1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በአድዋ ሲኒማ በሀገራችን የመጀመሪዉን ባለ ቀለም ፊልም “አስቴር “የተሰኘዉን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሀገራችን አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች በታደሙበት በይፋ መርቀን ከፍተናል።
ጥበብ ሀገርን በማነፅ ጉዞ ውስጥ አይነተኛ ሚና አላት። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዘርፉ የሀገራችንን የልዕናልና ጉዞ ሊያሳልጥ እንዲችል የኪነ-ጥበብ መሰረተ ልማቶችን ገንብቶ ለህዝቡ ጥቅም አቅርቧል፤ ይበልጥ የማስፋፋቱን ስራም አጠናክረን የምናስቀጥል ይሆናል።
የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተጠቀሙበት
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው እንዳስታወቁት ዛሬ ህዳር 8 በመርካቶ ድንች በረንዳ" ከቀኑ 6 ስአት 30 ተከስቶ የነበረዉ የእሳት ቃጠሎ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በስፍራው ተገኝተው ባደረጉት ርብርብ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን አስታዉቀዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የማህበር ቤት ባለቤቶች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ና ሌሎች አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የኮሪደር ልማት ስራው የከተማዋን ገፅታ በማሻሻልና በማደስ ለመኖሪያ ምቹና ሳቢ በማድረግ ሁሉም ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ተብሏል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የማህበሩ አባላት በሰጡት አስተያየት ልማትና የከተማ እድገት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በአፈጻጸም ሂደቱ ማብራሪያ ጠይቀዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የከተማዋ ልማት ዓለምቀፋዊ ተሞክሮን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመግለፅ፣ ነዋሪዎች የልማቱ ተባባሪ ለመሆን መዘጋጀታቸውን አድንቀዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም የልማት ተነሽዎችን መብት በማክበርና ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መግባቱን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው የኮሪደር ልማታችን ፕሮጀክት የአዲስ አበባ ውበት የሚያላብስ፣ የቱሪስት መዳረሻነሻቷን የሚጨምር እና ለነዋሪዎቿ ውብና ማራኪ ገፅታን የሚያጎናፅፍ ፕሮጀክት በመሆኑን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን እናንተም በበኩላቹ ለፕሮጀክቱ መሳካት እንድትተባበሩ ሲሉ ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ በዚህ ደረጃ እየተፋጠነ ያለው የእናንተ የህብረተሰበችን ቀና ተሳትፎ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ይገባል ተብሏል።
Lideta sub-city communication office
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
" የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና "
የብልጽግና ቤተሰብ የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ !! " በሚል መሪ ቃል በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ የብልጽግና ቤተሰብ የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
የብልጽግና ፓርቲ ቤተሰብ ጽዳት ዘመቻው ዋና ዓላማ ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ ማህበረሰቡ አስተሳሰቡን በመቀየር አካባቢውን ከአየር ብክለት በመጠበቅ ቆሻሻ ሀብት መሆኑን እንዲረዳ ማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የጉለሌ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እደተናገሩት ህዳር ሲታጠን በሚል በባህላዊ መንገድ ቆሻሻ ተሰብስቦ ይቃጠል ነበር አሁን ማጠኑን በማስቀረት ወደ ማጽዳት ዘመቻ እየሔድን ነው፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ በማድረግ ከሌሎችች የአለም ከተሞች ተወዳዳሪ በማድረግ ነዋሪዎቿ አካባቢያቸውንና ጤንነታቸው የተጠበቀ በአስተሳሰብ የበለፀጉ በኢኮኖሚ ያደጉ እዲሆኑ እንደሚገባና ቆሻሻ ሃብት መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በበኩላቸው ክፍለ ከተማውን የጽዳት ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ተግባራት በማከናወን በተለይም ጽዳት የአንድ ወቅት ስራ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራችን ለማድረግ ህብረተሰብ ተኮር እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል በህዳር ወር ቆሻሻን ከማቃጠል ወደ ህዳር ሲጸዳ በማረም ቆሻሻ ሀብት በመሆኑ ከማቃጠል ይልቅ በአግባቡ በማስወገድ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ብለዋል።
በክፍለ ከተማው በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ ብሎኮች በተካሄደው ጽዳት ዘመቻው የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የጽዳት አምባሳደሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።
Gullele communication-ጉለሌ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
"ህዳር ሲፀዳ!"በሚል መሪ ቃል በልደታ ክፍለ ከተማ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር በፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት አስተባባሪነት "ህዳር ሲፀዳ!"በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
የፅዳት ንቅናቄ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የልደታ ክ /ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ እንደገለፁት ጽዳት የአንድ ማሕበረሰብ የስልጣኔ መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ተግባሩ መደበኛ ሆኖ እንዲቀጥል ለነዋሪዎቻችን ግንዛቤ የመፍጠሩ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
አቶ ስንታየሁ አክለውም አዲስ አበባን እንደስሟ ውብና ፅዱ ለማድረግ እየተከናወነ በሚገኘው ስራ ላይ ነዋሪው ህብረተሰብ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
"በህዳር ሲፀዳ" መርሀ ግብር ላይ የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣ የወረዳ አመራሮች ፣የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ የሴፍቲኔት አባላት ፣ የፅዳት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሁነዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ጽዳት ስናፀዳ ሁሉም አካባቢውን ከማፅዳት ባሻገር በውስጣች ኢትዮጵያን የማይመጥኑ የተዛቡ አስተሳሰቦችን የማፅዳት እሳቤን ተላብሰን ነው"#አቶ_አዲሱ_ሻንቆ
******************
የብልፅግና ፓርቲ የተመሰረተበትን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የብልፅግና ቤተሰብ የፅዳት ዘመቻ በወረዳ 04 ጎተራ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ተካሄደ።
ፅዳቱን ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አዲሱ ሻንቆ(እጩ ዶክተር) ጽዳት ስናፀዳ ሁሉም አካባቢውን ከማፅዳት ባሻገር በውስጣች ኢትዮጵያን የማይመጥኑ የተዛቡ አስተሳሰቦችን የማፅዳት እሳቤን ተላብሰን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 5 ዓመታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን አከናውኗል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን ማስቀጠል ከአባላቱና ከደጋፊው ይጠበቃልም ብለዋል።
በፅዳት ዘመቻው ላይ ከአቶ አዲሱ በተጨማሪ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ፣ የወረዳ 04 አመራሮች ፣የጽዳት ሰራተኞችና አምባሳደሮች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የጎተራ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
Kirkos Communication-ቂርቆስ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
