ch
Feedback
ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር️

ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር️

前往频道在 Telegram

መጽሐፍትን በጥሩ ዋጋ እንገዛለን እንሸጣለን! ገፁን ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፉት 📚📚 አድራሻችን አዲስአበባ 0991001450

显示更多

📈 Telegram 频道 ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር️ 的分析概览

频道 ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር️ (@bookworlds1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 10 700 名订阅者,在 书籍 类别中位列第 3 544,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 089

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 10 700 名订阅者。

根据 28 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -77,过去 24 小时变化为 -2,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.59%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.42% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 0 次浏览,首日通常累积 794 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
መጽሐፍትን በጥሩ ዋጋ እንገዛለን እንሸጣለን! ገፁን ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፉት 📚📚 አድራሻችን አዲስአበባ 0991001450

凭借高频更新(最新数据采集于 29 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 书籍 类别中的关键影响点。

10 700
订阅者
-224 小时
-217
-7730
帖子存档
በ 1900 ማለትም ከዛሬ 118 ዓመት በፊት የታተመ የኦሮምኛ የማቴዎስ ወንጌል ማለትም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲሆን አሰጅግ ታሪካዊ ሰነድ ነው። መጽሐፉን በመደብራችን ታገኙታላችሁ። 0991001
+2
በ 1900 ማለትም ከዛሬ 118 ዓመት በፊት የታተመ የኦሮምኛ የማቴዎስ ወንጌል ማለትም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲሆን አሰጅግ ታሪካዊ ሰነድ ነው። መጽሐፉን በመደብራችን ታገኙታላችሁ። 0991001450

"የሴቶች ገመና መጽሐፍ ዋና ዋና ነጥቦች" 👉የሴቷ የግል ተግባራትና ምስጢራት 👉የሴቷ አካላትና የግል ንብረቶች 👉ሴቶች በቤታቸው ደብቀው የሚያስቀምጧቸው 5 ነገሮች 👉ሴቶች ስለወሲብ ምን ያህል
"የሴቶች ገመና መጽሐፍ ዋና ዋና ነጥቦች" 👉የሴቷ የግል ተግባራትና ምስጢራት 👉የሴቷ አካላትና የግል ንብረቶች 👉ሴቶች በቤታቸው ደብቀው የሚያስቀምጧቸው 5 ነገሮች 👉ሴቶች ስለወሲብ ምን ያህል ያስባሉ? 👉ሴቶች እራሳቸውን በራሳቸው በወሲብ ያረካሉን? 👉ሴቶች ከወንዶች ይበልጥ ውስብስብ የሆኑበት ምክንያቶች 👉የተለያዩ የሴት ምስጢራት 👉ድንግልናዬን መቼና እንዴት አጣሁ? 👉ገመናዊ ውይይት - የሴቷ ራስን በራስ ማርካት (ሴጋ) ምስጢር 👉የምትፈልጋትን ሴት ለማግኘትና ለማማለል 👉 በመጀመሪያው ዕይታ ሴቷን የሚማርክ የወንድ ዓይነት 👉የወንዶች መልክ በሴቶች ዘንድ ያለው ዋጋ ሴቶችን ቶሎ ወንድ እንዲቀርቡ የሚያደርጉ ነገሮች 👉አጫጭር ወንዶች ሴቶችን ለመማረክ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዓበይት ነጥቦች መጽሐፉን እኛጋ ታገኙታላችሁ! በpdf የምትሉ pdf እኔጋ የለኝም ። ከታች ባለው የቴሌግራም user name ጠይቁት። 👇👇👇 @gmy231 @gmy231

ይህ መጽሐፍ የ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምስቅልቅልና ማኅበራዊ ገጽታ በጥበብ የሳለ፣ የአንድ ታማኝ የሥርዓት ሰው መታሰቢያ ነው። መጽሐፉ የነገሥታቱን የሥልጣን ኮሪደር ውስብስብ ሽኩቻ
ይህ መጽሐፍ የ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምስቅልቅልና ማኅበራዊ ገጽታ በጥበብ የሳለ፣ የአንድ ታማኝ የሥርዓት ሰው መታሰቢያ ነው።  መጽሐፉ የነገሥታቱን የሥልጣን ኮሪደር ውስብስብ ሽኩቻና የባለሥልጣናቱን የጽናት ፈተና በጥልቅ ትንተና ያጋልጣል። የአፄ ኃይለ ሥላሴን ዘመን ውስብስብ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ገጽታዎች ጥልቅ በሆነ እይታ የሚተርክ እውነተኛ ትዝታ እና ማሽታወሻ ሲሆን  ደራሲው የነበራቸውን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች መሠረት በማድረግ፣ የዘመኑን የቢሮክራሲ ጉዞና የሥልጣን ሽኩቻ በድፍረትና በጥልቀት ጽፈውታል!

የተከፈለበት ማስታወቂያ! ያገለገሉ አሮጌ መጽሐፎችን እንገዛለን! ከታች ባለው user name አናግሩን! @gmy231 @gmy231

ከ 73 ዓመት በፊት የተጣፈ ግጥም! መንግስቱ ለማ✍️
ከ 73 ዓመት በፊት የተጣፈ ግጥም! መንግስቱ ለማ✍️

አዲስ መጽሐፍ ከተወዳጁ አዳም ረታ! በቅርብ ቀን! ከ 1000 በላይ ገፆች። ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር!
አዲስ መጽሐፍ ከተወዳጁ አዳም ረታ! በቅርብ ቀን! ከ 1000 በላይ ገፆች። ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር!

ጥሩ ውሎ ከበዕውቄ ጋር! በመጽሐፍት ዙሪያ ከአንባቢዎች ጋር መወያየት በጣም ደስታ የሚሰጠኝ ነገር ነው። ሁላችንም የየራሳችን የመጽሐፍት ምርጫ አለን! ፍልስፍና አጥብቀው የሚወዱ ሰዎች አሉ....ሐይማ
ጥሩ ውሎ ከበዕውቄ ጋር! በመጽሐፍት ዙሪያ ከአንባቢዎች ጋር መወያየት በጣም ደስታ የሚሰጠኝ ነገር ነው። ሁላችንም የየራሳችን የመጽሐፍት ምርጫ አለን! ፍልስፍና አጥብቀው የሚወዱ ሰዎች አሉ....ሐይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ጽሑፎች የሚማርካቸው ሰዎችም አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ስነ ልቦናን (ሳይኮሎጂን) መሰረት አድርገው የተፃፉ መጽሐፍትን ይወዳሉ። ሌሎች የታሪክ መጽሐፍትን ከልባቸው ይወዳሉ። ፍቅር ላይ የተፃፉ መጽሐፍትንም የሚወዱ አሉ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንድ ላይ ተጠቅልለው የሚገኙበት ድንቅ ትልቅ ቤተመጽሐፍ ደግሞ በዕውቄ ነው። በዕውቄ ግልብ አንባቢ አይደለም። አንዳንዴ ጊዜውን ከዬት እንደሚያገኜው ይገርመኛል። በዚህ የሩጫ ዘመን ላይ አዳዲስም ይሁኑ የጥንት መጽሐፎችን እያሳደደ የሚያነብበት ነገሩ በጣም ይገርመኛል። እና ከዚህ ታላቅ የስነ ጽሑፍ አባት ጋር ለሰዓታት በመጽሐፍት ዙሪያ ውይይት ማድረግ ትልቅ ቤተመጽሐፍት ውስጥ እንደመሆን አይነት ስሜት አለው።

"ዳንኤል ክብረት እና መጽሐፍ" ትላንት ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የመጽሐፍት አውደርእይ እየተደረገ ይገኛል። እኛም እንደ አንድ የመጽሐፍ ነጋዴ መጽሐፋችንን ይዘን በቦታው ተከ
"ዳንኤል ክብረት እና መጽሐፍ" ትላንት ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የመጽሐፍት አውደርእይ እየተደረገ ይገኛል። እኛም እንደ አንድ የመጽሐፍ ነጋዴ መጽሐፋችንን ይዘን በቦታው ተከስተናል። መጽሐፍትን ለመሸመት እና ለማዬት የሚመጡ ብዙ ደንበኞች ቢኖሩም በሃገሪቱ ውስጥ በመልካምም በመጥፎም ስማቸው የሚነሳ ሰዎች በቦታው ይገኛሉ። ለእኔ መልካም ከምላቸው ሰዎች መካከል አለማየሁ ገላጋይ፣በዕውቀቱ ስዩም፣እና ሌሎችም ይገኙበታል። ፖለቲከኞችን ስለማልወዳቸው መልካም የምለው ሰው የለኝም። ዛሬ ከፖለቲከኞች መካከል ዳንኤል ክብረት፣ ነብዩ ባዬ ጣሂር ሙሀመድ እና ሌሎቹም ለቤተመንግስቱ ሰውዬ ቅርብ የሆኑ ሰዎች በቦታው ተከስተው ነበር። ዳንኤል ክብረት አንባቢ ቢሆንም ንባብን ለክፋት ከተጠቀሙ ሰዎች መካከል እንደሆነ ይሰማኛል። ከመጽሐፌ ዝርዝር መካከልም "ፋኖነት" የተሰኜው መጽሐፍ ፊት ለፊት ተቀምጧል። ዳንኤል ክብረት ለአንድ አፍታ አተኩሮ ከተመለከተ በኋላ "ግርማዊነታቸው በአሜሪካ ሀገር"የተሰኜውን የከበደ ሚካኤልን መጽሐፍ ጠየቀ። ከበደ ሚካኤል ለኢትዮጵያ ስነጽሑፍ በተለይም ለዘመናዊ ግጥም ውለታ የዋሉ ሰው ቢሆኑም በባንዳነታቸው የሚታወቁ ሰው ነበሩ።(ሙት ወቃሽ አታድርገኝ) እና ምን ለማለት ነው.....!? ዳንኤል ክብረት አድናቂህ ነኝና ፎቶ እንነሳ ይለኛል😂 ብዬ ስጠይቅ መጽሐፍ እንኳን ሳይገዛኝ በመሄዱ አዝኛለሁ። የከበደ ሚካኤልን መጽሐፍ በመጠየቁ አልገረመኝም። "ግርማዊነታቸው በአሜሪካ ሀገር" የሚለውን መጽሐፍ በመጠየቁ ገርሞኛል። ለምን ካላችሁኝ "የንጉሱ ገመና" የሚለውን መጽሐፍ እኔድታነቡ ጋበዝኳችሁ። ገጣሚ ጊዜአለው

https://www.facebook.com/share/r/1M3A5MhAK6/ እየገባችሁ ሾፍ አድርጉኝ ትንሽ ተደናግሬአለሁ ልጅቷ ቆንጆ ስለሆነች።

"አዎ በጣም ያማል" ሞታችን አሟችሁ ለቅሶ ባትደርሱ፣ በደማችን ግብር ሰርግ ስትደግሱ። ባዘናችን ዳስ ላይ .... የደስታችሁ ድንኳን ተሰቅሎ ስናየው፣ ከሞታችን በላይ ይሄ ነው የያመው። አዎ በጣም ያ
"አዎ በጣም ያማል" ሞታችን አሟችሁ ለቅሶ ባትደርሱ፣ በደማችን ግብር ሰርግ ስትደግሱ። ባዘናችን ዳስ ላይ .... የደስታችሁ ድንኳን ተሰቅሎ ስናየው፣ ከሞታችን በላይ ይሄ ነው የያመው። አዎ በጣም ያማል....😓 በሌሎች እምባ ላይ ጥርስ ፍቆ መሳቅ፣ ሶስት ቀን ለመኖር አራት ቀን መሳቀቅ። አዎ በጣም ያማል.... ሁልጊዜ በሻማ ሞትን ማደባበስ፣ ለምት ተሰልፈን ለሚሞቱት ማልቀስ። አዎ በጣም ያማል.. ገጣሚ ጊዜአለው ✍️

