WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን
前往频道在 Telegram
WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን @WanosMesfin @WanosMesfinChat +251919484604 - @WanosM
显示更多869
订阅者
无数据24 小时
-27 天
-230 天
帖子存档
ትርጉም አልባ ግጥም
ሰሞኑን ግጥም - ግጥም ብሎኛል የበረከት በላይነህ 'የመንፈስ ከፍታ' ይሁናል የነሸጠኝ።
ስሙኝማ? ግጥም አልችልም፤ በቃ ምንም አላውቅም፣ እና ይህንን ከዚህ በታች ያለ ትርጉም አልባ ዝባዝንኬ ግጥም እንደ አጉል ግጥመኛ ( 😂 ይቅርታ ለካ ገጣሚ ነው ) ፣ ግጥም ላይ እንደሚራቀቅ ሰው ተሞዳምጃለሁ።
የሚገርመው አጉል የተመሠጥኩ ያህል የሚሰማኝ ነገር ነው። 😁 Even ቃላቱን 'ራሱ አላውቃቸውም።
ሀገር ፡ እንደ ፡ ልምቅ፣
ክስቴ ፡ ተቀርድዶ ፡ ሊደቅ፣
ፍቅረ-ንዋይ ፥ ሲንደቀደቅ፣
ባሕረ ፥ ስላቅ፣
አዋዘ ፥ ሰንደቅ።
መግፍዔ ፡ ክስቴ፦
ሐሩር ፡ ላይ ፡ ጎኅ ፡ ሲቀድ፣
ወለል ፡ ላይ ፡ ተነጥፎ ፡ ሲወድቅ።
እንዲኽ ሞሸረ፦
❝ በአንድ ፡ ቀና ፡ ቀን ፡ ቅኔ ፡ ተቀኝቼ፣
ቀና ፡ ስል ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ ቅን ፡ ሰው ፡ ተመልክቼ ❞
ክስው፥ድልው
ለሀገር ፡ እንድደምቅ፣
ፃዕር ፡ ላይ ፡ እንዳልወድቅ።
ኑባሬ ፡ ብርሃን፤ እንደ ፡ መብረቅ፣
ነፋሰ-ፅልመት ፡ ሲገረድድ ፥ ሲለቅ።
፨፨፨
ክሴተ-ልዑል ፡ መግፍዔ ፡ ሲራይ፣
አዋዝ-ግስው ፡ ክስት ፡ ለድይ።
መፍክሬ ፥ ክስቴ፦
ፅቡቅ ፡ ፅቡቅ ፡ አለ ፡ ሲዠምር!
ብቅ፥ብቅ ፡ ድሳዌ ፡ ወእንበለ ፡ ሕብር፣
ሥርወ፣ ግስወ ፡ ሀቤየ ፡ ኩሉ ፡ ክብር፣
ሠርቀ፣ አንቀ ፡ ወበ-ዲለ ፡ ድንበር።
ቀጠለናም፦ ግርምከ ፥ ግሩምከ!
ፀላዖ ፡ ፅላሎት!
ድርምባ ፡ ድርባቦት! ( ባ'ናቱ ፡ ከናንቦ! )
ቅርፋዔ ፡ ቲና ፡ ዘለከ፣
በንተለ ፡ ቅስትና ፡ አመንከ
ምጣኒ፣ ጽባኒ..
ንቡዔ ፡ ልቡከ ፡ ከመ ፡ ምስትርድምና |ቀባመ።
ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin
እነሆ የኔ እይታ!
ስለ የአእምሮ ሕዋሳት ሁነቶች(ኒውሮሎጂካል ኮንዲሽንስ) ብያኔእንደኔ እንደኔ 1. የብያኔ መስፈርቶች ሳይንሳዊነት:- የስነ አእምሮ ሁነቶች ምርመራዊ አቀራረብ ከሌላው አካላዊ ጤንነት ምርመራ የተለየ አቀራረብ አለው።ምልክቶች በባህሪ ስለሚገለፁ የአንድ ሁነት መኖር አለመኖር የሚረጋገጠው የታዩ ኢመደበኛ ባህርያት በሁሉም ቦታ ለረዥም ሰአት ከታዩ ጉዳዩ ስም ይሰጠዋል። ሲነገርም ሕክምናዊ ብያኔና መፍትሔ ለመስጠት የሚያስቸግር ከሆነ 'የባህርይ ስብስብ ውስጥ ይካተታል' ወይም ምልክቶች አሉት ይባላል እንጂ 'እገሌ የተባለ በሽታ(በሽታ ከሆነ) አለበት' ላይባል ይችላል። የዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ እነዚህ አእምሮአዊ ሁነቶች የሚመረመሩት በ ስታቲካዊ የምርመራ መመሪያ(DSM) በመሆኑ ከተጠቀሱት ባህርያት መካከል የተወሰኑትን ለተለየ የጊዜ ክፍተት ያለበቂ ምክንያት ከታዩ ሁነቱ አለ ይባላል። ስለዚህ ለሁነቱ ስም ከመሰጠቱ በፊት የነበሩ ታዋቂ ሰዎችን እንደምሳሌ ስንጠቀም ጉዳዩ አለባቸው ብሎ በእርግጠኝነት ከመናገር ይልቅ የመረመራቸው አካል እስከሌለ ድረስ ባህርያቱን ያሳያሉ ወይም ምልክቶቹ ነበሩዋቸው ማለት ብልህ አገላለፅ ይሆናል።እንዲህ አለማድረጉ ግን ለሙያዊ ብያኔዎች የሚሰጠውን ትኩረት ክብርና ግምት ስለሚያደበዝዝ ሙያው የሌለው ግን 'የሚያቅ' ሰው ሁሉ እየተነሳ ብያኔ እንዲሰጥ ያደፋፍራል። ይሄ ደግሞ ADHD እና OCD ላይ እንደሚታየው ራስን በራስ የመመርመርና ለሌለ እውነታ ስም ማውጣትና መፍትሄ ማዘዝን ያበረታታና ያሉትን እውነታዎች ደሞ አለመረዳትና ጣልቃገብነቶችን ማናናቅ ላይ ያመራል። 2. ኦቲዝም ያለበት ወይስ ኦቲዝማዊ ማንነት የሚታይበት?በተግባባንበት ነገር ላይ ስንነጋገር የቃላት ምርጫዎች ለውጥ ላያመጡ ይችላሉ።ሆኖም እንዲህ ባሉ መረጃ ሰጪ ወይም አወያይ ሐሳቦች ላይ ኒውሮሎጂካል ሁነቶችን ከሕመም ጋር የሚያያዙ ቃላትን መጠቀም ወደ ብየና ስለሚመሩ አንድ ባህሪ በተለያየ መንገድ እና ምክንያት እየተከሰተም ቢሆን ቅድመ ግምት ተፅእኖ ያሳደረበትን ውሳኔ እንድናሳልፍ ያደርጋል።ይሄ ደግሞ 'ያብዬን ለእምዬ' እንዲሉ ያንዱን ምልክት ለሌላኛው ሁነት ምስክርነት እንድንጠራ ያደርጋል። ይሄ በሆነበት ደግሞ ባህርያቱን ለሌቭል መጠቀም ስህተት የመሆን አጋጣሚን ይጨምራል። 3. ይህ አቀራረብ እውን ለጥብቅና ይረዳል? ሊረዳ ይችላል ግን በጣም ሰብጀክቲቭ ይሆናል። አንደኛ ኦቲዝማዊ ማንነት ፀጋም ፈተናም እንዳለው ሁሉ ፀጋ የሌለበ ኬዝም ያጋጥማል። ይሄ በሆነበት ብሩሁን ገፅ ስናስተዋውቅ ግለሰቦች ያልሆኑትን ናቸው የማለት ስህተት ውስጥ ልናስገባ እንችላለን።ለምሳሌ 'እንቶኔ እስከ 7አመቱ ድረስ አይናገርም ነበር። አሁን ግን አንደበተ ርቱዕ ተናጋሪ ነው' ብንል። ሰሚ 'የኔም ልጅ አሁን 4 አመቱ ነው ስለዚህ አለመናገሩ አሳሳቢ አይደለም' ወደሚለው ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ እንደምሳሌ የምንጠቀምባቸው ታሪኮች በጣም ሰብጀክቲቭ መሆናቸውን ሳንረሳ መጠቀም ይገባናል። አክሴፕታንስ ላይ ጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉትን ሊረብሽ ይችላል። 4. የኦቲዝም ሕብረሁኔታዊነት። ኦቲዝም ሕብረሁኔታዊነቱ በተፅዕኖው ደረጃና አይነትም ላይ የሚገለፅ መሆኑን መርሳት የለብንም። ይሄ ልዩነት ደግሞ ጣልቃገብነትም ሆነ ጥብቅናና እውቅናን ከስብስብ ይልቅ ግላዊ ለማድረግ ያስገድደናል።የሜሲ ኦቲስቲክነት ለአነስታይን ምኑ ነው?
Repost from Hakim
+2
በኦቲዝም ዙሪያ ለቀረበው ጽሑፍ እይታዬን ለማጋራት ወደድኩ
የቀረበው ጽሑፍ በኦቲዝም ዙሪያ ያለውን ሳይንሳዊ እና ታሪካዊ እውነታ በተሳሳተ መንገድ ቀልቦ፣ ማህበረሰባዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጠቀሜታውን ችላ በማለት የቀረበ ድምዳሜ ላይ የተመሠረተ ነው። የቀረበውን arguments በበሰለ ሳይንሳዊ፣ ማህበረሰባዊ እና ባህላዊ እይታ በዝርዝር እስኪ እንየው።
የስሑት እይታዎች ትችት እና ሳይንሳዊ ሙግት
የቀረበው ጽሑፍ «በታሪክ ውስጥ የነበሩ ታዋቂ ሰዎችን ከኦቲዝም ጋር ማያያዝ ሳይንሳዊ አይደለም» በሚል መነሻ የሚያቀርበው ሙግት የሕክምና ታሪክን፣ የስነ-አእምሮ እድገትን እና የወላጆችን ስነ-ልቦናዊ ተስፋ የመገንባት ተልዕኮን በውል ካለመረዳት የሚመጣ ነው።
፩. የዲያግኖሲስ ታሪካዊ አመጣጥ እና የቁሳዊ ምርመራ አለመኖር (Diagnostic History & Absence of Biomarkers)
የጽሑፉ አቅራቢ «ኦቲዝም በሕክምና፣ በምርመራ፣ በሳይንሳዊ ሒደት የሚረጋገጥ ነው» በሚል ያስቀመጠው ድምዳሜ መሠረታዊ የስነ-አዕምሮ ሕክምናን (Psychiatry) መርህ ይቃረናል፡
ምንም ዓይነት የደም፣ የላቦራቶሪ ወይም የሬዲዮሎጂ ምርመራ የለውም፡ ኦቲዝም እንደ ደም ብዛት፣ ስኳር ወይም ካንሰር በላቦራቶሪ ምርመራ (Medical Biomarker) የሚረጋገጥ ሕመም አይደለም። የኦቲዝም ማረጋገጫ (Diagnosis) የሚሰጠው የባህሪ፣ የመግባባት እና የማህበራዊ ግንኙነት ምልከታዎችን (Behavioral Criteria) መሠረት በማድረግ ብቻ ነው።
የታሪክ እና የስያሜ ዘግይቶ መምጣት፡
የኦቲዝም ስያሜ እና የምርመራ መስፈርት (Diagnostic Criteria) የተደራጀው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ (በተለይም ከ1980ዎቹ ወዲህ በDSM ስርዓት) ነው። ነገር ግን ስያሜው ከ1980ዎቹ በፊት አለመኖሩ፣ ከዚያ በፊት የነበሩ ሰዎች የኦቲዝም ባህሪያት አልነበራቸውም ማለት አይደለም። እንደ አልበርት አንስታይን፣ አይዛክ ኒውተን ወይም ሞዛርት ያሉ ከ200 እና 300 ዓመታት በፊት የነበሩ ሊቃውንት የኦቲዝም መገለጫ የሆኑትን ባህሪያት (Autistic Traits) በግልጽ ያሳይ እንደነበር የታሪክ ሰነዶች ያረጋግጣሉ።
፪. በታሪካዊ ግለሰቦች ላይ የሚታዩት የኦቲዝም ባህሪያት (Autistic Traits in Historical Figures)
እንደ Behavioral Innovations ባሉ መሪ የበህሪ ምርመራ እና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት የጥናት ሰነዶች ላይ እንደተጠቀሰው፣ ታሪካዊ ሰዎችን ከኦቲዝም ጋር ማያያዝ በዘፈቀደ ተረት ሳይሆን በታሪካዊ የባህሪ ማስረጃዎች ላይ የተመሠረተ ነው፦
አልበርት አንስታይን (Albert Einstein): እስከ 3 እና 4 ዓመቱ ድረስ አለመናገሩ (Delayed Speech)፣ አንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት የማድረግ (Repetitive and restrictive behavior) እና የማህበራዊ ግንኙነት (Social skill deficit) ፈተናዎች ነበሩበት።
ሞዛርት (Mozart): የተወሰኑ ተደጋገሚ የእጅና የሰውነት እንቅስቃሴዎች (Stereotyped Movements)፣ ለድምፅ ያለው ከፍተኛ ስሜታዊነት (Sensory Sensitivity) እና ማህበራዊ የግንኙነት ድክመቶች ነበሩበት።
ኤሚሊ ዲኪንሰን (Emily Dickinson): ከተለመደው ማህበራዊ ህይወት መገለል፣ ለስሜት ህዋሳት አነቃቂዎች (Sensory Stimuli) ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እና በብቸኝነት ስራ ላይ ብቻ ማተኮር።
ሚካኤል አንጄሎ (Michelangelo) እና ሰር አይዛክ ኒውተን (Sir Isaac Newton): በሰራቸው ስራዎች ላይ ያለው አባዜ ያዘለ የዝርዝር ትኩረት (obsessive attention to detail in his work) እና ከሰዎች ጋር የመቀራረብ ከፍተኛ ፍርሃት/ችግር።
እነዚህን ሰዎች በወቅቱ «ኦቲዝም» የሚል የህክምና ካርድ አልተሰጣቸውም በሚል ምክንያት የኦቲዝም ባህሪያቸውን መካድ ሳይንሳዊ ፍትሃዊነት አይደለም።
ታዋቂ ሰዎችን መጥቀስ ያለው ማህበረሰባዊ እና ስነ-ልቦናዊ ፋይዳ
በእኛ ባህልና ማህበረሰብ ውስጥ «አእምሮአዊ ወይም የዕድገት መዛባት» ያለባቸው ልጆች ሲወለዱ በብዙ ወላጆች ዘንድ የሚፈጠረው የመጀመሪያው ስሜት ተስፋ መቁረጥ፣ ብቸኝነት እና ጥልቅ የልብ ስብራት ነው። ያለው ጠቀሜታ እንመልከት፦
፩. የተስፋ ጭላንጭል ማሳየት (Inspiring Hope and Resiliency):
ወላጆች የልጆቻቸውን ፈተና እና የተግባቦት እክል በደንብ ያውቃሉ። ታዋቂ ሰዎችን መጥቀስ «ኦቲዝም ቀላል ነው» ለማለት ሳይሆን፣ «ልጆቻችን ተገቢውን ድጋፍ፣ ፍቅር እና የመማር እድል ካገኙ የትም መድረስ ይችላሉ» የሚል ተስፋን ለመስጠት ነው።
፪. የማህበረሰቡን የተዛባ አመለካከት/ስቲክማ መስበር (De-stigmatization):
በባህላችን ውስጥ ያሉትን አሉታዊ አመለካከቶች ለመቀየር የልጆቹን ድክመት ብቻ ሳይሆን የሚደነቅ እምቅ አቅማቸውን (Strengths-based approach) ማሳየት ወሳኝ ተልዕኮ ነው።
በዘመናዊ የኦቲዝም ባለቤቶች የተረጋገጠ እውነት፡
በአሁኑ ዘመን በህክምና የተረጋገጠላቸው እንደ ኤሎን መስክ (Elon Musk)፣ ሰር አንቶኒ ሆፕኪንስ (Sir Anthony Hopkins)፣ ዳን አክሮይድ (Dan Aykroyd) እና ቴምፕል ግራንዲን (Temple Grandin) ያሉ ሰዎች መኖራቸው፣ በታሪክ የነበሩትም (predecessors) እንደነበሩ በግልጽ ያሳያል።
ማጠቃለያ
በቀረበው ጽሑፍ ላይ «ሳይንሳዊ አይደለም» በሚል የቀረበው ክርክር የህክምና ታሪክን ክፍተት (Historical Diagnostic Void) ካለመረዳት የመጣ ነው። ኦቲዝም በሳይንስ የላቦራቶሪ ውጤት ሳይሆን በባህሪ የሚለይ በመሆኑ፣ ታሪካዊ ሰዎችን በባህሪያቸው መነሻነት መጥቀስ ሙሉ በሙሉ ምክንያታዊ እና አሳማኝ ነው።
ከሁሉም በላይ ግን፣ እነዚህን ታዋቂ ሰዎች መጥቀስ ለወላጆችና ለቤተሰብ ጥንካሬን የሚሰጥ፣ የልጆቻቸውን አቅም በበጎ መንገድ እንድናይ የሚያስችል እና ወላጆች በፅናት ልጆቻቸውን እንዲደግፉ የሚያነሳሳ ማህበረሰባዊ ብርሃን ነው። አመሰግናለሁ።
References
1. www https://academy.theibao.com/course/autism-spectrum-disorders
2. https://www.biermanautism.com/resources/blog/10-famous-people-with-autism-spectrum-disorder-asd/
3. https://behavioral-innovations.com/blog/20-famous-people-with-autism-spectrum-disorder-asd/
George Yehish: Psychologist, International Behavior Analyst candidate
@HakimEthio
በመላኩ ብርሃኑ
እኔ ኳስ ብዙ አላውቅም፡፡ “ብዙ አላውቅም” ሳይሆን ምንም አላውቅም። በዛሬው የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ ኮሜንታተሩ በርካታ ጊዜ 'ኩኩሬላ' የተባለ ተጨዋችን ስም ሲጠራ እየሰማሁት ነው፡፡ በእረፍት ሰዓት እነናኒ ስለዚህ የስፔን ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች ታሪክ ነገሩኝና እነሱ ኳስ እያዩ እኔ ስለርሱ አንዳንድ መረጃዎችን ሰርች ማድረግ ጀመርኩ፡፡
ኩኩሬላ ከባለቤቱ ክላውዲያ ሮድሪገዝ ጋር አማዞን ፕራይም ላይ ቀርቦ የሰጠው ኢንተርቪው ነው ቀልቤን የገዛው። እንባ ተናንቆት ፣ ብዙ የመናገር አቅም አጥቶ ሳየው የምር አሳዘነኝ።
የሪያል ማድሪድ ክለብ 55 ሚሊዮን ዩሮ ለዝውውር ያቀረበለት ይህ የቼልሲ ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላ በድርድሩ ያቀረበው ከኳስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ቅድመሁኔታ ነው ብዙዎች “ጀግና አባት” ብለው እንዲያደንቁት ምክንያት የሆነው።
የ4 ዓመት አድሜ ያለው የኩኩሬላ የበኩር ልጅ ማቲዎ ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ነው። "ማንኛውም ክለብ እኔን የሚፈልግ ከሆነ፣ መጀመሪያ የማደርገው ነገር ለልጄ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ወይም የቴራፒ ማዕከላት መኖራቸውን ማረጋገጥ ነው” የሚለው ኩኩሬላ የገንዘብ ጥቅማጥቅሞችን፣ የስታዲየም መሰረተ ልማቶችን ወይም የውል ዘመንን ከመመልከቱ በፊት፣ ዋናው ቅድመ ሁኔታው አዲሱ የማድሪድ ከተማ ኦቲዝም ላለበት ማቲዮ ለተባለው ልጁ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ማረጋገጥ እንደነበር ሲናገር እንባ እየተናነቀው ነው።
ለኩኩሬላ ዝና እና ገንዘብ ከዚህ የበኩር ልጁ ደህንነት በላይ አያሳስበውም። የሱን የእግር ኳስ ህይወት የሚወስነው የሚደራደርበት ገንዘብ እና የሚቀርብለት ጥቅማጥቅም ሳይሆን ለልጁ ምቹ የሆነ አገልግሎት የሚሰጥበት ስፍራ ማግኘት መቻሉ ነው።
"ለልጄ የሚስማሙ ትምህርት ቤቶችን ወይም የቴራፒ ማዕከላትን ማግኘት ወደማልችልበት ወደ የትኛውም ክለብ አልሄድም" ሲል በግልጽ የተናገረው ኩኩሬላ እጅግ በጣም የደነቀኝን አንድ ነገርም ብሏል።
“ልጄ የሚያሳየው ማንኛውም ትንሽ የእድገት ለውጥ ወይም የሚያስመዘግበው ስኬት፣ ከማንኛውምየእግር ኳስ ዋንጫ በላይ ለኔ ትልቅ ትርጉም አለው” ነበር ያለው።
የኩኩሬላ ልጅ እስካሁን መናገር አይችልም። ይህ ልጅ አሁን ባለበት እድሜ ከኦቲዝም ጋር እንደሚኖር የተረጋገጠ ቢሆንም በቂ ድጋፍ ካገኘ ግን ህይወቱ ሊለወጥ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። አባት እና እናት የትኛውም የህይወት ፈተና እና እድል ከልጃቸው ማቲዮ ደህንነት አይበልጥባቸውም። የነሱ የሁልጊዜም ምኞት ማቲዮ እንደወንድምና እህቶቹ ሆኖ ማየት ነው። ለዚህ ደግሞ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
ለዚህ ነው በስነልቡናም፣ በኑሮም እጅግ ከሚፈትነውና ወደማንም ቤት ቢገባ ከምንም ነገር በላይ ‘ቅድሚያ’ ከሚሆነው ኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ የሚያሳድጉ ወላጆች ሁሉ ‘ጀግኖች ናቸው’ የሚባለው።
I salute you #MarkCucurela 🙏
አንተን ለማየት ስል ኳስ ማየት ልጀምር ነው እንግዲህ! 😄
ከመላኩ ብርሃኑ የፌስቡክ ግለ-ገፅ የተወሰደ
ከኦቲዝም ጋር መኖር አለመቻል አይደለም!
Success Story | ስኬታማ ታሪኮች
ጄሰን አርዴይ (Jason Arday)
እስከ 11 ዓመቱ የንግግር ክህሎቱ ዝቅተኛና አንዳችም ቃል የማያወጣ ነበር፣ እስከ 18 ዓመቱም ማንበብና መፃፍ ይቸገር ነበር፤ ግና አኹን የካምብሪጅ መካነ-አዕምሮ (Cambridge University) ወጣቱ ፕሮፈሰር ኾኗል።
አዎ! ወጣቱ ኢንግሊዛዊ ሶሾሎጂስት ጄሰን አርዴይ (Jason Arday)
በደቡብ የሎንደን ክፍል እ/አ/አ በ1985 ተወለደ። በ3 ዓመቱ ከዕድገት መዘግየት (Global Developmental delay) እና ኦቲዝም ጋር እንደሚኖር በሕክምና ተረጋገጠ። በወቅቱ የነበሩ ባለሞያዎች ከዚህ በኃላ መናገርና ራሱን ችሎ መኖር አይችልም ብለው ነበር። ትንቢታቸውና ንግግራቸው ትክክል እንዳልነበር ግን አረጋገጠላቸው!
እናቱ ጊፍቲ የአዕምሮ ጤና ነርስና የፀረ-ዘረኝነት አቀንቃኝ ነች። በእያንዳንዱ የሕይወቱ ዳና እና ምዕራፍ ከጎኑ ነበረች፤ ብዙ ዋጋም ከፍላለታለች። ንግግር እንዲችል/እንዲማር ድግግሞሽና ሙዚቃን እንደጠቀመች ትናገራለች፤ ከበርካታ የቴራፒ ጊዜያት በኃላም ጄሰን ለውጦችን ማሳየት ሲጀምር የመጀመሪያ ቃሉንም በ11 ዓመቱ ተናገረ፤ ከዛም ጊዜ በኃላ በተከታታይ ንግግሮችን መልመድና መናገር ቀጠለ።
ከ2023 ወዲህ በ37 ዓመቱ ደግሞ 3 የአካዳሚክ መፅሐፎችን አሳትሟል፤ በ3 ዩኒቨርስቲዎችም ሶሾሎጂን፣ ስለዘር (Race) ያስተምራል። በሥራውም በውጤታማነት እያገለገለ ይገኛል። ለእርዳታ ድርጅቶችም ከ5 ሚሊየን ብር በላይ በመለገስ ፈንድሬሰርም ነው። አይበገሬው ጄሰን በምሽት ፈረቃ የፅዳት ሥራም ሠርቷል። ጥቁር በመኾኑ፣ ከኦቲዝም ጋር መኖሩ በአጠቃላይ በአዕምሮ ዕድገት ልዩነት (Neurodivergent) ሥር መኖሩ ብዙ ፍረጃ፣ ስቃይን ዐይቷል፤ በድልም አልፎታል። በየተለያዩ መድረኮች ንግግሮችን በማድረግ እያስተማረ፣ ለሌሎች ድምፅ እየሆነ ይገኛል።
Moral of the story: Never give up on your child!
በዋኖስ መስፍን
@WanosMesfin
የተስማማንባቸው ግን ስሑት የኾኑ ጉዳዮች
በኦቲዝም ዙሪያ ወላጆች፣ ተቋማት፣ ባለሞያዎችና 'ይመለከተናል' የሚሉ ሁሉ የጥብቅና ወይም የመሟገት (Advocacy) ተልዕኮ ላይ፣ የግንዛቤ የማስጨበጥ እንቅስቃሴ ላይ እና ሌሎች ማህበረሰቡን ለማንቃት፣ ለማስተማር ብሎም የተዛባ አመለካከትን ለመቀየር በሚደረገው ትግል ውስጥ የተስማማንባቸው ግን ስሑት የኾኑ ጉዳዮች አሉ።
በተሳሳተ መንገድ ከሚተላለፉ መረጃዎች መካከል በሕክምና/በሳይንስ ከኦቲዝም ጋር መኖራቸው ያልተረጋገጡ ሰዎችን መጥቀስ ይገኝበታል።
ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎች (A Person living with Autism) ማህበረሰቡ እነሱን የሳለበት/የሚረዳበት መንገድን ለመቀየር በመፈለግ የኛ ልጆች ድክመት ብቻ እንደሌለባቸው፣ ያጋጠማቸውን የአዕምሮ ዕድገት መዛባት ብቻ ላይ እንዳናተኩር በአጠቃላይ ኦቲዝም ጨለማ ጎን ብቻ እንደሌለው ለማሳወቅ ኦቲዝም የሌለባቸውን ሰዎች አለአግባብ እንጠቅሳለን።
ለምሳሌም፦
አልበርት አንስታይን (Albert Einstein)
ሊዮኔል ሜሲ (Lionel Messi)
አይዛክ ኒውተን (Isaac Newton)
ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ (Leonardo da Vinci)
ኒኮላ ቴስላ (Nikola Tesla)
ቶማስ ኤዲሰን (Thomas Edison)
አሌክሳንደር ግራሃም ቤል (Alexander Graham Bell)
ሞዛርት (Mozart)
ቻርልስ ዳርዊን (Charles Darwin)
ከላይ የተዘረዘሩት እና ሌሎች ያልተጠቀሱት ታዋቂ ሰዎች ከኦቲዝም ጋር ስለመኖራቸው የተረጋገጠ ሳይንስ የለም። ምንም እንኳን መጠቀሳቸው ጉዳት ባይኖረውም ትክክለኛውን እና ስህተቱን አጥርቶ ማወቅ ተገቢ ግን ነው።
ሆኖም በትክክል በሳይንስ/በምርመራ የተረጋገጡ ዝነኛ፣ ታዋቂ እና የዓለምን ታሪክ የቀየሩ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎች በጥቂቱ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል፦
ቴምፕል ግራንዲን (Temple Grandin)
ዳሪል ሃና (Daryl Hannah)
ሄሊ ሞስ (Haley Moss)
ጄኮብ ቬላዝኬዝ (Jacob Velazquez)
ካርሊ ፍላይሽማን (Carly Fleischmann)
ናኦኪ ሂጋሺዳ (Naoki Higashida)
ኮዲ ሊ (Kodi Lee)
ቶም ስቶልትስመን (Tom Stoltsmon)
ጄሰን አርዳይ (jason arday)
ኦቲዝም በሕክምና፣ በምርመራ፣ በሳይንሳዊ ሒደት የሚረጋገጥ እንጂ በግለሰቦች የሕይወት ታሪክ ላይ ተመሥርቶ የሚሠጥ ስያሜ አይደለም።
Paradigm shift !
ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin
Interview 🔴 LIVE
👤 Guest Speaker: Meseret Kinfe Haile
(Parent | Autism Advocate | Author of Yetikur enat negn and Yemaynagerew lioul | Founder of Lioul Foundation )
📆 Date: 10/07/2026 G.C | Friday
⏰ Time: 20:30 - 22:30
📌 Venue: https://t.me/MelaSpecialNeedsService?livestream=186b447a393de0c09f
👨💼 Moderator: Haleluya Ayele
We invite all Parents and families to join us in this Live webinar to share their experiences and knowledge.#Parents_Webinar 🤳 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService
