ar
Feedback
Nadi aron 2 traffic channel

Nadi aron 2 traffic channel

الذهاب إلى القناة على Telegram

Driving safty first

إظهار المزيد
648
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
የባላንስ አሰራር ማብራሪያ አንድ አሽከርካሪ ባላንስ የሚሰራዉ ወደ ዳገት ለመሄድ ከቆመበት ሲነሳ ሲሆን የባላንስ ዋና ጥቅም ተሽከርካሪ ስትራፕ አድርጎ(ተንሸራቶ) እንዳይነሳ ለማድረግ ነዉ። ዳገት ላይ የቆመን መኪና ፍሬን አሽከርካሪዉ በሚለቅበት ጊዜ የመሬት ስበት ሀይል(Gravity) ተሽከርካሪዉን ወደኋላ እንዲሽከርከር ያደርገዋል። በዚህ ጊዜ ከኋላ በቅርብ ርቀት የቆመ መኪና ካለ የመጋጨት አደጋ ይከሰታል። በተመሳሳይ የተሽከርካሪዉ ፊት ወደ ቁልቁለት ዙሮ የቆመ መኪና ወደኋላ ለመነሳት ቢፈልግና ባላንስ ሳይሰራ ፍሬን ቢለቅ አሁንም በመሬት ስበት(Gravity) ምክንያት ተሽከርካሪዉ ወደፊት ሄዶ ከፊቱ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር ይጋጫል። ስለዚህ ባላንስ ይህን ሁኔታ ለመቅረፍ የሚተገበር ነዉ። የተሽከርካሪዉ ፊት ወደ ዳገት የዞረ ከሆነ እና አሽከርካሪዉ ወደ ፊት መነሳት ሲፈልግ አንደኛ ማርሽ በማስገባት ባላንስ ሰርቶ ይነሳል። ይህ የፊት ባላንስ ይባላል። የተሽከርካሪዉ ፊት ወደ ቁልቁለት ዙሮ አሽከርካሪዉ ወደኋላ ማለትም ከቁልቁለት ወደ ዳገት ለመነሳትና ለመሄድ ሲፈልግ የኋላ ማርሽ በማስገባት ባላንስ ሰርቶ ይነሳል። ይህ የኋላ ባላንስ ይባላል። ባላንስ እንዴት እንሰራለን? ወንበራችንን አስተካክለን የደህንነት ቀበቶ ካሰርን በኋላ ሞተር አስነስተን ጉዞ ለመጀመር ዝግጁ እንሆናለን,ዳገት ላይ ወደፊት የምንሄድ ከሆነ 1ኛ ማርሽ ወደኋላ የምንሄድ ከሆነ ደግሞ የኋላ ማርሽ አስገብተን የእጅ ፍሬን እናወርዳለን። በዚህ ሂደት በቀኝ እግራችን የእግር ፍሬን ፔዳልን እንረግጣለን በግራ እግራችን ደግሞ ፍሪሲዮን ፔዳልን እንረግጣለን። ከዚህ በመቀጠል የግራ እግራችንን ከፍሪሲዮን ፔዳል ላይ ማንሳት እንጀምራለን።ቢያንስ እስከግማሽ ድረስ ፔዳሉን ለቀቅ ስናደርግ የሞተር ድምፅ ይቀየራል በዚህ ጊዜ ፍሪሲዮን ፔዳሉን ባለበት ይዘን የቀኝ እግራችንን ከእግር ፍሬን ፔዳል ላይ ሙሉ ለሙሉ እናነሳለን። በዚህ ጊዜ ተሽከርካሪዉ ያለፍሬን በፍሪሲዮን ብቻ ይቆማል። በመሬት ስበት ሀይል ወደ ቁልቁለት ስትራፕ አያደርግም (አይንሸራተትም) ከዚህ በመቀጠል የቀኝ እግራችንን ነዳጅ መስጫ ፔዳል ላይ በማሳረፍ ነዳጅ እየሰጠን የግራ እግራችንን ከፍሪሲዮን ፔዳል ላይ ቀስ በቀስ ሙሉ ለሙሉ ስናነሳ ተሽከርካሪዉ ይነሳል(ይንቀሳቀሳል)። አማርድ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም አድራሻ - ኮልፌ 18 እና ቤተል ስልክ:-  0929905092/93/94

+7
86a44d4e-e55f-43de-8d7a-536fba6740c7-watermark.mp414.66 MB

+3

+2

+8

+9

+8

+8

photo content
+2

+8