ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 789 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 322,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 211 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 789 名订阅者。

根据 10 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 77,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.52%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.65% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 331 次浏览,首日通常累积 726 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 11 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 789
订阅者
无数据24 小时
+1047 天
+7730 天
帖子存档
፠ ይህ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጕባኤ ቤትም ሲኖረው፤ ቀድሞ የ4ቱ ጕባኤያት ዋና ማስመስከሪያ ኹኖ ቆይቷል፤ ከአፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ መነኰሳት ዋና ማስመስከሪያ ኹኖ ይገኛል፡፡ እጅግ የሚገረመው ደግሞ ደብረ ሲመሠረት ያገለግሉ የነበሩት ካህናት 318 መሆናቸው ነው እኚህም በሥነ መለኮትን ት/ት እጅግ ሊቅ የሆኑ ሲሆን መጻሕፍትን በመተርጕም እና ምሥጢር በመግለጥ አገልግለዋል በዙ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል ፡፡ ፠ በ900 ዓ.ዓ አካባቢ ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር የመጡት የብሉይ ኪዳን መምህራን ቁጥር 318 መሆኑን መጻሕፍት ይናገራሉ ፡፡እነዚህም ወንጌል እና ግዕዝ ቋንቋን ያስፋፉ ናቸው፡፡ ኦሪትም በሕዝቡ ልቡና እንዲቀር ያደረጉ ፣ መጻሓፍትንም ( ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ )በመተርጐም አስተዋጾ ያደረጉ ናቸው ፡፡፡፡የኦሪቶቹ 318 ሊቃውንት ከአዲስ ኪዳኖቹ ሊቃውንት ቁጥር ጋር እኩል መሆናቸው እጅግ የሚያስገርም ታሪክ ነው ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

ኅዳር ፱ (9)፤ የሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) ክብረ በዓል ነው፡፡ በዚህችም ቀን ዳግመኛ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምነት ኤጲስ ቆጶሳት ሊቃውንት ስብሰባ በኒቅያ ከተማ በጻድቅ ንጉሥ በቈስጠንጢኖስ ዘመን ሆነ ፡፡ " ፠የተሰበሰቡበትም ምክንያት የሊብያው ሰው አርዮስ በእስክንድርያ በቄስነት ሲያገለግል ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን‹‹ወልድ በመለኮቱ ፍጡር ነው ብሎ ›› ክዷል ከዚያም: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ:: ፠ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር (በዚችም ዕለት በዓላቸው ይታሰበል ) :: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ:: ፠እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: ፠እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጥቂቶቹ 1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዓሉ በደብራችን ደብረሰላም የሚከበር(ነሐሴ 24) (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው) ስለ ቅዱስ ቶማስ እዚህ አነብብ https://t.me/medihanaelem/6993 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/posts/2985127341805344 2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው) 3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው) 4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው) 5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጉዋድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው) 6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው) 7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው) 8.ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ: ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው) 9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው) ፠ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው:: ፠በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው:: ፠በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመው በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር:: ፠ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ:: ፠ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ዻውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል:: ፠ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው:: ፠ቆይቶ ሰነፉ ዻዻስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!!!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው:: ፠ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል:: ፠በወቅቱም በመወገዙ 'ተበደልኩ' ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ:: ፠ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ዼጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ:: ፠በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:- 1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ:: 2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ:: 3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ፡፡ 4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ፡፡ 5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ፡፡ ፠ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖ እና ገሊላዊ ዻዻስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን ከጨረሱ በሁዋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል፡፡ ፠በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: መሠረቶቻችን: ብርሃኖቻችን: ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን:: =>318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቁልን:፡፡ በረከታችው ምልጃቸው አይለየን ፡፡ ------ የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ፤ ሐመረ ኖኅ ሠለስቱ ምዕት ቤ.ክ፤ በሃገራችን በሠለስቱ ምዕት (በ318ቱ ሊቃውንት ስም) ብቸኛ የሆነውና በአሁኑ ሰዐት ከ4ቱ የመጻሕፍት ጕበኤያት በኢትዮጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ መነኰሳት ዋና ማስመስከሪያ የሆነ ነው፡፡ ፠ በሃገራችን በሠለስቱ ምዕት (በ318ቱ ሊቃውንት ስም) ብቸኛ የሆነውና ከ1700-1701 ዓመታት በፊት በአፄ ቴዎፍሎስ (ስመ መንግሥት አጽራር ሰገድ) ታንጾ የነበረ ሲኾን ንጉሡ ሲያንጹትም የሠለስቱ ምዕት የአእላፍ መላእክትና የነቢያት ቤተ ከርስቲያን አድርገው ነው፤ ድርቡሽ ጎንደርን በ1880 በወረረ ጊዜ ጠፍ ኹኖ ቆይቶ በ2007 ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያኑ ድጋሚ ተሠርቷል፤

