Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 369 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 633,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 187 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 369 名订阅者。
根据 19 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -46,过去 24 小时变化为 37,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.37%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.87% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 438 次浏览,首日通常累积 1 210 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 20 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 369
订阅者
+3724 小时
+367 天
-4630 天
帖子存档
#ምስባክ #ቅድስት
ዘመጋቢት ፲፪፣ ፲፫ ወ ፲፬
የምስባኩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ
https://terakiapp.page.link/tEx8
#መስቀል_፤ መስከረም 17 ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ
አጋዥነት መስቀሉ እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽቦችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡
✤
#ተቀጸል_ጽጌ_(#መስከረም_10_/#አፄ_መስቀል_/)፤ መስቀሉ ወደ ሃገራችን የገባባት ዕለት ነው፡፡
✤
#መስከረም_21_፤ መስቀሉ መስከረም 10 ቀን ቀን ወደ ሃገራችን ከገባ በኋላ ‹‹መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ›› በተባለው ቃል መሠረት ከብዙ ፍለጋ በኋላ መስከረም 21 በግሸን ደብር ከርቤ ያረፈበት ዕለት ነው /ዝርዝሩን መስከረም 21 ይጠብቁ/፡፡
✤፠ንግስት እሌኒ በመስከረም 16 ቀን ደመራ አስደምራ፤ ፠፠✤✤መስከረም 17 ቁፋሮ አስጀምራ ፠፠፠✤✤✤በመጋቢት 10 ቀን ቁፋሮ ተጠናቅቆ መስቀሉ ተገኝቷል፡፡
፠ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን፤ የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሣልብን አሜን፡፡
፠ "በወንጌሉ ያመናችሁ፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፡፡"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/finotehiwott
አንኳን ለመስቀለ ኢየሱስ (መጋቢት 10) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡
በአዲስ አበባ (እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ) በብቸኝነት ከቀድሞ ጀምሮ የመስቀለ ኢየሱስ በዓል በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይከብራል ፡፡
** የመስቀል አገልጋይ ካህናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደመወዛቸው ከቤተ መንግሥት እንደሚከፈላቸው፤ ….)
በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤
መስቀል ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም የቤቱ የመስቀል ወረብ)
በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ
አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ
ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንተ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት
ድል በማድረጉ ነው፡፡
የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡
በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት
አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ
ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡
መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤
በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡
ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ ዕፀ መስቀልም በዓፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ ማርያም፣ ጋራ መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ
በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
* "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/
* ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/
* እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በዋይዜማ፣ በሰርክ ጕባኤ፣ በሰዐታቱ በኪዳኑ፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉና በቅዳሴው እንገናኝ፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
፠፠፠ #የመስቀል_ክብረ_በዓላት_
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
#መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤
#መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤
#share #like በብቸኝነት (እስከ ቅርብ ጊዜያት) ከንግሥት ዘውዲቱ ጀምሮ በደብራችን የመስቀል ክብረ በዓል መስከረም 17ና መጋቢት 10 ይከብራል፤ ይምጡና ያክብሩ
#ደመራ_፤
#ምስባክ #ቅድስት
ዘመጋቢት ፱ ፣ ፲ ወ ፲፩
#ምስባክ
ዘመጋቢት ፰
የምስባኩንና የመዝሙሩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ
https://terakiapp.page.link/Q34z
#ምስባክ #ዘወረደ
ዘመጋቢት ፭ ፣ ፮ ወ ፯
የምስባኩንና ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ
https://terakiapp.page.link/KdGK
#ምስባክ
ዘመጋቢት ፪ ፣ ፫ ወ ፬
ዛሬ ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ
#ምስባክ
ዘየካቲት ፴ ወመጋቢት ፩
የምስባኩንና የመዝሙሩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ
https://terakiapp.page.link/RjYa
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
