጎልግታ በነጻ ሲያገልግሉ እንዳደጉት ሁሉ ከ72 ዓመታት በላይ በነጻ በመዘምርነት በቅኔ ማኅሌቱ በቀኝ ክንፍ አገልግለዋል፡፡ *በ1942 ዓ.ም. በላላበላ የልደት በዓል ላይ በሥርዐተ ማኅሌት ቁመት ላይ የተዋወቋቸውና የቅርብ ጓደኛ (እንደ ወንድም የሚዋደዱት) ሊቀ ካህናት አፈወርቅ መኮንን ከመንግሥት ተሹመው በአውርፕላን አብራሪ እጅ ደብዳቤ ተልኮላቸው የአ.አ.አ የመናገሻ አራዳ ገነተ ጽጌ ፀሐፊና መዝገብ ሹም ሆነው ሚያዝያ 29/1959 ዓ.ም. መጡ፤ ነገር ግን ደብሩ በ40 ዓመታት ውስጥ በባንክ ያስቀመጠው ገንዘብ 44 ሺህ ብር ብቻ ነበር የተረከቡት፤ አዲስ የመጡትም ፀሐፊ ከግንቦት 1 እስከ ጳጕሜን 3 (በ4 ወር ከ3 ቀናት ውስጥ) ለደብሩ 105 ሺህ ብር ገቢ አደረጉ፤ ይህም ዜና በታዋቂው ጋዜጣ በመርስዔ ኀዝ አበባ ዘገቢነት ሲዘገብ አብዛኛውን ሕዝብ ጉድ አሰኘ፤ በአዲስ አበባ ያሉ የላስታ ላሊበላ ተወላጆችም ከፓርላማ ተመራጮች ከእነ ቀኛ አዝማች አበራ ጀምሮ መጥተው ደስታቸውን ገለጹ፡፡ መዘምር ሐኪም ማሞም ጓደኛቸውን በቅርብ ማግኘት ቻሉ፡፡ ታዲያ ይህ ወዳጅነታቸው ጠንክሮ ከ3ት ዓመታት በኋላ በ1962 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ የቅዱስ ላሊበላ ተወላጆች ተሰባስበው ‹‹ለቤዛ ኵሉ ዓለም›› ክብረ በዓል ምን እናድርግ የሚል ኅብረትን ፈጠረ፤ ይህም ኅበርት በርካት ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ለአብነትም ዋነኞቹ፤ 1ኛ) በየዓመቱ ከአ.አ. ወደ ቅዱስ ላሊበላ የሚወርዱ ተወላጆች የቤዛ ኵሉ ዓለም ይትበሃልን፤ ከታላቁ ምሁርና የታላቁ ደብር የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም የድጓ መምህር ከሆኑት ከመሪጌታ ይኄይስ ለ5 ወራት ጥናት አካሂዶ በላሊበላ የልደት ቀን አብሮ የሚሠለፍ ሁኗል፡፡ 2ኛ) ከቅዱሱ ላሊበላ ጀምሮ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ክብረ በዓል የሚለበሰው የሸማ ልብስ በማርጀቱ ሙሉ ልብስ ለማሠራት ተስማሙ፤ ይህንንም ኅብረት የሚያስተባበሩ ሰዎች ተመርጠው ወደ ሥራ ተገባ፡፡ እነርሱም፤ *መሪጌታ ይኄይስ ያለው፤ የኮሚቴ ሊቀ መንበር፤ የታላቁ ደብር የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም የድጓ መምህር *ሀብተ ወልድ መኰንን፤ ካህንና በተለያዩ ቦታዎች (በመርሐ ቤቴ፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ) የአውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ፤ *ሀብታሙ ዘውዴ፤ ካህንና በተለያዩ ቦታዎች የአውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ፤ *ወዳጅ ክብረት፤ የብርሃንና ሰላማ ማተሚያ ቤት መዘገብ ሹም፤ *ወረደ ቃል፤ መምሬ ይትባረክ፤ መኳንንት አበራ፤ ክህነት ሲሳይ፤ ... እንዲሁም በዋነኛነት ሥራውን በቅርብ እንዲያስተባብሩና እንዲመሩ እንደ ወንድም የሚዋደዱትን *ሊቀ ካህናት አፈወርቅ መኰንን *መዘምር ሐኪም ማሞ ገዛኸኝ በመሆን ነበር፡፡ #ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም_ላይ_የሚለበሰው_ልብስ_ጥንተ_ታሪክ_፤ ቅዱስ ላሊበላ ሕንፃውን አንፆ 9ኙን ደብተራ በቤተ ክርስቲያኑ ትክለኛ አድርጎ ሲሾም የ9ኙን ደባትር ቤተሰብና ቦታዋን ለቅዱስ ላሊበላ ሕንፃ መሥሪያ የሰጠችውን የቀ… ቤተስብ ሸማውን እንዲለብስ ሥርዐተ ሠርቶ ስለነበር ከትውልድ ወደ ትውልድ በዚሁ መልክ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ በ1962 ዓ.ም. ከላይ የጠቀስናቸው ኮሚቴዎች ለ200 ማኅሌታውያን (መዘምራን) ለ10ሩ ቤተ መቅደስ አገልጋዮች፤ ጃኖ (ጥንግ ድርብ የሆነና በቀይ ክር በልዩ አሠራር፥ ቀለሙ የማይለቅ፥ በጠንካራ ማግና ክር አ.አ. ዶርዜ ሰፈር የተሠራ)፤ በወቅቱ ከ20-30ብር የተሠራ፡፡ * 200 እጀ ጠባብ * 200 ሱሪ * 200 ነጭ ሐር ሱሪ

#አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና_፤ #ታኅሣሥ 29 ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር ከተባበረላቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ፠ #የበረሃው_ዕንቊ_ገዳም_መንበረ_ልዑል_ጽርሐ_አርያም_ደብረ_መጕናን_የመሠረቱ፡፡ ፠ አብርሃም ቅድስት ሥላሴን እንዳስተናገደ፤ #አቡነ_አብሳዲ_ደግሞ_ጌታችንን_ተቀብለው_እግሩን_ያጠቡ_ናቸው፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ፠ #ደቀ_መዛሙርቶቻቸው_በተሰየፉበት_አንገረብ_ወንዝ_ላይ_ #44ት #የፍል_ውኃ_ፈዋሽ_ጠበል_አንገረብ_የሚባል_ያላቸው፤ በሃገራችን ብዙሃን ሕዝብ ከሚጠመቅባቸው ጠበሎች ዋነኛው ከተጠማቂው ሕዝብ ብዛት የተነሣ #ቀንና_ሌሊት_ጥምቀት_የሚካሄድበት፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ፠ ከብቃታቸው የተነሣ ወደ ላይ ጽርሐ አርያምን ወደ ታች በርባሮስ ድረስ የሚደረገውን የሚመለከቱ፤ ፠ #ወላዴ_አእላፍ ፥ #ወላዴ_ቅዱሳን_ሊቃውንት፥ #አበ_ብዙኃን፥ #ወላዴ_ሰማዕታት የሆኑ፤ ፠ በፀሐይ ሰረገላ፥ በብርሃን መንኰራኵር እየተጫኑ እንደ ሐዋርያት የሚያስተምሩት፤ ፠ 470 ዓመታትን የኖሩት፡፡ ፠ ታኅሣሥ 29 የጌታችንና,ን የጻድቁን የልደት በዓል፤ ሙሉ አርማጭሆ እንዲሁም የትክል ድንጋይ፣ የዳንሻና አካባቢው ምዕመናን በ10ሺዎች የሚቈጠር ሕዝብ የሚያከብርላቸው፡፡ * ምንኵስናን የተቀበሉት ከአቡነ ዮሐንስ ከማ ነው፡፡ * በማንዳባ ገዳም ከ7ቱ ከዋክብትና ከ7ቱ ከዋክብተ ጣና አንዱ ከኾኑትና ደንጊያን እንደ ጀልባ ከሚጠቀሙት ከአቡነ ያሳይ ጋር ብዙ የጽድቅ ሥራና የትሩፋት ተጋድሎን ፈጽመዋል፡፡ * ቀድሞ በኤርታ ደብረ ማርያም ነበር የሚኖሩት፤ ኋላ ታቦተ ማኅበረ በኵርንና ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ይዘው ብዙ ቅዱሳንን ወዳፈለቁበት መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋበት ወደነበረው ገዳመ መጕና መጡ፤ ገዳሙ የሚገኘውም በጎንደር ታች አርማጭሆ ነው፡፡ ‹‹በሬ ሜዳ›› የሚባለው ቦታ ላይ የጌታችን ልደትና የጻድቁ ልደት ዝክር የሚዘከርበት ምርፋቅ ነው፡፡ ጻድቁ የተጓዙባቸው ምዕራፋት ከቁርባኔ ወንዝ እስከ መታጠቂያ በር 13ት ሲሆኑ የ13ቱ ሕማማት ምሳሌ ሲሆኑ፤ የመታጠቂያ በር ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ በ1407 ዓ.ም. በአፄ ይስሐቅ ዘመን ‹‹ዳሩ እሳት ፥ መሐሉ ገነት፡፡›› ተብሎ ተገድሟል፡፡ ወላዴ አእላፍ አበ ብዙኃን ዐምዳ ወብርሃና ለደብረ መጒና በቆብ የወለዷቸው በርካታ ቅዱሳን ቢኖርም፤ #ገዳማትን_የመሠረቱ_ለአብነት_ዋናዎቹ_፤ ፠ #አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ ሥልጣነ ክርስቶስ (አመራ ቊስቋም ገዳምን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ልብሰ_ክርስቶስ_ (ዳውጨና አማኑኤል ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ ማቴዎስ (ያይራ ተክለ ሃይማኖት ገዳምን የመሠቱ) ፠ #አቡነ_ዮሐንስ_ዘመረባ (ጊዮርጊስ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ ሰማዕቱ አቡነ ጽጌ ድንግል (እንኮ ድብ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ዘወልደ_ዳዊት (ጐረፍ ተክለ ሃይማኖትን የመሠረቱ) ፠ አቡነ መቅደሰ ክርስቶስ (ሳይኮ ኪዳነ ምሕረትን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ህላዌ_ክርስቶስ (አምስትያ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ ተላዌ ክርስቶስ ( ገዳምን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ከናፍረ_ክርስቶስ (ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ የማነ ክርስቶስ (ገው ጊዮርጊስን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ዕደ_ክርሰቶስ (የኢትዮጵያና የግብፅ ሐዋርያ ፥ የደብረ መጕና 3ኛ መምህር /አበምኔት/) ፠ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ (በትግራይ ገዳምን የመሠረቱ፤ ልደታቸው ከአባታቸው ጋር በታኅሣሥ 29 የተባበረላቸው) ፠ #ሰማዕቱና_በአባታቸው_ወንበር_የተተኩት_አቡነ_አምኀ_ጊዮርጊስ፡፡ (የደብረ መጕና 2ኛው መምህረ /አበምኔት/) ሲሆኑ፤ #ቅዱሳን_ደራስያን_ሊቃውንት_ከሆኑት_መካከል_ለአብነት_፤ ፠ #አባ_ገብረ_ኢየሱስ_ (የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ) ፠ #እጨጌ_በትረ_ጊዮርጊስ_ (በአፄ ፋሲል ዘመን የኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጕባኤ የነበሩና የቅባት ሃይማኖት መሪዎች እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን የረቱ …. በዚህም ሊቃነታቸው በዐይኑ ያየ ባለቅኔ፤ ‹‹ወረከብናሁ ለበትር ዘያደክማ ለሮሜ፤ ቅሩጸ በንባብ ወጽሩበ በትርጓሜ፡፡›› ብሎ የተቀኘላቸው የሊቃውንት ዋልታ፡፡ ፠ #አባ_ስብሐት_ለአብ_ (የመልክ ሥላሴ፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ዘይነግሥን የደረሱና 14ቱን ቅዳሴ ያመሠጠሩና በአንድምታ የተረጐሙ፣ በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ ከብዙ ሊቃወንት ጋር በመሆን የቅኔና የመጻሕፍትን ምሥጢር ከነሙሉ አገባቡና እርባ ቅምሩን እንዲሁም የአቡሻኽርን ሁሉ የቀመሩ፤ የንጉሡ የአድያም ሰገድ ኢያሱ መምህረ ንስሐ የነበሩ) ፠ #አባ_ዳንኤል_፤ (ብዙ መጻሕፍትን ያሰባሰቡና የጻፉ፤ ንዋያተ ቅድሳትን የሚሠርቅ ‹‹ቢዘራ ለበረድ ፥ ቢወልድ ልጁን ለጕጓድ፡፡›› ብለው ከ8000 በላይ ሊቃውንትን በማሰባሰብ እንዲወሰን ያደረጉ፡፡ #ከላይ_ያሉትን_ለአብነት_የጠቀስናቸውን_ቅሳንና_ሊቃውንት_አስተምረውና_ወልደው_፤ ለ90 ዓመታት ፍሬና ቅጠላ ቅጠል ተመግበው፤ ራቁታቸውን በጋ ከክረምት በበረሃው መንነው፤ ሳማ (አበርባራን) ለትሩፋትና ለተጋድሎ ለብሰው፤ በፀሐይ ሰረገላ፥ በብርሃን መንኰራኵር እየተጫኑ እንደ ሐዋርያት በማስተማራቸው፤ የጸጋና የቅብዐት ተካተዮችን እያስተማሩ ወደ እናት ቤ/ክ በመመለሳቸው፤ ** የሚያምረውን ሥጋዊ ደም ግባታቸውንና ሰውነታቸው እንደ ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብና እንደ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ወደ ቁስል በመቀየራቸውና ሥስቃዩንና መከራውን በመቻላቸው፤ ቁስላቸው ተልቶ ትሎቹን የገዳሙ አእዋፋት እስኪመገቡት ድረስ በመታገሣቸው፡፡ *** በርካታ ቃል ኪዳን አምላካችን ሰጥቷቸው በተወለዱ በ470 ዓመታቸው ዐርፈዋል፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ታኅሣሥ_29_ልደታቸው_ከጌታችን_ልደት_ጋር_የተባበረላቸው_ቅዱሳን፤ #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕናና የቆብ ልጃቸው #አቡነ መዝራዕ
+5
#ታኅሣሥ_29_ልደታቸው_ከጌታችን_ልደት_ጋር_የተባበረላቸው_ቅዱሳን፤ #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕናና የቆብ ልጃቸው #አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ፤ #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤ #ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤ #አቡነ አካለ ክርስቶስ፤ #መስፍኑ ኢያሱ፤ #አቡነ ዳንኤል ዘገርዓልታ፤ #ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡ #የቅዱስ_ላላበላ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ቦታዎች_፤ ፠ በደብረ ሮሐ ላስታ ቅዱስ ላሊበላ ፠ በመዲናችን በአዲስ አበባ አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ፤ በድርብነት ይከብራል፡፡ ፠ በአሸዋ ሜዳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ላሊበላ ወቅዱስ መርቆሬዎስ ወኪዳነ ምሕረት ወቅድስት ሥላሴ፡፡ ..(ሌሎችም ካሉ ከነፎቷቸው ጨምሩበት) #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፮፡፡ #ዐርብ_ታኅሣሥ_30፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈ
+1
#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፮፡፡ #ዐርብ_ታኅሣሥ_30፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋቸው፤ …. ……እንዳያመልጣችሁ፤ በሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ በብዙ ጕባኤያት ላይ ያልተዳሰሱ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ጕባኤ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ፤ #ደግመን_እንላለን_ይህ_ትምህርት_በፍጹም_እንዳያመልጣችሁ!!!!! ለተከታታይ ሳምንታት፤ ትምህርቱ ተከታታይነት ስላለው መቅረትና ማርፈድ አይመከርም!!፡፡ (፻፶፮ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ) #ዐርብ_ታኅሣሥ_፴፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት አሁንም በድጋሚ እንላለን ለሕይወታችን ወሳኝና በብዙ የትምህርት ጕባኤያት ላይ የማይዳሰሱ ትምህርቶች ስለሆኑ እንዳያመልጣችሁ!!!! የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