ስትገደል ያላዳነህ ታቦት ገደል ይግባ! ሐይማኖት ሰዎች የመሰረቱት ነገር ነው። የሰው ልጅ ዛሬም ነገም ይቀጥላል። ሐይማኖት ቢጠፋ የሰው ልጅ አይጠፋም። የሰው ልጅ ከጠፋ ግን ሐይማኖት ይጠፋል። ስለዚ
ስትገደል ያላዳነህ ታቦት ገደል ይግባ! ሐይማኖት ሰዎች የመሰረቱት ነገር ነው። የሰው ልጅ ዛሬም ነገም ይቀጥላል። ሐይማኖት ቢጠፋ የሰው ልጅ አይጠፋም። የሰው ልጅ ከጠፋ ግን ሐይማኖት ይጠፋል። ስለዚህ ሐይማኖት የሚኖረው በሰዎች ህልውና ነው። ከዛሬ ምናምን አመት በፊት የሆነ ተጋድሎ አድርጓል ብላችሁ ታቦት ቀርፃችሁ እሱን ከምትንከባከቡ ተደራጅታችሁ ራሳችሁን አድኑ። ታቦቱ እናንተን ከመገደል ካላዳነ ተራ እንጨት ወይም ጣውላ ነው። ከዚህ የዘለለ ዋጋ የለውም። ምን አልባት ከወርቅ የተቀረፀ ከሆነ ወርቁ ለተቸገሩ ሰዎች ሊጠቅም ይችላል ከዚያ ውጭ ግን ምንም የሚጠቅም ነገር የለውም። እሱን ይዞ መሰደዱም ዋጋ ቢስ ነው። እስከዛሬ በግፍ ስንገደል ታቦቱ መች አዳነን ኝንኳን እኛን ራሱንስ መች አዳነ? ስለዚህ ሰይፍ ለመዘዘብህ ሰይፍ ምዘዝና ራስህን አስከብር!

አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ያዘጋጀው የመጽሐፍት አውደርእይ የመጀመሪያ ቀን! ከምርጥና ከተወደዱ መጽሐፍቶች መካከል የትኛው ቀድሞ አይናችሁ ውስጥ ገባ!? ከኢትዮጵያ ውጭ ጨምሮ በሁሉም የዓለም ሀገራት መጽ
አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ያዘጋጀው የመጽሐፍት አውደርእይ የመጀመሪያ ቀን! ከምርጥና ከተወደዱ መጽሐፍቶች መካከል የትኛው ቀድሞ አይናችሁ ውስጥ ገባ!? ከኢትዮጵያ ውጭ ጨምሮ በሁሉም የዓለም ሀገራት መጽሐፎችን እናደርሳለን! 0991001450 ደውሉ እዘዙን።

ለመጽሐፍት አንባቢዎች መልካም ዜና በአይነቱ ልዩ የሆነውና ከ60 በላይ የመጽሐፍት ነጋዴዎችን የሚያሳትፈው አውደርእይ ነገ በ 4 ኪሎ አብርሆት ቤተ መዛግብት ይጀመራል! አውደርእዩ ለ10 ቀናት የሚቆይ
+2
ለመጽሐፍት አንባቢዎች መልካም ዜና በአይነቱ ልዩ የሆነውና ከ60 በላይ የመጽሐፍት ነጋዴዎችን የሚያሳትፈው አውደርእይ ነገ በ 4 ኪሎ አብርሆት ቤተ መዛግብት ይጀመራል! አውደርእዩ ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ዛሬ የድንኳን ሰቀላ እና ቦታ የማደላደል ስራ ሰርተን ጨርሰናል! እናንተም መጥታችሁ ትጎበኙን ዘንድ በታላቅ ደስታ እናበስራችኋለን! የንባብ ባህልን በማበረታታት አንባቢ ትውልድ እንፍጠር! ዴርቶጋዳ መጽሐፍት መደብር!

ምላስ እንደሆነ ከማውራት አይቦዝን፣ በምሰማው ሁሉ አለሁ እኔም ሳዝን፣ ችግርን በተስፋ ጎራዴን በጋሻ፣ ህመምን በክኒን መርዝን በማርከሻ፣ ስመክት ከርሜ ሰበረኝ ንግግር፣ ሃሜት ጆሮን አልፎ.... እስከ ነፍስ ይጓዛል ባይኖረውም እግር። ገጣሚ እንደልቡ

ዛሬ ተፀጽተሽ በእምባ እንደነገርሽኝ፣ ሰይጣን አሳስቶሽ ከሆነ የተውሽኝ፣ እኔን እንድትከጂ ላሳሳተሽ ሰይጣን፣ ለውለታው ምላሽ ላጭስለት እጣን፣ እንዴት ዝም ይሉታል ከሳት ውስጥ ያወጣን። ገጣሚ እንደልቡ

ታሪካችንን በባዕዳን እይታ እንዴት ተመዝግቦ ይሆን? ይህ በዶክተር ሄንሪ ብላንክ (Dr. Henri Blanc) የተጻፈው ድንቅ መጽሐፍ፣ ወደ ኋላ መቶ ሃምሳ ዓመታት መልሶ በወቅቱ ወደነበረው እውነተኛ
ታሪካችንን በባዕዳን እይታ እንዴት ተመዝግቦ ይሆን? ይህ በዶክተር ሄንሪ ብላንክ (Dr. Henri Blanc) የተጻፈው ድንቅ መጽሐፍ፣ ወደ ኋላ መቶ ሃምሳ ዓመታት መልሶ በወቅቱ ወደነበረው እውነተኛ ክስተት ይወስደናል። መጽሐፉ የኢትዮጵያን አንድነት ለመመለስና ሀገራቸውን ለማዘመን ሌሊትና ቀን በራዕይ ይደክሙ የነበሩትን የታላቁን ንጉሠ ነገሥት የአፄ ቴዎድሮስን ዘመን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የታሪክ መስታወት ነው። ጸሐፊው በወቅቱ በመቅደላ ምሽግ ውስጥ በእስረኝነት የነበረ በመሆኑ፣ መጽሐፉ ተራ ልብ ወለድ ሳይሆን በዓይን ምስክርነት የተደገፈ  እውነተኛ ማስታወሻ ነው። በውስጡም፦ 🔹 የንጉሡን ጽኑና የማይናወጥ አቋም፣ ጀግንነት እና የሀገር ፍቅር ስሜት፣ 🔹በወቅቱ የነበረውን የታገቱ አውሮፓውያን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት እና የመቅደላን የመጨረሻ ምዕራፍ፣ 🔹እንዲሁም የዚያን ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ባህል፣ አኗኗርና የሀገሪቱን መልከዓ ምድር ውበት በስፋት ይተርካል። መጽሐፉ አንድ ፍሬ በመደብራችን ላይ ታጀኛላችሁ!

በጠና ናፍቀሽኝ አቅፈሽ የኔን ምስል፣ ከማልቀስሽ ብዛት ታመሽ ይሆናል ስል፣ ልብሽ በዚህ ፍጥነት መርሳት ከጀመረ፣ የልጅነት ህልምሽ እንኳን አልሰመረ። እንኳን ዶክተር አልሆሽ እንኳን እውቀት ነሳሽ ታስቸግሪ ነበር... የታካሚ ህድ ውስጥ መቀስ እየረሳሽ። ገጣሚ እንደልቡ

ገጣሚ እንደልቡ እውነትም እንደልቡ!
ገጣሚ እንደልቡ እውነትም እንደልቡ!