ሰላም ለክሙ አርባዕቱ እነስሳሁ ፡፡ ለእግዚአብሔር መናብርቲኁሁ ፡፡ እሳታውያን ናሁ ሠረገላሁ ፡፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እንዘ ይብሉ ይሄልሑ፡፡ አሐተ ሰዓተ እንበለ አጽርዖ በጽርሑ ፡፡ ሰአሉ ለነ ትጉሃን ሐራሁ ፡፡ **መልክአ አርባዕቱ እንስሳ፡፡ በኢትዮጵያ ሀገራችን የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበሩባቸው አድባራትና ገዳማት በጥቂቱ:- 1.#ቤተ ፬ቱ(አርባዕቱ) እንስሳ (ማዕከላዊ ትግራይ አክሱም ጽዮን አጠገብ) 2.#ደብረ ዓሣ አርባዕቱ እንስሳ (ማእከላዊ ትግራይ ተምቤን) 3.#አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስቲያን (ሰሜን ጎንደር፤ጎንደር ከተማ) 4.#ቤተ አርባዕቱ እንስሳ አለት ፍልፍል (ሰሜን ወሎ አንጎት አካባቢ) 5.#መካነ ትጉሐን አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስቲያን (ደቡብ ጎንደር ደብረ ታቦር) 6.#ደብረ ኪሩብ አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስቲያን (ምዕራብ ሐርጌ መኢሶ አካባቢ) 7.#ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስቲያን (ምሥራቅ ሸዋ ዝቋላ) *በኤርትራ* 8.#አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስቲያን (ሃዞሞ የሚባል አካባቢ) 9.#ራቂት(ዓዲ ናላ) አርባዕቱ እንስሳ ቤተክርስትያን (በራቂት/ዓዲ ናላ) ****በደባልነት ያለ በአዲስ አበባ የሚከበርባቸው ቦታዎች*** 9.#ደብረ ጽጌ ቅድስት ማርያም (አዲስ አበባ፣ አደይ አበባ) 10.#ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን (አዲስ አበባ፣አራት ኪሎ) https://youtu.be/KrUaSIJ9_98 /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#እንኳን ለበዓለ ‹‹ኪሩቤል›› አርባዕቱ እንስሳ በሰላም አደረሳቹህ:: ኅዳር ፰፤ አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) | አራት ኪሎ ቤ.ክ በዓሉ በድምቀት ይከብራል :: *በኢትዮጵያ ሀገራችን የአርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበሩባቸው አድባራትና ገዳማት በጥቂቱ:- ከታች ይመልከቱ :: #share ያድርጉ ----- ከእግዚአብሔር በቀር የሚቆጥራቸው የሌለ የብዙ ሠራዊተ መላእክት በሰማይ ያሉ ሲሆን በዙውን አንድ እያልን በነገዳቸው እንቆጥራል፡፡ ስንቆጥርም የመጀሪያዎቹ ኪሩቤል (አርባዕቱ እንሳሣ )ናቸው ፨ ኪሩቤል ቃሉ ከአካድ/ጥንት ባቢሎናውያን ቋንቋ / የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም አማላጅ፣ኃያል፣ታላቅ ማለት ነው፡፡በአራቱ እንስሣ አምሳል የተገለጹ ጸውርተ መንበሩ ኪሩቤል ናቸው ፡፡ #ኪሩቤል የብዙ ቁጥር ሲሆን በነጠላ #ኪሩብ ይባላል፡፡ ፨ መላእክት ሆነው ሳለ ‹‹አርባዕቱ እንስሳ›› የተባሉበት ምክንያት ለቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በእንስሳት አምሳል በመገለጻቸው ነው፡፡ ፨ ኪሩቤል ከመቶው ነገድ መላእክት የአስሩ ነገድ መጠሪያ ስም ነው ፨ ከ3ቱም ሰማየ መላእክት በመጀመሪያይቱ በኢዮር ላይ ከአጋዕዝት በታች በ2ኛይቱ ከተማ የሰፈሩ ናቸው፡፡ ፨ ከእግር እስከ ራሳቸው በዓይን ተሸልመዋል - ዓይናቸውን እንደ ነብር ለምድ ዥንጉርጉር ነው፤አንድም እንደ መስታወት ስድ ነው ፤ ይኸውም ኪሩቤል ኃላፊያትንና መጻእያትን የማወቅ ክሂል ከልዑል አምላክ መቸራቸውን ያሳየናል ፤ ይህም የእግዚአብሔር ስራ ገደብ የማይጣልለት የቸርነት ሥራ ነው፡፡ መዝ 87፥ 35 ፨ነቢዩ ሕዝቅኤል እንደተመለከታቸወ ‹‹ ኪሩባውያን አፍራሱ ፤ ፈረሶቹ ናቸው ሲል ይገልጻቸዋል፡፡ ግብራቸውም ዙፋኑን ተሸክመው ሥላሴ ለወደዱት መገለጽ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ዙፋኑን ተሸክመው ይዘዋወራሉ ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር መገለጽ ሲፈልግ ዙፋኑን በዘፈቀደ ተሸክመው ስለሚታዩ ነው ፡፡ ፨ከአራቱ ኪሩቤል አንዱ ‹‹ ባራ ማራ ›› የሚባል ነው አንደኛነቱ የቁጥር እንጂ የክብር መበላለጥ አይደልም፡፡ ትርጕሙም ባራ ማለት በራ ማለት ነው ፡፡ በተፈጥሮ በራነት እንዳለ በመሸከምም በራነት ይኖራል ፡፡ ጸዋሬ መንበርነቱን ሲመለከትም ‹‹ ባራ ማራ መሊጦን ›› ብሎ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በምድራዊ ግሥ ገልጾታል፡፡ ፊቱም በአንበሣ ምስል ይገለጻል፤ ‹‹ ወቀዳሚ ይመስል አንበሳ ፤ የመጀመሪያው አንበሣን ይመስላል ›› እንዲል ራዕ 4፡፡ አንበሣ የአራዊት ንጉሥ ነውና በአለቃቸው ተመሰለ፡፡በአንበሣ መገለጹ ኃያልነቱን ሲያሳይ ነው ፍጻሜው ግን ‹‹ ሞዓ አንበሣ ዘእምነገደ ይሁዳ ›› የተበላው ክርስቶስ ይገለጣል ነው፡፡ ግብሩ ለአራዊት መለመን ሲሆን በሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ መመሰሉም የጌታን ሃያልነት ገልጾ ከማስተማሩ ጋር እና በአምሳለ አንበሳ የተሰሩ የግብፅ ጣዖታትን ቀጥቅጦ በማጥፋቱ ነው ፡፡ ፨‹‹መሊጦን መልአክ ›› ይህ ደሞ ሁለተኛው ሲሆን ሁለተኝነቱ የቁጥር እንጂ የክብረ መበላለጥ አይደልም፡፡ ትርጉሙም ዓምዳዊ ዘዐምድ እንደማለት ነው ዙፋኑን ተሸክሞ ‹‹ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ›› ብሎ ማመስገኑን ያሳያል ይህም መላእክት የሰማይ አምድ ናቸው ማለት ሳይሆን ግብራቸውን ያሳያል ፡፡ ቅዱስ ያሬድም ባራ ማራ .. መሊጦን ሲል ያዜማል፡፡‹‹ወካልዑ ይመስል ከመ ላሕም ››ሁለተኛውም ላም ይመስላል እንዲል ›› ራዕ እንዲል በላሕም ተመስሏል፡፡ በዚህም የተመሰለው ሉቃስ ሲጽፍ ‹ ‹ያን ላም አምጡት አርደን አወራርደን እንብላው ›› ሉቃ 15 ሲል ምሥጢረ ቁርባንን ጸፏል ፤ መሰየሙም ለዚህ ምክንያት ነው ፡፡ ፨‹‹እግረ ማጣ›› መልአክ ደግሞ አንዱ ነው ፡፡ቅዱስ ያሬድ ጸወርተ መንበር ብሎ በአንድነት ገልጻቸዋል፡፡ አምላካችንን በንጉሥ ፣ መንበረ ምንግሥቱን በኮር ፣ ሰማይ ውዱድን በአልጋ ፣ ኪሩቤልን በአራቱ እግሮቹ መስሎ ነው ፡፡ ይህ ከኪሩቤል አንዱ የሆነው መልአከ ፊቱ የሰው ልጅን ይመስላል ‹‹ወሣልሱ ይመስል ከመ ገጸ እጓለ እመ ሕያው ›› እንዲል ራእ 4 ፡፡ ይህ የሰው ፊት ያለው በማቴዎስ ይመሰላል ማቴዎስ ከአብርሃም ጀመሮ እስከ እመቤታችን ድረስ ልደተ አበውን ጸፏልና ፡፡ ፨‹‹ሱርትዮን መልአክ›› ይህ ደግሞ ትርጓሜው አገልጋይ ማለት ነው ፡፡ እሱም ዙፋኑን ተሸክሞ ሲያመሰግን ይኖራል ፡፡ገጹም ገጸ ንሥር ነው፤፤ ‹‹ወራቡዑ ይመስል ከመ ገጸ ንሥር›› እንዲል ራዕ 4፡፡ይህም ወንጌላዊውን ዮሐንስ የሚመስል ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጽፍ አመሣጥሮ ስለሚጽፍ ንሥር ደግሞ ከፍ ብላ ሌሎች አዕዋፍ የማይደርሱበትን ሰለምታይ እሱም እንዲሁ በ ንሥር ተመስሏል ፡፡ ፨ኪሩቤል (4ቱ እንሰሳ ) ለተወከሉበት መልክእ ቅድም እግዚአብሔር ጸሎት ያደርጋሉ #የሰው መልክ ያለው ኪሩብ ‹‹እግረ ማጣ›› #ለሰው ልጅ፣ #የአንበሳ መልክ ያለው ኪሩብ‹‹ ባራ ማራ ››#ለአራዊት፣ #የላሕም መልክ ያለው ኪሩብ ‹‹መሊጦን መልአክ ›› #ለቤት እንስሳት፣#የንስር መልክ ያለው ኪሩብ ‹‹ሱርትዮን›› ደግሞ #ለአእዋፍ ሁሉ እየጸለየ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ይህ ማለት ግን ምልጃቸው ገደብ አለው ማለት አይደለም አንዱ ለሌላኛው አንዱም ለሌላው መጸለይ መለመን ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ፨የሰው ፊት ያለው ዕውቀታቸውን ፣ የአንበሣ ፊት ያለው ግርማ ሞገሳቸውን ፣ የንስር ፊት ያለው ተመሥአቸውን ( ሲመሰጡ ሰማየ ሰማያት ይደርሳሉ )፡፡ ትህትናቸው የፍርሃት ምልክት ሲሆን ምድር ምድር የመለከታሉ ይህም ፊቱን ማየት ባሕርዩን መመርመር አይቻለንም ሲሉ ነው ፡፡ ግርማቸው ነበልባል ሲሆን እንደ እሳት ለተልእኮ ይፋጠናሉ ፡፡ አእምሮአቸው ግሩም ሲሆን በእውቀት ከሁሉ በላይ ናቸው ፡፡ አራት ፊትም ስላላቸው ለተልዕኮ አቅጣጫ አይቀይሩም ያለምንም ተፋልሶ ባለቡት ይቀጥላሉ እንጂ ‹‹ ሕዝ 1›› ለእያንዳንዳቸው አራት ክንፍ አላቸው ይህም በአጠቃላይ 16 ይሆናል ፡፡ ክንፋቸውስ 6 ነበር ነገር ግን በሰው አምሳል ስለተገለጡ ሁሉቱ እጃቸው ነበር ፡፡ እንጂ ያው ስድስት ክንፍ ነው ያላቸው ፡፡ ሁለቱ ክንፋቸውን ፊታቸውን ይሸፍኑበታል( ባህሪያን መመርምር አይቻለንም ሲሉ ) ሁለቱን ደግሞ እግራቸውን ይሸፍኑበታል( ከፊትህ ጸንቶ መቆም አይቻለንም ሲሉ ) ፣ ሁለቱን ደግሞ አንዱን ወደ ታች አንዱን ወደ ላይ ይዘረጋሉ( ቢወጡ ቢወረዱ አትመረመርም ሲሉ ) ፡፡ ፨የክንፋቸውም ጅግጅታ እንደ ፏፏቴ ከሩቅ ይሰማል ፡፡ ለመላእክት 6 ክንፍ ሲኖራቸው ለእንያንዳንዳቸው ኪሩቤል 16 ክንፍ በጠቅላላው 64 ክንፍ አላቸው ፡፡ ከዚኅ ጋርም ተያይዞ ‹‹ ከኪሩቤል እና ከሱራፌልም እሳ ትበልጣለች ›› የተባለቸው እመቤታችን እንዲዚህ መባሏ አንድም ኪሩቤል በክንፋቸው ጋርደው አምላከ ምሕረት ክርስቶስን ሲያመሰግኑባት አይቶ ነው ፡፡ ምልጃቸው አይለየን ፡፡ አሜን ! ---- በቅዱስ በዓለ ወልድ

ኅዳር 7 ( ፯ ) የሊቀ ስማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ ነው ። ፠ኅዳር 7 ከ፯ቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ አንዱ የኾኑት፤ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው፨ ------- መክብበ ሰማዕት ፥ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ኰከበ ልዳ፥ ፀሐየ ፋርስ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ የኢትዮጵያ ገበዝ፤ ከአውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የሚደርስ ፈጥኖ ደራሽ ሰማዕት፤ እንደ እናቱ (እኅቱ) ቅድስት ማርያም ርኁሩህ የኾነ፡፡ ኅዳር 7 ቅዳሴ ቤቱ (ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው ቤ.ክ የተመረቀበትና ቅዳሴ የተከናወነበት ክብረ በዓል) ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዚያ 23 ቀን በሰማዕትነት ከሞተ በኃላ አጋልጋዮቹ እጅግ የከበሩ ልብሶችና ያማሩ ሽቶዎች አዘጋጁ በከበረ አገናነዝም ገነዙት በመርከብም ጭነው ወደ ትውልድ አገሩ ልዳ አመጡት ነገር ግን ቤተሰቦቹ በሙሉ ማለትም አባቱ ዘሮንቶስ እናቱ ቴዎብስታ እህቶቹ ማርታና እስያ እንዲሁም አጭተውለት የነበረች እጮኛው ሁሉም ሞተው አገኙዋቸው፤ እንድርያስ የሚባል አጎት ነበረው ስጋውን ተቀበላቸው አገሬው ተሰበሰበ የእየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎድሮስ ተጠርቶ መጣ ቤተክርስቲያኑን አነጹለት ስጋውንም በዚያ በክብር አኖሩት፤ በዚህች ቀን እጅግ ብዙ የሆነ ድንቅ ታአምራትና ታላላቅ ኃይላት ተደረጉ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ይህንን ቀን ታከብረዋለች። ታላቁ ንጉሳችን እምዬ ምኒሊክ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ሲሰሩ ከዚሁ ከልዳ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ካለበት አፈሩን በመርከብ ከዚያም በበቅሎ አስጭነው አምጥተው ለቤተክርስቲያኑ መሰረት እንዳደረጉት እና ቅጥሩን ዙርያውንም እንደነሰነሱት መጻሕፍት ይናገራሉ ፡፡ ፠ ፠ በዓሉ በድምቀት በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ (በአራዳ ጊዮርጊስ) ይከበራል ———- ፨ ኅዳር ፯፤ (የአቡነ ገብረ እንድያስ በዓለ ዕረፍትና ነው)፨ ፠ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ተዓምራትን የሚሠሩት እንጨቱ ጸበላቸው_=ውስጥ ሲገባ መቊጠሪያ የሚያደርጉት ፤ (በፎቶ የምታዩት)፤ ፠ በጠበላቸው ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተዓምራትን የሚያደርጉት ፠ ፻ ትውልድ የሚያስምሩት፤ ፠ በደንጊያ ሠረገላነት የሚጓጓዙት፤ ፠ ከ፯ቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ አንዱ የኾኑት፤ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው፨ ቦታቸውን ክርስቲያን የኾነ ኹሉ ሊያየው የሚገባ የተዓምራት ቦታ ነው፤ ✤✣✤ #ጻድቁ_አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ_ወዘደብረ_ቆዘት_፤ ✤አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ፥ እናታቸው አርሴማ ሲባሉ፥ የትውልድ ሀገራቸው ወሎ፥ ቦረና፥ ጋሥጫ ሲኾን፤ የቀድሞ ስማቸው ንፍታሊም ይባል ነበር። ✤ ለትምህርት ሲሄዱ መምህራቸው ብዙኃኑን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ ብለው ትንቢት የተናገሩላቸው ሲኾን፤ የመጻሕፍትን ትርጓሜ በደንብ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሊም ይባል የነበረውን የቀድሞ ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው። ✤ ጻድቁ በአቡነ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፤ ብዙ አባቶች ሱባኤ በሚይዙበት በስኮሩ ሥላሴ ቤተክርስትያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል በወርቅ ጽዋ ማየ ሕይወት አጠጥቷቸዋል። ✤ ጻድቁ አባታችን ሙታንን በማስነሳትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል። ✤ ጻድቁ ዐርብ ፥ ዐርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን ና ክቡር ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በአየር ላይ ድንጋዩን እንደ ሰረገላ ፥ ዋርካውን እንደ ጥላ እየተጠቀሙበት ነበር። ይህ ሰረገላ የሆነው ድንጋይ በገዳማቸው ዛሬ ድረስ ይገኛል። (ፎቶውን ይመልከቱ) ✤ ጻድቁ አባታችን እግዚአብሔር ኀጥአንን እንዲምርላቸው ርቀት ወንዝ ከተሰኘው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሽከሙ ይጸልዩ ነበር። በዚህም ይጸልዩበት በነበረው ወንዝ ውስጥ በተአምራት መቊጠርያ የሚሰራ ጸበል ፈለቀላቸው፤ ጠበላቸው ውስጥም እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት መቊጠርያ ሆኖ ይወጣል፤ ይኸውም መቊጠሪያ ለብዙ ሕመሞች መድኀኒት ነው፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ✤ ✤ ✤ አቡነ ገብረ እንድርያስና ሊቀ ሰማዕቱ ስለ ሃገራችን በተቀበሉት ቃል ኪዳን ሰላምና ጤና ያውርዱልን፤ ጠላታችንን ከሃገራችን ያባርሩልን፨ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#ፎቶዎቹ ፤ እመቤታችን ከልጇ ጋር ያረፈችበት ገዳመ ቊስቋም ማርያም ገጽታ የሚያሳዩ _______________________________ ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡ ይህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭) የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ ፈጣን ደመና የተባለችውም እመቤታችን ነች፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡ እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡›› ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም) ኅዳር ፮ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡ ፍቶዎች በመ/ር ልዋም | የቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት :: #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

የቊስቋም ክብረ በዓልን በየት ሊየከብሩ ዐስበዋል??? #ኅዳር #፮፤ #በዓለ_ቊስቋም_፡፡ (በግብፅ ሀገር ባለች ደብረ ቊስቋም ዋሻ ከ፫ ዓመት ከ፮ ወር ስደቷ ያረፈችበት)፡፡ #በመላው_ዓለም_የቊስቋም_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ (ሌሎች ያልጠቀስናቸው አብያተ ክርስቲያናት ካሉ አሳውቁን) #በአዲስ_አበባ_የቊስቋም_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #መንበረ_ንግሥት_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ_፤ (#፫፻፷፭ት #ቀናት_ሙሉ_ዝክር_በማኅበረ_ሰላም_መድኀኔዓለም_የሚዘከርባት_ቤ/ክ) አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፥ ቊስቋም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ/ጊዮርጊስ (መርካቶ) (4 ኪሎ) → ሽሮሜዳ (መነን) → ቊስቋም፤ ፪. #ደብረ_ናዝሬት_ቅዱስ_ዮሴፍ_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክለ ከተማ፥ ደጃዝማች መርዕድ መንገድ፥ ቀለበት መንገድ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) (ከላጋር) (ከ4 ኪሎ) → ቦሌ → ሳሪስ /ቃሊቲ ቀለበት መንገዱ ላይ/ ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ፫. #ቃሊቲ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ሚካኤልና_ደብረ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ (ቃሊቲ ቊስቋም) አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) (ከላጋር) (ከ4 ኪሎ) → ቃሊቲ መናኸሪያ → ሰፈረ ገነት ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ፠፨፠ #እንዲሁም_በድርብነት_የሚከበርባቸው_፤ ፬. #ኮልፌ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፥ ጠሮ፥ አራት መንታ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ/አቡነ ጴጥሮስ ዐደባባይ/ → ዊንጌት → ጠሮ፡፡ ወይም፤ ከመርካቶ ኮልፌ አጣና ተራ → ጠሮ ፭. #ማኅደረ_መለኮት_ወይብላ_ቅድስት_ማርያም_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ የሺ ደበሌ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → የሺ ደበሌ፡፡ ፮. #ላፍቶ_ደብረ _ኢያሪኮ_መድኀኔ_ዓለምና_መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡ ፯. #መዝገበ_ምሕረት_ፋኑኤልና_ቊስቋም_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ፥ አጀንባ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት (ከሜክሲኮ) → አየር ጤና → ካራ፡፡ ፰. #ጉለሌ_ሸጎሌ_ኪዳነ_ምሕረት_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ አዲሱ ገበያ ፥ ቶታል፥ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል (ወደ ዊንጌት በቀለበት መንገገዱ ትንሽ ሄደው)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (አስኮ) → አዲስ ገበያ /ጸዮን ሆቴል/፤ #በኢትዮጵያ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_ #፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #ደብረ_ፀሐይ_ፋርጣ_ቊስቋም _ቤ/ክ፤ (በ1254 ዓ.ም. የተመሠረተች) አድራሻው፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ/ወልድያ → ፋርጣ፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ፋርጣ፤ ፪. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም_፤ አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎጃም (በመርጡለ ማርያም) → መካነ ሰላም ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤ ወይም፤ ከአ.አ. ቦሌ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐ ቤቴ ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፡፡ ፫. #አምባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም፤ አድራሻው፤ ዋግኽምራ ሀገረ ስብከት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ሰቆጣ (ዋግኽምራ)፡፡ ፬. #ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ ቸቸላ (ሆስፒታል አጠገብ)፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → ሆስፒታል → ቊስቋም፤ ፭. #ደሴ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፡፡ #ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከብርባቸው_ #፩ #ጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #ግብፅ_ቊስቋም _ማርያም_ገዳም_፤ (#እስከ_ቅርብ_ዘመናት_በግብፅ_የኢትዮጵያ_ርስት_የነበረ_) አድራሻው፤ ግብፅ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ → ግብፅ → ገዳመ ቊስቋም፤

፠ በኢትዮጵያ ደረጃ ኅዳር 6 የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል፤ ደቡብ ወሎ፤ ወግዲ፡፡ ደብረ ፀሐይ ጎንደር ቋስቋም ማርያም፤ ጎንደር ከተማ ከሆስፒታል አጠገብ፡፡ ፠ በአዲስ አበባ ታቦተ
+6
፠ በኢትዮጵያ ደረጃ ኅዳር 6 የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል፤ ደቡብ ወሎ፤ ወግዲ፡፡ ደብረ ፀሐይ ጎንደር ቋስቋም ማርያም፤ ጎንደር ከተማ ከሆስፒታል አጠገብ፡፡ ፠ በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤ ፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (#365ት_ቀናት_ሙሉ_ዝክር_በማኅበረ_መድኀኔ_ዓለም_አዳራሽ_የሚዘከርባት_ቤ/ክ) ፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ) ፠ቃሊቲ ቊስቋም ማርያም ቤ/ክ፡፡ … ሌላም ካለ ይንገሩን..

#ኅዳር_6፤ ደብረ ቊስቋም፤ #እመቤታችን_ከልጇ_ጋርስ_ደትን_የጀመረችበት_ዕለት_ነው፡፡ **ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋርለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) ከተሰደደች በኋላ #ግንቦት_24_ደግሞ_በዓተ_ግብጽ_ (ወደ ግብጽ ወደ ደብረ ቊስቊም ገብታ ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫ ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማው ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንድ አምላክ ልጇን አዝላ፤ በአንዲት አህያ ላይ ተቀምጣ፤ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ፤ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች፡፡ ከገሊላ ተነሥታ በጭንቅ፣ በመከራ፣ በረሃብና በጥም፣ በሐዘንና በድካም፣ በእንባ ተጕዛ በዚህች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታ በሥደት እጅግ ብዙ መከራ ተቀብላለች:: † የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: † ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: † የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: † የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: † የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: † እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች፣ ደከመች፣አዘነች፣ አለቀሰች፣ እግሯ ደማ፣ ተንገላታች:: ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳን ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: #መድኃኔ_ዓለም_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_ተሰደደ? #ለምን_ስደቱን_ወደ_ግብፅና_ኢትዮዽያ_አደረገ? 1. ፠ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና(ኢሳ 19፥1፣ ዕን. 3፥7) 2. ፠ምሳሌውን ለመፈጸም፤ የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም፥ ያዕቆብ (እሥራኤል):፥ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: 3. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19፥1) 4. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: 5. ሰው መሆኑ በአማን (በእውነት) እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: 6. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና 7. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ፠ በመጀመርያ ድንግል ማርያም ከርጕም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነበር:: በዚያም የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች፡፡ ፠ በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች:: ‹‹እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ፡፡›› እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ) ፠ ቀጥላም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች፤ ፠ ከደብረ ቢዘን ደብረ ሐዊ፣ በደብረ ዳሞ፣ አኵሱም፣ ደብር ዐባይ፣ ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ቆይታለች፤ ፠ በዋልባም ቆይታቸው ልጇ ገዳሙን በኢትዮጵያ በብጨኝነት ራሱ የገደመውን ገዳም መሥርቶ እየባረከ ወደ ጣና ሄደዋል፡፡ ፠ በጣና ገዳማትም፤ በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሸዋ ሔዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች:: ፠ ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች፤ በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሀገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች፡፡ ፠ በደብረ ኤረር ተራራ ላይም ከልጇ ኢትዮጵያን በዐሥራትነት ተቀብላለች፡፡ ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል:: እመቤታችን የሄሮድስን ሞት ከሰማች በኋላ ቊስቋም ከሚባል ተራራ ላይ ሆና ደስታዋን አብረዋት መከራን ከተቀበሉት ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር አከበረች፡፡ ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ኅዳር 6 ቀን ቊስቋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል፤ ሐሴትንም አድርገዋል:: #ግብጽ_ደብረ_ቊስቋም_፤ ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቊስቋም ታንጻ ተቀድሳለች፤ የቅዱሳን ማደሪያም ሆናለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፤ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን፣ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን፣ አስከትሎ ወረደ፡፡ የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው፤ ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ኾኗል:: ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡ ***ኅዳር 5 ለኅዳር 6 ከዋይዜማው ጀምሮ የሚባለውን ሙሉ ሥርዐተ ማኅሌትም እነሆ ብለናል፤ መልካም የማኅሌት ሌሊት ይሁንልን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram (https://t.me/finotehiwot1927) Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)