ch
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

前往频道在 Telegram

📈 Telegram 频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU 的分析概览

频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 454 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 042,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 328

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 454 名订阅者。

根据 28 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 550,过去 24 小时变化为 26,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 37.47%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.23% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 412 次浏览,首日通常累积 1 477 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33

📝 描述与内容策略

尚未提供频道描述。

凭借高频更新(最新数据采集于 29 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

14 454
订阅者
+2624 小时
+1347
+55030
帖子存档
"በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።" መኃ 2፡2 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube �
"በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።" መኃ 2፡2 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የ2016 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የመጀመርያ ቀን በጉራጌ ሀገረ ስብከት። ጥቅምት 2/01/2016 ዓም (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) በጉራጌ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅ
+5
የ2016 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የመጀመርያ ቀን በጉራጌ ሀገረ ስብከት። ጥቅምት 2/01/2016 ዓም (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) በጉራጌ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የ2016 ዓ.ም የትምህርት መርሐ ግብር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ባዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትግበራ መመርያውን ተከትሎ በ14 ክፍሎች ከ 1000 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን አስታወቀ። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር እንኳን ደስ አላችሁ! በ2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀውንና በሁሉም አኅጉረ ስብከት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በትግበራ
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር እንኳን ደስ አላችሁ! በ2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀውንና በሁሉም አኅጉረ ስብከት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በትግበራ ላይ ያለው ወጥ ሥርዓተ ትምህርት የመጀመርያ ፍሬውን አፍርቶ የቅድመ ሙከራ ትግበራ ከተጀመረባቸው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መካከል በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት 12ኛ ክፍል አስተምረው የደረሱ የሙከራ ትግበራ የመጀመርያው ተማሪዎች በመንበረ ፓትርያርክ በሀገር አቀፍ ደረጃም  በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ጥቅምት 3 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ  በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ባለወልድ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል። እርሶም በእለቱ ተገኝተው የጉባኤው ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

✥✥✥ ማኅሌተ ጽጌ የእመቤታችን ስደት ✥✥✥ ✥ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለው ወቅት ዘመነ ጽጌ (የጽጌ/ የአበባ ዘመን) ይባላል፡፡ በዘመነ ጽጌ አበባዎች ያብባሉ፤ ፍሬም ያፈራሉ፤ በዚህም ወቅት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር የጌታን ስደት እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ ✥ ማኅሌተ ጽጌ ፡ ማኅሌት የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ምስጋና ማለት ነው፡፡ ጽጌ የሚለውም የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ አበባ የፍሬ ምልክት ማለት ነው፡፡ ማኅሌት ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር ሲተረጎም ደግሞ የኣበባ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ይህም ድንግል ማርያም የማኅጸኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡ እመቤታችን እንዴት ተሰደደች ‹‹ #የኢትዮጵያ_ድንኳኖች_ሲጨነቁ_አየሁ ›› ዕንባቆም 3:7 አስቀድሞ ነቢዩ እንባቆም በተናገረው መሠረት ዓለምን ሁሉ የሚመግብ የሚያጠጣ ጌታን ይዛ ተሰደደች ተራበች ተጠማች የድንግል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? በዛ በአስጨናቂ የስደት ወራት አንድም ቀን የሚያሳድዷትን እንዲያጠፋቸው ወደ ልጇ አለመነችም በጎን የምትለምን እናት ለእኛ ለልጆቿ ፍቅር ትሕትናን ትስጠን ዘንድ ለሰው ልጆች ሁሉ ሩሕሩሕ የምትሆን ለፍጥረት ሁሉ የምታዝን ቤዛዊተ ዓለም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ከዮሴፍና ከሶሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደች፤ ከአባቶቿ ሀገር ወጥታ 3 ዓመት ከ6 ወር በዱር በገደሉ ተንከራተተች። እመቤታችን ከየት ወደ የት ተሰደደች አስቀድሞ በአባቶቻችን ቅዱሳን ነቢያት የተነገሩት ትንቢቶች እንድ እንድፈፀሙ ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ተሰደደች ይህም አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ በመንፈሰ እግዚአብሔር እየተቃኘ ቅድስት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ዐማኑኤልን ይዛ ወደ ግብጽ የመሰደዷን ነገር አስቀድሞ ተገልጾለት በምዕ ፲፱፥፩ ላይ፡- ✍️ "እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ" በማለት ከገነት የተሰደድነውን እኛን ወደ ቀደመ ርስታችን ሊመልሰን እንደመጣ አጠይቋል። ✍️ ጠላታችን ዲያብሎስን ከሰዎች ልብ አውጥቶ ለመስደድ፤ ክብር ይግባውና ወልደ እግዚአብሔር ልመናዋ ፈጥኖ በሚሰማላት "ደመና መፍጠኒት" በተባለች በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ ወደ ግብጽ የመሰደዱን ነገር አስቀድሞ ገልጾታል፡፡ ❤️ ይኸውም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ንጉሡ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊዉ ለዮሴፍ በሕልሙ ተገልጾለት "ተንሥእ ወንሣእ ሕፃነ ወእሞ ወጒየይ ውስተ ብሔረ ግብጽ" (ሕፃኑንና እናቱን ይዘኽ ወደ ግብጽ ሽሽ) ባለው ጊዜ ይኽ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ሊፈጸም ምልጃዋ ፈጥኖ በሚደርስ "ደመና መፍጠኒት" በተባለች በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ ወደ ግብጽ በኼደ ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ኹሉ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በነርሱ ዐድረው ያስቱ የነበሩ አጋንንት ኹሉ ሸሽተዋል፤ በመኾኑም በዚኽ የነገረ ማርያም አስተምህሮ እመቤታችን "ደመና መፍጠኒት" ወይም "ደመና ኢሳይያስ" ተብላ ተጠርታለች፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ለምን ወደ ግብፅ ሀገር ተሰደደ ✔️ሀ. ስደተ ቅዱሳንን ለመባረክ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደዱ የክርስትና ህይወት የመስቀል ላይ ጉዞ በመሆኑ ክርስቶስን አምነው ለተከተሉት ሁሉ በመከራና በስደት እንደሚያልፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ከዓለም ተመርጠው ለተከተሉት ደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር "እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ" በማለት ተናገረ 《ማቴ. 16፥24》 በዚህም ቃል መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ የተነሡ ክርስቲያኖች በብዙ መከራ ውስጥ አለፉ በበረሃ ተሰደዱ፣ በዱር በገደሉ ተቅበዘበዙ በሰይፉ ተመተሩ፣ በድንጋይ ተወገሩ፡፡ ዛሬም ቢሆን በእምነት የተሰደድን የተጨነቅን የምንጸልየው ስደትን ከኛ በፊት በሕጻንነቱ በቀመሰ ስደትን በሚያውቅ አምላክ ፊት ነው፡፡ ✔️ለ. ጣዖታተ ግብጽን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደደ ግብጽ ከነገሥታቶቿ ጀምሮ ጣዖትን የሚያመልኩ አህዛብ ነበሩ፡፡ እነዚህ ጣዖታት ደግሞ የበሬ፣ የላም፣ የአንበሳ፣ የወፍ ምስል አስቀርጸው ያመልኩ ስለነበር ለዚህም ከሙሴና ከአሮን ጸሎት የተነሳ የግብጻውያን የእጃቸው ሥራ መጥፋቱን፣ እግዚአብሔር በናቡከደነጾር አድሮ ወደ ግብጽ መምጣቱን፣ ጣዖታትን ማጥፋቱን የተነበየበት ከመሆኑ በላይ በዘባነ ማርያም ኅዙል /በማርያም ጀርባ ታዝሎ/ በፈጣን ደመና በተመሰለች ከእመቤታችን ጋር ወደ ግብጽ ተሰዷል፡፡ በዚህ ትንቢት ላይ እንደተገለጸው ግብጽ በጣዖታት የተሞላች በመሆኗ የጌታችን ስደት በግብጽ ያሉ ጣዖታትን ለማጥፋት እንዲሆን ተጠቅሷል፡፡ ✔️ሐ . ሰው መሆኑን ለመግለጽ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደደ ኢየሱስ ክርስቶስ አገሩን ሳይለቅ ከሄድሮስ ዓይን መሠወር ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን በአምላካዊ ጥበቡ ከሄሮድስ ዓይን ተሰውሮ ቢሆን ሥጋ መዋሐዱ ሰው መሆኑን አይገለጽም ነበር፡፡ በሄሮድስ ዓይን የማይታይ ከሆነ ሥጋን ሳይዋሐድ የተዋሐደ መስሎ የተገለጸ ሥጋና አጥንት የሌለው /ምትሐት/ ነው በተባለም ነበር፡፡ ከአዳም አካል አንድም ያልጎደለው ሙሉ ዳግማዊ አዳም መሆኑን እና የተዋሐደው ሥጋ የሚደማ የሚቆስል በሰይፍም ሆነ በጦር ቢወጋ ጉዳት የሚደርስበት ሰብአዊ ባሕርይ ያለው መሆኑን ለማስረዳት ስደተኛ ሆነ፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ከጠላቱ ማምለጥ የሚችለው ከጠላቱ ፊት ዞር በማለቱ እና በመሸሹ ስለሆነ ጌታም ከጠላቱ ከሄሮድስ ለመሸሽ ሰው እንደመሆኑ ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ✔️መ . ዲያብሎስን ለማሳደድ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደደ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከገነት ከወጣ በኋላ የእግዚአብሔርና የሰው ግንኙነት እየራቀ ሄደ፡፡ ይህን የፈጣሪና የፍጡር መራራቅ ያመጣው ዲያብሎስ ሲሆን በፈጣሪ መራቅ ፈንታ እርሱ መቅረብ ይፈልግ ነበር፡፡ ስለሆነም ፈጣሪው ከሰው ጓሮ ወደ ወጣበት የሰው ልጅ ሳይጠራ መምጣት ወይም መቅረብ ጀመረ፡፡ ዲያብሎስ የአዳምን ልጆች ተቆጣጠራቸው፡፡ ልባቸውን በፍቅረ ጣዖት ሸፍኖ አምልኮተ እግዚአብሔርን እንዳያዩ አደረጋቸው ብዙ የአዳም ልጆችም የአግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆን የሰይጣንን ፈቃድ ሲፈጽሙ ኖሩ፡፡ ጌታም "አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጪ ይጣላል" 《ዮሐ. 12፥31》 በማለት ሰይጣን ዓለሙን ተቆጣጥሮት እንደነበረ ይገልጻል፡፡ እግዚአብሔር ወልድ የሰውንሥጋ በተዋሐደ ጊዜ የፈጣሪና የፍጡር ግንኙነት እንደገና ተመሠረተ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አገሩን ለቆ በመውጣቱ ዲያብሎስን ከተቆጣጠረው ከሰው ልቡና አስወጣው ጌታ ከሄሮድስ ፊት እየራቀ ሲሄድ ዲያብሎስም ከሰው ፊት እየራቀ ሄደ፡፡ የጌታ ስደት በተዘዋዋሪ የዲያብሎስ ስደት ሆነ ጌታ የሚቀበለው መከራ ሁሉ ዲያብሎስን በርቀት የሚመታ መሣርያ ነበር፡፡ በመጨረሻም በመስቀል ላይ የሆነው የጌታ ሞት የዲያብሎስ ሞት ሆነ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን። አሜን !!!!!! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ ጥቅምት 01/02/2016 (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) የሲዳማ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ዋና መቀመጫ በሆነው በታላቁ ገዳም በ
+4
የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት  ትግበራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ ጥቅምት 01/02/2016 (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) የሲዳማ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ዋና መቀመጫ በሆነው በታላቁ ገዳም በሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም  መራሔ ድኅነት ሰንበት ትምህርት ቤት አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ለመተግበር የማስጀመሪያ መርሐ ግብር አከናውኗል። ወጥነት ያለው ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት  ተዘጋጅቶ በሲኖዶስ ጉባኤ ከጸደቀበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች በመተግበር ላይ ይገኛል።  እንደ መራሔ ድኅነት ሰንበት ትምህርት ቤት ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በያዝነው በ2016 ዓ .ም  የትምህርት ዓመት  ለመተግበር በዝግጅት ላይ የቆየ ሲሆን ለትግበራው የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት  መስከረም 26/ 2016 ዓ. ም በይፋ አስጀምሮ ። ትግበራው  ቅድመ መደበኛን  ጨምሮ  ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን  በአምስት ክፍል በመክፈል  እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ  ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የመማር ማስተማር የሚከናወን ይሆናል ። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።" ማቴ 5፡10 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 h
"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።" ማቴ 5፡10 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር ሊቀ ጳጳስ ዮናታን በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተልኪና ብራስላቭ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው። የሀገሪቱ መንግሥት ዩክሬን የ
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር ሊቀ ጳጳስ ዮናታን በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተልኪና ብራስላቭ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው። የሀገሪቱ መንግሥት ዩክሬን የምትመራበትን ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 109፣ 110፣ 161 እና 436 (2) በመጥቀስ በአራት ወንጀሎች ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት ክስ ይመሠርትባቸዋል። ጉዳዩን በአግባቡ ለመረዳት ሊቀ ጳጳሱ የተከሰሱባቸው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች ምን ምን እንደሚሉ አስቀድመን እንመለከታለን። አንቀጽ 109 በዐመጽ ለውጥ ለማምጣት ወይም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስወገድ ወይም በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የሚፈጸሙ ተግባራት አንቀጽ 110 – የዩክሬንን ሉዓላዊ የግዛት ወሰን ማለፍ ወይም ዳር ድንበሯን ለመለወጥ አስቦ መሥራት አንቀጽ 161 – ዘርን፣ ሃይማኖትን እና ዜግነትን መሠረት በማድረግ ልዩነት መፍጠር አንቀጽ 463 (2) – የጦርነት ፕሮፖጋንዳ መንዛት (ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን የኃይል ወረራ አይቀበሉም፣ ለሕጋዊነቱ ዕውቅና ሰጥተዋል፤ የሩሲያ ወታደሮችን አድንቀዋል) የሚሉ ናቸው። ... ማንበብ ይቀጥሉ ... 👇👇👇👇👇 https://eotc-gssu.org/a/የዩክሬን-ኦርቶዶክስ-ቤተ-ክርስቲያን-ሊቀ/ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮናታን እስር😼 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

ቅድስት አንስጣሲያ ሰማዕት ጥቅምት 1 ዕለተ ዕረፍቷ ነው። የሰማዕቷ ረድኤት በረከት ይደርብን! https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion/video/72887458127822226
ቅድስት አንስጣሲያ ሰማዕት ጥቅምት 1 ዕለተ ዕረፍቷ ነው። የሰማዕቷ ረድኤት በረከት ይደርብን! https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion/video/7288745812782222634?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7288000334784579078

"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፡12 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️You
"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፡12 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

“ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን” መቼም በየዘመኑ የማይሰማ ጉድ የለም። ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በየሀገሩ ይኖሩ የነበሩ አረማውያን እና አሕዛብ ክርስቲያኖችን ተከራክረው ማሸነፍ እንደማይ
“ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን” መቼም በየዘመኑ የማይሰማ ጉድ የለም። ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በየሀገሩ ይኖሩ የነበሩ አረማውያን እና አሕዛብ ክርስቲያኖችን ተከራክረው ማሸነፍ እንደማይቻላቸው ሲረዱ አንድ መላ ዘይደው ነበር። ይኸውም “ክርስቲያኖች የሰው ሥጋ ይበላሉ” ብለው በማስወራት ስለክርስትና የማያውቁ የሰው ልጆች እንዲርቁ በሌላ በኩልም ሃይማኖቱ ሕገ ወጥ ተብሎ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ማስደረግ ነበር። ይህም ሐዋርያት ወንጌልን ለመላው ዓለም ለማዳረስ በሚሰማሩባቸው ቦታዎች ሁሉ እንደ በግ እንዲታረዱ የሱ ምክንያት ነበረው። የአረማውያኑ አሳብ መከራውን ተሰቅቀው ሌሎች እንዲሸሿቸው ማድረግ ቢሆንም ውጤቱ ግን በተቃራኒው ነበር። ማንበብ ይቀጥሉ ... 👇👇👇👇👇 https://eotc-gssu.org/a/ክርስቲያኖች-መተት-አደረጉብን/ “ክርስቲያኖች መተት አደረጉብን” የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

"ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤" ዕብ 11፡35 እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደ
"ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤" ዕብ 11፡35 እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ! የእናታችን ረድኤት በረከት አማላጅነት በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይጠብቀን! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu