1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ህዳርን ሲፀዳ !በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የፅዳት ንቅናቄ መርሀ-ግብር ለ5 ተከታታይ ቀናት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
ምክርቤቱ ያለመከሰስ መብት ያነሳው የተከበሩ አቶ ሰዒድ አሊ ከማል ሲሆን ግለሰቡ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩበት ወቅት የኮሪደር ልማቱን ምክንያት በማድረግ ከግል በለሀብት ጋር በመመሳጠር የመንግስት ሀብትን ለግል ጥቅም እንዲውል በማድረግ ከፍተኛ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ መሆኑ ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ጠቁመው የቋሚ ኮሚቴውን ውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ምክር ቤቱም በከባድ ሙስና ወንጀል በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት የቀረበውን ያለመከሰስ መብት የማንሳት ጥያቄ በጥሞና አዳምጦ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማከናወን ጀምሯል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽን ማብራሪያዎችን የሚሰጡ ይሆናል::
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ…
ከተለያዩ ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻን በህገወጥ መንገድ ባልተፈቀዱ ቦታዎች ላይ የጣሉ ባለቤቶች ተቀጡ ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚያስወግዱ ድርጅቶች እና ባለቤቶች ላይ የደንብ ቅጣት ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
በዚህም መሠረት በወረዳ 9 ደሴ ሆቴል የተባለ ድርጅት በቀን የሚደረገውን ክትትል በመሸሽ በምሽት ከድርጅቱ ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻና ተረፈ ምርት በህገወጥ መንገድ ባልተፈቀደ ቦታ በመጣሉ 50 ሺህ ብር ተቀጥቶ ቆሻሻውን እንዲያነሱ ተደርገዋል።
በተመሳሳይ በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ሐይሉ ጮማ ስጋ ቤትና ግሮሰሪ የተባለ ድርጅትም እንዲሁ ከንግድ ቤቱ የወጣ ቆሻሻን በህገወጥነት ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሲያስወግዱ በመገኘቱ 50,000 ብር ተቀጥቶ ቆሻሻውን እንዲያነሱ ተደርጓል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 ሙባረክ ጫት ቤት የተባለ ድርጅት በህገወጥ መንገድ የጫት ተረፈ ምርት እና ሌሎች ቆሻሻዎችን በማስወገዱ 20,000 ብር የተቀጣ ሲሆን ይህ ድርጅት ከዚህ ቀደም ከሰራው ስህተት ባለመታረሙና ድጋሚ በህገወጥ ድርጊቱ በመቀጠሉ ጫት ቤቱን የማሸግ እርምጃ ተወስዷል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ ይህንን አስመልክቶ እንደገለጹት የክ/ ከተማው ነዋሪዎች በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ ሁሉ በጽዳቱም ዘርፍ ከመኖሪያ ቤት፣ ከንግድ እና ሌሎች ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻን በአግባቡ የመያዝና የማስወገድ ሃላፊነትን በአግባቡ በመወጣት ከተማችንን ጽዱ እና ውብ ማድረግ ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ"ህዳር ሲጸዳ" የጽዳት ንቅናቄ ጎን ለጎን ከጽዳት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህገወጥነትን ለመከላከል ከክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ከፅዳት አስተዳደር ፣ ከሰላምና ፀጥታ፣ከፖሊስ እና ደንብ ማስከበር ጽ/ ቤት የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተከታታይነት ያለው ህጋዊ አሰራርን የማስከበር ስራ እያከናወነ ይገኛል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በዛሬው የአዲስ አበባ ካቢኔ 4ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በኮሪደር ልማት አካባቢ ያሉ የግል ባለይዞታዎች የቅድሚያ የማልማት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበት አግባብ ላይ፣ የተጀመሩ ግንባታዎች የቦታ ማስፋፊያ ጥያቄዎች ፣ለኃይማኖት ተቋማት እና የባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የቦታ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸዉ አኳያ በመመርመር እንዲፈቀድላቸው እና ወደ ልማት እንዲገቡ ውሳኔ አሳልፏል ።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለማስተዳደር እና ለማልማት የወጣው ረቂቅ ደንብን መርምሮ ፤ ለማህበረሰቡ ከሚኖራቸው የጎላ አገልግሎት ማሳለጥ በሚያችላቸው አግባብ በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስተግባሪነት እንዲፈፀም ወስኗል።
የህዳር ሲጸዳ" የፅዳት ንቅናቄ ያለበት ደረጃ በዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና በቢሮ ሃላፊ ማእረግ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በመዲናችን ሁሉም አካባቢዎች እየተካሄደ ያለውንና ከተጀመረ 5 ቀናት ያስቆጠረውን "የህዳር ሲጸዳ" ንቅናቄ ያመጣውን ለውጥ ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።
በተለይም በጉለሌ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በተካሄደው ምልከታ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከብልጽግና የ5ኛ አመት ምስረታ ጋር ተያይዞ እየተካሄደ ያለው የፅዳት ንቅናቄ አላማ በዋናነት የከተማችን ነዋሪ ፅዳትን ባህል እንዲያደርግና ፅዳትን የየእለት ተግባሩ አድርጎ እንዲመለከተዉ በማለም ነዉ።
ከፍተኛ አመራሮቹ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ባካሄዱት ምልከታም ከአንዳንድ የንግድ ድርጅቶች የመስሪያ ቦታቸውን እና አካባቢያቸዉን በፅዳትና በንጽህና በመጠበቅ ዙሪያና የሚያመነጩትን ቆሻሻ ተገቢ የአወጋገድ ሂደትን መከተል እንደሚገባቸው የሚያስገነዝብ የጋራ ዉይይት አድርገዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በየክፍለ ከተሞች የሚገኙ የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ቢሮዎች የጽዳት ሁኔታ፣ አደረጃጀትና የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ከተመለከቱ በሁዋላ የስራ አስኪያጅም ሆነ የጽዳት ዘርፍ መዋቅሩ የሚሰራበት ተቋም፣ የመኖሪያ ቦታና አካባቢ የጽዳት ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በከንቲባ ጽ/ቤት እና በጊቢ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጋር በመሆን “ወርቃማዋ ሰኞ” ብለን ዘወትር ሰኞ የምናደርገውን የዉይይት ፕሮግራም አንደኛ ዓመት ዛሬ ማለዳ አክብረናል።
እነሱ ጨለማው ሰኞ (Black Monday ) የሚሉትን እኛ ወርቃማው ሰኞ ብለን ላለፉት 52 ሳምንታት ከጥዋቱ 2 እስከ 3 ሰአት ባለዉ ጊዜ የከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የኮሙዩኒኬሽን እና የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በጋራ በመሆን በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን እና እየተመካከርን ሳምንቱ ሙሉ ወርቃማ እንዲሆንልን መልካም ምኞት ተለዋዉጠን አብረን ቡና ጠጥተን ስራችንን እንጀምራለን።
ይህንን የምናደርገዉ የበለጠ ለተገልጋዮች ቅርብ ለመሆን እና አገልግሎታችንን ለማሻሻል እርስ በእርሳችን የምንመካከርበት፣ የምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት እንዲሁም እንደ መሪ ታች ካሉ ሰራተኞቻችን ጋር ጭምር ማህበራዊ ህይወታችንን ከስራችን ጋር በማስተሳሰር ለመቀራረብ እና ሃሳብ ለመለዋወጥ ሲሆን በዚህ ሁኔታ 52 ሳምንታትን አሳልፈናል። በዛሬዉ ፕሮግራማችን ደግሞ ዶ/ር ምህረት ደበበ ስለ ስራ እና ህይወት (work and life balance) ሚዛን መጠበቅ ትምህርት አካፍለውናል።
ፕሮግራሙ በከንቲባ ጽ/ቤት ይጀምር እንጂ ወደ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት እና መስሪያ ቤቶች የሚሰፋ ሲሆን እስከ አሁን የሄድንበትን የ52 ሳምንታት ቆይታችንን ጥንካሬ እና ድክመት ለይተን ወደ ሌሎች ቢሮዎቻችን የምናስፋፋው ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ምርታማነት ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ዛሬ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚመሩ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝቻለሁ። ዕሴት በተጨመረበት ቡና ኤክስፖርት እና ብረታ ብረት ምርት ላይ የተካነው ኤኤምጂ ሆልዲንግስ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በመስተዋት እና በአሉሚኒየም ሥራዎች የሚታወቀው አንድነት መስተዋት ቴክኖሎጂ የግሉ ዘርፍ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽዖ ማሳያ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማሳሰቢያ
በከፍተኛ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ የሆነው የመርካቶ አካባቢ ነዋሪዎች ከሌላው አካባቢ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር…
See more
