2 994
订阅者
无数据24 小时
+57 天
+530 天
帖子存档
2 994
+6
እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!!
Congratulations!!!
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ17ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 479 ተመራቂዎቹን ነገ ቅዳሜ 20/10/2018ዓ.ም በደማቅ ስነስርዓት ያስመርቃል።
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 479 የቅድመ ምረቃ፣ ድህረ ምረቃ እና የስፔሻሊቲ ተማሪዎችን ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው ግቢ ያስመርቃል።
ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 539 ሴቶች ሲሆኑ፣940 ወንዶች ናቸው።
ከተመራቂዎቹ መካከል 45 የሕክምና ዶክተሮች እና 15 ስፔሻሊስት ሐኪሞች ይገኙበታል።
ውድ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ17ኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎች፣ወላጆች እና ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ! ተመራቂዎች ለወደፊት ጉዞአችሁ የላቀ ስኬትን ከልብ እንመኛለን።
@wachemoo
2 994
#WachemoUniversity
ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁ ዋናውን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ እና እንዲሠራላችሁ የምትፈልጉ የተቋሙ ምሩቃን ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዋናው ዲግሪ ከማተሚያ ቤቱ በቀጥታ ታትሞ የሚመጣ በመሆኑ ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
እስከ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም የምትመዘገቡ ብቻ በመጀመሪያ ዙር ህትመት የሚደረግላችሁ ሲሆን፤ ከግንቦት 20/2018 ዓ.ም በኋላ የምትመዘገቡ በሁለተኛው ዙር የሚታተምላችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምዝገባ ለማድረግ 👇🏼
https://forms.gle/QnLVmNFTi9K7YdJh7
2 994
+9
የ 1ሺ 447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
የ 1ሺ 447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በአብሮነት በመሆን በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በእለቱም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተገኝተዋል ።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ በመልዕክታቸው፦ የኢድ አል-አድሐ ወይንም የአረፋ በዓል የእስልምና እምነት ተከታዮች ከፈጣሪ ዘንድ ያገኙትን ታላቅ በረከት፣ ፍቅርና አንድነት በጋራ የሚዘክሩበት ዕለት ሲሆን ይህም ታላቅ በአል ፍጹም ታማኝነትን እና ታዛዥነትን ያስተምረናል ብለዋል።
ኢድ አል-አድሐ የደስታና የፈገግታ ቀን ብቻ ሳይሆን ራስን የመሰዋት፣ የመረዳዳትና በአንድነት የመቆም ታላቅ መንፈሳዊ ትምህርት የሚቀሰምበት ውብ በአል ነው ብለዋል።
አክለውም ዶ/ር ዳዊት እንደተናገሩት በዓሉ በሰዎች መካከል ያለውን የርህራሔ፣ የደግነትና የወንድማማችነት ትስስርን ይበልጥ ያጠነክራል በማለት ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ መልካም የኢድ አል-አድሐ ( አረፋ ) በአል እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
@wachemoo
2 994
የእንኳን የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ መልዕክት ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት
ለዩኒቨርሲቲያችን እስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ፤
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዩኒቨርሲቲያችን ዋቸሞ፣ የተለያየ እምነትና ባህል ያላቸው ዜጎች በጋራ በፍቅርና በወንድማማችነት የሚኖሩባት፣ ዕውቀትና ጥበብ የሚቀሰምባት የልቀት ማዕከል ናት። ይህ በዓል በመካከላችን ያለውን አብሮነት፣ መከባበርና ሰላም ይበልጥ የሚያጠናክር እንዲሆን ምኞቴ ነው።
በተለይም በበዓሉ ወቅት የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና ያለንን ለሌሎች በማካፈል የታወቀውን የእስልምና እምነት እሴት በተግባር በማሳየት፣ ለአቅመ ደካሞች እጃችሁን እንድትዘርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በአረፋ በዓል የምናሳየው የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል በሥራችንና በትምህርታችንም ላይ ተንጸባርቆ፣ ሀገራችንንና ተቋማችንን ወደተሻለ ከፍታ ለማድረስ በጋራ እንድንቆም አሳስባለሁ።
በድጋሚ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!
ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
@wachemoo
2 994
+9
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በቴማቲክ ምርምሮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
*****
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በቴማቲክ ምርምር ፕሮጀክት ላይ በዛሬው እለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
በዕለቱም የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አካ/ም/ቴክ/ሽ/ማ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳራ ሽኩር፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አካ/ም/ቴክ/ሽ/ማ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አምሮ፣ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አካ/ም/ቴክ/ሽ/ማ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንዋር አህመድ፣ ሌሎች የዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ይህ ስምምነት በዩኒቨርሲቲዎቻችን መካከል ያለውን የምርምር ትብብር እና አጋርነት እንዲጠናከር የሚያግዝ ሲሆን፤ ችግሮቻችንን ለመፍታት፣ ሀብት ለመሳብ እና ከፍተኛ የምርምር ተጽእኖ ለማፍራት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
ምርምሩ በተለይም በሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ልማት ላይ ትኩረት በመስጠት በሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የሚሰራ ሲሆን፤ በክልሉ ውስጥ ያለ የህጻናት ልማት፣ የሴቶች ሚና እና ጎጂ ባህላዊ ልማዶችን በትንተና ያቀርባል ብለዋል።
አክለውም ዶ/ር ሳራ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የተጠናከረ ትብብር ሲኖር ሀብት የመጋራት እና ከፍ ያለ የምርምር አቅም እንደሚኖር ተናግረዋል።
በመጨረሻም ይህን መሰል ስምምነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመጥቀስ ለተደረገው የጋራ ስምምነት ዩኒቨርሲቲዎቹን ከልብ አመስግነዋል።
ግንቦት 12/2018 ዓ.ም
ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Let Your Light Shine in the Society!
@wachemoo
2 994
መልካም ዜና
የመዉጫ ፈተና ያለፉም ያላላፉም ተመራቂ ተማሪዎች ሐሙስ 13/11/2015 ዓ.ም በሚደረገው የምርቃ መርሃ ግብር ለይ እንድሳተፉ የተወሰነ በመሆኑ ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ።
Congratulations!
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
2 994
የመውጫ ፈተና ውጤት መታየት ጀመረ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በ " ኦላን ላይን " ማየት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ችሏል።
ምንም እንኳን ትምህርት ሚኒስቴር ውጤት መታየት የሚጀምረው ከማታ ጀምሮ መሆኑን ቢገልጽም ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተማሪዎችን የፈተናውን ውጤት እያዩ መሆኑን አረጋግጠናል።
የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username እና Password በማስገባት ነው።
ድረገፁ ተመራቂዎች ፈተናውን ማለፍ አለማለፋቸውን ካገኙት ውጤት ጋር Pass / fail እያለ ያሳውቃቸዋል።
2 994
ተማሪዎችየመዉጫ ፈተና ውጤታችሁን ከእሑድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣችሁን Username በመጠቀም በዚህ ሊንክ በ https://result.ethernet.edu.et በመግባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።
