ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 946 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 156,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 680

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 946 名订阅者。

根据 28 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -539,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.64%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.06% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 115 次浏览,首日通常累积 1 408 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 29 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 946
订阅者
-524 小时
-1197
-53930
帖子存档
ውድ ተከታታዮቻችን በዛሬው ዝግጅታችን የምንዳስሰው አንገብጋቢ እየሆነ የመጣውንና ሴቶች እህቶቻችንንና እናቶቻችንን እያጠቃ ስላለው የመሀጸን በር ካንሰር(cervical cancer) ነው፡፡ የመሀጸን በር ካንሰር(cervical cancer) ምንድን ነው??? -የመሀፀን በር ካንሰር (cervical cancer) የሚከሰተው የመሀጸን በር ላይ ያሉት ህዋሶች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲያድጉ ነው፡፡ -የመሀፀን በር የምንለው ከታችኛው ከመሀጸን ክፍል ወደ ሴት ብልት የሚከፈተው የሲሊንደር ቅርፅ ያለው ህብረህዋስ ነው፡፡ ለመሀፀን በር ካንሰር(cervical cancer) ተጋላጭ የሚሆኑት እነ ማን ናቸው??? 1. HPV (human papilloma virus) በተደጋጋሚ የሚጠቁ ሰዎች -ዋነኛው የመሀፀን ካንሰር መንስኤ ሲሆን ይህም ቫይረስ የሚታወቀው በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ከሰው ወደ ሰው በመተላለፍ የአባላዘር በሽታ በማስከተል ነው፡፡ 2. ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብርስጋ ግንኙነት መፈፀም 3. የሰውነትን የበሸታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ በሸታዎች ሲኖሩ ለምሳሌ ፡ ኤች.አይ.ቪ 4. ሲጋራ ማጨስ 5. ለረጅም ጊዜ በአፍ የሚዋጡ የወሊድ መቆጣጣጠሪያዎችን መጠቀም 6. ከ17 አመት እድሜ በታች ሆነው ልጅ ለመውለድ የተጋልጡ ሴቶች 7. 3 እና ከዛ በላይ ልጆችን መውለድ 8. በለጋ እድሜ የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የበሸታው ምልክቶቹ ምንድን ናቸው??? -በበሸታው የመጀመርያ ጊዜያት ውስጥ ምልክቶቹ ጎልተው አይታዩም፡፡ በብዛት የሚስተዋሉት ምልክቶች :- > ከመሀፀን ደም መፍሰስ > ከግንኙነት በኃላ የደም መፍሰስ > መጥፎ ጠረን ያለው ከመሀፀን የሚወጣ ፈሳሽ > የጎን እና ጎን ህመም > ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ወይም ሽንት > በማረጥ ጊዜ ደም መፍሰስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በምን መከላከል እንችላለን??? 1. Pap smear በማሰራት -ይህ ምርምራ በየስንት አመቱ እንደሚሰራ የሚወሰነው በእደሜዎት እና ካሎት ትጋላጭነት አንጻር ነው፡፡ 2. በግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀም 3. ሲጋራማጨስ ማቆም 4. መወሰን የማህጸን በር ካንሰር ደረጃዎች ደረጃ 0- የመጀመሪያዎቹ ህዋሶች ከቁጥጥር ውጭ በማህጸን በር ላይ ማደግ የሚጀምሩበት ግዜ ነው ደረጃ 1- በዚህ ግዜ ካንሰሩ የማህፀን በር ላይ ብቻ ያለ ሲሆን ይህም ሁለት ደረጃዎች አሉት ደረጃ 1ሀ- ካንሰሩ በማይክሮስኮፕ/ በአጉሊ መነፅር/ ብቻ የሚታይ ነው ደረጃ 1ለ- በዚህ ግዜ በማህፀን በር ላይ ያሉትን ለውጦች በአይናችን መለየት የምንችልበት ደረጃ ነው ደረጃ 2- በሽታው የማህጸን በርንና ማህፀንን የሚያጠቃልልበት ሲሆን ነገር ግን ወደሌላ ሰውነት ክፍሎች አልተሰራጨም፡፡ ደረጃ 3- የምንለው ካንሰሩ ማህጸንን አልፎ በዛ አከባቢ ያሉትን የመራቢና የብልት ክፍሎች ሲያጠቃ ነው ደረጃ 4- በዚህ ግዜ ካንሰሩ ወደ ሽንት ፊኛ አንጀት ጉበት አጥንቶችን ወይም ሳንባን ያጠቃል ህክምናዎቹ 1) ቀዶ ጥገና 2) የጨረር ህክምና እና 3) የመድሀኒት ህክምና ናቸው፡፡

የጥርስ ህመምን በቤት ውስጥ በቀላሉ ለማስታገስ ... የጥርስ ህመም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰትብን ይችላል። የጥርስ ህመም በሚያጋጥመን ጊዜ በርካቶች ለህመሙ ሲባል ምግብ ነክ ከሆኑ ነገሮች ለመራቅ የሚገደዱ ሲሆን፥ ይህንን ህመም ለማስታገስም እንደ አንቲባዮቲክስ ያሉ ማስታገሻዎችን መውሰድም በብዛት የተለመደ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ግን በቤት ውስጥ በቀላሉ ከተፈጥሮ በምናገኛቸው ነገሮች የጥርስ ህመምን ማስታገስ እንደምችልም ይነገራል። ከነዚህም ውስጥ፦ 1.ነጭ ሽንኩርት፦ በውስጡ በያዛቸው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት ለተለያዩ በሽታዎች እንደ ፈውስነት የሚያገለግለው ነጭ ሽንኩርት እንደ አንቲባዮቲክ በመሆን የጥርስ ህመምን ያስታግሳል ተብሏል። በነጭ ሽንኩርት የጥርህ ህመምን ለማስታገስ አንድ ወይም ሁለት ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ማኘክ መልካም ነው የተባለ ሲሆን፥ አልያም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ከገበታ ጨው ጋር በመደባለቅ የህመም ስሜት የሚሰማን ቦታ ላይ ማስቀመጥ ይመከራል። 2.ቀይ ሽንኩርት፦ በተለምዶ ቀይ ሽንኩርት በመባል የሚጠራው ሽንኩርት የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ከሚረዱን ተፈጥሯዊ ነገሮች ውስጥ ይመደባል። የጥርስ ህመም በሚሰማን ጊዜ ቀይ ሽንኩርት ማኘክ ህመሙን ለማስታገስ የሚረዳ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም ቀይ ሽንኩርት በጥርስ ህመም ምክንያት የሚከሰት የሰውነት መቆጣት እና ኢንፌክሽንን ይከላከላል። 3.የቅርንፉድ ዘይት፦ መጥፎ የሆነ የጥርስ ህመም ካለብዎት የቅርንፉድ ዘይትን መጠቀም መልካም መሆኑም ይመከራል። የጥርስ ህመም በሚከሰትብን ጊዜ የህመሙ ስሜት ያለበት ስፍራ ላይ የቅንፉድ ዘይቱን ማድረግ ይመከራል፤ ዘይቱን በምናደርግበት ጊዜ የመጠዝጠዝ ወይም የህመም ስሜት ቢሰማንም በኋላ ላይ ግን ትልቅ ፈወስን ያስገኝልናልም ተብሏል። 4.ለብ ያለ ውሃና ጨው፦ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ከሚመከሩ ተግባራት ለብ ያለ ውሃ እና ጨው መጠቀም ይገኝበታል። ይህንን ለማድረግም ለብ ያለ ውሃ እና ግማሽ ማንኪያ ጨው የሚያስፈልገን ሲሆን፥ ለብ ያለ ውሃን እና ጨውን በደንብ ማዋሃድ ይጠበቅብናል። ይህንን ውህድም በአፋችን ውስጥ በማድረግ መጉመጥመጥ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ስለሚረዳ በብዛት ይመከራል። 5.በረዶ፦ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ በረዶን መጠቀመም እንደ አማራጭ ከተዘረዘሩት ውስጥ ይገኛል። በረዶውን በፕላስቲክ መያዣ ውስጥ በማድረግ ወይም በንጹህ ጨርቅ በመጠቅለል የሚያመን ጥርስ ላይ ለ15 ደቂቃ ማስቀመጥ ይመከራል። ከዚህ በተጨማሪም በሚያመን የጥርሳችን አቅጣጫ በውጭ በኩል በጉንጫችን ላይ በረዶን በማስቀመጥ ማስታገስ ይቻላል። ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሄዎች የጥርስ ህመም በሚሰማን ጊዜ በአፋጣኝ ለማስታገስ የሚረዱ እንጂ ዘላቂ የሆነ መፍትሄን ስለማይሰጡ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ማግኘት መልካም ነው። እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

✍️ #መካንነትመካንነት አለ የምንለው መቼ ንው?መንስኤዎቹስ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ባልና ሚስት በወር ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት ግንኙነት እያደረጉ ለአንድ አመት ከቆዩና በዚህ ጊዜ ውስጥ እርግዝና ካልተፈጠረ መካንነት ይባላል። ይህ ግን በአመቱ ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳይጠቀሙ መሆን ይኖርበታል። የሴቷ እድሜ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነና በስድስት ወር ውስጥ እርግዝና ካልተፈጠረ የሐኪም እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው። 🔹 #መካንነት የሚለው ቃል ጭራሽኑ ማርገዝ አለመቻል ወይም አንዴ ካረገዙ በኋላ መድገም አለመቻልን (secondary infertility) የሚያመለክት ይሆናል። ብዙውን ጊዜ ባለመውለዳቸው የሚኮነኑት ሴቶች ቢሆኑም ምክንያቱ ግን በወንዱ ፣ በሴቷ፣ ወይም በሁለቱም በኩል ባለ የመካንነት ችግር ሊሆን ይችላል። አልፎ አልፎም አስፈላጊ ምርመራ ተደርጎ የመካንነቱን መንስኤ ማግኘት የማይቻልበት ሁኔታ (unexplained infertility) ይኖራል። ⏩ #ለሴቶች መካንነት #ዋና #ዋና #መንስኤዎች 🔺 እንቁላሎችን ወደ ማህጸን የሚያስተላልፉ ቱቦዎች ወይም ማህጸኑ በጠባሳነት በመጎዳት ምክንያት የቱቦዎች መጎዳት የወንዱ ስፐርም ወደ እንቁላል እንዳይደርስ እክል ይፈጥራል። ጠባሳዎቹ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰጡ መሃንነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። @ #ጠባሳዎቹ #የሚፈጠሩበት #ምክንያቶች 🔺 በአግባቡ ሕክምና ያልተደረገለት የአባለዘር በሽታ በማህጸን ቱቦዎች ጠባሳን ሲያስከትል ይችላል 🔺 በውርጃ ወይም በወሊድ ጊዜ የሚከሰቱ የኢንፌክሽን በሽታዎች በማህጸኑ/ በማህጸን ቱቦዎች ላይ ጠባሳ ስያስከትሉ፣ ⏩ #እንቁላል #የማዘጋጀት #ችግር 🔺 ለዚህ ምክንያቱ የሚፈለጉት ሆርመኖች በበቂ ሁኔታ ስለማይኖሩ ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ከ21 ቀናት ወዲህ ወይም ከ35 ቀናት ወዲያ የሚመጣ ከሆነ ይህ ችግር ሊኖር ይችላል ። አልፎ አልፎም በጣም መወፈር ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ኪሎ መቀነስ የእንቁላል ማዘጋጀት ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ⏩ #የማህጸን እጢ ⏩ #እንደ ስኳር በሽታ ፣ ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችም መካንነት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ⏩ #ለወንዶች #መካንነት #መንስኤዎች 🔺 ሰውነታቸው የሚያመርተው ስፐርም ቁጥር በቂ አለመሆን፣ ወይም የተሰሩት ስፐርሞች ቀልጣፋነት ማነስ። 🔺 በተለያዩ ምክንያቶች (ኢንፈክሽ ፣ ጨረር፣ወዘተ) ስፐርም የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ። በዚህም ምክኒያት ምንም እንኳን በወሲብ ጊዜ ማፍሰስ ቢችሉም ፣ የወንድ ፈሳሽ ውስጥ ስፐርም አይኖርም፡ በመሆኑም ማስረገዝ አይችሉም ። 🔺 ስፐርም ከብልታቸው መፍሰስ ሳይችል ሲቀር ( የዚህ ምክኒያት በአባላዘር በሽታዎች የፈሳሹን መተላለፊያ ቱቦዎች በመጎዳት ሊሆን ይችላል።) 🔺 ቫሪኮሴሌ 🔺 ስንፈተ ወሲብ 🔺 የተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች እና የመሳሰሉት ⏩ #ምርመራዎቹ 🔺 የሚሰሩት ምርመራዎች ለወንዱና ለሴቷ የተለያየ ቢሆንም ለሴቶች ፣ የሆርሞን ምርመራ፣ አልትራ ሳውንድ፣ የእንቁላል ምርመራ፣ የማህጸን ኤክስ ሬይ እንዲሁም ጀነቲክ ቴስት …. 🔺 ለወንዶች ደግሞ የስፐርም ምርመራ፣የቴስቴስትሮን ምርመራ( የሆርሞን ምርመራ)፣የዘር ፍሬ አካባቢ አልትራሳውንድ፣ እና ሌሎች… ⏩ #ህክምናው 🔺 ኢንፌክሽን ካለ እሱን ማከም 🔺 ከግንኙነት ጋር ያሉ ችግሮችን ማከም 🔺 የሆርሞን ህክምና 🔺 ቀዶ ህክምና 🔺 አጋዥ ቴክኖሎጂ መጠቀም (Assisted reproductive technology) 👉👉 #በወሊድ ችግር ከተጨናነቁ ባለሙያ በማግኘት ይመካሩ (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

«ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት» የፊት ቆዳችንን በአግባቡ ካልተንከባከብነው በቀላሉ የሚጎዳ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን የፊት ቆዳን መንከባከቢያ መንገዶች ይመልከቱ። - ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ - የፊት ሳሙና ወይም ሌላ ቅባት ሲቀቡ የፊትዎን ቆዳ ከመፈተግ ይቆጠቡ ይልቁንም በለስላሳና ክባዊ እንቅስቃሴ ቀስ ብለው ይቀቡት - ለፊት ቆዳዎት የሚስማማ ማርጠቢያ ክሬሞችን ይጠቀሙ ከመተኛትዎትም በፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ - የፊት ቆዳ ቀዳዳን ከሚደፍኑ ዘይታማ ከሆኑ ሜክአፖችና የቆዳ ክሬሞች ይራቁ - የቆዳችን ንፅህና መጠበቅ በተለይ ብጉር የሚያስቸግረን ከሆነ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ፣ ፊዞርሲኖል፣ ሳሊክሊክ አሲድ ወይም ሰልፈር ያለው ለፊትዎ የሚስማማ ሳሙና መጠቀም ብጉሩ በዚህ ካልቀነሰ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መድሃኒት በተለያየ ምክንያት የፊትና ሌላ የቆዳ አካል ላይ የቀረን ምልክትን ለማጥፋት ከፈለጉ የሚከተለውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ህክምናን ሊጠቀሙ ይችላሉ። መድሃኒቱን በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት፦ • አራት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጁስ • አራት የሻይ ማንኪያ ማር • አንድ አስኳሉ የወጣለት እንቁላል አዘገጃጀት • ፊትዎ/ቆዳዎ ንፁህና ደረቅ መሆን ስላለበት ይታጠቡት • በመቀጠልም ከላይ የተዘረዘሩትን በንፁህ እቃ ውስጥ በደንብ ያደባልቁ • ከዚያም ምልክት ባለበት የቆዳዎ ክፍል ላይ ይቀቡት • ከ15 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ይታጠቡት ጥሩ ውጤት ለማግኘት በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲጠቀሙት ይመከራል።

"ስለ ቶንሲል የምናውቀው አና የምንሳሳተው ምንድን ነው?" - ዶ/ር ንጉሴ ጫኔ ፤ የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም - ቶንሲል ምንድን ነው? ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም። ቶንሲል ማለት ትንንሽ አበጥ ያሉ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ አካላት ስብስብ ነው። ይህም በክብ ቀለበት ከምላስ ጀርባ የላንቃን የጎን ግድግዳ እና የላንቃን ክዳንና የአፍንጫን የውስጠኛ ክፍሎች ያስተሳስራል። - ቶንሲል ጥቅሙ ምንድን ነው? በአፍም በአፍንጫም የሚገቡ ተዋህስያንን መዋጋት ነው። የሰውነትን በር ከጠላት መከላከያ ነው። - ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው? ሁለቱም በላንቃ አካባቢ ይገኛሉ። ግንኙነታቸው ግን ጉርብትና እንጅ በአገልግሎት አይገናኙም። - Uvula/እንጥል እንጥል ማለት ከላንቃ ላይ የተንጠለጠለ ማለት ነው። ከቶንሲል ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። - የቶንሲል ህመም/tonsialiophayngitis? ይህ የቶንሲል እና የላንቃ አካባቢ በተዋህስያን መወረር ነው። - የህመም ምልክቶች ትኩሳት ፣ ለመዋጥ መቸገር ፡ ራስ ምታት ፣ የአፍ መሽተት ፣ የአንገት ንፍፊት እብጠት ፣ ማንኮራፋት ፣ ሳል የቶንሲል ህመም መተላለፊያ መንገዶች 1. በትንፋሽ ጠብታ 2. በንክኪ - የባክቴሪያ ቶንሲል በብዛት የሚያጠቃው ማንን ነው? የባክቴሪያ ቶንሲል ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናትን የሚያጠቃ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ5-15 እድሜ ያሉት ይጠቃሉ። የቫይረስ ሲሆን ለጋ ህጻናትም ይጠቃሉ። የቶንሲል ህመም ተያያዥ ችግሮች 1 ፡ መግል መቋጠር tonsiar, peritosilar or retropharyngeal abscess 2. የሳንባ ምች / የማጅራት ገትር 3. የልብ ህመም rheumatic heart disease ይህን ለመከላከል ቶንሲል እንዳመመን ወደ ጤና ተቋም መሄድ። 4. የኩላሊት ህመም PS glomerulonephritis 5. የቶንሲል መፋፋት adenotonsilar hyperthrophy - የቶንሲል ህመም ህክምና መጀመሪያ የባክቴሪያ ወይስ የቫይረስ ነው የሚለውን መለየት ያስፈልጋል። መለያ መንገዶች 1. የቫይረስ ከሆነ የጉንፋን ምልክት አብሮ ይኖራል ግን አንዳንድ ጊዜ እንደ ቫይረስ ጀምሮ ወደ ባክቴሪያ ሊቀየር ስለሚችል ጥንቃቄ ይፈልጋል። 2. መግል የያዘ ከሆነ የባክቴሪያ ምልክት ነው ግን ይህን በደንብ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል። 3. ድድ፣ ከንፈር ወይም ምላስ የቆሰሉ ከሆነ የቫይረስ ምልክት ነው። 4. የነጭ የደም ሴል እና ተያያዥ ምርመራ መድሃኒት 1. የህመም ማስታገሻ 2. እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ የተለያዩ ጸረ ባክቴሪያ አለበለዚያም ፀረ ቫይረስ መድሃኒት 3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ ረፍት ማድረግ። 4. ማር እና የውሃ ኢንፋሎት መታጠን 5. የብርቱካን ወይም ሎሚ ጭማቂ። @DrSofonias

የከባድ ኩላሊት ህመም የከባድ ኩላሊት ህመም ምልክቶች ምንድናቸው? ለኩላሊት ህመም በርካታ ነገሮች ምክንያት መሆናቸው ይነገራል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ህመሙ እንደቆየበት ደረጃ የተለያዩ የምልክት ደ
የከባድ ኩላሊት ህመም የከባድ ኩላሊት ህመም ምልክቶች ምንድናቸው? ለኩላሊት ህመም በርካታ ነገሮች ምክንያት መሆናቸው ይነገራል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ህመሙ እንደቆየበት ደረጃ የተለያዩ የምልክት ደረጃዎች እንዳሉትም የህክምነናባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውንም ይገልጻሉ፡፡ እነሱም ደም ማነስ፣ ደም የተቀላቀለበት ሽንት፣ የጠቆረ ሽንት፣ ንቁ አለመሆን፣ የሽንት መጠን መቀነስ፣ የእግር፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ፣ የድካም ስሜት ፣ የደም ግፊት፣ እንቅልፍ እጦት የሚያሳክክ ቆዳ ናቸው፡፡ እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መጥፋት፣ ወንዶች ላይ ብልትን ማስነሳት መቸገር፣በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ፣ የትንፋሽ እጥረት፣ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት እና ራስ ምታት መሆናቸው ይነገራል፡፡ በሌላ በኩል ሽንት ይዞ አለመቆየት ፣ በቂ ውሃ መጠጣት፣ጨው የበዛበት ምግብ አለመመገብ፣የአልኮል መጠጥ መጠን መቀነስ፣ሲጋራ አለማጨስና ሌሎች የኩላሊት ህመምን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡ እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

"ስለ አራስ ህፃናት የገላ አስተጣጠብ ምን ያህል ያውቃሉ?" - ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም . የአራስ ህፃናትን ገላ አስተጣጠብ በተመለከተ የተለመዱ ከቤተሰብ የሚጠየቁ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው > እምብርት ሳይወድቅ ገላ መታጠብ ይችላል? > አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃን የመጀመሪያውን ገላ መታጠብ መቼ ነው ማግኘት ያለበት /ያለባት ? . > ህፃናት አንዴ ቤት ከገቡ በኋላ ምን ያህል ጊዜ መታጠብ ይፈልጋሉ በቀን ሁለቴ ?በቀን አንዴ? በሳምንት ሦስቴ ? > እምብርት ሳይወድቅ እና ከወደቀ በኃላ ያለው የገላ እጥበት ይለያይ ይሆን? . >የአራስ ህፃናት ገላ ስናጥብ ሊወሰዱ የሚገቡ የደህንነት ምክሮች ምንድናቸው? >የጨቅላ ህፃናት ገላ እጥበት ከመጀመርዎ በፊት የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች ምንድናቸው? . >የጨቅላ ሕፃናት በ1 ኢንች ብቻ የውሃ ጥልቀት በሰከንዶች ሽርፍራፊ የመስመጥ አደጋ ሊገጥማቸው እንደሚችሉ ያውቃሉን? . የአራስ ልጅን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰውነት እጥበት ማከናወን ለቤተሰብ ደስታ የሚሰጥ ቢሆንም በተለይ ለመጀመሪያ ወላጅ የራሱ የሆነ ጭንቀት ሊፈጥርም ይችላል። ከዚህም አልፎ በውሃ የመታፈን አደጋም ሊያስከትል ይችላሉ! ከተወለደ በስንተኛው ቀን ማጠብ አለብኝ እንዴት አድርጌ ወዘተ የተለመደ የእናት ጥያቄዎች ናቸው። . - አዲስ የተወለደ ጨቅላ ህፃን ለመጀመሪያ ጊዜ ገላውን መታጠብ ያለበት ምች ነው? . በአሁኑ ሰአት የአለም ጤና ድርጅት ጨቅላ ህፃናት ከተወለደ ከ24 ሰአት በኃላ ገላቸውን እንዲታጠብ ይመክራል። እስከ 24 ሰአት ማዘግየት የተፈለገበትም ምክንያት . 1. ወዲያው ማጠብ የሰውነት ሙቀታቸውን ዝቅ ሊያደርግ ስለሚችል (hypothermia ) እንዲሁም የደም ስኳር መጠናቸውን ሊቀንስ ስለሚችል (hypoglycemia ) አጋላጭነት ስለሚኖረው . 2. የህፃኑን እና የእናትን ትስስር ለመጨመር ሲባል እና የጡት ማጥባት ስኬትን ሲለሚጨምር . 3. ህፃናት ከመወለዳቸው በፊት ቆዳቸው ቨርኒክስ በሚባል ነጭ ንጥረ ነገር የተሸፈነ ሲሆን ይህም ተፈጥሯዊ እርጥበት ከማገልገሉም በላይ የፀረ ባክቴሪያ ባህሪ አለው። እንደ አሜሪካ የሕፃናት ህክምና አካዳሚ ይህን ንጥር ነገር ለተወሰነ ጊዜ የራስ ቆዳቸው ላይ መተው እንደሚቻል ይናገራሉ። . - አምብርታቸው ያልወደቁ ጨቅላ ህፃናት እንዴት ነው ገላቸውን መታጠብ ያለባቸው? . ህፃናት ገና እንደተወሰዱ ህትብታቸው በራሱ ደርቆ ድኖ ተቆርጦ እስኪወድቅ ድረስ ገላቸውን ማጠብ አይቻልም። ስለዚህ ለሰስ ባለ ውሃ ውስጥ በርከት ያለ ንፁ ጥቅልል ጥጥ በመንከር በጥጡ መፅዳት ይቻላል። . እትብታቸው ደርቆ ድኖ የወደቀ ጨቅላ ህፃናት ገላ ማጠብ ከመጀመርዎ በፊት ሊያዘጋጇቸው የሚያስፈልጉ ግብአቶች - ለህፃናት ማጠቢያነት የተዘጋጀ የማጠቢያ ፕላስቲክ - የህፃናት የተዘጋጀ ቫዝሊን እና ሳሙና . - ከታጠበ በኃላ የሚቀይረው ሙሉ ልብስ እና ማቀፊያ - ንፋስ እና ቅዝቃዜ የሌለው የማጠቢያ ክፍል . - በቂ ሞቅ ያለ ውሃና ለመበረዣ የሚሆን ቀዝቃዛ ውሃ በተለያየ እቃ ማቅረብ - እጃችሁን በሳሙና መታጠብ . - ህፃኑን በማጠብያ እቃ ውስጥ በቂ ቀዝቃዛ እና ሙቅ ውሃ ይበርዙ - ውሃው ሲበረዝ እጅግ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። የነሱ ቆዳ እጅግ ለስላሳ ስለሆነ ለቃጠሎ ሊጋለጡ ይችላሉ።ይህንን የቃጠሎ አደጋ ለመቀነስ ሁል ጊዜ ከተበረዘ በኃላ በክርናችን መለካት አለብን። . - ስናጥባቸው ተሙለጭልጨው ሊወድቁ ስለሚችሉ ማጠቢያውን እና አካባቢውን አስተካክሎ መጀመር - የህፃኑን ልብስ ካወለቁ በኃላ ሳያቆዩት እንደማጠቢያው አመችነት ህፃኑን እቀፉት። በሚያቅፉበት ጊዜ አንገቱን እራሱን አማካኝ በማድረግ በግራ እጅ በመያዝ በቀኝ እጃችሁ ለህፃኑ ማጠቢያ ተብሎ በተዘጋጀው ዕቃ ላይ ቀስ ብላችሁ እና ቀና አድርጋችሁ በቂጥ አስቀምጡ። . ልብ ሊባል የሚገባው እንዳያፍነው ውሃ ወደ ፊቱ እንዳይመጣ እና ወደ አይኑ አፍንጫው እንዳይገባ በመጠንቀቅ እጃችሁን ትንሽ ሳሙና ቀብታችሁ ፀጉሩን ከግንባሩ ወደ ኃላ እጠቡት። የህፃናት ገላ ማጠቢያ ሳሙና አይን ስለማያቃጥል ሳናበዛ በጣታችን ነካ እያደረግን ቀስ አድርጎ ማሸት። እጃችሁን ውሃ ወስጥ እየነከራችሁም ፊቱን እጠቡት። . ልብ ሊባል የሚገባው ፊት ላይ ውሃ መፍሰስ የለበትም ሊያፍናቸው ስለሚችል ጆሮን የጆሮን ስር አንገት አጥባችሁ ስጨርሱ ወደ ታች ተሙለጭልጮ እንዳይወድቅ ይዘው ይጠቡ። . ሁሉም የሰውነት ክፍል በጥንቃቄ ጥርት ብሎ ከታጠበ በኃላ ለማለቅለቂያ ባዘጋጃችሁት ለብ ያለ ውሃ አለቅልቃችሁ አፅዱት ቀጥሎም ወዲያውኑ ተዘርግቶ በተቀመጠው ፎጣ ላይ አስተኞቶ ጥቅልል በማድረግ ገላው ላይ ያለውን ውሃ አድርቁ። ቀጥሎም የቆዳ ድርቀት ለመከላከል ካቀረባችሁት ቅባት ገላውን ይቀቡ። በመፀዳጃ አከባቢ በርከት አድርገው ይቀቡ። በመጨረሻም ሙሉ ልብሱን አልብሳችሁ በማቀፊያ በመጠቅለል እቅፍ ያድርጉት። . የህፃናትን የቆዳ ድርቀት ለመከላከል ሲባል በሳምንት ሶስት ጊዜ ማጠብ በቂ ነው ። . መልካም ጤንነት ተመኘሁ ለብዙሃን እንዲደርስ ሼር በማድረግ ይተባበሩን 🙏❤ @DrSofonias

ባለፈው ሳምንት ከሰማሁት አስደንጋጭና ቀልብ የሚስብ ዜና በሀገራችን ከ30-40 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በሱሰኝነት የተያዘ መሆኑን ነው። . ሱስ ስንል በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ የተያዘውን አይጨምርም። ሱሰኝ
ባለፈው ሳምንት ከሰማሁት አስደንጋጭና ቀልብ የሚስብ ዜና በሀገራችን ከ30-40 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በሱሰኝነት የተያዘ መሆኑን ነው። . ሱስ ስንል በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ የተያዘውን አይጨምርም። ሱሰኝነት በአጭር ቃል ባርነት ነው። ከላይ የተጠቀሰውን ቁጥር ስንዘረዝረው ፤ በማንኛውም መንገድ ላይ ከምታገኛቸው አስር መኪናዎች ውስጥ የአራቱ ሹፌሮች ወይ መርቅነዋል ፣ ወይ በሀንጎበር ደንዝዘዋል አልያም የሀራራ ሰዓት ደርሶባቸው ሲጣደፉ ጉድ ሊያደርሱ ይችላሉ እንደ ማለት ነው። . እንግዲህ አስቡት ከሰላሳ ሚሊዮን እስከ አርባ ሚሊዮን ሱሰኞች በአንድ ሀገር ውስጥ ለሱሰኝነት ሰለባ ሲሆኑ? ስለዚህ ወዳጄ በመንገድ ላይ የወደቀ ፎቅ ካየህ እንዳትደነቅ ፣ በእናታቸው ስም የሚጠሩ ልጆችም ቢበዙ እንዳትጠይቅ ፣ ትራፊክ አስቁሞክ ወይ ስጠኝ ወይ ግጨኝ ቢልክ ግር እንዳትሰኝ ፤ ሐኪም ቤት ሄደህ ለመርፌ ኋላህን ስትሰጥ መርፌው ቦታውን እንዳይስት ፈጣሪን ጠይቅ። ሱሰኝነት የትምህርት ደረጃ ሳያይ ፣ ዘር ሀይማኖት ፆታ ሳይለይ ሁሉንም እኩል የሚያጠቃ ወረርሽኝ ነውና። . በአገራችን የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ሲወድቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል። ለምን ይሆን ትውልድ አምካኝ በሆነው ሱስ ላይ ችላ ለማለት ተወደደ? . ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ

አነስተኛ የብልት ማነስ ችግር ያለባችሁ ሰወች ደውሉልን መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያ
አነስተኛ የብልት ማነስ ችግር ያለባችሁ ሰወች ደውሉልን መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተካክል ያሉበት ቦታ ድረስ ለተጨማሪ መረጃ (0992484672) በአዲስ አመራረት original vimax silver 60 capsual 🤗made in canada ✓ የብልትን መጠን ለመጨመር እንዲጨምር ✓ቶሎ የመጨረስ ችግር ✓ ለወሲብ ፍላጎት ማጣት በዘላቂነት ለመቅረፍ ፈለክ ስመጥር የሆነው new vimax silver 60 capsul እኛ ጋር ይገኛል። መፍትሄው አለ ከጎንዩሽ ጉዳት ነፃ  Tel ፦☎️ 0992484672 ዋጋ ፦3500ብር ብቻ ብዛት ለሚወስዱ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን 🚨በወሲብ ወቅት ብልቶ አልቆም ብሎ ወይም ቶሎ እየረጩ ወይም ቶሎ እየደከሙ ወይም ብልቶ ጥንካሬ በማጣት እየተልፈሰፈሰ ተቸግረዋል? በተጭማሪም ፦ 1) ብልት ውጥር እና ቀጥ ብሎ እንዲቆም 2)የብልትን ጡንቻዎች በማጠንከር የብልት መጠንን መጨመር(4 inch) 3)ቆዳ እንዲለጠጥ በማድረግ በዛው ልክ ውፍረት እንዲጨምር የሚያደርገውን ሁሉንም ግልጋሎት በአንድ ላይ የያዘውን ዘላቂ መፍትሄ   new vimax silver 60 capsul 💯%✓✓ original መሉ በሙኑ ከተፈጥሮ ንጥረነገሮች ብቻ የተሰራ የ ካናዳ ምርት የሆነውን አስመጥተናል ☎️ 0992484672 ላይ ይደውሉ Inbox👉 @SellerMan12 🚘🚖 ክፉለሀገር ላላችሁ እና ሌሎች ክልል ከተሞች ላላችሁ customers በ ፈጣን ems (posta) እንልካለን 🔴አድራሻ አዲስ አበባ #Free Delivery in AA 📦ለክፍለ ሃገር ደንበኞቻችን በፖስታ እንልካለን 👉ተጨማሪ t.me/Herbal_treatment_end_marketing

በተፈጥሮ የሚከሰት የወንድ የሽንት ቱቦ ጫፍ የአፈጣጠር ችግር [አማርኛ | Afan Oromo] ትርጉም፡ የሽንት ቱቦ ጫፍ የብልት ጫፍ ላይ መሆን ሲገባዉ ከብልት ጫፍ በተለያየ ረቀት ወረድ ብሎ ከስር አቅጣጫ ሲሆን። የበሽታዉ ምልክት፡ - የሽንት ቱቦ ጫፍ ከወንድ ብልት ከስር አቅጣጫ ሆኖ እንድየ ችግሩ ክብደት ከብልት ጫፍ በተለያየ ረቀት ወረድ ብሎ ሲገኝ። - የብልት አላባሽ ቆዳ ከላይ በኩል በዝቶ ከሰር ማነስ። - እንደየ ችግሩ ክብደት የተለያየ መጠን ያለው የብልት ወደታች ማጎንበስ ወይንም መጣመም። በጊዜ ካልታከም ሊመጡ የሚችሉ ችግሮች - ሽንት በትክክል ወደፊትና በትክክለኛዉ ፍሰት ረጭቶ ለመሽናት መቸገር። - ከበድ ያለው አይነት ከሆነ (ማለትም የሽንት ቱቦ ጫፍ ከብልት ጫፍ ወደታች ረቆ የሚገኝ ከሆነና ከፈተኛ መጠን ያለው የብልት ጥመት ካለ) ቆሞ ለመሽናት መቸገር። - ከፍተኛ መጠን ያለው የብልት መጣመም አብሮት ሲኖር ብልት ሲቆም ቀጥ ብሎ ያለመቆም ችግር እና ችግሩ ካልተስተካከለ ህጻኑ አድጎ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ግብረ ሰጋ ግኑኝነት ለማድረግ መቸገር። - በችግሩ ምክኒያት ህጻናት ከሌሎች ጤናማ ብልት ካላችዉ ልጆች ጋር በማነጻጸር ለሃሳብና ጭንቀት መጋለጥ። ሊሰጥ የሚገባ ህክምና - የሄን ችግር ያላቸዉ ህጻናት በግርዛት ወክት ተቆርጦ የሚጠፋው ቆዳ ችግሩን ለማስተካከል ስለሚረዳ ችግሩ በቀዶ ህክምና እስኪስተካከል ድረስ በፍጹም መገረዝ ዬለባችውም። - ህጻናት ስድስት ወር ከሞላችዉ በዋላና ትምህርት ከመጀመራቸዉ በፊት ባለዉ እድሜ በቀዶ ህክምና ማስተካከል ያስፈልጋል። . Rakkoo haala malee uummamuu fiinxa ujummoo fincaanii dhiiraa; yoo fiinxi ujummoo fincaanii fiinxa qaama saalaarra osoo hin taane, fiinxa irraa gadi siqee qaama saalaa gara jalaatiin ta’uu Hiika: Akkuma armaan olitti ibsame Mallattoolee dhukkubichaa: Qaawwaan fiinxa ujummoo fincaanii fiinxa qaama saalaa irraa gadi siqee qaama saala gara jalaatiin ta’uu. Haguuggiin (qolli) qaama saala karaa jalaa hanqatee karaa gubbaa baay’achuu Akkasumas gadi jallachuu yookiin gad dacha’uu qaama saala Yeroodhaan yoo yaalllamuu baatee rakkooleen dhufuu danda’an Karaa sirrii fi yaa’a qajeeltoodhaan fincaan fuulduratti darbatanii fincaahuuf rakkachuu. Rakkichi rakkoo isa gosa cimaa yoo ta’emmoo (jechuun fiinxi ujummoo fincaanii fiinxa qaama saalaa irraa baay’ee gadi fagaatee yoo argamee fii jallachuun qaama saala sadarkaa olaanaa yoo ta’e) dhaabbatanii fincaahuuf rakkachuu. Rakkichi gadi jallachuu qaama saala sadarkaa olaanaa waliin yoo ta’e, qaamni saalaa yeroo dhaabbattu sorooree dhaabbachuu dadhabuu fii yoo sirreefamuu baate yeroo daa’imni guddatu wal qunnamtii saala irratti rakkoo fiduu. Daa’imman rakkoo kana qaban, daa’imman biroo qaama saala sirrii qaban waliin wal bira qabanii ilaaluudhaan rakkoolee xiin sammmuu Kan akka dhiphachuutiif saaxilamuu. Yaala kennamuu malu Daa’imman Rakkoo kana qaban gogaan yeroo kittaanuu muramee badu rakkoo kana sirreessuuf waan gargaaruuf hanga rakkoon Kun baqaqsanii waldhaanuudhaan sirreefamutti gonkuma kittaanamuu hin qabani. Rakkoo kana daa’imman qaban umrii ji’a jahaa erga guutanii boodaa fii umrii barumsa eegaluu osoo hin gahiin duratti baqaqsanii waldhaanuudhaan sirreessuun barbaachisaadha. Dr. Sofonias Ermias MD, Ethiopia @DrSofonias

#የሳንብ_ምች_ምንድነው? ይህ የሳንባ ኢንፌክሽን ሲሆን ከቀላል እስከ ህይወት አስጊ እስከሆነ ደረጃ ሊደርስ ይችላል።ይህም ማሳል በአብዛኛው ደረቅ ፤ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግርን ያስከትላል።ይህ እክ
#የሳንብ_ምች_ምንድነው? ይህ የሳንባ ኢንፌክሽን ሲሆን ከቀላል እስከ ህይወት አስጊ እስከሆነ ደረጃ ሊደርስ ይችላል።ይህም ማሳል በአብዛኛው ደረቅ ፤ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግርን ያስከትላል።ይህ እክል በህጻናቶች፤እድሜያቸው ከ65 በላይ በሆኑ ፤እንዲሁም ተጓዳኝ ችግር ባላቸው ታካሚዎች ላይ ትልቅ ችግር ያስከትላል።የሳንባ ምች በአብዛኛው በባክቴሪያ የሚመጣ ሲሆን በቫይረስ እና በፈንገስም ሊከሰት ይችላል። #ምልክቶቹ_ምንድናቸው? ሳል ትኩሳት የአተነፋፈስ ለዉጥ ትንፋሽ ስንስብ ደረት ላይ የሚሰማ ህመም ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ብርድ ብርድ ማለት እና ማንቀጥቀጥ #በሃኪም_መታየት_ይኖርብኛል?መቼ? አዎ መታየር ይኖርቦታል።ይህ እክል ከቀላል እስከ ህይወት ደረጃ ሊደርስ ይችላል። #መቼ_ላታይ? ሳሉ እየባሰ ሚሄድ ከሆነ የአተነፋፋስ እክሉ በእለት ተእለት ክንዉናችን ላይ ችግር ካመጣ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ካለ ከ38.8 ወይም በላይ ልብ ላይ ህመም ካለ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሌላ እክል ካለ ለምሳሌ ስኳር የኩላሊት HIV ወይም ሌላ የሳንባ ችግር ካለ #የሳንባ_ምች_እንዴት_ነው_ሚታከመው? በባክቴያ የመጣ የሳንባ ምች በአንቲባዮቲክ ይታከማል።ቀላሉ ከሆነ በአፍ የሚወሰድ ተሰጥቶት እቤት መጠቀም ይቻላል ነገር ግን ከባዱ ከሆነ በመርፌ ሀኪም ቤት ተኝተው ሊታከሙ ይችላሉ።ይህ በሚያዮት ሃኪም ላይ ይወስናል። #መቼ_ነው_ወደ_ጤንነቴ_ምመለሰው? መድሃኒቱን መዉሰድ በጀመሩ ከ3 እስከ 5 ቀን ባለዉ ዉስጥ መሻሻል ያሳያሉ።አብዛኛው ታካሚዎች ህክምናዉን በጀመሩ በ1 ሳምንት ዉስጥ ወደ ተለመደው የእለት ተእለት ስራቸው ይመለሳሉ ነገር ግን የመደካከም ስሜት እና ሳሉ እስከ 1 ወር ሊቆይ ይችላል{ነገር ግን በፊት ከነበረው እየቀነሰ ነው ሚመጣው} የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት @DrSofonias

ሰላም እንዴት ናቹህ የብዙዎቻቹን ጥያቄ የማልመልሰው በጣም ስራ ስለሚበዛብኝ ነው ይቅርታ አርጉልኝ በተቻለኝ አቅም ለመመለስ ሞክራለው። ከዚ በፊት ስለ Vimax መረጃ ሰጥቻቹህ ነበር የአስመጪዎችን ስልክ እና አድራሻ በብዛት inbox ላይ ስትጠይቁኝ የነበራቹ ስልካቸው 0992484672 በ inbox ለማግኘት @SellerMan12