የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 037 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 314,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 091 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 037 名订阅者。
根据 28 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 656,过去 24 小时变化为 67,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.79%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.16% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 447 次浏览,首日通常累积 346 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 29 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 037
订阅者
+6724 小时
+2117 天
+65630 天
帖子存档
16 030
፡
እኔ ሃሳባዊ
ስፈልግ ማልተኛ
ወዳጅ ዘመዶቼ
የስደት ጓደኛ
መሔድ መመለስ
ነው
ሲበዛ መባዘን
ራሴን ለማግኘት
ሌላውን የማጣ
የምከት ከሐዘን
፡
ምክኒያቴም
ግልጽ እንጂ
ከቶ አልተሰወረ
መቆጨት አያሻም
ከመዳፍ ላልገባ
በአክናፍ ለ በ ረ ረ።
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
16 030
Modelling AutoCAD 3D Animation and Engineering Tutorial መማር የምትፈልጉ ይህን YouTube channel Subscribe አድርጉ
https://youtu.be/cl47Z61gj_8?si=CRyQLOBhLXTxgkK6
16 030
ባለ ትልቅ ህልሞች ግና መንገድ የጠፋን በመኖር የዛልን ብዙዎች ነን! ግን ቀን እንጠብቃለን። ንግግራችን ሁሉ ህግ የሚሆንበት ፤ እስትንፋሳችን እስትንፋስ የሚሰጥበት ፤ የሆነ ቀን አለ ያሻነውን በሚገባው ዋጋ የምንሸምትበት የሆነ ቀን አለ በመኖር ስንበረታና እኛ እስካለን ድረስ!!!
16 030
፡
ከልቡ ነው መውደድ ጥጉ
ምርቃቱ ደርሶ የሚያኖር
ቁጣው እንኳ 'ሚያለመልም
መሰረቱን ጠበቅ አርጎ
ስብዕናን 'ሚገነባ ማንነትን የሚቀልም
በርትቶ የሚያበረታ
ምክሩ ከክፉ የሚያርቅ
የሚያበቃ ለቁምነገር
ለፍቶ ደክሞ ያሳደገ
እንዴትስ ከሀሳብ ይጠፋል
መች ይረሳል ያባት ነገር
አባት እኮ ......
ለልጁ እንቁ ጌጡ ነው
መመኪያ ምሳሌነቱ
ክብርና ሞገስ የሞላው
ያረገ ፍቅርን እምነቱ
ይመራል በቀና መንገድ
ያሳያል ስኬት ጥበቡን
ተዘርቶ የተጠበቀ
በብቃት ማፍራት ማበቡን
አባት እኮ ......
ባይታይ ሀሳብ ሲገባው
ይዞት ነው ውስጡን በውስጡ
አክብረው ለወደዱት ሰው
ስቀው ነው ፍቅር የሚሰጡ
በርትቶ እያበረታ
አለሁ እያለ የሚያፀድቅ
የሚያበቃ ለቁም ነገር
እንዴትስ ከሀሳብ ይጠፋል
መች ይረሳል ያባት ነገር
✍Mekdi
፡
16 030
፡
ባቅምህ እየተጣጣርክ
የኑሮ ስሩን አጠንክር
ክንድህን ለስራ አበርታ
ምርኩዝህ ይሆንልሃል
ነገ ላይ እድሜ ሲያዳክም
ጉልበትህ የከዳህ ለታ
እይበት ደስታ አለምህን
ስኬትን ተጎናፀፈው
በራስህ ይበልህ ደሰ ደስ
በላብህ ሰርተህ ስትበላ
እንዲያ ነው አንጀትህ የሚደርስ
፡
16 030
፡
እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)
መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
...... ስልጠናው ሳይኖርህ
በሚያድጥ ዳገት ላይ በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች ሳይፎርሹ መቅለብ
ደርዘን ሙሉ አሎሎ
አሎሎ ቢጠፋ እሾህ ተድበልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ማለፍ ሹልክ ብሎ
እንደ ህልም እሪታ በሰለለ ገመድ
...... ባንድ እግር መራመድ
ይሄን ሁሉ አድርገህ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሃል አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ
ምንም ባትታደል አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ .....
ያልተራገፈ ጥርስ ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ አጨብጭብ ለራስህ
፡
16 030
፡
ጥርጉ መንገድህን
ገድበው ከያዙ
እንዳትንቀሳቀስ
ገባር አሰናድተህ
ጅረትህን ተወው
ወንዝ ሆነህ ፍሰስ
ያኔ
ውቅያኖስህ ነው
የመገደብህ መልስ።
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
16 030
፡
ለምን መሄድ አስፈለገ
ዳግም ዞረሽ ልትመጪ
ምን ሊፈይድ መመላለስ
ተደላድለሽ ላትቀመጭ
ወይ ጠቅልለሽ ላትወጪ
አንቺን ልተው ስፍጨረጨር
ካረፍሽበት ከልቤ ላይ
ሊጠፋ ሲል መልከ ገፅሽ
በአዲስ ተስፋ ይሞላኛል
እንደ ተራ ቀላል ነገር
መጣሁልህ የሚል መልስሽ
ተይ ግድ የለም .....
ቁምነገሬን ችላ ብለሽ
በነፍሴ ላይ አትቀልጂ
እኔን ብለሽ ከመጣሽ ነይ
ካልተመቸሽ ልሂድ ካልሽም
ላትመለሽ ሆነሽ ሂጂ
፡
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
