እውነት ለሁሉ [truth for all]
前往频道在 Telegram
ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው። قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ [ ሱረቱ ሰበእ - 49 ] «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡
显示更多3 003
订阅者
-624 小时
-307 天
-9330 天
帖子存档
💾በኢርሻድ እቅበተ ‐ ኢስላም ለሰለምቴ እህቶች የተዘጋጀ መሰረታዊ የእስልምና ትምህርት!
➡️በዚህ ልዩ መርሃ-ግብር ስለ እስልምና እምነት ምሶሶዎች (ዓቂዳህ) እና የዕለት ተዕለት ተግባራዊ ህጎች (ፊቅህ) እንዲሁም ኢስላማዊ አደቦችን በጣም ቀለል ባለ መልኩ እንማራለን።
➡️ትምህርቱ ለጥቂት ግዜያት የሚቆይ በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ። ምንም አይነት ክፍያ የለውም።
⚪መመዝገብ የምትፈልጉ⬇️
🌐@Al_Rashid_01 / @Sabi_nizwan / @FatimaMuh1
ወንድም ሀቢብ ከ ረዥም አመት በፊት በንጽጽሩ ካየኋቸው ጠንካራ ወንድሞች መሀከል ነው አሁን ላይ ደሞ አላህ ይጨምርለት ብሶበታል ቻናሉ ግቡ ብዙ ትጠቀማላቹህ
https://t.me/Habibresponds
📢አዲስ የኦንላይን ኪታብ ደርስ ማስታወቂያ
📚ለአንድ ወር የሚቆይ የቂርአት ፕሮግራም!
በትምህርቱ የሚቀሩ ኪታቦች፦
✒️ከዐቂዳ:- ኡሱሉ ሠላሠህ
✒️ከሙስጠለሕ አል-ሐዲስ፦ መንዙመቱል በይቁኒያህ
✒️ከፊቅህ፦ ሹሩጡ ሷላት
📌የኮርሱ ዝርዝር መረጃ፦
🗓 ቆይታ፦ 1 ወር
➥ደርሱን የሚሰጠው : ወንድም ሁሴን
🧻 ክፍያ፦ 300 ብር ብቻ
📲 ለመመዝገብ፦ @Hussu707 ን ያናግሩ
የዓሹራ ፆም
ያለፈውን አመት ወንጀል እንደሚያብስልን የነገሩን የዓሹራ(አስረኛው) ቀን ፆም ሐሙስ ነው።
የዓሹራን ቀን አይሁዶችም ይፆሙት ስለነበረ እነሱን ለመቃረን ዘጠነኛውን(የነገውን) ቀን መፆሙ በላጭ ነው።
◈ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾
“የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።
📚ሙስሊም ዘግበውታል: 1134
የነገውን(ዘጠነኛውን) ቀን ፆም እንፁም
https://t.me/iwnetlehullu1
🚫ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!
♻️እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!
📵እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!
☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ ላይ የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!
☞የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞እነዚህን አፀያፊ ምስሎችና ቪድዮዎች በማየት የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ካገኘው ተቃራኒ ፆታ ጋር ሁሉ ዝሙት ላይ የሚወድቅ ይሆናል። እንዲሁም ራስን ወደ ማርካት (masturbation) ሱስና የስንፈተ ወሲብ አደጋ ተጋላጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።
☞እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ? ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!
☞ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል? (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)
☞እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ! የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?
☞በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?
☞ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?
☞እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?
☞ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አድርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?
☞እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?
☞ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?
☞በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?
☞ጌታህ ቻይ ነው! ለግዜው ይተውኃል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ! ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላደረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!
☞ የዒባዳህን ጥፍጥና እንደሚያሳጣህ አምልኮ ላይ ደካማ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
ለዒባዳ በቆምክ ቁጥር የምታያቸው ምስሎች አዕምሮህን ተቆጣጥረው እንደሚፈታተኑህ ታውቃለህ? በዚህም ከአምልኮ መሸሽና ተስፋ ቢስነት ሊሰማህ ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ አደገኛው አዘቅት ክህደት የሚጎትት ጠንቅ ነው።
☞ ራስህን የምትጠላ የወንጀል ምርኮኛ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?
☞ለአላህ ብሎ አንዳች ነገርን
የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?
☞አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?
☞ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?
☞ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ?
☞ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?
☞ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?
✅✅✅✅✅
☞ለላጤዎች ምክር!
♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!
♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!
♻️ ማግባት ካልቻልክ ትርፍ የምትለውን ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ ስፖርት በመስራት፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......
♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብ
♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያደርግህ ተማፀን!
♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!
♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!
☞ለባለ ትዳሮች ምክር
♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!
♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ታማኝ ከትዳር ህይወት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!
♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!
♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማድረግ ባለቤቷን ማስደሰት አለባት!
✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህችን አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን/ሁኚ!
♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል። አስተንትን! በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታድርጋቸው!
ኢብኑ'ል ወርዲይ በግጥማቸው እንዲህ ብለዋል ፦
إنَّ أحلى عيشةٍ قضيتُها
ذهبتْ لذاتُها والإثمُ حلْ
ስሜቴን ያራገፍኩባቸው ጣፋጭ ግዜያቶች
ጥፍጥናቸው ሄዷል ወንጀሉ ቅን ቀርቷል/ተመዝግቧል
©️opy
♻️ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ይምራን!
🔗SHARE 🔗SHARE
https://t.me/iwnetlehullu1
የ ፕሮፌሰር ባርት የአዲስ ከዳን ህያሳ ሊቅ ንግግር ለኔ መነሻ ለጽሁፌ የሆነው ....
የዮሐንስ ወንጌል መግቢያ 1:1-18 በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይህ ክፍል ከሙሉ መጽሐፍ ጋር ወጣ ያለ እሳቤ ያለው የማይመሳሳል በይዘቱ ለየት ያለ ከወንጌሉ በመሆኑ በቀድሞ የወንጌሉ አካል ያልነበረ የተጨመረ እንደሆነ በብዙ ሙሁራን ዘንድ የታመነ ነው
የዮሐንስ ወንጌል መግቢያ (Prologue of Jhon)
መግቢያ
በመጽሐፍ ሕየሳ (biblical criticism) ላዕላይ (Higher criticism) እና ታህታይ (Lower criticism) ተብለው ይከፈላሉ በታህታይ ጽሑፋዊ ሕያሴ (Textual Criticism) እናገኛለን በዚህ ዘርፍ እንደ ወንድም ሳላህ ኡስታዝ ቃል አሚን ስራቸውን አላህ ይቀበላቸው ብሎም የበለጠ የምንጠቀም ያድርገን እና ዘርፉን ቃርመውታል ብለን ማለት እንችላለን ።
ዛሬ አዲስ በር ልክፈት እና በላዕላይ ሕየሳ ካሉ ዘርፎች ምንባባዊ ህየሳ (Literary criticism) አንዱን የጥናት መስክ ነው የሚያተኩረው የጽሁፉን አወቃቀር ትረካዊ ገለጻ ይዘት የአመለካከት ነጥብ ላይ ያጠነጥናል በሰፊው ትኩረት ሰጥተን አላህ ከረዳን የምናየው ይሆናል ኢንሻአላህ ። ወደ ዛሬው ርዕስ እናምራ ...
የዩሐንስ ወንጌል መግቢያ (ዩሀ 1:1-18)
ብዙን ጊዜ .. ልል አስቤ ኧረ ሁሌም ክርስትያኖች ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳዩን ሲባሉ በመጀመሪያው ቃል ነበረ ... የሚለውን ጥቅስ በፍቅር ይሰብካሉ ! እናስ ይሄ ክፍል በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተጨመረ ነው ቢባሉ .. ይቅር በሉኝ ወለም ብሎኝ ነው ብንባል ምን ይመስላቹሐል ...
በታህታይ የመጽሐፍ ሕየሳ የጽሑፍ ህየሳ በእደ ክታባት ተጠብቆ ለመኖሩ አያጣራጥርም በደንገል66 ደንገል75 በብራና አሌፍ ... መገኘቱ እርግጥ ነው ተዐማኚም ነው ። ታድያስ እንዴት ተጨመረ ብለህ ትሞግታለህ
ነገሩ እንዲህ ነው የዮሐንስ መግቢያ 1:1-18 እንዲሁ ላነበበ ከተቀረው የወንጌሉ ክፍል የአጻጻፍ ስልቱ ወጣ ያለ ሆኖ እናገኛዋለን በዚህም የተነሳ ሙሁራን በቀድሞው የወንጌሉ ክፍል ያልነበረ በኋላ ቆይቶ ከዋናው በኩረ ጽሁፍ በጻህፍት የተጨመረ መሆኑን ምሁራን አበክረው ይናገራሉ ።
የስነ መለኮት እንዲሁም የአዲስ ኪዳን ሙሑር ሩዶልፍ ቦልትመን የዮሐንስ ወንጌል መግቢያ ከሙሉ ወንጌሉ ለየት ያለ ትምህርን የያዘ ለዚህም ኢየሱስ ሎጎስ (ቃል) ተብሎ መወሳቱ በዚሁ በወንጌሉ መግቢያ እንጂ ሌላ ቦታ አለመኖሩ ብሎም “ቅድመ ክርስትና” ኖስቲካዊ መዝሙር ከግሪክ አፈታሪክ የተወረሰ ሳይሆን እንዳልቀረ እና ወንጌላዊያኑ ጻህፍት በወንጌል ውስጥ ከጨመሩዋቸው ቀደምት ሥነ-መለኮታዊ ወጎች እንደሆነ ተከራክሯል። ¹ የአዲሱ የመጽሐፍ ቅዱስ መደበኛ እትም በዮሐንስ ወንጌል መግቢያ ላይ እንዲሁ በወንጌሉ ከግሪክ አፈታሪክ ኑፋቄ የሆኑ ትምህርቶች እንዳለበት ማመኑ ልብ ይለዋል ።
ሬመንድ ብራውን በመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያው ይህኑን አስረግጦ ይገልጻል በመጀመሪያው መጽሐፉን በማዳራጀት ላይ ባለው (Readactor) አካል የተጨመረ እና ከቅድመ ክርስትና እሳቤዎች የተቀዳ የሆነ እና ከዋናው ወንጌላዊ ጽህፈት የተለየ በመሆኑ የርሱ ለማስለሰል የመጥምቁ ዮሐንስ ታሪክ እንደተጨረበት በአንከር የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ በተሰኘው ትልቅ እውቅና ካለው መጽሐፉ አኑሯል ² ። ሌሎችም ሙሑራን ልክ እንደ ጄምስ ዲ. ጂ.³ እና ዶድ ⁴ ይሄንኑ ያሰፍራሉ ።
ማጠቃልያ
የዮሐንስ ወንጌል መግቢያ በመጽሐፉ ሊህቃን እና በዘርፉ ጠበብቶች ጥያቄን የያዘ እና የዮሐንስ ወንጌል አካል እንዳልሆነ የሚታመን መሆኑ የተረጋገጠ የታመነ ነው እንደ ቅድ መነሻ የ ፕሮፌሰር ባርት ሙግት ከ ዋለስ ጋር ላይ በመነሳት እንዲሁም ከፕሮፌሰሩ ፖድካስት በመነሳት ለጥናት ተነሳስሼት የተጻፈ ነው ብዙ በመጽሐፉ ላይ የተጨመሩ ትምህርቶች ኖረው ትዮሎጂው ላይ ችግር አያመጣም ለምትሉ ክርስቲያኖች ... እውነት በሉ እስኪ..
✍️ ወንድም student
1 The Gospel of John: A Commentary Rudolf Bultmann page 13-28
2 Gospel According to John (Anchor Bible)Raymond E. Brown introduction
3 Christology in the Making James D. G. Dunn
4 The Interpretation of the Fourth Gospel C. H. Dodd
-✨ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ
(العبادة في الهرج كهجرة إلي)
«በችግር በፈተና ወቅት የሚደረግ ዒባዳ ወደኔ እንደመሰደድ ነው!»
[📙ሶሒሕ ሙስሊም 2948]
በዚህ ፊትና በበዛበት ግዜ ፖለቲካውን ለፖለቲከኞት ትተን በሚጠቅመን ነገር ዒባዳ ላይ እንጠነክር እንበርታ
በተለይ ያለንበት ወር ታላቅ ወር ነውና ዒባዳ ላይ እንበርታ አንዘናጋ ባረከላሁ ፊኩም
https://t.me/iwnetlehullu1
Repost from 𝑖𝑏𝑟𝑎ℎ𝑖𝑚 islamic Apologetics
ሚስጢር ሹክ ልበላቹህ 🌸
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ✨
ላኢሏሐኢለሏሁ ዋህደሁ ላሸሪከ ለህ ለሑል ሙልክ ወለሑል ሐምድ ወሑወ አላ ኩሊ ሸይዒን ቀዲር
ከአሏህ በቀር በሐቅ ሊመለክ የተገባው የለም ብቸውን ያለ አንዳችን ተጋሪ ሥልጣን ሁሉ ለርሱ ነው ምስጋናም ሁሉ ለርሱ ይገባል እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው
✨ ይህን ዚክር በቀን 100 ጊዜ ያለ
🌴10 በባርነት የተያዙ ሰዎችን ነጻ እንዳወጣ
🌴100 ምንዳ
🌴100 ሐጥያት
🌴እንዲሁም ከሰይጣን ጉትጎታ ቀኑን ይጠበቃል
ይህን ካለ ሰውም የተሻለ የሰራ በቂያማ ቀን የለም ከርሱ በላይ ያለ ቢሆን እንጂ💐
በርቱ ተበራቱ
ረመዳን የእዝነት የምህረት ወር 🌙
رمضان مبارك 🌙
أسأل الله أن يتقبل منا ومنكم الصيام والقيام.
وإن كان بدر مني تقصير أو خطأ، فإني أستغفر الله وأطلب منكم العفو والسماح.
➤➤መልዕክት ለሙስሊሞች በተለይ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች➤➤
በገና እና በመሳሰሉት የከሀዲያን በዓላት ላይ የሚዘጋጀውን ልዩ የካፌ ምግብ መብላትን በተመለከተ:
1: እንደ አጠቃላይ በነርሱ በዓል የተዘጋጀን ምግብ መብላት አይቻልም። ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ያዘጋጁት ምግብ ክልክል ስለሆነ ሳይሆን የተዘጋጀው ምግብ በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀ ስለሆነ አይፈቀድም።
ክልክል ነው። ከበዓል ውጭ ባለግዜ ግን ከላይ እንደተጠቀሰው ሀላል የሆነ ምግብ እስከሆነ ድረስ መብላት የተፈቀደ ነው።
2: ነገር ግን ካፌ ተጠቃሚ የሆናችሁ ሁሉ ማድረግ ያለባችሁ ነገር:
የተለያዩ አማራጮች ካላችሁ አትብሉ።
ለምሳሌ: ውጭ ላይ ቤተሰብና ዘመድ ካላችሁ ከነርሱ ዘንድ በመሄድ አሳልፉ፣።
ውጭ ላይ ገዝታችሁ መጠቀም የምትችሉ ከሆነም አትብሉ።
እነዚህና መሰል አማራጮች ከሌሏችሁ ግን፣
አላህ ከምንችለው በላይ አስገዳጅ ያልሆነ ውስጥ አዋቂ አምላክ ነውና
ካፌ ብትጠቀሙ ችግር የለውም።
" ክርስቲያን ወገኖችንም ሆነ የካፌ ሰራተኞችን ፣
<< እንኳን አደረሳችሁ! >> ማለት አይቻልም።
" እንኳን አደረሳችሁ!" ሲሉንም መመለስ የለብንም።
የካፌ ምግቡን በተመለከተ ሸይኽ ባሲጢይን አላህ ይዘንላቸውና በህይዎት ሳሉ እኛ የግቢ ተማሪ በነበርን ጊዜ ጠይቀናቸው ይህ ይዘት ያለው መልስ ነበር የመለሱልን።
በተረፈ አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው!
Ⓒ
https://t.me/iwnetlehullu1
አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ ሱረቱል ኢብራሒም አንቀፅ 24-26 የአማኝና የከሐዲዎችን ምሳሌ እንዲህ ያስቀምጣል፦
🔼ስለ አማኞች!
አማኞች ማለት መልካም ፍሬ ባላት ዛፍ ሲመሰሉ፤ ይህች ዛፍ ስርዋ ወደ መሬት በደንብ የሠደደ እና መሰረትዋ የማይናወጥ ሲሆን ቅርንጫፎችዋም ከመርዘማቸው የተነሳ ሠማይ የሚደርሱ ናቸው። ፍሬዋም በአላህ ፍቃድ ያለማቋረጥ ቀንም ሌሊትም ለተመጋቢ ዝግጁ ሲሆን ማፍራቷን አታቆምም። ይህም የተባረከ፣ የሚያምር፣ ጤነኛ፣ ንፁህና ጠቃሚ ፍሬ ነው። ይሕች ውብ ዛፍ የአማኞትምሳሌ ናት።
Ibrahim 14:24-25
(24) أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلࣰا كَلِمَةࣰ طَيِّبَةࣰ كَشَجَرَةࣲ طَيِّبَةٍ أَصۡلُهَا ثَابِتࣱ وَفَرۡعُهَا فِي ٱلسَّمَآءِ
(25) تُؤۡتِيٓ أُكُلَهَا كُلَّ حِينِۭ بِإِذۡنِ رَبِّهَاۗ وَيَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَالَ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
(24) አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን
(25) ምግቧን (ፍሬዋን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች፡፡ አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል፡፡
🔽በሌላ በኩል ስለ ከሐዲዎች!
ጌታችን አላህ ከላይ ካለው ገለፃ በኋላ በተቃራኒው ስለ ከሐዲዎች በሚገርም ሁኔታ እንዲህ ገልፆልናል።
Ibrahim 14:26
وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٖ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ ٱجۡتُثَّتۡ مِن فَوۡقِ ٱلۡأَرۡضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٖ
የመጥፎም ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተጎለሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደኾነች መጥፎ ዛፍ ነው፡፡
ይህቺ መጥፎ ዛፍ ናት! ከታች ምንም አይነት ስር ወይም መሠረት የላትም፣ ፍሬዎችዋም በጣም መራራ የሆኑ፣ የተጎለሰሰችና 'basement' የሌላት ዛፍ ናት። ይህቺም የከሐዲዎች ምሳሌ ናት!
ሱብሐን አላህ! ለሚያስተነትኑ ምን ያማረ ምሳሌ ነው!
ክርስትና አስተምህሮ በጥቅሉ ....
አንድ አምላክ እግዚአብሔር ራሱን ሰዋ ለእግዚአብሔር፣ ከእግዚአብሔር ፍጡራኑን ይድኑ ዘንድ ። እግዚአብሔር ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እንዲያድነው ! ግን እግዚአብሔር እግዚአብሔርን አላደነውም። በሰዎች ትብብር እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ገደለ። እግዚአብሔር የእራሱ አባት በተመሳሳይ የራሱም ልጅ ነው ። እርሱ ዘለላማዊ ሆኖ ሳለ ግን (ገና) የተባለ የልደት በዐል ይከበርለታል እርሱም ሰው ለሆነው አብርሀም የዘር ግንድ ነው። እርሱ እራሱን ወደ ምድር ልኮ ሰው ልጆች ጋር አብሮ በመኖር የሰው ልጆች እንዲገሉት ጫና በማድረግ ተገድሏል። ምክንያቱም ይህ ያለው ብቸኛ አማራጭ ነበረ የሰው ልጆችን በአንዲት ከ6000 አመት በፊት የኖረችን ሴት(ሔዋንን) ለሀጢያቷ ምህረትን ያደርግላት ዘንድ !
በሠሞንኛው የሐጂ ዑመር ገነቴ ህልፈት ትንሽ የማያስማማና አለመግባባት ቢኖርም የአንዳንድ ቡድኖች በዚሁ አጋጣሚ ጭንብላቸው ተገልጦ ትክክለኛ ፊታቸውን ያሳየ ሆኗል። በእርግጥ ክርስትያን ወገኖች በሙስሊሞችና በኢስላም ሀይማኖት ዙሪያ እውቀቱም ሆነ መብቱም ስለሌላችሁ ቅቤ አንጓች መሆን አያስፈልግም፤ ብዙ ማታውቁትና ያልገባችሁ ነገር ስላለ ጡልቅ ጡልቅ ማለቱ አይበጅምና አድቡ።
እንዲሁ በእንዲሁ እንዳለ ሙስሊም ነኝ የሚለው ሙሽሪኩ አካል ገና ካሁኑ የገሃነም ጓዱን ከወሐብያ እገሌ ይሻለኛል በማለት ወዳጅነቱን አጠናክሯል። እንግዲህ እኛም ዘመድ ከዘመዱ አህያ ካመዱ እንዲሉ ስትቀሰቀሱ አላህ አብሮ ይቀስቅሳችሁ ከሞት በኋላም አይለያችሁ ብለናል። 🙌
+1
●ቤትና መስጂዶችን ለቀብር አገልግሎት ማዋል
✨ውዱ ነቢያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ
﴿ألا وَإِنَّ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ كَانُوا يَتَّخِذُونَ مِنْ قُبُورِ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ أَلا فَلَا تَتَّخِذُوا القُبُورَ مَسَاجِدَ فَإِنِّي أَنْهَاكُمْ عَنْ ذَلِكَ﴾
“አዋጅ! ከናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦች የነቢያቶቻቸውን መካነ መቃብሮች መስጊድ አድርገው ይይዙ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ የቀብር ቦታዎችን መስጊድ አድርጋችሁ እንዳትይዙ በጥብቅ እከለክላችኋለሁኝ፡፡”
[📙ሙስሊም ዘግበውታል፡ ሐዲስ 532]
✨በሌላ ሐዲሳቸው ነቢያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ
لا تجعلوا بيوتكم مقابر
«ቤታችሁን መቃብር አታድርጉ።»
[📓ሙስሊም ዘግበውታል ሐዲስ 780]
https://t.me/iwnetlehullu1
"እሰልምልሻለሁ" ብሎ አግብቶ ካስወለዳት በኋላ ወይም ክርስትናን ተቀበይ አለበለዚያ ልጄን ትተሽ ጥርግ ማለት ትችያለሽ ይላታል።
እርሷም የዓይን ማረፊያ ልጇን እና የሞቀ ትዳሯን ትታ መሄድ ይከብዳትና ፍጡር እያመለከች ፍጡር ማምለኳ ስህተት እንደሆነም እያወቀች ወደ እሳት ትጓዛለች💔
ወደዚህ ጣጣ ውስጥ ከመግባቷ በፊት መጀመሪያ ከካሐዲ ወንድ መራቅ ነበረባት!
ይህ ጉዳይ በብዙ እኅቶቻችን ላይ እየሆነ ያለ ጉዳይ ነው።
وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
[ አል-በቀራህ - 120 ]
አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡
✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12
Repost from የኢስላም እውነት ለሁሉ Truth for all
"እሰልምልሻለሁ" ብሎ አግብቶ ካስወለዳት በኋላ ወይም ክርስትናን ተቀበይ አለበለዚያ ልጄን ትተሽ ጥርግ ማለት ትችያለሽ ይላታል።
እርሷም የዓይን ማረፊያ ልጇን እና የሞቀ ትዳሯን ትታ መሄድ ይከብዳትና ፍጡር እያመለከች ፍጡር ማምለኳ ስህተት እንደሆነም እያወቀች ወደ እሳት ትጓዛለች💔
ወደዚህ ጣጣ ውስጥ ከመግባቷ በፊት መጀመሪያ ከካሐዲ ወንድ መራቅ ነበረባት!
ይህ ጉዳይ በብዙ እኅቶቻችን ላይ እየሆነ ያለ ጉዳይ ነው።
وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
[ አል-በቀራህ - 120 ]
አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡
✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12