በልደት በዓል ከምዕመናን ጋር በመተባበር ነዳያንን ማስፈሰክ ከጀመርን እነሆ 3ኛ ዓመታችን ይህን ይመስላል፡፡ ሰ/ትቤታችን ዛሬ በሁሉም አጥቢያ የሚደረገው በትንሣኤ ነዳያንን የማስፈሰክ ተግባር በግንባ
+1
በልደት በዓል ከምዕመናን ጋር በመተባበር ነዳያንን ማስፈሰክ ከጀመርን እነሆ 3ኛ ዓመታችን ይህን ይመስላል፡፡ ሰ/ትቤታችን ዛሬ በሁሉም አጥቢያ የሚደረገው በትንሣኤ ነዳያንን የማስፈሰክ ተግባር በግንባር ቀደምትነት ከ50 ዓመታት በፊት መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ለነዳይን የሚያስብ እርሱ ምስጉን ነው፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

ለነዳያን የሚያስብ እርሱ ምስጉን ነው፤ እነሆ ለ3ኛ ጊዜ የልደት ነዳያንን የማስፈክ መልካም ሥራ ከምዕመናን ጋር በመተባበር ዘንድሮም ይቀጥላል፡፡
+2
ለነዳያን የሚያስብ እርሱ ምስጉን ነው፤ እነሆ ለ3ኛ ጊዜ የልደት ነዳያንን የማስፈክ መልካም ሥራ ከምዕመናን ጋር በመተባበር ዘንድሮም ይቀጥላል፡፡

የጌታችን ልደት በዋናነት የሚከበርባቸው ዐበይት ገዳማትና አድባራት፤ (ሌሎችም ካሉ ከተቻለ ከነፍቷቸው ላኩልን፡፡) ፠ በኢየሩሳሌም ቤተ ልሔም፤ ጌታችን በተወለደባት ፠ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም፤ ለመጀመሪ
+8
የጌታችን ልደት በዋናነት የሚከበርባቸው ዐበይት ገዳማትና አድባራት፤ (ሌሎችም ካሉ ከተቻለ ከነፍቷቸው ላኩልን፡፡) ፠ በኢየሩሳሌም ቤተ ልሔም፤ ጌታችን በተወለደባት ፠ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታ በተወለደባት ዕለት የጌታችን መወለድ የተበሠረባት /ቋራና መተማ/ ፠ ሰረባር በዓለ እግዚአብሔር፤ ቅዱስ ላሊበላ ከሕንፃዎቹ ሁሉ መጀመሪያ ያነጸው ውቀር ቤ.ክ. /ስሜን፤ ደረስጌ አጠገብ/ ፠ ደብረ ሮሐ ላስታ ላሊበላ ፠ ርዕሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ ቤ.ክ. /እጅግ ጥንታዊ ታሪክ ያለው ጽላቱ ከደበቡ ኢትዮጵያ የሄደና ኋላ ቊጥሩ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ የሆነ፤ ጎንደር ከተማ/ ፠ ደብረ ስብሐት ቀሃ ኢየሱስ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ፤ ጎንደር ከተማ/ ፠ ቂልጠፋት በዓለ ወልድ፤ (ጉራጌ ፥ እንደጋይ ወረዳ) ፠ ጉንችሬ በዓለ ወልድ፤ (ጉራጌ ፥ እነሞር ወረዳ) ፠ አሸዋ ሜዳ ቤሮ ደብረ ምህረት ቅዱስ ላሊበላ ቤተክርስቲያን፤ (በምዕራብ ሸዋ ፥ ወልመራ ወረዳ) በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ፤ ፠ አዲስ አበባ መካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ /በ1883ዓ.ም. የተመሠረተ፤ 4ኪሎ፤ አዲስ አበባ/ ፠ ፊሊዶሮ መድኀኔዓለም ቅዱስ ላሊበላ፡፡ # ፠በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ # ፠በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem