ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
前往频道在 Telegram
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
显示更多1 720
订阅者
-124 小时
-47 天
-1430 天
帖子存档
Young Ethiopian Leaders Initiative (YELI)
Experienced, Learned Leadership 🇪🇹
Let’s Rise Together.
Change Together.
Be Together.
At the end, We are fighting To...get...there👆🏼
https://t.me/YoungEthiopianLeadersInitiative
ግራ ዘመም
ደቦ ወይ ለየቅል የመኖር ትርጉሙ
ቀዳሚን ሲከተል የሰው ልጅ ማዝገሙ
ዛሬን በራስ ፍቺ አዲስ ትርጉም መስጠት
ወይስ ታስሮ መኖር በትላንት ድርሰት
መጠየቅ መመርመር ካዋለን በግራ
በምን ይታወቃል የህይወት ሚስጥሯ
#ሮቤል Robel Eshetu
Open Call: Iconic Waste Bin - Eco-Art Competition
📅 Till December 8, 2019
📍 Online
🙏 Events
Italian Cultural Institute & Guramayne Art Center
[0911702953, mifaddisart@gmail.com]
@eventsethiopia
Open Call: Iconic Waste Bin - Eco-Art Competition
📅 Till December 8, 2019
📍 Online
🙏 Events
Italian Cultural Institute & Guramayne Art Center
[0911702953, mifaddisart@gmail.com]
@eventsethiopia
To Ethiopian creatives, The Arts Mailing List newsletter – 25th Nov 2019 is out now!!!!! https://bit.ly/35vEitO
This week we bring you the amazing work of Mussie Belachew
Opportunities from @yehadigitalart etc…
Inspirational pieces from @getz_mag, @BigDreamET, @aterira, @EMVCommunity and so much more
አይገርምሽም
መኖርን የሚያክል የለም
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አድማስ ሩቅ አይደለም
ይኸውልሽ ደሞ ምስክር
ተመልከች የልቤ ማሳ ያበቀለውን ፍቅር
ይሄ የኔን ልብ እኮ ድፍን አገር የሚያውቀው
አንቺን በሸኘ ማግስት
ጭምት ባይተዋር ሆኖ ነው
ይሄ የኔ ልብ እኮ እንቺን በሸኘ ማግስት
ተስፉ ከሚባል ብርሀን
ክነገ ጀንበር ተኳርፎ
ስንትና ስንት ዘመኑን ትላንትናሽን ታቅፎ
ለሄደ ፍቅርሽ የኖረ
ምስኪን ምርኮሽ ነበረ
.
.
.
አይገርምሽም
መኖርን የሚያክል የለም
የጊዜ ጉዳይ ነው'ንጂ አድማስ ሩቅ አይደለም
ይኸው እኔም አፈቀርኩ
ያንቺን ትላንት ሳይሆን የነገዬን ዛሬ እወ'ኩ
.
.
.
በቃ..በቃ..ከንግዲህ ትላንትናሽን ሳይሆን ነገን እናፍቃለሁ
ዛሬ ሸኝቼ የሳምኳትን ልጅ ለነገ ቀጥሬያታለሁ
ደግሞ አፍቅራኛለች
ደግሞ አፍቅሬያታለሁ
ደግሞ አገኛታለሁ
.
.
.
በቃ..በቃ..
ከንግዲህ ብዕሬን የሞላው ቀለም
ስለ ተስፋ ነውንጂ የፅልመት ግጥም
አይፅፍም
አይገርምም
መኖርን የሚያክል የለም....!!!
,ዳግም ተካ
Brikti Fissehaye #ግጥምሲጥም @Bitip
*ውዱ ባለቤቴ*(ብርክቲ ፍስሃዬ)
.
ሃሳብና ናፍቆት ሆዴን ሲያስብሰው
የደከመ አካሌን እንቅልፍ ሲነሳው
ብዕሬን አነሳው...
የተንዛዙ ቃላት ገና ያልተጣሩ
እንዲያው እንዳሻቸው ስላንተ እያወሩ
ፍቅርን ሲዘምሩ
ዓለምን ሲዞሩ
መች በቃን አሉና
ዛሬም ያወራሉ ስላንተ ቁንጅና
ደምቆ ሲያበራ ፊትህ በፈገግታ
ድንገት ይጨምራል የልቤ ትርታ
ቀንም ሆነ ማታ
ባንተ ሃሳብ ትዝታ
ፍቅሬ ሲበረታ
ልብህን ልቤ ውስጥ ላኑረው በክብር
ለቃሌ ልታመን ልሁን ያንተ ፍቅር
ልውደድህ ዘላለም ልኑር በልብህ ውስጥ
ካንተ ውጪ ላላይ ለፍቅርህ ቃሌን ልስጥ
በነዚያ ከዋክብት በዚያ ደማቅ ምሽት
አይኔን ወደ ሰማይ ልኬ ስመለከት
አየው ያንተን ውበት
የፍቅርህን ጥልቀት
የውስጥህን ድምቀት
ባንተ ውስጥ ልኑር ዘወትር ስደሰት!
ኑር
#ግጥምሲጥም #ሰይፈተማም
ጽደቅ እንደ ችግኝ አፍላ እንደ ሾላ
ከአለም ደጉን ወስደህ መልካም ፍሬ ዝራ
ዘላለም ለመኖር 'አሁን'ን አትፍራ
አትቅጠፍ
ቅርንጫፍ
ካላፈራ ኋላ
2012
ዝምታዬ
#ሰይፈተማም Seife Temam
-------------
አፌ የተለጎመ
ዝም ሲል የኖረ
'ዝምታ ወርቅ ነው'
ብዬስ አልነበረ
ወርቅ ያብለጨልጫል
ይጣራል ከሩቁ
የጎንም ይሸሻል
ዝምን ግን ሲያጠልቁ
…
በእጄ ብትሆን ፀሀይ
ላይተን አላበራም ከውቅያኖሱ ላይ
ቢታዘዘኝ ዝናብ ቢሰማኝ ደመና
ምድር አልከውም ካልሰፈረ መና
የብቻዬም ቢሆን አየሩ ንፋሱ
አላስጠጋችውም ከሰውም አይደርሱ
… … … ... ... ነፍስ እስካላደሱ
Baby Killer
By: Seife Temam
I'm a baby killer
I hanged our infant love,
strangled it to death
and called it a self defense
because I was losing my self
I'm a baby killer
I kidnapped the toddler droplets
at the corner of my eyes
and silenced their screams
because they were telling my weakness
I'm a baby killer
I hated my self, my mind and my talent
I stopped writing to start killing my dream
but in between I take a pause
.
.
.
to write about killing the baby in me
that sacred light my dear saw in me
that source of infinite peace my dear felt in me
that endless goodness and ingenuity
that sense of being home
that... that part that makes me write baby poems
I killed it all...
Now, what's left of me is just a baby killer
with a baby poem about being a baby killer
and if you find my baby,
please tell her that I'm only calling my self this
but in reality
there is no love to hang, no tear to kidnap or no self to hate
cuz I am the baby and already dead
Off
By Elebethel Tessema
Of first texts and rendezvous unplanned,
Of shy glances and stare you down-s,
Of hidden feelings and meaningless fooling around,
Of no strings attached with cords so tight,
Of burried feelings and longing eye contacts,
Of joyful giggles, and confusion about what we are,
Of quick falls and arms that catched,
Of stolen kisses and territories marked so bright,
Of rushing feelings and sensual touches,
Of love spats and making up,
Of your wild hair and my groomed one,
Of your free spirit and my timid heart,
Of your loud presence and my looming behind like a shadow; so I can go wherever you go,
Of pushing limits and comfort zones,
Of "he's mine" and "she's mine" so everyone knows,
Of me showing you off and you hiding us,
Of cigarettes and chewing gums,
Of hard liquor and soft drinks in a club,
Of insecurities and validations,
Of pushing buttons and fishing out reactions,
Of harsh words and hidden cries,
Of your suspicions and my unwavering trust,
Of your dressed up lies and my hands that refuse to strip your lies,
Of empty threats and half promises,
Of dodged touches and breath stealing kisses,
Of warm hugs and cold shoulders,
Of your indecisiveness and my assurance,
Of your sudden lows and my failed attempts to pick you up,
Of hotel rooms and car rides,
Of my sobriety and of all your vices,
Of all your flaws I embraced and my differences you couldn't accept,
Of your stubbornness and my "let me fix this please",
Of your tests and my flying color pass,
Of your failure to be loved and me trying to prove myself time after time,
Of your tainted soul and my unscathed one,
Of growing close only to fall apart,
Of lovers and of strangers just as fast,
Of falling in love and falling out of love,
Of I love yous turned into leave me alone's,
Of forevers dissipating into see you Nevers,
Of locked hands letting go one finger by one,
Of you slipping away and my grasp on you to make you stay,
Of you...
Of me...
Of our doomed love from the very start.
🥀
የተውሶ ገላ
©️ THomas Admasu
የተዉሶ ገላ ያዉም ያልፈቀደ
የእሳት ሬሳ ሳይነብል ያመደ
በመታመን ሜዳ ዞትር የተካደ
ላላገኘው መጥቶ ሳላገኘው ሄደ
ሄደ
ይሂድ ያምድ ምናባቱ...
ነፍስ ስለተ ብርቱ...
ቃል ከርታታ ገልቱ...
ዓይን ቀና ገልበቱ...
ጉልበት...
ጉልበት የደከመ
ህዋስ የታመመ
ከንፈር የተመመ
ሰርቆ ከንፈር ሳመ።
ሳመ
ይሳም የታባቱ
መሳም የትናቱ
ልብ የከዳ ለታ
ዓይን የላመ ለታ
የአካላትህ ጅማት
የእዝኖችህ መስማት
የእናት የአባት አስማት
ሲከዱህ አንድ ላይ
ቀና በል ወደላይ
አቀርቅር ከመሬት
ከመበደር በላይ ኬት ይመጣል ምሬት?
ምሬት! ይምረር ምናባቱ
ብድር የት እናቱ
ልብ ከጎለመተ
ነፍስ ከሻገተ
ልሳን ከታገተ
ተበድሮ ስሞ በብድር አሳሳም
የተውሶ ፍቅር አይወፍር አይከሳም
.......
ናፈቀ ቀና ምውት ነው ወደደ ጠላ አይሰራም
ጨረቃ ቀን አታበራም።
.......
ፍቅር አይዋስም
ቃል አይላወስም
የተበደሩት ልብ የልብ አያደርስም።
......
አያድርሳ ደሞ እሱም የተውሶ
አያጠግብ አጉርሶ
ነፍስ አያክም ደርሶ
.....
(እንኳን ፍቅር ቀርቶ)
የተዉሶ ግጥም
ቤት በቅጡ አይገጥም
ሳቁ ለጆሮ አይጥም
ቢገጥ ባያገጥም
.
.
የትውሶ ገላ የተውሶ ፍቅር
/ይቅር/
የደበቅነው ዕውነት
© ታመነ መንግስቴ
በኔም ቤት
በአንችም ልብ
የታመቀው ነገር
አንድ ቀን ቢወጣ
ያቃጥላል አገር፡፡
የኔንስ ልንገርሽ
በልቤ ያልኩትን
ለሃሜት ስጎመጅ
በክፋት ስኳትን:
እንኳም ሰው አልሰማው
ስቦጭቀው ነበር
እግዚሃርን ሳማው፡፡
እሱ እንደሁ ታጋሹ
እያወቀ ረሳኝ:
ዋሽቸ ሰርቄ
ብበላም አከሳኝ፡፡
እናልሽ ዐለሜ!
የደበቅነው ዕውነት
ጭሶ ተጫጭሶ
ሳያቀጣጥለን፡
ውድ ሃሳብ እንሸምት
የረከሠ ጥለን!
የመነሻ ሃሳቤ በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ በቆየሁባቸው ወራት እውነተኛ መምህር ሆነው ያገኘሗቸው የኔታ #ማቴወስ ታደሠ ክፍል ውስጥ ያወጉን ነገር ነው፡፡
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
