ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በህብረቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ዝግጁ ናቸዉ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻልና የሚያጋጥም አደጋ ቢኖር ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የኮሚሽኑ የአደጋ ምላሽ ባለሞያዎች የአደጋ መከላከልና መቆጣጣር ተግባራቸዉን እያከናወኑ ይገኛሉ። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹና የቅድመ ሆስፒታል አምቡላንስ አገልግሎት ባለሞያዎች ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በቦታዉ የተገኙ ሲሆን ጉባኤዉ እስኪጠናቀቅ ድረስ በዚያዉ እንሚቆዩ ተገልጿል።… See more

አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማእከል! የመዲናችን አዲስ መልክ!

በከተማችን ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ የሚከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተደራጀና ዘመናዊ የአደጋ መቆጣጠር ዝግጁነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋም ከሆነዉ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራሮች ጋር በከተማዋ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በተቀናጀ ስትራቴጂ እና የሪፎርም አጀንዳ ላይ ተመስርቶ ቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል። የዉይይት መድረኩን የመሩት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጀነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በከተማዉ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን የሚከተሉ የንግድም ሆኑ ማናቸዉም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ የማስተካካያ እርምጃ በመዉሰድ አደጋን አስቀድሞ መከላከል ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዉ አፈጻጸሙን አስመልክቶ አስገዳጅ ህግና ደንቦችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። አያይዘዉም በመኖሪያና በሌሎች አካባቢዎች የሚያጋጥሙ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል በከተማና በየአካባቢዉ ያሉ የህዝብና የተቋማት አደረጃጀቶችን ማሳተፍ እንደሚገባ ጠቅሰዉ ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ ማናቸውም አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚችል የተደራጀና ዘመናዊ የአደጋ መቆጣጠር መገንባት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በሌላ በኩል ኮሚሽን መ/ቤቱ የህብረተሰቡን ደህንነት ከማናቸዉም አደጋ በመጠበቅ ረገድ እንደዚሁም በሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች ሁሉ የህዝብ አመኔታ በማግኘት ህብረተሰቡ የአደጋ መከላከሉን ስራ እንዲያግዝ ማድረግ ይገባል ብለዋል። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በከተማዋ የሚያገጥሙ አደጋዎችን አስቀድሞ የመከላከል ስራው በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል ጠቅሰዉ ለዚህም የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በአደጋ መከላከሉ ሰራ ዉጤታማ እንዲሆንም ከተለያዩ ከህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ጋር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

መረጃ በመዲናችን አዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ:- 1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ፤ 2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤ 3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸውን እና ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሱ እናሳውቃለን። የከተማችን ነዋሪዎች ተርሚናሎቹ ወደ ነበሩበት እስኪመለሱ ድረስ ለምታሳዩት ትእግስትና ትብብር እናመሰግናለን፡፡

አዲስ አበባ የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሳታፊዎችን ወደ ምድረ ቀደምት፣ የፓን አፍሪካኒዝም መነሻ እንዲሁም የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ተምሳሌትና ኩራት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁ ትላለች። አዲስ አበባ እንደ ስሟ ዉብ እና አዲስ ሆና በድንቅ የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት ልታስተናግዳችሁ ተዘጋጅታለች። ውድ የከተማችን ነዋሪዎችም በተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንግዶችን ተቀብላችሁ እንደምታስተናግዱ እምነቴ የፀና ነዉ። እንግዶቻችን የሚኖራችሁ ቆይታ ፍጹም ስኬታማ እና አስደሳች እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ የፅ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት በጋራ ዉይይት አካሂደዋል። በቀጣይ ጊዜያት በጉባኤው የተቀመጡ የስራ አቅጣጫዎቹ ተፈፃሚነት ላይ ሁላችንም በመረባረብ ታላቅ ሀገር ግንባታ እና የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ላይ ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ አመራሮቹ አመልክተዋል። ጠንካራ ተቋም; ብሄራዊ ገዥ ትርክት፣ የሰላም ግንባታ፣ የሪፎርም ውጤታማነት እና ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ የከተማችን ብሎም የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውም በዚሁ ወቅት ተመላክቷል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ከጃፓኖች የንጽህና አጠባበቅ ምን እንማራለን? "ማነው ትምህርት ቤቱን ማጽዳት ያለበት? ራሱ ያቆሸሸው!". አንድ ጃፓናዊ ተማሪ “አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ቤቴን ማጽዳት አልፈልግም ነበር፤ ነገር ግን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን አካል ስለሆነ ተቀበልኩት። ትምህርት ቤቱን ማጽዳት በጣም ጥሩ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም የምንጠቀመውን ነገሮች እና ቦታዎችን የማጽዳት ሃላፊነት ልንወስድ አስፈላጊ መሆኑን እንደሚገባን ስለምንማር ነው." "ተማሪዎቹ ከሰባት የ50 ደቂቃ ክፍለ ጊዜ የረዥም ቀን ቆይታ በኋላ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ጓጉተው በመማሪያ ክፍሎቻቸው ወንበርና ጠረጴዛዎቻቸው ላይ ተቀምጠዋል። ተማሪዎቹ መምህራቸው ስለ ነገው የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ ጥቂት መርሐግብሮችን ሲናገር በትዕግስት አያዳመጡ ናቸው.... ከዚያም ቀጠለና መምህሩ አስከትሎ የዛሬው የጽዳት መርሐግብራችን :-አለና “እሺ ሁላችሁም ተማሪዎች ፣ የዛሬውን የጽዳት ዝርዝር ቀጥሎ እኖደሚከተለው እገልፃለሁ አለ.... " አንደኛ እና ሁለተኛ ረድፍ የተቀመጣችሁ ተማሪዎች:- የመማሪያ ክፍላችሁን ታጸዳላችሁ። ሶስተኛ እና አራተኛ ረድፍ የተቀመጣችሁ "ኮሪደሩ እና ደረጃዎች"ን በማለት ቀጠለ አምስተኛ ረድፍ ላይ የተቀመጣችሁ ሽንት ቤቱን ታጸዳላችሁ.... ከአምስተኛው ረድፍ ጥቂት ጩኸቶች ከመሰማታቸው በቀር ሁሉም ህጻናት ተማሪዎች ተነሥተው ከክፍል ጀርባ ካለው ቁም ሳጥን ውስጥ መጥረጊያዎቹን፣ ጨርቆችን እና ባልዲዎችን ያዙና ወደ መጸዳጃ ቤት ሄዱ። ተመሳሳይ ትዕይንቶች በመላው ጃፓን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የዘወትር የእለት ተእለት ተግባር ነው። በዚህ መንገድ በጃፓን በፅዳት ላይ በህፃናት ላይ በተሰራው ስራና መላው የጃፓን ህዝብ ጽዳትን ባህል በማድረጉም ለመጀመሪያ ጊዜ ጃፓንን የጎብኘ ሁሉ በአገሪቷ ጽዳትና ንጽህና ይማርካሉ ይላል የቢቢሲ ዘጋቢዎች ስቲብ ጆን እና አንጀልስ ማሪን ካቤሎ የጃፓን ተማሪዎች “ለ12 ዓመታት የትምህርት ቤት ሕይወት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጽዳት የሁልጊዜ የተማሪዎች የዕለት ተዕለት መርሃ ግብር አካል ነው” ። በቤታቸው የተማሪዎች ወላጆች የመኖሪያ ክፍላቸውን እና እቃዎቻቸውን ንፁህ አለማድረግ መጥፎ እንደሆነ ለልጆቻቸው ያስተምሯቸዋል።" ይላሉ ዘጋቢዎቹ የጽዳትና የንጽህና ጉዳይ በትምህርት ቤት ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ በማካተቱ ልጆቹ ስለ አካባቢያቸው ንጽህና ግንዛቤ እንዲያዳብሩ እና እንዲኮሩ ይረዳቸዋል። ማነው ማፅዳት ያለበት? ማነው ትምህርት ቤት ማበላሸት የሚፈልገው? አንድ ጃፓናዊ ተማሪ “አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ቤቱን ማጽዳት አልፈልግም ነበር፤ ነገር ግን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን አካል ስለሆነ ተቀበልኩት። ትምህርት ቤቱን ማጽዳት በጣም ጥሩ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም የምንጠቀመውን ነገሮች እና ቦታዎችን የማጽዳት ሃላፊነት ልንወስድ አስፈላጊ መሆኑን ስለምንማር ነው." በጃፓን ጎዳናዎች ላይ ቆሻሻ አይታይም የመንገድ ጠራጊዎች እንዲሁ አይታዩም። ለምን ጃፓናውያን በሙሉ እራሳቸውን ከጽዳት ጋር በማለማመድ ጽዳትና ንፅህናን ባህላቸው ሰላደረጉ።

ውብ አዲስ አበባ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

እንኳን ደስ አለን !…