Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 366 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 631,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 191 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 366 名订阅者。
根据 20 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -39,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.39%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.98% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 441 次浏览,首日通常累积 1 226 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 21 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 366
订阅者
-524 小时
+297 天
-3930 天
帖子存档
ዝክረ አድዋ ለመሳተፍ ትኬት ለቆረጣችሁ ምእመናን በሙሉ
እንደሚታወቀዉ በቀን 24/06/2016 "ዝክረ አድዋ" መርሐግብር በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ ተዘጋጅቶ እንደነበር ይታወቃል ሆኖም መርሐግብሩ በተያዘለት ጊዜ ማካሔድ ስላልተቻለ ለቀጣይ ሳምንት በ29/06/2016 ከቀኑ 11:00 ሰአት ጀምሮ የተለወጠ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን
#በጣሊያን_ወረራ_ወቅት_አስተዋጽዖ_ካደረጉት_መካከል_ዐበይቶቹ_ገዳማትና_አድባራት፤ #ከካህናት፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጋዎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገድልና ዱር አላገኝ ስትል፤
ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡
እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460,770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746,800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤
300ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤
2,000 አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣
በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡
፠ይህንን እኩይ ተግሯን በግንባር ቀደምትነት የተፋለሟት፤ ዐበይቶቹም፤
፠ የ፳ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕታት #ብፁዕ_አቡነ_ጴጥሮስ_(ሐምሌ 22/1929 ዓ.ም. መሐል አ.አ ላይ በስምንት ጥይት ያረፉት)ና #ብፁዕ_አቡነ_ሚካኤል_ (ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም በኢሉባቦር ጎሬ ላይ በግፍ የተገደሉት)
፠ ጣሊያንን አውግዘው በታኅሣሥ 7/1928 ዓ.ም ሲሰየፉ፤ ከአንገታቸው ደም፥ ወተትና ውኃ የወጣው #ታላቁ_ሊቅ_አቡነ_ክፍሌ፡፡
፠ በግንቦት 28/1929 ዓ.ም. ቊጥራቸው 2,200 የሚሆኑ በግፍ የተጨፈጨፉ #የደብረ_ሊባኖስ_መነኰሳት፡፡
፠ በግንቦት 29/ 1929 ዓ.ም በቅዳሴ ላይ እንዳሉ የታረዱና ደመና የሸፈናቸው 43 #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ_መነኰሳት፡፡
፠ በሰኔ 12/ 1929 ዓ.ም በማስታኮት ላይ እያሉ የተገደሉ አስከሬናቸውን ሳይቀር በአካፋ የተሰቃየው 211 #የዝቋላ_መነኰሳት፡፡
፠ በጥቅምት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ 2116 የሆኑ #የደብረ_ዳሞ_መነኰሳት፡፡
፠ በሰኔ 3/1929 ዓ.ም 60 የታረዱ #የምድረ_ከብድ_መነኰሳት፡፡
፠ በሰኔ 15/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ በዚህም አንበሶች ከጫካ ወጥተው ያለቀሱላቸው፤ 91 የሚሆኑ #የአሰቦት_መነኰሳት፡፡
፠ በኅዳር 25/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ ሲታረዱም ብርሃንም የወረደላቸው፤ 143 #የአዲስ_ዓለም_ካህናትና_መነኰሳት፡፡
፠ በየካቲት 12/1929 ዓ.ም ከ30 ሺ በላይ በአካፋ ሳይቀር የተጨፈጨፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፡፡
፠ በመጋቢት 16/1929 ዓ.ም. ከላይ በቦንብ የውሃ ገንዳውን ጭምር፣ ከታች በመትረየስ የተፈጁት 515 #የማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም መነኰሳት፡፡ የበቁ አባቶችም በጸሎታቸውም አውሮፕላኗን የከሰከሷት፡፡
፠ በመጋቢት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ ብዛታቸው በውል ያልታወቁ #የደብረ_ዓባይ_ገዳም መነኰሳት፡፡
፠ በሚያዝያ 18 ና ሚያዝያ 20/1929 ዓ.ም የታረዱ 363 #የመርጦ_ለማርያምና_የተድባበ_ማርያም ካህናትና መነኰሳት፡፡
፠ በሐምሌ 29/1929 ዓ.ም. እየተለቀሙ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ ግማሾቹ የተሰፉትና ግማሾቹ ደግሞ በግዞት የተወሰዱት #የጎንደር_ሊቃውንት፡፡
