1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ጽዱ እና ማራኪ በሆነች መዲናችን ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቅ እና የሚያጋጥም አደጋ ቢኖር ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተጠሪ ተቋማት ከወትሮ በላቀ ዝግጁነት ተግባራቸዉን እያከናወኑ ይገኛሉ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹና የቅድመ ሆስፒታል አምቡላንስ አገልግሎት ባለሙያዎች 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ጉባኤው እስኪጠናቀቅ ድረስ በዚያዉ የሚቆዩ ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ በዓድዋ ጀግኖች ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን ስላኖሩ እና የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት የዓድዋ ድልና ታሪክ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራትና የፓንአፍሪካኒዝም መሰረት መሆኑን ስለገለጹልን ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Ministirri muummee Barbaadoos Miyaa Motali siidaa gootota Adawaa jala abaaboo kaa'uusaaniitiif,yaadannoo injifannoo Adawaa daaw'achuun Injifannoo fi seenaa adawaa uummata gurraacha hundaaf boonicha fi bu'uura paan-afrikaanizimii ta'uusaa waan nuuf ibsaniif galateeffachuun barbaada.
Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee yaa eebbisu!
የተጠሪ ተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የነዋሪውን ፍላጎት የሚያረካ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተጠሪ ተቋማት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው አጋማሽ 6 ወራት አፈጻጸም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት በተገኙበት ተገመገመ።
በመድረኩ የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት፣ የመብራት አገልግሎት እና የእሳትና አደጋ ስጋት መከላከልና መቆጣጠር አገልግሎት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እጥረት ሲከሰት ስለ አገልግሎቱ ለመጠየቅ በቅርበት በወረዳ ሊሰጥ ይገባል፤ የመብራት አገልግሎት ሲቋረጥ ለጥገና የተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረግ ቢቻል ሲሉ ተሳታፊዎቹ ጠይቀዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በተደረገ ጥናት ከ55% በላይ በአብዛኛው የእሳት አደጋ የሚከሰተው በኤሌክትሪክ ምክንያት መሆኑን የተደረገው የፎረንሲክ ጥናት የሚያመለክት እንደሆነና ህብረተሰቡም ከኤሌክትሪክ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እግደሚገባ ማሳሰቢያ ሲሰጥ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ከወድሁ የጥንቃቄ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና አያያዝን ጨምሮ በሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሁም በመብራትና ውኃ በተመለከተ በተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የሚለከታቸው ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ ማቃለያ ሲሰጡ እንደገለጹት በመብራት አገልግሎት የታየው መሻሻል በሌሎች ተቋማት ለመድገም የሚመለከታቸው ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የነዋሪውን ፍላጎት የሚመጥንና የሚያረካ አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ በዓድዋ ጀግኖች ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊን ተቀብለው የዓድዋ ድል መታሰቢያን አስጎብኝተዋል::
በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ከተማችን የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን የዓድዋ ድል የአንድነት እና የጽናት ተምሳሌት እንዲሁም በትብብር ማንኛውንም ሃይል የማሸነፍ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል::
የሚዲያ ተቋማትንና ህብረተቡን እንደዚሁም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የአደጋ ቅነሳ የንቅናቄ መድረክ ሊካሄድ ነዉ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በከተማዉ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የሚዲያ ተቋማትና ህብረተሰቡን እንደዚሁም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የአደጋ ቅነሳ የንቃንቄ ስራ እንደሚካሄድ ኮሚሽኑ አስታዉቋል።
ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም የንቅንቄ ሰነዱ በተገመገመበት ጊዜ እንደተገለጸዉ ትኩረቱን በአደጋ ቅነሳ ስራ ላይ ያደረገዉ የዚህን የንቅንቄ ስራ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና ኮሚሽን መ/ቤቱ በጋራ የሚመሩት ሲሆን በከተማዉ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች ተቋማትም እንደሚሳተፉበት ተገልጿል።
የአደጋ ቅነሳ ንቅናቄዉ ስራዉ ህብረተሰቡ እና ተቋማት እንደዚሁም አመራሩ የአደጋ መከላከልን ስራን የዕለት ተዕለት ተግባሩ በማድረግ ከተማዋ ከአደጋ የተጠበቀች ሰላማዊ ከተማ እንደሚያደርጋትም ተገልጿል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ሬ ከሰዓት በኋላ ከመከላከያ ሠራዊታችን ጀነራል አመራሮች ጋር በሀገራዊ እና ቀጠናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለሚካሄዱ ጥናቶች የመረጃ ሰብሳቢዎችና አስተባባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የጥናት እና ልማት ትግበራ ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በቀጣይ ለሚከናወኑ ጥናቶች ለመረጃ ሰብሳቢዎች እና አስተባባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬዉ ዕለት ሰጥቷል።
የስልጠናዉ ዋነኛ አላማ የሚጠኑት ጥናቶች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ተደራሽ የሚደረጉትን አገልግሎቶች ከማሻሻል፣ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ከማዘመንና አንፃር የመፍትሄ አቅጣጫን የሚጠቁሙ እንደሆኑ ተመልክቷል። ጥናቶቹ ትኩረት የሚያደርግባቸው ዋና ዋና ርእሰ ጉዳዮች ለመረጃ ሰብሳቢዎቹ ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ ላይ በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ም/ስራ አስኪያጅና የጥናት እና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለፁት የመረጃ መሰብሰቡ ስራ በዋናነት በቀጣይ የከተማችንን የአገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመንና እንዲሁም ቀልጣፋ ከማድረግና አገልግሎቶቻችንን በይበልጥ አጉልተን በማሳወቅ ረገድ እንደግብአት የሚያገለግል መሆኑን ጠቁመዉ የሚሰበሰቡት መረጃዎች ጥራትን ማዕከል ያደረገ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
አክለውም ትክክለኛ መረጃ ለትክክለኛ ዉሳኔ ስለሚረዳ በቀጣይ የሚሰበሰቡት መረጃዎች በጥራትና በትኩረት መሰብሰብ ያስፈልጋል ሲሉም አጽንኦት ተናግረዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
እንደ ስሟ ዉብ አበባ፣ የሀገር ክብር ፈርጥ ፣
የአፍሪካዊያን ኩራት ፣የነዋሪዎቿ ምቹ ቤት - አዲስ አበባ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ በተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እየተሳተፉ ለሚገኙ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የአለምአቀፉ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም አምባሳደሮች በአዲስ አለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ክቡር የኢፌዴሪ ፕረዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በተገኙበት አውደ ርእይ የጎበኙ ሲሆን ማምሻውንም በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ታድመዋል።
የአዲስ አለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ለአፍሪካ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ተጨማሪ የመሰባሰቢያ ማዕከል ሆኗል ፤ እንግዶቻችን ሁለተኛ ቤታችሁ በሆነችው አዲስ አበባ የሚኖራችሁ ቆይታ ፍጹም ስኬታማ እና አስደሳች እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
