ch
Feedback
SMH General Construction

SMH General Construction

前往频道在 Telegram

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(Eng sintayehu melese) tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

显示更多

📈 Telegram 频道 SMH General Construction 的分析概览

频道 SMH General Construction (@ethioengineers1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 23 449 名订阅者,在 家居与建筑 类别中位列第 418,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 425

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 23 449 名订阅者。

根据 21 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -286,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 20.32%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.83% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 765 次浏览,首日通常累积 2 071 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 26

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(Eng sintayehu melese) tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

凭借高频更新(最新数据采集于 22 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 家居与建筑 类别中的关键影响点。

23 449
订阅者
无数据24 小时
-647
-28630
帖子存档
🙏Stress ዓይነቶች 1. Tensile Stress (የመዘርጋት ውጥረት) ✅ቁሱ ሲጎተት የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅የSteel Reinforcement ✅Steel Tie Rod 2. Compressive Stress (የመጨመቅ ውጥረት) ✅ቁሱ ሲጨመቅ የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅Column ✅Concrete Block ✅ኮንክሪት በCompression ውስጥ በጣም ጠንካራ ነው። 3. Shear Stress (የመንሸራተት ውጥረት) በሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ምክንያት ቁሱ ሊንሸራተት ሲሞክር የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅Beam በSupport አቅራቢያ ✅✅Bolts Rivets

Flexible Pavement Layers (1) Wearing Course 👉ይህ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ የሚጓዙበት ንብርብር ነው። ስራው 👉መንሸራተትን መቀነስ 👉ውሃን መከላከል 👉ለስላሳ የመንገድ ገጽ መስጠት (2) Binder Course 👉Wearing Courseን ይደግፋል 👉የትራፊክ ጭነትን ወደ Base Course ያስተላልፋል (3) Base Course 👉የመንገዱ ዋና ጭነት ተሸካሚ ንብርብር 👉ከተመረጠ ድንጋይ (Crushed Aggregate) ይሠራል (4) Sub-base 👉Base Courseን ይደግፋል 👉ውሃን ያስወግዳል (Drainage) 👉የጭነት ስርጭትን ያሻሽላል (5) Subgrade 👉Subgrade የመንገዱ የተፈጥሮ አፈር ወይም የተጠናከረ አፈር ነው። 👉የSubgrade ጥራት የመንገዱን ዕድሜ በጣም ይወስናል።

⚡️የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes of Bid Opening) ለተጫራቾች መላክ እንዳለበት ያውቃሉ? - የመንግሥት የግዥ መመሪያዎችም ሆኑ የዓለም አቀፍ አበዳሪዎች (እንደ የዓለም ባንክ ያሉ) ሕጎች የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes) ወዲያውኑ ለተጫራቾች መላክ እንዳለበት በግልፅ ያስገድዳሉ። ይሁን እንጂ በተግባር ግን ይህ ሲደረግ ብዙም አይታይም። -  በመክፈቻው ላይ የተነበቡ ዋጋዎች፣ ቅናሾች እና የሲፒኦ ዝርዝሮች ተጫራቾች እንዲያውቁት በማድረግ ተጫራቾች የግዥ ሂደቱ ፍትሃዊ እና በሕግ መሠረት እየተመራ መሆኑን እንዲያምኑ ያደርጋል፤ ይህም ለወደፊቱ ተቋሙ የተሻሉና ተወዳዳሪ ዋጋዎችን እንዲያገኝ ይረዳል። - ግዥውን የሚፈፅመው ተቋም ይህን ካላደረገ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes of Bid Opening) እንዲላክላቸው መጠየቅ ይችላሉ

⚡️በTender Evaluation የሚመረመሩ ነገሮች ✅የኮንትራክተሩ ልምድ ✅የፋይናንስ አቅም ✅የቴክኒክ ብቃት ✅የመሳሪያ አቅም ✅የባለሙያ ቡድን ✅የሥራ ፕሮግራም ✅የቀረበው ዋጋ

Setting Out (ማስቀመጫ መስመሮች) ይህ በSurvey Engineer የሚሰራ ሥራ ነው። የሚደረጉ ሥራዎችBenchmark ማረጋገጥ ✅Grid Line ማስቀመጥ ✅Building Corners ማስቀመጥ ✅Foundation Center Line ማስቀመጥ መሣሪያዎች ✅Total Station ✅Level Machine ✅GPS (እንደ ፕሮጀክቱ አይነት) 🙏🙏 በSetting Out የሚፈጠር ስህተት በሙሉ ፕሮጀክቱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፤ ስለዚህ በConsultant መረጋገጥ አለበት።

Shrinkage እና Swellበተፈጥሮ አፈር ላይ እነዚህ ለውጦች ይከሰታሉ። 1.Swell 👉አፈር ሲቆፈር መጠኑ ይጨምራል። ምሳሌ 100 m³ የነበረ አፈር ከተቆፈረ በኋላ 120 m³ ሊሆን ይችላል። 2.Shrinkage 👉አፈሩ ተመልሶ ሲጠናከር መጠኑ ይቀንሳል።

🙏Method Statement ምንድን ነው? ⚡️Method Statement (MS) ማለት አንድ ሥራ እንዴት፣ በምን መሣሪያ፣ በማን፣ በምን የጥራት እና የደህንነት ሂደት እንደሚሰራ የሚገልጽ የጽሑፍ ሰነድ ነው። ዓላማው ✅ሥራው በአንድ ወጥ ዘዴ እንዲሰራ ✅ጥራት (Quality) እንዲጠበቅ ✅ደህንነት (Safety) እንዲረጋገጥ ✅የውል መስፈርቶች እንዲከበሩ

Lap Splice (የብረት መቀጠያ) የብረት ፋብሪካዎች የሚያመርቱት ስታንዳርድ የብረት ርዝመት 12 ሜትር ነው። ስለዚህ ረጅም ህንፃዎች ወይም ቢሞች ላይ ብረትን መቀጠል (Lap) ግድ ይላል። ✅የመቀጠያ ርዝመት (Lap Length): እንደ ዲዛይኑ እና እንደ ኮንክሪቱ ግሬድ የሚወሰን ቢሆንም፣ በግምት አብዛኛውን ጊዜ በሀገራችን 50×Φ (ሃምሳ ሲባዛ በብረቱ ዲያሜትር) ይወሰዳል። ለምሳሌ፡ የ Φ16 ብረት መቀጠያ ርዝመት 50×16 mm=800 mm (80 cm) መሆን አለበት። ቦታ (Location): ✅Beam ላይ: ከፍተኛ የቴንሽን (Tension) ዞን ላይ ብረትን መቀጠል አይፈቀድም። ለምሳሌ በቢም ታችኛው ክፍል መሃል ላይ (Mid-span) እና በቢም ላይኛው ክፍል ድጋፍ (Support) አካባቢ ላፕ ማድረግ አይመከርም። ✅Staggering: ሁሉም መቀጠያዎች በአንድ መስመር ላይ ማረፍ የለባቸውም። አንዱ ከተቀጠለበት ቦታ ወጣ ብሎ ሌላው እንዲቀጠል (Staggered) መደረግ አለበት።

🙏RFI (Request for Inspection) ምንድን ነው? 👉RFI ማለት ተቋራጩ (Contractor) አንድ ሥራ ተጠናቆ እንደሆነ በመግለጽ፣ አማካሪው (Consultant/Engineer) መጥቶ እንዲመረምረው የሚያቀርበው የምርመራ ጥያቄ ነው። 👉 እዚህ የተጠቀሰው RFI ማለት Request for Inspection ነው። በአንዳንድ ፕሮጀክቶች RFI ማለት Request for Information ሊሆን ይችላል፤ ስለዚህ በፕሮጀክቱ የሰነድ ስርዓት ውስጥ ያለውን ፍቺ መከተል አስፈላጊ ነው። 2. RFI መቼ ይቀርባል? RFI የሚቀርበው ሥራው ከመሸፈኑ (Cover) ወይም ወደ ቀጣዩ ደረጃ ከመሄዱ በፊት ነው። ለምሳሌ፦ ✅ Excavation ከተጠናቀቀ በኋላ ✅ Rebar ከተገጠመ በኋላ ✅ Formwork ከተጠናቀቀ በኋላ ✅ Concrete Casting ከመጀመሩ በፊት ✅ Waterproofing ከመሸፈኑ በፊት 3. RFI የሚያካትተው ✅RFI Number ✅Project Name ✅Location ✅Activity Description ✅Drawing Number ✅Specification Reference ✅Inspection Date ✅Contractor Signature ✅Consultant Decision

🙏በኢትዮጵያ የሚጠቀሙ የጨረታ ዓይነቶች 1. Open Tender (ክፍት ጨረታ) ✅ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟላ ተቋራጭ መወዳደር ይችላል። 2. Restricted Tender (ውስን ጨረታ) ✅የተመረጡ ተቋራጮች ብቻ ይሳተፋሉ። 3. Direct Procurement (ቀጥታ ግዥ) ✅በሕግ በተፈቀዱ ልዩ ሁኔታዎች ብቻ ይፈጸማል።

✅IPC የሚያዘጋጁት ማን ነው? 👉Site Engineer – የተሰራውን ሥራ ይለካል። 👉Quantity Surveyor (QS) – IPC ያዘጋጃል። 👉QA/QC Engineer – የጥራት ሰነዶችን ያረጋግጣል። 👉Resident Engineer / Consultant – ያረጋግጣል እና ያፀድቃል። 👉Employer – ክፍያውን ይፈጽማል።

🙏ለSite Engineer ወርቃማ ምክሮችሁልጊዜ ውሉን ያንብቡ። ✅የሚፈጠር ማንኛውም ለውጥ በጽሑፍ ያስመዝግቡ። ✅Site Diary በየቀኑ ይሙሉ። ✅ፎቶ ማስረጃዎችን ያስቀምጡ። ✅ማንኛውንም የውል ጉዳይ በቃል ሳይሆን በደብዳቤ ያረጋግጡ።

⚡️በኢትዮጵያ የሚታዩ የContract Management ስህተቶችVariation በጽሑፍ ሳይፀድቅ ሥራ መጀመር ❌ Daily Records አለመያዝ ❌ EOT በሰዓቱ አለመጠየቅ ❌ Site Instructions አለመመዝገብ ❌ ሰነዶችን በአግባቡ አለማስቀመጥ

🙏የSite Engineer የEarthwork ተግባራት 👇Cross Section መለካት 👇Cut & Fill ማስላት 👇Survey Team ማስተባበር 👇Compaction Test ማረጋገጥ 👇Earthwork IPC ማዘጋጀት 👇የDaily Progress Report ማዘጋጀት

⚡️Contract Management ምንድን ነው? 👉Contract Management ማለት የተፈረመውን ውል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በትክክል መተግበር፣ መቆጣጠር እና መዝጋት ነው። ዋና ዓላማው፦ ✅ጊዜ (Time) ✅ወጪ (Cost) ✅ጥራት (Quality) ✅ውል (Contract) 🙏በአንድ ላይ እንዲተዳደሩ ማድረግ ነው።

photo content

Site Engineer የቀን የሥራ ዝርዝርSite Diary መሙላት ☑ Daily Report ማዘጋጀት ☑ QA/QC Inspection ☑ Safety Inspection ☑ Labour መቆጣጠር ☑ Equipment መከታተል ☑ Progress መለካት ☑ Consultant ጋር መግባባት

🍉የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ጨረታ ሂደትን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በተከታታይ እንመልከት። 1. የፕሮጀክት ዝግጅት (Project Preparation) 🔑ይህ ከጨረታው በፊት የሚደረግ ደረጃ ነው። በዚህ ወቅት የፕሮጀክቱ ባለቤት (Employer) የሚከተሉትን ያዘጋጃል፦ ⏳የአዋጭነት ጥናት (Feasibility Study) ⏳የዲዛይን ሥራ ⏳የBOQ (Bill of Quantities) ⏳የቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን ⏳የግንባታ ስዕሎች (Drawings) ⏳የፕሮጀክት ወጪ ግምት (Engineer's Estimate) ⏳የበጀት ፈቃድ 🍎ማስታወሻ: በDBB (Design-Bid-Build) ስር እነዚህ ሁሉ ጨረታ ከመውጣቱ በፊት ይጠናቀቃሉ። 2. የጨረታ ሰነድ ዝግጅት (Bidding Document) 🔑በዚህ ደረጃ የጨረታ ሰነድ ይዘጋጃል። በአብዛኛው የሚካተቱት፦ 🌶Invitation for Bid (IFB) 🌶Instructions to Bidders (ITB) 🌶Bid Data Sheet 🌶Qualification Requirements 🌶BOQ 🌶Drawings 🌶Specifications 🌶General Conditions of Contract (GCC) 🌶Special Conditions of Contract (SCC) 🌶Contract Forms 3. የጨረታ ማስታወቂያ 🔑ጨረታው በጋዜጣ፣ በመንግስት ድረ-ገጽ ወይም በመግዥ ስርዓት ይገለጻል። ✤በማስታወቂያው ውስጥ፦ 👉የፕሮጀክቱ ስም 👉የሥራ አይነት 👉የጨረታ መዝጊያ ቀን 👉Bid Security 👉የብቃት መስፈርቶች ይገለጻሉ። 4. የጨረታ ማብራሪያ (Pre-Bid Meeting) ተጫራቾች ጥያቄ ያቀርባሉ። 🔑ከዚያ Employer ለሁሉም ተጫራቾች አንድ ዓይነት መልስ ይሰጣል። 🌶አስፈላጊ ከሆነ Addendum ይወጣል። 5. የጨረታ ማቅረብ 🔑ተጫራቾች የሚከተሉትን ያቀርባሉ፦ 🍎ቴክኒካል ሰነድ 🍎የዋጋ ሰነድ 🍎Bid Security 🍎የብቃት ማስረጃ 🍎የሥራ ልምድ 6. የጨረታ መክፈቻ (Bid Opening) 🔑በመዝጊያ ሰዓት ይከፈታል። 👉በዚህ ጊዜ ብቻ የሚነበቡት፦ 🌶የተጫራች ስም 🌶የቀረበ ዋጋ 🌶Bid Security መኖሩ 🌶ቅናሽ (Discount) ካለ 👉በዚህ ደረጃ ማንም አሸናፊ አይባልም። 7. የጨረታ ግምገማ (Bid Evaluation) 👍ይህ በጣም ወሳኝ ደረጃ ነው። ✤በቅደም ተከተል፦ 🌶Preliminary Examination 🌶Technical Evaluation 🌶Arithmetic Correction 🌶Financial Evaluation 🌶Post Qualification 🔑በእነዚህ በቅደም ተከተል ይከናወናሉ።

ሲሚንቶ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውና በጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርቆ ስራ ከጀመረ አመታትን ያስቆጠረው የመንግስት እና የግል ሽርክና የሆነው ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
ሲሚንቶ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውና በጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርቆ ስራ ከጀመረ አመታትን ያስቆጠረው የመንግስት እና የግል ሽርክና የሆነው ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደላሎች እየተፈተነ ይገኛል። ከወራት በፊት ከ1200-1500 ብር ይሸጥ የነበረው ይህ ሲሚንቶ አሁን ላይ ዋጋው በእጥፍ ጨምሮ ደብረብርሃን ከተማ ላይ እስከ 2500 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ፋብሪካው እየተቋቋመበት ቦታ ለሚ ላይ 1900 ብር እየተሸጠ ይገኛል። የሲሚንቶ አስመጪዎች እና ነጋዴዎች አሁን ከፋብሪካው ሲሚንቶ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን እና በደላላ መሆኑን ገልፀውልናል። ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ ከጀመረ ጀምሮ የሀገሪቱን የሲሚንቶ እጥረት በመቅረፍ እና ገበያውን በማረጋጋት እረገድ አስተዋጽኦው የጎላ ቢሆንም አሁን በደላሎች እየተፈተነ በመሆኑን የሚመለከተው አካል መፍትሔ ቢሰጥበት መልካም ነው።

⚡️በቁፋሮ (Excavation) ውስጥ የሚጠቀም ሾሪንግ (Shoring) ምንድን ነው? Shoring (ሾሪንግ) በቁፋሮ ሥራ ውስጥ የሚጠቀም ጊዜያዊ የመዋቅር ድጋፍ (Temporary Structural Support System) ሲሆን፣ የቁፋሮውን ወይም የትሬንች (Trench) ግድግዳዎች ለመደገፍ ያገለግላል። ዋና ዓላማው የአፈር መናድ (Soil Collapse) እንዳይከሰት፣ ሠራተኞችን ከአፈር መደርመስ (Cave-in) አደጋ ለመጠበቅ እና በአቅራቢያ ያሉ ሕንፃዎች፣ መንገዶች ወይም ከመሬት በታች ያሉ የአገልግሎት መስመሮች (Underground Utilities) በአፈር እንቅስቃሴ እንዳይጎዱ ማድረግ ነው። ለምን Shoring አስፈላጊ ነው? 1. የሠራተኞች ደህንነት (Worker Safety) ጥልቀታቸው ከ1.5 ሜትር (5 ጫማ) በላይ የሆኑ ቁፋሮዎች ከፍተኛ የአደጋ ስጋት አላቸው። Shoring የአፈር ግድግዳዎች እንዳይፈርሱና ሠራተኞችን እንዳይቀብሩ ይከላከላል። 2. የንብረት ጥበቃ (Asset Protection) በቁፋሮው ዙሪያ ያለው አፈር እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ የአቅራቢያ መንገዶች፣ ቤቶች፣ የንግድ ሕንፃዎች እና መሠረቶቻቸው (Foundations) እንዳይጎዱ ይጠብቃል። 3. የሥራ ቦታ ማዘጋጀት (Workspace Creation) ለኮንክሪት ማፍሰስ፣ የቧንቧ መዘርጋት (Pipe Laying) ወይም ሌሎች የመዋቅር ሥራዎች የተረጋጋና ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቦታ ይፈጥራል። የShoring ሥርዓቶች ዓይነቶች 1. Hydraulic Shoring (ሃይድሮሊክ ሾሪንግ) በቅድሚያ የተሠሩ የአሉሚኒየም ወይም የብረት ፓነሎች (Sheeting) እና የሚስተካከሉ የሃይድሮሊክ ሲሊንደሮችን ይጠቀማል። በትሬንች ቁፋሮ ሥራዎች በሰፊው ይጠቀማል፤ ምክንያቱም ከትሬንቹ ላይ ሆኖ በቀላሉ መትከልና ማስተካከል ስለሚቻል ሠራተኞችን ከአደጋ ይጠብቃል። 2. Soldier Pile Walls (H-Beam Shoring) ቁፋሮው እየተከናወነ ሲሄድ ከባድ የብረት H-ቅርጽ ምሰሶዎች (H-Beams) በተወሰነ ርቀት ወደ መሬት ውስጥ ይገባሉ። በእነዚህ መካከል የእንጨት ወይም የኮንክሪት ፓነሎች (Lagging) በመግጠም አፈሩ እንዳይፈርስ ይከላከላል። 3. Sheet Piling (የብረት ሺት ፓይል) እርስ በርስ የሚቆለፉ የብረት ሺቶችን (Steel Sheets) ወደ መሬት በመንዳት ቀጣይነት ያለው የመከላከያ ግድግዳ ይፈጥራል። በተለይ ለለስላሳ ወይም በውሃ ለተሞላ አፈር (Waterlogged Soils) በጣም ውጤታማ ነው። 4. Trench Boxes (Shields) በትሬንች ውስጥ የሚቀመጡ ትልልቅ እና ጠንካራ የብረት ወይም የአሉሚኒየም ሳጥኖች ናቸው። እነዚህ የአፈርን ግድግዳ በቀጥታ አይደግፉም፤ ነገር ግን ሠራተኞች በውስጣቸው በደህና እንዲሠሩ የመከላከያ ቅርፊት (Protective Shield) ይሆናሉ። Shoring እንዴት ይሠራል? Shoring በአብዛኛው ቁፋሮው እየጠለቀ ሲሄድ ከላይ ወደ ታች (Top-Down) ይገጠማል። ዋናው ሥራ፣ ለምሳሌ የመሠረት ግንባታ ወይም የቧንቧ ዝርጋታ፣ ከተጠናቀቀ በኋላ Shoring ከታች ወደ ላይ (Bottom-Up) በቅደም ተከተል ይወገዳል፤ በተመሳሳይ ጊዜም ቁፋሮው በጥንቃቄ በአፈር መሙላት (Backfilling) ይከናወናል። ማጠቃለያ Shoring በቁፋሮ ሥራ ውስጥ ለሠራተኞች ደህንነት፣ ለአቅራቢያ ያሉ መዋቅሮች ጥበቃ እና ለተረጋጋ የሥራ ቦታ መፍጠር የማይተካ ጊዜያዊ የመዋቅር ድጋፍ ሥርዓት ነው። የShoring ዘዴ ምርጫ በአፈር ዓይነት፣ በቁፋሮው ጥልቀት፣ በውሃ ሁኔታ እና በፕሮጀክቱ ባህሪ ላይ የተመሠረተ ነው።