፠ በየካቲት 18/1929 ዓ.ም. የተሠዉት የአዲስ አበባ #የካ_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ካህናት አባቶች፡፡
፠ በየካቲት 20/1929 ዓ.ም #በአ.አ ከተማ ያሉ በተለያዩ ገዳማትና አድባራት የሚገኙ ታላላቅ ሊቃውንት ተለቅመው እንዲሰበሰቡ ከተደረገና ከተደበደቡ በኋላ እጅና እግራቸውን አስረው እሳት አጉርሰዋቸዋል፡፡
፠ የትግራይ #ጨለቆት_ሥላሴ አገልጋዮችና (ርዕሰ ደብር የነበሩትን አስተዳዳሪውን ጨምሮ) አስረው ‹‹በሮማ ካቶሊክ ታምናላችው ወይስ በረሃብ ትሞታላችሁ?›› እያሉ በረሃብ አሠቃይተዋቸዋል፡፡ እምቢ ቢሏቸው ጽኑ ግርፋት ገርፈው ከለቀቋቸው በኋላ በመኪና ገጭተው ገድለዋቸዋል፡፡
፠ #ይደመቆ_ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/
፠ #አፈር_ባይኔ_ተክለ_ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/
፠ #አክርሚት_ቅዱስ_ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/
፠ #ጎበጥ_አገር_ገብርኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ እመ ምሕረት/
፠ #አንኮበር_ቅድስት_ማርያም ቤ.ክ.
፠ #ደረፎ_ቅድስት_ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/
፠ #ጎንቻ_መድኀኔ_ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/
፠ #አንኮበር_ቅዱስ_ሚካኤል ቤ.ክ.፡፡
#ጀግናውና_የቅኔው_አዝመራ_አለቃ_መርሻ_ወልደ_ማርያም
ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡
ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤
እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡
ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤
ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡
ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ ደግሞ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤
አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤
ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤
ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤
በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡
መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤
ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡
፠ ከ1927-1934 ዓ.ም. ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀገራችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤
*በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤
*ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤
**የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ ከ30,000 በላይ ሰማዕታት፤
*በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤
*በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤
*ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤
*በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤
*ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤
*ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡
*ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣
*350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡
**ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡ (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
#አድዋ፥ #ሶሎዳ፡፡ #9ኛው #የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት፡፡
9ኛ #አድዋ፥ #ሶሎዳ፡፡
ዓድዋ የሚለውን ስም የሠየሙት ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸው አባ ገሪማ ሲኾኑ፤ ዓድዋ ብዙ ተራሮችን የያዘች ሃገር ስትሆን፤ ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገው ከዓድዋ ተራሮች በግዙፉ #ሶሎዳ_ ተራራ ላይ ነው፡፡
#የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት_መነሻ
፠ ለአድዋ ጦርነት መነሻው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላ በሆነው አባ ማስያስ ሰላይነት ያጠኗትን ኢትዮጵያን ልትቀራመት መወሰኗ፡፡
፠ መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ (እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘች በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ራስ አሉላ አባነጋም ድባቅ መትቶ መለሳቸው፡፡
፠ ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በሚል ሰበብ ሌሎች ጦርነቶች ተቀሰቀሱ፡፡
ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡
#ኮከበ ክብር፥
*ሊቀ ሰማዕታት፥
*መክብበ ሰማዕታት፥
*የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥
*የልዳ ፀሐይ፥
*የኢትዮጵያ ገበዝ፥
*ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥
*፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥
*በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥
*፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥
*፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤
*እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤
/የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡/
ከ1878-1888ዓ.ም. #ከዓድዋ_በፊት_የነበሩ_8ቱ_አድዋዎችና_የዓድዋ_ሶሎዳ_ውጊያ፤
1ኛ) ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ #ዶጋሊ_ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰበት፡፡
2ኛ) ደጃች ደበብ፤ #ሰገነይቲ ላይ የተደረገ ውጊያ
3ኛ) ደጃች ባሕታ ሀጐስና ወንድማቸው አዝማች ሰንጋል፤ ከጄነራል ሳጎናይቲና ከተከታዩ ታንቲ ጋር ያደረጉት ውጊያ፡፡ ቀጥሎም ደጃች ባሕታና ዘመዳቸው ባሻይ ምስጉን የተሰዉበት #የሐላይ_መንደር_ ውጊያ፡፡
4ኛ) ራስ መንገሻ ዮሐንስ #በኰዓቲት_ ከጥር 13-15 የተዋጉበት፤ ጦርነቱ የተራዘመና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት፤ የሟች ቊጥር በመበርከቱ አሸናፊና ተሸናፊው ሳይለይ፤ የራስ መንገሻ ጦር ወደ ሰነዓፌ የተበተነበት፡፡
5ኛ) የራስ መንገሻ ዮሐንስ የጦር አዝማቾች (እነ ተስፋይ ህንጣሎ አጋሜ፥ ወልደ ማርያም፥ ቀኛዝማች ኃይለማርያም ወምበርታ፥ ቀኛዝማች አብርሃ፥ ደጃች ረዳ አባ ጉብራ /የራስ አርአያ ልጅ/) መሪያችንን ራስ መንገሻን አናስነካም ብለው #በደብረ_አላ_ ላይ የተዋጉት ውጊያ፡፡
6ኛ) ልዑል ራስ መኰንን (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥና የሐረርጌ ገዥ /የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት/)፤ #አምባ_አላጌ ላይ ጣሊያንን እንደ ንብ ወረው ትልቅ ጀብድ የሠሩበትና ለአድዋውም ወኔ ቀስቃሽ ውጊያ፡፡
7ኛ) ልዑል ራስ መኰንን፤ መቀሌ #እንዳ_ኢየሱስ (ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ የሚገኝበት) ላይ፤ ቀድሞ በቦታው ላይ ጠላት ሸምቆ ስለበረ ዙሪያውን ከበው ስንቅ በማሳጣት መሪው ማጆር ጋሊያኖ ማሩኝ ለጄነራሌ ለባራታሪ ሂጄ ዕርቅ ይሆናል አስማማለሁ፤ ብሎ በዕርቅ ያለቀበት፡፡ (ኋላ ግን ማጆር ጋሊያኖ ቃሉን በማጠፉና ጣሊያንን ለጦርነት በማነሳሳቱ የአድዋ ጦር ሁኗል፡፡)
8ኛ) ራስ ስብሐትና ደጃች ሐጐስ ተፈሪ (ቀድሞ ባንዳ ነበሩ) ማጆር ጋሊያኖ ለጄነራሉ ከማስማማት ይልቅ ጠብን በመምከሩና የጣሊያን ጦር በእንትጮ በኩል ከኢትዮጵያ ጋራ ሊዋጋ ሲገሰግስ የአካለ ጉዛይን ባላሃገር በማስተባበር #እንትጮ ላይ ደጀን ሁነው መክተው የተዋጉት ውጊያ፡፡
---
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/finotehiwotee
#ምስባክ
ዘየካቲት ፳፫ ወ ፳፬
የምስባኩንና የመዝሙሩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ
https://terakiapp.page.link/ZKmo
የወጣትነት ሕይወት በዓርብ ጉባኤ ፤
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ነነዌ በማስመልከት አባታዊ ቃለ በረከት አስተላለፉ፡፡
የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የጾመ ነነዌ መልዕክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
'ተንሥእ ወሑር ኅበ ነነዌ ሀገር ዐባይ - ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ"
ዮና ፩;፪
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት፤
መንፈሳዊ ተልእኮ ተቀብላችሁ በየተሰጣችሁ ጸጋ በተለያየ ስፍራ ሆናችሁ የምታገለግለ‐ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤
በመንፈስ ቅዱስ ልደት የከበራችሁ ምእመናን ወምእመናት ልጆቻችን በሙሉ፤ ዘመንን በዘመን እየተካ፣ መዓቱን በምሕረት እየመለሰ የሚያኖረን እግዚአብሔር እንኳን ለ2016 ዓ.ም ጾመ ነነዌ አደረሰን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩት የሰው ልጆች በኃጢአት በወደቁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ የሁሉ አባት በመሆኑ ተወልዶ ብልጫ የለም" እንዲሉ ከእስራኤል ውጭ ወዳለችው ነነዌ ነቢዩ ዮናስንና ነቢዩ ናሆምን ልኳል። በበደል ውስጥ ሆነው ቢጾሙም ሆነ ቢጸልዩ ጸሎቱ ድል የሚነሣ መሥዋዕቱም የሚያስምር አይሆንምና፡ ንስሐም ለድሀና አቅም ለሌለው የሚሰበክ ሳይሆን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያደፈ ሁሉ የሚጠራበት የሕይወት መስታወት ነውና የሕይወት ትንሣኤ በሆነው ንስሐ ነነዌን ለማንሣት ዮናስ ወደ ንጉሡና ወደ ሠራዊቱ የንስሐ ሰባኪ ሁኖ ተልኳል።
ነነዌ ከተማዋ አድጎ፡ ልማቷ ቢሰለጥንም እግዚአብሔር ግን የተመለከታት ፈርሳና ተበላሽታ ነበር፡፡ በፈረሰ ልብ የሚገነቡ ከተሞች የቀን ጉዳይ እንጂ ፍርስራሽ መሆናቸው አይቀሬ ስለሆነ ዛሬ ነነዌ ከታሪክ መዝገብ ላይ ብትሰፍርም በዓይን ግን የምትታይ አይደለችም። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የነነዌን ጾም ያወጀችው ዓመት ሙሉ የተጣላ በነዚህ ሦስት ቀናት እንዲታረቅ፣ ሲካሰስ የሚኖር ሕዝብም ወደፈጣሪው በንስሐ እንዲመለስ ነው።
እግዚአብሔር አምላክ ነቢዩን ወደ ነነዌ ሲልከው፡- “ተነሥተህ ሂድ" ማለቱ በበደል የሳተን በሩቅ ሆኖ መተቸት መንፈሳዊ ተልእኮ ባለመሆኑ ተነሥተን ብንሄድ፣ መንገድ አጋምሰን ወገኖቻችንን ብንፈልግ ሁሉንም ለንስሐ ማብቃት እንደምንችል ሲያስተምረን ነው፡፡ ለመነሣት ስንፍናንና ፍርሃትን ድል መንሣት ያስፈልጋል። ለይቅርታ ስንነሣ ትዕቢትን እናሸንፋለን። ፉክክርን እናርቃለን። ለጋራ ሀገራችን የጋራ መፍትሔ፡ ለጋራ ቤተ ክርስቲያናችን የጋራ መድኃኒትን እናገኛለን።
በሌላ በኩል አምላካችን እግዚአብሔር በደለኛይቱን ከተማ ታላቂቱ ከተማ በማለት ሲጠራት ሕዝቡንም ግራና ቀኙን የማያውቅ በማለት ራርቷል። እግዚአብሔር አምላክ አክባሪ፤ አዛኝ፡ በደለኛውንም በክብር እንጂ በውርደት የማይጠራ አምላክ ነው። እኛም ይህንን የነነዌን ጾም ስንጾም በአንድ በኩል እንጀራን የተራቡ፣ በሌላ በኩል ሰላም የተራቡ ወገኖች ስለአሉን ወደ እነዚህ ወገኖች የንስሐን ስብከት፣ የማጽናናትን መልእክት ይዘን መሄድ አለብን። በተጨማሪም ከቀዬአቸው የተፈናቀሉትን፡ በረሃብ፣ በመታረዝ፣ በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን የመከራ ማቅ በሕሊናችን ተሸክመን ስለጸሙ የተውነው የዕለት ቊርሳችንን ለእነርሱ ሞትን ማባረሪያ እንዲሆን ልንፈቅድ ያስፈልጋል።
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
ይህንን የነነዌ ጾም ልንቀበል ዋዜማ ላይ ባለንበት በዚህ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ጥንታዊ ከሆኑት ገዳማት አንዱ በሆነው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኙ፣ ዓለሙን ትተው በፈቃዳቸው ረሀብተኛ እና ጥማተኛ ሆነው ሀገርን በጸሎት የሚጠብቁ መነኮሳት ጫካው መኖሪያችሁ፣ ዳዋው ልብሳችሁ፤ ቅጠሉ ምግባችሁ መሆን አይችልም ተብለው የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎንጭተዋል፡፡ እነርሱ በሥጋ እየሞቱ እኛም በየቀኑ ሟቾችን እየቆጠርን በኀዘን ለመኖር የተፈረደብን ሆነናል፡፡
ይህ ለእነርሱ ክብር ቢሆንም ለቤተክርስቲያን ግን ታላቅ ደወል ያሰማ ክስተት ነውና ውሉደ ክህነት ቤተክርስቲያናችሁን የምትጠብቁበት፣ የመከራውን ማዕበል ለማለፍ በመንፈሳዊ ፍቅር አንድነትን ማጽናት የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
በመጨረሻም ታላቅ ሀገር ይዘን፣ ምድሩ ሳይጠበን አመል እያጋፋን ነውና ጸማችን፣ ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ለሀገር ደኅንነት፡ ለሕዝብ ድኅነት እንዲያመጣልን፡
እግዚአብሔር ይቅር ብሎን ዘመኑን በምሕረት ያሻግረን ዘንድ በታላቅ ንስሐ፣ በጸሎትና በአስተብቍዖት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ አባታዊ መልእክታችንን በመሐሪው አምላክ ስም እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ || ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ
የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም
ተ.ሚ.ማ
#ምስባክ
ዘየካቲት ፲፮ ወ ፲፯
የምስባኩንና የመዝሙሩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ
https://terakiapp.page.link/qfxs
የካቲት ፲፮ (16)
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል (#ቃል_ኪዳን_ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
፠ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ፤ ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኵሎ፡፡ (ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲዖልን ካየች በኋላ ስለኃጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች ፠ የካቲት ፲፮ ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች፡፡
፠ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ አገልጋይህ የምለምንህን ይህ ነው፡፡ ፨ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣ ፨ አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ፨ ለታረዙ ለሚያለብሱ፣ ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም ለሚያጠጡ (በስሜ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ)፣ ፨ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ ወይም ፨ ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣ ፨ በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ ፨ በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ሁሉ ከሲዖል ነፃ አድርጋቸው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረሃብና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡
#ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘየካቲት_16፤ #በዓለ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡ በሃገራችን በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የኪዳነ ምሕረት በዓል የሚቆመው ቁመት፤ የ3ት ዐበይት አድባራት አብነት ናቸው፡፡
እነዚህም፤
1ኛ) የላይ ቤት፤ የደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት አብነት
2ኛ) የታች ቤት አብነት፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ አብነት
3ኛ) የደፈጫ ኪዳነ ምሕረት አብነት ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደ የደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ ሁሉን አዘጋጅተንላችኋል፡፡ የላይ ቤት ከኾነ ‹‹ዘዐቢየ እግዚእ›› የሚለውን፤ የታች ቤት ከኾነ ‹‹ዘበዓታ›› የሚለውን እንድትጠቀሙ እናሳስባልን፡፡
በፎቶ ላይ ያሉት ቤተክርስቲያን፤
1ኛ) #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ
_ኪዳነ_ምሕረት ገዳም፡፡ ይህች ገዳም ታሪኳ ከታላቁ ገዳማችን ዋልድባ (ገዳመ ዋሊ) ለ2ኛ ጊዜ መሥፋፋት (መመሥረት ጋር) የተያያዘ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ይኸውም የሸዋ አባቶች ወደ ዋልድባ በ485 ዓ.ም. በንጉሥ አልአሜዳ ዘመነ መንግሥት ባቀኑ ጊዜ የተሰባሰቡባት ቦታ ናት፡፡ እነዚህም አበው ከመኖሪያ ቀዬቸው (ቡልጋ/ምንጃር/) ሁለት ታቦታትን (ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ዘምሕረት አምባ፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ዘአብየ ገዳምን) ይዘው ነበር፤ በዚህች በተቀደች ቦታ ይዘዋት በመጡት ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ገዳመ ሐመረ ኖኅን መሥረተዋል፡፡ የመድኀኔዓለም ታቦትን ደግሞ በታላቁ ገዳም በዋልድባ አኑረዋል፡፡ ይህች ሐመረ ኖኅ፤ - በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተስፋፍታ ተቋቋመች፡፡ - በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተ ጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡ - በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ - አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ - አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ - በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡ ይህች ቦታ ከታላቁ ገዳም ከዋልድባ ጋር አሁንም ግንኙነቷ እንደጠነከረ ነው፤ ከዋልድባ ያሉ አባቶች በተለያየ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በዋነኛነት የሚያርፉባት ጥንተ ርስታቸውም ናት፡፡ ይህች ቦታ በርካት ቅዱሳን በኪደተ እግር የረገጧት እንደመኾኗ፤ ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ፤ የብዙ መነኮሳት መጠጊያ፤ የህሙማን መፈወሻ፤ የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎችም አንዷ ናት፡፡
2ኛ) #ደብረ_መድኀኒት_ዐቢየ_እግዚእ _ኪዳነ_ምሕረት፤ . በሃገራችን ኢትዮጵያ የመጻሕፍተ ብሉያት አንድምታ ትርጓሜ ዋና ማስመስከሪያ መካነ አእምሮ (University) የኾነች፤ . ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእ በኪደተ እግር የረገጧት፤ . በአቋቋም በኩልም የላይ ቤት አብነት የኾነች፤ . የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያና ታላላቅ ሊቃወንት ወንበር ዘርግተው፥ ጕባኤ አስፋፍተው ያስተማሩባትና በማስተማር ላይ ያሉባት ቦታ ናት፡፡ የምትገኘውም ጎንደር ከተማ ነው፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts
#Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
