የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
前往频道在 Telegram
2 752
订阅者
-224 小时
+197 天
+5130 天
帖子存档
+9
የበዓለ ጰራቅሊጦስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ ።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባረገ በአስረኛው ቀን በተነሳ በሃምሣኛው ቀን ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች አምሳል የወረደበት በተዘጋ ደጃፍ የነበሩ ሐዋርያት ኃይል ያገኙበት ፣በአንድ ቀን ሶስት ሺህ ነፍሳት የተመለሱበት ታላቁ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን በዓለ ጰንጠቆስጤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የሐረርጌ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገ/መድሕን ንጉሴ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ገ/ሥላሴ በላይ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ ዋና አስተዳዳሪ፣ የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አዕምሮ ምስጋናው እና ሌሎችም የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት፣መምሕራን፣ የየሰንበት ት/ት ቤት አገልጋዮችና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ጰራቅሊጦስ
'' ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ዘሠረጸ እም አብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት''
በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው።
መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ
ጰራቅሊጦስ:- ናዛዚ ፣ መጽንዒ፣ መስተፍሥሒ ፣ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው።
ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ''እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ'' ብሎ ለሐዋርያቱ በሰጣቸው ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ ድንገት እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት መላው የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በሁሉም ላይ አረፉባቸው በዚህ ጊዜ ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በተለያዩ በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎለመሱ፤ ጥቡዓን ሆኑ፣ ፍርሃት ከውስጣቸው ተወግዶ መንፈሳዊ ድፍረት አግኝተዋል፤ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ሰማያዊ ሀብት ዕውቀትና ጸጋን ታድለዋል።
በዚህ ዕለት ሐዋርያት በተገለጠላቸው ቋንቋ ሲያስተምሩ ተቃዋሚ አይሁዳውያን ''ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ'' እያሉ ሐዋርያትን አሟቸው ቅዱስ ጴጥሮስም ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትሉት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ ሰዓቱም ገና ጠዋት ሦስት ሰዓት ነው
ይልቁኑ እናንተ በተንኮል ሰቅላችሁ የገደላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ከክፋታቸው ተመልሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመኑ በዚያች ብቻ ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ተመልሰዋል ዕለቱም የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ይባላል።
ከሶስቱ አካላት አንዱ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ጠብቆት አይለየን የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤታቸው በረከታቸው ይደርብን አሜን።
ጰራቅሊጦስ
“ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም መጽንኢ (በእምነት የሚያጸና)፣ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ)፣ ናዛዚ (ያዘኑትን የሚያረጋጋ)፣ መስተፍስሒ (የተጨነቁትን የሚያስደስት)፣ ከሣቲ (ምስጢርን የሚገልጽ) ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያርግ ሲል ቅዱሳን ሐዋርያትን ”እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” አላቸውና ዐረገ፡፡ ይህን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በኢየሩሳሌም ከተማ በጽርሐ ጽዮን በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ሁሉም በአንድ ልብ ኾነው በጾምና በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በሚያርግበት ጊዜም ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ተሰብስበው በአንድነት ሳሉ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐረገ በአሥረኛው ቀን በተነሣ በሃምሳኛው ቀን የጰራቅሊጦስ እለት ጧት በሦስት ሰዓት እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡
https://youtu.be/89NGmkNBgX4?si=ZbCkLomEs6Jq_Vwq
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ!!!
የበዓለ ጰራቅሊጦስ ዝማሬ
(በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅ/ ሚካኤል ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት)
የስሙ ምስክር
የስሙ ምስክር ያደረጋችሁ
ሐዋርያት ድንቅ ነው ግብራችሁ
ሐዋርያት ተገልጧል ክብራችሁ
ሑሩ ወመሀሩ ተብላችኋልና
እንዲሰማ ቃሉ የመንግሥቱ ዜና
አይታችኋልና የእጆቹን ተአምራት
ሰበካችሁ ለዓለም የመዳንን ብሥራት
መከራ መስቀሉን እንድትታገሱ
በበዓለ ሃምሳ ቃኝቷችሁ መንፈሱ
በአምሳለ እሳት ልሳናት ተከፍተው
አሕዛብ ተመለሱ በወንጌሉ አምነው
በዓለም ተነቦ ፊደል ሕይወታችሁ
በአንድ ቃል በአንድ ሐሳብ ታትሞ ልባችሁ
መሞት መነሣቱን ማረጉን ክርስቶስ
በበዓለ ሃምሳ ተሰብኳል በጴጥሮስ
የወንጌልን መረብ በእምነት ጥላችሁ
ለተጨነቀች ነፍስ ሰላምን ሰብካችሁ
የክርስቲያኖች ቤት በዓለም ተተክላ
ይኸው ታበራለች በክርስቶስ አምና
"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" ማቴ 19 ÷6
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጋብቻችሁን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸማችሁት የሰንበት ትምህርት ቤታችን የፍኖተ ብርሃን አገልጋይ እህታችን ሣራ ተዘራ እና ወንድማችን ሱራፌል መዝገበ የአብርሃምን እና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ ጋብቻችሁን ይባርክላችሁ።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ከልሎ በፍቅርና በጤና ይጠብቃችሁ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!
እንኳን ደስ አላችሁ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
በሰንበት ት/ቤታችን በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ የምርጫ መርሐግብር የማስታወሻ ፎቶዎች ከብዙ በጥቂቱ
ደብረ ምጥማቅ
ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ።
እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል። አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።
ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ።
ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ።
ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር።
እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።
እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፍኖተ ብርሃንን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች የተከናወነ የምርጫ ሂደት ሪፖርት
ያለፈው መጋቢት 20/2018 ዓ.ም አስመራጭ ኮሚቴዎች በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ ሲሆን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአዘጋጃቸዉ ሁሉም ስልጠናዎች ላይ በመገኘት ስልጠና ወስደዋል በዚህም መሰረት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መዋቅር በሚያዘዉ መሰረት በጎግል ፎርም / Google Form / እና በተለያዩ መንገዶች የአባላት ጥቆማ በመቀበል ከተጠቆሙት አባላት ዉስጥ 20 / ሃያ / አባላት ለስራ አመራር ( 40% ወይም 8/ ስምንት /ከመደበኛ አባላት 60% ወይም 12 / አሥራ ሁለት / ከልዩ መደበኛ አባላት ) እንዲሁም 8 /ስምንት / አባላትን ለኦዲትና ኢንስፔክሽን በመስፈርቱ መሰረት በመለየት በደብሩ ለሰባት ቀን ፀሎተ እጣን በማስደረግ በምርጫው እለት የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ያሬድ ለገሰ ፣ ከክ/ከተማ መ/ር ሚኪያስ ደስታ እና ተሾመ አምዲሳ በታዛቢነት በተገኙበት በጠቅላላ ጉባኤዉ የእጣ ማዉጣት መርሐ ግብር አከናውነናል ።
በዚህም መሰረት ከመደበኛ አባላት 4 /አራት/ አባላት ለስራ አመራር ሲመረጡ 4 /አራት/ አባላት በተጠባባቂነት ተይዟል ።
ከልዩ መደበኛ አባላት 7/ሰባት/ አባላት ለስራ አመራር ሲመረጡ 4/አራት/አባላት በተጠባባቂነት ተይዟል ። 5 /አምስት/ አባላት ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ሲመረጡ
3 /ሦሥት/ አባላት በተጠባባቂነት ተይዟል ።
በዚህም መሰረት የአስመራጭ ኮሚቴ ያስመረጣቸዉ አባላት ዝርዝር :-
=> ለኦዲትና ኢንስፔክሽን በዕጣ የተመረጡ
1, አቶ ሰለሞን ለገሰ
2, አቶ ሚኪያስ ፍቅሩ
3, ዲ/ን በኃይሉ ተፈራ
4, ዲ/ን ሸዋንግዘዉ ሀብቴ
5, አቶ ፀጋዘአብ ገ/መስቀል
=> ተጠባባቂ ዕጣ
የወጣላቸዉ ኦዲትና ኢንስፔክሽን
1, መ/ር አንዱአምላክ በፍቃዱ
2, ወጣት ጌታቸዉ ከበደ
3, ኢ/ር አሸናፊ ጥበቡ ሲሆኑ
=> 40% ከመደበኛ አባላት በዕጣ
የተመረጡ የስራ አመራር
1, ወጣት አብርሃም አስራት
2, ወጣት ዮናታን ብርሃኑ
3, አቶ በረከት ፍቅሩ
4, ዲ/ን አሌክሳንደር ወ/ገብርኤል
=> በተጠባባቂ ዕጣ
የወጣላቸዉ የስራ አመራር
1, ዲ/ን አብርሃም ታደሰ
2, ወጣት ተመስገን ገ/እግዚአብሔር
3, ወጣት የአብሥራ አክሊሉ
4, ወጣት ምትኩ አሰፋ
=> 60% ከልዪ መደበኛ አባል
በዕጣ የተመረጡ
1, መጋቤ ሠናያት መ/ር ወንድወሰን መኮንን
2, ኢ/ር ዳዊት አበበ
3, ቀሲስ ዮሴፍ ይኩኖአምላክ
4, ወጣት አበራ መላኩ
5, ወ/ት ሩት ሞገስ
6, አቶ ላቀዉ ይርጋ
7, ዲ/ን ዳንኤል ተክሌ
=> ለአዲስ አበበ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
በጠቅላላ ጉባኤ 12 ተኛ ሆኖ የተመረጠ
8, ዲ/ን ደረጄ ኤቢሳ
=> በተጠባባቂ ዕጣ የወጣላቸዉ
1, አቶ ሙሉጌታ ሰማን
2, ወ/ሮ ዮርዳኖስ ገ/እግዚአብሔር
3, መ/ር ስለሺ ይርጋ
4, ዲ/ን ዮናታን አርአያ
ሆነው ሰንበት ትምህርት ቤታችንን በአመራርነት ያገለግሉ ዘንድ ተመርጠዋል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን አገልግሎታችንን ይቀበልልን!!
