Diinii kee Anaakara (Md Ali)
前往频道在 Telegram
دروس وفتاوي ومحاضرات باللغة العفرية ★Diini barittooy, fatwaa kee Daqwa Qafar afat Tû mabul=> @Anaakar or @acmadxalol
显示更多1 618
订阅者
-124 小时
-27 天
无数据30 天
帖子存档
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሲጋራ
~~~
"ለማንም ሰው ሲጋራ መሸጥ አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ሲጋራ የተከለከለ ነውና። አላህ አንድን ነገር ክልክል ካደረገ የሽያጭ ዋጋውንም ከልክሏል። እንዲሁም እሱን መሸጥ በወንጀልና ወሰን በመተላለፍ ከመተባበር ነው።" [አሊቃኡ ሸህሪይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፡ 3/ 597]
-
ጫትም ላይ ተመሳሳይ ብይን ነው ያለው። መሸጥም፣ መግዛትም፣ ማጓጓዝም፣ መሸከምም፣ ማሸከምም፣ ሱቅን ለጫት ንግድ ማከራየትም፣ ... በየትኛውም መልኩ መተባበር አይፈቀድም።
=
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ፕራንከ በማድረግ የሚታወቀው ሶሀቢይ"
~
በዚህ መልኩ ርእስ ከሰጠ በኋላ የኑ0ይማን እና የሱወይቢጥን "ገጠመኝ" ማስረጃ አድርጎ የጠቀሰ ሰው አየሁ። የታሪኩን ጭብጥ ከፀሀፊው ልጥፍ ቀንጨብ አድርጌ ላቅርበው፦
{{ኑአይማን ሱወይቢጥን ምግብ ጠየቀው። አቡበክር ሳይመጣ አልሰጥህም አለው። በዚህን ግዜ ኑዐይማን ቆይ እሰራልሃለሁ ብሎት ወደ ሌሎች ነጋዴዎች ዘንድ በመሄድ "ባሪያ ትገዙኛላችሁ?" አላቸው። "አዎ በስንት እንግዛህ?" አሉት። "አይ ዋጋውማ ቀላል ነው ነገር ግን ባሪያው ጉድለት አለበት ጉድለቱን ሳልነግራችሁ አልሸጥላችሁም እስከነጉድለቱ ከገዛችሁኝ ነው የምሸጥላችሁ" አላቸው። "ጉድለቱ ምንድነው ?" ብለው ሲጠይቁት "ባሪያው ምላሱ ረጂም ነው ሁሌ ነጻ ሰው ነኝ ባሪያ አይደለሁም እያለ ይለፈልፋል" አላቸው። "ጉድለቱ ይህ ብቻ ከሆነ አብሽር እንገዛሃለን" አሉት። በ 10 ትናንሽ ግመሎች ተስማሙ። ግመሎችን ሰጥተውት እየነዳቸው ወደ ሱሀይቢጥ ጋር ነጋዴዎችን ይዟቸው መጣ። "ይሄው ባሪያው ውሰዱት" አላቸው። ሱሀይቢጥም "ኧረ ባሪያ አይደለሁም ነጻ ሰው ነኝ" ብሎ ቢጮህ "ዝም በል ይህ ነውር እንዳለብህ ቀድመን አውቀናል ዝም ብለህ ና" ብለው በገመድ አስረውት ወሰዱት።
አቡበክር ሲዲቅ ሲነገረው ስቆ ለነጋዴዎቹ ግመሎቹን መልሶላቸው ሱሀይቢጥን አስለቀቀው። ከጎዞ ሲመለሱ ለነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ኑአይማን ሱሀይቢጥ ላይ የሰራው ፕራንክ ሲነገራች እሳቸውም ሶሀቦቻቸውም ሳቁ ኑዐይማንን አልወቀሱትም።
ኑአይማን ሌሎችም በርካታ ፕራንኮች አሉት ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አይቃወሙትም ነበር ። }}
=
እንግዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ፕራንክ እየተባሉ ለሚለቀቁ ስራዎች ማስረጃ መሆኑ ነው። ሌላም ፀሐፊ ከዚህ በፊት ይህንንና ሌሎች ቂሳዎችን በተከታታይ ሲፅፍ አይቻለሁ።
ለማንኛውም በኢስላም እንዲሁ ኪታብ ውስጥ ስለተገኘ ብቻ አንድ ዘገባ ዝም ብሎ አይወስድም። ተቀባይነቱ ይፈተሻል። የዘርፉ ማለትም የሐዲሥ ሊቃውንት ደግሞ ምርቱን ከእንክርዳዱ አበጥረው እየለዩ አስቀምጠዋል። ወደ ተነሳንበት ዘገባ ስንመለስ የሐዲሥ ምሁራን ብይን ይህንን ይመስላል፦
1- አልቡሲሪይ "ይሄ ደካማ ሰነድ ነው" ብለዋል። [ሚስባሑ ዙጃጃህ: 4/115]
2- አልባኒይ ደካማ ነው ብለዋል። [ዶዒፍ ኢብኑ ማጀህ፡ 750]
3- ሹዐይብ አልአርናኡጥ ደካማ ነው ብለዋል። [ተኽሪጁ ሙሽኪሉል ኣሣር፡ 1620] [ ተኽሪጁል ሙስነድ፡ 26687]
ይልቁንም ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ
"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"
አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ እና አሕመድ የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡
የተጠቀሰውንም ሆነ ሌሎች ከኑ0ይማን ጋር ጋር የተያያዙ ቀልዶች ሰነዳቸው ደካማ እንደሆኑ የሚጠቀም አጠር ያለ ዳሰሳ በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid04D6qPPXykD7WodZJ5eW3Pms9የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMuneworPkcQBhiVjvwbKAc59Vf1hXwWxSKSQVnZZerTXq47l&id=354099817993687&mibextid=Nif5oz
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
🔊 የወር አበባ እና ፆም
🍂 ለእህቶች አሳሳቢ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠበት ደርስ
🎙 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
✔ ሙስሊም ሴት ለመፆም ብላ ሐይድን የሚያስቀር ኪኒን መዋጥ ይፈቀድላታል?
✔ ሙስሊም ሴት በሐይድ ግዜ ምን አይነት ዒባዳ ማድረግ ትችላለች?
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዛሬም ገንዘባቸውን ለጫት የሚያወጡ ሰዎች አሉ!
~
የኑሮ ውድነቱ እጅግ ከባድ ደረጃ ላይ ደርሷል። የቤተሰቡን ጉሮሮ ለመዝጋት እየተንገዳገደ ያለ ሰው ጫትና ሲጋራ ሲገዛ ማየት የእውነት ሱስ ምን ያህል ህሊናን የሚያውር ክፉ በሽታ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው። ልጆች አገር አቋርጠው በሰው ሃገር፣ በሰው ቤት ነጭ ላብ አፈስሰው የሚልኩትን ገንዘብ ለጫት ማዋል የጭካኔ ጥግ ነው። አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከሸዕባን 15 በኋላ መፆም
~
ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆምን በተመለከተ በዑለማዎች ሁለት አይነት ሀሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡
አንደኛው ወገን፡- መፆሙን የሚከለክሉ ናቸው፡፡ በርካታ ሻፍዒያዎች ይህንን አቋም መርጠዋል፡፡ ማስረጃቸውም፡-
“ሸዕባን ሲጋመስ እንዳትፆሙ” የሚለው ሐዲሥ ነው፡፡ [አቡ ዳውድ፡ 2337] [ቲርሚዚይ፡ 738]
ሌላኛው ወገን፡- ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም ይቻላል የሚሉ ናቸው፡፡ ይሄኛው ምርጫ የብዙሃን ዑለማዎች ምርጫ ነው፡፡ ማስረጃዎቻቸው፡-
1. አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልእክተኛ ﷺ “ረመዳንን በአንድ ቀን ፆም ወይም በሁለት ቀን ፆም አትቀደሙት፡፡ የተለመደን ፆም የሚፆም ሰው ቢሆን እንጂ፡፡ እሱ ግን ይፁም” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪ፡ 1969] [ሙስሊም፡ 1156]
ይሄ ሐዲሥ ረመዳን ሊገባ አንድና ሁለት ቀን እስከሚቀረው ድረስ መፆም እንደሚቻል ይጠቁማል፡፡ ስለዚህ ከሸዕባን አጋማሽ ጀምሮ ረመዳን ሊገባ አንድና ሁለት ቀን እስከሚቀረው ድረስ መፆም ይቻላል ማለት ነው፡፡ ቀድሞ ካስለመደው ፆም ጋር የገጠመለት ሰው ግን ከረመዳን በፊት ያለውን አንድና ሁለት ቀንም ጭምር መፆም ይችላል፡፡
2. እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡- “ነብዩ ﷺ ከረመዳን በስተቀር ሙሉ የፆሙት ወር የለም፡፡ እንደ ሸዕባን ፆም ያበዙበት አላየሁም፡፡” [ቡኻሪ፡ 1914] [ሙስሊም፡ 1082]
በሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ ብላለች፡- “ሸዕባንን ጥቂት ሲቀር እንዳለ ይፆሙት ነበር፡፡” [ሙስሊም]
3. እናታችን አሙ ሰለማ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡- “ነብዩን ﷺ ሁለት ወሮችን አከታትለው ሲፆሙ አላየሁም፣ ሸዕባንና ረመዳንን ቢሆን እንጂ፡፡” [ቲርሚዚይ: 736] አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑ ተርጊብ ወተርሂብ፡ 1025] እዚህ ላይ የሸዕባንን አብዛኛውን ለማለት እንጂ ሙሉ ለማለት አይደለም፡፡ በዐረብኛ በዚህ መልኩ መግለፅ የተለመደ ነውና ይላሉ ዑለማዎች፡፡
እነዚህ ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም ይቻላል የሚሉ ዓሊሞች የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሌሎችም ማስረጃዎች አሉ፡፡ ግን ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም አይቻልም የሚሉ አካላት ያቀረቡትን “ሸዕባን ሲጋመስ እንዳትፆሙ” የሚለውን ሐዲሥ በተመለከተ “መፆም ይቻላል” የሚሉት ዓሊሞች ምን አሉ?
1. ከፊሎቹ ሐዲሡ ደካማ ነው ሲሉ ዘግተዋል፡፡ ኢማሙ አሕመድ፣ ኢብኑ መዒን፣ አቡ ዙርዐህ፣ ዐብዱረሕማን ብኑ መህዲ፣ በይሀቂ እና ሌሎችም ሐዲሡ “ሙንከር ነው” በማለት ደካማ እንደሆነ ከገለፁት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
2. ከፊሎቹ መልእክቱ የተገደበ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ሐዲሡን ቲርሚዚይ፣ ኢብኑ ሒባንና ኢብኑ ማጃህ ሶሒሕ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ኢብኑ ሐዝም፣ ኢብኑል ቀይምና ሸይኹል አልባኒይ ሐዲሡን ደካማ ነው ያሉትን ጠንከር አድርገው ሞግተዋል፡፡ ሆኖም ግን የሐዲሡ መልእክት ከነጭራሹ ከሸዕባን አጋማሸ በኋላ መፆምን ለመከልከል ሳይሆን ቀድሞ ልምድ ሳይኖረው ወይም በወሩ የመጀመሪያ አጋማሽ ምንም ሳይፆም ከሁለተኛው አጋማሽ በኋላ የሚፆምን ነው የተከለከለው ይላሉ፡፡ ኢብኑ ባዝ፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድና ሌሎችም ይህንን ሀሳብ ከደገፉት ውስጥ ናቸው፡፡
3. ከፊሎች ደግሞ በሐዲሡ ውስጥ የተገለፀው ክልከላ ሐራምነት የሚደርስ ሳይሆን እንደማይበረታታ ለመጠቆም ነው ይላሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለረመዳን ፆም መዳከም እንዳይከተል ለማሳሰብ ነው ይላሉ፡፡ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ሐዲሡ ሶሒሕ እንኳን ቢሆን ክልከላው ሐራምነት አይደርስም ይላሉ፡፡ አልቃሪም ይህንን ሀሳብ መርጠዋል፡፡
ሲጠቃለል፡-
1. ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ መፆም የሚከለክለውን ሐዲሥ አብዛኞቹ ዑለማዎች ደካማ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ከላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች መነሻ በማድረግ በሁለተኛው የሸዕባን አጋማሽ ውስጥ መፆም እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
2. ነገር ግን የመጀመሪያው አጋማሽ ውስጥ ያልፆመ፣ ሰኞና ሐሙስ ወይም መሰል ልማድ የሌለው ሰው እንዲሁ ከሸዕባን አጋማሽ በኋላ ለመፆም ባይነሳ የተሻለ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከልካዩን ሐዲሥ “ሶሒሕ ነው” የሚሉ ዓሊሞች ትንታኔ ጠንከር ያለ ስለሆነ ከሸዕባን 15 በኋላ ያለምንም መነሻ ፆም በመጀመር እራሳችንን ኺላፍ ውስጥ ከማስገባት ልንቆጠብ ይገባል፡፡
3. ሰኞና ሐሙስ ወይም ሌላ ያስለመደው ፆም ያለው ሰው፣ እንዲሁም በመጀመሪያ የሸዕባን አጋማሽ ውስጥ ሲፆም የነበረ እና መሰል ሰበቦች ያሉት ሰው ፍላጎቱ ከሆነ በሁለተኛውም አጋማሽ መፆም ይችላል፡፡ ወልላሁ አዕለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 26/2010)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//IbnuMunewor
Repost from ዳር አልሺፋእ የማማከር አገልግሎት
ፆም እና ጤና
👇👇👇👇
ፆማችን በኢኽላስ ስንፆም አላህ ዘንድ ካለው የላቀ ደረጃ በተጨማሪ በተለይ በዚህ ውፍረት ዐለም ዓቀፍ የማህበረሰብ ጤና ችግር በሆነበት ሰዓት በጣም ያረዘመ የምግብ ክልከላ [ፆም] የሚከተሉት የጤና ጠቀሜታዎች አሉት
—የአምሮ የማሰብ አቅም [cognitive performance] ይጨምራል
—አላስፈላጊ የሰውነት መቆጣት [inflammation] ይቀንሳል
—ሰውነት ውስጥ የተከማቸ ስብን በማቅለጥ ጤናማ አቋም ያስገኛል
—ውፍረትን ተከትለው የሚመጡ የብዙ ካንሰሮችን ተጋላጭነት ይቀንሳል
—የmetabolic እና ተላላፊ ያልሆኑ እንደ ስኳር ፣ ደም ግፊት እና ስትሮክ አይነት ገዳይ በሽቶች ተጋላጭነት ይቀንሳል
—አጠቃላይ ንቁነትን ይጨምራል
» በዚህም ምክንያት ሙስሊም ያልሆኑ አካላት እንኳን ሰውነት ገንቢዎችን [body builders] ጨምሮ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቅባት ለመቀነስ አልፎ አልፎ የሚፆመውን [intermittent fasting] ለጤናቸው ሲሉ ይተገብራሉ።
ከዚህ በተጨቃራኒው ፆም ጤናቸውን ሊጎዳቸው የሚችል
—ህፃናት
—በድሜ የገፉ
—ነፍሰ ጡሮች
—ተላላፊ ያልሆኑ እንደ ስኳር [በተለይ ጥሩ ክትትል ያልነበራቸው እና የደም ስኳር በቁጥጥር ስር ያልሆነ] በሽተኞች
መፆም ለይኖርባቸው ወይም ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እና ሃኪማቸውን በማማከር ቅርብ ክትትል ማድረግ ሲኖርባቸው
* ርሃሀብ የሚያስነሳው የጨጓር ህመም[gastric ulcer] ያለባቸው ደግሞ ከፍተኛ የምግብ ጥንቃቄ፣አጫሽ ከሆኑ ረመዳንን እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ማቆም ፣ቡናና የሚያስነሳባቸውን ነገር ሁሉ ማስወገድ ይኖርባቸዋል
...ስናፈጥርም ከተቻለ ቴምር እና ቀለል ያሉ ምግቦችን መጠቀሙ ኸይር ነው።
አለህ እኛንም እናንተንም ረመዳንን ደርሰውበት ከሚጠቀሙበት ያድርገን
https://t.me/drdawudconsultancy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ነፃ ካልወጡ ነፃ አውጪዎች ተጠንቀቂ!
~
የፊታችን ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው አሉ፡፡ ወይ ፈረንጅ! አመቱን በሙሉ እኮ “የምንትስ ቀን” እያሉ ሊዘጉት ነው፡፡ ፈረንጅ ሲስል የሚስለው ሌላው ክፍል ነጩ ሰው “የግብረ ሰዶማውያን ቀን” ብሎ ቢጀምር ያለምንም ማመንታት ይከተላል፡፡ አሁንም ስላለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ብቻ ማርች ስምንትን ለሴቷ ሰጧት አሉ፡፡ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!!”
እለቱን ሳስታውስ አንድ ነጭ አስተማሪ ስለ ሴቶች “መብት” እንቅስቃሴ እያወራ የተናገረው ነገር ከአመታት በኋላ ትዝ አለኝ፡፡ የሴቶችን መብት ካፋጠኑ ነገሮች አንዱ ብስክሌት ነው ነበር ያለው፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ይደንቀኝ ነበርና ኢንተርኔት ገብቼ ሳስስ ለካንስ ሀሳቡ የሱ ብቻ አይደለም፡፡ ይሄ ነገር ሰዎቹ ምን ያክል ቂ ሎ ች እንደሆኑ እና ነፃነት ሲሉም ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው አተያይና ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላለው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡ እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነ ገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡ አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይደሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
እህቴ ሆይ! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩ ንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል?! እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል?! ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል?! ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል?! እመኚኝ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡ አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብ - ዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡ የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለሀጫቸው የሚዝረበረብለትን የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡ በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን መሆን ካማረሽ ግን ግፊበት፡፡ ጀሀነምን የሚቋቋም ገላ ካለሽ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ፡፡
ንቂ! ያለበለዚያ ይሄ በስጋዊ ፍላጎት የታወረው “ጠበቃሽ” የኮንዶም ማስታወቂያ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ያለበለዚያ ይሄ ካንገት በታች እንጂ ካንገት በላይ የሌለው ርካ ሽ በ ድ ን ከምንም በታች አርክሶሽ የሱ ርካሽ ሸቀጥ ማሻሻጫ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡ እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡ አላማ ቢስ አትሁኚ፡፡ ያለበለዚያ ኮምፓስ እንደሌለው መርከብ ዋለሽ ዋለሽ አስከፊ ፍፃሜ ላይ ትደርሻለሽ፡፡
ተጠንቀቂ!! ከሸሪዐው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቅሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡ ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከኢስላም ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡ ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው፣ ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ቅቤ አንጓች “እንባ ጠባቂ” ተኩላ ግን የአኺራ ምንነቱም አይገባውም፡፡ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡ ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ የአህያ ባል ከጂብ አያስጥልም፡፡ ለናቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ፣ ለእህቱ የማይሆን ሰካ - ራም ነፃ ያወጣኛል ብለሽ ከገመትሽ የመጨረሻ ቂ ል ነሽ፡፡ እሱ እራሱ በስሜቱ የሚገዛ የስሜት ባሪያ ሆኖ በየትኛው ሞራሉ ነው አንቺን ነፃ የሚያወጣሽ?! ቀድሞ ነገር ምን ሲደረግ ለሰካ - ራም ጆሮሽን ሰጥተሽ?! ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡ በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት የስሜት አሮንቃ ውስጥ ይነክርሻል፡፡ በደጋሚ ምላሱ ጭንቅላትሽ ላይ ተብትቦብሽ የስሜት ባሪያ ሆነሽ ረክሰሽ፣ ከማንም በላይ ብቁና ንቁ የሆንሽ ይመስልሻል፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሐያእሽ ባለመሟጠጡ በግልፅ ባታወጪው እንኳ ውስጥሽ ለኢስላም ይደፈርሳል፡፡ ለነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለሽ ክብርም ምናልባት ካልጠፋ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ፡ እውነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከመቶ ሺ በላይ ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት? እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡ እናም እልሻለሁ፡ በኢስላም ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡ የተኩላ ሰለባ እንዳትሆኚ ንቂ፡፡ የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ረመዳን እየተቃረበ ነው። ከወዲሁ ዝግጅት መጀመር ይኖርብናል። ከምንዘጋጅባቸው ነገሮች ውስጥ ቀዳሚው የእውቀት ዝግጅት ነው። በዚህ ረገድ ከተጳፉ ኪታቦች ውስጥ አጠር ብሎ ግን ብዙ ጥቅሞችን የያዘው የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ አል-ወሷቢ
"مذكرة في أحكام الصيام"
የተሰኝው ኪታብ በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም ተቀርቶ ተጠናቆል ሙሉ ደርሱን እኒህን ሊንኮች በመጫን በቀላሉ ማግኝት ይችላሉ።
የኪታቡ ፒዲኤፍ ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1575
ክፍል - አንድ ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1582
ክፍል - ሁለት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1592
ክፍል - ሶስት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1670
ክፍል - አራት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1672
ክፍል - አምስት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1674
ክፍል - ስድስት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1689
ክፍል - ሰባት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1704
ክፍል - ስምንት ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1722
ክፍል - ዘጠኝ ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/1738
ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኝት ቻናሉን ይቀላቀሉ ↓↓↓
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
Repost from Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
በሸዕባን አጋማሽ ላይ የሚፈጸም ልዩ ዒባዳህ የለም።
በዚህ ዙሪያ የመጡ ሐዲሦችም ደካማ ናቸው።
ሸይኽ ዶ/ር አልፈውዛንን አዳምጧቸው።
||
t.me/MuradTadesse
Repost from Kassis Faage
حكم تخصيص ليلة النصف من شهر شعبان بالصلاة والصيام؟
▪قال الشيخ ابن باز رحمه الله:
ما ورد في فضل الصلاة فيها فكله موضوع.
#المرجع 📚 [مجموع الفتاوى (١-١٨٦)]
•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
▪قال الشيخ ابن باز رحمه الله:
الاحتفال بليلة النصف من شعبان بالصلاة أو غيرها, وتخصيص يومها بالصيام بدعة منكرة عند أكثر أهل العلم,
وليس له أصل في الشرع المطهر,
بل هو مما حدث في الإسلام بعد عصر الصحابة رضي الله عنهم .
#المرجع 📚 [مجموع الفتاوى (١-١٩١)]
•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
▪قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله:
الصحيح أن صيام النصف من شعبان أو تخصيصه بقراءة أو بذكر لا أصل له،
فيوم النصف من شعبان كغيره من أيام النصف في الشهور الأخرى.
#المرجع 📚 [مجموع الفتاوى (٢٠-٢٣)] .
•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
▪قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله:
صيام يوم النصف من شعبان بخصوصه ليس بسنة وإذا لم يكن صومه سنة كان بدعة، لأن الصوم عبادة فإذا لم تثبت مشروعيته كان بدعة.
#المرجع 📚 [مجموع الفتاوى (٢٠-٢٦)] .
•┈┈┈•✿✿•┈┈┈•
حكم قيام ليلة النصف من شهر شعبان ؟
🎙قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله:
قيام ليلة النصف من شعبان له ثلاث مراتب:
١- أن يكون له عادة في قيام الليل
فيفعل في ليلة النصف ما يفعله في غيرها من غير أن يخصها بزيادة فهذا أمر لا بأس به.
٢- أن يصلي في ليلة النصف من شعبان دون غيرها من الليالي فهذا بدعة.
٣- أن يصلى في تلك الليلة صلوات ذات عدد معلوم، يكرر كل عام، فهذه المرتبة أشد ابتداعاً من المرتبة الثانية وأبعد عن السنة.
#المرجع 📚 [مجموع الفتاوى]
•┈┈┈•✿✿•┈┈┈•
#መልካም_ሚስት ♥
ባለቤቱን ለማጨት ከሽማግሌዎቹ ጋር ወደ ቤቷ አቀና። ልታገባት የምትፈልጋት ሴት ልታይህ ትፈልጋለች በመባሉ ነው አብሯቸው የሄደው። ቤት ገብተው ልጃችሁን ለልጃችን እንዳሉ ከአላህ ቃል ምን ያህል በቃሉ እንደሐፈዘ እንስቲቱ ጠየቀች።
እርሱም "አጫጭር ሱራዎችን እንጂ አልሐፈዝኩም ነገር ግን በአላህ ፈቃድ መልካምና ሷሊህ የአላህ ባርያ ለመሆን እጥራለሁ" አላትና አንቺስ?! በማለት ጠየቃት። ሽማግሌዎቹ በተዳዱበት ቃለ ምልልሱን አጦፉት።
"ጁዝ አማን በከፊሉ ሐፍዣለው" አለች።
እውነተኛ ሰው መሆኑን ከንግግሩ ስታረጋግጥ ልታገባው ተስማማች።
ከጋብቻ በኋላ ቁርአንን በቃላቸው አብረው ሊሐፍዙ ቃል ተጋብተው ተስማሙ። ውጥናቸው ሰምሮ ኒካሑ ታሰረ።
ከሱረቱል መርየም ሒፍዛቸው ተጀመረ የቤታቸው ጣራና ማገር ከሐለቃው እየታደሙ ቁርአኑን በልባቸው አተሙ። ሙሉ በሙሉ የአላህን ቃል ሐፈዙ። ሚስት የቡኻሪ ሐዲሶችን እንቀጥል ስትል ሐሳብ አቀረበች። እሱም ተስማማ ወደ ሐዲስ ሒፍዙ ተሸጋገሩ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ባል ወደ አባቷ ቤት ለዚያራ አቀና። በጨዋታ መሐል "አልሐምዱሊላህ ልጅህ ከሰሞኑ ቁርአንን በቃሏ ሐፈዛ ቡኻሪን ጀምራለች" አለ አባቷን እየተመለከተ። ስለሷ ሲያወራ አይጠግብም እንዲሁ ከንፈሮቹን ያንቀጠቅጣል ፅናቷ መልካምነቷ በህመም ላይ ሆና እንኳ የቁርአን ሒፍዝ ፕሮግራሟን ዝንፍ አለማድረጓን ተመልክቷል።
አባት በንግግሩ ግራ እየተጋባ ወደ ልጁ ክፍል አመራ። ብዙ ወረቀቶችን አምጥቶ ከፊቱ አስቀመጠ። ሚስቱ ከማግባቷ በፊት ቁርኣንንና ስድስቱን የሐዲስ መጽሃፎች መሐፈዟን የሚያሳዩ ወረቀቶችን ተመልክቶ እጁን በአፉ ላይ ጫነ።
የእውቀቱ ማነስ ሳያሳፍራት መልካምነቱን ተቀብላ የበታችነት ሳይሰማው ባሏን የሰራችው ይህቺ ሴት ክብርና ምስጋና ይገባት።
★★★★ ★★★ እናንተ ወጣቶች ሆይ!! ★★★★★★★
ሷሊህ ወጣን ባልሆንም ሷሊህ ልታደርገኝ የምትጥርን መልካም ሚስት ለግሰኝ ብላችሁ ዱዓ አድርጉ።
Via Mahi Mahisho
Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የደርስ መቀዛቀዝ
~
ብዙ አካባቢ የደርስ እንቅስቃሴ እየተቀዛቀዘ ነው። በተለይ በወንዶች በኩል። አንፃራዊ በሆነ መልኩ የተወሰነም ቢሆን ሴቶች ጋር የሚሻል ነገር አለ። ወንዱ ግን በብዙ አካባቢ ከቁም ነገር ይልቅ በወሬ ተጠምዷል። ይሄ የሚያሳዝን ነገር ነው። ወንድሜ የፈለገ ብትዳከም ከደርስ አትዳከም። ጊዜው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዒልም የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። በየ ጥጉ አፍ ለአፍ ገጥሞ ስለ እምነታዊ ውዝግብ፣ ስለ ፖለቲካ፣ ስለ ኳስ ማውራት ፋይዳ የለውም። ኸይር ያለው ከዒልም ማእድ ዘንድ ነው። ቢሆንልህ ራስህን እውቀት ታስታጥቃለህ። የረባ ነገር ባትጨብጥ እንኳ በርግጠኝነት ከኸይር አትርቅም።
አንዳንዱ ስለ ውዝግብ፣ ስለ ረድ ካልተወራ በቀር የዒልም ማእድ አይስበውም። ቢገኝ እንኳ ትኩረትም ንቃትም የለውም። እያዛጋ ይቆያል። ያንቀላፋል። ረድ ሲሰማ ግን ሁለ መናው ጆሮ ይሆናል። ህዋሳቱ ሁሉ ይነቃቃሉ። እከሌ በእከሌ ላይ ተናገረ ሲባል በቀጣይ ያኛው ምላሽ ይሰጣል በሚል አሰፍስፎ የሚመጣው ብዙ ነው። የሚፈልገውን ካላገኘ ወደ ተለመደው ዱካኩ ይመለሳል። ይሄ ህክምና የሚሻ በሽታ ነው። ዝርዝሩ ይቆይና ባጭሩ ለዒልም ያለን ጉጉት ፈፅሞ ሊቀዛቀዝ አይገባም። ከዒልም መራቅ ማለት አደገኛ ዝንባሌ ነው። ከዒልም መራቅ ማለት ከዲን መራቅ ማለት ነው። ከዒልም መራቅ ማለት በድንቁርና ለመጓዝ እጅ መስጠት ማለት ነው። ስለዚህ የዒልም ፍለጋ ጥረት የሌለበት ኑሮ ለመኖር ፈፅሞ አትቀበል። ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ደግሞ ነገ የተሻለ ንቃት ያለው ሰው ለመሆን ቆርጠህ ተነስ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የበደል ማሽኖች ሆነናል
~
ዘመኑ እጅግ በደል የበዛበት ዘመን ነው። በሃሜት፣ ክብርን በማጉደፍ፣ ደም በማፍሰስ፣ ሐቅን በመንጠቅ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በመስሪያ ቤት፣ በየመስኩ የበደል ማሽኖች ሆነናል። ለኛ ቅርብ የሆነን፣ ባለ ውለታችን እንበድላለን። ምንም የማያውቀንን ለይቅርታ እንኳ የማናገኘውን ሰው እንበድላለን። ፖለቲካውም፣ ማህበራዊ ህይወቱም፣ ንግዱም፣ ሁለ ነገራችን በጣም በበደል የተጠላለፈ ሆኗል። በደዕዋው ዘርፍ ያለው መበዳደልማ ለማውራትም የሚሰቀጥጥ ነው።
በዚህ ዘመን ያለውን በደል ለየት የሚያደርገው ሰው ለተውበትና ለይቅርታ ብዙም ዝግጁ አለመሆኑ ነው። በፊት በፊት ረመዳን ሲመጣ፣ ደዕዋ ሲደረግ፣ ሰው ሲሞት፣ ... ሰዎች ይደነግጡ ነገር። ዐፍውታ ይጠያየቁ ይላቀሱ ነበር። ዛሬ ይሄ በጣም ሳስቷል። በወንጀል ጀብደኛ ሆነናል። ከነ ቂማችን፣ ከነ ወንጀላችን እንፆማለን። ፆም ላይ ሆነን ወንጀል እናተራምሳለን። ሰለፎች ቂም ይዘው ረመዳን እንዲያገኛቸው አይፈልጉም ነበር። ረመዳን ከፊታችን ነውና ከልባችን አልቅሰን እንዘጋጅ። ከየትኛውም ዓይነት በደል እንራቅ፣ እንመለስ። ከፊታችን ቀብር፣ ሲራጥ፣ ምርመራ አለና እንዘጋጅ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
`` Tû fayxi (xaaqimto)``
★ Assalaamu Qaleykum
Waracmatullaahi
Wabarakaatuh
★★★
★ Dumah yan daban qafar xaaqinto abak masuginna, abaanam hinnay aba mara assacakkkuk sugen!
★ Qafar num qululuh ulqut gaba luk suga way, gersi buxah yamaate waqdi "mafaxa, cayyeh" axcuk(gaddalsitiyya luk ) yen.
* Innih elle enbe dariifal tama qaada kaxxam caylaluk ten "certoh hila" iyyaanam fanah tan kaxxa hilisiyyi qaada yoh sugte !!
★ A waktil xaaqimto naddal qaada akkuk temeetem tamballe !!
¶ Dumah qafar 3diicam kaxxa qaybik abalul sugte!!
① Xaaqintoh sinam guba culaanam
② Diraabah ane wayni xaagu yaceenim
③ Garqiinoh sinam cakki yadreenimi
★ Ta sidiicam qafae addal kaxxa qaybik abaluk sugte , taway laakin kaxxam gibdih tan caddo gufak tamaatem tamballe!
★ Ceelalleh....
Num tu faxk yamaate,....
* Woo inki tû fayxih addat a 3diicam inkih tan.
* Naharaak abu kak aaxige wee numul lakqo essera( xaaqinto1)
* Lakal woo lakqo geyuh geysiisih akke waynuuy, able wayni calway yoo gee iyya(2 diraaba)
* illacaboh usug diraabat yadrem faxam marin cakki( 3 tah rado)
★ Meqe toobokoy, num calwayitek isik yayse maral tu esseritam taqabi mali, laakin #gaat_caffaytu waannaanih num diraabak qasiina sunkut hayya heenih, geenik xaaqimtooy, weenik garqiinoh yardeenim kexxam umam kinnim nasmitem faxximta!!
¶ Woh kaaduk inni moyyak axcem hinnay, #Ashrafal_Khalqhi (Ginok inkih yayse farmoytih (ﷺ) yab kinni!
عن أبي هريرة رصي الله عنه قال: قال رسول الله ﷺ: «مَن سأل الناس أموالهم تكثُّرًا فإنما يسأل جمرًا فليَستقلَّ أو ليستكثرْ» رواه مسلم.
★ Abaa hureyra Yalli kaak raabitay , tatruse cadiisil: Meqe NABI ﷺ " yassameggê gidah sinam essereh yan num esseram xikciin(gira) kinni, daggoysitee kee assamagge yakkay..." iyye Muslim xaagise
★ Gersi cadiisil...
عن عبد الله بن عمر رضي الله عنه قال: قال النبي ﷺ: «ما يزال الرجل يسأل الناس حتى يأتي يوم القيامة ليس في وجهه مُزْعَة لحم».
★ Ibnu qumar Yalli kaa yakcanuh neh tatruseh yan cadiisil, Meqe NABI ﷺ " num tu sinaamal esseraamak makata, ilaa qhiyaamah ayro foocal cado tifaluk amaate waam fan," iyye.
★Ta namma cadiisik baritnam.....
① Xaaqinto waasolem kinnim.
② xaaqimak orbisitaanam girâ xikcino kinnim.
③ Seehadat Xaaqima num , qhiyaamah ayro foocal lafoofaksa cadok tifaluk amaate wayuwaam....wwc kak baritna.
¶ Laakin toh inna waqdi, tû fayxi (essero) elle xiqtah tan ximmooma tanih.
=> Toh .
① Calaalik tan mogo tibbixe numuy, woo mogo meklam yefferek ( Woo mogoh meklah gide geyam fanah esseram kaah xiqtah, ohuk bisol kaah maxiqta)
② Qawwalayla edde boddeh tan numuy, duyye kak finqitte( kaa gufte qawwalaylak ibi maysaadah gide geyah gide)
③ tu luk sugeeh, baaciteh yan numuy , baacal 3diica numuy qadlile kah sumaaqitte.
★ Tama sidiica numuh tu sinaamal esseritaanam keenih xiqtah, keeenit boode calway kee baacak ibi maysaada geyaanah gide, too gide geeniksa ossotina gorrisaanam maxiqta!!
★ Away mangih tamballem, tû fayxi mari yenbeggeemih( dirab kee nummah fanal) sabbatah, tu sinni maray cato cakkisita edde biyaakita, xaaqima marak sinam laclacteemih sabbatah, garrah wagga haanah, sinnih taturan.
¶ Tokket nummaak cakkisita maskinti edde dabqam bictah !!
★ Toysa meqe tooboy, gaat kee madaaqa waaan waqdi , tû fayxih wes iyya mara fayisnam faxximta!
Oson kaaduk sinni kak digaalaanam faxximta!
★Yab mangoh immay, amakket ayseede(Yalli barkat edde neh haaay )
✍ Md Ali
( Diinii kee Anaakara)
https://t.me/httpsDiiniKeeAnaakara
``Mogo ``
★ Assalaamu Qaleykum
Waracmatullaahi
Wabarakaatuh
[ >>>>>>>>><<<<<<<<<<<<]
★ Naharsi saaku mogo quukaanam kaxxam gibdim kinnim dagoom muduqqa siinih heeh suge.
★ Asaaku jumqatta elle abeh an masjidil imaam khutba " mogo" wagsiisak nee kassiise(Meqe Jaza Yalli kaah yaaxagay ).
★ Anu khutba edde yabbateemit inkih miyabnammay, baxsaluk sidiica ximmo kak kassiisam gibbateyyo(Insha Allaah).
① Ibnu Qumar (R.qanhum) baahe xaagul, Meqe NABI ﷺ " Yallih gital jihaadah rabe numuh Yalli zambitte inkih cabah mogo kak raqtay immay" iyye. Muslim xaagise.
② Abuu qhatada (R.qanhu) baahe xaaguk, iyyaamah "Inki saaku Meqe NABI ﷺ jihaadah rabaanamaay, Yallal yaaminenim Yallih garil kaxxam muxxolem kinnim kassiisak suge.
Tokkel inki sacaabiti sollayeh " Yallih farmoytaw (ﷺ) anu Yallih gital jihaadah rabek, Yalli anu abe zambitte inkih yoh cabelee?" iyye.
~ Tokkem Meqe NABI ﷺ " yeey, gibdaabinal isbirraay, wohut Yallak geyuwaa galtot loowitakaay, wadirih hinnnay, naqboytat foocah koositak naddoowek, abe uma taama Yalli kaah cabah" iyye.
~ Dagoom xokobbaye waqdi,...
Meqe NABI ﷺ " (woo essero hee sacaabittak) aninnaay kah itteh sugtem? " kaak iyye.
Qagseh "Anu Yallih gital jihaadah rabek, Yalli anu abe zambitte inkih yoh cabelee?" iyye.
~ Meqe NABI ﷺ kaal gacseh "yeey, Kaa gufu xiqa gibdaabinal isbirraay, wohut Yallak geyuwaa galtot loowitakaay, wadirih hinnnay, naqboytat foocah koositak naddoowek, abe uma taama Yalli kaah cabah, #mogo kak koh raqtay immay, away Jibriil yol yemeeteh tutucca yot iyyeeh tamannah yok iyye" iyye. Muslim xaagise.
★Cubbusa,
★ Jibriil qaraanak amok kah yemeetem kaxxam gibdi caagid kinnim sinnih cubbusa!!
② Gersi cadiisil tanim,...
Sacaabak num rabeeh, kaa kaqlissaay, kaffaanissaay, bicissa heenih Salaatul Janaaza kaal abâ gidah Meqe NABIH ﷺ farmo ruuben.
yemeeteh, kabbaye waqdi " sin kataysih amol mogo tanim maayle?" iyye.
~ Sacaaba " yeey 2dirham kaal tan" iyyen.
→ Meqe NABI ﷺ " sinni wakliital salaatita hay" keenik iyyeh kaal salaate kal isih yuduure.
~ Tokkel Abuu qhataada xeqsita sacaabiiti " kay amol tan mogo anu akkuqeyyo" iyye.
~ Tooway, mogo kaak nukkuqehik, salaat kaal abâ gidah ama iyyenih, Meqe NABIH ﷺ farmo ruuben.
~ Meqe NABI ﷺ Mogo yukkuqe numuk " a mogo kay fillak kattateh, ku fillal haytee?" Iyye.
Woo sacaabiiti " Yeey Yallih farmoytaw " iyye.
Tooway kaal salaateh, gersi saaku " mogo mekeltee" axcuk woo num essere, naharsi saaku " mamekliyyo" iyye. Gersi saaku kas essere " mekleh Yallih farmoytaw ﷺ " iyye.
Meqe NABI ﷺ "ku kataysal digaala tawayvxabbocowteh " iyye.
★ Akkel ta cadiswak baritnam,....
① Yalli gersi zambitte inkih caba way, mogo sinaamah cabewaam...!
② Mogo fillal kak anuk rabe numuk, woo mogo mekella haanam fan kah diggalsimak sugam....!
③ Mogo elle tan numul salaatul janaaza abaanam taqabilem...!
④ Mogo fillal kak tan num faxe meqe taama yaalle way, jannatti culma taqabi kaaklem!
★ Meqe toobokoy, meqe maqanxiixow, ......
=> Marin cakki fillal siinik quukaanam meqem hinna!
=> Kak daccarsimnam faxximta.
=> Mogo net tenekaa tekkek le waktil xayuk tet mekellam faxxinta.
~~\\~~~~
🎙 Sifa Md
✍ Md Ali
( Diinii kee Anaakara)
https://t.me/httpsDiiniKeeAnaakara
Repost from Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
ይደመጥ‼
========
✍ «የፍቅረኛሞች ቀን» (Valentine's Day) የሚባለውን በተመለከተ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ቤተል ሮም (አል-ፋሩቅ) መስጅድ ያደረገው ኹጥባ!
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቂት የማይባሉ ሙስሊሞችም በዚህ ኢ-ኢስላማዊ ድርጊት እየተለከፉ ነውና ይገሰጹ ዘንድ ለሌሎችም አስተላልፉት። ምናልባት በኛ አንድት ሼር ሳቢያ ይህን ሰምቶ ከድርጊቱ የሚቆጠብ አንድ እንኳ ሙስሊም ቢኖር ትልቅ አጅር ነውና!
||
t.me/MuradTadesse
