ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye)

⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye)

前往频道在 Telegram

📈 Telegram 频道 ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) 的分析概览

频道 ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (@ethiolawtips) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 533 名订阅者,在 法律 类别中位列第 615,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 622 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 533 名订阅者。

根据 01 十一月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 107,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.95%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.28% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 511 次浏览,首日通常累积 1 255 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️ Youtube👇 https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1 Facebook 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL”

凭借高频更新(最新数据采集于 02 十一月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 法律 类别中的关键影响点。

13 533
订阅者
无数据24 小时
+157 天
+10730 天
帖子存档
የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ /ረቂቅ/ አጭር ማብራሪያ ​ይህ ሰነድ ስለ አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ዋና ዋና ነጥቦችን የያዘ አጭር ማብራሪያ ነው። ሙሉ ሰነዱን ከተያያዘው የPDF ፋይል ማግኘት እና ማውረድ ትችላላችሁ።

✍️ ስልጣን በሌለው አካል የተሰጠ ውሳኔ በይግባኝ ባይሻርም እንኳ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንደ ቀድሞ የተሰጠ ውሳኔ(res judicata) ተቆጥሮ አዲስ የቀረበን ክስ ሊያግድ አይችልም በማለት የፌዴራል
+6
✍️ ስልጣን በሌለው አካል የተሰጠ ውሳኔ በይግባኝ ባይሻርም እንኳ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንደ ቀድሞ የተሰጠ ውሳኔ(res judicata) ተቆጥሮ አዲስ የቀረበን ክስ ሊያግድ አይችልም በማለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰመቁ 256261 የሰጠዉ አስገዳጅ የየሕግ ትርጉም። ✍️✍️የሰበር ችሎቱ ትንታኔና ውሳኔ 1. የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የስልጣን ወሰን ✅ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች አነስተኛ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋሙ በመሆናቸው፣ የገጠር መሬት ክርክርን የመዳኘት ስረ-ነገር ስልጣን የላቸውም። ✅ማህበራዊ ፍርድ ቤት የኢፌድሪ ህገ-መንግስትን (በተለይም አንቀጽ 40ን) በመጣስ ያለስልጣኑ የሰጠው ውሳኔ ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም። 2. የስረ-ነገር ስልጣን እና የሰበር ውሳኔ (መ/ቁ 105677) አተረጓጎም ✅ተጠሪው "አንድ የዳኝነት አካል ስልጣን ባይኖረውም የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ እስካልተሻረ የጸና ነው" የሚለውን የሰበር መዝገብ ቁጥር 105677 ትርጓሜ እንደ መከራከሪያ አቅርበው ነበር። ✅ሆኖም የሰበር ችሎቱ ይህ ትርጓሜ የሚያገለግለው ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች (ወረዳ፣ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት) ብቻ መሆኑን ገልጿል። ✅መደበኛ ስነስርዓት የማይከተል እና አነስተኛ ጉዳዮችን ለማየት የተቋቋመ አካል (ማህበራዊ ፍርድ ቤት) ህገ-መንግስትን ጥሶ የሰጠው ውሳኔ "በይግባኝ አልተሻረም" በሚል ሊጸና አይገባም በማለት ችሎቱ ተንትኗል። 4. የፍርድ ቤት ግዴታ ✅የስልጣን ክርክር በባለጉዳዮች ባይነሳም እንኳ፣ ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት ስልጣን ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት። 👉🏿በመሆኑም ወረዳ ፍርድ ቤት "መሬቱ ለአመልካች ይገባል" በማለት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።

🧬 የ DNA ውጤት 0% ቢሆንም "አባት ነህ፤ ቀለብ ትከፍላለህ!" የሚለው የኢትዮጵያ ሕግ:: አንድ ባልና ሚስት በትዳር ውስጥ እያሉ ልጅ ይወለዳል። ባልየው ልጁን የራሱ አድርጎ፣ ስሙን ሰጥቶ፣ እያሳደገ 7 ዓመታት ያልፋሉ። በኋላ ግን በትዳራቸው ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር፣ ባልየው በልጁ ላይ ጥርጣሬ ገብቶት በሚስቱ ድብቅ የዘረመል (DNA) ምርመራ ያደርጋል። ውጤቱም ያልጠበቀው ሆነ! "0% Match" - ማለትም ልጁ የእሱ አይደለም! 👉ባልየው ይሄንን ተጨባጭ የሳይንስ ማስረጃ ይዞ ወደ ፍርድ ቤት ይሮጣል። "ክቡር ፍርድ ቤት፣ በሳይንስ ልጁ የእኔ ስላልሆነ አባትነቴ ይሰረዝልኝ፤ ቀለብም እንዳልከፍል አድርጉኝ"በማለት ክስ ያቀርባል። ሚስትም ልጁ ከሌላ ሰው መሆኑን አታስተባብልም። ነገር ግን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች (በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን ጨምሮ) የባልን ጥያቄ ውድቅ ያደርጉታል! "DNA-ው ያንተ ባይሆንም፣ በሕግ ግን አሁንም አባት ነህ፤ ቀለብም ትከፍላለህ"የሚል አስገራሚ ውሳኔ ይሰጣሉ። ፍርድ ቤቱ ይህንን የሚወስነው ዝም ብሎ ሳይሆን፣ የተሻሻለውን የኢትዮጵያ ቤተሰብ ሕግ መሠረት በማድረግ ነው፦ 1. የጊዜ ገደብ (Limitation Period)፦ በቤተሰብ ሕጋችን አንቀጽ 168 መሠረት፣ አንድ አባት "የልጅነት ክህደት ጥያቄ" (Disavowal of Paternity) ማንሳት የሚችለው፣ ልጁ መወለዱን ወይም እውነታውን ባወቀ በ180 ቀናት (በ6 ወር) ውስጥ ብቻ ነው። ከዚህ ጊዜ ካለፈ መብቱ በይርጋ ይታገዳል። 7 ዓመት ጠብቆ መምጣት በሕግ አይቻልም። 2. የልጁ የላቀ ጥቅም (Best Interest of the Child)፦ ልጁ ለዓመታት የአንተን ስም ይዞ፣ አንተን "አባዬ" እያለ፣ ሥነ-ልቦናው ከአንተ ጋር ተቆራኝቶ አድጓል (በሕግ ቋንቋ "የልጅነት ሁኔታን ይዞ ተገኝቷል / Possession of Status")። ሕጉ በዚህ ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው የባልን ስሜት ለመጠበቅ ሳይሆን የልጁን ሕይወት ላለማመሰቃቀል ነው። ሕጉ ባልን "ስትፈልግ አባት፣ ስትፈልግ ባዳ መሆን አትችልም" ይለዋል። ስለዚህ በሳይንስ አባት ባትሆንም፣ በሕግ ዘላለማዊ አባት ሆነሃል! ይህ የቤተሰብ ሕጋችን ድንጋጌ ፍትሐዊ ነው ትላላችሁ? የሳይንስ እርግጠኝነት (DNA Test) የሕግን የይርጋ ጊዜ ገደብ መሻር የለበትም? ባልየው ያላወጣውን ልጅ ቀለብ እየከፈለ እንዲያሳድግ ማስገደድ፣ የሚስትን ስህተት ማበረታታት እና የባልን መብት መጣስ አይሆንም? ወይስ ሁሌም ቢሆን የልጁ ጥቅም ይበልጣል? Ethiopian Law

#በክርክር_ወቅት_በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 41 መሠረት ጣልቃ እንዲገባ የተፈቀደለት ተከራካሪ በመጀመሪያ ሊያቀርብ የሚፈልገውን መቃወሚያ እንዳያቀርብ የሚከለክለው ህግ የሌለ በመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ በማለት #የፌደራል_ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 108647 በሆነው በቅጽ 20 ላይ የተሰጠ የህግ ትርጉም። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 41:234/1/

Job Vacancy. Principal Attorney Position, with benefits packages. At Nib International Bank Share Company.
Job Vacancy. Principal Attorney Position, with benefits packages. At Nib International Bank Share Company.

ቅዳሜ ጥቅምት 7 በቫምዳስ ሲኒማ(ለም ሆቴል አካባቢ) ከጠዋቱ 2:30-6:30 አይቀርም። "ፍትህ ለሀገሬ "
ቅዳሜ ጥቅምት 7 በቫምዳስ ሲኒማ(ለም ሆቴል አካባቢ) ከጠዋቱ 2:30-6:30 አይቀርም። "ፍትህ ለሀገሬ "

የፌደራል_ተጨማሪ_እሴት_ታክስ_ደንብን_ለማሻሻል_የወጣ_ደንብ_ረቂቅ.pdf

“ፍትሕ ለሃገሬ” ላለፉት አምስት ዓመታት ገደማ አቅሜ በፈቀደና በገባኝ ልክ ከብዙ ውጣ ውረድና ጫናዎችጋ እየሰራሁ እዚህ ደርሷል። በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም. ጠዋት 2:30 ተኩል
“ፍትሕ ለሃገሬ” ላለፉት አምስት ዓመታት ገደማ አቅሜ በፈቀደና በገባኝ ልክ ከብዙ ውጣ ውረድና ጫናዎችጋ እየሰራሁ እዚህ ደርሷል። በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም. ጠዋት 2:30 ተኩል ላይ ደግሞ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ቫምዳስ ሲኒማ ፕሮግራሙን ለማስቀጠልና ለማሻሻል በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ከእናንተ ጋር ለመወያየት ፕሮግራም ይዘናል። ፍትሕ ለሃገሬን በሀሳብ፣ እንግዳ ሆኖ በመቅረብ፣ ይጠቅማታል ድካሟን ያቀልላታል ብላችሁ ባሰባችሁት ያገዛችሁኝ እና ፕሮግራሙ ጥቅም አለው ብላችሁ የምታምኑ የሕግ ባለሙያ ባልደረቦቼ ሁሉ በእለቱ ተገኝታችሁ የማሻሽለውን፣ “ቢሆን ጥሩ ነው”፣ “ይሄ ቢቀር ይሄ ቢጨመር” የምትሉትን እንድታካፍሉኝ በአክብሮት ጋብዣችኋለሁ። #ፍትሕለሃገሬ @highlight በጠበቃ ወ/ሮ ሊያ ተረፈ

Criminal procedure and evidence law New published 2019.pdf

መልካም ዜና ለአንባቢዎቻችን እና ለሕግ ባለሙያዎች በሙሉ! 📖✨ አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ መድብል ለሕትመት በቃ! የፍትሕ ሥርዓታችንን ለማጠናከር እና አገልግሎቱን ይበልጥ ለማቀ
መልካም ዜና ለአንባቢዎቻችን እና ለሕግ ባለሙያዎች በሙሉ! 📖✨ አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ መድብል ለሕትመት በቃ! የፍትሕ ሥርዓታችንን ለማጠናከር እና አገልግሎቱን ይበልጥ ለማቀላጠፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ መድብል በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታትሞ ለገበያ መቅረቡን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን። መድብሉን ማግኘት የምትፈልጉ ማንኛውም ፍላጎት ያላችሁ አካላት ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሽያጭ ሱቆች በአካል በመገኘት ገዝታችሁ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። በተጨማሪም የፍትህ ሚኒስቴር የሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ አመራር እንደገለጹት፤ ህብረተሰቡና የሕግ ባለሙያዎች ከመድብሉ የሶፍት ኮፒ (Soft Copy) አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በፍትሕ ሚኒስቴር ይፋዊ ገጽ ላይ የተጋራውን ትክክለኛና ይፋዊ ቅጂ ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል። የአገራችንን ፍትሕ ሥርዓት ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋት የተጀመረው ጥረት አካል የሆነው የመድብሉ የእንግሊዝኛ ቅጂም በቅርብ ቀን ታትሞ ለንባብ እንደሚበቃ በዚሁ አጋጣሚ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። 📎 የአማርኛ ቅጂውን ሶፍት ኮፒ (PDF File) ከዚህ ማስታወቂያ ጋር አያይዘን ያቀረብንላችሁ ስለሆነ ከታች በማውረድ (Download በማድረግ) እንድትጠቀሙ በአክብሮት እንጋብዛለን! https://drive.google.com/file/d/195NTCZrkV1AjUklHGCgEuO7CQmd92ku2/view?usp=sharing

ለፖሊስ የተሰጠ የእምነትቃል =====/////===== በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/መሠረት አንድ ተከሳሽ ለፖሊስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆኑ የ
+3
ለፖሊስ የተሰጠ የእምነትቃል =====/////===== በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/መሠረት አንድ ተከሳሽ ለፖሊስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆኑ የቀረበውን ክስ ለማስረዳት የሚችል ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆን አለመሆኑ በፍ/ቤት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚገባው እንጂ ከወዲሁ ተቀባይነት አለው ተብሎ ድምዳሜ የሚወሰድበት ስላለመሆኑ፤ በሰ/መ/ቁ 152038 (ሕዳር 28ቀን 2011ዓ.ም)ቅጽ 23

የማስረጃ ምዘና መርኅን ስለመጣስ:- ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ (የሰው ምስክርም ሆነ የሰነድ) መርምረውና መዝነው ፍሬ ነገርን የማጣራት ኃላፊነት አለባቸው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495
+2
የማስረጃ ምዘና መርኅን ስለመጣስ:- ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ (የሰው ምስክርም ሆነ የሰነድ) መርምረውና መዝነው ፍሬ ነገርን የማጣራት ኃላፊነት አለባቸው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495) በተለይም፣ የቀረበን የሠነድ ማስረጃ ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ወይም ሳይመረምሩ በሰው ምስክሮች ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ የሚሰጥ ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መርኅን የሚጥስና መሠረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495 -30/5/2013 ዓ.ም ውሳኔ ተሰጥቷል።

New Criminal Procedure Code 2018 Final.pdf13.01 MB

Repost from Jura Legal Update
New Criminal Procedure Code 2018 Final.pdf13.01 MB

በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ በተሰጣቸዉ የፌ
በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ  በተሰጣቸዉ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዉክልና ስልጣናቸዉ በቀጥታ ያዩዋቸዉን የፈዴራል ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ስልጣን ያላቸዉ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑ በክልሉ እንዲደራጁ  የተደረጉት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ናቸው ተብሎ ተወስኗል፡፡👇 https://t.me/ethiolawtips

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1196(1) መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ሰው የንብረቱ ባለቤት ለመሆኑ የሕግ ግምት የሚወሰድ በመሆኑ፣ ይህ ግምት ሊፈርስ የሚችለው ካርታው ከሕግ ውጪ መሰጠቱ ወይም ሰነዱን የመስጠት ሥልጣን በሌለው አካል የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ በሰው ምስክርነት ወይም ገንዘብ አውጥቻለሁ በሚል ክርክር ብቻ ሊፈርስ አይችልም። ​በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (1 እና 2) መሠረትም የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጠበቀው በሕጋዊ መንገድ በተያዘ ይዞታ ላይ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት በወላጅ ስም በተመዘገበ ይዞታ ላይ ገንዘብና ጉልበት በማፍሰስ ቤት ቢገነቡ እንኳ፣ ይዞታውም ሆነ በይዞታው ላይ የተገነባው ቤት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ሊሆን አይችልም። ​በቤቱ ግንባታ ላይ በትዳር ዘመን በባልና ሚስት የተደረገ የገንዘብ ወጪ ወይም አስተዋጽኦ ካለ፣ ግምቱን ከመጠየቅ ውጪ በሌላ ሰው ስም ባለው ይዞታ ላይ ያረፈውን ቤት የጋራ ንብረታችን ነው ብለው የክፍፍል ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም። ​ስለሆነም፣ በጋብቻ ውስጥ በወላጆች ስም ባለው መሬት ላይ የሚገነባ ቤት የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ሳይሆን የባለይዞታው ንብረት እንደሆነ የሚቆጠር ሲሆን፣ በፍቺ ጊዜ የትዳር አጋሮች መብት የሚጠበቀው ያወጡትን ገንዘብ በድርሻቸው ተመላሽ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ እንጂ የንብረቱን/የቤቱን ክፍፍል በመጠየቅ አይደለም። ​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ አቶ ብርሃኑ ከበደ እና ም/ኢ/ር ጥሩነሽ ዱባለ፣ መዝገብ ቁጥር 132 (ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም)