ch
Feedback
ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

前往频道在 Telegram

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

显示更多

📈 Telegram 频道 ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  的分析概览

频道 ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  (@computer_android_tricks) 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 983 名订阅者,在 教育 类别中位列第 17 269,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 838 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 983 名订阅者。

根据 04 三月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -107,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 0%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 0 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH”

凭借高频更新(最新数据采集于 05 三月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 教育 类别中的关键影响点。

11 983
订阅者
无数据24 小时
-337 夊
-10730 夊
帖子存档
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 9 ደርሰዋል! የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሁኔታን አስመልክቶ በጤና ሚንስቴር በተሰጠ መግለጫ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሰዋል። መጋቢት 10 ከተያዙ
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 9 ደርሰዋል! የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሁኔታን አስመልክቶ በጤና ሚንስቴር በተሰጠ መግለጫ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሰዋል። መጋቢት 10 ከተያዙት ውስጥ ፡- - የ44 ዓመት ጃፓናዊ (ከዚህ ቀደም ከተያዙት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ የነበራቸው) - የ85 ዓመት እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊ (ከውጪ ከመጡበት ከየካቲት 23/2012 ዓ/ም ጀምሮ ራሳቸውን ለይተው ሲከታተሉ የነበሩ) - ሶስተኛው የ39 ዓመት ኦስትራዊ ዜጋ ሲሆን በመጋቢት 6/2012 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ተገቡ ናቸው። ሁለቱ ታማሚዎች በጥሩ ጤንነት ላይ ሲሆኑ የ85 ዓመት ዕድሜ ታማሚ ግን #ከባድ የሚባል ህመም ቢኖራቸውም አስፈላገው ክትትል እየተደረገላቸው ነው #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከቻይና በልጧል። በጣልያን በኮሮና ቫይረስ 3,405 መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ �
በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከቻይና በልጧል። በጣልያን በኮሮና ቫይረስ 3,405 መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

በጃፓን የተመረተው መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ውጤታማ መድሀኒት ሆኖ አግኝቼዋለሁ ስትል ቻይና ገለጸች፡፡ ዘጋርዲያን በዘገባው እንዳመለከተው አዲስ የጉንፋን ዝርያ ያለውን በሽታ ለማከም ጃፓን የምትጠቀመ
በጃፓን የተመረተው መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ውጤታማ መድሀኒት ሆኖ አግኝቼዋለሁ ስትል ቻይና ገለጸች፡፡ ዘጋርዲያን በዘገባው እንዳመለከተው አዲስ የጉንፋን ዝርያ ያለውን በሽታ ለማከም ጃፓን የምትጠቀመው መድሀኒት የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑን የቻይና ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ በጃፓን ፋጂ ፊልም የተመረተው “ፋቪፒራቪር” የተሰኘው መድሀኒት በሁዋንና ሼንዜን ከተሞች በ340 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ላይ ተሞክሮ ጥሩ ውጤት መታየቱ ተገልጿል፡፡ የጃፓን ብሄራዊ ቴሌቪዥን NHK የሚኒስትሩን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው የኮሮና ቫይረስ የነበረባቸው ሰዎች መድሀኒቱ ከተሰጣቸው ከቀናት በኋላ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ምንጭ፦ EBS TV #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

#COVID19 በጣሊያን የሚገኙ ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህወታቸው ማለፉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጸ፡፡ ከነዚህም መካከል የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ለአራት ቀናት ያህል በህክም
#COVID19 በጣሊያን የሚገኙ ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህወታቸው ማለፉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጸ፡፡ ከነዚህም መካከል የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ለአራት ቀናት ያህል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ያለፈው የ50 ዓመት ጎልማሳና የቢሮ ሰራተኛ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ ልጆቻቸው ጋር ጣሊያን የሄዱ አንድ ኢትዮጵያዊ እናትም ሰሞኑን እንደጉንፋን አድርጎ የጀመራቸው ህመም፣ የኮሮና ቫይረስ ሆኖ በመገኘት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከትናንት በስትያ ማረፋቸው ተገልጿል፡፡ #EBS #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

የኮሮና ተጠቂዎች 200,000 አልፈዋል! በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ200,000 አልፏል። ውድ ቤተሰቦቻችን የሚተላለፉ የጥናቃቄ መልዕክቶችን በእርጋታ
የኮሮና ተጠቂዎች 200,000 አልፈዋል! በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ200,000 አልፏል። ውድ ቤተሰቦቻችን የሚተላለፉ የጥናቃቄ መልዕክቶችን በእርጋታ ተግብሩ ፤ ሰው የሚበዛባት ቦታ አትገኙ ፣ የእጃችሁን ምፅህናም ጠብቁ ፣ ከሚያስነጥሱ ፣ ከሚያስሉ ሰዎች እንድትርቁ ይመከራል። በተጨናነቁ የትራንስፖርት አማራጮች ከመጠቀም ተቆጠቡ፣ ከሰዎች ጋር በእጅ አትጨባበጡ፤ የቫይረሱ ምልክት ከታየባችሁ ራሳችሁን አግልሉ፣ በ8335 ጥቆማ ስጡ። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

መጋቢት 8፣2012 የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ በ1 ዓመት ያህል ተራዘመ። ዩሮ 2020 በመጭው ሰኔ ወር ይካሄዳል ተብሎ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በ-#ኮሮና_ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት በ1ዓመት እ
መጋቢት 8፣2012 የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ በ1 ዓመት ያህል ተራዘመ። ዩሮ 2020 በመጭው ሰኔ ወር ይካሄዳል ተብሎ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በ-#ኮሮና_ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት በ1ዓመት እንዲራዘም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር መወሰኑን BBC አውርቷል። ማህበሩ ውድድሩ በ1ዓመት ያህል እንዲራዘም የወሰነው በቪድዮ ኮንፍረንስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ መሆኑን የወሬ ምንጩ ፅፏል። በተመሳሳይ ወሬ በዚህ ዓመት ሰኔ 2020 ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የኮፓ አሜሪካ በ1ዓመት እንዲራዘም እና ሐምሌ 2021 እንዲካሄድ የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ማህበር ወስኗል። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

❗የእስራኤል ሳይንቲስቶችም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ክትባትን አዘጋጅተው አጠናቀዋል። በመጪዎቹ ቀናት ለዓለም ህዝብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክትባቱ ግን አገልግሎት ላይ እስኪውል ድረስ
❗የእስራኤል ሳይንቲስቶችም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ክትባትን አዘጋጅተው አጠናቀዋል። በመጪዎቹ ቀናት ለዓለም ህዝብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክትባቱ ግን አገልግሎት ላይ እስኪውል ድረስ ጥቂት ወራት እንደሚወስድ ET አስነብቧል። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 5 ደረሱ! በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተያዙ ሰዎች አሁን ላይ 5 መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናግረዋል። አምስተኛው ግለሰብ ከዱባ
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 5 ደረሱ! በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተያዙ ሰዎች አሁን ላይ 5 መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናግረዋል። አምስተኛው ግለሰብ ከዱባይ የመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል። ⭐በመንግስት የተላልፉ ውሳኔዎች፦⭐ • ሰፋ ያለ ቁጥር ያላቸው ስብሰባዎች ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት እንዳይካሄዱ • የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሰፋ ያሉ የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ለሁለት ሳምንታት እንዳይካሄዱ • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላ ሀገሪቱ ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ • እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ሳይወጡ እና ሳይገቡ ክትትል እየተደረገላቸው እንዲቆዩ • በእምነት ተቋማት የሚደረጉ ሰፋ ያሉ የአምልኮ ሥርዓቶች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንዲቀንሱ የሚደረግበትን አግባብ የሃይማኖት መሪዎች እንዲያመቻቹ ተጠይቋል፡፡ #PMOEthiopia #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

ህዝባችን ሆይ ተረጋጉ አትፍሩ አትደንግጡ! ለምን ካላችሁ እንሆኝ . 1. ኮሮና ቢይዛችሁም 97% የመዳን እድል ስላለ . 2. ኮሮና እኛ ካረዳነው በስተቀር ቀጥታ ካየሩ ስለማይዘን! ይህ ማለት ኮሮና ወይ በእጃችን አምጥተን አፍንጫ፣ አፍ፣ አይነችንን ካልነካን ወይም ደግሞ ከሚያስነጥስ ሰው 1 ሜትር ክልል ውስጥ ካልተገኘን ስለማይዘን . 3. ፍህራትና ድንጋጤ ላላስፈላጊ ሌላ ወጪ፣በሽታ ወይም አደጋ ስለሚያጋልጥ! ለምሳሌ ብዙ ሰዋች ለኮሮና ምንም የማይጠቅም አልኮሆል የሌለው እጅ ማፅጃ (non alcohol based sanitizer) በብዙ ብር እየገዙ መሆኑ። . 4. በፍርሃት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ስንሞክር መደረግ ያለባቸውን ጥቂት ነገሮች ሊረሱ ስለሚችል . ስለዚህ ምን እናድርግ . 1. ግዴታ ካልሆነ በቀር ህዝብ ከሚሰበሰብባቸው ቦታዎች መራቅ! የተጨናነቀ ታክሲ ፣ ባስ ፣ ጭፈራ ቦታዎች ፣ ስብሰባዎች ፣ የእምነት ወይም ፀሎት ስብሰባዎች ፣ ሰላማዊ ሰልፍችና የመሳሰሰሉት . 2. አዘውትረን እጆቻችንን በውሀና ሳሙና ቢያንስ ለ20 ሰከንድ መታጠብ! በተለይም የበር መያዣ ፣ የቧንቧ እጄታ ፣ ማብሪያ መጥፊያ ፣ ሳንቲም ብር ከነካን በኋላ (አልኮል ያለው እጅ ማፅጃ ወይም sanitizer መጠቀም ይቻላል) . 3. የሚያስሉ ወይም የሚያስነጥስ ሰው ከ2 ሜትር በላይ መራቅ! . 4.ሳል፣ትኩሳት፣ሰውነት መዛል እንዲሁም ትንፋሽ ማጠር ካለን ከሌሎች ንክኪ እራሳችንንና የምንጠቀምበትን እቃ ለይተን ተገቢውን ህክምና ለማግኘት ለሚመለከተው በማሳወቅ የምንወዳቸውንና ቤተሰቦቻችንን መታደግ . 5. መጨባበጥ ፣ መሳሳም ማቆም። የሚያስነጥስ ወይም የሚያስል ሰው በክርኑ አፍ አና አፍንጫውን መሸፈን . 6. ሁሉም ሰው መረጃ ከታመነ ምንጭ ብቻ ቢወስድና መረጃው ሌላቸቸው እናቶች ፣ አባቶች ፣ ወንድም እህቶች በማድረስ ቢተባበር እላለሁ። . ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ Hint from ✅ የዶክተር አለ #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

ከመግለጫው የተወሰደ፦ - ከጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ንክኪ የመበራቸው 117 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። - ምርመራ ከተደረገላቸው እና ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ካላቸው ግለሰቦች መካከል
ከመግለጫው የተወሰደ፦ - ከጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ንክኪ የመበራቸው 117 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። - ምርመራ ከተደረገላቸው እና ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ካላቸው ግለሰቦች መካከል 3 ግለሰቦች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል። - በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የ44 እና የ47 አመት የጃፓን ዜና ሲሆኑ አንደኛው ደግሞ የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ ነው። - ሁሉም አዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ እና ቫይረሱ ከተገኘበት የመጀመሪያ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ናቸው። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

በኢትዮጵያ ከጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተገልጿል!!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከያ መንገዶች። #ኮሮና_ቫይረስ #Ethiopia #Covid_19 #coronavirus
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከያ መንገዶች። #ኮሮና_ቫይረስ #Ethiopia #Covid_19 #coronavirus

አጫጭር መረጃዎች፦ - ኢትዮጵያና ሱዳን የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝን ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ አፍሪካ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የሚግኝባቸው ሀገራት 17 ደርሰዋል። - በዛሬው ዕ
አጫጭር መረጃዎች፦ - ኢትዮጵያና ሱዳን የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝን ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ አፍሪካ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የሚግኝባቸው ሀገራት 17 ደርሰዋል። - በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ 8 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ሪፖርት በመደረጉ በሀገሪቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 24 ከፍ ብሏል። - በDRC ደግሞ ዛሬ ተጨማሪ 1 የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት ተደርጓል። በዚህም DRC ውስጥ ያሉ የኮሮና ተጠቂዎች 2 ሆነዋል። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

‍ #ለጥንቃቄ #አንብባችሁ #ለሌሎችም #አስተላልፉ ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል! ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃ በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ! ᐸ ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡ ᐸ ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡ ᐸ በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! ᐸ የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡ ❶. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡ ᐸ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡ ᐸ አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡ ❷. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡ ❸. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ ❖በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው? ①. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል:: ②. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! ❖ በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል? ❶. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ᐸ ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ᐸ ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡ ❷. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡ ❸. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ፡፡ #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት ደረሰበት.....! - ከኹለት ሳምንት በፊት በኢትዮ ቴሌኮም የውስጥ ሲስተሞች ላይ የራንሰምዌር (Ransomeware) ጥቃት መድረሱን፣ ሠራተኞችም የኢ-ሜይል ልውውጣቸውን
ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት ደረሰበት.....! - ከኹለት ሳምንት በፊት በኢትዮ ቴሌኮም የውስጥ ሲስተሞች ላይ የራንሰምዌር (Ransomeware) ጥቃት መድረሱን፣ ሠራተኞችም የኢ-ሜይል ልውውጣቸውን መጠባበቂያ ሳያስቀሩ ከዋና ሲስተም ጋር እንዳያገናኙ እና ይህንን ካደረጉ ልውውጦቻቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አርብ የካቲት 10/2012 ለድርጅቱ ሠራተኞች የተላኩ መልዕክቶች አረጋግጠዋል። - ሲ.አር.ኤም (Customer Relationship Management Software/CRM) ከተባለው እና የደንበኛ መረጃዎችን ከሚይዘው ሲስተሙ ውጪ ያሉ የቴሌኮሙ ስርአቶች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። More https://telegra.ph/አዲስ-ማለዳ-03-03 [ አዲስ ማለዳ ] ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

ቲዊተር ሰራተኞቹን ወደ መስሪያቤት እንዳይመጡ ሊያደርግ ነው..... ቲዊተር የድርጅቱ ሰራተኞች ስራቸውን ከቤት ሆነው እንዲሰሩ አድርጓል፡፡ ድርጅቱ ይህን ያደረገው እየስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ
ቲዊተር ሰራተኞቹን ወደ መስሪያቤት እንዳይመጡ ሊያደርግ ነው..... ቲዊተር የድርጅቱ ሰራተኞች ስራቸውን ከቤት ሆነው እንዲሰሩ አድርጓል፡፡ ድርጅቱ ይህን ያደረገው እየስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ነው ማለቱ ተሰምተል፡፡ ይህ ደግሞ በሆንግኮንግ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ለሚገኙ ሰራተኞቹ ግዴታ ጭምር መሆኑን ነው ያሳወቀው፡፡ ድርጅቱ በርቀት ሆኖ መስራት ለማስለመድ ሙከራ እያደረገ ይገኛል፡፡ በቅርብ ጊዜም ኢትዮጵያን የጎበኘው የቲዊተር ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃክ ዶርሲ በአፍሪካ ከአራት እስከ ስድስት ወር ለመቆየት እንዳሰበ አስታውቆ ነበር፡፡ [ BBC] ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

ኢትዮ ቴሌኮም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ዝርዝርን ይፋ አደረገ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሀይወት ታምሩ ተቋሙ በመደበኛ ብሮድባንድ ማሻሻያ ላይ ሲያደርገው የነበረውን ስራ ማጠናቀቁን አስታውቋል። ይሄን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ማሻሻያ ይፋ ማድረጊያ መርሀ ግብር ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለተሻለ ምርታማነት በሚል መሪ ቃል በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል። ተቋሙ ማሻሻያውን ማጠናቀቁን አስመልክቶም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል። በማሻሻያው መሰረትም ለመኖርያ ቤት 69 በመቶ ቅናሽ ፣ ለድርጅቶች 65 በመቶ፣ VPN ደግሞ 72 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል። ለመኖርያ ቤት ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት 978 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 499 ብር፣ ለ ሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 1768 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 699 ብር ፣ ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት ደግሞ ከ3191 የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 1099 ብር እንዲቀንስ መደረጉ ተገልጿል። ለድርጅቶች ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት 1369 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 709 ብር፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 2475 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 999 ብር፣ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 4468 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 1575 ብር እንዲቀንስ ተደርጓል። ለድርጅት ደንበኞች የብሮድባንድ ኢንተርኔት ቪ ፒ ኤን ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት 1809 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 499 ብር፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 2846 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 899 ብር ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 5137 ብር የነበረው ወርሀዊ ክፍያ ወደ 1439 ብር እንዲቀንስ ተደርጓል። ለአዲስ ደንበኞች የብሮድባንድ ኢንትርኔት የአገልግሎት ማስገቢያና የተቀማጭ ገንዘብ (deposit) ሙሉ በሙሉ የተነሳ ሲሆን ለነባር ደንበኞች ደግሞ የተቋረጠ አገልግሎት ማስቀጠያ ከክፍያ ነፃ እንዲሆን ተደርጓል። ማሻሻያው በዋጋ ብቻ ሳይሆን በፍጥነትም ጭምር መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል። ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለመኖርያ ቤት የ 3 በመቶ ፍጥነት ፣ ለ ድርጅቶች 4 በመቶ ፍጥነት ይጨምራል ሲሉ ተናግረዋል። በመርሀግብሩ ላይ እንደተገለጸው በአንድ ሀገር የ 10 በመቶ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እድገት ወይም ስርፀት የ 1 ነጥብ 38 በመቶ አጠቃላይ ምርታማነትና እድገት ያመጣል። በሔኖክ አስራት የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━