የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 932 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 411,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 116 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 932 名订阅者。
根据 25 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 604,过去 24 小时变化为 -23,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.64%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.10% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 419 次浏览,首日通常累积 334 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 26 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 932
订阅者
-2324 小时
+1447 天
+60430 天
帖子存档
15 974
🚛 ከባድ ተሽከርካሪው ገደላማ ስፍራ ላይ ሲጓዝ ሚዛኑን መጠበቅ ባለመቻሉ ወደ ገደላማው ስፍራ ሲወድቅ ታይቷል፡፡
መጋቢት 30 2018 - እሮብ
ለበ
ሲኖትራክ ይማር🙏
15 974
ማን ይጠረጥራል
ጠልፎ እንደሚጥል ምርኩዝ ያደረጉት
እኔስ ምን ኣውቃለው
ኣቅም እንኳ እንደሚያንስ ጠጎ ለመነሳት
የከርሞው እንዲሽር
ማንን እና እንዴት
ካሳ ይጠየቃል በገዛ ራስ ጥፋት..
. meron
15 974
ወገን ስለዚህ አስረዱን በነዳጅ ጭማሪ ምክንያት የማሳጅ ዋጋ በየጊዜው እየጨመረ ነው በማለት ደንበኞች ቅሬታ እያቀረቡ ነው?!
በእርግጥ የቧንቧ ውሃ እስክትመጣ ለሳምንታት ሳንታጠብ እየጠበቅን ያለነውን አይመለከትም!
15 974
" ሜሉ ተሻለሽ ውሎሽ እንዴት ነበር " አልኩኝ ጥያቄዎቼን አከታትዬ እና ትኩስ ግንባሯን እየሳምኩ
" ደናነኝ ብሩኬ ግን ምሳ በልተካል " አለችኝ ጤንነቷ ሳይሆን የኔ በርሃብ መዋሉ አሳስቧት
" እኔማ በልቻለሁ ይልቅ ላንቺ እያሰብኩ ነበር ምሳ እንድትሰራልሽ ቤሪን ነግሬያት ነበረ መጥታለች " ? አልኩ
" አሁን አሁን ነው የወጣችው መክሰስም ሰርታልሃለች " አለችኝ አይን አይኔን በናፍቆት እያየች
" እሺ ያከሆነ ተጣጥቤ ልብሴን ቀይሬ ምግቡን ይዤ መጣሁ " ብዬ ሻውር ገብቸ ልብሴን ለባብሸ ምግቡን ይዤ ሜሉ ወደተኛችበት ሶፋ አመራሁ
" ተነሺ ! ተነሺ ! " ብዬ የለበሰችውን አንሶለ ገለጥኩ " እንዴ ! ለምንድነው ሻወር ወስደሽ ልብስ ያልቀየርሺው ? ደሞም ቅድም በስልክ ለቤሪም ነግሬያት ነበረ ትታጠብ ብዬ አልነገረችሽም ?" አልኩኝ ንድድ ብየ
" ነግራኛለች ግን እኔ እምቢ አልኩ " አለች ዝግ ባለ ድምፅ
" አሁን ተነሺና ሻወር ውሰጂ " አልኳት ከሶፋው ቀና እያረኳት
እምብዬው ! እምብዬው ! ብላ ደረቴ ላይ ፊቷን ቀብራ ዝም አለች
" ለምንድነው ማትታጠቢው ደሞም ዶክተሩን አናግሬዋለሁ መታጠብ ትችላለች ብሏል " አልኩኝ ፊቷን ከደረቴ ቀና ለማድረግ እየሞከርኩ
" እየበረደኝ ነው አልታጠብም አለች " ፊቷን ቅጭም እያደረገች
" እሺ ውሃውን አሞቀዋለሁ "
" ሙቁን አልወደውማ ! " አለች ትከሻዋን ሰበቅ አድርጋ
" ጭራሽ በዚህ እንጨቃጨቅ ? ለምንድነው ምልሽን ማትሰሚ ?" አልኩ ጥያቄዬን ከንዴት ጋር ቀላቅዬ
" ኡፍ ! ብሩኬ ኡፍ ! " ብላ በተደገፈችው ትራስ ደረቴን መታ አድርጋ ለመታጠብ ገባች
እኔም ሻወሯን እስከምትጨርስ ትኩስ ነገር ላፈላላት ኪችን ገባሁ ።
✍ Henok
15 974
ሰበር 🔥
አሜሪካ እና ኢራን የ2 ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል ። የሆርሙዝ ሰርጥም ሙሉ ለሙሉ ይከፈታል ።
አሁን ገበያውን ጣሪያ ያወጣህ ነጋዴ ሁላ እኛ ሳንቀጥለው ጦርነቱን በጊዜ አውርድ!!!
15 974
አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር‼️
#በአዲስ_አበባ ከተማ ሥጋ በኪሎ 650 ብር እንዲሸጥ ተወሰነ‼️
#የአዲስ_አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የሸቀጦች እጥረት እንዳይከሰትና ገበያው እንዲረጋጋ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ቢሮው በተለይ የሥጋ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በአንድ ኪሎ 650 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።
መንግስት ደሞ April the fool. አለፈ እኮ
15 974
አንቺ ሴት ለምንድነው ምትጨነቂው ? ለምንድነው የምታለቅሺው? በይ አሁን ተነሺ ! ወገብሽን እሰሪ የወንድ ጥገኛ አትሁኚ በራስሽ ቁሚ ፈጣሪሽን ይዘሽ ወደ ፊት ቀጥይ 💪💪💪
ይቺ አለም የውድድር ናት ውድድሩን ምታሸንፊው ቁጭ ብለሽ አይደለም ይልቅ ቁጭ ያልሺበት ጊዜ አሁን አልቋል ። አሁን ጊዜው የምትንቀሳቀሺበት ነው ። ዓላማሺን ከፊት አድርጊው ለቤተሰቦችሽ መከታ ሁኚ ። ቤተሰቦችሽን ለመርዳት ፆታሽ ወንድ መሆን አያስፈልግም ዓላማና ወኔ ይኑርሽ ። የሀገራችን ኢኮኖሚ ለመንቀሳቀስ አመቺ ባይሆንም አንቺ ግን ልዩ ሴት ነሽ መንገድ አታጪም አንድን ጉንዳን ይዘን በአፈር ውስጥ በነፍሱ ብንቀብረው ጉንዳኑ ሲንቀሳቀስ አፈሩ እየተሸረሸረ ከተቀበረበት ይወጣል ያ የሚሆነው ደግሞ በመንቀሳቀሱ ነው ። አንቺም ተንቀሳቀሺና ከላይሽ ላይ ያሉትን ጭንቀቶችንሽ አራግፊ ።
ጠንካራ ሴት ሁኚ እሺ ፈጣሪ ካንቺ ጋር ነው አይዞሽ 💪💪💪💪
✍ Henok
15 974
ሁሌም ከምቀመጥበት ቦታ ቁጭ ብየ አስባለሁ ። ማሰብን ትክዝ ማለትን ባንድ ነገር ላይ ትኩረት ሰጥቸ መመልከትን እወዳለሁ ።
ሰው ቤት መጥቶ ስብስብ ሲል አልወድም ወደ ፀጥተኛውና ከቀዝቃዛው ክፍሌ እገባለሁ ። ብዙ ወሬ አልወድም በችሎታዬም አልኩራራም ። አለባበሴ ቀለል ያሉ ናቸው ። ቡና በጣም እወዳለሁ የቡና ደምበኛዬም ሜላት ናት እኔን ትረዳኛለች። ሁሌ ምቀመጥባት አብዛኛው ሰው ከሚቀመጥበት ቦታ ፈንጠር ብላ ያለች አንድ ወንበርና አንድ ጠረንጴዛ ያለች ቦታ ናት ። ሌሎች በጀማ ተቀምጠው ስለ ሀገራችን ኢኮኖሚ ፣ ስለ ፖለቲካ ፣ ስለ ግለሰብ ፣ ስለ ቤተሰባቸው ሚስጥርም ጭምር እዚ ቡና ቤት ቁጭ ብለው እንደ Party አበባ ይበትናሉ ። እኔ መፅሐፌን ከፍቸ ቡናዬ ጋ አጣጥማለሁ።
አዲስ ሰውም ስተዋወቅ በቀይ መስመር ዙሪያዬን አጥራለሁ ። ያቺን ቀይ መስመር ካለፈ ግን ግንኙነቱን አቋርጣለሁ ስለ ራሴ ብዙ ማውራት አልወድም ። እኔን የሚመስጠኝ ሰው አዲስ ነገር ለማወቅ የሚጓጓ እንጂ የሰውን ደካማ ጎን አምጥቶ እኔ ጋ ለሃሜት የሚመጣን አልቀበልም ። ያ የራሴ ቀይ መስመር ነው ። ለዛም ይመስለኛል ብዙ ጓደኛ የሌለኝ ። ሃሜት ላይ የተመሰረተ ጓደኝነት አሸዋ ላይ እንደ ተሰራ ቤት ነው በትንሽ ስህተት ይፈርሳል ።
እንደ ባዘቶ የጠራውን ብቸኝነቴን እወደዋለሁ ፀጥታ ላይ መቆየት ዝምምምምም ማለት ጭጭ ማለት ትኩረት ማድረግ እ ወ ዳ ለ ሁ ❤
✍ Henok
15 974
ድንበርን በእባብ እና አዞ‼️
ህንድ ድንበሯን ለመጠበቅ እባቦችን እና አዞዎችን ልትጠቀም መሆኑ ተሰማ‼️
ሂንዱ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ሃይል መመሪያን በመጥቀስ እንደዘገበው
በህንድ-ባንግላዴሽ ድንበር በሚገኙ ወንዞች፣ረግረጋማ ቦታዎች እና አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎች ላይ አዞ እና እባብን ለድንበር ጥበቃ ለማሰማራት እቅድ መነደፉን ዘገባው ጠቅሷል።
ምስል-በ AI የበለፀገ
15 974
አንዳንዴ ውስጥህ ሊያታላልህ ሚሞክረው አንዳንድ ነገሮች ከሌሎች ይልቅ ለአንተ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በማሳመን ነው።
ለምሳሌ የምትሸጠው ነገር ለአንተ ገንዘብ ላይ ገንዘብ ማምጫ ሊሆን ይችላል ለአንዱ ግን የእለት እስትንፋሱ ነው።
15 974
የአባቴ ጥንካሬ ሁሌም ሳስበው ይገርመኛል ። አንድን ነገር አሳካለሁ ብሎ ላመነበት ነገር ተስፋ አይቆርጥም እስከ መጨረሻው ይፋለማል ።
አባቴ ድንቁርናን አይወድም በመንጋ ማሰብን አይወድም ። አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ በጠቆመበት መንገድ አይሄድም ቆም ብሎ ያስባል፣ ይጠይቃል ያውቃል።
ልጅ ሆኜ ከወንድሜ ጋ ኳስ እየተጫወትን " እኔንም አስገቡኝ "? አለ እኛም ግባ ብለን መጫወት ጀመርን
መሃል በገባ ጭዋታ ነበረ እየተጫወትን የነበረው እኔ ከመሃል ሁኜ ኳሷን ለመንካት እየታገልኩ እነሱ ( ወንድሜና አባቴ ) አላስነካ አሉኝ ።
" አረ በቃኝ ደክሞኛል" ብዬ ከጨዋታው ወጣሁ እሱም ወደ እኔ ተጠግቶ " ይሀውልህ ልጄ መሃል በገባ ጨዋታ ላይ ያንተ እንቅስቃሴ ዝግ ያለ ከሆነ እነሱ እንዲያርፉ ክፍተት እየሰጠህ ነው ። አንተ በፍጥነት ሮጠህ ኳሷን መቀማት አለብህ ካልሆነ ይደክምሃል ተስፋም ትቆርጣለህ ። ያንተ ፍጥነት እነሱን ያስጨንቃቸዋል አንተ በሮጥክ ቁጥር ለማን ኳሷን እንደሚሰጡ ይወዛገባሉ አንተም ትቀማለህ ግን ለዚያ ደግሞ ያንተ ፍጥነትና ተስፋ አለመቁረጥ ትልቅ ሚና አላቸው ። "
አሁን እኮ ነው ያሰብኩት አባቴ ትልቅ መምህሬ ነው ። ሰሞኑን ስልችት ሲለኝ ያነቃቃኝ የአባቴ ንግግር ።
✍ Henok
15 974
<<
በራስ ለመቆም ቆርጠን የተነሳል ለት
ነኝ ብለን ያልነው ማንነት ይጠፋል።
በቤተሰብ በጓደኛ በማህበረሰብ
ተደግፈን ከሩቅ ሆነን የተቸነውን ህይወት እንኖራለን
እንፈርድበት የነበረውን የሰው ድካም ሆነን እናገኘዋለን ።
ኩራታችንና ፍርሃታችን የመኖር ጠላት ይሆኑን ይጀምራል ኣይመጥነኝም ያልነውን ጭራሽ እናሳድዳለን።
ህይወት የተነገረን እንዳልነበር የሰውን ተሞክሮ የመድገም ያህል ግልጽ እንዳይደል በራስ መቆም ስንጀምር ይገባናል።
ከሰው ኣስተያየትና ኣመለካከት በላይ የውስጥ ሰላም ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እንረዳለን
ትርምስምሱ ወደወጣበት ኣለም ስንነቃ
የነበረው እንዳልነበር ይሆናል እኛም፡ያልሆነውን የመሆን እድል ይኖረናል ።
ብዙ ነገራችን ልክ እንዳልነበር ካለንበትም ሰብረን መውጣት እንዳለብን ይሰማናል።
ችግሩ ሚመጣው የመሰማቱ ግዜ፡ላይ ኣደለም ሰምተን መለወጥ እንዳለብን ያመንን ግዜ ላይ ነው። ችግሩ ትልቅ መነዋወጥን ያመጣል ይንን ኣውቆ መቀበል ተቀብሎም ወዳልነበርነው ማንነት እና ሆነን ወደማናቀው ልንሆነው ወደምንሻው እኛ
የመቀየር መንገዱን ስንጀምር የዛኔ ግን ጀግንነቱ ይለያል።
>>
15 974
ስለ ሆሳዕና (Palm Sunday) የሚገርሙና ምናልባትም የማታውቋቸው እውነታዎች፦
"ሆሳዕና" የሚለው ቃል ትርጉም
ብዙዎቻችን "ሆሳዕና" ማለት የምስጋና ቃል ብቻ ይመስለናል፤ ነገር ግን ትርጉሙ "አሁን አድን" (Save us now/Please save) ማለት ነው። ሕዝቡ ኢየሱስን ሲቀበሉት "ጌታ ሆይ አሁን አድነን" ብለው እየለመኑትና እየጸለዩለት ነበር።
የአህያዋ ምስጢር (ሰላም እንጂ ጦርነት አይደለም)
በጥንት ዘመን ነገሥታት ለጦርነት ሲወጡ በፈረስ ላይ ይሳፈሩ ነበር። በሰላም ጊዜና ለደስታ ሲመጡ ግን በአህያ ላይ ይሳፈራሉ። ኢየሱስ በአህያ ላይ መሳፈሩ "እኔ የሰላም ንጉሥ እንጂ የጦርነት ንጉሥ አይደለሁም" የሚል ትልቅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው።
የዘንባባው (Palm) ምስጢር
ዘንባባ በዛ ዘመን "የድል" (Victory) ምልክት ነበር። ሰዎች ዘንባባውን መሬት ላይ ያነጠፉት ኢየሱስን እንደ አሸናፊ ንጉሥ ስለቆጠሩት ነው። እኛም ዛሬ በጣታችን ላይ የዘንባባ ቀለበት የምናደርገው ያንን የድል ምልክት ለማስታወስ ነው።
የሕፃናት ጩኸት
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው፣ በዛን ዕለት በቤተ መቅደስ ውስጥ በከፍተኛ ድምፅ "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ" እያሉ የጮሁት ሕፃናት ነበሩ። ሽማግሌዎቹና ፈሪሳውያኑ ዝም እንዲሉ ቢፈልጉም፣ ኢየሱስ ግን "እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ብሎ የሕፃናቱን ንጹሕ ምስጋና ተቀብሏል።
የኢትዮጵያ ሆሳዕና ልዩነት
በሌሎች ሀገራት ዘንባባውን ይዘው ብቻ ነው የሚሄዱት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግን ዘንባባውን ቀለበት፣ አክሊልና መስቀል አድርገን እንሰራዋለን። ይህ የሚያሳየው ኢየሱስን በልባችን አንግሰን፣ በመስቀሉ ድል ማግኘታችንን የምንገልጽበት የራሳችን ውብ ባህልና ዕምነት ነው።
እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳች
15 974
ሆሳዕና❤️🩹
"ሕፃናት 'ሆሳዕና በአርያም'🌿 እያሉ በንጹሕ ልባቸው ዘመሩ... ጌታ ሆይ የእኛንም ልብ እንደ ሕፃናቱ ንጹሕ አድርግልን።
Enkuan aderesachu evry1🫶🏻
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
