ar
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

تُعد قناة ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 805 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 171 في فئة الطب والمرتبة 1 704 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 805 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 11 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -422، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -3، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 17.48‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 6.17‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 463 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 223 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 6.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 12 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الطب.

19 805
المشتركون
-324 ساعات
-697 أيام
-42230 أيام
أرشيف المشاركات
የደም ማነስ ምልክቶች የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል መነሻው፣ የበሽታው ከባድነት እና ማንኛውም የጤና ችግር(ክንታሮት፣ ቁስለት፣ የወር አበባ ችግር ወይም ካንሰር የመሳሰሉት) አስተዋጽዎ ያደርጋሉ። ያለብዎት የደም ማነስ ቀለል ያለ ከሆነ ወይም ከብዙ ጊዜ በፊት ከተከሰተ ምንም አይነት ምልክት ላናይ እንችላለን። ለማንኛውም አይነት የደም ማነስ የጋራ የሆኑ ምልክቶች እነሆ፦ — የድካም ስሜት እና ጉልበት ማጣት — ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት በተለይ እንቅስቃሴ ስናደርግ — የትንፋሽ ማጠር እና ራስ ምታት — የትኩረት ማጣት — የማዞር ስሜት — የቆዳ መገርጣት — የእግር ጡንቻ መሸማቀቅ — የእንቅልፍ ማጣት 1. በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖሩባቸው ይችላል — ባልተለመደ ሁኔታ ወረቀት፣ በረድና ቆሻሻዎችን ለመመገብ መፈለግ — ጥፍሮቻችን ወደላይ መታጠፍ(መበላሸት) — የአፍ መሰነጣጠቅ እና መቁሰል 2. በቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ በቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል — በእጅና እግር ላይ መርፌ የመወጋት ስሜት መሰማት — የመዳሰስ ስሜት ማጣት — መንቀጥቀጥ እና ለመራመድ መቸገር — የእጅና እግር መንቀርፈፍ እና መጠንከር(መገተር) — የአስተሳሰብ መለዋወጥ 3. በሊድ(lead) መመረዝ የሚከሰት የደም ማነስ በከባድ ሁኔታ በሊድ መመረዝ ወደሚከተሉት ምልክቶች ያመራናል — ሰማያዊ_ጥቁር መስመር በድድ ላይ መኖር — የሆድ ህመም — የሆድ ድርቀት — ማስታወክ 4. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት የሚከሰት የደም ማነስ — የአይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን — ቡናማ ወይም ቀይ ሽንት — የእግር ቁስለት — ህፃናት እንዳይፋፉ/እንዳይዳብሩ መሆን — የኩላሊት ጠጠር በሽታ አይነት ምልክቶች 5. ሲክል ሴል የደም ማነስ የሲክል ሴል የደም ማነስ ምልክቶች — የድካም ስሜት — ለኢንፌክሽን መጋለጥ — በህፃናት ላይ የዕድገት እና ብስለት መዘግየት — የመገጣጠሚያ፣ ሆድ፣ እጅና እግር በተወሰነ ቆይታ በተደጋጋሚ ከባድ የህመም ስሜት መከሰት ናቸው የደም ማነስ ህክምና የደም ማነስ ህክምና እንደመነሻው ይወሰናል፦ በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ይህ አይነት የደም ማነስ የአመጋገብ ስርዓታችንን እና ብረት በመውሰድ ማከም ይቻላል። ይህ የብረት እጥረት የተከሰተው ከወር አበባ ውጪ በሆነ የደም መፍሰስ ከሆነ የሚፈስበትን ቦታ ማወቅ እና እንዲቆም ማድረግ ተገቢ ነው። ተጨማሪ የተለያዩ የጤና ነክ መረጃዎች እንድደርስዎ የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ @DrSofonias

መጥፎ የእግርና የጫማ ጠረንን ለማስወገድ 7 ቀላል ዘዴዎች በእግር እና በጫማ ውስጥ በሚፈጠር ከፍተኛ ሙቀት እና የእግር ቁስለት፣ ባክቴሪያ፣ ለእግር የማይስማሙ የካልሲ ምርቶች እና ጫማዎችን መጫማት ለዚህ ችግር እንደ መንስኤ ይወሰዳሉ። በጫማ ጠረን ምክንያት ብዙ ሰዎች ይሰቃያሉ፡፡ የችግሩ ግዝፈት ምን ያህል እንደሆነ የሚገባን ሰዎች ከእኛ አጠገብ መቀመጥ ሲቸገሩ ስናይ ነው፡፡ ታዲያ ይህን ከሰው የሚያቆራርጥ መጥፎ የእግር እና የጫማ ጠረን እንዴት መከላከል እንዳለብዎት ከዚህ በታች ያሉትን መፍትሄዎች ይመልከቱ። በጣም ቀላል ናቸው፤ በቤት ውስጥ ሊሞክሯቸው ይችላሉ፡፡ አንብበው ሲጨርሱ በጫማ ጠረን ለሚቸገሩ ወዳጆቻችሁ ሼር በማድረግ ውለታ ዋሉላቸው… መፍትሄዎች ለእግር፤ 1. የሻይ ቅጠል - ሁለት ጥቅል የሻይ ቅጠሎችን በሶስት ብርጭቆ ውሃ ማፍላት እና ከፈላ በኋላ በማውጣት፥ ከዛም በግማሽ ባልዲ ውሃ ቀዝቀዝ ማድረግ እና የውሃ ሙቀቱ ለእግር ተመጣጣኝ ከሆነ እግርን ዘፍዝፎ ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች ማቆየት እና ለሳምንት ያህል ይህን መደጋገም። 2. ዝንጅብል - መካከለኛ ቁመት ያለውን ዝንጅብል በመቆራረጥ እና ለ15 ደቂቃዎች ያህል ውሃ በመጨመር ማፍላት፥ ቀጥሎም ፈልቶ የወረደው ዝንጅብል ላይ ተወቀጠ የቡና ዱቄት መጨመር። ከዛም የሁለቱን ውህድ በአግባቡ አማስሎ በመቀላቀል ውስጠኛውን የእግር ክፍል ዘወትር ከመኝታ በፊት ለተከታታይ ሁለት ሳምንት በአግባቡ አዳርሶ ማሸት። 3. ቤኪንግ ሶዳ - አንድ የሾርባ ማንኪያን ቤኪንግ ሶዳ በእጅ ማስታጠቢያ ግማሽ ለብ ያለ ውሃ መቀላቀል እና እግርን እስከ 20 ደቂቃዎች ድረስ መዘፍዘፍና ከዛ አድርቆ መተኛት፤ ይህን ለአንድ ተከታታይ ሳምንት ማድረግ መልካም ነው። 4. ጨው - እግርን ለብ ባለ ጨዋማ ውሃ መዝፍዘፍም ሌላው መፍትሄ ነው፤ አንድ ተኩል የሾርባ ማንኪያ ጨውን በአንድ ጆግ ውሃ በማፍላት ቀዝቀዝ አድርጎ እግርን ለ20 ደቂቃ መዝፈዝፍና ይህንንም ለሁለት ሳምንታት ያህል መሞከር። 5. ዘይት - ከበቆሎ የተዘጋጁ የአሲድ መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዘይት መሰል ፈሳሽ ኬሚካሎችም ለዚህ ችግር መፍትሄ ናቸው፤ እግር ላይ የሚከሰትን አላስፈላጊ እርጥበትና ላበት በማስወገድ ጤናማ ያደርጉታልና። 6. ሽንኩርት - አነስ ያሉ አራት ራስ ሽንኩርቶችን ልጦ በስሱ መጨቅጨቅ፤ ቀጥሎም በደንብ ታጥቦ የፀዳው እግርዎ ላይ በጨርቅ በማድረግ ማሰር እና ከሶስት ሰአታት በኋላ በመፍታት ማናፈስ። 7. አልኮል - እግርን በደንብ ታጥቦ ማፅዳት እና ማደራረቅ ቀጥሎም የተወሰነ አልኮልን ውስጠኛው እግር ላይ በማፍሰስ ማዳረስ እና ማሻሸት በደንብ ሲደርቅም እግርን አናፍሶ ከደቂቃዎች በኋላ ጫማ ማድረግ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች እግርዎን ከማንኛውም የባክቴሪያ እና የፈንገስ ክምችት የመከላከል እና ምናልባት የተፈጠረ መጥፎ ጠረን ካለም ያንን ለማስወገድ የሚረዱ ናቸው። ከላይ እንደገለፅንላችሁ በጫማ ጠረን ለሚቸገሩ ወዳጆቻችሁ ሼር በማድረግ ውለታ ዋሉላቸው… መረጃው ብዙዎች እንዲያነቡ ሼር ያድርጉ ። ተጨማሪ የተለያዩ የጤና ነክ መረጃዎች እንድደርስዎ የቴሌግራሜን ቻናል ይቀላቀሉ @DrSofonias

በአካል ክፍል ደስተኛ አለመሆን =================== ኪሩቤል የሁለተኛ አመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው። አፍንጫው ጎራዳ እንደሆነ ያስባል። ሁልጊዜ ፊቱን ሲታጠብ አፍንጫውን በመስታወት ይመለከታል። ትምህርት ቤት ወይም መኪና ላይ መስታወት ካጋጠመው ፊቱን በተለይ ደግሞ አፍንጫውን ሳይመለከት ማለፍ አይችልም። ከሰዎች ጋር ሲያወራ ሰዎች አፍንጫውን የሚመለከቱት ይመስለዋል። ጭንቀቱ እየጨመረ ሲመጣ መስታወት ፊት የሚያሳልፈው ሰአት እየጨመረ ሄደ። እየተባባሰ ሄዶ "እንደዚህ አይነት አፍንጫ ይዤ እንዴት ከዶርም እወጣለሁ?" ብሎ ክላስ መቅጣት መጀመረ። ብቸኝነት እያበዛ መጣ። ኪሩቤል ለህክምና ሲመጣ አፍንጫው የተለየ ነገር አልነበረውም። ህክምናው ረጅም ጊዜ ቢወስድም አሁን ጭንቀቱ ሙሉለሙሉ ጠፍቶለታል። አልፎአልፎ ካልሆነ ስለአፍንጫው አያስብም። መስታወት ፊት ብዙ ሰአት መቆም ቢተውም አንፀባራቂ ነገሮች አጠገብ ሲያልፍ ግን አሁንም ፊቱን መመልከቱ አልቀረም። ብዙ ሰዎች ደስተኛ ከማይሆኑበት የሰውነት ክፍል ፊት ዋነኛው ሲሆን ከፊትም አፍንጫ ቀዳሚ ነው። ከአፍንጫ በተጨማሪ ወንዶችን የፀጉር መግባት፣ የብልት መጠን እና ተክለ ቁመና የሚያሳስባቸው ሲሆን ሴቶች ደግሞ ግንባር፣ ጆሮ፣ የጡት መጠንና ቅርፅ፣ እንዲሁም የሰውነት ቅርፅ ያሳስባቸዋል። አብዛኛው (?ሁሉም) ሰው ቅር የሚለው የሰውነት ክፍል ይኖረዋል። ይህ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ጭንቀት የሚያስከትል ከሆነ ምያዊ እገዛ ያስፈልገዋል። ከላይ ታሪኩ የተፃፈው ኪሩቤል ስሙ ኪሩቤል አይደለም። የሚማረውም ሌላ የትምህርት አይነት ነው። መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው።

ክብደትዎን መቀነስ ይፈልጋሉ ? እንግዲያውስ እነዚህን ምግቦች ያስወግዱ - ክብደት መቀነስ ቀላል ተግባር ባይሆንም ሰዎች ክብደት በመጨመራቸው የሚመጡባቸውን የጤና ችግሮች ለማስወገድ ጥረት ሲያደርጉ ይሞክራሉ ፡፡ ክብደታችን ከልክ ሲያልፍ ከሚመጡብን ወስብስብ የጤና ችግሮች መሃከል የልብ በሽታ፣ስትሮክ፣የስኳር በሽታ ፣ድብርት እና ካንሰር ይጠቀሳሉ ፡፡ ክብደት መቀነስ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ከመቀልበስ ባሻገር በየጌዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ጤነኛ አመጋገብ የተስተካከለ ክብደት እንዲኖረን ያደርጋል ፡፡ በአንፃሩ የምንመገበውን ምግብ አለማወቅ የምንፈልገውን ክብደት ለመቀነስ አዳጋች ያደርግብናል፡፡ ከታች የተዘረዘሩት ምግቦች ደጋግመን ከተመገብናቸው ክብደት የመቀነስ አላማችን ግቡን እንዳይመታ ያደርጉብናል፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ፡፡ ቺፕስ እን ፍሬንች ፍራይስ (ድንች ጥብስ) ከፍተኛ የሆነ የካሎሪና የቅባት መጠን ያለው በመሆኑ ክብደት ለመቀነስ ለሚያስብ ሰው የሚመከሩ አይደሉም፡፤የተጠበሰ ድንች የደም ውስጥ የስኳር እና ኢንሱሊንን መጠን በመጨመር የምግብ አወሳሰዳችንን የተዛባ ያደርገዋል፡፡ ድንች መመገብን ከወደዱ ከመጥበስ ይልቅ የተቀቀለ ቢሆን ጤነኛ ይሆናል ፡፡ የሶዳ መጠጦች በሶዳ መጠጦች ውስጥ የሚገኙ አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች የረሃብ ስሜትን በመፍጠር አብዝተን እንድንመገብ ያደርጉናል ፡፡ ጥማችንን ለሙቁረጥ ንፁህ ውሃ አልያም ውሃ በሎሚ አማራጭ ብናደርግ ለጤናችን አሰብን ማለት ነው ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሶዳ መጠጦችንአብዝቶ መጠጣት የሆድ አካባቢ ስቦችን ይጨምራል ፡፡ ቅባት የበዛበት ስጋ ጮማ እንዲሁም የአሳማ ስጋ እጅግ ብዙ ስብ ስለሚኖረው ክብደትን ይጨምራል ፡፡ ፈንዲሻ ዘይት አብዝቶ ስለሚወስድ ደጋግሞ መመገብ ክብደት መቀነስ ለሚፈልግ ሰው አይመከርም ማርጋሪን ማርጋሪን ከቅቤ የበለጠ እጅግ በቅባት የተሞላና በምግብ ይዘቱም ደካማ ነው ፡፡አብዝተን እና ደጋግመን ከወሰድነው ክብደት ከመጨመር ባሻገር ለልብ በሽታ ያጋልጠናል፡፡ ነጭ ዳቦ (ፉርኖ) በምግብ ይዘቱ እጅግ ደካማ ሲሆን በውስጡ የያዘው ካርቦሃይድሬት ውፍረትን ያስከትላል ፡፡ ስንመገበው የማጥገብ ሳይሆን ቶሎ ቶሎ የመራብ ስሜትን ይፈጥርብናል፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮአዊ የሆነውን ከስንዴ የሚዘጋጅ ዳቦ ብንጠቀም ይመከራል ፡፡ፓስታ እና የመሳሰሉትንም አዘውትረን ከመመገብ መቆጠብ አለብን ፡፡ የአልኮል መጠጦች የአልኮል መጠጦች ምንም አይነት የምግብ ይዘት የሌላቸው ሲሆን የካርቦሃይድሬት ፣ የስብና የፕሮቲን መፈጨት ሂደትን በማዘግየት ተጨማሪ ስብ በሰውነታችን እንዲከማች ያደርጋል ፡፡ የታሸጉ ጭማቂዎች የታሸጉ የፍራፍሬ ጭማቂዎች ጁስ በመደረግ ሂደት ተፈጥሮአዊ የምግብ ይዘታቸውን ከማጣታቸው ባሻገር የያዙት የስኳር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ክብደትን ይጨምራሉ፡፡ እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

ክብደትዎን መቀነስ ይፈልጋሉ ? እንግዲያውስ እነዚህን ምግቦች ያስወግዱ - ክብደት መቀነስ ቀላል ተግባር ባይሆንም ሰዎች ክብደት በመጨመራቸው የሚመጡባቸውን የጤና ችግሮች ለማስወገድ ጥረት ሲያደርጉ ይሞክራሉ ፡፡ ክብደታችን ከልክ ሲያልፍ ከሚመጡብን ወስብስብ የጤና ችግሮች መሃከል የልብ በሽታ፣ስትሮክ፣የስኳር በሽታ ፣ድብርት እና ካንሰር ይጠቀሳሉ ፡፡ ክብደት መቀነስ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ከመቀልበስ ባሻገር በየጌዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ጤነኛ አመጋገብ የተስተካከለ ክብደት እንዲኖረን ያደርጋል ፡፡ በአንፃሩ የምንመገበውን ምግብ አለማወቅ የምንፈልገውን ክብደት ለመቀነስ አዳጋች ያደርግብናል፡፡ ከታች የተዘረዘሩት ምግቦች ደጋግመን ከተመገብናቸው ክብደት የመቀነስ አላማችን ግቡን እንዳይመታ ያደርጉብናል፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ፡፡ ቺፕስ እን ፍሬንች ፍራይስ (ድንች ጥብስ) ከፍተኛ የሆነ የካሎሪና የቅባት መጠን ያለው በመሆኑ ክብደት ለመቀነስ ለሚያስብ ሰው የሚመከሩ አይደሉም፡፤የተጠበሰ ድንች የደም ውስጥ የስኳር እና ኢንሱሊንን መጠን በመጨመር የምግብ አወሳሰዳችንን የተዛባ ያደርገዋል፡፡ ድንች መመገብን ከወደዱ ከመጥበስ ይልቅ የተቀቀለ ቢሆን ጤነኛ ይሆናል ፡፡ የሶዳ መጠጦች በሶዳ መጠጦች ውስጥ የሚገኙ አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች የረሃብ ስሜትን በመፍጠር አብዝተን እንድንመገብ ያደርጉናል ፡፡ ጥማችንን ለሙቁረጥ ንፁህ ውሃ አልያም ውሃ በሎሚ አማራጭ ብናደርግ ለጤናችን አሰብን ማለት ነው ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሶዳ መጠጦችንአብዝቶ መጠጣት የሆድ አካባቢ ስቦችን ይጨምራል ፡፡ ቅባት የበዛበት ስጋ ጮማ እንዲሁም የአሳማ ስጋ እጅግ ብዙ ስብ ስለሚኖረው ክብደትን ይጨምራል ፡፡ ፈንዲሻ ዘይት አብዝቶ ስለሚወስድ ደጋግሞ መመገብ ክብደት መቀነስ ለሚፈልግ ሰው አይመከርም ማርጋሪን ማርጋሪን ከቅቤ የበለጠ እጅግ በቅባት የተሞላና በምግብ ይዘቱም ደካማ ነው ፡፡አብዝተን እና ደጋግመን ከወሰድነው ክብደት ከመጨመር ባሻገር ለልብ በሽታ ያጋልጠናል፡፡ ነጭ ዳቦ (ፉርኖ) በምግብ ይዘቱ እጅግ ደካማ ሲሆን በውስጡ የያዘው ካርቦሃይድሬት ውፍረትን ያስከትላል ፡፡ ስንመገበው የማጥገብ ሳይሆን ቶሎ ቶሎ የመራብ ስሜትን ይፈጥርብናል፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮአዊ የሆነውን ከስንዴ የሚዘጋጅ ዳቦ ብንጠቀም ይመከራል ፡፡ፓስታ እና የመሳሰሉትንም አዘውትረን ከመመገብ መቆጠብ አለብን ፡፡ የአልኮል መጠጦች የአልኮል መጠጦች ምንም አይነት የምግብ ይዘት የሌላቸው ሲሆን የካርቦሃይድሬት ፣ የስብና የፕሮቲን መፈጨት ሂደትን በማዘግየት ተጨማሪ ስብ በሰውነታችን እንዲከማች ያደርጋል ፡፡ የታሸጉ ጭማቂዎች የታሸጉ የፍራፍሬ ጭማቂዎች ጁስ በመደረግ ሂደት ተፈጥሮአዊ የምግብ ይዘታቸውን ከማጣታቸው ባሻገር የያዙት የስኳር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ክብደትን ይጨምራሉ፡፡ እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮቻችን በዛሬው ዝግጅታችን የምንዳስሰው አንገብጋቢ እየሆነ የመጣውንና ሴቶች እህቶቻችንንና እናቶቻችንን እያጠቃ ስላለው የመሀጸን በር ካንሰር(cervical cancer) ነው፡፡ የመሀጸን በር ካንሰር(cervical cancer) ምንድን ነው??? -የመሀፀን በር ካንሰር (cervical cancer) የሚከሰተው የመሀጸን በር ላይ ያሉት ህዋሶች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲያድጉ ነው፡፡ -የመሀፀን በር የምንለው ከታችኛው ከመሀጸን ክፍል ወደ ሴት ብልት የሚከፈተው የሲሊንደር ቅርፅ ያለው ህብረህዋስ ነው፡፡ ለመሀፀን በር ካንሰር(cervical cancer) ተጋላጭ የሚሆኑት እነ ማን ናቸው??? 1. HPV (human papilloma virus) በተደጋጋሚ የሚጠቁ ሰዎች -ዋነኛው የመሀፀን ካንሰር መንስኤ ሲሆን ይህም ቫይረስ የሚታወቀው በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ከሰው ወደ ሰው በመተላለፍ የአባላዘር በሽታ በማስከተል ነው፡፡ 2. ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብርስጋ ግንኙነት መፈፀም 3. የሰውነትን የበሸታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ በሸታዎች ሲኖሩ ለምሳሌ ፡ ኤች.አይ.ቪ 4. ሲጋራ ማጨስ 5. ለረጅም ጊዜ በአፍ የሚዋጡ የወሊድ መቆጣጣጠሪያዎችን መጠቀም 6. ከ17 አመት እድሜ በታች ሆነው ልጅ ለመውለድ የተጋልጡ ሴቶች 7. 3 እና ከዛ በላይ ልጆችን መውለድ 8. በለጋ እድሜ የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የበሸታው ምልክቶቹ ምንድን ናቸው??? -በበሸታው የመጀመርያ ጊዜያት ውስጥ ምልክቶቹ ጎልተው አይታዩም፡፡ በብዛት የሚስተዋሉት ምልክቶች :- > ከመሀፀን ደም መፍሰስ > ከግንኙነት በኃላ የደም መፍሰስ > መጥፎ ጠረን ያለው ከመሀፀን የሚወጣ ፈሳሽ > የጎን እና ጎን ህመም > ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ወይም ሽንት > በማረጥ ጊዜ ደም መፍሰስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በምን መከላከል እንችላለን??? 1. Pap smear በማሰራት -ይህ ምርምራ በየስንት አመቱ እንደሚሰራ የሚወሰነው በእደሜዎት እና ካሎት ትጋላጭነት አንጻር ነው፡፡ 2. በግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀም 3. ሲጋራማጨስ ማቆም 4. መወሰን የማህጸን በር ካንሰር ደረጃዎች ደረጃ 0- የመጀመሪያዎቹ ህዋሶች ከቁጥጥር ውጭ በማህጸን በር ላይ ማደግ የሚጀምሩበት ግዜ ነው ደረጃ 1- በዚህ ግዜ ካንሰሩ የማህፀን በር ላይ ብቻ ያለ ሲሆን ይህም ሁለት ደረጃዎች አሉት ደረጃ 1ሀ- ካንሰሩ በማይክሮስኮፕ/ በአጉሊ መነፅር/ ብቻ የሚታይ ነው ደረጃ 1ለ- በዚህ ግዜ በማህፀን በር ላይ ያሉትን ለውጦች በአይናችን መለየት የምንችልበት ደረጃ ነው ደረጃ 2- በሽታው የማህጸን በርንና ማህፀንን የሚያጠቃልልበት ሲሆን ነገር ግን ወደሌላ ሰውነት ክፍሎች አልተሰራጨም፡፡ ደረጃ 3- የምንለው ካንሰሩ ማህጸንን አልፎ በዛ አከባቢ ያሉትን የመራቢና የብልት ክፍሎች ሲያጠቃ ነው ደረጃ 4- በዚህ ግዜ ካንሰሩ ወደ ሽንት ፊኛ አንጀት ጉበት አጥንቶችን ወይም ሳንባን ያጠቃል ህክምናዎቹ 1) ቀዶ ጥገና 2) የጨረር ህክምና እና 3) የመድሀኒት ህክምና ናቸው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 8809 ዶክተር አለ ብለው ይደውሉ፡፡

ውድ ተከታታዮቻችን በዛሬው ዝግጅታችን የምንዳስሰው አንገብጋቢ እየሆነ የመጣውንና ሴቶች እህቶቻችንንና እናቶቻችንን እያጠቃ ስላለው የመሀጸን በር ካንሰር(cervical cancer) ነው፡፡ የመሀጸን በር ካንሰር(cervical cancer) ምንድን ነው??? -የመሀፀን በር ካንሰር (cervical cancer) የሚከሰተው የመሀጸን በር ላይ ያሉት ህዋሶች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲያድጉ ነው፡፡ -የመሀፀን በር የምንለው ከታችኛው ከመሀጸን ክፍል ወደ ሴት ብልት የሚከፈተው የሲሊንደር ቅርፅ ያለው ህብረህዋስ ነው፡፡ ለመሀፀን በር ካንሰር(cervical cancer) ተጋላጭ የሚሆኑት እነ ማን ናቸው??? 1. HPV (human papilloma virus) በተደጋጋሚ የሚጠቁ ሰዎች -ዋነኛው የመሀፀን ካንሰር መንስኤ ሲሆን ይህም ቫይረስ የሚታወቀው በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ከሰው ወደ ሰው በመተላለፍ የአባላዘር በሽታ በማስከተል ነው፡፡ 2. ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብርስጋ ግንኙነት መፈፀም 3. የሰውነትን የበሸታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ በሸታዎች ሲኖሩ ለምሳሌ ፡ ኤች.አይ.ቪ 4. ሲጋራ ማጨስ 5. ለረጅም ጊዜ በአፍ የሚዋጡ የወሊድ መቆጣጣጠሪያዎችን መጠቀም 6. ከ17 አመት እድሜ በታች ሆነው ልጅ ለመውለድ የተጋልጡ ሴቶች 7. 3 እና ከዛ በላይ ልጆችን መውለድ 8. በለጋ እድሜ የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የበሸታው ምልክቶቹ ምንድን ናቸው??? -በበሸታው የመጀመርያ ጊዜያት ውስጥ ምልክቶቹ ጎልተው አይታዩም፡፡ በብዛት የሚስተዋሉት ምልክቶች :- > ከመሀፀን ደም መፍሰስ > ከግንኙነት በኃላ የደም መፍሰስ > መጥፎ ጠረን ያለው ከመሀፀን የሚወጣ ፈሳሽ > የጎን እና ጎን ህመም > ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ወይም ሽንት > በማረጥ ጊዜ ደም መፍሰስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በምን መከላከል እንችላለን??? 1. Pap smear በማሰራት -ይህ ምርምራ በየስንት አመቱ እንደሚሰራ የሚወሰነው በእደሜዎት እና ካሎት ትጋላጭነት አንጻር ነው፡፡ 2. በግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀም 3. ሲጋራማጨስ ማቆም 4. መወሰን የማህጸን በር ካንሰር ደረጃዎች ደረጃ 0- የመጀመሪያዎቹ ህዋሶች ከቁጥጥር ውጭ በማህጸን በር ላይ ማደግ የሚጀምሩበት ግዜ ነው ደረጃ 1- በዚህ ግዜ ካንሰሩ የማህፀን በር ላይ ብቻ ያለ ሲሆን ይህም ሁለት ደረጃዎች አሉት ደረጃ 1ሀ- ካንሰሩ በማይክሮስኮፕ/ በአጉሊ መነፅር/ ብቻ የሚታይ ነው ደረጃ 1ለ- በዚህ ግዜ በማህፀን በር ላይ ያሉትን ለውጦች በአይናችን መለየት የምንችልበት ደረጃ ነው ደረጃ 2- በሽታው የማህጸን በርንና ማህፀንን የሚያጠቃልልበት ሲሆን ነገር ግን ወደሌላ ሰውነት ክፍሎች አልተሰራጨም፡፡ ደረጃ 3- የምንለው ካንሰሩ ማህጸንን አልፎ በዛ አከባቢ ያሉትን የመራቢና የብልት ክፍሎች ሲያጠቃ ነው ደረጃ 4- በዚህ ግዜ ካንሰሩ ወደ ሽንት ፊኛ አንጀት ጉበት አጥንቶችን ወይም ሳንባን ያጠቃል ህክምናዎቹ 1) ቀዶ ጥገና 2) የጨረር ህክምና እና 3) የመድሀኒት ህክምና ናቸው፡፡

የጥርስ ህመምን በቤት ውስጥ በቀላሉ ለማስታገስ ... የጥርስ ህመም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰትብን ይችላል። የጥርስ ህመም በሚያጋጥመን ጊዜ በርካቶች ለህመሙ ሲባል ምግብ ነክ ከሆኑ ነገሮች ለመራቅ የሚገደዱ ሲሆን፥ ይህንን ህመም ለማስታገስም እንደ አንቲባዮቲክስ ያሉ ማስታገሻዎችን መውሰድም በብዛት የተለመደ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ግን በቤት ውስጥ በቀላሉ ከተፈጥሮ በምናገኛቸው ነገሮች የጥርስ ህመምን ማስታገስ እንደምችልም ይነገራል። ከነዚህም ውስጥ፦ 1.ነጭ ሽንኩርት፦ በውስጡ በያዛቸው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት ለተለያዩ በሽታዎች እንደ ፈውስነት የሚያገለግለው ነጭ ሽንኩርት እንደ አንቲባዮቲክ በመሆን የጥርስ ህመምን ያስታግሳል ተብሏል። በነጭ ሽንኩርት የጥርህ ህመምን ለማስታገስ አንድ ወይም ሁለት ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ማኘክ መልካም ነው የተባለ ሲሆን፥ አልያም የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ከገበታ ጨው ጋር በመደባለቅ የህመም ስሜት የሚሰማን ቦታ ላይ ማስቀመጥ ይመከራል። 2.ቀይ ሽንኩርት፦ በተለምዶ ቀይ ሽንኩርት በመባል የሚጠራው ሽንኩርት የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ከሚረዱን ተፈጥሯዊ ነገሮች ውስጥ ይመደባል። የጥርስ ህመም በሚሰማን ጊዜ ቀይ ሽንኩርት ማኘክ ህመሙን ለማስታገስ የሚረዳ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም ቀይ ሽንኩርት በጥርስ ህመም ምክንያት የሚከሰት የሰውነት መቆጣት እና ኢንፌክሽንን ይከላከላል። 3.የቅርንፉድ ዘይት፦ መጥፎ የሆነ የጥርስ ህመም ካለብዎት የቅርንፉድ ዘይትን መጠቀም መልካም መሆኑም ይመከራል። የጥርስ ህመም በሚከሰትብን ጊዜ የህመሙ ስሜት ያለበት ስፍራ ላይ የቅንፉድ ዘይቱን ማድረግ ይመከራል፤ ዘይቱን በምናደርግበት ጊዜ የመጠዝጠዝ ወይም የህመም ስሜት ቢሰማንም በኋላ ላይ ግን ትልቅ ፈወስን ያስገኝልናልም ተብሏል። 4.ለብ ያለ ውሃና ጨው፦ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ከሚመከሩ ተግባራት ለብ ያለ ውሃ እና ጨው መጠቀም ይገኝበታል። ይህንን ለማድረግም ለብ ያለ ውሃ እና ግማሽ ማንኪያ ጨው የሚያስፈልገን ሲሆን፥ ለብ ያለ ውሃን እና ጨውን በደንብ ማዋሃድ ይጠበቅብናል። ይህንን ውህድም በአፋችን ውስጥ በማድረግ መጉመጥመጥ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ስለሚረዳ በብዛት ይመከራል። 5.በረዶ፦ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ በረዶን መጠቀመም እንደ አማራጭ ከተዘረዘሩት ውስጥ ይገኛል። በረዶውን በፕላስቲክ መያዣ ውስጥ በማድረግ ወይም በንጹህ ጨርቅ በመጠቅለል የሚያመን ጥርስ ላይ ለ15 ደቂቃ ማስቀመጥ ይመከራል። ከዚህ በተጨማሪም በሚያመን የጥርሳችን አቅጣጫ በውጭ በኩል በጉንጫችን ላይ በረዶን በማስቀመጥ ማስታገስ ይቻላል። ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሄዎች የጥርስ ህመም በሚሰማን ጊዜ በአፋጣኝ ለማስታገስ የሚረዱ እንጂ ዘላቂ የሆነ መፍትሄን ስለማይሰጡ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ማግኘት መልካም ነው። እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

✍️ #መካንነትመካንነት አለ የምንለው መቼ ንው?መንስኤዎቹስ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ባልና ሚስት በወር ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት ግንኙነት እያደረጉ ለአንድ አመት ከቆዩና በዚህ ጊዜ ውስጥ እርግዝና ካልተፈጠረ መካንነት ይባላል። ይህ ግን በአመቱ ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳይጠቀሙ መሆን ይኖርበታል። የሴቷ እድሜ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነና በስድስት ወር ውስጥ እርግዝና ካልተፈጠረ የሐኪም እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው። 🔹 #መካንነት የሚለው ቃል ጭራሽኑ ማርገዝ አለመቻል ወይም አንዴ ካረገዙ በኋላ መድገም አለመቻልን (secondary infertility) የሚያመለክት ይሆናል። ብዙውን ጊዜ ባለመውለዳቸው የሚኮነኑት ሴቶች ቢሆኑም ምክንያቱ ግን በወንዱ ፣ በሴቷ፣ ወይም በሁለቱም በኩል ባለ የመካንነት ችግር ሊሆን ይችላል። አልፎ አልፎም አስፈላጊ ምርመራ ተደርጎ የመካንነቱን መንስኤ ማግኘት የማይቻልበት ሁኔታ (unexplained infertility) ይኖራል። ⏩ #ለሴቶች መካንነት #ዋና #ዋና #መንስኤዎች 🔺 እንቁላሎችን ወደ ማህጸን የሚያስተላልፉ ቱቦዎች ወይም ማህጸኑ በጠባሳነት በመጎዳት ምክንያት የቱቦዎች መጎዳት የወንዱ ስፐርም ወደ እንቁላል እንዳይደርስ እክል ይፈጥራል። ጠባሳዎቹ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰጡ መሃንነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። @ #ጠባሳዎቹ #የሚፈጠሩበት #ምክንያቶች 🔺 በአግባቡ ሕክምና ያልተደረገለት የአባለዘር በሽታ በማህጸን ቱቦዎች ጠባሳን ሲያስከትል ይችላል 🔺 በውርጃ ወይም በወሊድ ጊዜ የሚከሰቱ የኢንፌክሽን በሽታዎች በማህጸኑ/ በማህጸን ቱቦዎች ላይ ጠባሳ ስያስከትሉ፣ ⏩ #እንቁላል #የማዘጋጀት #ችግር 🔺 ለዚህ ምክንያቱ የሚፈለጉት ሆርመኖች በበቂ ሁኔታ ስለማይኖሩ ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ከ21 ቀናት ወዲህ ወይም ከ35 ቀናት ወዲያ የሚመጣ ከሆነ ይህ ችግር ሊኖር ይችላል ። አልፎ አልፎም በጣም መወፈር ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ኪሎ መቀነስ የእንቁላል ማዘጋጀት ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ⏩ #የማህጸን እጢ ⏩ #እንደ ስኳር በሽታ ፣ ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችም መካንነት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ⏩ #ለወንዶች #መካንነት #መንስኤዎች 🔺 ሰውነታቸው የሚያመርተው ስፐርም ቁጥር በቂ አለመሆን፣ ወይም የተሰሩት ስፐርሞች ቀልጣፋነት ማነስ። 🔺 በተለያዩ ምክንያቶች (ኢንፈክሽ ፣ ጨረር፣ወዘተ) ስፐርም የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ። በዚህም ምክኒያት ምንም እንኳን በወሲብ ጊዜ ማፍሰስ ቢችሉም ፣ የወንድ ፈሳሽ ውስጥ ስፐርም አይኖርም፡ በመሆኑም ማስረገዝ አይችሉም ። 🔺 ስፐርም ከብልታቸው መፍሰስ ሳይችል ሲቀር ( የዚህ ምክኒያት በአባላዘር በሽታዎች የፈሳሹን መተላለፊያ ቱቦዎች በመጎዳት ሊሆን ይችላል።) 🔺 ቫሪኮሴሌ 🔺 ስንፈተ ወሲብ 🔺 የተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች እና የመሳሰሉት ⏩ #ምርመራዎቹ 🔺 የሚሰሩት ምርመራዎች ለወንዱና ለሴቷ የተለያየ ቢሆንም ለሴቶች ፣ የሆርሞን ምርመራ፣ አልትራ ሳውንድ፣ የእንቁላል ምርመራ፣ የማህጸን ኤክስ ሬይ እንዲሁም ጀነቲክ ቴስት …. 🔺 ለወንዶች ደግሞ የስፐርም ምርመራ፣የቴስቴስትሮን ምርመራ( የሆርሞን ምርመራ)፣የዘር ፍሬ አካባቢ አልትራሳውንድ፣ እና ሌሎች… ⏩ #ህክምናው 🔺 ኢንፌክሽን ካለ እሱን ማከም 🔺 ከግንኙነት ጋር ያሉ ችግሮችን ማከም 🔺 የሆርሞን ህክምና 🔺 ቀዶ ህክምና 🔺 አጋዥ ቴክኖሎጂ መጠቀም (Assisted reproductive technology) 👉👉 #በወሊድ ችግር ከተጨናነቁ ባለሙያ በማግኘት ይመካሩ (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

«ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት» የፊት ቆዳችንን በአግባቡ ካልተንከባከብነው በቀላሉ የሚጎዳ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን የፊት ቆዳን መንከባከቢያ መንገዶች ይመልከቱ። - ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ - የፊት ሳሙና ወይም ሌላ ቅባት ሲቀቡ የፊትዎን ቆዳ ከመፈተግ ይቆጠቡ ይልቁንም በለስላሳና ክባዊ እንቅስቃሴ ቀስ ብለው ይቀቡት - ለፊት ቆዳዎት የሚስማማ ማርጠቢያ ክሬሞችን ይጠቀሙ ከመተኛትዎትም በፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ - የፊት ቆዳ ቀዳዳን ከሚደፍኑ ዘይታማ ከሆኑ ሜክአፖችና የቆዳ ክሬሞች ይራቁ - የቆዳችን ንፅህና መጠበቅ በተለይ ብጉር የሚያስቸግረን ከሆነ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ፣ ፊዞርሲኖል፣ ሳሊክሊክ አሲድ ወይም ሰልፈር ያለው ለፊትዎ የሚስማማ ሳሙና መጠቀም ብጉሩ በዚህ ካልቀነሰ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መድሃኒት በተለያየ ምክንያት የፊትና ሌላ የቆዳ አካል ላይ የቀረን ምልክትን ለማጥፋት ከፈለጉ የሚከተለውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ህክምናን ሊጠቀሙ ይችላሉ። መድሃኒቱን በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት፦ • አራት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጁስ • አራት የሻይ ማንኪያ ማር • አንድ አስኳሉ የወጣለት እንቁላል አዘገጃጀት • ፊትዎ/ቆዳዎ ንፁህና ደረቅ መሆን ስላለበት ይታጠቡት • በመቀጠልም ከላይ የተዘረዘሩትን በንፁህ እቃ ውስጥ በደንብ ያደባልቁ • ከዚያም ምልክት ባለበት የቆዳዎ ክፍል ላይ ይቀቡት • ከ15 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ይታጠቡት ጥሩ ውጤት ለማግኘት በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲጠቀሙት ይመከራል።

"ስለ ቶንሲል የምናውቀው አና የምንሳሳተው ምንድን ነው?" - ዶ/ር ንጉሴ ጫኔ ፤ የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም - ቶንሲል ምንድን ነው? ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም። ቶንሲል ማለት ትንንሽ አበጥ ያሉ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ አካላት ስብስብ ነው። ይህም በክብ ቀለበት ከምላስ ጀርባ የላንቃን የጎን ግድግዳ እና የላንቃን ክዳንና የአፍንጫን የውስጠኛ ክፍሎች ያስተሳስራል። - ቶንሲል ጥቅሙ ምንድን ነው? በአፍም በአፍንጫም የሚገቡ ተዋህስያንን መዋጋት ነው። የሰውነትን በር ከጠላት መከላከያ ነው። - ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው? ሁለቱም በላንቃ አካባቢ ይገኛሉ። ግንኙነታቸው ግን ጉርብትና እንጅ በአገልግሎት አይገናኙም። - Uvula/እንጥል እንጥል ማለት ከላንቃ ላይ የተንጠለጠለ ማለት ነው። ከቶንሲል ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። - የቶንሲል ህመም/tonsialiophayngitis? ይህ የቶንሲል እና የላንቃ አካባቢ በተዋህስያን መወረር ነው። - የህመም ምልክቶች ትኩሳት ፣ ለመዋጥ መቸገር ፡ ራስ ምታት ፣ የአፍ መሽተት ፣ የአንገት ንፍፊት እብጠት ፣ ማንኮራፋት ፣ ሳል የቶንሲል ህመም መተላለፊያ መንገዶች 1. በትንፋሽ ጠብታ 2. በንክኪ - የባክቴሪያ ቶንሲል በብዛት የሚያጠቃው ማንን ነው? የባክቴሪያ ቶንሲል ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናትን የሚያጠቃ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ5-15 እድሜ ያሉት ይጠቃሉ። የቫይረስ ሲሆን ለጋ ህጻናትም ይጠቃሉ። የቶንሲል ህመም ተያያዥ ችግሮች 1 ፡ መግል መቋጠር tonsiar, peritosilar or retropharyngeal abscess 2. የሳንባ ምች / የማጅራት ገትር 3. የልብ ህመም rheumatic heart disease ይህን ለመከላከል ቶንሲል እንዳመመን ወደ ጤና ተቋም መሄድ። 4. የኩላሊት ህመም PS glomerulonephritis 5. የቶንሲል መፋፋት adenotonsilar hyperthrophy - የቶንሲል ህመም ህክምና መጀመሪያ የባክቴሪያ ወይስ የቫይረስ ነው የሚለውን መለየት ያስፈልጋል። መለያ መንገዶች 1. የቫይረስ ከሆነ የጉንፋን ምልክት አብሮ ይኖራል ግን አንዳንድ ጊዜ እንደ ቫይረስ ጀምሮ ወደ ባክቴሪያ ሊቀየር ስለሚችል ጥንቃቄ ይፈልጋል። 2. መግል የያዘ ከሆነ የባክቴሪያ ምልክት ነው ግን ይህን በደንብ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል። 3. ድድ፣ ከንፈር ወይም ምላስ የቆሰሉ ከሆነ የቫይረስ ምልክት ነው። 4. የነጭ የደም ሴል እና ተያያዥ ምርመራ መድሃኒት 1. የህመም ማስታገሻ 2. እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ የተለያዩ ጸረ ባክቴሪያ አለበለዚያም ፀረ ቫይረስ መድሃኒት 3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ ረፍት ማድረግ። 4. ማር እና የውሃ ኢንፋሎት መታጠን 5. የብርቱካን ወይም ሎሚ ጭማቂ። @DrSofonias