ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
"ህዳር ሲጸዳ" የጽዳት ንቅናቄ በመዲናችን ሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል። መዲናችን ከብክለት የፀዳች ውብ፣ ማራኪ ለነዋሪዎቿ ተስማሚ ከመሆን ባሻገር ሁለንተናዊ ተምሳሌትነቷን ለማብሰር እያደረገች ያለውን ሁለንተናዊ ትጋት ለማሳለጥ በመታተር ላይ ትገኛለች። በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የብልፅግናን 5ተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የወጣቶች ቀን በሚል መሪ ቃል የፅዳት መርሃ ግብር በትናንትናው እለት ተከናውኗል። በንቅናቄው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል ፣ የየካ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና፣ የየካ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፓ/ዘርፍ አቶ ተራማጅ ተረፈ፣ የክ/ከተማ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ከሁሉም ወረዳ የተወጣጡ የወጣት ሊግ አመራር አመራርና አባላት ተገኝተዋል። ጽዳት የሁልጊዜ ተግባራችና ባህል ሆኖ መቀጠል አለበት ያሉት አቶ ይብሬ እስማኤል ‹‹ህዳር ሲጸዳ!›› በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ የጽዳት ንቅናቄው መደረጉ ከወትሮው ለየት ያደርጋልም ብለዋል፡፡ የክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና በበኩላቸው የንቅናቄ መርሃ ግብር ጽዳትን ባህል በማድረግ የበለጸገች ሀገርን ለመገንባት እንዲያስችል ዘንድ ሁሉም ወጣቶች ለጽዳት ተግባራት አጋዥ እንዲሆን አሳስበዋል፡፡ የካ በብልጽግናዊ የመደመር ዕሴቤና ትጋት የሁለንተናዊ ከፍታ ጉዞዋን በተጨባጭ እያስመሰከረች ትገኛለች። የመዲናዋ ድምቀት የሆነችዋ የካ በነዋሪዎቿ የተናበበ ትጋት፤ በማይደክሙ መሪዎቿ ቅንጅታዊ አሰራር አምራና ተውባ ከብከልት የፀዳች ለመሆን እየታተረች በዕምርታዊ የከፍታ ለውጥ ላይ ነች። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመረዳት እራሱንና አካባቢዉን ከአደጋ ለመከላከል የሚያስችለዉን የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን ጀምሯል። የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የክፍለ-ከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስታዉቋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገለግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ የምክር ቤታችንን 4ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አከናውነን ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱልን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እንዲሁም ማብራሪያ ሰጥተናል። ከተማችንን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እና የኑሮ ጫናን ለማቅለል እንዲሁም ዓለምአቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ ያከናወንናቸው ስራዎች ነዋሪዉን ተጠቃሚ ያደረጉ፣ ያስደሰቱ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መሆናቸውን የምክር ቤት አባሎቻችን የገለፁልን ሲሆን የኮሪደር ልማት ተነሺዎች አዲስ የገቡባቸው ቤቶች እና አካባቢዎች ንጹህ ተደርገው፣ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት እየተሟላላችው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀውልናል። በሌላ በኩል ህዝቡ እንዲመለስለት ያቀረባቸው ጥያቄዎችንም ያነሱልን ሲሆን በተለይ የዘገዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በፍጥነትና ጥራት እንዲጠናቀቁ፣ ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንዲሁም የልማት ተነሺዎች ከማህበራዊ ትስስራቸው ሳይበታተኑ ምቹ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤትና አካባቢ ማዘጋጀታችንን አጠናክረን እንድንቀጥል አሳስበውናል።እኛም በምክርቤት ከሰጠነዉ ማብራሪያ በላይ ተግባራዊ ምላሽ የምንሰጥይ ሆናል ። በተለወጠ አዲስ የስራ ባህል በጥራትና በፍጥነት በላቀ የኃላፊነት ስሜት የመረጠንን እና እምነት የጣለብንን ህዝብ ዝቅ ብለን ማገልገላችንን እንቀጥላለን! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ፣ ህጋዊ ደረሰኝ የመቁረጥ እና የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ነው፡- አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ፣ ህጋዊ ደረሰኝ የመቁረጥ እና የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡ ከምክር ቤት አባላት በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡት አቶ ጃንጥራር አባይ የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል ስልጠና በመስጠትና የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን እንዲሁም ውጤት የተገኘበት መሆኑን አንስተዋል፡፡ ይህን መሰል ማዕከል በሁሉም ክፍለ ከተሞች ማዳረስ ከበጀት አኳያ እንደማይቻል ነገር ግን በሂደት እየሰፋ መሄድ እንዳለበት አንስተዋል፡፡አሁን ላይ ይህንን ማእክል ማጠናከር ፣ማበልጸግ እና ማደራጀት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የወጣቶች የስብዕ እና መገንቢያ ማዕከላት ወደ ስራ አለመግባትን በተመለከተ ጉዳዩን ፈትሾ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ እና ማስተካከያ እንደሚደረግ ያነሱት አቶ ጃንጥራር እስከ አሁንም ማዕከላቱ ወደ ስራ ሳይገቡ መዘግየት እንዳልነበረባቸው ተናግረዋል፡፡ የአርሶ አደሮችን የይዞታ ካርታ በተመለከተ መመሪያውን ተግባዊ በማድረግ ረገድ መዘግየት አለ ያሉት አቶ ጃንጥራር ይህ ስራ እስካሁንም ማለቅ እንደነበረበት አስታውቀዋል፡፡ ይህም ከመረጃ አለመጥራት ጋር ተያይዞ መዘግየቱን አንስተዋል፡፡ ችግሩን አርሞ በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ስራውን ለመጨረስ አቅጣጫ መያዙን አንስተዋል፡፡ ከመስሪያ ቦታዎች ጋር ተያይዞ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄም 110 የመስሪያ ቦታዎችን በመመሪያው መሰረት በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችን በመለየት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ ረገድ ሰፊ ችግር እንደሌለም ጠቁመዋል ፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከማቅረብ አኳያ ላለፉት ዓመታት ትልቅ ስራ መሰራቱን ያወሱት አቶ ጃንጥራር ፡፡ በትራንስፖርት ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲሰፋ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም ላለፉት 2 እና 3 ዓመታት አውቶቡሶችን በመግዛት በማሰማራቱ በኩል ጥሩ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ በመልሶ ማልማት ተነሺ የሆኑ እና አቃቂ ፣ገላን፣ ጉራ እና አራብሳ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ ነውም ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የአውቶቡሶችን ስምሪት ጨምሮ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከሰነድ አልባ ይዞታዎች ጋር ተያይዞ መመሪያ መኖሩን ያወሱት አቶ ጃንጥራር ማንኛውም ሰነድ አልባ ሰነድ አልባ የሚያሰኘው ሁኔታ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ይህ ስራ ፈጥኖ ማለቅ የነበረበት ስራ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ ትክክለኛ ሰነድ አልባ ሆነው ሰነድ ያልተሰጣቸውን ችግር በመፈተሽ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ከደረሰኝ መቁረጥ ችግር ጋር ተያይዞ የተነሳውን ጥያቄ በተመለከተ በከተማዋ ሁሉም አካባቢዎች ደረሰኝ የመቁረጥ ስራ መከናወን እንዳለበት ተወስኖ ወደ ስራ መገባቱን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ረገድም ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በተደረገ ውይይት ደረሰኝ አንቆጥርም የሚል ሀሳብ እንደሌለ ነገር ግን ትኩረቱ ጅምላ እና አከፋፋዮች ላይ መሆን እንዳለበት ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ ረገድ ውይይቱ መቀጠሉን እና በጉዳዩ ላይ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡ በከተማዋ የሚሰራው የልማት ስራ ገቢን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ደረሰኝ እየቆረጡ የገቢን መሰረት ማስፋት፣ህጋዊነትን ማስፈን ፣በህግ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን መብት መጠበቅ እንደሚገባ እና በዚህ ረገድ የምክር ቤት አባላትም እገዛ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡ ትልቁ የገቢ ማእከል የሆነው መርካቶን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተለይም ከገቢ ደረሰኝ መቁረጥ እና ከባለሙያ ስምሪት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ችግሮች እየታረሙ የሚሄዱ መሆናቸውንም አቶ ጃንጥራር አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቧቸውን ተሿሚዎች በሙሉ ድምፅ አፅድቋል:: በዚህም መሰረት:- 1. ኢ/ር ወንድሙ ሴታ - በም/ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ 2. አቶ ተንኩዌይ ጆክ ሮም - የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ኃላፊ 3. አቶ ይመር ከበደ ይማም የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር 4. ዶ/ር ግዛቸው አይካ - በአዲስ አበባ ምክርቤት የመሰረተ ልማትና መዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የቦታ ለውጥ ያደረጉ 1. አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ 2. አቶ ቢንያም ምክሩ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 3. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቅቋል::

ከንቲባ አዳነች ግብር እና ደረሰኝ ከመቁረጥ ጋር በተያያዘ ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ምላሽ:- በመርካቶ ህጋዊ ግብይት እንዲደረግና ለእያንዳንዱ ግብይት ነጋዴው ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለን:: እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በዘላቂነት ለማስተካከል የምናደርገውን ጥረት በጥናት ላይ ተመርኩዘን ክትትል ስናደርግ የቆየን ሲሆን ያገኘነው ግኝት በርካታ ህገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንዳሉ ተመልክተናል:: በዚህም ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል:: ግብር ለማስከፈል እና ደረሰኝ እንዲቆርጡ ለማድረግ ባደረግነው ሂደት በሀሰት ውዥንብር በመንዛት መጋዘኖችን በመዝጋት በምሽት እቃዎች ሲጫኑ ተመልክተናል:: ይህ ፍፁም ስህተት ሲሆን ግብርን መሰረተ ልማት ለመዘርጋት፣ ከተማችንን ለማስዋብ፣ ተማሪዎችንና አቅመ ደካሞችን ለመመገብ እንዲሁም ሀገር ለመገንባት የምንጠቀምበት በመሆኑ በቀጣይ ህጋዊ ስርዓት በመዘርጋት እና ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::

ከንቲባ አዳነች ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቆዎች ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ምላሽ:- - በልማት ተነስተው በለሚኩራ ክ/ከተማ እና ቃሊቲ ክ/ከተማ ለገቡ ነዋሪዎች የትራንስፖርት አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት የተደረገ ሲሆን በዚህም በሁለቱም ሳይቶች የከተማ አውቶቡስ፣ ሚዲባስ እና ውስጥ ለውስጥ ደግሞ ባጃጆችን በመመደብ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል:: - ከታሪፍ በላይ የማስከፈል ችግርን ለመቆጣጠር የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች፣ ትራፊክ ፖሊስ እና በትራፊክ ማጅመንት ተቆጣጣሪዎች አማካኝነት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን ከታሪፍ በላይ በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ - የታሪፍ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ እንደ ከተማ ከታሪፍ በላይ በማስከፍል 1066 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡ በተጨማሪም ታሪፉን ህዝቡ እንዲያውቅ በተሸከርካሪዎች ውስጥ ታሪፍ እንዲሰቀል አቅጣጫ ወርዶ እየተሰራ ሲሆን ታሪፍ ባልሰቀሉ 4020 ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡ በሌላ መንገድ ማታ ላይ የሚያጋጥሙ የትራንስፖርት እጥረቶችን ለመቅረፍ ማታ ላይ የአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ተደርጓል፡

ህዳርን ሲፀዳ !በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የፅዳት ንቅናቄ መርሀ-ግብር ለ5 ተከታታይ ቀናት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት አንስቷል። ምክርቤቱ ያለመከሰስ መብት ያነሳው የተከበሩ አቶ ሰዒድ አሊ ከማል ሲሆን ግለሰቡ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩበት ወቅት የኮሪደር ልማቱን ምክንያት በማድረግ ከግል በለሀብት ጋር በመመሳጠር የመንግስት ሀብትን ለግል ጥቅም እንዲውል በማድረግ ከፍተኛ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ መሆኑ ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ጠቁመው የቋሚ ኮሚቴውን ውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። ምክር ቤቱም በከባድ ሙስና ወንጀል በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት የቀረበውን ያለመከሰስ መብት የማንሳት ጥያቄ በጥሞና አዳምጦ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማከናወን ጀምሯል:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽን ማብራሪያዎችን የሚሰጡ ይሆናል::