ch
Feedback
ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

前往频道在 Telegram

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

显示更多

📈 Telegram 频道 ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  的分析概览

频道 ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  (@computer_android_tricks) 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 983 名订阅者,在 教育 类别中位列第 17 269,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 838 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 983 名订阅者。

根据 04 三月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -107,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 0%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 0 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH”

凭借高频更新(最新数据采集于 05 三月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 教育 类别中的关键影响点。

11 983
订阅者
无数据24 小时
-337 夊
-10730 夊
帖子存档
ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አግልግሎቱ ላይ ማሻሻያ እና የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል። በዚህም ለግል ተጠቃሚዎች እስከ 69 በመቶ፣ ለVPN አግልግሎት እስከ 72 በመቶ እንዲሁም ለኢንተ
ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አግልግሎቱ ላይ ማሻሻያ እና የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል። በዚህም ለግል ተጠቃሚዎች እስከ 69 በመቶ፣ ለVPN አግልግሎት እስከ 72 በመቶ እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች እስከ 65 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ማድረጉን ነው ያስታወቀው። #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

‍ ‍ #በኢ_ሜይል አካውንቶች ላይ የሚቃጡ የመረጃ ጥቃቶች ምን ዓይነት ናቸው? #እንዴትስ_መከላከል_እንችላለን ? ✏️ፊሺንግ #Phishing አንዱ የሳይበር ጥቃት ዓይነት ሲሆን የኢ-ሜይል አድራሻችንን መሠረት በማድረግ ለሚፈፀም የጥቃት ዓይነት የተሰጠ ሙያዊ ቃል ነው፡፡ የፊሺንግ ጥቃት ወንጀለኞች ግላዊ የሆኑ መረጃዎቻችንን ለመስረቅ ወይም ላልተገባ ዓላማ ለማዋል የሚጠቀሙበት የማጭበርበሪያ መንገድ ነው፡፡ ለምሣሌ የባንክ የሒሳብ ቁጥራችንን ወይም የይለፍ-ቃሎቻችንን ለመመንተፍ በኢ-ሜይል አድራሻችን የሚላኩ የማደናገሪያ መልዕክቶች ናቸው፡፡ ✏️በኢ-ሜይል አድራሻ የሚላኩ የፊሺንግ መልዕክቶች ለተጠቃሚዎች እውነተኛ የሚመስሉ፤ ተጠቃሚውን ከተለያየ ዓይነት የጥቃት ሥጋት ለመጠበቅ ወይም ለመርዳት እንደሆነ የሚገልፁ እና አንዳንድ ጊዜም ተጠቃሚዎች ሎተሪ ወይም ነጻ የትምህርት ዕድል አሸናፊ እንደሆኑ የሚያበስሩ በመምሰል የማታለል ዓላማ ያላቸው ይዘቶች ናቸው ✏️የመረጃ መንታፊዎቹ ያዘጋጁትን አገናኝ #Link ተጠቃሚዎች እንዲከፍቱ በማግባባት እውነተኛ የዕድሉ አሸናፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በሚመስል አግባብ አካውንታቸውን እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃል እንዲያስገቡ በመጠየቅ ጥቃት ለማድረስ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡ የፊሺንግ ጥቃት ፈጻሚዎች ዋና ዓላማ የግለሰቦችን የባንክ ቁጥር ለመመንተፍ ወይም ግላዊ መረጃዎችን ለሌሎች አሳልፎ ለመሸጥ በማቀድ የሚፈጸም ህገ-ወጥ ተግባር ነው፡፡ ✏️የፊሺንግ ጥቃትን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ⚙የርዕሰ ጉዳዩ ትክክለኛነት መረጋገጥ /Subject Line and Tone/ #አብዛኛውን ጊዜ ከምንጠቀምባቸው ባንኮች ወይም የፋይናንስ ተቋማት የተላኩ የሚመስሉ የፊሺንግ መዝባሪዎች መልዕክቶች በኢ-ሜይል አድራሻዎቻችን ተልከው እናገኛለን፡፡ በዚህ ወቅት መልዕክቶቹን ከመክፈታችን በፊት ትክክለኛ አድራሻ መሆኑን ወደ ባንኮቹ ወይም ፋይናንስ ተቋማቱ በመደወል ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ አንዳንድ የመልዕክት አድራሻዎች የትክክለኞቹን የፋይናንስ ተቋማት ስያሜ በተወሰነ ፊደል ለውጥ በማድረግ በቀላሉ ለማታለል የሚሞክሩ ናቸው፡፡ ⚙አባሪ /Attachments/ #የፊሺንግ ጥቃት ፈጻሚዎች ኢ-ሜይል አካውንታችንን ለመስረቅ የኛን ትኩረት የሚስቡ አባሪ ፋይሎችን የሚልኩልን ሲሆን ፋይሎቹን በምንከፍታቸው ጊዜ የተላኩልን መልዕክቶች ለህገወጥ ተግባር ሆን ተብለው የተሰሩ ማጥመጃዎች በመሆናቸው ኮምፒውተራችንን ለጉዳት ያጋልጣሉ፡፡ በመሆኑም ሁሉም አባሪዎች ጠቃሚ መረጃዎች ናቸው ብሎ ማሰብ ተገቢ አለመሆኑንና የሚላክልንን መልዕክት ከምናውቀው ትክክለኛ አካል የተላከ መሆኑን መረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ ⚙አገናኝ /Link/ #ሁልጊዜም በኢ-ሜይል ለሚላኩ አገናኞችን በምንከፍትበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ የተላኩልን ሊንኮች ትክክለኝነታቸውን ለማረጋገጥ ሊንኩን በቀጥታ በድረ-ገጽ ላይ በመተየብ እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ አንዳንድ የፊሺንግ ሊንኮች “Click here”፣ “Preview document” ወይም “Sign In” የሚሉ እንድንከፍት የሚጋብዙ ቃላትን ይጠቀማሉ፡፡ ⚙ስልክ ቁጥሮች /Phone Numbers/ #በኢ_ሜይል የሚላኩ የማረጋገጫ ስልክ ቁጥሮችን መጠራጠር ተገቢ ነው፡፡ የተላከልን ስልክ ቁጥሩ ትክክለኛነቱን ከባንክ ደብተር ላይ ከሚገኝ አድራሻ በመውሰድ ደውለን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ አለ በለዚያ በኢ-ሜይል የቀረበልንን መልዕክት በኢ-ሜይል አድራሻችን በተላከ ስልክ ቁጥር ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ከደወልን አጥፊዎች አስቀድመው ያዘጋጁት ቁጥር ከሆነ በሚፈልጉት መንገድ መረጃ በመስጠት ለጥቃት ልንጋለጥ ስለምንችል ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ═══════════════ 📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!! 📢: @Computer_Android_tricks ╚═════📌Share📌════╝

‍ ✍የፌስቡክ ኩባንያ የቲዊተርና ኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገጾች የሳይበር ጥቃት ማስተናገዳቸው ተሰማ ✍አዲስ አበባ ጥር 30/2012፡ የግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ፌስቡክ በቲዊተርና የኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ትናንት አርብ ለአጭር ጊዜ በመረጃ በርባሪዎች ቁጥጥር ውሎ እንደነበር ተነገረ። ✍አወርማይን /OurMine/ የተባለው የመረጃ በርባሪዎች ቡድን በኩባንያው የኢንስታግራምና የቲዊተር ገጾች ላይ "ፌስቡክ እራሱ ተሰብሮ ይገባበታል" በማለት ጽሁፍ አስፍሮ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡ የበይነ-መረብ መረጃ ጠላፊ ቡድኑ እንዳለው በፌስቡክ ላይ የሰነዘረው ጥቃት በኢንተርኔት ላይ ያለን ለጥቃት ተጋላጭነት ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ነው። ✍ በፈረንጆቹ ጥር ወር ላይም ቡድኑ ተመሳሳይ ድርጊትን በአሜሪካ እግር ኳስ ቡድኖች ገጾች ላይ ፈጽሞ ነበር። ቡድኑ በፌስቡክ የቲዊተር ገጽ ላይ "ሰላም፤ አወርማይኖች ነን። ፌስቡክ በደህንነት አስተማማኝነት ከትዊተር የተሻለ ቢሆንም ከመሰበር አያመልጥም" የሚል መልዕክትን አስፍሮ ነበር፡፡። ✍አወርማይን ቀደም ባለው ጊዜ የትልልቅ ተቋማትንና የታዋቂ ግለሰቦች አካውንቶች ላይ ጥቃት በመፈጸም የሚታወቅ መቀመጫው ዱባይ ውስጥ እንደሆነ የሚነገርለት የበይነ-መረብ በርባሪ ቡድን ነው። ቡድኑ እንደሚለው የሚፈጽማቸው ጥቃቶች በበይነ መረብ ላይ ያለውን ደካማ የደህንነት አጠባበቅን ለማጋለጥ ነው። አሁን ላይ በመረጃ ጠላፊዎች ተሰብረው የነበሩት የፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ወደነበሩበት መመለሳቸው ተገልጿል። ምንጭ፡-BBC #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

በአዲስ አበባ ተግባራዊ የተደረገው የLte advance 4G ኔትወርክ አገልግሎት ከቀድሞዎቹ በምን ይለያል? ኢትዮ ቴሌኮም የLte advance 4G አገልግሎት በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል
በአዲስ አበባ ተግባራዊ የተደረገው የLte advance 4G ኔትወርክ አገልግሎት ከቀድሞዎቹ በምን ይለያል? ኢትዮ ቴሌኮም የLte advance 4G አገልግሎት በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ተግባራዊ ያደረገው የLte advance 4G አውታረ-መረብ (network) አብዛኛው ማህበረሰብ እየተጠቀመበት ካለው ከሁለተኛ ትውልድ (2G) ፣ ከሦስተኛው ትውልድ (3G) እና ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ከሆነው ከአራተኛው ትውልድ (4G) በምን ይለያል? ያንብቡት ☟☟ https://telegra.ph/INSA-02-04 [ INSA ] ═══════════════ 📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!! 📢: @Computer_Android_tricks ╚═════📌Share📌════╝

​​📌ቀለል ባለ መንገድ ኮምፒውተርን ወይንም☛ላፕቶፕን ፍላሽ ዲስክ ተጠቅመን አዲስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እንዴት መጫን እንደምንችል ነው። 🔸🔸ማዘጋጀት ያለብን ነገሮች🔸🔸 1. 4 ጂቢ ወይንም ከዛ በላይ የሆነ ፍላሽ ዲስክ 2. Rufus የተሰኘ Software 3. መጫን የምንፈልገውን በ ISO format የተዘጋጀ ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም( WINDOWS XP 7,8,8.1 or 10) ስንገዛ ወይም ስናወርድ እንደዛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። 4. ይሄን ስራ የምንሰራበት ላፕቶፕ 🔹🔹አስራሩ እንዴት ነው?🔹🔹 ▪️Rufus የሚባለው ፕሮግራም አሉ ከሚባሉ ለዚ ስራ የሚያገለግሉ ቀለል ያለ እና ፈጣን ስለሆነ ለዛሬ በሱ እንዴት እንደምንሰራ እናያለን:- ▪️ያዘጋጀነውን 4ጂቢ ፍላሽ ዲስክ ኮምፒተራችን ላይ እንሰካለን።▪️ 1.ፕሮግራሙን ዳውንሎድ ካረግን በኀላ መጫን ሳያስፈልገን ራይት ክሊክ አርገን ራን አስ አድሚንስትሬተር ብለን እንከፍተዋለን ከዛ አብዴት ሲጠይቅ no እንመርጣለን። 2.ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኅላ ፍላሽ ዲስኩን ዲቫይስ የሚለው ሜኑ ተጭነን እንመርጠዋለን። 3.ከዛ iso image የሚለው ቦታ ሄደን ቅድም ይዘጋጀነውን የዊንዶውስ ሶፍት ኮፒ አስገብተን ድራይቭ ሌተሩን እንመርጣለን። ✏️ ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር አውቶማቲካሊ ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም ማለት ነው። 4. ከዛ start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል የምንፈልግው ፍይል ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን። እሱን ካረጋገጥን በኅላ ok እንለዋለን። 5. በስተመጨረሻ ፕሮግራሙ የዊንዶውን ሴትአፕ ወደ ፍላሽ ዲስኩ ኮፒ በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል። ✏️ ፕሮግራሙ ኮፒ አድርጎ ሲጨርስ close የሚለውን በተን ክሊክ መጫን የምንፈልገው ኮምፒተር ላይ ወስደን እንጠቀማለን። 🔸🔸በUSB ኮምፒውተሮን እንዴት ፎርማት ማረግ ይችላሉ🔸🔸 1.ኮምፒውትሮን turn off ያርጉ 2.ቅድም ከላይ ያዘጋጀነውን USB ፍላሽ አስገብትው turn on ያድርጉ። 3.F2 ወይም F12 ን (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ይለያያል) ይጫኑ እና ቀጣይ ትዕዛዙን ይከተሉ። 4." install windows " የሚለው ሲመጣልዎ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ ከዛም next ን ክሊክ ያድርጉ። 5."Please read the license terms" የሚለው ሲመጣልዎ "I accept the license terms" የሚለውን ክሊክ ያርጉ 6."Which type of installation do you want?" ሲልዎት Custom የሚለውን ይምረጡ። 7."Where do you want to install Windows?" የሚለው ፔጅ ላይ "Drive options" የሚለውን ክሊክ 8.ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን "partition" ይምረጡና "format" ላይ ክሊክ ያድርጉ 9.ፎርማት አድርገው ሲጨርሱ "next" ላይ ክሊክ ያድርጉ 10. ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን (instruction ) በመከተል window install ያድርጉ። ═══════════════ 📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!! 📢: @Computer_Android_tricks ╚═════📌Share📌════╝

​​💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል? ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ ➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ➢ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን:: ❖ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል .... ☛ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡ ❒የ F1 ጥቅሞች ► ከ”Windows ቁልፍ (button) ጋር በጋራ ስንነካው help menuን ያመጣልናል፡፡ ► Excel እና Word በምንጠቀምበት ወቅት ከ Control ጋር በጋራ ስንነካው Hides or displays ribbon menu ያደርግልናል፡፡ ❒የ F2 ጥቅሞች ◕ Alt + Ctrl + F2 - opens Document Library in Microsoft Office ◕ Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer ❒የ F3 ጥቅሞች ► Opens search feature in Windows Explorer ► Shift + F3 - lets you change from lowercase to uppercase to all caps in Word ► Opens find feature in Firefox and Chrome ❒የ F4 ጥቅሞች ◕ Alt + F4 closes window ◕ Places the cursor in the address bar in Explorer ❒የ F5 ጥቅሞች ► Starts slideshow in Power Point ► Refreshes Internet browser pages ► Opens Find and Replace in Microsoft Office ❒የ F6 ጥቅሞች ◕ Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word ◕ Ctrl + F6 lets you easily switch between Word documents ❒የ F7 ጥቅሞች ► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word ► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word ❒የ F8 ጥቅሞች ◕ In Excel, enables extend mode for arrow keys ◕ Enables safe mode in Windows ❒የ F9 ጥቅሞች ► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word ► Updates fields in Word ❒የ F10 ጥቅሞች ◕ Opens menu bar ◕ Ctrl + F10 maximizes window in Word ◕ Shift + F10 does the same thing as a right click ❒የ F11 ጥቅሞች ► Exits and enter full screen mode in browsers ► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel ❒የ F12 ጥቅሞች ◕ Opens Save As in Word ◕ Shift + F12 saves Word document ◕ Ctrl + F12 opens Word document ❖ ውድ የ Tech-Zone ቤተሰቦች ድጋፋችሁን ቻናላችንን ሟር በማድረግ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                  👇🏾👇🏾👇🏾 @Computer_Android_tricks        ━ ••• ━ •••

💻የኮምፒውተር #ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸው ምንድነው? ❖ከ F1-F12 በተኖች ጥቅም ሰፋ አድርገን እናቀርብላችኋለን። ❒▩⇒ #150 👍Like
💻የኮምፒውተር #ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸው ምንድነው? ❖ከ F1-F12 በተኖች ጥቅም ሰፋ አድርገን እናቀርብላችኋለን። ❒▩⇒ #150 👍Like

​​💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል? ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ ➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ➢ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን:: ❖ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል .... ☛ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡ ❒የ F1 ጥቅሞች ► ከ”Windows ቁልፍ (button) ጋር በጋራ ስንነካው help menuን ያመጣልናል፡፡ ► Excel እና Word በምንጠቀምበት ወቅት ከ Control ጋር በጋራ ስንነካው Hides or displays ribbon menu ያደርግልናል፡፡ ❒የ F2 ጥቅሞች ◕ Alt + Ctrl + F2 - opens Document Library in Microsoft Office ◕ Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer ❒የ F3 ጥቅሞች ► Opens search feature in Windows Explorer ► Shift + F3 - lets you change from lowercase to uppercase to all caps in Word ► Opens find feature in Firefox and Chrome ❒የ F4 ጥቅሞች ◕ Alt + F4 closes window ◕ Places the cursor in the address bar in Explorer ❒የ F5 ጥቅሞች ► Starts slideshow in Power Point ► Refreshes Internet browser pages ► Opens Find and Replace in Microsoft Office ❒የ F6 ጥቅሞች ◕ Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word ◕ Ctrl + F6 lets you easily switch between Word documents ❒የ F7 ጥቅሞች ► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word ► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word ❒የ F8 ጥቅሞች ◕ In Excel, enables extend mode for arrow keys ◕ Enables safe mode in Windows ❒የ F9 ጥቅሞች ► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word ► Updates fields in Word ❒የ F10 ጥቅሞች ◕ Opens menu bar ◕ Ctrl + F10 maximizes window in Word ◕ Shift + F10 does the same thing as a right click ❒የ F11 ጥቅሞች ► Exits and enter full screen mode in browsers ► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel ❒የ F12 ጥቅሞች ◕ Opens Save As in Word ◕ Shift + F12 saves Word document ◕ Ctrl + F12 opens Word document ❖ ውድ የ Tech-Zone ቤተሰቦች ድጋፋችሁን ቻናላችንን ሟር በማድረግ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                  👇🏾👇🏾👇🏾 @Computer_Android_tricks        ━ ••• ━ •••

🇪🇹 በብዙ የቻናላችን ተከታታዮች ጥያቄ መሰረት የተዘጋጀ።🇪🇹 ✍ ለአንድሮይድ ስልኮች በተደጋጋሚ ኢንተርኔት ገብተው ሲወጡ በዛ ያለ ገንዘብ እየወሰደባችሁ ለተቸገራችሁ በሙሉ የሚከተለውን ሁለት የተለታዩ መፍትሄዎችን ይዘን ቀርበንላችኋል። 🥇የስልኮቻችንን Setting በማስተካከል 🥈 Software በመጠቀም ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🇪🇹 @Computer_Android_tricks ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✍ የሚከተሉትን የስልኮቻችንን Setting በመጠቀም ኢንተርኔት ስንጠቀም በዛ ያለ ገንዘብ እንዳይወስድብን ማደረግ እንችላለን። 🔘 Setting -> Connection ( Wireless and networks) ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ ስንገባ ኢንተርኔት በጣም የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን እንደወሰዱት መጠን ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ ይክፈቷቸው። Foreground (ከፍተው የተጠቀሙት) እና Background (ያለፍቃድዎ እና ሳይታዩ አፑ በራሱ የተጠቀመው) ምን ያህል Mega Bytes እንደሆነ ያስቀምጠዋል። እሱን ዝቅ አድርገው Limit background process ከሚለው ፊት ያለውን [ √ ] በማድረግ ይምረጡት። ይሄም ካለ እኛ ፈቃድ አፑ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል ሲሆን ወደ ሗላ እየተመለስን ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ አፖች እየከፈትን መዝጋት (Limit) ማድረግ አለብን። 🔘 ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን መዝጋት ይኖርብናል። 🔘 🔺 አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ (samsung 5830 አይነቶች) Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ Setting-> Accounts and Sync ገብተን Background data የሚለውን አለመምረጥ ። 🔺በተጨማሪም Setting -> Privacy የሚለውን በመክፈት Back up my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ። ይህ አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በላይ ለሆኑትም ይሰራል። 🔘 ለ Huawei ስልኮች Data usage ለመግባት፣ Setting —> wireless & Networks -> more .. — > Data Usage -> Restrict background data የሚለውን [ √ ] በማድረግ መምረጥ Setting -> personal ከሚለው ስር Location access የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት። ይሄም ስልካችን ያለንበትን ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ያደርጋል። 🔘 Setting -> Developer option (About phone ከሚለው ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ ታች ስንወርድ Background Process limit የሚለውን እንክፈት። ይሄ ሁሌም ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን ይመርጠዋል። እዚህ ላይ No background process የሚለውን እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard limit ስለሚቀየር እየገባን መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10 አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል። 🔘 ☞ Developer option የሚለውን Setting ውስጥ ካጡት የሚከተለውን ያድርጉ። Setting ->About phone የሚለው ውስጥ እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንካው። ከዚያ ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone ከሚለው ከፍ ብሎ Developer option ያገኙታል። 🔘 🔺የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ (update) መዝጋት። ለዚህም Setting -> About phone (device) -> Software update ገብተን Auto update የሚለው የተመረጠ ከሆነ [ √ ] እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ። 🔘 GPS መዝጋት . ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት የማይጠይቁ አፖችን (ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣ ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ ... የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት ያስቀራል። 🔺Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን ኢንተርኔት አለመግባት። ✍ ውድ እና የተከበራችሁ የ"Computer" እና የ"አንድሮይድ ትሪክስ ቻናል ተከታታዮች ከላይ የጠቀስናቸውን የስልኮን Setting ካስተካከሉ በእርግጠኝነት ለኢንተርኔት የሚያወጡትን ገንዘብ ይቀንሳሉ። ✍ ነገር ግን ይሄን ማስተካከል ካሸገሮት በቀላሉ እንዴት አድርገን በሶፍትዌር መዝጋት እንችላለን የሚለውንም እነሆ ብለናል። 🔷 መጀመርያ ከላይ የለቀቅንላችሁን አፕሊኬሽን ( DataEye) የሚለውን ስልካችን ላይ እንጭናለን ከዛ አብልኬሽኑን ስንከፍተው ከላይ ባለው ምስል "A" ላይ እንደምታዩት በ Usage ስር date saving mode Off/On የሚል አለ እሱን On ስናደርገው በምስል "B" ላይ እንደምታዩት ያሳየናል። 🔹ከዛም በቀጥታ Control በሚለው ስር ስንገባ በምስል "C" እንደምታዩት መጠቀም የምፈልጉትን ብቻ Open ታደርጋላችሁ ለምሳሌ አሁን እኔ መጠቀም የምፈልገው በምስል "C" ላይ የሚታዩተን ብቻ ስለሆነ ሌሎቹን በሙሉ በምስል "D" እንደምታዩት ሁሉንም ዘግቻለው (Block) አድርጊያለው ይህ ማለት እኔ ከከፈትኳቸው በምስል "C" ካሉት ውጪ ምንም አይነት አፕሊኬሽን አይሰራም ማለት ነው። 🔻ለምሳሌ ይሄን አስተካክለን ከጨረስን ብኋላ ሄደን ኢንተርኔት ከፍተን የዘጋንውን አፕሊኬሽን ብንከፍተው "DataEye" on ላድርገው off የሚል ምርጫ ይሰጠናል ያኔ On ብለንው ብንከፍት ኢንተርኔት አይሰራልንም ተዘግቷል ማለት ነው ያለኛ ፍቃድ ሊሰራ አይችልም። 👽ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ኢንተርኔት ከመክፈታችን በፊት መጠቀም የምንፈልገውን ከፍተን ሌላውን በምስል "D" እንደምታዩት መዝጋት አለብን ማለት ነው። ⚠️ ከዚህም በተጨማሪ ስልካችሁ #telegram ስትጠቀሙ ብዙ ብር እየወሰደባችሁ ከተቸገራችው አሁኑኑ የቴሌግራሞን setting ያስተካክሉ‼️ •••••••ቴሌግራሞን ይክፈቱ•••••••••• ⬇️ °👉Setting ° ⬇️ °👉data and storage ° ⬇️ °👉automatic media downloaded ° ⬇️ °👉#click *when using Mobile data* ° 🔑🗝🔑 ° 🔰 #Unmark❌ all & #save it ☞ [_]....photos ☞ [_]....voice messages ☞ [_]....videos ☞ [_]....files ☞ [_]....music ☞ [_]....GIFS ✴️ ከላይ የጠቀስናቸውን መፍትሄዎች ካስተካከሉ እመኑን በእርግጠኝነት በትንሽ ብር ለረጅም Time መጠቀም ይችላሉ። 🇪🇹 #ኢትዮጵያዊነት_መልካምነት ነው። #እባኮትን #ለ10 ጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️ ♡♡♡♡♡እናመሰግናለን!!♡♡♡♡ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🔘 @Computer_Android_tricks

Name : DataEye ,5.0 MB ━━━━━━━━━━━━ Version : v2.2.122 latest. ━━━━━━━━━━━━ ✴️: For Andriod Apk ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🔘 @Computer_Android_tricks

‍ ኮሮና ቫይረስ : በ 12 ሀገራት ተስፋፍቷል ==================== * ኮሮና ቫይረስ በቻይና 56 ሰዎችን ለሞት፣ * 2 ሺህ ሰዎችን ደግሞ ለህመም ዳርጓል፡፡ * የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትልና ለሞትም ሊዳርግ የሚችል የቫይረስ ዝርያ ነው፡፡ * በሽታው በትንፋሽ፣ ባልበሰሉ ምግቦች እና በቫይረሱ ከታመሙ ሰዎች ጋር በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል። * ትኩሳት፣ ሳል እና የአተነፋፈስ ችግር ደግሞ ምልክቶቹ ናቸው፡፡ * ቫይረሱ ከቻይና ባሻገር በአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ አውስትራሊያ፣ ታይላንድ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ ቬትናም፣ ሲንጋፖር፣ ማሌዥያ እና በኔፓል እንደተከሰተ እየተዘገበ ነው፡፡ #መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

❖ ፍላሽ ዲስክ ኮምፒዩተርዎ ላይ ሲሰካ ሾርት ከት እየሆነ ተቸግረዋል? ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃ ❑ ፍላሽ ዲስካችን ወይም ኮምፒዩተራችን በቫይረስ ሲጠቃ በውስጡ ያሉት ፋይሎች በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሾርትከት ይቀየራሉ። ይህም ማለት ዋናው የኛ file(ፋይል) ይደበቅና ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው። ❑ የዚህ ቫይረስ ሌላው አስቀያሚ ገጽታ ከኮምፒዩተር ወደ ሌላ ኮምፒዩተር በቀላሉ በፋላሽ አማካኝነት ሊተላለፍ መቻሉ ነው። ✏️ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይህን ሾርትከት ቫይረስ የምናጠፋበትን Tricks. እናካፍላችኋለን ተከታተሉን። ❑By using CMD❑  cmd (command prompt) በመጠቀም ይህ ዘዴ ከሁሉም የተሻለ ውጤታማ ሲሆን ለሀርድ ዲስኮች ለፍላሾች እንዲሁም ለሞባይል ስልኮች ያገለግለናል። 1. በመጀመሪያ cmd እንከፍታለን። Win + R then we write Cmd ( run፦cmd፦enter) 2. cmd ከከፈትን በኋላ ለማጽዳት የምንፈልገው ፋላሽ ዳይሬክተሪ እንሄዳለን። ( ለምሳሌ ፍላሹ removable disk G ከሆነ G:\ ብለን እንጽፋለን።) 3. በመቀጠል ይህን ኮማንድ እንጽፋለን። G፡*.* /d /s -h -r -s (G ለምሳሌ ሲሆን እናንተ በራሳችሁ ፋላሽ ሆሄ ትቀይሩታላችሁ።) 4. አሁን ኢንተርን ስትጫኑ ከሾርትከት ቫይረስ ተገላገላችሁ ማለት ነው። መረጃዎቹን ጠቃሚ ሆነው እንዳገኛችኋቸው ተስፋ እናደርጋለን።። ══════❁✿❁ ══════         🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ @Computer_Android_tricks        ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛

⚙Software ማለት ስልካችን የሚሰራበት ፕሮግራም ሲሆን computer ፣ flasher box እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን እንዲሁም ኮዶችን በመጠቀም የምንሰራው ስራ የ software ጥገና እንለዋለን። ❖ Software በመጠቀም የምናስተካክላቸው የተለያዩ የስልክ ችግሮች አሉ። ለምሳሌ ☛ በራሱ በርቶ የሚጠፋ ስልክ ☛ ምንም የማይበራ ስልክ ☛ አንድ የምንፈልገውን ፕሮግራም ስንከፍት ብቻ የሚጠፍ እና ሌሎች ፕሮግራሞችን ግን በ አግባቡ የሚሰራ ስልክ ☛ በ security የተዘጋ ስልክ ☛ network መከፈት የሚፈልግ ስልክ እና የመሳሰሉትን ሊያካተት ይችላል። ⚙ Software መስራት የሚከትሉትን ያካትታል። ❒ flash ማድረግ ❒ restore ማድረግ ❒ format ማድረግ ❒የተዘጋ ስልክ መክፈት ❒ iphone jailbreak ማድረግ ❒ internet መክፈት ❒ music ፣ video እና game መጫን ወዘተ.... ✏️ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት ለማከናወን computer ፣ flasher box እና የተለያዩ software ፕሮግራሞች ያስፈልጉናል። ⚙ FLASHER BOX ማለት ስልካችንን ከ computeራችን ጋር እንዲገናኝ የሚያደርግ መሳሪያ ነው። የተለያዩ የsoftware ቦክሰሮች ገበያ ላይ ይገኛሉ። አንድ software box ከሌላው ቦክስ የሚለየው በሚሰራቸው የስልክ አይነቶች ነው። ⚙ ቀጥሎ የምታዩት የ "software" ቦክሶች አይነት የተለያዩ ስልክ መስራት የሚያስችሉ ሲሆኑ በተለያየ ፕሮግራም ይዘንላችሁ እንቀርባለን። ❶ UFS ❷ Z3X ❸ Cyclone ❹ Infinity ❺ Avator ❻ Volcano ❼ Farous....etc ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

✍ ዛሬ ደግሞ ቃል በገባንው መሰረት ከትላንትናው የቀጠለ Steve Jobs ህይወቱ ከማለፉ በፊት ከተናገረው አስተማሪ ፅሁፍ እናካፍላችሁ።(አንብቡት አትቆጩም) 📌 የአፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ ሲሞት ኩባንያው 700 ቢሊየን ዶላር ይገመት ነበር ፤ በታሪክ ሀብታሙ ኩባንያ ነበር። ስቲቭ ከመሞቱ ከጥቂት ቀናት በፊት "ስለ ሕይወት ትርጉም" ትንሽ ማስታወሻ ጥሎልን አልፏል። ✏️ማስታወሻው፦📝 "በሕይወቴ በቢዝነስ ረገድ የስኬት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ ፤ በሌሎች አይን ከኔ የበለጠ ለስኬት ተምሳሌትነት የሚመረጥ ሰው የለም" "ነገር ግን ከስራ ባሻገር በሕይወቴ ብዙ ደስታ አልነበረኝም። ሀብታምነት የተለማመድኩት የህይወቴ አካል ከመሆን ያለፈ ትርጉም አልነበረውም።" "በዚች ታምሜ አልጋ ላይ በዋልኩበት ቅጽበት ፣ በመላው ሕይወቴ የተቀበልኩት ሽልማትና ያገኘሁት ሐብት ሞት እየቀረበኝ በመጣ ቁጥር ትርጉም የለሽ ሆኖብኛል" "በጨለማው ውስጥ የሕክምና መርጃ መሳሪያዎችን አረንጓዴ መብራት አያለሁ ፤ ድምፃቸውንም እሰማለሁ። በእያንዳንዷ ሰከንድ የሞት መላእክት ትንፋሹ እየቀረበኝ ሲመጣ ይሰማኛል" "አሁን አንድ ነገር ገብቶኛል። በህይወታችን ሙሉ አጥፍተን የማንጨርሰው ገንዘብ ካገኘን በኋላ ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሌሎች ዝንባሌዎችን ማዳበር አለብን።" "ሙዚቃ ፣ ስነጥበብ ወይም መፅሀፍት ሊሆኑ ይችላሉ። የልጅነት ምኞታችንን መከተል ሌላ ነው ወይም የፍቅር ግንኙነት። መንፈሳዊነትም አለ። ብቻ ለነፍሳችን የሚሆን ጠቃሚ ግን በገንዘብ ሊገዛ የማይችል ነገር መሆን አለበት።" 📍"ገንዘብን ብቻ ማሳደድ ግን በመጨረሻ እንደኔ ጠማማ ፍጥረት አድርጎ ያስቀራችኋል።"📍 "እግዚአብሔር ስሜትን የሰጠን ፍቅርን እንድናጣጥም እንጂ ገንዘብ በሚፈጥርብን የውሸት ስሜት ተታለን እንድንቀር አይደለም" "ሕይወቴን በሙሉ ካከማቸሁት ግዙፍ ሐብት ውስጥ አንዲት ሳንቲም እንኳን ይዤ መሄድ አልችልም። ከኔ ጋር ልወስደው የምችለው ብቸኛ ነገር በፍቅር የቀለሙ ትዝታዎችን ብቻ ነው።" "ያ ነው እውነተኛ ሃብታችሁ ፣ የማይከዳቹ ወዳጃችሁ። በሄዳችሁበት ሁሉም ብርሀን እና ጥንካሬ ይሆናችኋል" ✏️"በአለም ላይ ውዱ አልጋ የህመምተኛ አልጋ ነው። አንድ ሰው መኪና እንዲነዳላችሁ ፣ ስራ እንዲሰራላችሁ ልትቀጥሩ ትችላላችሁ። የናንተን ህመም ግን ማንም ሊሸከምላችሁ አይችልም።" "ቁሳዊ ነገሮች ሁሉ ቢጠፉ ሊተኩ ይችላሉ። አንድ ነገር ግን ከጠፋ ዳግም አይገኝም። እሱም ሕይወት ነው።" "አሁን በሕይወታችን የትኛውም ደረጃ ላይ ብንሆን መጋረጃው የሚጋረድበት ቀን ይመጣል።" "ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር ፍቅርን ተጋሩ" "እራሳችሁን ተንከባከቡ። ለጓደኞቻችሁ ዋጋ ስጡ..." Source - Google & Wikipedia •••~~~~~~~~~~~~~~~~~~~••• 📢: @Computer_Android_tricks

📌 Steve jobs 🔖 ✍ አመተ ምህረቱ 1955 ላይ ይቆጥር ነበር በአሜሪካዋ san Francisco እንዲህ ሆነ ባለምጥቁ አይምሮ ልጅ ወደዚህች ምድር ተቀላቀለ። ከ ሶርያ ለትምህርት ብሎ ከመጣው ወላጅ አባቱ እና የካቶሊክ እምነት ተከታይ ከሆነች እናት የተገኘው Steve ገና በ ጨቅላነቱ ነበር ለማደጎ ልጅነት የተሰጠው። የዚህም ምክንያት ጥንዶቹ ገና የ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ስለነበሩ እና በ ሁለቱ መካከል በነበረው የ ባህል እና የእምነት ልዩነት ቤተሰብ ደስተኛ ሊሆን ባለመቻሉ ነበር። ነገር ግን ከብዙ የመከራ አመታት በሃላ ትዳር መስርተው lisa የተባለች ሌላኛው እህቱን አፍርተዋል። steve ለማደጎ ከተሰጠ በሃላ አሳዳጊ ከነበረው አባቱ ጋር በትርፍ ጊዜያቸው ኤሌክትሮኒክስ እየጎረጎረ ያሳልፉ ነበር ። ከአመታት በኋላ ወደ ዩኒቨርስቲ የመግባት ዕድል የነበረው steve ለስድስት ወራት ብቻ ተምሮ ለማቋረጥ በቅቷል ይሄም የሆነው በትምህርት ሰርአቱ ላይ ተቃውሞ ስለነበረው ነው። ✍ በ 1974 ወደ ህንድ አቅንቶም ስለ enlightenment እና ስለ zen Buddhism እውቀት ለመቃረም ሞክሮሯል። እንግዲ ከዚህ በኋላ ነበር ኮሌጅ እያለ ከተዋወቀው ጋደኛው steve wazniak ጋር በመሆን በቤታቸው ጋራጅ ውስጥ ቀን ከሌት ኤሌክትሮኒክስ በመጎርጎር ማሳለፍ የጀመሩት። ለመጀመሪያ ጊዜም ህልማቸው ፍሬ አፍርቶ በ 1976 apple 1 ኮምፒውተርን ለገበያ ለማብቃት ችለው ሰፊ ተቀባይነትን በማግኘት ወደ 80000 የ አሜሪካ dollar ሊያስግቡ ችለዋል። ✍ በቀጣይ አመትም apple 2 ን ለገበያ አቅርበው ስኬታማ ሆነዋል። ነገር ግን በ 1984 በብዙ ወጪ የተሰራውን apple lisa ገበያ ላይ ቢያቀርቡም ከዋጋው መወደድ የተነሳ ለኪሳራ ተዳርገዋል። በዚህም የተነሳ steve የመባረር እጣ ገጥሞታል። ይሄን አስመልክቶ በ 2005 የ ዩኒቨርሲቲ ምርቃት ላይ ተጋብዞ እንዲህ ብሎ ነበር 🔸"....እናም እኔ 30ኛ ዓመቴን እንደያዝኩ - ተባረርኩ! ...እንዴት ነው ራሳችሁ ካቋቋማችሁት ኩባንያ የምትባረሩት? ነገሩ እንዲህ ነው። አፕል እያደገ ሲመጣ በጣም ክህሎት አለው ብዬ ያመንኩበት ሰው አብሮኝ ኩባንያውን እንዲመራ ቀጠርነው፡፡ በመጀመሪያ ዓመት አካባቢ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበሩ። ቀስ በቀስ ግን የድርጅቱን መፃኢ ዕድል በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ራዕያችን እየተራራቀ መጣና በስተመጨረሻ ጭርሱኑ ተለያየን፡፡ ስንለያይ፣ የዳይሬክተሮቹ ቦርድም ለእሱ ወገኑና፣ በ30 ዓመቴ ተባረርኩ። ሀገር ባወቀው አሳፋሪ ሽንፈት - ተባረርኩ! ህይወቴን የሰጠሁለት ነገር በአንዴ ከእጄ በንኖ ጠፋ፡፡ ይጎዳል - ተጎዳሁ..." ✏️ appleን ከተሰናበተ በኋላም ተስፋ ያልቆረጠው ስትቭ Next የተሰኘ አዲስ ድርጅት በመክፈት እንዲሁም pixarን በመግዛት በሌላ ስኬት ብቅ ሊል ችሏል። ከ ስቲቭ መሰናበት በኋላ apple የውድቀት መንገዱን ተያይዞት ነበር። ከ 10 አመታት በሃላ apple የ ስቲቭ የነበረውን Nextን ሲገዛው ስቲቭም ወደ ስራ በመመለስ CEO ለመሆን በቅቷዋል። ስለዚህ ሁኔታም በዛው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንዲህ ብሎ ነበር 🔸 "... ከአፕል ባልባረር ኖሮ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ላገኝ እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በዕርግጥ በጣም መራር መድኃኒት ነበር። ግን እንደምገምተው ለበሽተኛው የግድ አስፈላጊ ነበረ፡፡ አንዳንዴ ህይወት አናታችሁን ትቀውራችኋለች፡፡ እምነት ግን አትጡ፡፡ በሽንፈቴ ውስጥ ሁሉ እንዳላቆም ፣ እንድቀጥል የረዳኝ የምሰራውን መውደዴ ለመሆኑ ጨርሶ ጥርጥር የለኝም፡፡ 🔍 የምታፈቅሩትን ልታገኙ ይገባል - ይህ ደግሞ ለስራችሁም ሆነ ለፍቅራችሁ ወሳኝ ነው፡፡ ስራችሁ የህይወታችሁን ትልቁን ክፍል የሚይዝ ነው። እናም በስራችሁ ልትረኩ ዘንድ የምትሰሩት ነገር ታላቅ መሆኑን ልታምኑበት ይገባል፡፡ ♥ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የምትወዱትን ስትሰሩ ነው! የምትወዱትን ሥራ እስካሁን ካላገኛችሁት ለመፈለግ አትቦዝኑ። ፈልጉ - አትርጉ፡፡ እናም፣ እንደሁሉም ከልብ የሆነ ነገር ሁሉ፣ ስታገኙት ታውቁታላችሁ።♥ እንደሁሉም ታላላቅ ግንኙነቶች ሁሉ፣ ዓመታት በነጎዱ ቁጥር፣ ይበልጡን እያማረና እየሰመረ ሂያጅ ነው፡፡ ስለዚህ ፈልጉ፤ አትርጉ!..." ከዛ በሃላ apple አለማችን ላይ በጣም ዝነኛ ካምፓኒ ሊሆን በቅታል። ለመጀመሪያ ጊዜም full touch screen ስልኮችን ለ አለም አስተዋውቃል። ስቲቭ በ 1991 ትዳር የመሰረተ ሲሆን የ 3 ልጆች አባት ነበር። በ 2003 ጀምሮ በ ጣፊያ ካንሰር ሲሰቃይ የኖረው steve ህመሙ ጸንቶበት በ 2011 ለህልፈተ ህይወት ሊያበቃው ችላል። በአለም ላይ ሞቱ ብዙሀንን ያስደነገጠ ነበር። "ቀጣዩን የ ስቲቭ ጆብስ በህመሙ ሲሰቃይ የተናገራቸውን አስተማሪ ንግግሮች ነገ እናቀርብላችኋለን። ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ 📢: @Computer_Android_tricks