ch
Feedback
Gelila kindergarton and Primary school

Gelila kindergarton and Primary school

前往频道在 Telegram
318
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
የተሻለ ውጤት የሚያመጡ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል❓ 📢 12 ወሳኝ ነጥቦች 📖1 ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ። ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ። 📖 2 መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ...የተሳሳተው ን እያስተካከሉ ይጓዛሉ። 📖3 ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ። 📖4 አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ.... 📖 5 ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም። 📖6 ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ:: 📖7 በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡ 📖8 ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡ 📖9 ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡ 📖10 ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡ 📖11 ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡ 📖12 እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡

+3
የ6ኛ ክፍል  ሞደል ጥያቄ       📘   አዘጋጅ ለሚ ኩራ ፅ/ቤት       📘 2ኛ መንፈቅ አመት 2016     📘 የትምህርት አይነት                   👉 አካባቢ ሳይንስ              👉 አማርኛ             👉 ሒሳብ             👉 እንግሊዝኛ                                         

+5
የ8ኛ ክፍል  መለማመጃ ጥያቄ       📘   አዘጋጅ ኤቨረስት ዩዝ አካዳሚ       📘 2ኛ መንፈቅ አመት 2016     📘 የትምህርት አይነት                   👉 አጠቃላይ ሳይንስ              👉 አማርኛ             👉 ሒሳብ             👉 እንግሊዝኛ              👉  ሲቲዚንሽፕ                    ሶሻል                            

በ2016 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ በወረዳ 3 ት/ጽ/ቤት በተደረገው ትምህርታዊ አውደ ዕርዪ የገሊላ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከወረዳው ካሉ ትምህርትቤቶች አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኑ
+9
በ2016 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ በወረዳ 3 ት/ጽ/ቤት በተደረገው ትምህርታዊ አውደ ዕርዪ የገሊላ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከወረዳው ካሉ ትምህርትቤቶች አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኑዋል!!!   #ለመላው የገሊላ ማህበረሰብ እንኳአን ደስ አላችሁ!!!

👉ለ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ተማሪዎች አጭር ማስታወሻ! ✅የ8ኛ ክፍል 👉ሞዴል ሚያዚያ 15-18/8/2016 ዓ.ም ሲሰጥ ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም ሲሰጥ ✅6ኛ
👉ለ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች  ተማሪዎች አጭር ማስታወሻ! ✅የ8ኛ ክፍል 👉ሞዴል ሚያዚያ 15-18/8/2016 ዓ.ም  ሲሰጥ  ክልል አቀፍ ፈተና  ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም ሲሰጥ ✅6ኛ ክፍል 👉ሞዴል ፈተና ከሚያዚያ 15-18/8/2016 ዓ.ም  የሚሰጥ ሲሆን ክልል አቀፍ   ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል!! ✅ከተማሪዎች ምን ይጠበቃል?? 👉የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ብቻ (5ኛ ክፍል ሳይጨምር) የሁለቱን ሴሚስተር እቅድ አውጥቶ  በአግባቡ ማጥናት 👉የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ብቻ (7ኛ ክፍል ሳይጨምር) የሁለቱን ሴሚስተር እቅድ አውጥቶ በአግባቡ ማጥናት ✅ከመምህራንና ከት/ቤቶች ምን ይጠበቃል? 👉መምህራና እና ት/ቤቶች አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት የይዘት የማጠናቀቅ ምጣኔ(portion coverage ) በአግባቡ እንዲጠናቀቅ ማድረግ :: 👉ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን የስነ ልብና ምክርና አስፈላጊው እገዛ (ወርክሽት ፣ሞዴል ፈተናዎች እና ያለፋ አመታት ፈተናዎችን በማሰራት)  እገዛ ማድረግ :: ✅ከተማሪ ወላጆች ምን ይጠበቃል?? 👉ተማሪዎች እቅድ አውጥተው እንዲያጠኑ ማበረታታት እና አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ:: 🤲በጋራ ርብርብ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ ምግባር እናሻሽል🤲!

🌙🌙 ዒድ ሙባረክ 🌙🌙 عيد مبارك كل عام وانتم بخير 💫✨💫💫✨💫💫✨ تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አዕማል ✨✨✨✨✨✨
🌙🌙 ዒድ ሙባረክ 🌙🌙 عيد مبارك كل عام وانتم بخير 💫✨💫💫✨💫💫✨ تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال          ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም               ሷሊሀል አዕማል ✨✨✨✨✨✨✨✨ ⭐️ Eid Mubarek⭐️

#በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው። #በዛሬው እለት በተካሄደው 5B ከ 6A ባደረጉት ጠንካራ ፉክክር ጨዋታ 6A 5 ለ 4 በሆነ ውጤት አሸን
+2
#በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው። #በዛሬው እለት በተካሄደው 5B ከ 6A ባደረጉት ጠንካራ ፉክክር ጨዋታ 6A 5 ለ 4 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል!!!!

23/07/18 በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው!! #በዛሬው እለት 8A ከ7B ባደረጉት ጨዋታ 8A ከጨዋታ ብልጫ ጋር 10ለ2 አሸንፏል !
+6
23/07/18 በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው!! #በዛሬው እለት 8A ከ7B ባደረጉት ጨዋታ 8A ከጨዋታ ብልጫ ጋር 10ለ2 አሸንፏል !!!! #የጨዋታው ዳኛ መ/ር ተመስገን አስማማው!!!!

+5
❗️❗️❗️Addis Ketema Sub-city 2015 E.C Second Semester Model Exam❗️❗️❗️

20/07/18 የሁለተኛው መንፈቅ አመት የ8ኛ ክፍል የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል !!! #ኤዶምያስ መኮንን ከ8A 1ኛ #ኤርሚያስ አዲሱ ከ8A 2ኛ #ኤደን ኩሽ ከ8B 3ኛ
+6
20/07/18 የሁለተኛው መንፈቅ አመት የ8ኛ ክፍል የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል !!! #ኤዶምያስ መኮንን ከ8A 1ኛ #ኤርሚያስ አዲሱ ከ8A 2ኛ #ኤደን ኩሽ ከ8B 3ኛ

የኢፌዴሪ ዴይ ኬር መመሪያ.pdf2.97 KB

#በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው #በዛሬው እለት 8B ከ 7A ባደረጉት ጠንካራ ፉክክር 8B 11 ለ 7 አሸንፏል #የጨዋታው ዳኛ መ/ር ተመስ
+9
#በስፖርት ክበብ አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው #በዛሬው እለት 8B ከ 7A ባደረጉት ጠንካራ ፉክክር 8B 11 ለ 7 አሸንፏል #የጨዋታው ዳኛ መ/ር ተመስገን አስማማው #ጨዋታው ነገም ቀጥሎ ይካሄዳል #ተተኪ ስፖርተኞችን ለማግኘት የት/ቤት የውስጥ ውድድሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው!!!! #ስፖርት ለወዳጅነት!!! #ስፖርት ለጤንነት!!!

የእርዳታ ተማፅኖ #ከ2008-2013 በገሊላ የመጀመሪያ ት/ቤት የሥራ ባልደረባችን የነበረው#ቴዎድሮስ ሸዋፀጋ ወላጅ እናት ሁለቱም ኩላሌታቸው ከጥቅም ውጪ ስለሆነ በሳምንት ሦስቴ ዲያሊሲስ እያደረጉ ነው#ለሁለት አመት ያክል ለብቻው ዲያሊሲስ እንዲያደርጉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ብቸኛ ልጃቸው የሆነው #ቴዳ ሁሉንም ወጪ እራሱ እየሸፈነ እያሳከማቸው ነው#አሁን ላይ ይህን ለማድረግ አቅም ስላጣ #ከዚህ በፊት በት/ቤታችን ሶሻል ኮሜቴ አስተባባሪነት #የት/ቤታችን መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞችን በማስተባበር ድጋፍ አድርገንለት ነበር# አሁን ላይ ግን ቪድዮ ላይ እንደምናየው #ብቻውን ያን ማድረግ ስላቃተው #የጓደኛችን የሥራ ባልደረባችንን የሆነውን #የቴዳን እናት ከጉኑ በመሆን የቻልነው የአቅማችንን #በፀሎትም በዱአ #ወንድማችንን እናግዛው!!! #የገሊላ ቤተሰብ ደሞ በበጎ ተግባር የማይታማ ስለሆነ #የቀድሞ የት/ቤታችንን መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች የቻላችሁትን ድጋፍ እናድርግለት# #ቴዳ እስካሁን እያሳለፍክ ያለሆን ነገር እኛ በደንብ ስለምንረዳ #አሁንም ከፈጣሪ ጋር የቻልነውን ነገር እናደርጋለን!!!! #ቴዳ አይዞን !!!!ፈጣሪ አቅሙንና ብርታቱን ይስጥክ እስከቻልነው ድረስ ከጉንክ ነን!!!!!

✅የፈተና መረጃ ለ6ኛ፣8ኛ  ተፈታኝ ተማሪዎች 1️⃣ የ6ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ) በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:- 👉አማርኛ 👉እንግሊዘኛ 👉ሒሳብ 👉አካ/ሳይንስ  እና 👉ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል ✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም) ✅ 8ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ) በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:- 👉አማርኛ 👉እንግሊዘኛ 👉ሒሳብ 👉ሶሻል ሳይንስ 👉አጠ/ሳይንስ 👉የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል ✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም) 👉በመሆኑም የፈተና ወቅት እየተቃረበ በመሆኑ ተማሪዎች በዚህ መረጃ መሰረት በአግባቡ ማጥናት ይጠበቅባቹሀል:: 👉  ት/ቤቶች  እና የተማሪ ወላጆች በዚህ መረጃ መሰረት ተማሪዎቻችን አመርቂ ውጤት እንዲያመጡ የጋራ ርብርብ እናድርግ‼️ 👉ሁሉም ፈተናዎች በሰኔ ወር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል

ማስ ስፖርት 5 ከት/ቤቱ ርዕሳነ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር

ማስ ስፖርት 3 ከት/ቤቱ ርዕሳነ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር

ማስ ስፖርት 2 ከት/ቤቱ ርዕሳነ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር