ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Nadi Aron 2 Traffic

Nadi Aron 2 Traffic

前往频道在 Telegram
1 147
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档

photo content

photo content

photo content
+6

photo content

photo content

photo content

+9
ህዝብ_1_የመንጃ_ፍቃድ_ፈተና_ባላንስ_አሰራር360p.mp410.62 MB

photo content
+5

ሲሆኑ ለዚህም ጥፋት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለጥፋቱ1 ነጥብ ተመዝግቦበት እስከ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት ተደንግጓል፡፡ በደረጃ ሁለት ላይ ተቀመጡ ጥፋቶች በመካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ጥፋቶች ሲሆኑ እነሱም የተሟላ የጭነት ማቀፊያ /እስፖንድ/ ሳይኖር ጭነት ጭኖ ማሽከርከር፣ ጥሩንባ ያለአግባብ መጠቀም፣ በመንገድ ላይ ተሽከርካሪ ማጠብና ማሳጠብ፣ በተከለከለ ስፍራና ሁኔታ ተሽከርካሪን ማቆም፣ ከመጠን በላይ የሆነ ድምጽ እያሰሙ ወይም በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጡ ማሽከርከር፣ በእግረኛ ላይ ውሃ መርጨት፤ ለእግረኛ ቅድሚያ መከልከል የመሳሰሉ ጥፋቶች ሲሆኑ  ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለጥፋቱ 2 ነጥብ ተመዝግቦበት እስከ 1,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡ ሌላው በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ጥፋቶች ከባድ ጥፋቶች ሲሆኑ ይህም የጉዞ ረድፍን ወይም መስመርን ሳይጠብቁ ማሽከርከር፤ ከተሽከርካሪው የመጫን አቅም በላይ ትርፍ ሰው መጫን፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገሩ ወይም መልእክት እየተጻጻፉ ወይም እያነበቡ ማሽከርከር፣ በጭነት ተሽከርካሪ በህግ ከተፈቀደው ውጪ ሰውን መጫን፣ የደህንት ቀበቶ ሳያስሩ ወይም ተሳፋሪዎች ማሰራቸውን ሳያረጋጋግጡ ማሽከርከር፣ ቀይ የትራፊክ መብራት መጣስ፣ በተከለከለ መንገድ ወይ አቅጣጫ ማሽከርከር፣ ጫት እየቃሙ ወይም አደንዛጅ እጽ ወስዶ ማሽከርከር የመሳሰሉ ጥፋቶች ሲሆኑ ለዚህም ጥፋት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ለጥፋቱ 3 ነጥብ ተመዝግቦበት እስከ 1,500 ብር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት በደንቡ ላይ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን አሽከርካሪው ለሁለተኛ ጊዜ እና ከዛ በላይ ያጠፋ እንደሆነ የቅጣት ነጥቦቹ እየተደመሩ የሚጣለውም ቅጣት ከፍ እያለ የሚሄድ ይሆናል፡፡ ሌላው በዚህ ደንብ ላይ ልዩ ደረጃ ያላቸው ጥፋቶችን የተቀመጡ ሲሆኑ እነዚህም ጥፋቶች ተሽከርካሪ በማሽከርከር በሰው ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከር፣ በህግ ከተፈቀደው የፍጥነት መጠን በላይ በፍጥነት ማሽከርከር፣ አፈር፣ አሸዋ ድንጋይና ተመሳሳይ ነገሮችን የሚመለከተው አካል ሳይፈቅድ በተሽከርካሪ ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ ማራገፍ፣ ጉዳት አድርሶ በቦታው ያለመቆም ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ሕክምና በመውሰድ እንዲታከም አለማድረግ የመሳሰሉ ጥፋቶችን እንደየ ጥፈቱ ቅለት እና ክብደት መጠን እንዲሁም የጥፋቱ ነጥብ ከ8 እስከ 21 ነጥብ  በሚሆንበት ጊዜ ከብር 1,500 አስከ 10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲሁም ከ6 ወር እስከ 1 አመት ከ6 ወር የሚደረስ እግደን ያካተተ ቅጣትን አካቷል፡፡ ደንቡ ሌሎች የደንብ መተላለፍ ጥፋቶችን አብዛኛውን ግዜ አሽከርካሪ ባልሆኑ ሰዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶችን ያካተተ ሲሆን ይህም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኙ በእጅ የሚገፋ ጋሪ በመንገድ ላይ መንዳት፣ በመንገድ ላይ እንስሳትን መንዳት፣ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል መጨመር ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጪ መቀመጫ መጨመር፣ ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ተሽከርካሪዎችን ወይም እግረኞችን የሚያውክ ቁሳቁስ ወይም ሸቀጥ በእግርኛ ወይም በተሽከርካሪ መንገድ ላይ ማስቀመጥ፣ የንግድ ሥራ መስራት፣ ያለፍቃድ የእግረኛ ወይም የተሽከርካሪ መንግድ መቆፈር፣ የአሽከርካር ብቃት ማረጋገጫ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ማሽከርከር፣ ከፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የጽሑፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና ማከናወን የመሳሰሉ ጥፋቶችን የሚያካትት ሲሆን እንደየ ጥፋቱ ቅለት እና ክብደት ከብር 100 እስከ ብር 20,000 በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስከጣ ተደንግጓል፡፡ ደንቡ በእግረኞች የሚፈጸሙ ጥፋቶችንም ያካተተ ሲሆን ተገቢ ጥንቃቄ ሳያደርጉ መንገድ ማቆረጥ፣ ለተሽከርከሪ የተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት መቆም ወይም መጓዝ፣ እግረኛ መንገድ በሌለበት መንገድ ቀኝ ጠርዝ ይዞ መጓዝ፣ ለእግረኛ መንግድ ተብሎ ከተከለለ መንግድ ውጪ መጓዝ፣ በብረትም ሆነ በግንብ ተለይተው የታጠሩ መንገዶች ዘሎ መንገድ ማቋረጥ፣ በጆሮ ማዳመጫ የተለያዩ ድምጾችን እያዳመጡ ማንገድ ማቋረጥ፣ ለእግረኛ ክልከል ነው የሚል ምልክት ባለበት መንገድ ወይም እግረኛ እንዳያቋርጥ በተከለከለበት የማሳለጫ ወይም የቀለበት መንገድ ማቋረጥ ከብር 100 እስከ በር 150 የሚያስቀጣ ነው፡፡ 👉ማጠቃለያ  በአጠቃላይ አሽከርካሪዎች፣ እግረኞች እና ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች የትራፊክ ሕግን በማክበር እና በሰው ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ በመቀነስ ረገድ ያለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንዲሁም ሕግን በመጣስ ከሚመጣ ተጠያቂነት እራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል፡፡ @ የ ኢ.ፊ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ** 👉መግቢያ በአገራችን የትራፊክ አደጋ በሰው ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል፡፡ ለዚህም የአሽከርካሪዎች እውቀት፣ ልምድ እና ሥነምግባር ማነስ፣ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ደረጃ፣ የመንገዶች ጥራት እና የእግረኞች አስተዋፅኦ እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ ይህንን አደጋ በተቻለ መጠን መቀነስ ይቻል ዘንድ የሕግ ማዕቀፍ ሊበጅለት የሚገባ በመሆኑ የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 ወጥቶ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ ይህ ጽሑፍ በደንቡ ላይ የተደነገገውን የመንግድ ትርፊክ ጠቅላላ ሥነ ሥርዓት እና ጥሰቶች ያሚያስከትሉትን ቅጣት በአጭሩ ይዳስሳል፡፡ 👉የመንገድ ትራፊክ ጠቅላላ ሥነ ሥርዓት  በቸልተኝነት ማሽከርከር አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ቸልተኝነትን ማስወገድ እና በጥንቃቄ ማሽከርከር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም በደንቡ አንቀጽ 5 የተመለከተ ሲሆን አሽከርካሪዎች በሚያሽከርከሩበት ወቅት የጊዜ እና የአየሩን ሁኔታ፣ የተሽከርካሪውን የቴክኒክ ብቃት፣ የመንገዱን አይነት እና በመንገዱ ላይ የሚተላለፈውን የተመላላሽ ሁኔታ እና ብዛት ሳይገምቱ በትምህርት ቤት፣ በመኖሪያ አከባቢ፣ በገበያ ቦታ፣ በሀይማኖት ተቋማት፣ በጤና ተቋም እና በሌላ በመደበኝነት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ሰው ተሰብስቦ በሚገኝበት ወይም ሊገኝ በሚችልበት አከባቢ ያለ ጥንቃቄ ወይም በህዝብ ላይ ጉዳት ሊያስከትል በሚችል ፍጥነት ወይም በመንገዱ ለሚተላለፍ ለሌሎች ደህንነት ሳያስቡ እና በሚገባ ሳይጠነቀቁ ወይም በከተማ ክልል ከከፍተኛ ወደ ዝቅተኛ የሚያደርጉትን የፍጥነት ለውጥ ወይም የሽግግር ዞን እና በኮንስትራክሽን ዞን የመንገድ ተጠቃሚዎችን ትራፊክ ደህንነት ከግምት ሳያስገቡ በቸልተኝነት ማሽከርከር የለባቸውም፡፡ 👉ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ምስል ማሽከርከር ልዩ ትኩረትን እና ጥንቃቄን ያሚጠይቅ ተግባር እንደመሆኑ እያሽከረከሩ ተንቀሳቃሽ ስልክን እና ምስሎችን መጠቀም አሽከርካሪዎችን ትኩረት በማሳጣት ለአደጋ ማጋለጡ እሙን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በደንቡ ክልከላ የተደረገበት ሲሆን ይኸውም ከአደጋ ጊዜ አገልግሎት ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም አሽከርካሪ  ተንቀሳቃሽ ስልክን ወይም ሬዲዮን በእጁ ይዞ እየተነጋገረ፣ አጭር የጽሑፍ መልእክት እየጻፈ፣ እየላከ ወይም እያነበበ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ማሽከርከር እንዲሁም ማንኛውም አሽከርካሪ ከጂፒኤስ አቅጣጫ ጠቋሚ ምስሎች በስተቀር ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በተሽከርካሪ ውስጥ እያየ ማሽከርከር እንደሌለበት በደንቡ አንቀጽ 6 ተደንግጓል፡፡ 👉የደህንነት ቀበቶ በሰው ሕይወት አካል እና ንብረት ላይ ያሚደርስን አደጋ እና ጉዳት ለመቀነስ የደህንት ቀበቶ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በመሆኑም በደንቡ አንቀጽ 7 መሰረት ማንኛውም አሽከርካሪ ከሞተር ብስክሌት በስተቀር የደህንነት ቀበቶ ሳያስር በመንገድ ላይ ማንኛውንም አሽከርካሪ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም አሽከርካሪ ከሞተር ብስክሌት በስተቀር ሌላ ተሸከርካሪን በሚያሽከርክርበት ወቅት በተሸከርካሪው የፊት እና የኋላ መቀመጫ ላይ የተሳፈሩ ሰዎች በሙሉ የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ማረገገጥ እንዲሁም ከሰባት አመት በታች የሆነን ህጻን በተሽከርካሪው ውስጥ ይዞ የሚጎዝ አሽከርካሪ በተሽከርካሪው የኋለኛው ክፍል ባለ መቀመጫ የህጻናት ደህንነት መጠበቂያ መሳሪያ  መታሰራቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ወይም ሀገር ውስጥ የሚገጣጠም ወይም የሚመረት ማንኛውም የሞተር ተሽከርካሪ የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶዎች የተገጠመለት መሆን እንዳለበት እና በጤና እክል ምክንያት የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶ ማስር የማይችሉ አሽከርካሪዎች ወይም ተሳፋሪዎች የሀኪም ማስረጃቸውን መያዝ እና በተጠየቁ በማንኛውም ጊዜ ለትራፊክ ተቆጣጣሪ የማሳየት ግዴታ እንዳለባቸው በድንጋጌ ተደንግጓል፡፡ 👉የመንገድ ቀኝ ይዞ ስለማሽከርከር አንድ አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ ቀኙን ይዞ ማሽከርከር እንዳለበት በደንቡ በአንቀጽ 10 የተደነገገ ሲሆን በደንቡ አንቀጽ 2 ስር የትራፊክ ተቆጣጣሪው ለትራፊክ ፍሰቱ አስገዳጅ ሆኖ ሲያገኘው ማንኛውም አሽከርካሪ የመንገዱን ግራ ጠርዝ ይዞ እንዲያሽከረክር ሊፈቅድ ወይም ሊያስገድድ እንደሚችል ከድንጋጌው መረዳት ይቻላል፡፡ 👉ተሽከርካሪን ማሽከርከር የሚከለከልበት ሁኔታ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ሁኔታ ለትራፊክ አደጋ በምክንያትነት የሚጠቀስ ሲሆን ይህንንም ለመከላከል ደንቡ በአንቀጽ 9 ላይ ማንኛውም አሽከርካሪ፡- አሰራሩ፣ እቃዎቹ እና ሁኔታው በተሽከርካሪ አሰራር ህግ ከተወሰነው ውጪ ከሆነ አመታዊ ምርመራ ተደርጎለት የቴክኒክ ብቃቱ ያልተረጋገጠ ከኋላ አንጸባራቂ ምልክት የሌለው መለያ ቁጥሩ በግልጽ የማይታይ ወይም የተቆረጠ ሰሌዳ የለጠፈ ወይም የፊት እና የኋላ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ያልለጠፈ በህግ ከተወሰነው በላይ ጢስ፣ እንፋሎት፣ ዘይት ወይም ነዳጅ የሚተፋ እና በሌሎች ተላላፊዎች እና በአከባቢ ላይ ጉዳት የሚያመጣ ወይም የሚያውክ ወይም በሚገባ ባለመታደሱ ወይም የቴክኒክ ሁኔታው በሚገባ ባለመጠበቁ ወይም ከአጫጫኑ ጉድለት የተነሳ በህግ ከተፈቀደው መጠን በላይ ድምጽ የሚያሰማ ተሸከርካሪ ማሽከርከር የለበትም፡፡ በተጨማሪም በተሽከርካሪው ውስጥ ከመጠን በላይ ማንኛውንም ድምጽ እያሰማ ወይም በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ማሽከርከር እንደሌለበት ተደንግጎ ይገኛል፡፡ 👉 ለእይታ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ስለ ማሽከርከር ሌላው በደንቡ አንቀጽ 11 መሰረት ማንኛውም አሽከርካሪ እይታውን የሚያውክ ሁኔታ ሲገጥመው ወይም በተወሰነ ርቀት ለማየት ባልቻለ ጊዜ የሚሄድበትን ነጠላ መስመር ለውጦ ወደ ሌላ መስመር ለመሻገር እንደማይፈቀድለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡ 👉የመንገድ አጠቃቀም ጥንቃቄዎች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከአሽከርካሪዎች በተጨማሪ ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎችም የየራሳቸው ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ይኸውም በደንቡ አንቀጽ 8 የተመለከተ ሲሆን በመንገድ የሚጠቀም ማንኛውም ሰው   በሕይወትም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ማድረግ   ለትራፊክ እንቅፋት ያለመሆን እና   አግባብነት ባለው አካል ካልፈቀደ በስተቀር በተሽከርካሪ ወይም በእግረኞች መንገድ ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ተግባራትን መፈጸም እንደሌለበት ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም በደንቡ አንቀጽ 79 መሰረት እግረኞች የእግረኛ መንገድ በሌለበት ወይም መንገድ ለማቋረጥ ካልሆነ በስተቀር በተሽከርካሪ መተላለፊያ መሄድ የተከለከሉ ከመሆኑም በተጨማሪ የግራ ጠርዝ ይዘው መሄድ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡ 👉ቅጣት የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ  በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶችን በመዘርዘር ያስቀመጠ ሲሆን ለጥፋቶቹም ደረጃዎችን አስቀምጧል፡፡ ቀላል የሆኑ ጥፋቶች ማለትም እንደ ተሽከርካሪን ያለአግባብ መጎተት፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ብስክሌት መንዳት፣ የተሟላ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ኪትና የእሳት ማጥፊያ ሳይኖር የንግድ ተሽከርካሪ ማሽከርከር፣ የሚበኑ ወይም የሚበተኑ ነገሮችን ጭኖ ያለአግባብ ማሽከርከር፣ በትራፊክ መብራ ወይም መስቀለኛ መንገድ ላይ በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ መስጠት፣ ከ13 አመት በታች የሆነን ህፃን ከአሽከርካሪው ጎን በሚገኘው አስቀምጦ ማሽከርከር የመሳሰሉ ጥፋቶች

photo content
+1

የመቀየሪያ /ሰርቪስ/ ጊዜቸው
+7
የመቀየሪያ /ሰርቪስ/ ጊዜቸው

photo content